cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት

በዘመናዊው ቴክኖሎጂ ታግዘን ስለ ህይዎታችን የምንወያይበት፣ የምንመካከርበት እና የምንጠያይቅበት የቴሌግራም ገፅ ነው! ለማግኘት @KSintayehu ማዕከለ አራዊት ንኬልኅ አልቦ ዘይሰምዐነ እስመ አራዊት ይቤዝኁ እምኔነ መኑ ጠቢብ ወመለብው ከመ እግዚአብሔር አገው!

Больше
Рекламные посты
690
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
+130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ህዳር 25 ✝️ እንኳን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ንግስ በአል አደረሳችኹ❤ ለክርስትና ሃይማኖት የሚከፈል ትልቁ ዋጋ ሰማዕትነት ነውና ቤተ ክርስቲያን ለምስክሮቿ ሰማዕታት ልዩ ክብር አላት። ከኮከብ ኮከብ እንዲበልጥ ሁሉ ከሰማዕታትም ቅዱስ ጊዮርጊስን እና ቅዱስ መርቆሬዎስን የመሰሉት ደግሞ ክብራቸው በእጅጉ የላቀ ነው። ቅዱስ መርቆሬዎስን ብዙ ጊዜ ሊቃውንት "ካልዕ (ሁለተኛው) ሊቀ ሰማዕታት" ሲሉ ይገልጹታል። ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ግዛቶች በአንዱ (አስሌጥ) ከአባቱና ከሚስቱ ጋር የሚኖር "አሮስ" የሚሉት ሰው ይኖር ነበር። ሚስቱ ደም ግባት የሠመረላት እርሱም ደግነት ያለው ሰው ቢሆኑም የሚያመልኩት ግን ጣዖትን ነበር። አንድ ቀን አሮስ ሚስቱን ከቤት ትቶ ለአደን ከአባቱ ጋር ወጣ። እንደ ልማዳቸው ወጥመዱን አስተካክለው ተደበቁ። የወጥመዱ ደወል ሲያቃጭል "እንስሳ ተያዘልን።" ብለው ሲሯሯጡ ዓይናቸው ያየው ነገር በድንጋጤ እንዲፈዙ አደረጋቸው። ሁለት ገጻተ ከለባት በወጥመዱ ውስጥ ተይዘው ነበር። እነዚህ ፍጡራን ሰዎች ናቸው። ግን ባልታወቀ የተፈጥሮ አጋጣሚ እንደዚህ እንደ ሆኑ ይታመናል። ግን እጅግ ግዙፍ፣ ከአንገታቸው በላይ እንደ ውሻ፣ ወገባቸው እንደ ሰው፣ ጉልበታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ታችኛው እግራቸው የጋለ የናስ ብረት የሚመስል ነው። እነዚህን ፍጡራን ሰማያዊ ካልሆነ ምድራዊ ፍጡር አይችላቸውም። አንበሳና ነብርን እንኳ እንደ ጨርቅ በጣጥሰው ይጥሏቸው እንደ ነበር ይነገራል። ዓይናቸው እንደ እሳት ይነድ ስለ ነበር ማንም ትክ ብሎ ሊያያቸው አይችልም። ምሥጢራቸውን ግን የሚያውቀው የፈጠራቸው አምላክ ነው። ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና አሮስና አባቱ ባዩአቸው ጊዜ ደንግጠው ወደቁ። ገጻተ ከለባቱ የብረት ወጥመዱን እንደ ክር በጣጥሰው የአሮስን አባት በቅጽበት በሉት። አሮስን ሊበሉት ሲሉ ግን ድንገት ቅዱስ መልአክ ወርዶ በእሳት ሰይፍ አጠራቸው። "ከእርሱ የሚወጣ ቅዱስ ፍሬ አለና እንዳትነኩት።" አላቸው። ወዲያውም መልአኩ ያንን ኃይለኝነታቸውን አጠፋው። በዚህ ጊዜ ሁለቱም ወደ አሮስ ሒደው ሰገዱለት። አሮስም ወደ ቤቱ ወስዶ ደበቃቸውና የሆነውን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት። ጥቂት ቆይታም ጸንሳ ወለደች። ልጃቸውን ፒሉፓዴር (ፒሉፓተር) ሲሉ ስም አወጡለት። ትርጉሙም "መፍቀሬ አብ - የአብ ወዳጅ" ማለት ነው። ከዚያም አሮስ ሚስቱን፣ ልጁንና ሁለቱን ገጻተ ከለባት ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ ተጠመቀ። አበው ካህናት እሱን "ኖኅ"፣ ሚስቱን "ታቦት"፣ ልጁን ደግሞ "መርቆሬዎስ" ሲሉ ሰየሟቸው። መርቆሬዎስ ማለትም "ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ - የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ" እንደ ማለት ነው።
Показать все...
3
#የሉም_ሞተዋል የሉም ሞተዋል ሲሉን ኖረን የሉም ጠፍተዋል ሲሉን በዝተን አለን በእግዚአብሔር ሁሉን አልፈን አለን በጌታ ሁሉን አልፈን ለካ ሰው ሰለሮጠ አይቀድምም ጉልበታም ስልታገለ አይጥልም ጎልያድ ወድቋል በዳዊት ጠጠር የኛ አምላክ ስሙ ከፍ ይበል ይክበር እግዚአብሔር ስሙ ከፍ ይበል ይክበር አዝ = = = = = በሚነድ እሳት መሐል ሆነን አልሞትንም ዛሬም አለን በዝተን ያልሰማ ሁሉ ይስማ ይግረመው ያመለክነው እግዚአብሔር እንዲህ ነው(፪) አዝ = = = = = ጨክነን እኛ ሰይፉን ባንመዝ በእጃችን ጦር ጉመድን ባንይዝ ይዋጋል ዝም አይልም እግዚአብሔር ልጆቹን ፈጥሮ አይሰጥም ለፍጡር(፪) አዝ = = = = = አሕዛብ ሥጋችንን ሊያጠፉ ቢደክሙ ብዙ ዘመን ቢለፉ ካሸናፊዎች ሁሉ በልጠን አልሞትንም ዛሬም አለን በዝተን(፪)
Показать все...
አዲሳልም_የድራ_ልጅ_የሉም_ጥፍተዋል_ሲሉን_በስትን.m4a7.48 KB
👍 1👏 1
ወደ ቤተ መቅደስ ሲገቡ ስልክ ማጥፋትዎን አይርሱ ከሚል ማስታወቂያ እየቀደሱ ቲክ ቶክ ወደመግባት የተሸጋገርን ደግሞ መቼ ነው? ሰው እንዴት እንኳን እየቀደሰ ይቅርና መቅደስ ውስጥ ለምን ስልኩን ይከፍታል?
Показать все...
ንግስተ ሰማያት ንግስተ ሰማያት ወምድር ማርያም ድንግል /2/ ተፈጸመ /5/ ማኀሌተ ጽጌ /2/
Показать все...
ተፈጸመ_5_ማኅሌተ_ጽጌ_2__xAdoeHiXzJk_139.m4a9.23 KB
Фото недоступноПоказать в Telegram
✏ጠሪ አክባሪ ነው ! 👉ታላቅ የመጽሐፍ ምርቃት ♣ ኅዳር ፰ ቀን ሌላ ቀጠሮ እንዳትይዙ አደራ እላለኹ! በዕለቱ፥ ስለ ጠቢበ ጠቢባን ቁም ነገርን የምትቀሥሙበት መንፈሳዊ ጉባኤ ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል!! ♣ለበለጠ መረጃ፦ ኅዳር ፰ ቀን ፳፻፲፮ ዐ.ም፥ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት፥ ከቀኑ ፯ ሰዓት ጀምሮ በማኅበረ ቅዱሳን አዳራሽ በአካል መሳተፍ ይቻላል!! 📍ጠሪው፦ ኤፍሬም የኔሰው (የጠቢበ ጠቢባን ተርጓሚ፣ አዘጋጅ እና አሳታሚ)።
Показать все...
፡ "በቦታህ መምህር፤ ያለቦታህ ደግሞ ተማሪ ሁን›› ... በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል። --- ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ። --- የታየህን አሳይ፣ ያልታየህን አጥራው። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል። --- ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ። --- የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው። --- ክፋት አይሙቅህ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት። --- ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ። ላለው አትሩጥ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው። --- ለሀብታም አትሳቅ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን፣ ነገርህን በልክ፣ ቃልህን በጣዕም፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው። --- እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ። --- ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም። --- በዓላማ ኑር፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ። --- የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን፤ የትላንቱንም አስብ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና። --- ዓለም ዋዣቂ ናት። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ! --- መነቀፍን አትፍራ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል። --- ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት፤ የበታቾችህንም ተመልከት። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው። --- ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ። --- ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው። --- ልጅነት የለሰለሰ መሬት፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ። --- የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው !! --- ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል። --- ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል። --- እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ። --- የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው። --- ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ። --- ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር
Показать все...
1
ምን መፍትሔ ሰጠኸውና? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና። ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል። --- ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል። --- ቂም አፍን የሚያመር፣ ልብን የሚያነቅዝ፣ ተግባርን የሚያልፈሰፍስ ነውና ለበደለህ ሰው ቅያሜህን ግለጥለት፤ ቂመኝነት በክፉ መሸነፍ እንጂ ጀግንነት አይምሰልህ። --- ከህሊናህና ከመንፈሳዊ አማካሪህ ሳትመክር ምንም ነገር አትወስን፤ አጥርተህ ሳትሰማ ቃል አትግባ። መከራ ካልደረሰ በቀር ባል በሌለበት ቤት ውስጥ ከሚስቲቱ ጋር ብቻህን አትቀመጥ። --- የሚበልጥህ ልኩራብህ እንዳይልህ፣ ያነሰህ ልድረስብህ ብሎ እንዳያጠፋህ የሀብትህን ልክ እንዳታወራ፤ በገዛ አፍህ ባንዱ ትከብራለህ ባንዱ ትቀላለህና። --- በጣም በማክበርህ እንዳታመልከው፤ በጣም በመናቅህ እንዳታዋርደው ሠው እንዳንተ መሆኑን እወቀው። --- የእኔ መናገር ምን ይለውጣል? ብለህም ስህተትን አትለፍ፤ የእኔ አስተዋፅኦ ምን ይጠቅማል? ብለህም ስጦታህን አትጠፍ። --- መልካም ቃል ከስጦታ ይበልጣልና መልካም ቃል ተናገር፤ ማንኛውም ስጦታ ከልመና ወንበር አያስነሣም። የተስፋ ቃል ግን እንደሚያስነሣ አውቀህ ለሰዎች የተስፋ ቃል ስጣቸው። --- ትምህርት ለዕውቀት ያዘጋጃል እንጂ ዕውቀትን አይጨርስም። ዕውቀትህን የምትይዝበትን ሥነ-ሥርዓት ግን ያሳይሃል። አእምሮህን ለማረቅ ትምህርት፣ ሰውነትህን ለመግዛት ትዕግስት፣ ከማንም ጋር ለመኖር ሥነ-ሥርዓት ያስፈልግሃል። ለህሊናህ እረፍት ግን እምነት ያሻሃል። ተከታይ ለማበጀት ደግሞ ግልጽ መሆንና ታማኝነት ግድ ይልሃል። --- አንተው እውነትን ጠልተሃት ዘመኑ እውነትን ጠልቷል አትበል። ዘመን እኔና አንተ ነን፤ በራሱ ክፉና ደግ የሆነ ዘመን የለም። --- መልካም ምክር ብትሰማ ሕይወት ቀላል ይሆንልሃል። ትክክለኛም ውሳኔ ከመልካም ምክር ነውና..!! ,,,,,,,,,,,,,,,,,, (((የመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ነው ተብሎ ፌስቡክ ላይ ሲዘዋወር የተገኘ)
Показать все...
👍 1 1
*መቼ ነው* እውነተኛ ክርስቲያኖች የምንሆነው? *መቼ ነው* እግዚአብሔር በፈጠራቸው ነግሮች የምንማረከው? *መቼ ነው* እግዚአብሔር ለምን እንደፈጠርን የምንረዳው? *መቼ ነው* እግዚአብሔር እንደሚፈልገው መኖር የምንጀምረው? *መቼ ነው* ስለ ሀይማኖታችን በሙሉ ልብ እምንናገረው? *መቼ ነው* እማይጠቅም ንግግር ከመናገር የምንቆጠበው? *መቼ ነው* ለመልካም ስራ ምሳሌ የምንሆነው? *መቼ ነው* በስግደታችን በፆማችን የምንጠቀመው? *መቼ ነው* ጾለታችን ተሰሚነት የሚያገኝው? * *መቼ ነው* ውሎና አዳራችን በቅዱስ ቃሉ ሚሆነው? *መቼ ነው* ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ የምንመካው? *መቼ ነው* ያአለምን ትልቅነት ከልባችን የምናወጣው? *መቼ ነው* ቤታችን ውስጥ ያለው የተበላሸ ሂዎት የሚስተካከለው? *መቼ ነው* ቤታችን ውስጥ መጸሐፍ ቅዱስ ውዳሴ ማሪያም የሚወራው? *መቼ ነው* ውሽት እምናቆመው? *መቼ ነው* የእግዚያአብሔርን ውሳኔ መቃውም እምናቆመው? *መቼ ነው* እኔ እኔ ማለት ትተን ውንደሜ እህቴ ማለት እምንጀምረው? *መቼ ነው* ለሰዎች ከክርስቶስ ውጪ ጌታ እንደሌለ እምንናገረው? *መቼ ነው* ጥሩና ለጋሽ መልካም ሰው የምንሆነው? *መቼ ነው። ክርስቲያንነታችንን የምናስተዋውቀው? *መቼ ነው* ለድሃ እምናዝነው?. *መቼ ነው* ትዳራችን ስላም ሚያገኝው? *መቼ ነው* የጋብቻን ጥቅም ተገንዝበት ለትዳር የምንቻኮለው? *መቼ ነው* ከሀሜት; ስውን ከመበድል; ከማስቀየምና ከማማት እምንላቀቀው? *መቼ ነው* ወላጆቻችንን እምናስደስተውና እምንታዝዝው? *መቼ ነው* ያልተጣራ ውሬ ካማውራት እምንቆጠበው? *መቼ ነው* እምንዋደደው? *መቼ ነው* እግዚአብሔር በሰጠን ነገር ደስተኞች የምንሆነው? *መቼ ነው* ስግደት ፆም ፆለት የምንላመደው? *መቼ ነው* የበድለንን ይቅር የመንለው? *መቼ ነው* ከራስ ወዳድነት እምንላቀቀው? *መቼ ነው* ከሞት ቡኃላ ላለው ሂወት ስንቅ እምናዘጋጀው? *መቼ ነው* አባቶችን እምናከብረው? *መቼ ነው* ለእውቅት ጊዜ የምንሰጠው? *መቼ ነው* ባወቅነው የምንሰራው? *መቼ ነው* የ ምንሞትበትን ቀንም ይሁን ስፍራ እንደማናውቅ ተገንዝበን በተጠንቀቅ የምንቆመው? *መቼ እረ መቼ ነው* ክርስትናን የምንኖረው? *መቼ ነው* ለእነዚህ ተግባራዊ መልስ የምንመልሰው እግዚአብሔር ይርዳን አሜን። ውስብሃት ለእግዚአብሔር ወወላዲትድንግል ወለመስቀሉ ክብር
Показать все...
ዛሬ ይምርሃነ ክርስቶስ መታሰቢያ ቀን ነው ።።።።።።።።።።።። ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ከላስታ (ከዛጉዌ) ነገሥታት መካከል ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ፣ ቅዱስ ገብረ ማርያም፣ ቅዱስ ላሊበላና ቅዱስ ነአኵቶለአብ እነዚህ አራቱ ነገሥታት እንደ መልከጼዴቅ (ዘፍ 14፡18) ክህነትን ከንግሥና፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ እግዚአብሔርንም ሰውንም በቅድስና አገልግለው አልፈዋል፡፡ በንግሥናቸው ሀገርን በመልካም ሥራና በቅድስና ከማስተዳደራቸው በተጨማሪ ቅዱሳን ጻድቃን ሆነው እግዚአብሔርን በብዙ ድካም በመልካም ተጋድሎአቸው ያገለገሉና አገልግሎታቸውም ሆነ ቅድስናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ሞትን ሳያይ እንደነ ሄኖክና ኤልያስ የተሰወረ አለ፤ ከእነርሱም ውስጥ በባሕር ላይ ቤተ መቅደሱን ያነጸ አለ፤ ከእነርሱም ውስጥ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶት የቤተ መቅደሶቹን አሠራር ራሱ ጌታችን በቃሉ ያስረዳው አለ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ በክህነቱ ሲቀድስ 40 ዓመት ሙሉ ቅዱስ ቁርባኑን መላእክት ከሰማይ እያመጡለት የነበረ አለ፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ነገሥታት ገድላቸውና ትሩፋታቸው፣ ምግባር ሃይማኖታቸው እጅግ ድንቅ ነው፡፡ ከ10ኛው እስከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (920-1253 ዓ.ም ገደማ) በላስታ ቡግና ምድር የነገሡ የላስታ ቡግና ተወላጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ነገሥታት የንግሥናቸው መጠሪያ ‹‹የዛጉዌ ሥርወ መንግሥት›› ወይም ‹‹የላስታ መንግሥት›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከዛጉዌ ነገሥታት ውስጥ የመጀመሪያው ንጉሥ መራ ተክለሃይማኖት የዐፄ ድልነአድን ልጅ መሶበወርቅን አግብቶ አራት ልጆችን ወልዷል፡፡ ሦስቱ ወንዶች ጠንጠውድም፣ ግርማ ስዩምና ዣን ስዩም ይባላሉ፡፡ ጠንጠውድም ገብረ መስቀልን ወለደ፣ ግርማ ስዩም ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ወለደ፣ ዣን ስዩም ደግሞ ቅዱስ ገብረማርያምንና ቅዱስ ላሊበላን ወለደ፡፡ ገብረ መስቀልም ጣራው ክፍት ሆኖ ዝናብ የማያስገባውን ገዳም የመሠረቱትን የመቄቱን ታላቁን አባት አቡነ አሮንን ወለደ፡፡ ቅዱስ ገብረማርያም ደግሞ ቅዱስ ነዓኵለአብን ወለደ፡፡ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ሳለ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ‹‹ከጠንጠውድም በኋላ የምትነግሠው አንተ ነህ›› በማለት ከነገረው በኋላ በመንገዱ ሁሉ እየተራዳው ወደ ኢትዮጵያ ይዞት መጥቷል፡፡ በቤተ መቅደስ ገብቶ ሲቀድስ መላእክት ሰማያዊ ኅብስትንና ጽዋን አምጥተው እየሰጡት እርሱም ለሕዝቡ ሁሉ ያቆርባቸው ነበር፡፡ ሕዝቡን የሚባርክበትም መስቀል ከሰማይ ነው የወረደለት፡፡ ዛሬም ድረስ አለ፣ በዓል ሲሆን ካህናት አባቶች እያወጡ ሕዝበ ክርስቲያኑን ይባርኩበታል፡፡ ጌታችን ለይምርሃነ ክርስቶስ በአካል ተገልጦለት እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ እንደማይፈርስ ቃልኪዳን የሰጠውንና አሁን በላስታ ላሊበላ ያለውን ቤተመቅደሱን በባሕር ላይ እንዲሠራ ነግሮት በኋላም በቦታው ላይ እጅግ አስደናቂ ቃልኪዳን ሰጥቶታል ደግ ንጉሥ፤ፃድቅ ካህን፤ቤተ መቅደሱን በባህር ላይ ያነፀ መሀንዲስ ከ፲፩የዛጉዌ ነገስታት አንዱ ንጉስም ቅዱስም የነበረው ይህ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ልደቱ ግንቦት 19 ቀን ነው። በላስታ ወረዳ ሳይ (ዛሬ ሸጐላ ማርያም) ከምትባል ቦታ ላይ ወንጌልን እያስተማረ፣ ድውያንን እየፈወሰ ተቀምጦ ፡፡ ትምህርቱንና ተአምራቱን ያዩት የአካባቢው ሰዎችም ‹‹ነፃነትና ፍቅር የሚገኝብህ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! እኛ ሰላማዊ ብርሃናዊ ብለን ስም አወጣንልህ፣ ያንተ ግን ስምህ ማን ይባላል ንገረን›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹ስሜ ይምርሃነ ክርስቶስ ነው›› አላቸው ይህኔ ሕዝቡ ሁሉ በሹክሹክታ ‹‹ይምርሃነ ክርስቶስ የሚባል ሲነግሥ ሃይማኖት ይቀናል፣ ፍርድ ይስተካከላል›› እያሉ አባቶቻችን ሲናገሩ ሰምተናል አሉ፡፡ ከጠንጠውድምም ሞት በኋላ ማንም እንዳልነገሠ ሲያረጋግጡ የማን ልጅ እንደሆነ እንዲነግራቸው በእግዚአብሔር ስም ለመኑትና የጠንጠውድም ታናሽና የዣን ስዩም ታላቅ ወንድም የሆነው የግርማ ስዩም ልጅ እንደሆነ ነገራቸው፡፡ እነርሱም ‹‹የተነገረው ትንቢት ደርሷልና ሳንዘገይ እናንግሠው›› ብለው ሥርዓተ መንግሥቱን ፈጽመው በዙፋን ላይ አስቀመጡት፡፡ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ በትረ መንግሥቱን ከያዘ በኋላ ሁሉም ሰው በተለያዩ እንቅስቃሴዎቹ ውስጥ እንደ ወንጌሉ ቃል እንዲኖር በግዛቱ ሁሉ አወጀ፡፡ እግዚአብሔርም የሚመሰገንበትን ቤት መሥራት አሰበና የተፈቀደለትን ቦታ እንኪያገኝ ድረስ ዛዚያ በምትባል ልዩ በሆነች ስፍራ ድንኳን ተክሎ እንደ ሙሴ አምላኩን ማገልገል ጀመረ፡፡ በዚህም ቦታ ሕዝቡን ከሰማይ በወረደለት መስቀል እየባረከና እርሱ ለቅዳሴ በሚገባበት ጊዜ ከአምላኩ የሚሰጠውን ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ እያቆረበ ለ22 ዓመት በድንኳኗ ውስጥ ኖረ፡፡ ከነዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ተገለጠለትና እንዲህ አለው፡- ‹‹ወዳጄ ይምርሃነ ክርስቶስ ይህን ሥፍራ (ዛዚያን) ልቀቅ፣ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ ቦታ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ አይወርድልህም፡፡ ወደማሳይህ ቦታ ተነሥተህ ሂድ፣ በዚያም እስከ ዕረፍትህ ቀን ድረስ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ ይወርድልሀል፡፡ ይህን ዓለም ለማሳለፍ እስከምመጣበት እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ የእኔ ጌትነት የአንተም የቅድስና ሕይወት የሚነገርበት፣ የሥጋህ የዕረፍት ቦታ የሚሆንበት፣ ለምትሠራው መቅደስ ክዳን የሚሆን ሣር የማትፈልግበት ሰፊ ዋሻ እሰጥሀለው ፣ በዚያ ቤተ መቅደሴን ሥራ፣ እኔ በምትሠራው ቤተ መቅደስ ከአንተ ጋር ለዘለዓለም ቃልኪዳኔን አቆማለሁ፡፡ በምታንጸው ቤተ መቅደስ ውስጥ ‹አቤቱ የይምርሃነ ክርስቶስ አምላክ ሆይ! ስለወዳጅህ ስለ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ብለህ ይቅር በለኝ› እያለ ‹አባታችን ሆይ!› የሚለውን ጸሎት የሚጸልይ ዕለቱን እንደተጠመቀ አደርገዋለሁ፡፡ ነገ ማለዳ ተነሥተህ ወግረ ስሂን ወደ ሚባለው የዕረፍትህ ቦታ ወደሚሆነው ዋሻ ሕዝብህን አስከትለህ ሂድ፤ በዚያም ቤተ መቅደሴን አንጽ›› ብሎ ቃልኪዳን ሰጠው። ይምርሐነ ክርሰቶስም ሕዝቡን ይዞ ተነሳና አሁን ከቅዱስ ላሊበላ ቤተ መቅደሶች 42 ኪ,ሜ ርቀት ላይ ወደሚገኘውና ጥቁር አለታማ ተራራ ሥር ወዳለው የውግረ ስሂን ዋሻ አመራ። ሲደርስም ቦታው የሰዎች ይዞታ ሆኖ ስላገኘው እኔ ንጉሥ ነኝ ብሎ እነርሱን በግፍ ሳያስለቅቅ ካሳ ከፍሎ ስፍራውን ተረከባቸው። ውስጡ ግን ውሀ የቆመበት ባህርና ርኩሳት መናፍስት የሞሉት ስለነበር መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መናፍስቱን አባሮ በባሕሩ ላይ ቤተ መቅደሱን እንዴት እንደሚያንጽ ገለጠለት። እርሱም በተነገረው መሠረት ለግንባታው የሚያስፈልጉ እቃዎችን ከኢየሩሳሌም አስመጥቶ ማነጽ ጀመረ።የውሀውን ክፍል እንጨት ረብርቦ አፈር እየበተነ ደለደለው። ሰዎች በባህር ላይ መሠራቱን እንዳይጠራጠሩም አነስተኞ መስኮትነገር አበጀለት። (በዚህችም አሁን ድረስ በክንድ ርቀት ያህል ከሥር ያለው ውሀ ይነካል።)ከበላዩም ስስ ሆነው የተፈለጡ ድንጋዮችን በኖራ እያቦካ በማያያዝ በእኩል መጠን እየገነባ በመሀከላቸው እንደ መቀነት የተጠረቡ እንጨቶችን በማስገባት አሳምሮ አነፀው። ውስጡንም በሦስት ቤተ መቅደሶች ከፈለው በየመስኮትና በየበሮቹም ላይ እንደ ዐይነ እርግብ ሆነው የተፈለፈሉ ሐረጎችን አደረገበት ጣሪያውንም በሰባቱ ሰማያት ምሳሌ ምስጢር ባላቸው የተለያዩ ቅርፆች አስዋበው።ይህን አድርጎ ሥራውን ከጨረሰ በኋላም የቅዱስ ገብርኤልን የእመቤታችንንና የቅዱስ ቂርቆስን ታቦታት አስገባበት።በድጋሚም ቤተ መንግሥቱን በዛው ዋሻ ውስጥ
Показать все...