cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ትምህርት በቤቴ®

A channel created for sharing 🔺study tips, 🔺short notes, 🔺tutorials, 🔺educational news, 🔺life tips and some motivational quotes ... Buy ads: https://telega.io/c/AAAAAFAvYe4hmoy1ouXbBA 📩 For comment- @Tmhert_bebete_info_bot

Больше
Рекламные посты
85 468
Подписчики
-7124 часа
-3677 дней
-1 73130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
#Update አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና #በድጋሜ የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች ውጤት ይፋ ተደርጓል፡፡ በድጋሜ የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ ተፈታኞች ውጤት ሲማሩበት ወደነበረው ተቋም መላኩንና ተፈታኞችም ወዛው በመሔድ ማየት እንደሚችሉ በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለቲክቫህ ተናግረዋል። በተጨማሪም👇 https://result.ethernet.edu.et/ ላይ በመግባት ውጤት ማየት ይቻላል። በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር ለተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ እንደሚችሉም ተጠቁሟል። ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇 ❤️ @temhert_bebete ✅ ❤️ @temhert_bebete
Показать все...
👍 1 1
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀመረ! የ2016 ዓ.ም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀምሯል።በዛሬው ዕለት የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ መሆኑ ታውቋል፡፡ፈተናውን በይፋ ያስጀመሩት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)÷ ዛሬ የሚሰጠው ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የበይነ መረብና የወረቀት ፈተና በድብልቅ ነው ብለዋል። በመላ ሀገሪቱ የተጀመረው የበይነ መረብና የወረቀት ፈተና እንደ ሀገር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተያዘው እቅድ አካል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡በመላው ሀገሪቱም ፈተናው በሰላም እየተሰጠ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ይሰጣል።የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከ700 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በወረቀትና በኦላይን እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡ በትግራይ ክልል ደግሞ በሁለት ዙር ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን ከትናንት ሐምሌ 2 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።ይህም የሆነው በቀድሞው ሥርዓተ-ትምህርት የተማሩ በ2013 እና በ2014 የትምህርት ዘመን መፈተን የነበረባቸው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተና የሚወስዱ በመሆኑ ነው። [FBC] ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇 ❤️ @temhert_bebete ✅ ❤️ @temhert_bebete
Показать все...
👍 5
የወሰዳቸውን 52 ኮርሶች በሙሉ A+ ያመጣው ተመራቂ ተማሪ መርቲኑ ቶሌራ በ2016 ዓ.ም ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ በአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቋል፡፡ ባለብሩህ አዕምሮው ተማሪ መርቲኑ 4.00 አጠቃላይ ውጤት (CGPA) በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ተማሪ መርቲኑ በዩኒቨሲቲ ቆይታው የወሰዳቸውን 52 ኮርሶች በሙሉ A+ በማምጣት ድንቅ ውጤት አስመስግቧል። ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇 ❤️ @temhert_bebete ✅ ❤️ @temhert_bebete
Показать все...
🏆 21🥰 5👍 4👏 3 2😁 2😱 1
#Tigray #UEE በትግራይ ክልል በወረቀትና በበይነ መረብ እየተሰጠ ያለው ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና ተጀምሯል። ፈተናው በክልሉ በሁለት ዙር ከሐምሌ 2-12/2016 ዓ.ም በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡ የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 2-5/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ ከ31 ሺህ በላይ የማኅበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዚህ ዙር ለፈተና እንደሚቀመጡ ይጠበቃል፡፡ ተፈታኞች በአጠቃላይ የፈተና ዲሲፕሊን ዙሪያ ገለፃ በተቋማቱ ተደርጎላቸዋል፡፡ 📌በሌሎች ክልሎች ነገ የሚጀምር ይሆናል ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇 ❤️ @temhert_bebete ✅ ❤️ @temhert_bebete
Показать все...
👍 4 1
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ከቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደሚፈተኑበት ተቋማት ገብተዋል። ዛሬ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኞች ገለፃ ሲሰጡ የዋሉ ሲሆን ሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነገ ኦረንቴሽን እንደሚሰጡ ይጠበቃል። የመጀመሪያው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ይሰጣል። ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇 ❤️ @temhert_bebete ✅ ❤️ @temhert_bebete
Показать все...
👍 6 4
የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መርሃግብር መልካም እድል ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇 ❤️ @temhert_bebete ✅ ❤️ @temhert_bebete
Показать все...
👍 5🔥 2 1🙏 1
ስለ ዘንድሮ 12ኛ ክፍል ፈተና “ በሙከራ ላይ እኛ ያጠፍናቸው ጣቢያዎች አሉ እንጂ ፈተና ይቀራል ብለን የሰጠነው መግለጫ የለም ” - ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪ ወላጆችና ከተማሪዎች ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ስለተጠየቀበት የበየነ መረብ (ኦንላይን) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱን ጠይቋል። ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ምን አሉ ? “ ፈተና በሁለት አይነት መልኩ (በኦንላይንና በወረቀት) ይሰጣል። በኦን ላይን የሚሰጠው ዩኒቨርሲቲ ላይ ተመድበው የነበሩ አብርሆት ላይብረሪና ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ብቻ ይሆናሉ። የተቀሩት ግን በሁሉም በግልም በመንግስም መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩ ት/ቤቶች ሆኖ በተመደቡበት (ድልድል የወጣላቸው ት/ቤቶች ያውቃሉ) መሠረት ፈተናውን በወረቀት ይወስዳሉ። በኦንላይን ፈተና የሚወስዱት፦ - በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ  - በሲቪል ሰርቪስ - በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  - በአዲስ አበባ ሳይንሰና ቴክኖሎጂ - በጳውሎስ ሚሊኒየም የተመደቡ በዚያ ይወስዳሉ። እንዲሁም፣ በአብርሆት ላይብረሪ ላይ የተመደቡ ተማሪዎች፣ የሁለቱ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በኦንላይን ይወስዳሉ። የቀሩት ግን በሌላ መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩት ስለታጠፈ በወረቀት ይወስዳሉ። በወረቀት የሚወስዱት ዩኒቨርሲቲ ነው የሚገኙት በባለፉት ሁለት አመታት እንደተሰጠው ማደሪያቸውም፣ መዋያቸውም፣ መፈተኛቸውም እዛው ይሆናል። አድረው ሲጨርሱ ነው የሚወጡት። በኦንላይን የተመደቡት ግን ውሎ ገብ ነው። ተፈትነው ወደ ቤታቸው ሂደው አድረው ተመልሰው በጠዋት መጥተው ይፈተናሉ። ” ብለዋል። የተፈጠረው ውዝግብ ምንድን ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ፥ “ የተፈጠረ ነገር የለም። በድብልቅ መንገድ እንደምንጥ ታሳቦ ነበረ። እሱን ነበር ስንለማመድ የነበረው ” ነው ያሉት። “ አሁን More እርግጠኛ በተኮነበት መፈተኛ ጣቢያ (ከላይ በተገለጹት) ብቻ ይሰጣል። ” ሲሉ አክለዋል። ትምህርት ቤቶች “ ቀርቷል ” ሲሉ ተስተውለዋል፤ ታዲያ መረጃውን ከየት አግኝተውት ነው ? ቢሮው ትዕዛዝ አውርዶ ነበር ? ስንል ኃላፊውን ጠይቀናል። ዶ/ር ዘላለም ፥ “ በዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ጣቢያቸዎች እንደሚሰጥ ነገር ግን ሌሎች ጣቢያዎች የነበሩት፣ በእነርሱ ላይ ካልሆነ በስተቀር ' ቀርቷል ' ተብሎ የተሰጠ መግለጫ አልነበረም ” ብለዋል። አክለው፣ “ ለሙከራ ስንሞክርባቸው የነበሩ እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ተማሪዎችና ቤተሰብ ላይ እንግልት እንዳይሆን እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ቀንሰናል ” ያሉት ኃላፊው፣ “ በእርግጠኝነት ሊፈጸሙባቸው ተብሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ የተወሰኑት ላይ ግን ተወስኗል ” ብለዋል። ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው እንደቀረ ያስተላለፈው መልዕክት ነበር ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ፣ “ ትምህርት ሚኒስቴር እኮ በገጹ ላይ አስታውቋል እንዳልቀረ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። “ በሙከራ ላይ እኛ ያጠፍናቸው ጣቢያዎች አሉ እንጂ ፈተና ይቀራል ብለን የሰጠነው መግለጫ የለም። በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች ተይዘው የነበሩት በተለያዩ ምክንያቶች ተቀንሰዋል ” ብለዋል። ቢሮዎ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፣ ለትምህርት ሚኒስቴር ጻፈው ተብሎ ሲሰራጭ የነበረው ደብዳቤ (ከላይ ተያይዟል) የቢሮ ነው ? ለሚለው ጥያቄ ፥ “አዎ። ትክክል ነው !! ” ብለዋል። “ አሁን ባልናቸው ጣቢያዎች ማለት ነው። በፊት በ153 ጣቢያዎች ብለን ነበር ይዘን የነበረው አሁን ግን በእርግጠኝነት ይሳካል የተባለበት ቦታ ከላይ የተጠቀሱት ጣቢያዎች ብቻ ናቸው ” ሲሉ ተናግረዋል። በመሆኑም በተቀመጠው መርሀ ግብር መሠረት ተማሪዎች ከምንም አይነት ውዢምብር ራሳቸውን ጠብቀው ከቢሮውና ከትምህርት ሚኒስቴር በሚወርዱ መመሪያዎች ብቻ ተረጋግተው እንዲፈተኑ አሳስበዋል። #TikvahEthiopia ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇 ❤️ @temhert_bebete ✅ ❤️ @temhert_bebete
Показать все...
👍 17 3😢 1
#NationalExam የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ጀምረዋል። ተፈታኞች ከትናንት ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲ እየገቡ ናቸው። ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ/ም ይሰጣል። በትግራይ ክልል ፈተናው ከሐምሌ 2 እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል። በትግራይ በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት የተማሩና በ2013 እና በ2014 የትምህርት ዘመን መፈተን የነበረባቸው ተፈታኞች ናቸው ፈተናቸውን የሚወስዱት። ትምህርት ሚኒስቴር የዘንድሮውን ብሔራዊ ፈተና በወረቀት እንዲሁም የተመረጡ ተማሪዎች ደግሞ በኦንላይን እንደሚወስዱት አሳውቋል። ዘንድሮ ከ700 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተናው ይቀመጣሉ። የፀጥታ ችግር ባለባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር ፈተና ይዘጋጅላቸዋል። ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇 ❤️ @temhert_bebete ✅ ❤️ @temhert_bebete
Показать все...
👍 14 2
✳️ በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች! 😊 🔰 ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው ። ይህም ጤናማ ፍርሀት ለፈተና እንድንተጋ ስለሚረዳን በተሻለ ለመዘጋጀት እንዲሁም ጥሩ ትኩረት ለመድረግ ያስችለናል።  ሆኖም ግን ይህ ጭንቀት ወይም ቴንሽን መጠነኛ ካልሆነ ወደ መደናገር እና ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። በዚህም የተነሳ ፈተናችንን በጥሩ እንዳናስኬድ እና ተገቢውን ትኩረት እንዳንሰጥ ያረገናል ።  ከዚህም ሀሳብ ጋር በተያያዘ ለዚህ አይነቱ ጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ እንድንገባ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ:  •📌 አሉታዊ ሀሳቦች ወደ አዕምሮ በመምጣት ሀሳባችን በሙሉ ስለ ፈተናው አስከፊነት እና ስለውጤት መበላሸት አብዝተን ስናስብ ። •📌 በቂ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ግመታ እና ድምዳሜ አጠቃሎ ስለፈተናው ማሰብ ።  •📌 የውጫዊ ተፅእኖ እንደ ቤተሰብ ፣ መምህራን እና ጓደኛ የሚመጡ ጫናዎች አስተሳሰባችን ላይ ይህ መሆን አለበት ወይም መሆን የለበትም የሚል አቋም መያዝ ስህተትን እንዳንቀበል እና መሳሳትን እንድንፈራ ስለሚያረግ በፈተና መዳረሻ ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። 📌• ሙሉ ሀሳብን ወደ ፈተናው ይዘት እና ሁኔታ ከማተኮር ይልቅ ወደ ውጤት እና ነጥብ ብቻ ላይ ማተኮር እና ማስላት።  እነዚህ ዋና ዋናዎቹ በፈተና ወቅት ውጥረትን እና ጭንቀትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ናቸው።  ስለዚህ ተፈታኞች የተወሰነ ዘዴን በመጠቀም ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤ 🙌🏾 ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤ 🎯• ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።  🎯• ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ይህ ማለት ስለፈተናው ክብደት እና አስከፊነት ከማሰብ በተቃራኒው በአይነ ህሊና (visualization) ዘና ብለን ስንፈተን እና ፈተናውን በተገቢ መንገድ ስንፈተን በአእምሮችን መሳል ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በክፍል ውስጥ በብቃት የሰራናቸውን ፈተናዎች እና የገኘነውን ጥሩ ውጤቶች ማሰብ።  እናም ምን አይነት ፈተና ሊመጣ ይችላል ብለን አብዝተን አለመጨነቅ ይልቅ የሚመጣው ፈተና ከዚህ በፊት ከተማርነው የተለየ አለመሆኑን መረዳት እና መጪውም ፈተና በተመሳሳይ እንደምንሰራው ማሰብ። 🎯 • ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። ምክንያቱም ከላይ እንደ ምክንያት ለተቀመጡት ነጥቦች ከዚህ ሀሳብ በተያያዘ አንድ ተማሪ በፈተና ጥሩ ውጤት ባያገኝ እና ቢሳሳት ቀድሞውኑ ወደ ጭንቅላቱ የሚመጣው አለማወቁ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እና ቤተሰቦቹም ሆነ መምህራን እንደ ሰነፍ እና ዋጋ እንደሌለው ስለሚገመት ስህተትን አስተካክሎ ለቀጣይ ለማሻሻል እና ለመማር መሰናክል ይፈጥራል።   ስለዚህ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።  🎯• ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።  🎯• የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል። 🔰 ፈተና ከጀመርን በኋላ መድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤ 🍁 • ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።   🍁• አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።  🍁• ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ። 🍁 • በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር፡፡ ለምሳሌ ;አሁን ደህና ነኝ ፥ ጥሩ ሆኛለሁ ወይም በምናምነው ሀይማኖት ጊዜ የማይወስድብንን አጭር ፀሎት በልባችን መፀለይ። ከዛም መልሰን በተረጋጋ መንፈስ ፈተናውን መጀመር።  🍁• ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤ 🍁  • በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ። 🍁• ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።  🍁• በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። ይልቅ በጣም ሳንንቀራፈፍ ተረጋግተን ፈተናውን  መስራት እና ፈተናውን ከጨረስን በኋላ ተመልሰን የሰራነውን ጥያቄ አጠቃላይ ማየት። 
Показать все...
👍 14🔥 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቴሌግራም Officially ወደ ገንዘብ መስሪያ አፕነት እየተለወጠ ነው በትላንትናው እለት ሰው በመጋበዝ ብቻ በርካታ ገንዘብ የመሰብሰብ እድልን ፈጥሯል ብዙዎችን ገና አልነቁበትም እመኑኝ ከየትኛውም ኤርድሮፕ በላይ በዚ ገንዘብ ታገኛላችሁ። ያገኛችሁን ታወጣላችሁ list ሚደረግ ነገር የለም ክፍያው በ TON ነው https://t.me/major/start?startapp=433177540 በዚህ ሊንክ ማየት ይቻላል
Показать все...
👍 5😁 1
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.