cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Telkhis (هذه عقيدتنا)

Рекламные посты
6 311
Подписчики
-524 часа
-227 дней
-9930 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
እናት እና አባቷ ሳይጋቡ ወለዷት። እሷም ከተወለደች በኋላ አልተጋቡም። ተራራቁ ኧረ እንዳውን ልጅቷን እናቷ ሳትሆን አባቷ አሳደጋት። ከሚስቱ ከወለዳቸው ልጆቹ አብልጦ እየተንከባከበ፣ ወደአኼራ ሲሸጋገር ራሱ ይችው ልጁ እንዳትበደልበት ዉርስ ውስጥ እንድትካተት ኑዛዜን አስተላልፎ አለፈ። ልጅቱ አደገች። ለቁም ነገር ደረሰች። ትዳር ለመመስረት ብዙ ርቀትን ትሄዳለች። ሊያገቧት የሚሹ ወንድሞች ጉዳዪን ሲያውቁ በአባትሽ መጠራት የለብሽም። ስምሽን ቀይሪ ይሏታል። ጋሻና መከታ ሆነው ያሳደጓትን እነዚያን ወንድሞቿን እነሱኮ ባዳዎች ናቸው፣ አጅነብዮች። ከነሱ ጋር ብቻሽን መገኘት የለብሽም። እንደጸጉር፣ እጅ፣ እግር ፣አንገት--- ያሉ ሰውነቶችሽን ራሱ ሊያዩት አይፈቀድላቸውም ይላሉ። ለትዳር ወሊይ መሆን አይችሉምና አንች በነሱ ኒካህ ማድረግ አትችዪም ይላሉ። ለሷ ደግሞ እነኚህ ወንድሞች የሚያነሷቸውን ሀሳቦች መቀበል እጅግ በጣም ከባድ ነው። በዚሁ ምክንያት ጉዳይዋ ጫፍ ይደርስና እንደገና ዜሮ ይሆናል። ሀቂቃ በዚህ ዙሪያ እንደጉድ የተሰራጩ የምሁራኖቻችን ፈተዋዎች መረጃዎችንም ተጨባጭ ግኝቶችንም ባካተተ መልኩ በደንብ ሊከለሱ ይገባቸዋል። እንዴት ያለ አንዳች #ግልጽና_ትክክለኛ መረጃ አባት የለሽም፣ በእናትሽ ተጠሪ፣ ወሊይ አልባ ነሽ ይባላል?
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
እስኪ 5ትም 100ቶም ብትሆን እንደአቅማችሁ ጣል አድርጉበት እህት ወንድሞች። ለመጨረስ በጣም ረጂም አመታት ወሰደብንና አግዙን እስኪ
Показать все...
እኛም በወረዳችን ላይ ኹለፋኡ ራሺዲን የሚሰኝ መስጅድ በመስራት ላይ ከተሰማራን አመታት አለፉን። አሁን ላይ የማጠናቀቂያ ስራዎች ይቀሩናል። መስጅዱን በዋነኝነት የሰሩት በአረብ ሀገር የሚኖሩ የኩታበር ወረዳ ተወላጆች ናቸው። በተጨማሪም ደግሞ በአሜሪካ የሲያትል ሙስሊሞች በቃላት የማይገለጽ ትልቅ ዉለታ አለብን። አሁን ላይ የቀረን ምንጣፍ ሚናራ የመብራትና የዉሃ መስመር ዝርጋታ የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ደረጃዎች ናቸው ሰሞኑ በዋትስ አፕ ተሰባስብን ሁላችንም የምንችላትን ያክል ሳንቲም እያሰባሰብን ነው። እንደሚታወቀው እኛ ብዙ የሚድያ ሽፋን የለንም። ፕርጀክቱ በታዋቂ ሰዎችም አይደገፍም። ግን እንድሁ እሱም ስሙም ከማይታወቁበት ቦታ ላይ መስጅድ በማሰራቱ ላይ #ሊላህ ብሎ የሚያግዝ ካለ ቢተባበረን ምንዳውን ከአላህ ዘንድ በዝቶ ተበራክቶ ያገኘዋል።
Показать все...
#በለተሞ_መንጋ የምርቃና ስብከት ለተጠለፋችሁ ሁሉ! ~ 1ኛ፦ እነዚህ ሰዎች የመንሀጅ ግንዛቤያቸው የተንሻፈፈ፣ የግል አመላቸውንና ሰለፊያን የሚያምታቱ ስለሆነ የሰለፊያን ግንዛቤ ከነዚህ ሰዎች አትውሰዱ። ይልቁንም ጊዜው የሚመች ነውና ከነ ኢብኑ ባዝ፣ አልባኒይ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ፈውዛን፣ ዐብዱልሙሕሲን አልዐባድ፣ ... ኪታቦችና የድምፅ ቅጂዎች ተጠቀሙ። ከነሱም በላይ የቀደምት ዑለማዎችን አካሄድ በሚገባ ፈትሹ። እነዚህ ሰዎች ሰለፊያ ነው ብለው የሚያቀርቡላችሁ ከክፉ አመላቸውና ሸውራራ ግንዛቤያቸው ጋር የተቀላቀለ ቡድንተኛ አካሄድ ነው። የሱና ዑለማኦችን የሚያጣቅሱት ለሽፋን ያህል ነው። 2ኛ፦ ደዕዋችሁ የአካባቢያችሁን ተጨባጭ ያገናዘበ ይሁን። አዲስ ብሄርተኛ ይመስል መንሀጅ በተገነዘባችሁ ማግስት በትንሽ በትልቁ ሌሎች ጋር አትላተሙ። እነዚህ የሚያጋጯችሁ አካላት ከምትገቡበት አጣብቂኝ እንድትወጡ የሚያግዝ ይሄ ነው የሚባል ሃሳብ እንኳ ማቅረብ አይችሉም። እነሱ እንደሆኑ ለራሳቸው ጥቅም ሲሆን ካሜራ ውስጥ እንዳይገቡ እየተሹለከለኩ፣ ማስክ እያጠለቁ የሚጣዱ ናቸው። እነሱን ተከትላችሁ ደዕዋችሁ ቢሰናከል ብዙ ርቀት ወደ ኋላ ይመልሷችኋል። 3ኛ፦ ለፍረጃና ለተብዲዕ አትቸኩሉ። በቂ የመንሀጅ ግንዛቤ ያልያዘ ሰው ፈፅሞ ለተክ -ፊርና ለተብዲዕ ብቁ አይደለም። ነገሩ በሚገባ ተገልጦልናል ብላችሁ በምታምኑበት ጉዳይ ራሱ በመናገራችሁ የሚገኘውን ትርፍና ኪሳራ አስሉ። የደመ ነፍስ አካሄድ ማንንም አይጠቅምም። 4ኛ፦ የለተሞ ጭፍራዎች ጋር መጓዝ መስጂዶቻችሁን ያሳጣችኋል። ከማህበረሰብ ጋር ያጋጫችኋል። በሂደት ደዕዋችሁን ወይ ሙሉ ለሙሉ ያጠፋዋል። ወይ ደግሞ በእጅጉ ያቀጭጨዋል። ብዙ ካበላሻችሁ በኋላ ግራ ቀኝ አይታችሁ የተሻለ መስለሐ ያለበትን ውሳኔ ብትወስኑ ራሱ እነዚህ እባቦች ከማንም በላይ የሚናደፉት እናንተን ነው። የቻግኒው ሸይኽ ከማል አፍሪ ጉዳይ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል። ቀድመው በነዚህ አካላት የተሳሳተ አቅጣጫ ይዘው ነበር። አሁንም ምን ያህል እንደነቁ አላውቅም። የተሻለ መስለሐ አይተው መስጂድ ገብተው ሲያስተምሩ እድሜያቸውንም፣ ውለታቸውንም በማይመጥን መልኩ እያብጠለጠሏቸው ነው። "ያሳደጉት ውሻ፣ ያሳጣል መድረሻ!" 5ኛ፦ የአካባቢያችሁን መስለሐ ራሳችሁ ወስኑ። በሩቅ ያለ ሰው ያላችሁበትን ተጨባጭ ላያውቅ ይችላል። በተለይ እነዚህ ከህሊናቸው የተጣሉ አካላትን ፈፅሞ አታማክሩ። እንኳን ለናንተ ለራሳቸውም የሚሆኑ አይደሉም። አስፈላጊ ሲሆንና ከተቻላችሁ ዑለማኦችን አማክሩ። እነዚህ የሚጮሁትን የማይኖሩ ደናቁራን እንዳያሳስቷችሁ። ለተሞ በራሱ ምስክርነት ከ10 አመት በላይ ኢኽዋንን ሲያደንቅና አብሮ ሲጓዝ የኖረ ሰው ነው። አሁንም ከተወሰኑት ጋር ያፋጠጠው የጥቅም ግጭት ነው። እንጂ የጥቅም ቃል ሲገባለት እንኳን ከነዚህ ጋር ይቅርና ቀድሞ ተብዲዕ ካደረጋቸው ሰዎች ጋር ራሱ ሊታረቅ እልል ሲል ነበር። አሁንም የተሻለ ካየ ለሌላ ይፈርማል። ባህሩም ከሙብተዲዕ ጋር መቀማመጥ ሲል ለዲን ተቆርቁሮ አይደለም። የራሱ አንዱ ጋሻጃግሬ ከሚያወግዛቸው አካላት ጋር የመስጂድ ኮሚቴ አባል ነው። ኮሚቴው በመጅሊስ መዋቅር ስር እንደሆነ አስተውሉ። የባህርዳሩም ጭፍራ ዲን አይደለም ከመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ጋር ያፋጠጠው። "ለኛ የተላከ ኪታብ ወስደውብን ..." እያለ ነው የህፃን ለቅሶ የሚያለቅሰው። ራሳቸው በቡኻሪ መስጂድ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድን ፕሮግራም አስተዋውቀው ሲያበቁ እነዚህ ከህዝቡ ብር ሲሰበስቡ ጊዜ ጨርቃቸውን ጣሉ። በቀናት ልዩነት ውስጥ ተነስተው አስጠነቀቁ። ስሜታቸውን የማይቆጣጠሩ፣ ይሉኝታ የማያውቁ ጉዶች ናቸው። እንጂ ዛሬ ለተብዲዕ የሚመዙትን ጉዳይ እየጠቀሱ ተብዲዕ ግን አናደርግም ሲሉ እንደነበር የድምፅ መረጃ አለ። 6ኛ፦ በደዕዋ ላይ ተመዩዝ አስፈላጊ ነው። ተመዩዝ ማለት ግን በራስ ላይ በር ዘግቶ መጮህ አይደለም። ከሆነላችሁ ያለ ንክኪ አስተምሩ። መድረክ ካገኛችሁ አቋማችሁ የተጠበቀ እስከሆነ ድረስ በሱፊዮች መስጂድ እንኳ ቢሆን አስተምሩ። ታላላቅ መሻይኾች በሱፊያ መስጂዶች ያስተማሩበት ተጨባጭ አለ። ለምሳሌ ሸይኽ ረቢዕ ሱዳን ውስጥ በሱፊያ መስጂድ አስተምረዋል። "በአቋም ቢገናኙ ነው ከነ እንትና መስጂድ የሚያስተምሩት" የሚለው የነዚህ ሰዎች ጩኸት ዝቅ ቢል ድንቁርናቸውን ከፍ ቢል አታላይነታቸውን ነው የሚያሳየው። ለአመታት ሂዝቢዮች ላይ ቁጭ ብለው ሲማሩ ነው የኖሩት። ባህሩ፣ ሁሴን ሲልጢ እና ጠሀ ኸዲር ለዚህ ምሳሌ መሆን ይችላሉ። ራሳቸው የሳዑዲ ጃሚ0ዎች በሒዝቢዮች የተጥለቀለቁ እንደሆኑ ይገልፃሉ። ራሳቸው በንዲህ አይነት ተቋማት ቁጭ ብለው እየተማሩ እኛ ጋር መጥተው እንትናን ከእንትና ጋር አየነው እያሉ አድብተው ይጠብቃሉ። በሰሜን ወሎ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ ዞኖች የመጅሊስ መዋቅር ውስጥ የገቡ አሉ። ለተሞ በሚያብጠለጥላቸው የየመን መራኪዝ የሚማሩ የለተሞ መንጋዎች አሉ። የመን መዕበር ድረስ ሄደው ሙሐመድ አልኢማም ዘንድ የሚማሩ ሁሉ አሉ። እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ዐረብኛ ትምህርት በሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሙመይዐ ከሚሏቸው እና ኢኽዋኒዮች ዘንድ ቁጭ ብለው የሚማሩ አሉ። ከዚህም የባሰ ሱፊዮች ዘንድ ሳይቀር ሉጋ የሚማሩ አሉ። ራሳቸው በሚሰሩት ጉዳይ ሌሎችን ተብዲዕ የሚያደርጉ የማፊያ ስብስብ ናቸው። ጩኸታቸው የእውነት መስሏችሁ እነሱን የተከተላችሁ በጊዜ ብትነቁ ይሻላችኋል። ጥሪዬ በተለይ መሬት የረገጠ ደዕዋ ላላችሁ ነው። ደዕዋችሁን ሳታጡት በፊት ደጋግማችሁ አስቡበት። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
ሱጁድ እጅግ ያማረው የሶላት ክፍል ነው። ለዚህም ሲባል የሚሰገድባቸው ቦታዎች ራሱ መስጅድ ነው የሚባሉት። መስጅድ ማለት ሱጁድ የሚደረግበት ቦታ ማለት ነው። ይህም ሱጁድ እጅግ ወሳኙ የሶላት ክፍል ባይሆን ኖሮ የመስገጃ ቦታዎች መስጅድ ሳይሆን መርከዕ ወይም መቃም የሚል መጠሪያ ይሰጣቸው ነበር። (የሩኩዕ ወይም የቂያም ቦታዎች) ሶላት እንደጥቅልም ሱጁድ የሚል ስም የተሰጠው እንድሁ ወሳኝነቱን ለመግለጽ ነው። ክቡር ነብያችንስ صلى الله عليه وسلم ቢሆኑ እስኪ ሱጁድ በማብዛት አግዘኝ ብለውት የለ ከርሳቸው ጋር በጀነት ስለመጎራበት የጠየቀውን ባልደረባቸውን ኸላድን رضي الله عنه ። ሱጁድ አብዛ ማለታቸው ሶላትን አብዛ ለማለት አይደለ? በሱጁድ ላይ እንበርታ!! T.me/telkhis
Показать все...
አብዛኛው ኢጅማዕ አለበት በሚል የሚነገረው ቅርንጫፋዊ የፊቅህ እይታ በዑለማኦች ሁሉ ስምምነት ላይ የተደረሰበት አይደለም። ይሄን እጅግ በበርካታ ጉዳዮች ላይ አረጋግጫለሁ። ምሳሌዎችን እንጥቀስ ቢባል መድረኩ አይበቃንም። ስለዚህ አንዳንድ ምሁራኖች በሆነ ጉዳይ ላይ ለሚኖር አለመግባባት "የዑለማኦች ስምምነት አለበት" የሚልን መከራከርያ በማቅረብ የሚቃወማቸውም ምሁር ጸጥ ለማስባል መሞከራቸው ሊያስደነግጥ አይገባም። ሸይኽ አልባኒ T.me/telkhis
Показать все...
3 ውስብስብ የፊቅህ ትምህርት ምእራፎች --------------------------------------- ታዋቂው የዘመናችን የሀዲስ ሊቅ ሸይኽ ዐብዱልሙህሲን ዐባድን ከሀይድ ጋር የሚያያዝ አንድ ጥያቄ ጠየቅኳቸው። እኔ 3 ጉዳዮችን በተመለከተ ለሚቀርቡልኝ ጥያቄዎች ምላሽ አልሰጥም። ይልቁኑም ወደሌሎች መሻይኾች ነው የማስተላልፈው ብለው መለሱልኝ። እነዚህ 3 ጉዳዮች 1- ከወር አበባ ደም ጋር የሚያያዙን ጥያቄዎች 2- ከፍቺ ጋር የሚያያዙን ጥያቄዎችና 3- ሰዎችን ከእስልምና በማስወጣት ዙሪያ ላይ የሚቀርቡልኝ ጥያቄዎች ናቸው ብለው መለሱልኝ ይላል ሸይኽ ዐሲም ቀርዩቲ حفظهما الله T.me/telkhis
Показать все...
Follow the Telkhis channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaBBlGt47XeIIY7K9U23
Показать все...
Telkhis | WhatsApp Channel

Telkhis WhatsApp Channel. አጠር አጠር ያሉ ቁምነገሮችን በዋነኝነትም #አልሙለኸሱል_ፊቅሂይ የሚለውን ኪታብ መልእክቶች አጋራበታለሁ።. 108 followers

በጥቅሉ የስራ መዝገቦቻችን በሶስት መልኩ ይከፈላሉ ይላሉ ነብዩ صلى الله عليه وسلم። 1ኛው- በፍጹም አላህ ይቅር የማይለውና የማይምረው ወንጀል የተጻፈበት መዝገብ ሲሆን ይህም የሺርክ ወንጀል የተጻፈበት ነው። 2ኛው- አላህ ብዙም ቦታ የማይሰጠውና የማያጠብቀው እሱ ከፈለገ ይቅር የሚለው፣ የሚሰርዘውና ግለሰቡንም ለጀነት የሚያበቃው አይነት የስራ መዝገብ ነው። በዚህ መዝገብ ውስጥ የሚካተቱት ባርያ በራሱ እና በጌታው መካከል የፈጸማቸው ጥፋቶች ናቸው። በሀዲሱ ላይ እንደምሳሌ የተጠቀሱትም ያልጾማቸው ቀናቶች ያሉበት ወይም #ሆን_ብሎ_ያልሰገዳቸው_ሶላቶች ያሉበት ግለሰብን ነው። 3ኛው የስራ መዝገብ ደግሞ አላህ በፍጹም የማያልፈው (የማይተወው) የስራ መዝገብ ነው። በዚህ መዝገብ ውስጥ የሚካተቱት ወንጀሎች ፍጡራኖች ላይ የተፈጸሙ ግፎች ናቸው። ስርቆት፣ ስም ማጠልሸት፣ ግድያ፣ ስድብ፣ እርግማን፣ ድብደባ እንደምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ። ሀዲሱን ያስተላለፈችው እናታችን ዐኢሻ رضي الله عنها ስትሆን አህመድ፣ ሀኪምና በይሀቂይ ዘግበውታል። ከፊል የሀዲስ ሊቃውንቶች ይህንኑ ሀዲስ ትክክለኛና ተቀባይነት ያለው መሆኑን ሲገልጹ ሌሎች ደካማ ነው ብለውታል። ሸይኽ አልባኒ رحمه الله ይሄ ሀዲስ ደካማ መሆኑን ቢገልጹም ነገር ግን በዚህ ሀዲስ ውስጥ የተገለጹት መልእክቶች ፍጹም ትክክለኛና ተቀባይነት ባላቸው በሌሎች መረጃዎች የተደገፉ ናቸው ይላሉ። T.me/telkhis
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.