cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

ይህ የኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤተክርስቲያን ወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት ቻናል ነው 👉👉ለጠቅላላ @weldwahid 👉👉ለአብነት እና ግእዝ ቋንቋ ትምህርት @weldwahidabinet 👉👉 ለቤተ መጻሕፍት አገልግሎት @Abaiyesuslib 👉👉ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @mels_asteyayet

Больше
Рекламные посты
1 020
Подписчики
+624 часа
+237 дней
+8530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የፍጥረት ኹሉ ምንጭ የኾነውን እርሱን እመረምራለሁ ብለህ አትባክን። ህላዌ ራሱ የተሰጠን ከእርሱ ከእግዚአብሔር መልካምነት የተነሣ ነውና። እኛን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን ከእኛ አገልግሎት እጠቀም ብሎ አይደለምና። እኛም ስለ ፈጠረን ወይም ሕያዊትና ለባዊት ነፍስን ስለ ሰጠን ወይም ከሌሎች ፍጥረታት ይልቅ ልዑላን አድርጎ ስለ ፈጠረን ወይም በሚታዩት ፍጥረታት ላይ ገዥዎች አድርጎ ስለ ሾመንና ይህን በትረ መንግሥት ስለ ሰጠን ብቻ ሳይኾን [የሚጎድለው ኖሮ እንሞላለት ዘንድ] እኛ ለእርሱ የማናስፈልገው በመኾናችንም ልንገዛለትና ልናመልከው ይገባል። የመልካምነቱ አስደናቂነት እኛን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን እርሱ ከእኛ አገልግሎት የሚያገኘው አለመኖሩ ላይ ነውና። በእውነቱ እኛ መላእክትና ሰማያውያን ኃያላት ኹሉ ካለ መኖር ወደ መኖር ከመምጣታችን በፊት እርሱ በመንግሥቱ፣ በልዕልናውና በጌትነቱ አለና። እኛን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን እነዚህንና ሌሎች ብዙ የብዙ ብዙ መልካም ነገሮችን ለእኛ ያደረገው ለሰው ልጆች ካለው ፍቅር የተነሣ ብቻ ነውና። © መግቦተ እግዚአብሔር በቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ገጽ ፶፱
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
🌹    የነገረ ማርያም ትምህርት    🌹      🌹    ሰባተኛ  ጉባኤ            🌹         🌹  ግንቦት 18/2016   🌹            🌹    4:00-6:00   🌹               🌹መካነ ቅዱሳን🌹
Показать все...
👍 1
አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ! አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሷል፤ ያበሰብሷልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው? ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
Показать все...
2
+++ እግዚአብሔር ሲቀጣን ... +++ "[አንድ] ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡ "እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡" © ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ፥ ገ. 36
Показать все...
5
"ኃጢአትን ኃጢአት የሚያደርገው በገቢር መፈጸሙ ብቻ እንደ ኾነ አድርጋችሁ አታሰቡ፡፡ ኃጢአትን ኃጢአት አድርጎ በእኛ ላይ ፍዳ የሚያመጣው ቁርጥ ሕሊናችን ነው፡፡" ~ ኦሪት ዘፍጥረት፥ ድር. 22፥9
Показать все...
👏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
“ማግባት ስትፈልግ አስቀድመህ ጸልይ፤ አሳብህን ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እግዚአብሔር መርጦ እንዲሰጥህ ለምነው፡፡ ጭንቀትህን ኹሉ በእርሱ ላይ ጣለው፡፡ አንተ እንደዚህ እርሱ እንዲመርጥልህ የምታደርግ ከኾነም፥ አክብረኸዋልና እርሱም ለአንተ በጎ የትዳር አጋርን በመስጠት ያከብርሃል፡፡ ስለዚህ በምታደርገው ነገር ኹሉ ሽማግሌህ እርሱ እግዚአብሔር እንዲኾን ዘወትር ጠይቀው፡፡ አስቀድመህ እንደዚህ ካደረግህም፥ ወደ ትዳር ከገባህ በኋላ ፍቺ አይገጥምህም፡፡ ሚስትህ ሌላ ሰውን አትመኝም፡፡ በሌላ ሴት እንድትቀናም አታደርግህም፡፡ በመካከላችሁ [ለክፉ የሚሰጥ] ጠብና ክርክር አይኖርም፡፡ ከዚህ ይልቅ ታላቅ የኾነ ሰላምና ፍቅር በመካከላችሁ ይሰፍናል፡፡ እነዚህ ካሉ ደግሞ ሌሎች በጎ ምግባራትን፣ ትሩፋትን ለመፈጸም አትቸገሩም፡፡” © ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ፣ ገጽ 33
Показать все...
👍 4 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 " ኪዳነ ምህረት ማርያም" አተበቁዓኪ አነስ ትቤዝዊ በኪዳንኪ ዘዚአየ ነፍስ "እስመ በሥራይኪ ለቁስልየ ቅብዕኒ ፈውስ" ኪዳነምህረት" ማርያም ሆይ! በመድኃኒትሽ ቁስሌን እንድትፈውሽ በኪዳንሽ ቤዛነት ነፍሴን እንድታዳኚ እማለድሻለሁ። አሜን።                🌹 መልክአ ኪዳነምህረት🌹
Показать все...
👍 3
"እንበልና በመንገድ እያለፋችሁ ሳለ አንድ ሰው የሰውን ሰገራ ሲቆሰቁስ ብትመለከቱት ይህን በማድረጉ አትገሥጹትምን? በሐሜተኞች ላይም እንደዚህ አድርጉ፡፡ ምክንያቱም በእጅ የተቆሰቆሰው የሰው ሰገራ፥ በሐሜት የሌሎች ሰዎችን ኃጢአት የመቆስቆስና ንጹሕ ያልኾነ ሕይወታቸውን የማጋለጥ ያህል ሽታ የለውም፤ ውስጥንም ኾነ ነፍስን አይጎዳም፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ በእንተ ሐውልታት
Показать все...
2
የምጽዋት ብዛት የሚመዘነው በሚሰ’ጠው ገንዘብ ቁጥር ሳይኾን ስጦታውን በሚሰጥ የልብ ስፋት ነው፡፡ አንዲት ድኻ ሴት ያላትን ጥቂት እንጀራ ምንም ከሌላት ከሌላ ሴት ጋር ተካፍላ የምትበላ ከኾነ፥ ወርቅን በሙዳዬ ምጽዋት ከሚጨምር ባለጸጋ ሰው እጅግ ትበልጣለች፡፡ ነገር ግን ምንም እንኳን ይህ እውነት እንደ ኾነ ብዙ ክርስቲያኖች ቢያውቁም፥ ምስጋና የሚሰጡት ወርቅ ለሰጠው ነው፡፡ አንድ ባለጸጋ ጠቀም ያለ ገንዘብ ለቤተ ክርስቲያን ቢሰጥ እጅግ ያመሰግኑታል፤ ካለው የሀብት ብዛት የተነሣ ያንን በመስጠቱ ምንም ባይጎድልበትም እንኳ፥ በሰዎች ዘንድ እጅግ ቸር እንደ ኾነ ተደርጎ ይንቆለጳጰሳል፡፡ ድኻው ጥቂት ገንዘብ ቢሰጥ ግን ሰዎች ስለ እርሱ ምንም ትንፍሽ አይሉም፡፡ ምናልባት ያቺ የሰጣት ገንዘብ’ኮ በኋላ እርስዋን በማጣቱ ምክንያት ተርቦ እንዲያድር ልታደርገው የምትችል ትኾን ይኾናል፤ ነገር ግን ይህን በማድረጉ የሚያመሰግነው አንድ ሰውስ እንኳ አይገኝም፡፡ በእውነት ያለ ሐሰት ምንም ሳይጎድልበት የሰጠውን ባለጸጋውን አመስግኖ ያለውን ኹሉ የሰጠውን ድኻ ሳያመሰግኑ ከሚቀሩ ከእነ ጭራሹ ምስጋና ባይኖር ይሻል ነበር፡፡ ስለዚህ እውነተኛ ምጽዋት የሚባለው የባለጸጋውም ይኹን የድኻው በአግባቡና በሥርዓቱ ልናውቀው ይገባናል፡፡ ማመስገን የሚገባንም ከዚያ በኋላ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የምስጋናችን ስጦታም ሰዎች ከልባቸው ከሚሰጡት ገንዘብ ብዛት አንጻር ሊኾን ይገባል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Показать все...
👍 4 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
🚌  ጉዞ ወልድ ዋህድ  🚎 ⛪️ ወደ ጻድቃኔ ማርያም    📆 ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም                  👉  ትኬቱን  በሰንበት ት/ቤቱ        መዝሙር ቤት ያገኙታል ለበለጠ መረጃ 📱 09 85 46 75 66                                    ይደውሉ።   👉በዚህ ጉዞ ላይ በመሳተፍ በረከት ያገኙ ዘንድ               ‼️ ፈጥነው ይመዝገቡ  ‼️
Показать все...