cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

DA'AWA SELEFIYA IN AMBO UNIVERSITY

ከቁርኣን እና ሐዲሥ፣[በሰለፎች አረዳድ] እንዲሁም ከታማኝ ዑለማዎችና ከትክክለኛ ቂያስ የተጠናከሩ      #አጫጭር የድምፅ ፋይሎች      #ተከታታይና ወቅታዊ ፅሁፎች ሁሉንም፤በተለይም ተማሪዎችን የሚመለከቱ ይለቀቅበታል። ይቀላቀሉን አስተያየት ሲኖራችሁ ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️ @Dsiaunivbot  ብታሳውቁን ይደርሰናል። ★ ጀዛኩሙልሏህ ኸይራ።

Больше
Рекламные посты
496
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
-830 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

🍂ጥቂት ምክሮች ለኔና ለአምሳያዎቼ እውቀት ፈላጊዎች ቁ:1⃣2⃣ በዑለሞች መካከል በተፈጠረ ጉዳይ ላይ መቻኮል የእኛ ስራ አይደለም። ዑለሞች ከእውቀታቸው አንፃር በመካከላቸው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሊለያዩ፣ አንዱ አንዱ ላይ ምላሽ ሊሰጥ ይችላል። ታድያ እኛ ነገራቶቹን የመፍረድ አቅም ላይ እስካልደረስን አንዱን ጥለን አንዱን አንጠልጥለን የምንጓዝበት መርሆ ሊኖረን አይገባም። አንዳንዴ እኛ የምናልቃቸው እና ኪታቦቻቸውን የምንቀራ የሆኑ ዑለሞች በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ሌሎች ዑለሞች ሊቃወሟቸውና ምላሽ ሊሰጡባቸው ይችላሉ። ታድያ የተቹትን በመጥላት ጠርዝ ረግጠን እነርሱን በቅናት፣ በምቀኝነትና በአላዋቂነት ልንፈርጅ አይገባም። በተለይም ምላሽ ሰጪ ዑለሞቹ ቁጥራቸው የበዛና ያቀረቡት መረጃም አሳማኝ ከሆነ። ይህም በባለፈው ክፍል ካየነው ወገንተኝነት የሚመነጭ እንደሆነ ልብ ይሏል። አቡ ሁዘይፋህ https://t.me/nurmesjed ቁጥር 11: t.me/nurmesjed/2529
Показать все...
🍂ጥቂት ምክሮች ለኔና ለአምሳያዎቼ እውቀት ፈላጊዎች ቁ: 1⃣1⃣ ➡️ወገንተኝነትን ራቅ! ወንድሜ ለሃቅ እንጂ ለግለሰብ ወገንተኛ መሆን ከእኛ አይጠበቅም። የህ ለብዙዎች ሀቅን ለመሸሽ እና ቢዳዓ ላይ ለመውደቅ ምክንያት መሆኑን ዑለሞች ያወሳሉ።  ለሸይኽ፣ ለኡስታዝ፣ ለዳዒ ወዘተ ወገንተኛ መሆን የጃሂልዮች መንገድ አንዲሁ የቢዳዓ ባልተቤቶች መገለጫ ነው። ስለዚህም ወገንተኝነታችን ለአላህ ኪታብ እና ለመልእክተኛው ንግግር ሊሆን ግድ ነው። እንዳንዶች አነርሱ ዘንድ ካልቀራህ፣ የእነርሱን ሸይኽ ካላወደስክ፣ የእነርሱን አቋም "ሁሉ" ካላንፀባረቅ ምን ጠንካራ ብትሆን የሱና ሰው አድርገው አይቆጥሩህም። ይህ የተክፊርዮች አካሄድ ከመሆን የሚድን አይደለም። ታድያ ወንድሜ የሱና ሰዎች በርካቶች ሊሆኑ ይችላሉ። እኛ በምናውቀው ቦታ ብቻ ስላልተገኙ፣ እኛ የምንቀራውን ኪታብ ስላልቀሩ፣ እኛ የምንለውን ሁሉ ስላላሉ ከሱና ይወጣሉ ማለት አይደለም። በሃቅ ላይ የፀና የሆነ ሁሉ፤ ብናውቀውም ባናውቀውም የሃቅ ሰው ከመሆን የሚከለክላው ነገር እንደሌለ ልናውቅ  ይገባል። እንዲሁም ዛሬ ተንሰራፍቶ የምናየው የብሄር፣ የዘር፣የጎሳ ወገንተኝነት እኛ ዘንድ ቦታ ሊኖረው አይገባም። ውዴታችን ለሀቅ እና ለሀቅ ባልተቤቶች ብቻ ሊሆን ይገባል። ✍ አቡሁዘይፋህ https://t.me/nurmesjed ክፍል 10: t.me/nurmesjed/2508
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
🍂ጥቂት ምክሮች ለኔና ለኔ አምሳያ ደረሶች። ወንድሜ በዲንህ ላይ ጠንከር በል፣ እውቀትን በመማር ላይ በርታ። ባወቅከው ለመስራት ጥረት አድርግ።  ያወቅከውና በቅጡ የተረዳኸውን መልካም ነገር ደግሞ ለፈላጊዎቹ ለማድረስ ሞክር። ታድያ ለንግግርህ ቦታ እና አድማጭ ምረጥለት። ባገኘህበት ሁሉ የመጣልህን አታውራ። ያወቅከውን ሁሉ ደግሞ አትናገር። የተሳሳቱትን ለመመለስ  የምትሄድበት መንገድ አግባብነት ያለው ይሁን። ያለ ደረጃህ በነገራቶች ላይ አትፍጠን። ለዑለሞች የሚተው ጉዳዮችን ምረጥ። በተለይም በዑለሞች መሃከል "ትክክለኛ" ኺላፍ (ልዩነት) ያለባቸው ጉዳዮች ላይ አቋም ከመምረጥህ በፊት የልዩነቶቹ ሁኔታ አጢን። በተቃራኒው ባሉ አካላት ላይም ድንበር አትለፍ። ብዙዎች በዚህ ተፈትነው ከውቀቱ ሳይጠቀሙ ሲቀሩ አይተናልና። ምን ተሳስተዋል ብለህ ብታምን እንኳን ወደ ሱና የተጠጉ ሰዎች ላይ ለስለስ በል፣ በማስረጃ ምከራቸው። የቢዳዓ ባልተቤቶችን እየተወዳጀህ በተወሰኑ መስአላዎች የተለዩህ ወንድሞችህ ላይ ድንበር አትለፍ።  ጨረስኩ አላህ መልካሙን ይግጠመን። 🖊 አሁ ሁዘይፋህ’ https://t.me/amhakfelagijemaa
Показать все...
DA'AWA SELEFIYA IN AMBO UNIVERSITY

ከቁርኣን እና ሐዲሥ፣[በሰለፎች አረዳድ] እንዲሁም ከታማኝ ዑለማዎችና ከትክክለኛ ቂያስ የተጠናከሩ      #አጫጭር የድምፅ ፋይሎች      #ተከታታይና ወቅታዊ ፅሁፎች ሁሉንም፤በተለይም ተማሪዎችን የሚመለከቱ ይለቀቅበታል። ይቀላቀሉን አስተያየት ሲኖራችሁ ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️ @Dsiaunivbot  ብታሳውቁን ይደርሰናል። ★ ጀዛኩሙልሏህ ኸይራ።

Come and participate! https://cutt.ly/kwRfxIA4
Показать все...
02:21
Видео недоступноПоказать в Telegram
2.91 MB
00:38
Видео недоступноПоказать в Telegram
1.63 MB
00:38
Видео недоступноПоказать в Telegram
6.80 KB
البيان_المسدد_لإبطال_شبهات_الإحتفال_بالمولد.pdf8.99 KB
🍂ስንት አመትሽ ነው? ያልተጠበቀው አስደማሚው ገጠመኝ። ከደርስ እየወጣሁኝ በግምት እድሜያቸው አርባዎችን ምን የዘለለ ምን አልባትም ሃምሳዎችን የተጠጋ የሚመስሉ እናት ከፊት ለፊቴ ተመለከትኩ። ኪታባቸውን የያዙበት መያዣ የኪታቦቻቸውን ቅርፅ የደበቀ ስለነበር፤ ከመድረሳው ይሆን የወጡት ወይስ መንገደኛ ይሆኑ ብዬ አሰብኩ። ከፊቴ ቀድመውኝ ተረኛው ባጃጅ ላይ ተሳፈሩ። የቀረው ቦታ ከሳቸው ጎን ነበርና በተቀረችው ቦታ ቁጭ አልኩኝ። አሁንም ከመድረሳ ይሆን የወጡት ወይስ ከሌላ ቦታ?  ምን ብዬ ልጠይቃቸው እያልኩ ሳብሰለስል፤ ትንሽ እንደተጓዝን አለባበሴንና የኪታብ ቦርሳዬንም አስበው መሰለኝ፤ በሆነች ጉዳያቸው ላይ ሰበቡን እንዳደርስላቸው አማከሩኝ። ከደርስ እየወጡ እንደሆነ፣ እቤትም እንግዳ እንዳለባቸው ነገር ግን ከደርሱ አይበልጥብኝም ብለው እንደመጡ፣ ሰፈራቸውም መሰል ቂርአቶች እንደማያገኙም አወሱኝ። ደነገጥኩ! በዚህ እድሜያቸው ለቂርአት ያለቸው አመለካከት አስደመመኝ። ከመውረጃቸው ሲደርሱ በኢስላማዊ ሰላምታቸው ተሰናበቱኝ።  አላህ መጨረሻቸውን እንዲያሳምርላቸው እለምነዋለሁ።  አንቺስ እህቴ ስንት አመትሽ ነው? ለዲን ትምህርቶች ያለሽ አመለካከት እና ልፋት ምን ያህል ነው?  ዛሬ ባሉሽ የእረፍት ቀናት ሳይቀር ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጥደሽ ታሳልፊዋለሽ?  በእንቅልፍ፣ በጨዋታ እና በመዝናናት ብቻ እድሜሽን ትፈጃለሽ?  ወይስ ለቀጣዩ ህይወትሽ የምታስቀምጭው ቅሪት አለሽ? እስቲ ንቂ! ብዙ ቀስቃሾች ባሉቡት በዚህ ዘመን መተኛት ደግሞ እጅጉን ያሳፍራል። ✍ Abuhuzeyfah
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.