cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Za-HABSHA Abbisiniya

አሁን ላይ ፌክ ቻናሎች በበዙበት በዚ ሰዓት ትክክለኛና የተረጋገጡ #የጦር ግንባር ዜናዎችንና የተለያዩ ወቅታዊ እና እውነተኛ መረጃዎችን በታማኝነትና በፍጥነት ፈልፍሎ የሚያቀርብ የቴሌግራም "የመረጃ ቋት ቻናል ነው "በ ከሀገር ውስጥና የውጭ መረጃዎችን እናደርሳችሁዋለን በሚዲያ ከመተላለፉ በፊት በዚህ ማገኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ። @Zahabsha https://t.me/c/1325491570/2

Больше
Рекламные посты
196
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступно
40/60 የንግድ ቤቶች ጨረታ ! የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የከተማ አስተዳደሩ በ40/60 ፕሮግራም በተለያዩ ክ/ከተሞች ያስገነባቸውን 5,397 በጋራ መኖሪያ ቤቶች ሕንፃ ላይ የሚገኙ ንግድ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ እንደሚፈልግ ዛሬ አሳውቋል። ኮርፖሬሽኑ ለሽያጭ ያቀረባቸውን የንግድ ቤቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ተወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት በኮርፖሬሽኑ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከጥር 3/2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ የካቲት 6/2015 ዓ.ም. ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ባሉት 28 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ በአካል በመቅረብና የማይመለስ ብር 400 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ተብሏል። የት ነው የጨረታው ሰንድ የሚገዛው ? - አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ - ሰንጋ ተራ 40/60 ቤቶች ብሎክ 4 - የካ ክ/ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ - የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን 4ኛ ፎቅ - 40/60 ቦሌ ቡልቡላ ቅርንጫፍ 1 ጽ/ቤት - 40/60 አያት 49 ማዞርያ ብሎክ 21 ቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት የጨረታ ሳጥን የካቲት 6/2015 ከቀኑ 11 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ የካቲት7/2015 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራጮች በተገኙበት ይከፈታል ተብሏል። ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ እንደሚያገኙም ከኮርፖሬሽኑ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
Показать все...
Фото недоступно
መልካም የገና በዓል! Ayyaana Qillee Gaarii! ርሑስ በዓል ልደት!
Показать все...
#Update " የፈተናውን ውጤት በአጭር ጊዜ እናሳውቃለን " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አሳውቋል። አገልግሎቱ ፤ ይህ የፈተና ሥራ በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ አወንታዊ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምስጋና ያቀረበ ሲሆን ለተፈታኞች ደግሞ መልካም ውጤት ተመኝቷል። " በአጭር ጊዜ ውስጥ የፈተናውን ውጤት የምናሳውቅ ይሆናል " ያለው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ተፈታኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት አስተላልፏል።
Показать все...
Фото недоступно
#ታህሳስ19 የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በቁልቢ እና በሐዋሳ እጅግ ከፍተኛ ምዕመን በተገኘበት በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል። በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የንግስ በዓሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው። ቅዱስነታቸው እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በደረሱበት ወቅት እጅግ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ወደ ቁልቢ እና ሀዋሳ ለዚሁ የንግስ በዓል ያመሩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት እንደገለፁት ከሆነ የበዓሉ ታዳሚ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መሆኑንና በዓሉ በሰላም እየተከበረ ስለመሆኑን አመልክተዋል። Photo Credit : የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት Social Media /
Показать все...
Фото недоступно
ፎቶ ፦ ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በትግራይ መዲና መቐለ ዛሬ ታህሳስ 19 ቀን 2015 ዓ/ም " እንኳዕ ንዓመታዊ ክብረ በዓል ቁዱስ ገብሪኤል ኣብፀሓኩም እንዳ ገብሪኤል መቐለ። ሎሚ ታሕሳስ 19, 2015 ዓ.ም " Credit : ቢንያም ግርማይ
Показать все...
Фото недоступно
" ... አንድ ተማሪ ከነልጇ ህይወታቸው አልፏል " - የቤኒሻንጉል  ጉሙዝ ትምህርት ቢሮ የ2ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ወደሚፈተኑበት ተቋም እየገቡ እንደሆነ ይታወቃል። ዛሬ ከወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል። በ2ኛ ዙር ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመፈተን ከሚዢጋ ወረዳ ወደ አሶሳ ሲመጡ በነበሩ ተማሪዎች ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሶ ነበር። ከክልሉ ትምህርት ቢሮ በተገኘ መረጀ በደረሰው የተሸከርካሪ አደጋ ፤ አንድ ተማሪ ከልጇ ጋር ሕይወታቸው አልፏል። በአምስት ተማሪዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ ምንጭ፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የማህበራዊ ትስስር ገፅ
Показать все...
Фото недоступно
ወሎ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞችን እየተቀበለ ነው። ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ1 ሺህ 900 በላይ የሚሆኑ የሁለተኛ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች ተመድበውለታል። ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ 21/2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።
Показать все...
Фото недоступно
ከውሸት ዜናዎች ተጠንቀቁ። በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በህይወት በነበረበት ሰዓት የዓይን ብሌኑን ለመለገስ ቃል በገባው መሰረት የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ የአርቲስቱን ቃል ተፈፃሚ ማድረጉ አይዘነጋም። ነገር ግን ከአርቲስት ታሪኩ ጋር በተያያዘ በዩትዩብ እና በሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች ሀሰተኛ ዜናዎች እና መልዕክቶች እየተሰራጩ መሆኑን የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ አሳውቋል። የዓይን ባንኩ " የታዋቂው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ዓይን ለመጋቢ ሃድስ እሸቱ አለማየሁ ተሠጠ " ተብሎ በዩትዩብ የሚተላለፈው ዜና የወሸት ዜና መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪ የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ተደርጎላቸው " ኪድ ኢትዮጵያ " በተሰኘ ዩትዩብ ላይ ቀርበው ቃለመጠይቅ ያደረጉ ታሪኩ ሁሴን እና ሜላት ተሰማ የተባሉ ታካሚዎች ጣቢያው ላይ ካደረጉት ቃለ መጠይቅ አውድ ውጭ በመውሰድ " የአርቲስት ታሪኩ የዓይን ብሌን የተሰጣቸው " እያሉ የተለያዩ ዩቱበሮች እና የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚወች ቻናሉ ላይ ያልተላለፈውን መልእክት እያሰራጩ መሆኑን የዓይን ባንክ ገልጿል። ወጣቶቹ ከተሰራላቸው ከአንድ አመት በላይ  እንደሆናቸው የገለፀው ባንኩ " እነሱም የሱ የተሰራልን ነን " ብለው ምንም አይነት መልዕክት አላስተላለፉም ብሏል።  የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ ፤ የተለገሱ የዓይን ብሌኖች የሚነሱት በኮድ ስለሆነ የማን ለማን እንደተሰራ አይታወቅም ሲልም አሳውቋል።
Показать все...
Фото недоступно
#እንድታውቁት ስለ ዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ፦ (የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ) - የዓይን ባንኩ ንቅለ ተከላ የተደረገላቸው ሰዎች የማን እንደተሰራላቸው አያሳውቅም፤ - ባንኩ አስፈላጊውን ፍተሸ በማድረግ ለንቅለ ተከላ ማዕከላት ያሰራጫል፤ - የዓይን ባንኩ የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና ከሚሰሩ ተቋማት ጋር ይሰራል፤ - የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና የሚሰጠው የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ የሚሰራበቸው ማዕከላት ውስጥ ብቻ ነው እነዚህም ፦ 👉 ዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕርሄንሲቭ ሪፈራል ሆሰፒታል 👉 ቅ.ጳውሎስ ሚሊኔም ኮሌጅ 👉 ጎንደር ስፔሻላይዝድ ማስተማሪያ ሆስፒታል 👉 ጅማ ስፔሻይዝድ ማስተማሪያ ሆስፒታል 👉 ሐዋሳ ስፔሻላይዝድ ማስተማሪያ ሆስፒታል ናቸው። በተጨማሪም አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የግል የዓይን ህክምና ጣቢያወች መካከል ፦ 👉 ብሩህ ቪዢን ልዩ የዓይን ክሊኒክ 👉 ዋጋ ቪዥን ልዩ የዓይን ክሊኒክ 👉 አልአሚን የዓይን ህክምና ማዕከል 👉 ላቪስታ ስፔሻሊስት የዓይን ክልኒክ ናቸው። የኢትዮጵያ ዓይን ባንክን በምን ላግኛቸው ? አድራሻ ፦ ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ስልክ ፦ 0111223838 0930006367 0930006368 Email [email protected] #የኢትዮጵያ_ዓይን_ባንክ @
Показать все...
Фото недоступно
" በነዚህ ወጣቶች ያለጊዜ ሕልፈት የተሰማኝን ሐዘን ገልፃለሁ "  - ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ከትላንት በስቲያ ታህሳስ 10 /2015 በመዲናችን አዲስ አበባ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኛ አብራው የምትኖረውን እጮኛውን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለ በኃላ እራሱን ከ13ኛ ፎቶ ወርውሮ (መገናኛ አምቼ ፊት ለፊት ባለዉ የፌደራል ዳኞች መኖሪያ ጊቢ) ህይወቱን ማጥፋቱ በርካቶችን አሳዝኗል የመዲናይቱም መነጋገሪያ ሆኗል። ዳኛው ትንሳኤ በላነህ የሚባል ሲሆን በዕለቱ እራሱን ከ13 ፎቅ ላይ ወርውሮ ከማጥፋቱ በፊት አብራዉ የምትኖረዉን እጮኛውን ህይወት አጥፍቷል። ህይወቱ ከማለፉ ከሰዓታት በፊትም በ " ፌስቡክ ገፁ " ላይ ፅፎታል የተባለ አንድ መልዕክትም በማህበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ የብዙሃን መነጋገሪያ ሆኗል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕ/ት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ፤ ክስተቱ በጣም አሳዛኝ መሆኑን ገልፀዋል። " ባልተጠበቀ ሁኔታ እጮኛቸውን በመግደል ራሳቸውን ያጠፉት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኛ ተንሳይ በላይነህ ሞት በጣም አሳዛኝ ነው " ያሉት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ፤ " ዳኛው #መደበኛ_ያልሆነ ጠባይ ያሳዩ እንደነበረ ይህ ሁኔታ ከተከሰተ በኃላ ተጠቁሟል " ሲሉ ገልፀዋል። " የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት መደበኛ ሥራ መሥራት የሚችሉ ሰዎች ሥራቸውን እያከናወኑ አንዳንድ ጊዜ የአእምሮ ጤንነት ችግር ሊኖርባቸው ይችላል ፤ " ያሉት የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዜዳንቷ " እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ሲታዩ እገዛ ሊያደርግ ለሚችል ክፍል ማሳወቅ አስፈላጊ ነው " ብለዋል። በወጣቶቹ ያለጊዜ ሕልፈት ሐዘን እንደተሰማቸው የገለፁት ወ/ሮ መዓዛ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል። @t
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.