cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Kolfe P.P - ብልፅግና

Больше
Рекламные посты
2 347
Подписчики
Нет данных24 часа
-127 дней
-2630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
አረንጓዴ አሻራ የኢትዮጵያ ህዝብ ለችግሮች በቀላሉ እጅ የማይሰጥና ጠንካራ መሆኑን ማሳያ ነው !! ኢትዮጵያ የበለፀገ ታሪክ፣ ባህልና ብዝሃነት ያላቸው ህዝቦች በጋራ የሚኖሩባት ሀገር ናት። እንደ ሀገር ድህነት፣ ድርቅ፣ ግጭትና የአየር ንብረት ለውጥ የመሳሰሉ ብዙ ፈተናዎች ገጥመዋታል። የሀገራችን ግብርና የኢኮኖሚው ዋና ምሶሶ ቢሆንም በዝናብ የዝናብ፣ የውሃ ሃብት እና የተፈጥሮ ስነ-ምህዳር ላይ ከፍተኛ ጥገኛ በመሆኑ ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ እጅግ ተጋላጭ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ የኢትዮጵያን የልማት ግቦች ፈተና ላይ የሚጥል እና የሚሊዮን ህዝብ መተዳደሪያ የሆነውን ግብርና አደጋ ላይ የሚጥል ነው። ኢትዮጵያ ግን በቀላሉ ተስፋ የምትቆርጥ ሀገር አይደለችም። እድገቷንና ብልፅግናዋን ለመጪዎቹ ትውልዶች ማስቀጠል የሚችል ለአየር ንብረት ለውጥ ተመራጭ የሆነ አረንጓዴ ኢኮኖሚን የመገንባት ራዕይ ያላት ሀገር ናት። የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ እና ለማላመድ፣ የተራቆተ አካባቢውን ወደነበረበት ለመመለስ እና የተፈጥሮ ካፒታልን ለማሳደግ ደፋርና ትልቅ እርምጃ የወሰደች ሀገር ናት። መልካም እለተ ሰኞ ተመኘን #kolfe_prospertiy_party- ብልፅግና #kolfepp
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የብልጽግና ተምሳሌት የሆነች እንደ ስሟ አዲስ እና አበባ ከተማ በመገንባት ቃል በተግባር እንፈፅማለን !! አዲስ አበባን እንደ እንደ ስሟ አዲስ እና አበባ የማድረግ ስራው በአመራሮቻችን ቁርጠኝነት እና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ 7/24 መርህ አድርጎ በመስራት የኢትዮጵያን ብልፅግና አይቀሬነት የታየበት ከመሆኑም በላይ የስራ ባህልን ከአስተሳሰብ ጀምሮ የቀየርንበትም ነው ። የአዲስ አበባ ስሟን የሚመጥን የቱሪዝም መዳረሻ እና በአለም ተወዳዳሪ ከተማ በማድረግ በአለም ላይ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ የማድረግ ስራ በፓርቲያችን ራዕይ በመነሳት ከተማ እና የከተማ ልማትን በማፋጠን እና ከተሜነትን ማስፋፋት መሰረት ያደረገ ነው ። የኮሊደር ልማት ቃል በተግባር የመፈጸም በተግባር የታየበት ኘሮጀክትን በጥራት እና ፍጥነት ጊዜ መፈጸም የተቻለበት ነው። ይህን ተግባር በሁሉም መስክ አጠናክሮ በመቀጠል የኢትዮጵያን ሁለተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ ይገባል ። መልካም ቀን ይሁንለዎ! #Kolfe_Prosperity_Party- ብልፅግና #kolfepp
Показать все...
👍 2
የረዳን ፈጣሪ ክብርና ምስጋና ይሁንለት! "በጎነት"ብለን በሰየምነው የመኖሪያ መንደር የተገነቡ ሁለት ባለ 9 ወለል ዘመናዊ ሕንጻዎችን እና የስራ ዕድል መፍጠሪያ ማዕከላትን መርቀን ለ140 አቅመ ደካሞች እና አካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች አስተላልፈናል። በልደታ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቆርቆሮ ሰፈር በሚባለው የተጎሳቆለ የመኖሪያ መንደር ይኖሩ ለነበሩ አቅመ ደካሞች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ማየት ለተሳናቸው፣ ለተለያየ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ እና በልማት ለተነሱ ነዋሪዎች ያስተላለፍናቸው ምቹ የመኖሪያ ቤቶች ሳሎን፣ መኝታ ቤት፣ የማብሰያ እና የመጸዳጃ እንዲሁም የመኝታ ክፍሎች ያላቸው ዘመናዊ ቤቶች ናቸው። በዚህ የበጎነት መንደር ካስተላለፍናቸው የመኖሪያ ቤቶች ጋር በማቀናጀት የእናቶችን ጫና የሚያቀል የህጻናት ማቆያ፣ ለአካባቢው እናቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር ዘመናዊ የእንጀራ መጋገሪያ፣ የሚሰሩ እጆችን ከስራ የሚያገናኙ የወንዶችና የሴቶች የውበት ሳሎኖችን እንዲሁም የልብስ ስፌት ማሽኖችን አዘጋጅተን ለነዋሪዎቹ የስራ እድል ፈጥረናል። በመኖሪያ መንደሩ ቤት ለሰጠናቸው ማየት የተሳናቸው ነዋሪዎች እንቅስቃሴ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ኬኖች፣ ለአካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች ደግሞ ክራንችና ዊልቸሮችን አዳርሰናል። ሰርቶ ካገኘው ላይ ለወገን በጎ ለመስራት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመተባበር ቤቶቹን የገነባውን ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በራሴና በነዋሪዎቹ ስም እያመሰገንኩ፣ በጎነት አያጎድልምና ፈጣሪ ጨምሮ እንዲሰጠው እመኛለሁ። የሚሰሩ ልማቶች ሁሉ ለሰው ልጆች ተስፋ የሚሰጡ እና የኑሮ ጫናን የሚያቃልሉ ይሆኑ ዘንድ ሰው ተኮርነታችን በተግባር የሚገለጽ ነው። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Показать все...
በክፍለ ከተማው የስልጤ ልማት ማህበር (ስልማ) አመታዊ ኮንፈረንስ በአሁኑ ሰዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል። በኮንፈረንሱ አቶ አሊ ከድር የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የስልማ ልማት ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ፣የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንገቱ ዳኛቸው ፤የኢትዮጵያ ኢንተር ፖራይዞች ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አብዱልፈታ የሱፍ፤የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሃላፊ እንዲሁም የክፍለ ከተማው ስልማ ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ ኢብራሂም መሀመድ፣የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የልማት ማህበሩ አባላት እና የክብር እንግዶች ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው። በሸወ ከተመ በኮልፌ ጎ/ከተመ የስልጤ ላቶ ሴረ /ስልመ/ አይደኜ ኮንፈረንስ በትረሶት ደር ኢትረከባን። የዲን አቦትቸ የፌድራል፣የከተመ አትንዳዳሪ ዋ የጎ/ከተማይ ጎትለኜ ዋሻሾ ፣የባድ ባሊቅቸ ፣የላቶ ሴራይ ቆራርቸ ዋ የማልነግዳዶ ዋ ሉላ ሉሌ የፌሩይ አመሠብ በትረከበቢ ኤት ባውጄ አያም ኢትሀበዳን።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ባለፉት ጥቂት አመታት ዋናውን የዝናብ ወቅት ምርት ሳናስተጓጉል የበጋ ስንዴ ልማት ጥረታችንን ለማስፋፋት ችለናል። የዛሬው ምልከታ የስራዎችን ቀጣይነት የተመለከትንበት ነበር። ግብርና ጠንካራ ኢንቨስትመንት ይፈልጋል። በሰብል የምንሸፍነው የመሬታችን ይዞታም ቀስ በቀስ በመጨመር ላይ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር) #prosperity #aa_prosperity #aappaddis
Показать все...
👍 2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንግግሮችና መልዕክቶች የያዘና ከ''መስከረም እስከ መስከረም'' የተሰኘ  መጽሃፍ  ለንባብ በቃ። መጽሃፉ ላይም ሙያዊ ውይይት በወዳጅነት ፓርክ  ተካሂዷል። በመደረኩም ተማሪዎች ከመጽህፉ የተመረጡ ገጾችን ለውይይት መነሻ ሃሳብ እንዲሆኑ በንባብ ያቀረቡ ሲሆን፣ በተለያዩ የስራ መስኮች የተሰማሩ ተሳታፊዎችም በመጽሃፉ የተሰነዱ መልዕክቶች ላይ ሙያዊ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። መጽሃፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ አገር አቀፍ ሁነቶች፣  ዓለም አቀፉ ጉባኤዎችና በዓላት  ላይ ያስተላለፏቸውን 91 መልክቶችና ንግግሮች ያያዘ ነው።
Показать все...
👍 1
Перейти в архив постов
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.