cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

መዝሙር ግጥሞች ቤት

ይህ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የምንማማርበት Channel ነው !  ወደ ቻናላችን በመቀላቀል 👇 ➲ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መፅሐፍትን በPDF ➲ስንክሳር ትምህርቶች ➲ መዝሙራትን በግጥሞች ➲ ኪነ-ጥበብ ➲ ጥያቄዎችን በሐይማኖት ብትኖሩ እራሳችሁን መርምሩ"   ( 2ኛቆሮ -13 ፥ 5)👇 Group ገጽ👇👇 https://t.me/Orthodoxs_Tewahdo_menfeswi_group

Больше
Рекламные посты
17 033
Подписчики
+2824 часа
+5397 дней
+2 65030 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
2
Фото недоступноПоказать в Telegram
🕊  💖  ▬▬    †    ▬▬  💖  🕊 [ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [   ❝  ከአንቺ ግን .... !  ❞  ] 🕊 ❝ እግዚአብሔር ዐሥሩን ቃላት በእጁ የጻፈባቸውን ሁለቱን ጽላት በደብረ ሲና ሰጠ ከአንቺም እግዚአብሔር ቅዱስ ጽላትን ፈጠረ ይኸውም ሥጋው ነው። [ዘፀአ.፴፬፥፳፰-፴] ከደብረ ሲና እሳት ጨለማ መጣ ፤ ከአንቺ ግን ሰው የሆነ አምላክ ተገኘልን፡፡ በደብረ ሲና በአይሁድ ላይ ድንጋፄ ሀውክ ተደረገ ፤ በአንቺም በአይሁድ በሄሮድስ በዲያብሎስና በሠራዊቱ ላይ ጽኑ ድንጋፄ ተደረገ፡፡ [ዘፀአ.፳፥፲፰ ፡፡ ዕብ.፲፪፥፲፱]  ❞ [      ቅዱስ ኤፍሬም      ] ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን። †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
Показать все...
🥰 1
[ + ቸሩ ሆይ + ] .mp34.67 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
💛 🕊     ቅ ዱ ስ አ ማ ኑ ኤ ል     🕊 ❝ ሰላም ለአስተርእዮቱ በሥጋ ዘአስተርአየ ገሃድ ከመ የሀበነ ጸጋ ❞ [  በግልጽ ጸጋን ያድለን ዘንድ በሥጋ የተገለጠ ለኾነ ለእርሱ አገላለጥ ሰላምታ ይገባል ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ❝ ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል ፤ እነሆ ፥ ድንግል ትፀንሳለች ፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች ፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ❞ [ ኢሳ.፯፥፲፬ ] " Therefore the Lord himself shall give you a sign; Behold, a virgin shall conceive, and bear a son, and shall call his name Immanuel." [ Isaiah 7:14 ] 🕊                        💖                     🕊                              👇
Показать все...
✥●ከ4'ቱ ወንጌላውያን ዘግየት ብሎ የፃፈው ማን ነው ? መልስ ለማግኘት 👇👇👇 https://t.me/addlist/gpX29GzfGs43MWE0
Показать все...
ሀ.ማቴዎስ
ለ. ማርቆስ
ሐ. ሉቃስ
መ. ዮሀንስ
🕊 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ:: አሜን:: 🕊   †  ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ [ እል-በረዳይ ] [ St. Jacob baradaeus ]  †   🕊 [ በተለይ በሃገራችን የተዘነጋ የሚመስለው የምሥራቅ ኮከብ - ኮከበ ጽባሕ ] 🕊 "ያዕቆብ" ለሚል ስም ትርጉምን የሰጡ አበው በ2 መንገድ ያትቱታል:: ፩. አኃዜ ሰኮና:: ነገሩ ከወልደ ይስሐቅ ወርብቃው ርዕሰ አበው ያዕቆብ ጋር የተያያዘ ቢሆንም አበው ግን ለትህትና ይተረጉሙታል:: ፪. አእቃጺ / አሰናካይ:: ነገሩ ስድብ [ አሉታዊ ] ይምሰል እንጂ በዚህ ስም የተጠሩ አበው ሁሉ ለአጋንንትና ለመናፍቃን ትልቅ መሰናክል ሆነውባቸው ኑረዋልና አባባሉ ምስጋና እንጂ ነቀፋን አይወክልም:: የ፮ኛው መቶ ክ/ዘመን ምሥራቃዊ ኮከብ ቅዱስ ያዕቆብም ለመለካዊ መናፍቃንና ለተዋሕዶ ተገዳዳሪዎች ትልቅ መሰናክል ሆኖባቸዋል:: የቀናችውን ቀርነ ሃይማኖትንም አጽንቷል:: ብዙ ጊዜ "ዘ" - እልበረዲ መባሉን ይዘው በ"ዘ" ምክንያት እልበረዲን እንደ ሃገር የቆጠሯት አልጠፉም:: በረከታቸው ይድረሰንና ትጉሑ ዻዻስ አቡነ ጐርጐርዮስ ካልዕ ግን ለዚሁ መላምት "የለም!" ባይ ናቸው:: 'የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ' በተሰኝ ተወዳጅ መጽሐፋቸው "እል-በረዲ" ማለትን በዓረብኛ ከሠጋር በቅሎ : ከሥሙር ሠረገላ ጋር አነጻጽረው አስቀምጠውታል:: ለምን ቢባል - እንደ ሠረገላ በተፋጠነ አገልግሎቱ ወዳጅንም ጠላትንም አስደምሟልና:: +ቅዱስ ያዕቆብ የተወለደው በ፮ኛው መቶ ክ ዘመን መጀመሪያ [ በ፭፻ አካባቢ ] ሲሆን ያረፈው ደግሞ በ፭፻፸፰ ዓ/ም እንደሆነ ይታመናል:: ነገሩን ልብ ስንለው ቅዱስ ማኅሌታይ ያሬድን - ወዲህ በዘመን : ወዲያ ደግሞ በአገልግሎት ይመስለዋል:: እርግጥ ነው ለውለታው የሶርያ ቤተ ክርስቲያን "ያዕቆባዊት" ስትባል የእኛዋስ ምናለ "ያሬዳዊት" ብትባል የሚል ቁጭትን ያመጣል:: + ጊዜው [ ፭ኛውና ፮ኛው መቶ ክ/ዘመን] ወዲህ ወርቃማ : ወዲያ ደግሞ ጨለማ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ዘመን ነበር:: ¤ በብርሃንነቱ በተለይ በምሥራቁ ዓለም ያበሩ አበው እነ ያዕቆብ ዘስሩግ : ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ : ያዕቆብ ዘእልበረዲን የመሰሉ አበው ተገኝተውበታል:: ሲያልፍ ደግሞ ዘይኑንና አንስጣስዮስን የመሰሉ ደጋግ ነገሥታት በዘመኑ መነሳታቸውን እናስባለን:: + በተቃራኒው ግን ዘመኑ ቤተ ክርስቲያን ለ፪ የተከፈለችበት : መለካውያን የነገሥታቱ ደጀን አላቸውና ተዋሕዶ ሃይማኖትን ከሥሯ ነቅሎ ለማጥፋት ብዙ የሞከሩበት ዘመን ነውና ጨለማነቱ ይጐላብናል:: + በእርግጥም ከመርቅያን እስከ ዮስጢኖስ ዳግማዊ ዘመን ድረስ ለ፻ ዓመታት መለካውያኑ የልዮን ልጆች ፪ ባሕርይ ማለትን ሊያሰፉ : ተዋሕዶንም ሊያጠፉ የከፈቱት ዘመቻ ሊሳካ ጫፍ የደረሰ ይመስል ነበር:: + ግን አማናዊት ቤቱን የማይተው አማናዊው ጌታ መድኃኔ ዓለም አርመኖቹን ስቦ በ፬፻፺ዎቹ ወደ መንጋው ቀላቀለ:: በግብጽ አባ ቴዎዶስዮስን : በሶርያ ደግሞ ታላቁን ሊቅ ቅዱስ ሳዊሮስን አስነስቷል:: ከቤተ መንግስትም ስም አጠራሯ ያማረ ንግሥት ታኦድራን ማርኯል:: በእነዚህ ቅዱሳን ትጋት የለመለመችው ተዋሕዶ እንደ ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ ያለ አርበኛን ግን ያገኘችው በጭንቅ ቀን ነበር:: + ሰው መሆን ሰው በጠፋባቸው ቀናት ነውና : በግብጽና በቁስጥንጥንያ በትምህርትና ምናኔ ላይ የነበረው ቅዱሱ ታጥቆ ለአገልግሎት የተሰለፈው በ፭፻፴ዎቹ አካባቢ ነበር:: + ጊዜው ወዲህ አንበሳው ቅዱስ ሳዊሮስ ከሶርያ ወደ ግብጽ እንደተሰደደ ያረፈበት ነበር:: ወዲያ ደግሞ ሊቁ አባ ቴዎዶስዮስ የግብጹ ለግዞት የተዳረገበት ነበርና የተዋሕዶ ምዕመናን ያለ እረኛ ተቅበዘበዙ:: የቤተ መንግስቱ ተጽዕኖ ደግሞ ፪ ባሕርይ በማይሉት ላይ እሥራትና ግድያን ወደ ማወጅ ተሸጋግሯልና የምእመናን ቁጥር እጅጉን መመንመኑ ቀጠለ:: + ይህ ዕረፍት የነሳው ቅዱስ ያዕቆብ በበኩሉ ነገሩን በዝምታ ሊያልፈው አልወደደምና አገልግሎቱን አሰፋ:: ሌሊቱን በጸሎት ያድራል:: ቀን በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ማስተማር ባይችል በየቦታው እየዞረ ያስተምር ነበር:: + ከትምህርቱ ጣዕምና ከመልእክቱ ሥምረት የተነሳም ምእመናን እንደገና ተነቃቁ:: እርሱም ከግብጽ እስከ ሶርያ : አልፎም እስከ ቁስጥንጥንያ ድረስ ያለ ዕረፍት ሲሰብክ ፵ ዘመናትን አሳለፈ:: በተለይ አዲስ አማኞችን ያጠምቅ ዘንድ በእሥረኛው ቅዱስ ቴዎዳስዮስ ኤዺስ ቆዾስነትን ተቀብሏል:: + የሶርያ [ አንጾኪያ ] የፕትርክና መንበሩ ክፍት ሆኖ እርሱን ቢጠብቀውም እርሱ ግን የዚህ [ የስልጣን ] ፈላጊ አልነበረምና ሌሎች እንዲሾሙበት አድርጉዋል:: + ቅዱስ ያዕቆብ በስብከት አገልግሎት ምሥራቁን ዓለም ሲያበራ የተባበሩት ደቀ መዛሙርት ቢኖሩም ያሳለፈው ድካምና መከራ ግን ተወዳዳሪ አልነበረውም:: በተለይ የወቅቱ የአንጾኪያ ኃያላን መኩዋንንትና ሹመኛ መናፍቃን ብዙ አሳደውታል:: + እርሱ ግን በጥበብና በፈሊጥ እዚያው ደጃቸው ላይ የነበሩ ምዕመናንን በእረኝነት ጠብቁአል:: ለዚህ ሲባልም ራሱን እየቀያየረ የመሣፍንቱን አጥሮችና ቅጥሮች አልፏል:: ለቤተ ክርስቲያን ክብርም እንደ እብድ : እንደ ሴትም መስሎ የወንጌልን ዘር ዘርቷል:: ¤ ከብዙ ፈተናና አገልግሎት በሁዋላም በተወለደ በ፸፰ ዓመቱ [ በ፭፻፸፰ ዓ/ም ] ዐርፎ በክብር ተቀብሯል:: ¤ ትልቁ መታሰቢያው የሶርያ ቤተ ክርስቲያን "ያዕቆባዊት" : ምዕመኑ "ያዕቆባውያን" መባላቸው ሲሆን እኛ ደግሞ በአንገታችን ላይ እንድናስራት ባስተማረን ማዕተብ [ ማኅተም ] ዘወትር እናስበዋለን:: ለመጀመሪያ ጊዜ ማዕተብን በአንገት ላይ ስለ ማሰር ያስተማረ እርሱ ነውና:: ¤ የምሥራቁን ኮከብ እል-በረዲ ያዕቆብን በየዓመቱ ሰኔ ፳፰ ቀን በነገረ ቅዱሳን መደበኛ ጉባኤ [ ጐንደር ] እናከብራለን:: ሶርያውያን ደግሞ July 31 [ ሐምሌ ፳፬ ቀን ] ያከብሩታል:: " እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: " [ ማቴ. ፭ ፥ ፲፫ - ፲፮ ] አምላከ ቅዱስ ያዕቆብ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን:: ከቅዱሱ በረከትም አይለየን:: † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.