cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Ethio Facts 🇪🇹 ኢትዮ ፋክት️

ኢትዮጵያ ትቅደም Walk a mile in my shoes, Then you will know how I feel.

Больше
Рекламные посты
380
Подписчики
-124 часа
+67 дней
+4430 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

" ... ኢትዮጵያ ጎረቤታችን ናት፤ ከእነሱ ጋር ቢዝነስ መስራት እንፈልጋለን " - ሰኢድ ሀሰን አቡዱለሂ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች / #UAE / ንብረት የሆነው ' ዲፒ ወርልድ ኩባንያ ' የሚያስተዳድረው የበርበራ ወደብ የኢትዮጵያን 30 በመቶ ጭነት እንዲያስተናግድ የሶማሌላንድ ባለስልጣናት ማቀዳቸው ተሰምቷል። ለዚህ የወደብ አጠቃቀምና የጉምሩክ ሥርዓቶችን የተመለከተ ስምምነት በኢትዮጵያና ሶማሌላንድ መካከል መፈረም አለበት። ስምምነቱ ወደ መጨረሻውው ምዕራፍ መድረሱንና በሚቀጥሉት 60 ቀናት ተጠናቆ ሊፈረም እንደሚችል የሶማሌላንድ የወደቦች አስተዳደር አሳውቋል። የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሰኢድ ሀሰን አቡዱለሂ ፥ " ኢትዮጵያ ጎረቤታችን ናት፤ ከእነሱ ጋር ቢዝነስ መስራት እንፈልጋለን በአሁን ወቅት የወደብ አጠቃቀም ስምምነት ወይም Transit Agreement እያዘጋጀን ነው። አንዴ ስምምነቱን ከተፈራረምን በመጀመሪያው ዓመት ከኢትዮጵያ ጭነት 30% እናስተናግዳለን " ብለዋል። ይህን በተመለከተ " ስምምነቱ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸው በአንድ ወይም ሁለት ቀሪ ጉዳዮች ላይ እየተወያየን ነው ምናልባት በመጪዎቹ 60 ቀናት ሊጠናቀቅ ይችላል ከ60 ቀናት በኃላ እንፈራረማለን " ሲሉ ተደምጠዋል። ከወራት በፊት እ.አ.አ ጥር 1 ላይ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት (MoU) በተመሳሳይ ወደ ተግባር የሚገባበት የመጨረሻው ስምምነት በ2 ወራት ገደማ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሌላንድ ባለስልጣናት ገልጸዋል። መግባቢያ ምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ውይይቶች ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን የቴክኒክ ኮሚቴዎችም መታጨታቸውን ተናግረዋል። ይህ የመግባቢያ ስምምነት ወደ #መጨረሻው ደርሶ ወደ ተግባር ከገባ ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ የባህር ዳርቻ የጦር ሰፈር በሊዝ ኪራይ የምታገኝ ሲሆን ሶማሌላንድ በበኩሏ ለረጅም አመታት ስትፈልገው የነበረውን እውቃና የማግኘት እድል እንደሚፈጥርላት ባለስልጣናቱ አመልክተዋል። ለንግድ ስራ ሌላ ወደብ መገንባት ሳያስፈልግ የበርበራ ወደብን ኢትዮጵያ እንደምትጠቀምበት ገልጸዋል።
Показать все...
"በትግራይ ክልል ከሕዝቡ በማፈንገጥ በጠብ-መንጃ አፈሙዝ ችግራቸውን ለመፍታት የጦረኝነት አስተሳሰብ የሚያራምዱ ሃይሎች የሰላም ዕድሉን እንዲጠቀሙ ትጥቅ እንዲፈቱ የትግራይ ሕዝብ ተው ሊላቸው ሊመክራቸውም ይገባል። የሰላም ዕድሉን ከመጠቀም ይልቅ የጦርነት መንገድን መርጠው የሚገፉበት ከሆነ ግን መንግስት ሕግ ማስከር ቀዳሚ ስራው ነውና ሕግ ለማስከበር ይገደዳል።" ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Показать все...
👍 3
ሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ በሁለት ወራት ገደማ የመጨረሻውን ሥምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል! ለሶማሌላንድ እውቅና ለኢትዮጵያ የባሕር ኃይል የጦር ሠፈር በኪራይ የሚሰጠው ሥምምነት በሁለት ወራት ገደማ ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ለባሕር ኃይል የጦር ሠፈር ልትከራይ የምትችላቸው ሦስት አማራጭ ቦታዎች መለየታቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የሶማሌላንድ ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ዲፕሎማቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝደንት ሙሴ ቢአብዲ የተፈራረሙት “የአጋርነት እና የትብብር የመግባቢያ ሥምምነት” በመጪዎቹ ወራት ወደ ተግባር ይሸጋገራል ብለው እየጠበቁ ነው። የመግባቢያ ሥምምነቱ ከአራት ወራት በፊት ታህሳስ 22 ቀን 2016 ሲፈረም ድርድሩ በአንድ ወር ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ መንግሥት በወቅቱ አስታውቆ ነበር። የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ የመግባቢያ ሥምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ውይይቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን እና የቴክኒክ ኮሚቴዎች መታጨታቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። “ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ ነበር” ያሉት ዶክተር ኢሳ ካይድ በረመዳን የጾም ወር ወቅት ሒደቱ ቢቀዛቀዝም በመጪዎቹ ወራት ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ሥምምነቱን ወደ ተግባር የሚያሸጋግር የመጨረሻውን ሥምምነት ሊፈራረሙ እንደሚችሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። “ሁሉም ነገር ሁለቱ ቡድኖች በሥምምነቱ ላይ ለመደራደር ሲገናኙ ይወሰናል” ያሉት ዶክተር ኢሳ “የሕግ እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች አሉ። በመጪዎቹ ወራት ምን አልባትም በሁለት ወራት ገደማ ይጠናቀቃል ብዬ አስባለሁ” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። የሶማሌላንድ የፋይናንስ ሚኒስትር ሳዓድ አሊ ሽሬ ሥምምነቱ ተፈርሞ “ዕውቅና ስናገኝ በዓለም አቀፍ መድረክ ድምጽ ስለሚኖረን በፖለቲካ ረገድ ጠቃሚ ነው” ሲሉ ተስፋቸውን ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል። ሶማሌላንድ የምታገኘው ዕውቅና “ለኢንቨስትመንት፣ ለንግድ፣ ለጉዞ እና በዕድገት በር ስለሚከፍት በኤኮኖሚ ረገድ ጠቃሚ ይሆናል” የሚሉት የፋይናንስ ሚኒስትሩ ሶማሌላንድ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ሥርዓት እንድትተሳሰር ይረዳታል የሚል ተስፋ ሰንቀዋል። “ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ መበደር እንችላለን” ሲሉ የተናገሩት ዶክተር ሳዓድ አሊ “በዕውቅናው ምክንያት እጅግ በርካታ በሮች” ለሶማሌላንድ እንደሚከፈቱ ይጠብቃሉ። ሥምምነቱ ከተፈረመ ሶማሌላንድ ዕውቅና ስታገኝ ኢትዮጵያ የባሕር ኃይል የጦር ሠፈር የምታቋቁምበትን ወደብ በኪራይ ታገኛለች። ሶማሌላንድ 850 ኪሎ ሜትር ገደማ በሚረዝመው የባሕር ዳርቻ ኢትዮጵያ ልትከራይ የምትችልባቸውን ሦስት ቦታዎች በአማራጭነት መለየታቸውን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ አረጋግጠዋል። “የለየናቸው የተወሰኑ ቦታዎች አሉ። ከኢትዮጵያ አቻዎቻችን ጋር ከተገናኘን በኋላ አንዱ ይመረጣል” ያሉት የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተለዩትን ሦስት ቦታዎች ስሞች ከመናገር ተቆጥበዋል። ኢትዮጵያ የደርግ ሥርዓተ መንግሥት ወድቆ ኤርትራ ነጻነቷን ስታውጅ የፈረሰውን የባሕር ኃይል መልሳ ያቋቋመችው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በፈረንሳይ እና የቀድሞ የባሕር ኃይል መኮንኖች ድጋፍ የባሕር ኃይሉን በአዋጅ መልሶ ያቋቋመው በ2011 ነበር።
Показать все...
👍 1
ቡርኪናፋሶ ቢቢሲ እና ቪኦኤን ጨምሮ ከሰባት በላይ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን አገደች። ምዕራብ አፍሪካዊቷ ቡርኪናፋሶ ከሰባት በላይ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን አግዳለች። ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ሂውማን ራይትስ ዋች የቡርኪና ፋሶ ጦር 50 ህጻናትን ጨምሮ 223 ንጹሀንን ገድሏል ሲል ሪፖርት አውጥቷል። ይህንን ሪፖርት መነሻ በማድረግም በቡርኪና ፋሶ ያሉ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዋቢ አድርገው ዘገባ የሰሩ ሲሆን የሀገሪቱ መንግስትም እገዳ ጥሎባቸዋል፡፡ በቡርኪና ፋሶ መንግስት እገዳ ከተጣለባቸው ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች መካከልም ቪኦኤ፣ ቢቢሲ፣ ለሞንዴ፣ ዘ ጋርዲያን፣ ዶቸቪሌ፣ ቲቭ5 ሞንዴ ኦስት ፍራንስ፣ ኤፒ እና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በቡርኪና ወታደራዊ መንግስት እገዳ የተጣለባቸው ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እስካሁን በጉዳዩ ዙሪያ ያወጡት መግለጫ የለም፡፡ ማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪና ፋሶ የአጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ የቡርኪና ፋሶ መንግስት በሚዲያዎቹ ላይ እገዳ የጣለው የሀገሪቱን ጦር ስም አጠልሽታችኋል በሚል ሲሆን የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርትንም ውድቅ አድርጓል፡፡ በመፈንቅለ ስልጣን ስልጣን የተቆጣጠረው የወቅቱ የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መንግስት ከምዕራባዊን ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት በየጊዜው በማቋረጥ ላይ ሲሆን እንደ ዓለም ባንክ እና አይኤምኤፍ ያሉ አበዳሪ ተቋማትም ግንኙነታቸውን አቋርጠዋል፡፡ አፍሪካ ህብረት እና የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ወይም ኢኮዋስ ቡርኪናፋሶን ጨምሮ መፈንቅለ መንግስት ያደረጉት ማሊ እና ኒጀርንም ከአባልነት ሲያግድ ሀገራቱ በምላሹ ከኢኮዋስ አባልነት መውጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡
Показать все...
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በሊባኖስ ቴል አቪቭ የሚለውን መለያ ቃል እንዲሸፍን ተገደደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ለእስራኤል እንደ ሀገር እውቅና ባልሰጠችው ሊባኖስ  ሀሙስ እለት በቤሩት አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በአውሮፕላኑ ላይ "ቴል አቪቭ" የሚለውን መለያ ቃል ለመሸፋፈን ተገዷል። ኤርፖርቱ የፀጥታ ጥበቃው ET-ኤኤክስኬ የሚል መለያ ቁጥር ያለው አውሮፕላኑን ቴል አቪቭን ማድረጉን የሊባኖስ የሲቪል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር ዘግቧል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኑን ከገዛ በኋላ ያረፈበትን የመጀመሪያ አውሮፕላን ማረፊያ ስም ማተም የተለመደ መሆኑን ገልጾ አውሮፕላኑ ራፊቅ አል ሃሪሪ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እስኪደርስ ድረስ ዝርዝሩን እንዳላስተዋለ ተሰምቷል። ሊባኖስ እና እስራኤል አሁን ላይ ጦርነት ውስጥ ይገኛሉ። ቤይሩት እና ሌሎች የሊባኖስ ከተሞች ላለፉት አስርት አመታት በእስራኤል ወረራ ስር ናቸው። ይህም የሊባኖስ አቪዬሽን ዳይሬክቶሬት ከቤሩት ከመነሳቱ በፊት የቴል አቪቭ ምልክት እንዲሸፍን እና አየር መንገዱ ከእስራኤል ጋር የተያያዙ አርማዎችን ወይም ህትመቶችን የያዙ  አውሮፕላኖች ዳግም ወደ ሊባኖስ እንዳይጠቀም አስጠንቅቋል። በጥቅምት 8 በሊባኖስ ቡድን ሂዝቦላህ እና እስራኤል መካከል ድንበር ዘለል ጦርነት ከጀመረ በኋላ እስራኤል በሊባኖስ ከተሞች እና መንደሮች ላይ ተከታታይ ጥቃት አድርሳለች። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል)ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3-5 ለማህበራዊ ሳይንስ ሐምሌ 9-11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል። በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። ስለሆነም ተፈታኞች እና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ተብሏል።
Показать все...
👍 1
የአውሮጳ ህብረት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች የሚሰጠውን ቪዛ ለመገደብ መወሰኑን አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግስት ህገ ወጥ ስደተኞችን ለመቀበል ከህብረቱ ጋር መተባበር ባለመቻሉ የቪዛ ገደብ እንዲጥል ምክንያት እንደሆነው የአውሮጳ ህብረት ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። የህብረቱ እርምጃ የተሰማው  በጦርነት ከተመሰቃቀሉ የአፍሪቃ ሃገራት በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካኝነት የሜድትራንያን ባህርን አቋርጠው የሚመጡትን ስደተኞች ለማስቆም ብርቱ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት ነው። በህገ ወጥ መንገድ ወደ ህብረቱ አባል ሃገራት የገቡ እና መመለስ ያለባቸውን ዜጎቿን እንድትቀበል በትብብር ለመስራት ሲደረግ የነበረውን ግምገማ ማጠናቀቁን  የገለጸው የአውሮፓ ህብረት በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ትብብር «በቂ አይደለም » ብሏል። የአውሮጳ ህግ አውጪዎች የተሻሻለውን የፍልሰት ስርዓት ባለፈው ወር መጨረሻ  ነበር ያጸደቁት ። የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ ማእከል እንዳለው የፍልሰት ስርዓት ማሻሻያው  ያለ ህጋዊ ሰነድ  ወደ ህብረቱ የሚገቡ የስደተኞችን ቁጥር ይቀንሳል።
Показать все...
አንድን ግለሰብ ኢ-ሰብአዊ በሆነ መልኩ በመደብደብ አስነዋሪ ተግባር የፈጸሙ አባላቱን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማጣራት ላይ መሆኑን የድሬዳዋ ፖሊስ ገለጸ፡፡ ሰሞኑን ሶስት የድሬ ዳዋ ፖሊስ አባላት አንድን ግለሰብ ከበው ኢ-ሰብአዊ በሆነ ሁኔታ የመደብድበ አና የማንገላታት ተግባር ሲፈፅሙ የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ሲንቀሳቀስ ተመልክተናል ሲል የድሬ ፖሊስ አመልክቷል። በዚህ አስነዋሪ ተግባር የድሬዳዋ ፖሊስ አመራር እና አባላት በእጅጉ ማዘኑንም መምሪያው ጠቁሟል።የተከሰተው አስነዋሪ ተግባር የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያን በፍጹም የማይወክል እና የማይገልጽ ተግባር በመሆኑ በጽኑ እናወግዛለን ብሏል። በመሆኑም ‹‹በጀግንነት መጠበቅ ፤በሰብዓዊነት ማገልገል›› የሚል መሪ ቃል አንግቦ ዜጎችን ከማንኛውም ጥቃት በጀግንነት ለመጠበቅ ሌት ተቀን የሚተጋው፤ ህይወቱን በጀግንነት ለመክፈል የቆረጠው ፤ የዜጎችን ሰብአዊ ክብር ጠብቆ ለማገለገል ቁርጠኛ አቋም ይዞ ወደ ስራ የገባው የድሬደዋ ፖሊስ ፤ የዜጎችን ሰብአዊ መብት አክብሮ በማስከበር ረገድ ለአፍታም ቸል እንደማይል ደግመን ደጋግመን ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡ ስለሆነም በአሁኑ ወቅት በምስሉ ላይ የሚታዩትንና በዚህ አስነዋሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሳተፉ ሶስት አባላትን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን እያጣራ መሆኑን የድሬዳዋ ፖሊስ አሳውቋል። አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
Показать все...
አየርላንድ ድንበር ተሻግረው የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ እመልሳለሁ አለች! የአየርላንድ መንግሥት ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችለውን ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ጀመረ።የአየርላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሞን ሃሪስ የአገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችል ሕግ አርቅቆ ለአገሪቱ ካቢኔ እንዲያቀርብ አዘዋል። ዩናይትድ ኪንግደም በሕገ-ወጥ መልኩ ወደ አገሯ የሚገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እልካለሁ ማለቷን ተከትሎ ዩኬ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ ላለመመለስ ሲሉ እንደ አየርላንድ ያሉ አገራትን አማራጭ መዳረሻቸው እያደረጉ ነው።የአየርላንድ የፍትሕ ሚኒስትር ሄለን ማክኤንቲ በቅርቡ ወደ አየርላንድ ከተሻገሩ ስደተኞች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት መነሻቸው ዩኬ ነው ብለዋል። የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማይክል ማርቲን የዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ እቅድ ገና ከአሁኑ በአየርላንድ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው ብለዋል።ከቀጥቂት ቀናት በፊት ለበርካታ ወራት ብዙ ሲያወዛግብ የቆየው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የሚያስችለውን ሕግ የአገሪቱ ፓርላማ ጸድቆ ሕግ ሆኗል። ይህ ሕግ ኢንግሊሽ ቻናል ተብሎ በሚጠራው የውሃ አካል በኩል በጀልባ በሕገ-ወጥ መንገድ ዩኬ የደረሱ ስደተኞችን በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ሩዋንዳ የሚልክ ነው።ስደተኞቹ በዩኬ የሚያቀርቡት የጥገኝነት ጥያቄ የሚታየው ሩዋንዳ ተወስደው ሲሆን፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው አዎንታዊ መልስ የሚያገኝ ከሆነ ስደተኞቹ እዚያው እንዲቆዩ ይፈቀድላቸዋል። ነገር ግን የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ ከሆነ ደግሞ ስደተኞቹ ሌላ ምክንያት በማቅረብ በሩዋንዳ አልያም በሌላ ሦስተኛ አገር የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ፈጽሞ ወደ ዩኬ መመለስ ግን አይችሉም።ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ሕጉ ተግባራዊ ሆኖ ሐምሌ 2016 ዓ.ም. ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንደሚጀር አስታውቀዋል።
Показать все...
የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ"ችግሮችን በዘላቂ ሁኔታ ለመፍታት እንጂ ለጊዜው የሚደረግ ተግባር እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል"---ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሀገራዊ የምክክር መድረክ አስፈላጊ ነቱ "ችግሮችን በዘላቂ ሁኔታ ለመፍታት እንጂ ለጊዜው የሚደረግ ተግባር እንዳይሆን መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ፕሬዚዳንቷ በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የሃሳብ ልዩነት እያደረስብን ያለው ኪሳራ ትልቅ በመሆኑ ይህ መድረክ የሚኖረው ጠቀሜታ ላቅ ያለ መሆኑንም አመላክተዋል። ፕሬዘዳንቷ ይህን የተናገሩት በዛሬው ዕለት በሀገራዊ የምክክር  ሂደቱ የሴቶች ተሳትፎና ድርሻ ምን መሆን አለበት በሚል በተካሄደ ውይይት ላይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሀገራዊና እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሀሳብ ልዩነቶች ወይንም አለመግባባቶች መኖራቸውን አንስተው ፣እነዚህን የሀሳብ ልዩነቶች ወይም አለመግባባቶች እንደ ምክክር ባሉ ሰላማዊ አማራጮች ከመፍታት ይልቅ የሃይል  አማራጮች ጥቅም ላይ ሲውል ይስተዋላልም ነው ያሉት። በመሆኑ በሀገራችን ግማሽ ያህሉን የህዝብ ቁጥር የሚይዙት ሴቶች  ውሳኔ በሚሰጥባቸው ቦታዎች ላይ መኖር ለአገር ጥቅሙ ብዙነው ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቷ ሴቶች በሀገር ጉዳይ ላይ በየትኛውም መስክ ከወንዶች እኩል ድምፃቸውን ማሰማት መብታቸው ነው፣ በመሆኑ እኩል ንቁ ተሳትፎ እንዲያ ደርጉ እንጂ  ለቁጥር ወይም ለኮታ ማሟያ መሆን የለበትም ብለዋል፡፡ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ በምክክሩ የሴቶች ድርሻ መኖሩ በከፍተኛ ሁኔታ የአገረ መንግስት ግንባታ ይፋጠናል፣ ዘላቂ ሰላምም እንዲሰፍን ጉልህ ሚና አለው፣ ለዚህም የሌሎች ሀገራት ተሞክሮን ማየት ተገቢ ነው  ብለዋል፡፡ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በበኩላቸው፣ የምክክሩ ሂደት የሴቶች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በዚህ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች 30 በመቶው የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ብለዋል፡፡ በምክክሩ ሴቶች በንቃት  የሀሳብ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫና ድጋፍ እያደረግን፣ በምክክር መድረኩ ሴቶች ድምፃቸው ጎልቶ የሚሰማበት እንዲሆን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
Показать все...