cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜

📚📚እንኳን በደህና መጡ📖📗🧾 ➥ እዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ የ አማርኛ እና እንጊሊዘኛ ..... መፅሀፍትን በ 📙 Pdf እና ትረካዎችን እና ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮችን ያገኛሉ። 📖 ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል‼️ B-) :-መረዳዳት ቢኖር ሁሉም ቢተባበር 100K ይደርስ ነበር ። For any comment @Meki3

Больше
Эфиопия6 972Амхарский5 126Книги9 525
Рекламные посты
1 855
Подписчики
-324 часа
-47 дноК
+130 дноК
Время активного постинга

Загрузка данных...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Анализ публикаций
ПостыПросмотры
Поделились
Динамика просмотров
01
መደነቅ የምናቆምበት ጊዜ አለ ስላገኘነው የማንቦርቅበት ስላጣነው የማንቆዝምበት የመጣን አንደ አመጣጡ የምንቀለበልበት ልሂድ ያለን እንደ ፍላጎቱ የምንሸኝበት አንዳንድ ጊዜ አለ. . . . . መታገል የምናቆምበት @Meki3
764Loading...
02
መደነቅ የምናቆምበት ጊዜ አለ ስላገኘነው የማንቦርቅበት ስላጣነው የማንቆዝምበት የመጣን አንደ አመጣጡ የምንቀለበልበት ልሂድ ያለን እንደ ፍላጎቱ የምንሸኝበት አንዳንድ ጊዜ አለ. . . . . መታገል የምናቆምበት @mejnun_me
10Loading...
03
🔻::::::::::::::ሚስኪኑ አፍቃሪ::::::::::::🔻 ፀሀፊ✍✍ መሐመድ ክፍል 🔟 ባታውቀኝም የሆነ ፍንጭ እያገኘች ይመስላል። እኔም ሀሳቤን ቀይሬ እንድታውቀኝ ፍላጎት አደረብኝ።የት ትምርት ቤት ነበር ምትማረው? እናንተ ጋ ። እኔ አቅሀለው ? በጣም። ኧረ እኒጃ እኔ 12 ኛ ክፍል ማስታወሰው ሰው የለም አለች። እስቲ ትምርት ቤት ቤስት ጓደኛዬ የምትያቸውን 5 የወንድ ጓደኞችሽን ንገሪኝ አልኳት። ነገረችኝ ።አብዱ፣ኢብራሂም፣ .......... ፣እና ማሜ እነዚ የኔ ምርጥ ጓደኞቼ ናቸው አለች።ከነገረችኝ ውስጥ የሁለቱን ስም ረስቻቸዋለው። የኔ ስም መኖሩ ገርሞኛል። በቃ ከነዚ አንዱ ነኝ አልኳት።ማወጣጣቷን አላቆመችም። እሺ ለምን ስምህን በሴት ስም አደረከው ? አንቺን ለማግኘትናበወንድ ስም ባረገው አታናግሪኝም ብዬ ነው። ለምን እኔን ማግኘት ፈለክ ? እዚጋ ነበር ብሶቴን በሙሉ የዘረገፍኩት። በጣም እንደምወዳት፣ግን ለሷ እንደማልገባ ወይም እንደማልመጥናት። እሷ አግብታ ብትወልድ ራሱ እሷን መውደዴን እንደማልተው ።እሷን በማውራት እርካታና ደስታን እንደማገኝ።እንዲ ራሴን ደብቄ የማናግራትም ለዚህ እንደሆነ ነገርኳት።( ፍቀር ማለት የወደዱትን የራስ ማድረግ ማለት ብቻ እንዳልሆነ አምናለው)። ስለዚ s ዬን ማውራትና ጓደኛ መሆን እንጂ የግድ የኔ ትሁን አላልኩም። የኔ ብትሆን ደስተኛ ነኝ። ይህን ስላት "ማልመጥን የሚለውን እርሳው መማንም ለማንም ማይመጥን የለም" አለችኝ። ልክ ነበረች ።ኮንፊደስ የለኝም አላልኳቹም? ለዛ ነው ። ጥያቄዋን ቀጠለች። ስምህን ሀሊማ ለምን አልክ ሀሊማ ማናት? በነገራችን ላይ ይሄ ቃለ ምልልስ የአንድ ቀን አይደለም ። ከአንድ ወር በላይ ሆኖናል። ነሀሴ ወር አልቆ መስከረም ገብቶዋል ። እኔም ፈተና አልፌ አማራ ሀገር (ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ) መመደቤንም አውቂያለው። አልሀምዱሊላህ። ወደ ቃለ ምልልሱ ስመልሳቹ። ሀሊማ በጣም የምወዳት እህቴ መሆኗን ነገርኳት። (ሚስኪን) ስለዚች እህቴ የምታውቀው ታሪክ እንዳለ ረስቼዋለው። "እንደው የሆነ ቀን የነገርከኝ" ብላ አሾፈችብኝ። እኔ ግን አልገባኝም።ምክንያቱም ስለ እህቴ እንደነገርኳት ተረስቶኛል። አሁን አስራ አንደኛው ሰአት የደረስን ይስላል። እንዲህም አለችኝ ።"""አብዲንና እነዛ ስማቸውን የረሳኋቸውን ልጆች ጠቅሳልኝ እነሱ ከኔ እኩል 11ኛ ክፍል ናቸው። ኢብራሂም ና ማሜ 12 ናቸው። ኢብራሂም ደግሞ እንዲ አዋርቶኝ አያቅም። ስለዚ ካሁን ቡሀላ ብዙም አናወራም። እኔ ማላውቀው ሰው ሲያስለፈልፈኝ አልወድም። አሪፍ አወጣጭ ነኛ?""""" ብላኝ ከ fb ወጣች ደነገጥኩ፣ ተናደድኩ፣ ጬስኩ ፣ተቃጠልኩ።ውርደትና የበታችነት ተሰማኝ። እንዴት አይሰማኝም ። እኔ መሆኔን ስታቅ ካሁን ቡሃላ እንደማናወራኮ ነው የነገረችኝ።እየተጠላሁ የምወድ ፣እየተገፋሁ የምቀርብ አሳዛኝ ሚስኪን። ደሜ ፈልቶ ፣ እልህ እስከ አናቴ ተናንቆኝ ፣ ፍም እሳት የዋጥኩ ይመስል ሆዴ እየተቃጠለ ረጅም መልእክት ፃፍኩላት።የመሰናበቻ መሆኑ ነው።ደንታም እንደማይሰጣት አቃለው። የመልእክቱን መደምደሚያ በሚከተለው ጥያቄያዊ ትእዛዝ አደረኩት እንዲ ይላል።""""""ይኸውልሽ s እኔ አንቺን ማገኝባቸው መንገዶች በሙሉ ተዘግተዋል ።የቀረው fb ብቻ ነው። አሁን እኔ ብሎክ ባደርግሽ ስትናፍቂኝ የ fb ስምሽን ስለማውቀው ዳግም ሌላ fb ከፍቼ ልበጠብጥሽ እችላለው። እናም አንድ ነገር ብቻ ተባበሪኝ ።አንቺ ብሎክ አድርጊኝና የ fb Hilwan የሚለውን ስምሽን ቀይሪው። ከዛ የትም ብፈልግሽ ኬትም አባቴ አላገኝሽም።""""""""" ብያት k fb ወጣሁ በማግስቱ ዳታ አብርቼ ስገባ "" በጣም አዝናለው እንዲ ይፈጠራል ብዬ አላሰብኩም """"" መልካም ህይወት። የሚል መልእክት ልካልኝ ብሎክ አደረገችኝ። ግልግል። ከዚ ቀን አንስቶ ሳልረሳት ረስቺያት፣ ዳግም ስለሷ ላላስብ ለራሴ ቃል ገባሁ። ትንሽ የመረጋጋት ነገር ይታይብኛል።ምክንያቱም ከሷ በግልፅ እስክሰማና ብዙ ሙከራዎችን እስከ ማደርግ ድረስ ሁሉ ነገሬን የተውኩላትን እንስት ላለመተው የዛኔ ላይብረሪ እያለው ወስኜ አልነበር?አሁን ሁሉም ነገር ስለተገለፀልኝ ለቆራጥነት አልተቸገርኩም። እነሆ እኔ ወደ ካምፓስ መግቢያዬ ደርሶዋል ። ጥቅምት ዘጠኝ ነው ምሄደው።ቢያንስ ሳምንት ቢቀረኝ ነው። ከአዲሳበባ ስወጣ ይበልጥ እሷን እንደምረሳ ና አዲስ እኔነቴን እንደማገኝ ውስጤ እያጫረብኝ ነው። ዛሬ ቀኑ ሐሙስ ከቀኑ 11 ሰአት ነው። ፆመኛ ስለሆንኩ በጣም ደካክሞኛል።መንገድ ላይ ነኝ። ወደ ሰፈሬ በቢላል መስጊድ በኩል የተጎሳቆለ ሰው መስዬ፣ ከድካም የተነሳ እግሮቼን ከመሬት እያንፏቀቅኩ፣ ቲሸርቴ ተዝረክርኮ ከፊል ደረቴን እያሳየ፣የለበስኩት ትልቅ ነጠላ ጫማ አቧራ አያነሳ እግሬን ሌላ ጫማ አስምሎት፣ ልቤ በሀዘን፣ እምሮዬ በትካዜ ፣ሆዴ በረሀብ ተቃጥሎ በመንገዱ ግራ ጠርዝ ወደታች እየተራመድኩ ነው። ድንገት ቀና ስል s ዬ ኬት መጣች ሳይባል አይን ለአን ተጋጨን። እሷ ከታች እየመጣች ነበር ። እኔ ከላይ።ያየሁትን ማመን ከበደኝ፣ደርቄ ቀረሁ ፣ አምላኬ ግን ምን አርጌ ነው? ምን አጥፍቼ ይሁን? እንዲ የማልወጣበት ማጥ ውስጥ የገባሁት?ምናለ የዛኔ እዛ ቁራን ቤት አስቀራ ስባል እምቢ ባልኩ። #ክፍል_11 ✍✍ይቀጥላል
1351Loading...
04
🔻:::::::::::::::ሚስኪኑ አፍቃሪ:::::::::::🔻 ✍ፀሀፊ መሐመድ ክፍል 9⃣ኝ በዚህ እቅዴ መሰረት ነበር sዬን ዳግም የማገኝበትን ተስፋ የሰነቅኩት።እሱም አዲስ የ fb acount ከፍቼ ፣ስሜን በሴት ስም አድርጌ የsዬን fb ስሟን ስለማውቀው friend request ልልክላት ። ከዛ ሴት መስዬ ላዋራት ። ብዙ ከተግባባን ቡሀላ ወንድ መሆኔን እነግራትና ከዛ ቀስ እያልኩ ማንነቴን አሳውቂያት እሷን ለማግኘት መሰዋት መክፈሌን እንድትረዳ ለማድረግ ነው ።አሪፍ ሀሳብ ነው ፣ግን ትግስትና ጊዜ ይጠይቃል። የ fb ስሜን በታላቄ ታላቅ እህቴ ስም ነው ያደረኩት።ሀሊማ ትባላለች ስለዚች እህቴ ለsዬ ስሟንና ከቤታችን ቀይና የሁላችንም ታላቅ እንዲሁም እኔ በጣም የምወዳት እህቴ መሆኗን ትምርት ቤት እያለን አጫውቻት ነበር።sዬ እህቴን በአካል ባይሆንም በደንብ ታቃታለች። አሁን የረመዳን ወር አልቆ ፣ፈተናም ጨርሰን፣እኔም በ 15 ቀን አንዴ ምመላለስበት የነበረው ጉዳዬን ከግብ አድርሼ የተቀመጥኩበትና ቀጣይ የፈተና ውጤት የምጠባበቅበት ወቅት ነበር።ዝናቡና ደመናው ክረምቱ በደንብ መግባቱን ያሳብቃሉ።ለብርዱ እንደልብስ ለደመናው እንደ ብርሀን የምትሆነኝ እንስት በአካልም በስልክም ከተለየኋት ግንቦት አልፎ ሰኔ ፣ሰኔ አልፎ ሀምሌ ገብቶዋል። ሁለት የሀዘን ወራቶችን ካሳለፍኩ ቡሀላ ነበር እቅዱን ያቀድኩት።አሁን fb frind ሆነናል ።sዬ ብዙ ነገር ትፖስታለች ፣በጣም ብዙ ኮሜንት ይሰጣታል።ከምትፖስታቸው ነገሮች አብዛኞቹ ስለ ጋብቻ መልእክት የሚያስተላልፉ ናቸው።ትንሽ ግራ ያጋባሉ ። የሚሰጣትን ኮሜንት ሳነብ አንድ የገረመኝ ነገር አነበብኩ።ምን ይላል መሰላቹ። " አንቺ ልጅ ምን አስበሽ ነው?" አላት የሆነ ልጅ። እሷም ቀጠለች " አቆላምጣው እገሊዬ ምንላርግ ማግባት አምሮኝ እኮ ነው" አለች።ትንሽ ደነገጥኩ።እንደዛ ችላ ምትለኝ የነበረው ልታገባ አስባ ይሆን? ራሴ ራሴን የጠየኩት ጥያቄ ነበር። መልስ የለም።እኔ ስለ ትዳር ለማሰብ ገና አስር አመት ይቀረኛል።ብዙ ነገራችን አራምባና ቆቦ እየሆነብኝ ተቸግሬያለው።እኔም በበኩሌ ኮሜንት ሰጠኋት።ግን በውስጥ ሚሴጅ ነው።የማግባት ፍላጎት ያለሽ ተመስያለሽ ።አልኳት ። አዎ ሀሉዬ አለችኝ ።እቺ ልጅ ሁሉንም ነው እንዴ ምታቆላምጠው? በሌላ ጊዜም ጥያቄዬን አቀረብኩላት "የወንድ ጓደኛ አለሽ"?ሴት መስያት ስለነበር በግልፅ ነበር ምትነግረኝ። የለኝም አለችኝ።ትንሽ ተረጋጋው። ጥያቄዬን ቀጠልኩ"ወንዶች ባንቺ እይታ ምን ይመስላሉ?" "አይ ሀሉዩ ሁሉም የሚፈልጉትን እስኪያገኙ ድረስ ንግግራቸው ሁሉ ማሬ ፍቅሬ ነው ። ሚፈልጉትን ሲያገኙ ፀባያቸው ይቀያየራል" እሷ ነበር የተናገረችው።ደነገጥኩ ደሞ እኔ ምን አድርጊያት ነው? አይ እኔን አይወክልም።ታዲያ የጎዳት ሰው አለ ማለት ነው? ልክ ነሽ Hilu አልኳት። የ fb ስሟ Hilwan ነው ብያቹ አልነበር? በኔ ቤት ማቆላመጤ ነበር። ቀጠለች "አንቺስ ሀሉዬ አግብተሻል?" አለችኝ ። አንቺ ስትለኝ በውስጤ እተዝናናሁ ኧረ Hiluye እኔም እንዳንቺ የተጎዳሁ ነኝ ። አልኳት። አልዋሸሁም በሷ የተጎዳሁ ነኝ። "አይዞሽ ሀሉዬ አላህ ያቃል" አለችኝ።ጥያቄዬን ስጠይቃት እሷም ስትመልስ። ተግባባን እኔ ዱባይ ሀገር ለስራ መሄዴንና በቅርቡ እንደምመለስ አድርጌ ነው የነገርኳት። በደንብ ተግባብተናል አንዳንድ ያልገቡኝ ሚስጥሮችን አወጣጥቼያት ነበር።ከዱባይ ስመለስ እንደምንገናኝም አውርተናል። በዚ አጋጣሚ ድጋሚ አንድ ነገር ብልጭ አለልኝ ። በፊት ቁርአን ቤት እያለን አንድ በጣጣጣም የምታምር ቁርአን ሰጥታኝ ነበር። ይህ ቁርአን ነጋ ጠባ sዬን ያስታውሰኛል ።እንዲ ከመራራቃችን በፊት እሷን በአካል ለማግኘት ስል ብዙ ጊዜ ቁርአንሽን አትፈልጊውም ልስጥሽ ስላት እሷ ግን ማሜ አንተ ጋር ይቀመጥ ትለኝ ነበር።ምናልባት ለመገናኘት ከተቀጣጠርን ከሩቅ ሆኜ በህፃን ልጅ ቁረአኑን አቀብያት በfb በሴት ሆኜ ሳዋራት የነበርኩት እኔ መሆኔን አሳውቄ ላስደነግጣትም አሰቤ ነበር።ግን አልተሳካም ልንቀጣጠር አልቻልንም። የአረፋ በአል ተቃርቦዋል።ጥቂት ቀናት ነው የቀሩት እኔም ከዱባይ መጥቻለው sዬ እንኳን ደህና መጣሽ ብላኛለች። ጉዴን አላወቀች አይፈረድባትም።አሁን ወደ ሁለየኛው እቅዴ ምሸጋገርበት ሰአት ነው።እሱም ወንድ እንደሆንኩና ዱባይም እንዳልነበርኩ ልነግራት። ትንሽ ፈርቻለው ።ብሎክ ብታደርገኝስ፣ ማንነትህን ካልነገርከኝ እንዳታዋራኝ ካለችኝስ?፣የኔ ሀሳብ ደሞ አሁን ማንነቴን እንድታውቅ አልፈለኩም ። የኔ ፍላጎት ወንድ መሆኔን ብቻ ካወቀች ቡሀላ በ fb የተዋወቀችው የወንድ ጓደኛዋ ለመሆን እና በጓደኝነት ከተጣጣምንና ከተመቻቸን ቡሀላ እንደ ሰርፕራይዝ ማንነቴን ለመንገር ነው። ከቀኑ አስር ሰአት ነው ።fb ገባሁ online ላይ አለች ።አሰላሙ አልኩም ሒሉ ።ወአለይኩም አሰላም ሀሉዬ። እንዴት ነሽ? አለሁ። አንቺ እንዴት ነሽ? አልሀምዱሊላህ ደና ነኝ። ሒሉ አንድ ሚስጥር ልንገርሽ አትቆጭም? ኧረ ሀሉዬ የምን ሚስጥር ነው ንገሪኝ ችግር የለውም።አትጣይኝም? ለምን እጣላሻለው ንገሪኝ? ብሎክ እንደማታደርጊኝ ቃል ጊቢልኝ? እሺ ቃል እገባለው ንገሪኝ። እኔ ሴት አደለሁም ወንድ ነኝ😧😳። አፈረጥኩት። " ወይ ዘንድሮ እሺ ማነህ ደሞ አንተ?" አለች። የኧኧኧኧፈራሁት ደረሰ። እሱንማ አሁን አልነግርሽም። አልኳት ቃል ስላስገባኋት ብሌክ አታደርገኝም ብዬ። "ይቅርታ እኔ ከማላውቀው ወንድ ጋር ማውራት አልደልግም። አለች። እንደምንም ብዬ እኔ አንቺን ማናገር ብቻ ነው ምፈልገው ፣ መተዋወቁ ምንም አይሰራም አንቺን ብቻ በማናገሬ ደስታን አገኛለው አልኳት ።እንደፈለክ ። አለችኝና ከfb ወጣች። ደስ አለኝ። በሌላ ቀን fb ገባሁ። እህቴ ቤት ነው ያለሁት። ሀይ ሒሉ አልኳት። ሀይ አለችኝ።ማቆላመጥ አቆመች። ብዙ አወራን ፣ብዙ ተጨዋወትን።ያለ የሌለውን ሳወራ ፣ስቀልድ ስተስቅ፣ቀየን። በመጨረሻም " ማን ብዬ ልጥራህ" አለችኝ።እንደተመቻቸን ገመትኩ።ግንኙነታችንን ወዳዋለች ማለት ነው አልኩ በሆዴ። ከዛ መለስኩላት" ፈላጊዬ ወይም F እያልሽ ልትጠሪኝ ትችያለሽ አልኳት። ሳቀች hhhhhh ። አሳሳቅሽ ደስ ይላል ።አላኳት። እንዴት? አለች። መለስኩላት HaHaHaHa እያሉ መሳቅ ሰርአት ያጣ ነው። ያንቺው ደስ ይላል አለኳት።አመሰግናለው F. አለችኝ። አውሽኝ እመልስልሻለው? አይ እምቢ ። ቋጣሪ ብተሰጭኝ ምን አለበት። እሺ ውሰደው። ባንዳፍ hhhhhh አልኩ።ከዚ ጊዜ ቡሀላ ሳታውቀኝ ቢሆንም በጣም ደስተኛ ነኝ።ሁሌም በደንብ እናወራለን።እኔ መሆኔን ብታቅ ግን እንዲ ታወራኛለች? አይ አታወራኝም ። ከዚ ቀደም የነበረውን አስታውሳለው ከሌላ ወንድ ጋ እያወራች ከኔ ጋ ሲሆን ለምን ከበዳት?አላቅም።ወንድ መሆኔን ከነገርኳት ገዜ አንስቶ ማንነቴን ለማወቅ ማትፈነቅለው ድንገይ አልነበረም።እስቲ ካደረግናቸው ቃለ ምልልሶች መሀከል ጥቂቱን ላውጋቹ። ተከተሉኝ። አሷ ነበረች ጀማሪዋ ........................................... ....ተማሪ ነክ?ነበርኩ ።ዘንድሮ ካምፓስ ነኝእኔን የት ነው ምታቀኝ?ትምርት ቤት።የትሰፈር ነክ? ኧረ እሱንማ ከነገርኩሽ ታቂኛለሽ። እንዴት አቅካለው አንተ ብቻ ነክ በሰፈሩ ወንድ። እናንተ ሰፈር አልኳት።አሪፍ ነው አንድ ሰፈርነና አለች። #ክፍል_10 ይቀጥላል✍✍
1560Loading...
05
🔻:::::::::::::::ሚስኪኑ አፍቃሪ::::::::::🔻 ክፍል::::::::8⃣ት ግን ተስፋ አልቆረጥኩም በሶስት ቀን አንዴ ምናምን መደወሌን ተያይዤወለው ።እሷግን ሚስኮልም አርጋ አታቅም።ዛሬ ቀኑ በማያቃጥል ፀሀይ ደምቆ ላየብረሪው በሰው ጢም ብሎ ከጠዋት ጀምሮ በአሪፍ ድባብ ላይ ነው።ያሁሉ አንባቢ ተሰብስቦ ከፀጥታው ብዛት የተነሳ የትንፋሽ ድምፅ ራሱ ይሰማል ። በዚ መሀል አስር ሰአት አካባቢ ስልኬ ጠራ ያልገመትኩት ስልክ ።sዬ ነበረች እየፈጠንኩ ከላይብሪው ወጥቼ ስልኩን አነሳሁት። ሃሎ ማሜ ላይብረሪ እየመጣን ነው። ቦታ አለ? አለችኝ።ዛሬ ማውቀው የ sዬ ድምፅ ነው። ደስ ያላት ትመስላለች። ልታጠኑ ነው? አልኳት።ምክንያቱም ትምርት እንደማትወድ ነበር ምገምተው። አደለም አሳይመንት ልንሰራ ነው አለችኝ ።ብቻዋን አደለችም ።ቦታ እንደማይጠፋ ነግሪያት ስልኩን ዘጋችዉ።ወደ ውስጥ ገብቼ ቦታዬ ላይ ቁጭ አልኩ። ከጎኔ ክርስቲያን ሴቶች አሉ። ከፊት ለፊቴ ደሞ ወንዶች ናቸው ምንም ቦታ ላገኝላቸው አልቻልኩም ።ትንሽ እንደቆየሁ ከፊይ ለፊት ያሉት 3 ልጆች መፃፋቸውን ይዘው ተነስተው ሄዱ።ማመን ከበደኝ እንዴት ሊሆን ቻለ።3ወንዶች ለ3ሴቶች ቦታ ለቀው ሄዱ። ለዛውም እኔ ፊት።ቦታውን ያዝኩላቸው።ብዙም ሳይቆዩ sዬ ከባለ መነፅሯና ከዛች ከእንደራሷ አይነት ቀጫጫ ልጅ ጋር ላየብረሪ ገቡ።እነዚ ጓደኞቿ ትምርት ቤት እኔን ከsዬ ጋር ሲያዩኝ የተለየ ስሜት ፊታቸው ላይ አይባቸው ነበር። ይኮሳተራሉ፣እንደማፈር ይላሉ ፣ፊት ያዞራሉ፣ ወይም ካሉበት ቦታ ተነስተው ይሄዳለው። እኔ የትም አላውቃቸውም።አንድ ቀን ግራ ሲገባኘኝ s እቺ ባለመነፅሯ ማናት? በጣም ነው ምፈራት ብዬ ጠየኳት። ቁራን ቤት ትቀራ ነበር አለችኝ። አስቀርቻትም አቃለው ማለት ነው። ወይ ውርደት አልኩ በሆዴ ።ለካ አስቀሪ መሆኔን አውቃ ነው እንዲ ምትሆነው። እናም ላይብረሪ ውስጥ ከዛ ሁሉ ሰው መሀል እኔን እስኪያዩኝ ባለመነፅሯ ውር ውር አለች።sዬ ለየት ያለ ጅልባብ ለብሳለች ። በጣም አምሮባታል ።የኔ ታናሽ ሳይሆን ታላቅ ነው ምትመስለው።ጅልባቡ ከግርማ ሞገሷ ጋ ተደምሮ ትልቅ ሰው አስመስሏትል።በእጄ ምልክት ስሰጣቸው sዬ በኔ አቅጣጫ በኩል ባለው ወንበር ስትቀመጥ ሁለቱ ደሞ ከጎኔ ከነበሩት ሴቶች አቅጣጫ ተቀመጡ። ገና ሲገቡ ጀምሮ ያ የሚያጠና ወንድ በሙሉ አአአአአአአ ብሎ ሊጎርሳቸው ይመስል በስስት ሲመለከታቸው አስተውያለው። ዛሬ ከሳምንታት ቡሀላ አየኋት ።ውስጤ እየከዳኝ ነው። ከገባች ሰአት አንስቶ ማጠና እየመሰልኩ ሰርቄ እያየኃት ነው። የማጠናው አደለም መስመሩ ገፁም ጠፍቶብኛል። እነሱ ግን ብዙም ሳይቆዩ ወዲያው ነበር አሳይመንታቸውን መስራት የጀመሩት። ማንበብ ሲያቅተኝ ጠረጴዛ ላይ ያስቀመጠችውን ስልኳን አንስቼ ቀጥታ ጋላሪ ውስጥ ነበር የገባሁት ።እቤት ሆና በከፊል ተገላልፃ የተነሳቻቸውን ፎቶዎች ወደራሴ መላክ ጀመርኩ። የስልኬ የሚሴጅ ድመፅ የፍየል ጩኸት ስለነበር ፎቶው ሲገባ ጮኸ የላይብረሪው ሰው ሁሉ ነበር በአንድ ድምፅ የሳቀው ። ሶስት ፎቶ ላኩኝ ሶስቴ ሚእእእእእ አለ። ይሳቁልኝ ይሳቁብኝ ማውቀው ነገር የለም።እሷም ሳትቀር እሳቀች ነበር። ግን ፎቶ እየላኩኝ መሆኔን እሷም አልባነነችም። መግሪብ ሲደርስ ተነስተው ሄዱ። ስለ ፎርሙላው ከነ አካቴው ጠይቃኝ አታቅም። ረስታዋለች። ከላይብረሪው ቡሃላ ድጋሚ ግንኙነታችን በስልክ ብቻ ሆነ።አንድ ቀን ነው ትዝ ይለኛል በጣም እየተጨዋወትን በስልክ ከ30 ብር ካርድ የሚበልጥ አወራን ። የዛኔ ነበር fb ፈሬንዷ እንድታደርገኝ የጠየኳት ።fb ላይ ማውራት ከጀመርኩ ጀምሮ በጣም ተቀዛቅዘናል። ሲላት ትንሽ ታወራኝና ዝም ፣አንዳነዴ ጭራሽ አታናግረኝም።አሁን እኔም ፋራ መሆን የለብኝም ሰው በይሉኝታ እንዲያደርግልኝ ስለማልፈልግ ማቆም እንዳለብኝ ወሰንኩ።ለራሴም ቃል ገባሁ መርሳት መቻል እነዳለብኝ ። ካሁን ቡሃላ በምንም አይነት መንገድ ማግኘት እንደማልችልና ተስፋ መቁረጥ እንዳለብኝ ቆራጥ ውሳኔ ወሰንኩ። ምክንያቱም እንደጠላችኝ በብዙ ነገሮች ምልክት አየሁዋ።ከዚ በላይ መለመን የለብኝም።ስልኳን ከስልኬ አጥፍቼ የራሴን ህይወት መኖር ጀመርኩ።ሳልነግራት መደወል ተውክ ።ጠፋሁ ።አንድም ቀን ደውላ አታቅም።ግን ከተወሰኑ ጊዚያት ቡሀላ ግን ናፍቆቱን መቋቋም አቃተኝ ለመደወል ብዬ ስለኳን ኬት ላምጣው፣ ደሞ fb ላይም ብሎክ አረጊያታለው። በማስታውሰው መጠን የተለያዩ ቁጥሮችን ሞከርኩ ግን የደለትኩትን ስልክ ቁጥሯን ላገኝ አልቻልኩም። ማን ደልት አለኝ? ድጋሚ ራሴን መውቀስ ጀመርኩ። (ሚስኪኑ ማሜ) ።በዚህ ሀዘን ውስጥ ሆኜ፣ሳልናፍቃት ናፍቃኝ፣ሳትወደኝ ወድጃት፣ሳትደውል ደውዬላት፣ አንድ እጅ ብቻውን ማጨብጨብ አይችልምና አንድ ብቻዬን ሆኜ ምንም መፍጠር እንደማልችል በድምፅ አልባ አዋጅ እየተነገረኝ ነው። እኔ ግን ተስፋ አልቆርጥም ።ትግሌን እቀጥላለው ማንንም አላማክርም።በአንድ እጅ ማጨብጨብም እንደሚቻል በተግባር አሳያለው እያልከኩ ውስጤ እየነደደ ሀሳብ ማፍለቅ ጀመርኩ።ያለ እቅድ ማይሆን የለምና አንድ በጣም የሚያምር ሀሳብ ከመጋደሚያዬ ላይ ሆኜ መጣልኝ። ወዲያው ነበር ለመተኛት ካሰብኩበት ብድግ ብዬ የተነሳሁት።በዚ እቅዴ መሰረት sዬን ዳግም የማገኝበትን ተስፋ የሰነቅኩት። ምን ይሆን እቅዱ ቀጣይ ክፍል ላይ እንገናኝ። #ክፍል_9 ✍ይቀጥላል።።።
1790Loading...
06
🔻::::::::::::::ሚስኪኑ አፍቃሪ::::::::::::🔻 ክፍል: :::::::::7⃣ት መርዶው ባጭር አረፍተ ነገር በ3 ቃላት ብቻ የሚገለፅ እኔን እንክትክቴን ያወጣኝ ንግግር ነበር። አሱም እንዲህ ይላል "12 ቶች መግባት አትችሉም"።ለኔ ብቻ ነበር መርዶው ለሌላውማ ብስራት ከብስራትም በላይ ነበር ።ተማሪው ግማሹ ያፏጫል ፣ከፊሉ ይጮሀል፣ከፊሉ ደሞ እንደኔ አይነቱ ፊቱን አጨፍግጎ ነገሩን በትዝብት ይከታተላል። 11 ዶች መታወቂያ እያሳዩ አየገቡ ስለነበር ምናልባት ስትገባ ካገኘኋት ብዩ ባይኔ በር በሩን ስመለከት ቆይቼ አይኔ ደከመው።እሷም ቀድማ ገብታለች። አይኔ ከግቢው አጥር አሻግሮ ወደ ውስጥ እያየ ድመት ወተት አይታ ለመጠጣት እንደምትቋምጠው እኔም ጊቢ ውስጥ ለመግባት እቋምጥ ነበር። ግን ምን ዋጋ አለው አልችልም😢😢😢😢😢። ልክ የዛኔ sዬ የፎርሙላውን ትርጉም ሰላልነገርኳት በቀዘቀዘ መንፈስ ጥላኝ እንደሄደችው፣ ዛሬ እኔም ስሜቴን የምነግርበትን አጋጣሚ ስላከሸፉብኝ በቀዘቀዘ መንፈስ ዳግም እዚህ ትምርት ቤት ላልመለስ ወደ ቤቴ አቀናሁ። ከተዋወቅን አንድም ቀን በስልክ አውርተንአናውቅም ምክንያቱም ቀን በቀን በአካል እንገናኝ ስለነበር አላስፈለገም።አሁን ግን የቤት ምርኮኛ ሁኛለው።ከዚ ቀደም እንደነገርኳቹ ብቸኛ ነኝ ከሰው መቀላቀል ብዙም አይደላኝም።ከራሴ ጋር ማውራት አበዛ ነበር።አሁን ግን ከብዶኛል ጭርታ እንዳልወደድኩት አስጠልቶኛል።ወላጁን በሞት እንደ ተነጠቀ ታዳጊ ዝም ብሎ ብሶት ብሶት ይለኛል። ከጥቂት ቀናት ቡሀላ ትንሽ ወደ ራሴ መመለስ ጀምሪያለው። አእምሮዬ ላይም የፈተናው ነገር ብልጭ ብልጭ ይልብኛል።ከቤታችን ጥሩ ደረጃ ላይ እንድደርስ ምጠበቀው እኔ ነኝ።ታላላቆቼ ሁሉም ከታች ክፍል ነው ትምርት ያቆሙት። 12 ከመግባቴ በፊት በነበረኝ የማጥናትና ጎብዞ የመማር ባህሪዬ ነው ቤተሰቤ ሚያውቁኝ።በፍፁም አንድም ቀን ባልባሌ ቦታ ይገኛል ብለው ጠርጥረውኝ ስለማያውቁ አይቆጣጠሩኝም የትዋልክ የት አደርክ እያሉኝም።እናም ዩኒቨርስቲ የመግባት ህልሜ ጨልሞ እየታየኝ የቤተሰቤ ሸክም መሆኔ ደግሞ ይበልጥ አያበገነኝ ሲመጣ ድንገት የማላወቅ ሀይል ገፍትሮ ላይበረሪ አስገባኝ።የቀረችኝን አንድ ወር እረፍት የሌለው የ24 ሰአት ጥናት ማጥናት ተያያዝኩት።በ sዬ ናፍቆት የቆሰለው ማንነቴ ድብርቱን ሚያስረሳው ነገር ሳያገኝ አይቀርም።አሁን ከጥናቱ ጋ በጣም ተጣጥመናል፣ያለችኝ አጭር ጊዜ ስለሆነች ትኩረቴን ቀላልና የሚሰሩ ሳብጀክቶች ላይ አድርጊያለው።በተጨማሪም የትምርት ቤታችን ሰቃይ ተማሪዎችንም የመግባባት እድሉንም ስላካገኘሁ።ውስጤ ፈተናውን የማለፍ ተስፋው እያንሰራራልኝ ነው።ቁርስ በላው ላይብረሪ፣ምሳ በላው ላይብረሪ፣ ምሽት 3 ሰአት ሲል እቤት እገባለው።ታዲያ በዚ ሙድ ወስጥ ሆኜ ድብርቴ ቢጠፋም sዬን መርሳት አልቻልኩም። ከዚ በላይ መቆየት አልቻልኩም መደወል እንዳለብኝ ይሰማኛል።ውስጤ ደግሞ እሷ ለምን አልደወለችም? ይለኛል።አንተ ብቻ ነህ ምትወዳት? እንድጠራጠር እያረገኝ ነው። አይ እሷ እንደምጠላኝ ካፏ እስክሰማ መጠበቅ አለብኝ እያልኩ ከራሴ ጋ አመነታለው። ደወልኩ ሰአቱ ከመግሪብ ቡሀላ ነው።ቀኑን ሙሉ በነሻጣ ሳጠና ውዬ ውስጤ እርካታና ተስፋን በጥናቱ ምክንያት ተላብሶ በአሪፍ ሙድ ሆኜ ነበር። ለመግሪብ ሰላት ወጥተን ስንመለስ ነበር የደወልኩት ስልኩ ተነሳ።ልቤ መብረቅ የመታው መሬት ይመስል ሲሰነጠቅ ይሰማኛል። (ሚስኪን)።ሄሎ ቀጥሎ የሰማሁት ቃል ነበር። ግን ዝግ ያለ፣የመኮሳተርም ባህሪን የሚያንፀባርቅ ፣ ከምንም በላይ ደግሞ በቀዘቀዘ ስሜት የተለቀቀ ድምፅ ነበር።እኔ ደሞ ሰው ሲንቀኝ፣የበታች አርጎ ሲያየኝ ከማይ ምንም ነገር ቢቀርብኝ እመርጣለው።ሰው ሰው ሆኖ እንዴት ሰውን ከራሱ በታች አድርጎ ይመለከታል? ???እናም ይህን ድምፅ ከሰማሁ በኃላ ቀኑን ሙሉ የገነባሁት ሙዴ ድምጥማጡ ጠፋ።በዚም አላበቃም ሄሎ ሳልላት በመደወሌ ፀፀተኝ።ለነገሩ አንዴ ደውያለውና በጆሮዋ አልዘጋው። ሄሎ ሰላሙ አለይኩም ።እኔ ነበር ያልኩት። ዋለይኩመሰላም ።ማን ልበል? የሚል ድምፅ ተመለሰልኝ። ስልኬ እንደተራራ ነበር የከበደኝ ምለው ጠፋኝ።መጀመሪያ ሰልኩ ሲጠራ ድንጋጤ ሲወረኝ፣ሃሎ ሲባል ነሻጣዬ ደስታዬ ሲነፈግ፣አሁን ደግሞ ማን ልበል ስባል ንዴት አገንፍሎኛል። ማን ልበል እንዴት ልትል ቻለች? በደስታ ላወራ የነበረው ስልክ አሁን ንዴት በተላበሰ መንፈስ ሊሆን ነው። s መሀመድ ነኝ። አልኩ እንደምንም እራሴን አያረጋጋሁ። እንደፍሪጅ ውሀ በቀዘቀዘው ድምፇ ።እእእእ ማሜ እንዴት ነህ ሰላም ነው አለችኝ። ዘገነነኝ ።ማሜ ስባል ዛሬ አስጠላኝ።ማላውቃት ሆነችብኝ።በራሴ አፈርኩ።አፌ ሁሉ ተሳሰረ።እንደምንም 3 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተሰነባብተን። ስልኩ ተዘጋ ግያለው ፣መፃፌን ይዤ ወደ ቤቴ አመራሁ።እንደሰከረ ሰው ያረገኛል።ምን ሆና ይሁን እንደዛ ምትስቅ ምትጫወት ልጅ? በስልክ ለተፈጠረው ነገር ምንም መልስ አጣሁለት።ምክንያቱ ባልታወቀ ነገርማ ዝም ብዬ ማንነቴን ሁሉ የረሳሁባትን እንስት አልፋታም ። ብዙ ማረጋገጫዎችን ለመሞከር ወሰንኩ ።ቀን ቀን እያጠናው ማታ ወደ ቤት መግባት ሆኖዋል ስራዬ ጥሩም ተጉዣለው።ውስጤ ምንም ፈተናውን የመውደቅ ፍራቻ የለም አልሀምዱሊላህ ጭንቀቴም ፍራቻዬም ወደሷ ዞሮዋል። በየቀኑ አልደውልም ሙዴና ነሻጣዬን መምጫቸውን ጠብቄ ነው መደወል ምፈልገው ምክንያቱም ደስተኛ ሆኜ ለማውራት እንዲመቸኝ ።ደወልኩ ከቀኑ 11 ገደማ ይመስለኛል ።ተነሳ የዛሬው ድምፅ ይሻላል ።አወራን ፣አሁንም ትምርት ቤት እየሄደች እንደሆነ ነገረችኝ። ማልዋሸው ነገር ቢኖር በአካል ማቃት sዬ ግን አደለችም።ፍፁም በስልክ ተቀይራለች ። ሁሉም ሰው ይሆን በስልክ ሚቀያየረው።ወይስ ቴሌዎች ሊያጣሉን ፈልገው የሌላ ሰው ድምፅ አያሰሙኝ ነው ?። ምለው ጠፍቶኛል መደወል ለመተው ባላስብም ግን ቅፍፍ ብሎኛል ።የሆነ በማልፈልገው ነገር ላይ ተገድጄ ምደውል ምደውል እየመሰለኝ ነው። #ክፍል_8 ይቀጥላል::::::✍
1650Loading...
07
🔻::::::::::::::ሚስኪኑ አፍቃሪ:::::::::🔻 ክፍል 6⃣ ዛሬ ትላንትና ነገ እያልን ስለሱ እያወራንለት የነበረው ቀን ነው።sዬ ልታገኘኝ የፈለገችበት ጉዳይ እስካውቅ ጓጉቻለው። ረፍት ላይ ተገናኘን።ለምን በድንገት መምጣት እንደተወች አልጠየኳትም።እኔ በባህሪዬ ሰው በይሉኝታ ምንም ነገር ለኔ ብሎ እንዲያደርግ አልፈልግም። ውስጡ ያዘዘውን እንዲያደርግ ነው ፍላጎቴ።እሷም ጠፋች ።የራሷ ምክንያት ይኖራታል ብትነግረኝም ባትነግረኝም እንደፈለገች። ምንም እንዳልተፈጠረ ፈገግ እያልኩ። አሰላሙ አለይኩም s ። መልስ ሰጥታኝ ።" ማሜ ቁራን ቤት አዲስ የገባው ውስታዝ ኪታብ ሲያስቀራ አይገባኝም። አንተ ከተመቸህ እዚ በምሳ ሰአት እየተገናኘን አስቀራኝ" አለችኝ ። ገርሞኛል።እንዲሁም አስፈርቶኛል። የተወደድኩም እየመሰለኝ ነው። ብዙ ጊዜ ሰው ሲስቅልኝ፣ሲያቆላምጠኝ እና እኔ በምችለው እርዳታዬን ሲፈልግ የወደደኝ ይመስለኝ ነበር።(ሚስኪን) ።ሁኔታዋ በኪታብ ሰበብ በየቀኑ ለመገናኘት ዘዴ እየዘየደች ይመስላል። እርግጠኛ ነሽ መቅራት ትፈልጊያለሽ? አልኳት። እንደምትፈልግ ስትነግረኝ። ከነገ ጀምሮ እንደምንገናኝና መቅራት እንደምንችል ፈቃደኛ መሆኔን ነግሪያት ተለያየን። ከዛ ቀን ጀምሮ የተቋረጠው ግንኙነታችን እንዳዲስ ቀጥሎዋል። እሷም እኔም የየራሳችን ኪታብ ይዘን የትምርት ቤቱ ሜዳ ጋ አንድ ጥግ ስር የመጀመሪያ ቂራት ለመቅራት ተቀመጥን።የየራሳችን ኪታብ ያስፈለገው ያልተገባ ቅርርቦሽና ንክኪ እንዳይፈጠር ነበር። እኔ ማስረዳቴን ቀጠልኩ የሷ ሁኔታ ግን ግራ ሚያጋባ ነበር። አይኗ ኪታቡ ላይ ሳይሆን እኔ ላይ ነው ።እየሰማችኝ አደለም ።ሼም ያዘኝ።ገባሽ ?አልኳት ቀና ብዬ እያየኋት። አንገቷን እየነቀነቀች አይኗን እኔ ላይ ተክላ አው አለችኝ። ፌቴን አዙሬ አነብላት ቀጠልኩ ከተወሰነ ደቂቃቡኋላ ዳግም ዞሬ ሳያት አሁንም እያየችኝ ነው።ይሄ ነገር ወዴት ወዴት እያመራ ነው? በውስጤ አጉረመረምኩ። አሁን የጠረጠርኩት ነገር እውነት መሰለኝ። ስሜቷን ለመረዳት በማሰብ ከአንድ መሰረመር ያልበለጠ ቀርተን ኪታቡን ዘግቼ ለዛሬ ይበቃናል አልኳት።አወራን ፣አወራን፣አወራን፣ ትፈነድቃለች፣ትስቃለች ፣እኔ በሷ ሳቅና ደስታ እረካለው።ለሞራሏ እገለፍጣለው ።ተጨዋውተን ተለያየን።ግን በውስጤ እየተገረምኩ ነው። ኪታቡንስ ልንተወው ነው? በነጋታው መቅራት እንደምትፈልግ ለማረጋገጥ ብዬ ላስቀራት ብሞክርም ፊቷ ላይ ምንም የመቅራት ፍላጎት ማንበብ አልቻልኩም። ትንሽ ታዘብኳት ግን ደስ ብሎኛል ።ከኔ ጋ ለመሆን ፍላጎት እንዳላት ራሴን አሳመንኩት። ኪታቡም ተረሳ እኔም እሷን በሙሉ አይን ማየት አብዝቻለው።ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ፀጉሯ የመመልከት አቅሙን አግኝቻለው።ግን ከመዳፏና ከፊቷ በቀር ሌላ የሚታይ ቦታ አልነበራትም።ረጅም ጉርድ፣ ካልሲ ትለብሳለች።አይን ትልቅ ተፅዕኖ አለው።ያያል ለልብ ማሳሰቢያ ይሰጣል።ልብ ደሞ ይሸፍታል።አእምሮ ብዙ ነገር ያስባል፣ብዙ ነገር ያቅዳል። አልሀምዱሊላ ከማየት የዘለለ አእምሮዬ ሌላ ምንም አላዘዘኝም። ሁሌም ስትመጣ የምትይዘው ደብተር ነበር ከለታት አንድ ቀን አንዴ ልየው? ብያት የማየት እድሉን ስትሰጠኝ እውስጡ በርካታ የፍቅር ግጥሞችና ከጀርባው ደግሞ ስሟን፣ስልኳን፣ ሆቢዋን፣ ባጠቃላይ ስለሷ ብዙ ኢንፎርሜሽን የሚናገር ፅሁፍ አለ። ጌም ነገር ነው የሚሞላ ። ግጥሞቿ አብዛኞቹ በፍቅር የተጎዳ ሰውን የሚገልፁ ናቸው። በግጥሞቿ አንድ በጣም የምትወደው ሰው እንዳለ ተረድቻለው።ግን ማን ነው? እኒጃ ራሴን በፍፁም አልጠረጥርም ።ከተዋወቅን አመት ሳይሞላን፣ከማውራት በቀር ምንም ነገር ሳናደርግ እንዴት ሊሆን ይችላል?ጠየኳት" እቤት ወስጄ ደብተሩን ላንብብ?" አሷም አለችኝ "ውሰደው በዛውም ሚሞላውን ሙላ " አለችኝ። እኔም ግጥሞቿን አነበብኩ በቃሌም የሸመደድኩት ነበር። በዛውም ሚሞላውን ሞላሁ። በዚ አጋጣሚ ነበር ስልክ የተለዋወጥነው።እንዲ እንዲ እያልን የግቢ ላይፋችንን እያሳለፍን ነው።ግጥም ታነብልኛለች ።እኔ ደሞ ልክ Bed story ይመስል ተመስጬ ሳዳምጣት። እሷ ስጦታ ስታመጣልኝ እኔ ደሞ ልቤን በስጦታ መልክ ስሰጣት።ወሩ ሚያዝያ ነው ።በቀጣይ ወር የ 12 ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወሳጅ ነኝ ። ግን አደለም ስለ ፈተና ላስብ ተማሪ መሆኔን ራሱ ሳልረሳው አልቀርም። አሁን ያስጨነቀኝ ትምርት ቤታችን ለፈተና ዝግጅት እንድናደርግ በሚል ከፈተና አንድ ወር ቀደም ብሎ ነው ትምርት ሚዘጋልን።እሷ 11 ኛ ክፍል ስለ ሆነች እስከ ሰኔ እዚው ትቆያለች።ከዚ ቡሀላ የት አባቴ ነው ማገኛት? ሰፈሯን አቅጠጫውን እንጂ የት እንደሆነ አላቅም።ባውቅስ እንዴት ብዬ ነው ሰፈሯ ምሄደው።የለመድኩት እሷ መጥታ እንደምትወስደኝ ነው።ግራ ገባኝ ።እሷም መለያየታችንን ብታውቅም ምንም ነገር አላለችኝም። 12 ቶች ትምርት ጨርሰን ግቢውን ለቀን ለመውጣት 2 ቀን ሲቀረን እንደሌላው ጊዜ ሜዳ ስር ተቀምጠን ማውራቱን ትተን ከግቢ ወጣን። በበርበሬ ወይምበጨው በረንዳ አርገን አቧቦራ መስጊድን አቋርጠን በኳስ ሜዳ በኩል አድካሚ የሆነ ወክ አድርገን ወደ ጊቢ ገባን።ሁለታችንም ደስተኛ እንመስላለን።የዛኔ የማረሳወ አጋጣሚ ቢኖር ልክ ወካችንን ጨርሰን ግቢ ከመግባታችን በፊት መናኸሪያ አካባቢ አንድ መኪና ሊገጫት ወይም ሊገፈትራት ሞክሮ ነበር።ግን አላህ አተረፋት። ከዛ ቢገጨኝስ ስትል ተከትዬሽ ነበራ ጎማ ውስጥ ምገባው አልኳት።ተገርማ" እነዴለምን? አለችኝ። ወክ እናርግ ብዬ ይዤሽ የወጣሁት እኔ ነኝ ስለዚ አንቺ በመኪና አደጋ ብትሞቺ እኔ እንደገደልኩሽ ነበር ምቆጥረው። ከፀፀቱ ለመዳን አብሬሽ ብሞት እመርጣለው ለማለት ፈልጌ ነበር አባባሌ። ያ ቀን የማጄላንን የመሬት መዞር ታሪክ ያስታወሰኝ ነበር።ደክሞናል እነሱ ክፍል ጀርባ ቆምን።የእኛ ክፍል ተማሪዎች ከሰአት ላለ መማር አድማ አድርገው ከግቢው እየጨፈሩ ወጡ። ከነሱጋ ለመሄድ እየቸኮልኩ s ቻው በቃ፣ስለ ወኩ በጣም አመሰግናለው ደስስስስ ብሎኛል አልኳትና ።እጇን ይዤ የሆነ ፎርሙላ ፃፍኩላት። እኔና እሷ ከተዋወቅን ዛሬ ተሳስቼ በደስታ መንፈስ እጇን ነካኋት።የፎርሙላው ትርጉም ሲፈታ "አፈቅርሻለው" ነበር ሚለው። ምንድነው ስትለኝ ሰው ጠይቀሽም ቢሆን ትርጉሙን ፈልጊው ብያት እንደ ህፃን እያረገኝ ከክፍል ጓደኞቼ ጋ ከግቢው ወጣን
1941Loading...
08
በነጋታው እረፍት ሰአት ሲደወል እየከነፈች ክፍል ድረስ መጥታ ማሜ ኧረ ምን ማለት ነው ንገረኝ አለችኝ።አቤት ቀልብ ስትስብ ትንፋሿ እየተቆራረጠ፣ክንፍ እያለች ፣ፈገግታና ጉጉት በሞላበት ያ ውብ ፊቷ በአይኗ እየተማፀነችኝ ነበር ትርጉሙን የጠየቀችኝ።በሰአቱ ከሁኔታዋ አንፃር ትኩር ብዬ ሳያት አንዲት እናት ያአንድ አመት ህፃን ልጇን አቅፋ በስስት አይን አይኑን እንደምታየውና ወድያና ወዲ እያረገች እንደምታጫውተው እኔም sዬን ባደረኳት ብዬ ተመኘሁ። ትከሻዋን ደገፍ አድርጌ ይዣት ወደ ክፍሏ ግማሽ መንገድ ከሸኘኋት ቡሀላ አርብ ከዚ ትምርት ቤት ስንወጣ እነግርሻለው አልኳት።እንድነግራት በጣም ጓጉታ ስለነበር አልነግርሽም ስላት ሞራሏን ሳልሰብረው አልቀርም።በቀዘቀዘ መንፈስ ሆና ትታኝ ሄደች ።እለቱ አርብ ነው ገና ከጠዋቱ ከቤቴ ሳልወጣ ነበር የዘነበው።መንገዱ ሁላ ጭቃ ሆኖዋል ።ትምርት ቤትም ባልሄድ ያስብላል ።ግን ከምንም በላይ ለsዬ ፍቅሬን ምነግርበት እንዲሁም ትምርትቤታችንን ምንሰናበትበት ቀን ነው። ዲንጋይም ቢዘንብ የመሄድ አቋሜን አልቀይርም!!!!! እየተጓዝኩ ነው ዛሬ ልክ የዛኔ የመጀመሪያ ቀን sዬን ለማግኘት ስጓዝ እንደነበረው አይነት ስሜት እየተሰማኝ ነው። ትምርት ቤት እየተቃረብኩ ሰመጣ በር አካባቢ ብዙ ፖሊሶች ተሰልፈው ቆመዋል።የመኪና መንገዱ ደሞ በተማሪዎች ተጥለቅልቆዋል። ከትርምሱ መሀል ገብቼ ነገሩን ሳጣራ። ፀፀትን ሚያለብስ፣አልቅስ አልቅስ ያስባለኝን፣ብጮህ የሆዴን የእልህ ቃጠሎ የማያሰታግስ የሆነ መርዶ ተነገረኝ ። #ክፍል_7 ✍✍✍ ይቀጥላል
2191Loading...
09
🔻:::::::::::ሚስኪኑ አፍቃሪ::::::::::::🔻 ክፍል 5⃣ት እኔም ፊቴን ወደሷ ሳላዞር አልቀርም። ቀጣዩ ላይፌ ምን ሆነ? ከተሰናበተችኝ ሰአት አንስቶ ሆዴ እየሳቀ ፣የተወዳጅነት ስሜት እየተሰማኝ፣በዛ በሚያስጠላው ፈገግታዬ እየተፍነከነኩ ወደ ዙሁር ሰላት አመራሁ።በነገራችን ስስቅ ሰው እንዳያየኝ እጄን አፌ ላይ አደርጋለው ወይም አነገቴን እደፋለው።ላለ ማስፎገር።ለምዶብኛል። አንዳንዴ ግን እየረሳሁት ሰው ፊት እገለፍጣለው። ወይኔ ካለፈ ቡሀላ እንዴት እንደምሸማቀቅ። ግን እኮ እኔ እንደ ማስጠላ ምንም ማረጋገጫ የለኝም ግን እንዲው ስስቅ ሚያስጠላብኝ ስለሚመስለኝ ነው። ለዚ ሁሉ ምክንያቱ ደሞ ታላቅ እህቴ ናት።ታሪኩ እንዲህ ነው። ይመስለኛል የ15 አመት ጎረምሳ እያለሁ እኔና ሁለት ታላላቅ እህቶቼ አንበሳ ጊቢ ለመዝናናት ሄደን ነበር። እዛ ያሉትን አንበሳና የተለያዩ እንስሶችን እስኪሰለቹን በአይን ከሰለልናቸው ቡሀላ።እንደተለመደው ሴቶች ዛፍና አበባ ባለበት ሁሉ ፎቶ ያምራቸው አደል? ስልካቸው ቦታ እስኪያጥረዉ ድረስ መነሳት ጀመሩ። እኔም ጣል ጣል እየተነሳው ነበር ።በዚህ መሀል ነበር የታላቄን ታላቅ እህቴን አቅፌ ታላቄን አንሽን ብለናት ልታነሳን ስትል ለፎቶው ውበት ብዬ ፈገግ ስል ምን ብትለኝ ጥሩ ነው? እስቲ ገምቱ። ኮስተር በል አንተ ስትስቅ አያምርብህም!!!!! የፈጣሪ ያለህ እንዴት ሞራል ሚሰብር ንግግር ነው።ይኸው ከዛ ጊዜ ጀምሮ በገዛ ጥርሴ እንደ ኪራይ ቤት እየተጠነቀክኩ ነው ምጠቀመው።ወደ ጉዳዬ ስወስዳቹ:-- እስቲ ተከተሉኝ-------------------------------------------------------መስጊድ ደረስኩ። ሰገድኩ።ምሳ ሳልበላ የከሰአት ትምርት ለመማር ክላስ ገባሁ ።አሁን ውስጤ በጣም ረክቶዋል።ልክ በከፍተኛ ጥም ውስጥ ሆኜ ቀዝቃዛ ወሀ እንደጠጣሁ፣ ለቀናት ሳልበላ በድንገት ተመግቤ እንደረካሁ ያህል የመንፈስ እርካታ ይሰማኛል።በዛ መንግስት በሰራው ሰባራ ዴክስ ተቀምጬ በባለ ስልጣን ዙፋን ላይ የተቀመጥኩ ያህል እየተሰማኝ፣አእምሮዬ ቀጣይ በሚያሳልፋቸው ጣፋጭ ጊዜያቶች ምራቅ አያስዋጠኝ በሀሳብ ባህር እያስዋኘኝ ነው።አቤት የባህሩ ጥልቀት!! መጨረሻውን ሳላይ ከሰመጥኩበት ሀሳብ የቀሰቀሰኝ የትምርት ቤቱ ደወል ነው። ደብተሬን ይዤ ሳልማር እንደተማረ፣ሳይገባኝ እንደ ገባው ተማሪ ሆኜ ከተማሪ እኩል ወደ ቤት ለመሄድ ተነሳሁ። ከግቢ ወጥቼ ቀኝ ግራዬን ስመለከት በሁለተኛው በር መግቢያ ዳር ላይ አጅሪት ቆንጂት ጅልባብ ለብሳ ቆማለች። አሁን ነው በባለፈው ከኃላዬ ስትከተለኝ የነበረችውን መላእክት ያየኃት። ዋው በጅልባብ እንዴት እንደምታምር።ይህንን ደግሞ ደጋግሜ ነግሬያታለው።ምናልባት ጅልባብ ለመተው ሀሳብ ከሰነቀች ለሀይማኖቷ ባይሆንም ለውበቷ ስትል እንድትለብስ ብዬ ነበር አነጋገሬ። እሷን ብቻ እያየሁ ባልበላ ባልጠጣ ምመርጥበት ደረጃ ደርሼ ነበር በሰአቱ።ሚስኪን እኮ ነኝ። ውስታዟ መሆኔን ከነ አካቴው ጠፍቶኛል። ሁሉ ነገሬ እሷ ሆናለች። በእጇ የጠብቀኝ ምልክት አሳየችኝ ። አብረን ወደ ቤት እያወራን አመራን ። መንገዱ ለካ እንዲ አጭር ነው ሳላውቀው ሰፈር ደረስን ።መንገድ ላይ አብረን ሆነን ሚያየን ሁሉ አቤት ስታምሩሩሩሩ ሚሉን ወይም ከኃላ በቅናት መንፈስ ማጅራቴን ብለው ሚደፉኝ ነበር የሚመስለኝ። ብቻ ውስጤ ኩራትን ተላብሶ ፣ ቀናም ብዬ በሙሉ አይን ሳላያት መንገዳችን አልቆዋል። ሁለት መንታ መንገድ መገንጠያ ላይ ቆምን ።የሷ ሰፈር በቀኝ መገንጠያ ላይ ባለው መንገድ በኩል ሲሆን የኔ በግራ ባለው ነው። እሺ s ቻው ስላት ።ቻው እሺ ማሜ አለች ። ደስስስ አለኝ ።እንዴት ደስ አይለኝ ማሜ እኮ ነው ያለችኝ። የተወሰኑ እረምጃዎችን ወደኃላ እየተራመድኩ በሚያስጠላው ፈገግታዬና በአይኔ ሸኘኃትና ዞሬ ወደ ቤቴ አመራሁ። የዛን ቀን መኪና ራሱ እንዲ በፍጥነት ሚያደርሰኝ አይመስለኝም።መንገዱ እንዴት አባቱ ነው ያጠረው።ወይስ ፀሀይ ሲመታው እሳት እንደነካው ፌስታል ኩምሽሽ ማለት ጀምሮዋል? የወቀሳ ጥያቄ መንገዱን እየጠየኩት ቤቴ ገባሁ ።ጠግቤ ነበር ምግብም አላሰኘኝም ። ግን እኮ ከቁርስ ቡሀላ ምንም አልቀመስኩም። ካሁን ቡሀላ እኔ ሁለት ሰው ሆኚያለው። ስበላ ፣ሰተኛ፣ስቀራ ፣ስማር፣ስቀመጥ ፣ስቆም በሁሉም ቦታና ጊዜ sዬ አለች። ሲመስለኝ ግን ከጭንቅላቴ ባንዱ ጎን በመንፋስ ጠጋ በል ብላ ሳትቀመጥ አትቀርም። ዋናው ፍቅር ነው ይበቃናል ።ትቀመጥ ለዘላለም።መጃጃል ጀምሬያለው።ብቻዬን ሆኜ ፈጌ መጫር አብዝቻለው። በሀሳብ የህንድ ፊልም ከሷጋ እየሰራሁ ነው። እጆቼን ዘርግቼ እንደ ሻሩክ እያረገኝ ነው። ሰማይ ላይ እየተንሳፈፍኩም ይመስለኛል።ጋንጃ በኦክስጅን መልክ ወስጃለው እንዴ? ግራ ገብቶኛል። የሆነ የሆነ ሰአት ላይ እንደ መባነን ስል ራሴ በራሴ ላይ እስቃለው።አንዴ አንታርቲካ የበረዶ ተራራ ላይ ስንሯሯጥና ልብሷን ንፋስ ፊቴ ላይ ሲያለብሰኝ፣ አንዴ ደግሞ በጣም ንፁህና በጣም አረንጓዴ በሆነ ጀነት ውስጥ ተቀምጠን በፍቅር አለም ቅልጥ ስንል ይታየኛል ።ከዚ በላይ መጃጃል አለ እንዴ?በነጋታው በረፍትና በምሳ ሰአት እክፍሌ ድረስ መጥታ አብረን ከሰው ገለል ምንልበትን ቦታ መርጠን አወራን ፣ተጨዋወትን ።ለካ ከተቃራኒ ፆታ ሲኮን በማያስቅ ይሳቃል?ፍቅር ለካ መጃጃል ነው።የኔና የሷ ክፍል ከግቢው በዳርና በዳር በኩል ስለነበር ትንሽ ይራራቃል።ሁልጊዜም እሷ ነበረች ክፍሌ ድረስ ምትመጣው እኔ ደሞ ያቺ ኮሪደር ላይ ቆሜ እጠብቃታለው። አንድም ቀን ክፍሏ ሄጄ አላውቅም። እኔ እንደምፈራና እሷ ክፍል መምጣት እንደማልችል እነግራት ነበር። እሷም ችግር የለውም ብላኛለች። በቃ ከዚ ቀን አንስቶ ለትምርት ሳይሆን በምሳና በረፍት ሰአት ከሷ ለማውራት ብዬ ብቻ ነበር ምሄደው። ቅዳሜና እሁድን እየጠላሁዋቸው መጣሁ። የተዋወቅነበት ሳምንት አልቆ በቀጣይ ሰኞ ከረፍት ስንወጣ ትመጣለች ብዬ ነበር ።ግን ስለቀረች ከክፍል ወጥቼ ግቢ ውስጥ ወክ ሳረግ ከኃላዬ እየሮጠች መጣች። የመጣችበትን አቅጣጫ ዞሬ ሳይ ባለመነፅሯ ና አንዲት እንደ sዬ ቀጠን ያለች ልጅ ዶናት ቤቱ ፊት ለፊት ቆመዋል ።ከጓደኞቿጋ ዶናት እየበሉ እንደነበር ገመትኩ ።በእጇም ዶናት ይዛ ነበር። እንዴት ነሽ ሰላም ነው? ውይ እነዚ ቃላቶች ሚሸጡ ቢሆን ኖሮ አንደኛ እኔ ነበርኩ በነፃ ማከፋፍለው። ቅዳሜና እሁድ እንዴት እንደረዘመብኝ አልኳት።የውነቴን ነበር። "እኔም" አለች አይን አይኔን እያየች።አፍራታለው፣አከብራታለው በሙሉ አይን አላያትም።በጨረፍታ እያየሁ ጎንበስ ነው ስራዬ።ምክንያቱም ቁራን ቤት እያለሁ በአእምሮዬ የምስላት መላእክት ስለምትመስለኝ።እኔም ያለችው ቃል ግን በረፍት ሰአት ከመቅረቷ ጋር አልስማማ ብሎኛል። እንካ ዶናት ባላህ ስትለኝ እየተቅለሰለሰች። ዛሬ ሰኞ አደል ረሳሽው? ፆመኛ ነኝ አላኳት። ከዚም በፊት ምሳ እንደማልበላ ከነገርኳት ቡሃላ ምሳ ልተጋብዘኝ ስትጠይቀኝ እንደምፈራ ነግሬያት ስለነበር ነው ዛሬ በአላህ ያለችኝ። እሺ ብላኝ እሷም ወደ ጓደኞቿ ተመለሰች እኔም ወደ ፊት አመራሁ።እኔና እሷ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሁነን መስከረም አልቆ፣ጥቅምት ፣ጥቅምት አልቆ ህዳር፣ህዳር አልቆ ታህሳስ ገባ። ይህን ጊዜ ሁላ ስንገናኝ እሷ ነበረች ክፍሌ ድረስ እየመጣች ምትወስደኝ።ረፍት ላይ መምጣት ካቆመች ቆይታለች።የትምህርት ቤታችን ሜዳ ጋ አሪፍ መከለያ ዛፍ ስር ተቀምጠን እሷ በብዛት እያወራችልኝ እኔ በብዛት አንገቴን ደፍቼ ሳደምጣት 3 ወር ገደማ ሞላን።
2250Loading...
10
ይህን ዝምታዬን ጠልታ እንዳትርቀኝ ብዬ እኔም ርእስ እየፈጠርኩ ለማውራት አስብ ነበር።ኧረ መቅሱድንም አማክሬዋለው። ኧረ መቅሱዴ ሚረባ ወሬ ማውራት አልቻልኩም ቅር ይላት ይሆን ብዬ ተጨንቄ ስጠይቀው እሱ ግን አዋራታ ይለኛል እየቀለደ። እዛች ዛፍ ስር ሆነን ስለብዙ የህይወቷ አጋጣሚዎች ተርካልኛለች። ስለ ቤተሰቦቿ ፣ ስለ ሴት ጓደኞቿ፣ከዚ በፊት ስለነበራት የተቃራኒ ፆታ ገጠመኞቿ ወዘተ። ሰሞኑን sዬ መቅረት አብዝታለች እንደ በፊቱ ክፍል አትመጣም ኮሪደሩም ጋ ቆሞ መጠበቅ ሰልችቶኛል። ምክንያቷ አልገባኝም።አስጠልቺያት ይሆን?ሌላ ጓደኛ ያዘች? ወይስ እኔም ክፍሏ ሄጄ እንዳመጣት ፈልጋ ነው? መቅሱዴን አማከርኩት sዬኮ መምጣት አቆመች አልኩት። መፍትሄ ነግሮኝ አያቅም። ከዛ እኔ አንድ አቋም ያዝኩኝ ።ምሳ ሰአት ሲደርስ እሷን ለመርሳት ስል ወደ ቤቴ እየሮጥኩ ልሄድ ከዛ አርፍጄ መጥቼ ክፍል ለመግባት። ምክንያቱም እኔ ኮንፊደንስ የለኝም እኔን ቆሻሻ እሷን ንፁህ መላእክት አርጌ ነበር ምቆጥረው ። ተፀይፋኝ ከሆነ የቀረችው በደንብ ካይኗ ለመራቅ ነበር እቤት እየሄድኩ ያለመደብኝን ምሳ በሰአቱ መብላት የጀመርኩት ።ካየኋት ሳምንት አልፎታል።አቤት የለመዱት ነገር ሲታጣ እንዴት እንደሚያም። እኔ አይናፋርነቴ ይዞኝ እሷ ምክንያቱ ባልታወቀ ነገር ተጠፋፍተን ሳለ ድንገት አንድ ቀን ከምሳ መልስ ክፍሌ አርፍጄ ስገባ አንድ ሁለት የሚሆኑ የክፍሌ ተማሪዎች ማሜ ሚስትህ እየፈለገችህ ነበር ብለው ጮሁ። ባልሰማ ሆኜ ነገሩን ቀለል አርጌና ችላ ብዬ ተውኩት ። ነገር ግን በማግስቱም መቅሱድ ብቻዬን ይዞኝ ነገ እረፍት ላይ በጣም ላገኝህ እፈልግሀለው ብላሀለች ብሎኝ ሄደ። ትንሽ ደነገጥኩ ፣ኩራትም ተሰማኝ። ነገንም ናፈኩኝ። የነገ ሰው ይበለን። #ክፍል_6 .........✍✍ ይቀጥላል
2300Loading...
11
⭐መለያየት ሞት አይደለም!! የሚጥም ፣ ጎርባጣ እለት ተጨማምቆ ሳስታውስሽ ከልብ የተወለደች ውብ ፈገግታ ካስፈገገኝ ፤ እብደታችን ገጠመኙ ዝብዘባችን ተፋፍገው ተጣምረው ካስቀደዱኝ ። አይ እሷ ብዬ ፈግጌ ካስታወስኩሽ በቃ ሌላ ምን አለ የህይወት ትርፉ ትዝታም አይደል ? ሞትማ የተንሰፈሰፉለትን ገላ ፤ የናፈቁትን ነፍስ፤ የኮሩበትን እርምጃ ካጠለሹ ነው ፤ በፍቅር ውስጥ የነበረን ገመና አውላላ ሜዳ ላይ መዘርገፍ መናናቅ ነው! መለያያትማ ተፈጥሮ ነው ገና ነፍሳችንስ ከስጋችን ይለይ የለ ?! እውነት እወድሻለሁ መለያየት ሞቴ የሚሆነው የጠላሁሽ የጣጣልኩሽ እለት ነው።
2510Loading...
12
🔻:::::::::::::ሚስኪኑ አፍቃሪ:::::::::🔻 ✍እዉነታኛ ታሪክ ለይ የተመሰረተ ክፍል 4⃣ት እሺ እንዴት አደራቹ? የኔንስ አጠይቁኝ ። አካሌን ያቺ ስሟ ብቻ ፍራሽ በሆነችዋ ፍራሼ ላይ አጋድሜ፣ አይኔን እንደወንፊት ፀሀይን እያጠለለ በሚያስገባው ጣራችን ተክዬ፣ ጆሮዬን ለአይጦች ሁካታ፣ ለውሾች ጫጫታና ከሩቅ ለሚሰሙ የጅቦች አስፈሪ ድምፅ አውሼ፣ ልቤንና አምሮዬን ደሞ ለ sዬ ሳትጠይቀኝ ሰጥቼ ባዶ እኔነቴን ታቅፌ ነው ያደርኩት።አሁን እንደመጀመሪያ ቀን ባይሆንም በትንሽ ጉጉት ውስጥ ሆኜ በተረጋጋ መንፈስ ዩኒ ፎረሜን ለብሼ ከእቅዴ ጋ ወደ ትምርት ቤት እየሄድኩ ነው። ዛሬ የመጨረሻ እድሌን ምሞክርበት ነው። ከ3ኛ ክፍለ ጊዜ ቡሀላ ለረፍት ተለቀቅን። በእቅዴ መሰረት እኔ ከክፍል ሳልወጣ አንድ በጣም ሚቀርበኝ የክፍል ጓደኛዬን ክፍሏ ድረስ ሄዶ ተዋውቋትና ማንነቷን አጣርቶ እንዲመጣና ከዛ በሩቁ ሊያሳየኝ ላኩት። አሪፍ እቅድ ነዋ ።ለሞራሌም ቢሆን አው በሉኝ።ይህ ልጅ መቅሱድ ይባላል። በጣም ተጫዋች እና ቀልደኛ ልጅ ነበር።በዚ ተጫዋችነቱ ደግሞ ከኔ በበለጠ ሰው የመቅረብና የመግባባት ችሎታ ነበረው። ስለዚ ለተልእኮው ተገቢና ተመራጭ አድረጌዋለው።የማግኔት souse እና north pole ሲቀራረቡ እንደሚሳሳቡት ሁሉ።እሱም ከ ሶስት የትምርት ቤት ሚስቶቹ ጋር እነሱ እንደ souse እሱ እንደ north pole ልብ ለልብ ይሳሳባሉ።(ሰሚራ፣ሀያት እና ሪም ይባላሉ) ሀያት እኛ ሰፈር ናት። ያብራሀም የሳራ ያርግላቸው ብለናል እንግዲ😜የበረሀ አፈር ልክ ውሀ ሲፈስበት በቅፅበት ወደ ውስጡ እንደሚያስገባው ሁሉ እሱም የእንስቶች ልብ ውስጥ የመግባት ችሎታ ሳይኖረው አይቀርም።እሷንም ልቧ ውስጥ ገብቶ ያመጣልኛል የሚል ተሳፋ አድሮብኛል።በሰውነት መጠን ከኔ ቢበልጥም ።በእድሜ ግን አንድ ምንሆን ይመስለኛል።ከሱ ሚገርመኝ እጁ ነው ። በጣም ፈርጣማ ነው። ታፋውን በውሰት ወደ እጅነት ቀይሮት ሳይሆን አይቀርም።እስፖርተኛ ቢመስልም ብዙ ጊዜ እንደማይሰራ አረጋግጦልኛል።ተፈጥሮ የሰጠችው የስፖርተኝነት አቋም ነው።ልኬው ነበር ስሜቴን ስላልተረዳልኝ ይሆን አጣኃት ብሎ እንደቀልድ ነግሮኝ ላሽ አለኝ። አሁን በጣም ሳልናደድ አልቀርም በቃኝ። ካሁን ቡሀላ እሷን በመፈለግ ራሴን አላስጨንቅም።ክፍሌን ነግሪያት አደል ከመጣች ትምጣ ብዬ የወንድነት ባህሪ ለማሳየት ሞከርኩ።ግን ውስጤን አላመንኩትም። ፍለጋ ባቆምም ከክፍሌ ፊለፊት ባለው ኮሪደር መሰጣት የለተለት ተግባሬ ሆኖዋል። ክፍላችን 2ኛ ፎቅ ላይ ስለነበር ።ግቢ ውስጥ ወዲያናወዲ ውር ውር የሚሉ ተማሪዎችን በቀላሉ ለመቃኘት አግዞኝ ነበር።በነገራችን ላይ ኮሪደር ላይ ቆሜ መቆዘም የጀመርኩት በሷ ምክንያት አደለም። ምክንያቱ እንዲህ ነው።; መግቢያ ላይ እንደ ነገርኳቹ ክረምት ላይ አንድ አዳሪ ቁራን ቤት ገብቼ ነበር። ሂፍዙን በ2 ወር መጨረስ ስላልቻልኩ with draw ሞልቼ ላንድ አመት ለማቋረጥ ብዬ አባቴ በግድ ተማር ስላለኝ በጣም አዝኜ ለተወሰኑ ጊዜያት ትምርት ቤት ውስጥ ከማንም አላወራም ብዬ እቆዝም ነበር። በዛ ምክንያት ነበር ያቺን ኮሪደር የተቆጣጠርኳት።ቢሆንም ከጊዜያት ቡሀላ ወደ ትምርቱ ሙድ እየገባሁ መጣሁ።ግን ማጥናት ሚባል ነገር ያስጠላኝ 12 ኛ ክፍል ነው። ምክንያቱም ክረምት ላይ የጀመርኩትን ሂፍዝ ቀንና አዳር ሆኜ መከታተል ቢያቅተኝም ። በ 15 ቀን አንዴ እየሄድኩ ላዛልቀው ቆርጬ ስለነበር ነው። ትምርት ቤት እገባ ነበር እንጂ አልማርም ነበር።ከትምርት በፊትና በትምርት መልስ ለ 15 ቀኑ በጣም እዘጋጅ ነበር። ለማንኛውም ይህቺን ኮሪደር ሳልሰለቻት አልቀርም ረፍት ወጣሁ ፣ምሳ ወጣሁ ቀላል ላልተባለ ሰአት እሷ ላይ ሆኜ በአይኔ ወደ ታች ሳማትር አሳልፋለው።በ2ኛው ወይም በ3ኛው ቀን ይመስለኛል ለምሳ በተለቀቅንበት እዛችው ቦታዬ ላይ ሆኜ ወደታች ሳይ ነበር።በሰአቱ አብዛኛው ተማሪ ለምሳ ወደ ቤቱና ወደ ሚሄድበት ስለሄደ ግቢው በከፊል ጭርታን ተላብሶ ነበር።ጣል ጣል ሚመላለስ ተማሪ እንጂ ትርምስ አልነበረም ።በዚህም የተነሳ እኔ እዛ ከፍታ ላይ ሆኜ ስመለከት አንድ ሰው ሁለቴ ከተመላለሰ ይህ ሰው ሁለተኛው ነው እያልኩ ምለይበት ደረጃ ላይ ነበር። እና በዚ ሁኔታ ነበር ሁለት ሴቶች አንዷ መካከለኛ ውፍረት ያላትና ምንፅር የለበሰች ስትሆን ።አንዷ ደግሞ ቀጠን ያለች ከዩኒፎርሟ ውጪ ምንም መለዮ ያላየሁባት ስትሆን ግን በጣም ለየት ያለ የሚመስል አረማመድ ምትራመድ ልጅ ናት።እነዚ ልጆች አንዴ እኔ ወዳለሁበት ፎቅ ground ስር ይገባሉ ሲላቸው ፊለፊት ወዳለውchemistry labratory ክፍል አካባቢ ይሄዳሉ። እንዲ እያሉ አንድ ሶስት ጊዜ ያህል ከተመላለሱ ቡሀላ።በመጨረሻ እኔ ወዳለሁበት ፎቅ ግራውንድ ስር ገቡ። አኔ ከላይ ስላለሁ ግራውንድ ስር ምን እነደሚሰሩ ስለማይታየኝ አሁንም ደግመው መውጣታቸውን በአይኔ እየጠበኩ ነው።ግን ቆዩ ተመልሰው አልወጡም እይታዬን ወደሌላ ቦታ አርጌ መቆዘሜን ቀጠልኩ ።አላሳዝንም ምሳ ኮ አልበላሁም። ለነገሩ እኔ ምሳ ምበላው ብዙ ጊዜ 9 ሰአት ስንለቀቅ ነው። እናም እነዚ ሴቶች ብዙም ሳይቆዩ አንዷ ቀጠን ያለችዋ።ወይም ለየት ያለ አረማመድ ያላት ልጅ ለካ ከኃላዬ ተደንቅራለች። እኔ ሚስኪኑ ከታች አይኔን ተክዬ ፈዝዣለው።አላየኃትም። ደስ በሚል ድምፅ አሰላሙ አለይኩም አለችኝ። መልስ ሰጥቼያት ዞር ብዬ ሳያት ያቺ ናት ውር ውረ ስትል የነበረችው።ቀጠለችና መሀመድ ነህ ?አለችኝ። ሳልመልስላት አንዴ የውሸት ሳቅ ሳቅኩና። አው s ነሻ አልኳት። ለምን እንደሳኩ ታቃላቹ ቅድም ሳያት ገምቼ ነበር።ለነገሩ አያስቅም ።ወሬ ጠፍቶብኛል።እንዴት ነሽ? ሰላም ነው? ምጠላቸው ቃላቶች። የተወሰነ አወራን።የውነት ይሁን የውሸት አላቅም ተሳሳቅን። የዛን ቀን ካለችኝ ነገር ማረሳው "ያባታችን ስምኮ አንድ ነው" አለችኝ።ፋዘር ተደብቆ ሌላ አግብቶ ወልዶሽ እንዳይሆን አልኳት ። በምን እድሌ ብላኝ አረፈችው።እንዴ ወንድምና እህት ልንሆን? ብዬ ጮህኩኝ ግን በሆዴ ነበር የጮህኩት። የኔም የሷም አባት ስማቸው አብዱራህማን ነው። ያቺ ባለ መነፅሯ እየጠበቀቻት ስለ ነበር ተዋውቀን መልኳን አይቻት ፣እንደምንገናኝ ነግራኝ ተለያየን። ካሁን ቡሀላ ምን ይሆን የዚህ ትምርት ቤት ቆይታዬ? እኔ ማለት በተማሪዎች እይታ ስታይ ጨዋ ቢጤ ፣ከተቃራኒ ፆታ ቁጥብ የሆንኩ፣ለትምርት ቤቱ ጀመአ ለአሚርነት ምፈለግ፣መስገጃ ቦታ ቀድሜ እየተገኘሁ መሰገጃ ማዘጋጅ አይነት ነኝ። አሁን ከ sዬ ጋ እንዴት ልሆን ነው። አእምሮዬ ሌላ ስራ ጀምሮዋል ብዙ ጥያቄ ይጠይቀኛል። ከሷ ጋ ግቢ ውስጥ ከታየህ ቁራን ቤት ምታስቀራቸው ሴቶች ያዩሀል፣አላህ ይቆጣሀል፣ ሰላት ወቅት ያልፍሃል።እኔ ግነ አሻፈረኝ ብዬ እሷን መረጥኩ። የዚኔ ይመስለኛል ሽንፈቴ የጀመረው። አላህም እንዲህ ብሎ አደል የተናገረው " እነሆ ወደ ዞሩበት እናዞራቸዋለን" እኔም ፊቴን ወደሷ ሳላዞር አልቀርም። ቀጣዩ ላይፌ ምን ሆነ? #ክፍል_5 ✍✍ ይቀጥላል..
2250Loading...
13
ፍቅር እና ቁጥር ስንግባባ ሰሞን እኔ መላመድን ለማምለጥ የምባትል ባተሌ ነበርኩ። የተጣመርኩት ባይኖርም ራሴን ብቻዬን እወደዋለሁ። የማልደራደርበት ማንነት ነበረኝ። ሌሎችን የማደንቅበትና የማከብርበት የማንነት መለኪያያዎችም ነበሩኝ። እሱ ---- አላውቅም የሱን ፍላጎት........ ብቻ አላጣደፈኝም። የተለየ ፍላጎት እንዳለውም ሊያሳየኝ አልተፍጨረጨረም። የሰው ፍላጎት እና ሀሳብ ሲጫንብኝ እንደማልወድ ገብቶታል። ማባበሉ አጥንቶ የቀመረበት ነበር። ጆሮዬ ከአንዴም ሁለቴ ከድቶኛል እና በተቆለጳጰሰ የፍቅር ዓረፍተ ነገር የሚደነግጥ ልብ እንደሌለኝ አውቋል። ቀስ በቀስ ለፍፅምና የተጠጋ እሱነቱን ነው የጋተኝ። በገንዘብ ተተምነው ውድ የሆኑ ስጦታዎች እየገዛ አይደለም ያቀበጠኝ፤ በአንድ አንጎል የምናስብ እስኪመስለኝ ድረስ የሚያስፈልገኝን እና ለልቤ የቀረቡ ስጦታዎችን ነበር የሰጠኝ። ውደጂኝ አላለኝም። እንድወደው ምንም አስተዋፅኦ እንዳላደረገ ዓይነት፣ .....የቀን ተቀን እሱነቱን እየኖረ እንደሆነ ዓይነት ፣....... እኔን ለመማረክ የጨመረው ምናምኒት ትጋት እንደሌለ ፣.......... ለሃጬ እስኪዝረበረብ በሱሱ ለመተብተቤ ያበረከተው ምንም እንደሌለ ሁላ ......ከደሙ ነፃ ነኝ...... እኔ የእለት ተእለት እኔነቴን ነው የኖርኩት ዓይነት እጁን ተለቀለቀ። የሰው ልጅ አዘቦታዊ ማንነት እንዴት እንዲህ እንከን አልባ ይሆናል ብዬ አልጠየቅኩም። በየእለቱ እየገለጠ ያስነበበኝን የማንነቱን ምሰሶዎች ሰብስቤ እሱ ነው ያልኩትን እሱን በልቤ ገነባሁ ፣ በአዕምሮዬ ሳልኩ። ለዚህ ማንነት እጅ ሰጠሁ። እዚህ ጊዜ ላይ ፍቅሩን ፣ ጊዜውን ፣ ጆሮውን ፣ ልቡን ፣ ገላውን ፣ትኩረቱን ያልሰጠኝ የለም። 100% እሱነቱን ያለስስት ነበር የሰጠኝ። እስክበስል ማገዶ እንደምፈጅ ገብቶታል። አልተጣደፈም። ከሞከኩኝ ኋላ እስክበሰብስ እንደምታሽ ገብቶታል። ሱሴ የሆነ ጊዜ ላይ ....... ያለእርሱ ትንፋሽ እንደሚያጥረኝ የገባው ሰዓት ላይ ....... የሂሳብ ቀመሩን ይጫወት ጀመረ። ቀስ በቀስ ከመቶ እሱነቱ ይገምሰው ገባ። ፍቅሩንም ጊዜውንም ጆሮውኑም ልቡንም ገላውንም ትኩረቱንም በግማሽ ቦደሰው። 50% !! ልቤ የምትደገፈው ምርኩዝ ስታስስ የነጠቀኝን ትንሽ ይጨምርበታል። 75%!! ........ ጨዋታው ይሄ ነው። 100 እንደነበር ይጠፋኛል። ካጣሁት ግማሽ ይልቅ የተጨመረልኝ እሩብ ያስቦርቀኛል። ልቤ መልሳ እሱን ማምለኳን ትቀጥላለች። መልሶ ከ75% ወደ 25% ሲወርድብኝ የአየር ቧንቧዬ የጠበበ ያህል ደረቴን ያፍነኛል። መልሶ 25% እሱን ይጨምርልኛል። ግማሽ እሱነቱን እንደነሳኝ አላላዝንም። የጨመረልኝ ያስደንሰኛል። አንድ ቀን ገላውን ለሌላ ሴት አዋሰብኝ። እዚህ ጊዜ ላይ ከሙሉ እሱነቱ 5% ፐርሰንቱን እንኳን አልሰጠኝም። በብዙ ትዕግስት እና ጥበብ ውስጤ የገነባው እሱነቱ ግን አሁንም አልተገመሰም። ወይም በቀላሉ እንዳይፈርስ አድርጎ ከዓለት ገንብቶታል። ወይም ማመን አልፈልግም። ፍንክች አይልም። አልካደኝም። በእንባ ታጅቦ ይቅርታ ጠየቀኝ። ይቅርታውን በአግቢኝ ጥያቄ እና ቀለበት አጀበው። የምለው ገባችሁ? ከአምስት 25% ነዳው አይደል? ያደረገውን ሳይሆን ያደረገልኝን እያሰብኩ ተፍለቀለቅኩ። ስለሚወደኝ አይደል አዳራሽ ሙሉ ህዝብ ጠርቶ ፕሮፖዝ ያደረገኝ? ሶስት ቀን የት እንዳለ እንኳን ሳይነግረኝ ዘግቶኝ ይከርምና በአራተኛው ቀን ለእናቴ ከክርስታል የተሰራ የአበባ ማስቀመጫ ገዝቶ ከች ይላል። ሶስቱን ቀን ረስቼ ለእናቴ ላሳያት ፍቅር እሸነፋለሁ። እሱ ከሚያሳየኝ የዘቀጠ ማንነት ይልቅ በልቤ ያነገስኩት ማነነት ላይ ሙጭጭ አልኩ። በሂሳብ ቀመሩ ተወናበድኩ። የእሱን ስዕል ከልቤ ከማፍረሴ ብዙ ቀን ቀድሞ እኔ ፈረስኩ። የእሱን እውነተኛ ማንነት አምኜ ከመቀበሌ ከብዙ ቀናት ቀድሞ የራሴ ማንነት ጠፋኝ። መላመድን ላመልጠው የምሸመጥጥ አትሌት አልነበርኩ? እሱ ከልቤም ከህይወቴም ሲወጣ ለመሮጥም ለማምለጥም ለማሰብም የተረፈ አቅም አልነበረኝም። ** ** ***** ውብ ቀን ውብኛ ዋሉልኝማ!!♥️❤️♥️❤️ ሜሪ ፈለቀ
2261Loading...
14

15
🔻:::::::ሚስኪኑ አፍቃሪ:::::::::🔻 ፀሀፊ መሀመድ✍✍ ክፍል 3⃣ት ማይደረስ የለምና ደረስኩ።ገባሁ። ቆይ ቆይ ከመግባቴ በፊት አንዳንድ ነገር ላውጋቹ።አካላቹን እዚው ትምርት ቤት በር ጋ አድርጉና።በመንፈስ ተከተሉኝ። እኔ መሀመድ እባላለው።ማሜ ሲሉኝ ደስ ይለኛል። ማምዬ ሲሉኝማ ተውኝ ጮቤ ነው ምረግጠው በተለይ sዬ። ድምፅ አልባ ሳቅ ይተናነቀኛል። ካባቴ አብዱራህማንና ከናቴ አስማ በ 1988 በ 8ኛ ወር ቀራኒዮ ክፍለ (ከተማ ባንዲት ሰላሳ ብር አባቴ በተከራያት ጠባብ ቤት ውስጥ ያለ ችግር እንዲው ይህን አለም ተቀላቀልኩ።አሁን ከብዙ የህወት መንገዶች ቡሀላ የ 12 ኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ትምህረቴን ከጀመርኩ አስራ ምናምን ቀኖች ተቆጥረዋል። ይኸው ትምርት ቤት በር ላይ ነኝ።ስለተዋወቅን ደስ ብሎኛል😜። ያቺ መላእክት ደሞ ሰሟን መናገር ባልፈልግም ፣ የ fb ስሟ Hilwan, የ viber ደሞ Sitra, የ whats app ግን Eman ይመስለኛል ።እርግጠኛ አደለሁም። ደሞ ፈልጓት አሏቹ። አታፍሩምኮ። መቼም አታገኟትም።ካሁን ቡሀላ "S"ዬ ብዬ ነው ስለሷ ማወጋቹ። ያው ትክክለኛ ስሟ በ s ስለሚጀምር ነው። ያው እንደነገርኳቹ አይናፉርና፣ሴትን ልጅ ከማክበር ይሁን ከመውደድ የተነሳ አላቅም ለሴት በጣም እሽቆጠቆጥ የነበረበት ጊዜ ነበር። በሉ እንግባ።ገባሁ። ውስጤ ብዙ ነገር እያሰበ ነው። እሷን ስፈልግ ከ ሩቅ ሆና ብታየኝስ? ግን እንዳሰብኳት መላእክት ተሆን ይሆን?ደሞ ካገኘኋት ቡሀላ ምንድነው ምላት? ያለ መጋረጃ ላናግራት ነው? እያልኩ ከራሴ ጋር እየተወዛገብኩ ወደ ጊቢው ስዘልቅ ተማሪዎች የዜግነት ክብር ብለው ሁሉም ወደየ ክፍላቸው እየገቡ ነው። s ዬን ምፈልግበት ጊዜ በማጣቴ እየተበሳጨሁ ወደ ክፍሌ አመራሁ። እረፍት ሰአት እየጠበኩ ነው። ተደወለ እየሮጥኩ ወዳለችበት ክፍል ሄድኩ ግን አንድ መቶ ሜትር ያክል ሲቀረኝ እግሮቼ ከዱኝ።መሄድ አቆሙ ።አንድ ጥግ ይዤ ወደ ክፍሏ አቅጣጫ እየተመለከትኩ ነው።ብዙ ቆንጆ ሴቶች ተከታትለው ለረፍት ይወጣሉ።እቺ ትሆን እቺ ትሆን እያልኩ እንደ ፓርቲ እጩ ስመራርጥ የረፍት ሰአት አልቆ ተደወለና ፊቴ እንደኮሰሰ ወደ ክፍል ገባሁ። ምሳ ሰአት ደረሰ ፈለኩአት ፈለኩዋት ግን የህልም እንጀራ ሆነችብኝ። እኔ እሷ ሳታየኝ ለማየት ነው እንጂ ክፍሏ ብሄድኮ አገኛት ነበር።ምን ዋጋ አለው ፈሪ ነኝ፣ውስታዟ ነኝ፣ባይ ዘዌ ውስታዝ ስላቹ እውነት ሆኜ እንዳይመስላቹ። እነሱ እንደዛ እያሉ ስለሚጠሩን ነው። እኛም አምነን ተቀብለናል። ያ ሁሉ እንቅልፌን ያጣሁለትን ቀን ፣እንዲደርስ የቋመጥኩለትን ቀን እንዲው እሷን ፍለጋ ስባዝን አለቀ።ግን እሷም እንደኔ እየፈለገችኝ ነበር ይሆን? እኒጃ አላህ ይወቀው።ወደ ቤት ተለቀቅን ተስፋ ስቆርጥ ደብተሬን ጨምድጄ ይዤ ጉዞ ወደ ቤት ተያያዝኩት።ብዙ ጊዜ ብቻየን ነው ምሄደው።በነገራችን ላይ ብቸኝነት በጣም እወዳለው።ከራሴ ጋር ማውራት አበዛለው። የመንገዴን ሩቡን የህል ከተጓዝኩ ቡሀላ አጋጣሚ የሆነ የመኪና ድምፅ ሰምቼ ወደ ኃላ ስዞር። ከኔ በ 5 ርምጃ ርቀት ላይ ሆና ምትከተለኝ ውብ ልጅ አየሁ። በቅፅበት ነበር ፊቴን የመለስኩት።አላህኮ ይፈጥራል። ምን ይሳነዋል። ጅልባብ ለብሳለች፣ የፊቷ ቅላት ከጅልባቧ ደማቅ ጥቁረት ጋር ተደማምሮ የፊቷን ኑር አጉልቶታል። ቀጠን የለች ፣ፊቷ ሞላ ያለ። ቁመቷ አጭርም ረጅምም ማትባል መካከለኛ ናት።በቅፅበት ስለሆነ ያየኃት ብዙ ነገር ማለት አልችልም።ደግሜ መዞር እንኳ አልቻልኩም። ደነገጥኩ እሷ ትሆን? እኒጃ። ግራ ገባኝ ዞሬ ላናገራት? እሷ ባትሆንስ? ከራሴ ጋ መከራከር ጀመርኩ ድጋሚ መዞር አቃተኝ። እኔ መንገዴን ተያያዝኩት እሷም መከተሏን ቀጠለች።አንድ ሀሳብ መጣልኝ ። የመንገዱን ጥግ ይዤ ልሄድ ከዛ ፍጥነቴን ልቀንስ ወዲያው ወደ ዳር ወጣሁ ዝግ አልኩ። ግን እሷም ከኔ በእኩል አቅጣጫ ሆነች እንጂ ቀድማኝ ሄዳ በደንብ የማየት እድሉን አልሰጠችኝም። ያን ቀን ሳይሳካልኝ አለፈ ቤቴ ገባሁ በሩን ያለ ጥፋቱ ሳንጓጓው፣ የበላሁበትን ሳህን ወዲያና ወዲ ስወረውር ምክንያቴ እሷን አለማግኘቴ ነበር። ለነገ አዲስ እቅድ እያቀድኩ ነው።እንዴት ልወቃት፣እንዴትስ ላናግራት? አንድ ሀሳብ መጣልኝ አሪፍ ሳይሆን አይቀርም።አይ ማሜ አንተኮ አታስብ እያለ ያሞግሰኛል ።ማን? እንዳትሉ። ከራሴጋ ነው። ማወራው። ምን ይሆን እቅዱ? አብረን ምናየው ይሆናል። #ክፍል_4 ✍✍✍ ይቀጥላል#
2071Loading...
16
Media files
2580Loading...
17
Media files
10Loading...
18
🔻::::::::::: ሚስኪኑ አፍቃሪ::::::::::🔻 ክፍል 2⃣ት ✍ፀሀፊ:- መሀመድ, محمد، Mohammed የዚህን ጊዜ ነበር አንዲት ልጅ መጥታ በመጋረጃው አድርጋ በጆርዬ አንድ ነገር ሹክ ያለችኝ። ምን ይሆን? የሰማሁትን ድምፅ ማመን አቃተኝ፣ለምን አያቅተኝ ይህች ልጅ እኮ እዛ ካሉ ሴቶች ሁሉ እኔና ቶፊቅ ከሚባለው በላይ የምናከብራት፣የምንወዳት፣በጣም ርጋታ የተላበሰች ። ለቁራን ቤቱ ደሞ እንደ አለቃ ነበረች። በመልክ ስለማናቃት እኔም ቶፊቄም ትልቅና ና እድሜዋ ከፍ ያለ ይመስለን ነበር። ሁልጊዜ ስለሷ እየተደመምን እናወራለን።ቁራን ላይ ደከም ያለች ቢሆንም ግን በቁራን ቤቱ ላይ ለሚደረጉ ማንኛውም ተግባራት ግንባር ቀደም ነበረች። ይህ ጉጉቷ በጣም ያስቀናን ነበር። በአይነ ህሊናዬ መልኳን ስስለው አላህ ይህችን ልጅ ከዩሱፍ መልክ በትልቁ ዝቆ ያፈሰሰባት ያህል ውብ ሆና ትታየኛለች። በዛ ላይ አንዳንዴ እዛው ቁራን ቤት ውስጥ ራሷን ስታ ትወድቅ ነበር። በምትወድቅበት ገዜ ደግሞ የማቃሰት ድምፅ ታሰማ ነበር።እንዲህ ትል ነበር"እባክህን አትነቀኝ ፣አትግደለኝ ፣እባክህን እባክህን"ትላለች። ይመስለኛል ሲህር (ድግምት) ነው። እውነቴን ነው ይህን ድመፅ ስሰማ ምሆነው እስኪጠፋኝ ድረስ ይጨንቀኝ ነበር፣ አልቅስ አልቅስ ይለኝ ነበር። አንጀቴን እንክት አርጋ ትበላው ነበር። ሰው ምንም ለማያቃት ሴት እንዲ ይሆናል??? አያድርስ ነው።ደሞ በጥሩ ጎኗ እንደምቀናባት ሁሉ ላለባት ህመምና ቁራን ለሚከብዳት ነገር በጣም ታሳዝነኝ ነበር። ወንድ ልጅ ሲያፈቅር ታሳዝነኛለች በሚል ማባበያ ሊያስቀይስ ይሞክራል።እኔም እንደዛ ሳይሆን አይቀርም። ታድያ የሰማሁትን ለስላሳ ድምፅ: አለ አደል ባልሰማ ሙድ ሆኜ ድምፁን አስደገምኩት። ምን? አልኳት ደገመችው ።"well come ሳትለኝ "አለችኝ ። የምን well come ? እኔ ነኝ እሷ well come መባል ያለበት? ጠየኳት ።እሷም ቀጠለች "አናንተ ትምርት ቤት ገባሁ እኮ well come ሳትለኝ" ብላኝ አረፈችው።ውስጤ ሀሴት ሞላው ፣ደሰሰሰሰሰ አለኝ። ይገርማል አንዳንዴ ስለሷ ሳስብ ምናለ አንድ ጊዜ መጋረጃውን ገልቤ ባያት እል ነበር። ነበር አሁን ጭራሽ ትምርት ቤቴ መጣች። ያለ ምንም ግርዶሽ ፣ያለ ማንም ከልካይ ከጠዋት እስከ ዘጠኝ ሰአት ላያት ፣ባይኔ ልመገባት እደጃፌ ድረስ አመጣልኝ። ቁራን ቤት መሆኔን ረሳሁት ነገ ደርሶ እስካያት ቋመጥኩ። ነገ ሚባለው ቀን እንዴት እንደናፈቀኝ እኔ ነኝ ማቀው።ለጥያቄዋ መልስ የሚሆን አንድ ነገር ነገርኳት ።እንዴ አስረኛ ክፍል ነበርሽ? የት ነበር ምትማሪው? ወደ አስራ አንድ አለፍሽ? እኛ ትምርት ቤት 11 እና 12 ብቻ ነው ያለው። ማትሪክ ያለፉ ተማሪዎች ወደኛ ጋ ነው ሚመደቡት። እሷም እንደዛ ነው የተመደበችው። ቀጠልኩና እንዲህ አልኳት። "እኔኮ ባካል አላቅሽም፣ ደሞ ማትሪክ ተፈታኝ እንደሆንሽ አላቅም ነበር"።እሷም ቀጠለችና "እኔም እኮ ባካል አላቅህም" አለችኝ ባላምናትም አመንኳት። እኛ ትምርት ቤት 11 እና 12 ኛ ክፍል 26 26 ሴክሽኖች ስለነበሩ እሷን ለማግኘት እንዲቀለኝ ሴክሽን ስንት ደረሰሽ አልኳት። ነገረችኝ። አገኝሻለው አልኳት። ያንተስ? ስትለኝ ክው አልኩ ። የተፈላጊነት ስሜት ተሰማኝ።ተግደረደርኩ ዝም አልኳት ።ደገመችው ያንተስ? ዝም ያንተስ? ዝም ።ውስታዝ ያንተን አትነግረኝም? አልቻልኩም ነግሬያት ከቁራን ቤቱ እግሬ አውጪኝ ብዬ ወጣሁ። ውስጤ ፍርሀት ፣ደስታ ፣ ጭንቀት እተፈራረቁ እበጠበጡኝ ነው። ነገ ሚባለው ቀን ታክሲ አጥቶ ነው እንዲ የቆየው ወይስ መንገድ ስቶ አልፎኝ ነው። ብቻዬን ሆኜ መፈላሰፍ ጀምሪያለው።ትንሽ እብደት ቢጤ ሳይጀምረኝ አይቀርም።ነጋ የተፈጥሮ ነገር ነውና ሳይነጋ አልቀረም። ልቤ ትላንት ነው ትምርት ቤት የሄደው ለዛውም ያለ ክፍሉ ወደ ልጅቷ ክፍል ገብቶ እየጠበቃት ነው። ዩኒ ፎርሜን ለብሼ ልቤ ራቆቱን ቢሄድም አካሌን ቀይ በጥቁር ዩኒፎረሜን አልብሼዉ በደመነፍስ ወደ ትምርት ቤት አቀናሁ። ልማር ይሁን እሷን ልፈልግ አልገባኝም አካሄዴ። ግን ዝም ብዬ እየሄድኩ ነው። ከተማው በሰው ይተራመሳል እኔ ግን ጭር ባለ በረሀ ውስጥ ብቻዬን ያቺን መላእክት እያሰብኩ እየሄድኩ ነበር። ከቤት ትምርት ቤት 20 ደቂቃ ቢሆንም 20 ቀን ራሱ እንዲ ረዝሞብኝ አያቅም። ማይደረስ የለምና ደረስኩ ፣ገባሁ #ክፍል_3 ✍✍ይቀጥላል👇 #ሼር በማድረግ ያስተላልፉ
2701Loading...
19
❤️ሚስኪኑ አፍቃሪ❤️ ➡️እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ✍ፀሀፊ:- መሀመድ, محمد،Mohammed ርእሱን ሚስኪኑ ብዬዋለው። ይገልፀዋል።ሚስኪኑ እኔው ነኝ ።ባዩም እኔው ነኝ። ወቅቱ ክረምት ነው።ሂፍዝ ማእከል ገብቼ የወጣሁበት ። ይህን ክረምት ትንሽ ላቆየውና 6 ወር ገደማ ወደ ሀኀላ ልመልሳቹ።እና እላቹዋለው 11 ኛ ክፍል ተማሪ ሳለሁ የቁርአን ቤት የሴቶች ውስታዝ ጠፍቶ ። አስቀሪ እስኪገኝ በሚል አሚራችን እኔንና አንድ ጓደኛዬን ገብተን ቦታውን እንድንሸፍንና ሴቶቹ እንዳይበተኑ የበኩላችንን እንድናደርግ አዘዘን። መቼም የአሚር ትዛዝ ነውና እምቢ አንል። ለነገሩ እኔም ደስተኛ ነበርኩ በትዛዙ። ምክንያቱን አላህ ይወቀው ። ከዛ በፊት እኔ ማለት አደለም ብዙ ሴቶች ባሉበት ማውራት አደለም አንድ ሴት ስትነካኝ እንደ ኢትዮፕያ ብርቅዬ እንስሳ ምበረግግ ደናባራ ነበርኩ። ሴት ማለት ለኔ ወንዶች ላይ ያሉ እንደ መብላት መጠጣት መሽናት መናፈጥ መቆሸሽ ምናም ን የሚባሉ እንከኖች የሌሉባት መላእክት አርጌ ማይ ሚስኪን ወጠጤ ነበርኩ።ለነገሩ አይፈረድብኝም አስተዳደጌ ነው። እናም ይህን ባህሪ ይዤ ነበር ዘላለም ማረሳውን ድራማ የተሰራብኝ። አሁን 11ኛ ክፍል ሁለተኛ ሴሚስተር ነው ።ከትምርት መልስ የታዘዝንበት ቁራን ቤት ከአስር ቡሀላ እየተርበተበትን ገባን። ጓደኛዬ ደፋር ቢጤ ስለነበር የኛ መምጣት ምክንያቱን በዝርዝር ነገራቸው። ላልተወሰነ ጊዜም ከኛ ጋር እንደሚቆዩ ነግሯቸው ለነገ ቀጥረናቸው ተለያየን።አልሀምዱሊላህ ነገሩ በመጋረጃ ስለነበር ብዙም አላስፈራኝም ይገርማል ያን ለት አይምሮዬ ሁሉ ባራቱም አቅጣጫ ስለነሱ በማሰብ ተጠምዶ ነበር ሳልበላ የጠገብኩበት፣ሳልጠጣ በጥም የረካሁበት፣ ፊቴ እንደ መስከረም አደይ አበባ የፈካበት ቀን ነበር ። የነገ ሰው ይበለን ማይደርስ የለምና ማስቀራት የጀመርንበት እነሆ ሁለተኛው ዙር ደረሰ ።እኔማ አካሌ ነው እንጂ ከትላንት ጀምሮ ከዚ ቁራን ቤት አልወጣሁም ነበር። የሴት ጥማት አለብህ ለዛ ነው ብትሉ አይገርመኝም። ምክንያቱም እኔ አልፈጠርኩት ፈጣሪ የሰጠኝ ተፈጥሮ ነው።ደሞ ሴት ብወድ: ሴት እናቴ ናት፣ሴት እህቴ ናት፣ሴት ሀገሬ ናት ።ሊያኮራኝ እንጂ ላፍር አይገባኝም።አብሮኝ የተመደበውን ልጅ ትንሽ ላስተዋውቃቹ እስቲ። ተውፊቅ ይባላል። በቁመቱ አጠር ያለ፣ቀይ ፣ፈገግታው ሚያምር፣ ደፋር ና በራስ መተማመን የተቸረው ገና አስራዎቹ እድሜ ላይ ያለ ልጅ ነው። የአስረኛ ክፍል ውጤት ስላልመጣለት ፊቱን ወደ ስራ አለም አዙሮዋል። እሱ ከኔ ሚለየው እኔ በነገራቶች ላይ ችላተኛ ስሆን እሱ ግን ባመነበት ነገር ላይ አልሸነፍ ባይ ነው። በጣም ማደንቅለት ባህሪ ነው። እሺ ይህን ያህል ስለሱ ከነገርኳቹ።በሁለተኛው ቀን የሴቶቹን ስም ዝርዝር ወስደን ወደመጣንለት አላማ ገባን።በዚህ ሁኔታ ቀኖች እየተቆጠሩ ፣ወሮች እየሆኑ መጡ።የኛና የሴቶቹ እድሜ የተቀራረበ በመሆኑ ይመስለኛል በጣም ተጣጥመናል። በጣሙን ተቀራርበናል።ከማስቀራት አልፎ ነገሩ ወደ መተዋውቅና ስለ ግል ጉዳይ ማውጋት ተያይዘነዋል። ሚገረመው መንገዱን ከፋቾቹ ሴቶቹ መሆናቸው ነው። ምን ጉዳይ እንዳለበት ሰው ድመፇን አለስልሳ ውስታዝ እነዲ ሆኜ እንዲ ሆኜ እያለች የውስጧን አውግታኝ አንጀቴን እየበላችኝ እንዴት አልፈተን።ለማንኛውም አሁን በጋው አልቆ ክረምት ሊገባ ቀናቶች ብቻ ነው የቀረው። እኔና ቶፊቄ ሁሉንም ማለት ይቻላል ባካል ባይሆንም በድምፅና በባህሪ ለይተን አውቀናቸዋል።እነሱ ግን በመልክም ጭምር ያቁናል። ከነዚ መሀከል በጣም የወደድናቸው እንዳሉ ሁሉ በጣም የሚጠላ ባህሪም የነበራቸው ነበሩ።ሚገርመው ነገር እኔ ለዚ ክረምት አዳሪ የቁራን ትምርት ቤት ለመግባት ስለተገደድኩ ይህን ከተቃራኒ ፆታዎቼ ጋር የነበረኝ ጣፋጭ ግንኙነት ለማቆም ተገደድኩ።በጣም እየናፈቁኝ ሳልሰናበታቸው ካዲሳበባ ወደ ኦሮሚያ ክልል አቀናሁ። እዛ ሆኜ ፍቅር ይመስል ይናፍቁኝ ነበር።ሚገርምኮ ነው ሰው 50 ሴት ይናፍቀዋል? ለዛውም መልካቸውን ማያውቃቸው።ግን እኔም እናፍቃቸው ይሆን? ሁሉም ባይሆኑም ከኔ በጣም ቀረቤታ የነበራቸውማ እናፍቃቸዋለው።ተስፋ አይከለከል ። ሁለቱ ወር በሁለት አመት ልክ አሳልፌ መመለሻዬ ደርሶ ቅድሚያ ያቀናሁት ወደ ዛ ወደ ናፈኩት ቁራን ቤት ነበር። ግን እንደነበረው አላገኘሁትም በኔ ቦታ ሰዉ ተተክቶ ነበር። ቢሆንም አነድ ጥግ ይዤ ተቀመጥኩ ።የዚህን ጊዜ ነበር አንዲት ልጅ መጥታ በመጋረጃው አድርጋ በጆሬዬ አንድ ነገር ሹክ ያለችኝ።ምን ይሆን? #ክፍል_2 ✍ይቀጥላል ሼር በማድረግ ለዎዳጆ ያድርሱ
2742Loading...
20
#የባከኑ_ቀናት ✍ ፀሀፊ፡ ሂባ_ሁዳ በ ኢትዮ ልቦለድ የቀረበ       ልብ አንጠልጣይ ታሪክ እንዴት አያችሁት የወደዳችሁት እስኪ like👍 Join us: https://t.me/fiction_boock
2730Loading...
21
የባከኑ ቀናት ክፍል አስራ አምስት (የመጨረሻው ክፍል) (ሂባ ሁዳ) . . ዝምታው ያስፈራል፤ ረጅም ደቂቃ ዝም አለ። <<ማሂ እሺ አሁንስ?>> <<አሁንማ... አሁንማ ኢብቲ...ተስፋ የቆረጠ ሰው አታውቂም?...ራሱን የጠላ ሰው?... መኖር የሰለቸው? ....እየኖረ የሞተ?.... ህልሙን ቅዠት የሆነበት?... ከራሱ ርቆ በሌሎች የተደበቀ.... ልቡን ላለማድመጥ ጩኸት የሚፈጥር?... ከኑሮ ለመሸሽ በጪስ የተወሸቀ?...ኢብቲ ከፊትሽ ያለው ለሴቶች ክብር ብሎ የሚጣላው ማሂር እኮ አይደለም። የሴቶችን ክብር የሚወስድ እንጂ..>> ድምፁ በሲቃ ታፈነ አይኖቹ መሸከም ያልቻሉትን ዕንባዎች ሲለቋቸው ቁልቁል ፈሰሱ። ከዚህ በላይ ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም። ድንዝዝ ያሉት እጆቼ ዕንባዬን መጥረግ ተሳናቸው። ምንም ቃል መናገር አልቻልኩም የማሂ ዕንባ እያይሁ ከማንባት ውጪ። እንደምንም ራሱን አረጋግቶ ግንባሩን በሁለት እጆቹ ደጋፍ አደረገ <<ኢ.ብ..ቲ>> ድምፁ መቆራረጥ ጀመረ። <<አ.ል.ች.ል.ም እንዲህ መኖር አህ.ህ.ህ>> እጆቹ እንደመንቀጥቀጥ አደረጋቸው። <<ማሂሬ ደና ነህ?>> በጣም ደንግጫለው አይኑን ይጨፍናል መልሶ ይገልጣል .. <<ማሂ ማሂሬ?>>ድምፁ ጠፋብኝ <<ትንሽ ደቂቃ ብቻ... ይ.ተ.ወ.ኛ.ል ..>> . <<ኢብቲ አየሽ አይደል እዚህ ድረስ ነኝ.. በሰዐቱ ካልተጠቀምኩ እንዲህ ነው የሚያደርገኝ መውጣት ማልችለው ሱስ ውስጥ ወድቄያለሁ። ኢብቲ ከዚህ ቡኃላ የኔ የምለው ምንም አይነት ነገር የለኝም፤ የኔ ቀርቶ እኔም አልኖርም። እኔ እኮ አሁን አንቺን ማግኘቴ ደስ ብሎኛል። ቢያንስ እንደኔ ሌላ ሰው ሰው በማጣት የህልሙ ብርሃን ጭላንጭል ሲሆን... ጭላንጭሉን ወደ ብርሃን እንዲቀየር እንደምታግዥው ለራሴ ቃል ትገቢልኛለሽ። ከአሁን በኃላ ሰሚ ላጡ አባሽ ለሚፈልጉ ዕንባዎች እንደ አሁኑ አብረሻቸው ከማልቀስ ይልቅ መፍትሄ እንደምታመጪላቸው እንድትነግሪኝ እፈልጋለሁ። ኢብቲ ያለፈው ፀፅቶሻል? ጎድቶሻል አይደል? በሌሌች አስተካኪው። ከመስማት ማድመጥን ልመጂ። ማየት ብቻ ሣይሆን በመመልከት አስተውዪ ...>> <<ማሂሬ እንዴት ልቻለው? ይሄን ሁሉ ከመሆኑ በፊት እኮ..ማሂ ይሄ ሁሉ በኔ እኮ ነው! ራሴን ምን ብዬ ላሳምነው?>> ከዚህ በላይ ማውራት አልቻልኩም ስቅስቅ ብዬ ከማልቀስ ውጪ። <<ኢብቲ ነገርኩሽ እኮ... በቃ ያለፈ ታሪክ ነው። ያገኘሁሽ ሁላ በኔ ምክንያት መጨነቅሽን ትተሽ ሰላምሽን እንድታገኚ ነው።>> <<ማሂ ለዚህ ሁሉ ስህተት ምንድነው ይቅርታው?>> <<ኢብቲዬ ማርፈድ ከትምህርት ቤት ይልቅ ህይወት ላይ ዋጋ ያስከፍላል። በኔ ህይወት አንቺ አልዘገየሽም፤ እኔ ቸኮልኩ እንጂ.. እኔን እርሺኝ ከአሁን በኃላ የሚመጡትን ማሂሮችን እርጂያቸው። ከዚህ በላይ ስታለቅሺ የማየት አቅሙ የለኝም። ማንም አንቺን ባያስከፋሽ ምኞቴ ነው። በኔ ምክንያት እንድታለቅሺ ከቶ አይቻለኝም። ቃል እንድትሰጭኝ ፈልጋለሁ ማሂን በድዬዋለሁ ብለሽ እንደማታለቅሽ..>> <<ማሂ ጭራሽ ከአዕምሮዬ በላይ ሆንክብኝ እኮ። ያልከኝን ሁሉ አደርጋለሁ ግን በጣም ይ.ቅ.ር.ታ...ስለሁሉም>> ድምፄ ታፈነ ማውራት እየፈለኩ ግን አንደበቴ ተሳሰረ። ከሚቆራረጠው ትንፋሼ በቀር .. <<ማ.ማማ..ሂ.እኔ... >> ወደኔ ተጠጋ ሊያባብለኝ ሞከረ፤ ግን አልሆነለትም። ዕንባዎቹ እየተሽቀዳደሙ መሰለኝ። ለመጥረግ ብሞክርም እንደ አዲስ የሚፈሱት እጄን አረጠቡት። እንደ ትኩስ ውሃ ቢያቃጥለኝ፤ ልቤ ከሚለበልበው ህመሜ በላይ የሱ ሲቃ ገዘፈብኝ። እጄን ከፊቱ ላይ አወረዳቸው ወደ ጆሮዬ ተጠጋ። <<ኢብቲ እኔ ከአሁን በኃላ የለሁም። ስለኔ ብለሽ ሌሎች ማሂሮችን እርጂያቸው ስለኔ ስታለቅሺ ከዚህ በላይ ማየት አልችልም>> ለመጨረሻ ጊዜ ከማሂ የወጡ ቃላት ነበሩ። ማሂ እያየሁት በምን ፍጥነት በር ጋር እንደ ደረሰ እኔንጃ ብቻ በር ጋር ሲደርስ አንዴ ዞር ብሎ አይቶኝ ከአይኔ ሸሸ። . ከደቂቃዎች ቡኃላ ተረጋጋሁና አካባቢዬን አስተዋልኩ፤ ጠረዼዛው ላይ ማሂ ሂሳብ አስቀምጧል በኩባያ ሙሉ ወተት አለ። ማሂ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ውሃ ሰማያዊ ጂንስ ጃኬት አለ አንስቼ ያዝኩት፤ የማሂሬ ነበር። ለትናንቱ ህመሜ ዛሬ ማስታገሻ አጊቻለሁ...ትናንት ላይ የባከኑት ቀናት ዛሬ ላይ ዋጋ አስከፍለውኛል ያውም በማሂሬ! . ሁላችንም ውስጥ ትላንት አለ፤ ትናንታችን ውስጥ ደግሞ ስህተቶች አሉ፡፡ ምናልባት የኛ ምናልባትም ደግሞ በህይወታችን ዉስጥ የገባ የሌላ ሰው ስህተት አለ፡፡ ከትላንት ስህተታችን ለመታረም መቁረጥ አለብን፡፡ እኛ ህይወት ውስጥ ስህተት የሚፈጠረው በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በእኛ ምክንያት ነው፡፡ ባለማወቅ ሰዎችን ብዙ ጎድተና፤ እንዲያዝኑ አድርገናል፤ በእርግጥ ሰዎችን ከልክ በላይ የሆነ ቦታ እንዲሰጡን የሚያደርጉ ነገሮች አሉ፡፡ ግና ትክክል ነው ብለው አውቀውም ሆነ ሳያውቁ የነሱን የህይወት ፈተና ማለፊያ ያደርጉናል... አልያም እናደርጋቸዋለን፡፡ ይሁና.......! ሁሉም በየራሱ መንገድ ትክክል ነው፡፡ በቃ...አሁን ዛሬ ላይ ነን። ምናልባት ነገ ብለን ትናንት ተስፋ ያደረግነው ነገር ዛሬ ላይ ፀፀት ሆኖ ይሆናል፤ ግን አልፎዋል አራት ነጥብ፡፡ ያ ሁሉ ተስፋ፣ ፍቅር፣ እምነት፣ ስህተት ....በቃ ሁሉም ትላንት ነው፡፡ ዛሬ ሌላ ቀን ነው! አዲስ ከስህተት ተምረን የምንለወጥበት ባለፉ ስህተቶች ድጋሚ የማናልፍበት። ሌላ ከኖርነው እድሜ ላይ የተጨመረችልን ልዩ ቀን። ያለፈው ይሁና.......! ይሄን ሁሉ አልፈን እንድንቆም ለረዳን አላህ ምስጋና አቅርበን ነጋችንን የምንስልባት ባለ ፀሀይ ቀን፡፡ እርግጠኛ ነኝ ነገ ከትላንት ይሻላል፡፡ የሄደው ነገር ሁሉ ለመልካም ነው፡፡ ዛሬዬን ያዘጋጀልኝ ጌታዬ ነገዬን የተሻለ እንደሚያደርግልኝ አምናለው፡፡ ምናልባት አልሄድንም ይሆናል ፤ አልመጣንም ይሆናል ፤ ግን ፈቀቅ ብለናል ፡፡ ቅድም ማሂ በሰጠኝ ወረቀት ጀርባ መሞነጫጨር ጀመርኩ... ምን አልባትም ለማሂ የፃፍኩት የመጨረሻ ቃላቶቼ ናቸው። #ግራጫ_ቀናቶች ~~~~ ጣዕም የለሽ ህይወት ትርጉም አልባ ኑሮ ፤ ቀንም ሆነ ምሽት የሳግ እንጉርጉሮ ፡፡ በጥቁር ደመና እንባን ያቀረሩ ፤ በሳቅ በትወና ባዷቸውን የቀሩ ፤ ወይ ከነጭ አልሆኑ ወይ ደግሞ ከጥቁሩ ፤ ብዙ ቀኖች አሉኝ በመሃል የቀሩ ፡፡ የፃፍኩትን ወረቀት ሳጣጥፍ ከጀርባው ሌላ ፁሁፍ በትናንሹ ተፅፎ አይሁ ለማንበብ ወረቀቱን ዘረጋሁትና ማሂ እንዳለኝ በአትኩሮት ለማንበብ ራሴን አብሰብ አደረኩ። ❝ግን በመሄድና በመምጣት የጊዜ ርዝማኔ ውስጥ የተስፋ ስብራቶች፣የልብ ቁስሎች ፣ የአእምሮ መላሸቆች ስንት ይሆኑ...? ባለመኖር እውነታ ውስጥ ስንት የመኖር ህልም ይሞት ይሆን.....? በትናንት ህመም ውስጥ ስንት ዛሬዎች ባከኑ፤ የነገ ህልሞች ደቀቁ............❞ አንብቤ ስጨርስ እንደ ጀት ቅርፅ ሰራሁበት ከካፌው እንደወጣሁ ወደ ሰማዩ ለቀኩት..በአንዱ መስመር ሲሄድ እኔ በሌላኛው መስመር ሄድኩ .... #ተፈፀመ...
2840Loading...
22
#የባከኑ_ቀናት ✍ ፀሀፊ፡ ሂባ_ሁዳ በ ኢትዮ ልቦለድ የቀረበ       ልብ አንጠልጣይ ታሪክ እንዴት አያችሁት የወደዳችሁት እስኪ like👍 Join us: https://t.me/fiction_boock
10Loading...
23
#የባከኑ_ቀናት ✍ ፀሀፊ፡ ሂባ_ሁዳ በ ኢትዮ ልቦለድ የቀረበ       ልብ አንጠልጣይ ታሪክ እንዴት አያችሁት የወደዳችሁት እስኪ like👍 Join us: https://t.me/fiction_boock
10Loading...
24
የባከኑ ቀናት ክፍል አስራ አራት (ሂባ ሁዳ) . . ለማሂ በቴሌግራም መልዕክት ላኩለት <<ሰላም ማሂሬ...>> <<ወዬ እንዴት ነሽልኝ ውድ አለሽልኝ?>> <<አልሃምዱሊላህ አለሁልክ እ..አወቅከኝ? ኢብቲሳም ነኝ ..>> <<ኧረ እንዴት ሆኖ አንቺን እረሳለው.. እየጠበቁሽ ነበር ትመጪያለሽ ብዬ የሚለውን ግጥም ታውቂዋለሽ ሃሃሃሃ>> <<ሃሃሃ አላውቀውም.. እና እንዴት ነክ ሁሉ ሰላም?>> <<የዋህ ምን ይሆናል ብለሽ ነው አለሁልሽ>> <<መኖር ደግ ነው...እና ቤተሰብ ሰላም ነው ናቸው?>> ኡፍ ከምን ጀምሬ ማውራት እንዳለብኝ እንጃ... <<እኔ እያለሁ ምን ሊሆኑ..አንቺ ጋርስ ?ሁሉ ሰላም ነው?...>>ስለ በፊቱ አንዳንድ ነግሮችን አንስተን ስንስቅ ትንሽ ቆየን። <<በቃ ኢብቲ ደክሞኛል ልተኛ ነው ነገ እናወራለን...>> <<እሺ ሰላም እደር ...>> ከኦን ላይን ወጥቼ ማሂን እንዴት ማውራት እንዳለብኝ ማሰብ ጀመርኩ መሽቶ ነበርና ከሃሳቤ ጋር በዛው አሸለብኩ። * ከሰኞ ጀምሮ በተከታታይ የፋይናል ፈተና ስለነበረኝ ኦንላይን ብዙም አልኖርም። ከማሂ ጋርም ሰፊ የማወራበት ሰዐት አላገኘሁም። እንደምንም እየገባሁ መልዕክት አስቀምጥለታለሁ። ግን ምላሹ ሁሉ ቀልድ ነው፤ አልያም ወሬ ይቀይራል። ነገራቶችን ሸፋፉኖ ማለፉ ምንም አልተዋጠልኝም፤ የሚጠቀማቸው ቃላት ጭራሽ የማላውቀው ሰው እያወራሁ ይመስለኛል። ፈተና ስጨርስ ሊያገኘን እንደሚችል ጠየቀኝ... ሳላመነታ ተስማማሁ። ግን ሳገኘው ማሂር ወፍሮ ይሁን..ወይንስ ረዝሞ..ያ ፈገግታው ይኖር ይሁን...ወይስ...ኮስታራ ሆኖዋል..ማሂ የተሻለ ሂወት ውስጥ ይሁን...ወይስ መጥፎ ሂወት እየገፋ ይሁን..አሁን ደስተኛ ነው ...አልያም ብሶተኛ.. ማሂ ምን አይነት ህይወት ውስጥ ይሁን? * #ከሳምንት_ቡኃላ #ዕለተ_ቅዳሜ_8:00 #ጦር_ሃይሎች * <<ሰላም ምን ልታዘዝ?>> ከወገቡ ጎንበስ እንደማለት እያለ አፈራርቆ ያየናል፤ አስተናጋጁ። <<ኢብቲ ምን ይሁንልሽ ምሣ ምናምን ...?>> <<አይ ማሂ በልቻለሁ ወተት ይሁንልኝ..>> <<በቃ ለኔ ማኪያቶ..>> <<ወተቱ በትልቁ በትንሹ ?>> አስተናጋጁ ደግሞ ጠየቀ። <<በትልቁ አድርግላት ድመት ነገር ናት ..>> <<ሳፊ ወይስ ...>> <<ዉይ ኖርማል አድርግላት በቃ!>> አስተናጋጁ ፈጠን ፈጠን እያለ ተራመደ። <<በፈጣሪ ካልዲስ ደግሞ አያዝጉ። ትልቅ፤ ትንሽ...ሳፊ ምናምን ከዛ ደግሞ ከአንድ ሰዐት በኃላ ይዘው ይመጣሉ..>> <<ያው እያወራህ ከሆነ ችግር የለውም ከቸኮልክ ነው የሚያበሳጨው...>> <<ኧረ ኢብቲ እኔ ትግስት የለኝም መጠበቅ ምናምን ኡፍፍፍ። አንቺ ፀሃይዋ አንቺ ልከሻት ነው በረታችብኝ እኮ>> ከላይ የለበሰው ውሃ ሰማያዊ ጃኬት አውልቆ ወንበሩ ላይ አንጠለጠለው። <<ምነው?>> አይኔ ወዳረፈበት እጁ ግራ በመጋባት ተመለከተ። <<ኦውውው ይሄን አይተሽ ነው እንዴ>> እጁ ላይ ወደ ተሳለው ታቶ እያመላከተኝ <<አያምርም እንዴ?>> <<አይ ገርሞኝ ነው...>>ምን ማለት እንዳለብኝ ግራ እየተጋባሁ.. <<አንዴ መጣሁ ..>> ወደ ውጪ መራመድ ሲጀምር በደንብ ለማየት ሞከርኩ። ፀጉሩ ተንጨባሯል፤ ሰውነቱ ከስቷል፤ እስካሁን ምንም አልነገረኝም ምን ውስጥ ሊሆን ይችላል? ብዙ ነገራቶች ለአፍታ ተፈራረቁብኝ.. . <<ኢብቲ ወዴት ሄድሽ?>> <<ኧረ አለሁ ከመቼው ተመለሰክ ..>> <<አይ ስገባ አይቼ ነበር ቀድመሽኝ እንዳትገቢ ስቸኩል አልፌው መጣሁ። አሁንም እንደምትወጂ እርግጠኛ ነኝ..>> ሎሊፖፕ አቀበለኝ። <<እውነት ነው በሎሊፖፕማ አልጨክንም አንተ ደግሞ አትረሳም ሃይ ጎበዝ ነህ...>> <<አይ ኢብቲ እንዴት ይረሳል>> ሌላ ሃሳብ ውስጥ ሲገባ አትኩሬ ተመለከትኩት። በፊት በኩል ጥቁር ፀጉሩ አሁን በሌላ ቀለም ተቀይሯል፤ ድቅድቅ ብሎ የተሳሰረ የሚመስለው ቅንድቡ በአንዱ በኩል ተቆርጦ መሃል ላይ ክፍተት ተፈጥሯል፤ ከንፈሩ አካባቢ በልዟል... ከዛ በላይ መመልከት አልቻልኩም ማሂ መጥፎ ሁኔታ ውስጥ እንደገባ አሰብኩ። እኔ ማስበው እንዳይሆን ፈራሁ.. <<ማሂ?>> <<ወዬ...ተመሰጥኳ? ታውቂያለሽ ኢብቲ ያ ጊዜ ደስ ይል ነበርኮ..>> <<ማሂ አሁን እንዴት ነህ በአላህ? ደህና ነህ?>> <<ደህና አልመስልማ? ምነው አስፈራሁሽ እንዴ?..ባይሆን ጠጪ እስቲ>> <<ማሂ የተገናኘነው ሻይ ቡና ለማለት አይደለም...እንድናወራ ነው። ...እስቲ አውራኝ እንዴት ነህ..>> <<ለምን ስለኔ ትጨነቂያለሽ? ትወጂኛለሽ እንዴ?..>> ማሂ አይን አይኔን ሲያየኝ ይባስኑ አጨናነቀኝ። <<እንዴ ማሂ ለምን እጠላሃለው? ለምን አሎድህም?>> <<እንደሱ ነው እንዴ>> ከልብ በማይመስል ፈገግታ መለሰልኝ። <<ማሂ ሁሉንም ነገር አውቃለሁ። ማውቄ እኔን ጎድቶኛል ምክንያቱም ያኔ ምንም ላደርግልህ አልቻልኩም ነበር። አሁን ግን...>> <<አሁን ምን? እስቲ ምን ታውቂያለሽ? ሃሃሃ... ምን ታውቂያለሽ ከስሜ ውጪ..?>> <<እሺ አንተ ንገረኝ ማላውቅ ከሆነ..>> <<ከምን እስከ ምን ኢብቲ? ብታውቂስ ቆይ ምን የምትለውጪው ነገር አለ? ሰምተሽ አይዞህ ልትዪኝ ነው? አመሰግናለሁ..>> ማኪያቶውን በሁለት ትንፋሽ ጨለጠው፤ ፊቱ መቀያየር ጀመረ። ዛሬ ምንም ቢፈጠር ለመቀበል ዝግጁ ሁኜ ነው የመጣሁት ብቻ በትዕግስት ማሂን መቆጣጠር አለብኝ። . <<ማሂ ስላንተ ባቢ እና አቤላ ሁሉንም ነገር ነግረውኛል። ወላሂ ማሂሬ ያን ጊዜ አንተን ማግኘት አልቻልኩም። በርግጥ እስኪነግሩኝ መጠበቅ አልነበረብኝም፤ አንተ በተግባር ብዙ ልታሳየኝ ጥረህ ነበር። ግን እኔ አልገባኝም አለ አይደል.. ወተት ነጭ ነው እስክባል ድረስ። ማሂ አውቃለሁ በኔ ላይ ተስፋ ነበረህ፤ ያን ተስፋ አጨለምኩብህ አይደል? ማሂ ከተለያየን በኃላ እኮ ብዙ ፈልጌህ ነበር፤ ግን አላገኘሁክም። አውቃለሁ ሳንለያይ በፊት ቁጥርህን ስትሰጠኝ አልተቀበልኩህም። እኔ ይሄ ሁሉ ይፈጠራል ብዬ አላስብኩም ነበር። ማሂ እኔ ስላንተ በማሰብ ራሴን ተወቃሽ አድርጌ ላለፉት አመታት በፀፀት ውስጥ አለሁ። እባክህን ማሂ አንድ ነገር እንኳን እንዳደርግ ፍቀድልኝ...ቢያንስ አሁን ያለህበትን ሁኔታ ንገረኝ።>> አይኑን ከኔ ላይ አነሳና ወደ ጠረዼዛው አጎነበሰ። <<ኢብቲ ታውቂያለሽ? እንደ አሁን ሰዐት በራሴ ተስፋ የቆረጥኩበት ጊዜ የለም። ያኔ እኮ በቃ መሉ ለሙሉ የምፈልገውን ህይወት የማገኝ መስሎኝ ነበር። ቆይ ኢብቲ አንድ ሰው ወዶ አላዋቂ ይሆናል እንዴ? እኔ እኮ እምነቴን ለማወቅ ብዙ ቦታዎች ሄጄ ነበር። ለካ ለማወቅም ትንሽ ማወቅ አለብሽ። <ገና ጀማሪ ነህ..እንዴት ትንሽ እንኳን አታውቅም? ምናምን.. እስቲ ስገድ> እህህ! ስርአቱን አውቄ ለመስገድ አይደል እንዴ እነሱ ጋር መሄድ የፈለጉት? ቆይ ሌሎችስ ስለ እምነቴ አላውቅም አስተምሩኝ ማለት የሌሎች መሳለቂያ ሙድ መያዣ ማድረግ ምን ይጠቅማል? ኢብቲ በናትሽ ስለተውኩት ነገር አታስወሪኝ። ..ብቻ ያኔ ካንቺ ብዙ ጠብቄ ነበር፤ በቃ አልሆነም ደግሞ እንደማገኝሽ እርግጠኛ ነበርኩ። ግን እንዲ ከረፈደ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ይሄን አንብቢው እስቲ ከዋሌቱ ላይ ከሁለት ወረቀት አንዱን አውጥቶ ሰጠኝ ወረቀቱ እጥፍጥፍ ብሏል በዛ ላይ የቆየ ይመስላል። ተቀብዬ ከፈትኩት
2460Loading...
25
#ትዝታ . . ትዝታ እኮ ሳቅ ነው ቢኖረውም ትካዜ፤ ትዝታ ታሪክ ነው የማይረሱት ጊዜ፤ እኔም ኑሪያለሁኝ በትዝታ አለም፤ ስለአንች በማሰብ ስለአንቺ በማለም። መኖር ከተባለ እኔም ኑሪያለሁኝ፤ በዝምታ አለም ሁሌ እየፈራሁኝ፤ በአይናፋር አንደበት ዝምታን መርጬ፤ ከመናገር ይልቅ በሀሳብ ቀጭጬ፤ ራሴን በመደበቅ ማውራትን ፈርቼ፤ በስቃይ ኑሪያለሁ ግራ ተጋብቼ። . ራሴን በመውቀስ ራሴን በመስደብ፤ በዚች አስቸጋሪ በዚች ፈታኝ አለም፤ በተመስጦ ታሪክ በሚመስል የህልም፤ እውነት ኑሪያለሁኝ 'ኔነቴን በማሰብ። . <<ግጥም እንደምትፅፍ አላውቅም ነበር።>> ግጥሙን አንብቤ ቀና እያልኩ። <<ምንም አታውቂም አልኩሽ ኮ ..ብዙ ፅፌ ነበር ግን የሆነ ቦታ ቁጭ ስል እንዲበሩ እለቃቸዋለሁ እስካሁን ምንም አላገኘሽም እንዴ...>> ፈገግ ለማለት ይሞክራል። <<እሺ ማሂ ያለፈውን ታሪክ አወራን፤ እሱ እንደግጥምህ ነው.. ትዝታ ልንለው እንችላለን። አሁንስ እሺ ማሂ አትደብቀኝ እባክህን..>> <<ኢብቲ ላንቺ ምንም አይጠቅምሽም አውቃለሁ። ነገራቶችን ለማስተክልከል ትፈልጊያለሽ ግን የማይስተካከል ህይወት አለ>> <<ማሂ በናትህ ህመሜን ቀንስልኝ...>> ንግግሬን አላስጨረሰኝም <<እናቴ ብትኖር እዚህ ነገር ውስጥ የምገባ ይመስልሻል? ተያ ኢብቲ... በቃ አንቺ እንደምታስቢኝ አይነት ማሂር አይደለሁም፤ ልሆንም አልችልም። መጥፎ ሰው ነኝ፤ አሁን ምንም አላማ የለኝም። እውነቱን ልንገርሽ? ያኔ በረመዳን ሚሪንዳ ስጠጣ እንደዛ ለደነገጥሽው ለምነግርሽ ነገር ምን ልትሆኚ እንደምትቺ ብዙ ጊዜ አስቤ ነበር። ስለኔ ከአሁን በኃላ እንድትጨነቂ አልፈልግም ኢብቲ። እኔ ማሂ በአሁኑ ሰዐት አልንገርሽ ያኔ በምታውቂኝ ማሂ ኑሪበት..>> አይኖቹ እንባ አቀረሩ። እኔ ምን አይነት ስሜት ውስጥ እንደሆንኩ ልናገረው አልችልም፤ ብቻ እንደምንም ራሴን ለመቆጣጠር እታገላለሁ። <<በመጀመሪያ ኢብቲ እወቂ.. በጣም እንደምወድሽ። እንዲህ ስልሽ ግን ባልሆነ መንገድ እንዳትረጂኝ ምን አልባት እህት ስለሌለኝም ይሆናል። እናቴን በልጅነቴ ማጣቴም ይሆናል። እነሱን የምትተኪልኝ ይመስለኝ ነበር፤ ከአንቺ ጋር እህትና ወንድም ሁነን እንዴት እንደምንሆን እንደምናድግ ብዙ ጊዜ አስበው ነበር። አለ አይደል የራሳችን ላይፍ ኖሮን ሁላ እንደ ፍሚሊ ልንኖር.. ብቻ ብዙ ብዙ ሃሳብ ሆኖ ቀረ እንጂ፤ እስካለፉት ሶስት አመታት ድረስ..>> አይኑን ማየት አልቻልኩም አንገቴን ከመሰብር ውጪ። ዝምታው ያስፈራል፤ ረጅም ደቂቃ ዝም አለ። <<ማሂ እሺ አሁንስ?>> . . #ክፍል_15 የመጨረሻው ክፍል... ነገ ይቀጥላል...
2790Loading...
26
የባከኑ ቀናት ክፍል አስራ ሁለት (ሂባ ሁዳ) . . ከአቤላ ጋር ቁጭ ካልን በኃላ ..ምን አለ የማሂም እንዲሁ ቀልድ ነው ብላችሁኝ ደስታዬ ሙሉ ቢሆን እያልኩ አስባለሁ። እነ ዩሲም ምርጥ ውጤት ስላመጡ በጣም ደስ ብሏቸዋል። ሶስታችንም የትምህርት ቤቱ ሰቃይ ሆነናል። እኔ ግን ልቤ ላይ ሌላ ጭንቀት አለ እሱም ማሂር ነው። በቃ በአንድ አጋጣሚ ተገናኝተን በሌላ አጋጣሚ ተለያየን ማለት ነው? እኔ ግን እጣፈንታን ተቀየምኳት.. ራሷ አገናኝታን ራሷው አለያየችን። አሁን ማሂር ምን ይሁን የሚሆነው.. <<ኢብቲ ማሂ ስለወደቀ ከፋሽ አ? እኔም ደብሮኛል የሌለ አብሬው ብወድቅ ነው ያልኩት>> አቤላ እንዲህ ሲለኝ ስለ ማሂ እያሰብኩ ስለነበረ ደነገጥኩ። <<አዎ አቤላ አሳዘነኝ.. ሁኔታውን አይተኸዋ። እኔ ምልህ እስቲ ስለ እሱ ንገረኝ... ፋሚሊዮቹ ምን አይነት ናቸው?>> <<አይ ስለወደቀ እንኳን አይቆጡትም አያሣስብሽ..>> የጠየኩት ጥያቄ የገባው አልመሰለኝም። <<ሣይሆን አላይደል እምነታቸው ላይ...>> <<እእ እሱን ነበር እንዴ የጠየቅሽኝ... አንድም እኮ የጓዳው እሱ ነው። ለዛ ነው ቶሎ ሆድ የሚብሰው፤ ሰውም ብዙ የማይቀርበው እንዳያጣ ስለሚፈራ ነው። ኡፍፍ ብራዘር ምርጥ ልጅ ኮ ነበረ>> <<ማለት አቤላ ቤተሰቦቹ ላይ ችግር አለ? ማለቴ አይስማሙ?>> <<ሣይሆን እናቱ ከሞተች ቆየት ብሏል። ያኔ ጩጬ ነበር፤ ፈታ ብሎ ነበር የሚያድገው። እናቱ ከሞተች በኃላ ነገራቶች ተቀየሩ ፋዘሩም ሌላ ሚስት አገባና ከአዲሱ ሚስቱ ጋር እምነቱን ቀየረ፤ በፊት ኮ ምርጥ ሼኪ ነበር ይባላል። በቃ ማሂሬም ትምህርት ቤት ብቻ አስገብተው ላሽ አሉት፤ ግን ፋዙካው የሌለ ነው የሚወደው። እንዲከፋው ምናምን አይፈልጉም ግን የሚፈልገውን አላሟሉለትም። አለ አይደል ከመሰረታዊ ነገር ውጪ እሱ በጣም የሚያስጨንቀው እምነቱ ነበር። በፊት ብዙም አያርፍም ነበር ሲቆይ ሲቆይ ግን የሌለ ይሸምመው ጀመረ። አብሶ ሙስሊሞችን ሲያይ ሽምቅቅ ነው የሚለው፤ አንዳንዴ ምን እንደሚሉት አይገባውም። ከነርሱ ጋር እንደፈለገ ፈታ ብሎ አያወራም፤ ምክንያቱም እነሱ ከሚያውቁት ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። ሲጠይቃቸው ደግሞ <እንዴት አታውቅም ለስሙ ሙስሊም ነህ> ብለው ሙድ መያዣ ያደርጉታል። ለዛም ነው ከኔና ከባቢ ጋር ብቻ የምታይው፤ እኛ ከድሮም አብረን ስለተማርን ሁሉንም ነገር እናውቃለን። ምንም አንደባበቅም.. በቃ እኔ ማሂሮ የመጭ ነው የሚያሳዝነኝ፤ የሌለ ምርጥ ልጅ እኮ ነው በናትሽ። አንድ ጥሩ ሰው ቢገጥመው እኮ የሌለ ደስተኛ መሆን ይችላል።>> <<አቤላ እኔ ግን ምን አይነት ሰው ነኝ? እንዴት ምንም ማድረግ ያቅተኛል..>> <<ኢብቲሣም ምንአልባት ከዛሬ ቡኃላ አንገናኝም ይሆናል ከመለያየታችን በፊት ግን ልነግርሽ የምፈልገው ነገር አለ ...>> አቤላ እጁ ላይ ያለውን ክር እያሽከረከረ ንግግሩን ቀጠለ። <<ኢብቲ በመጀመሪያ ያሳለፍነው ጊዜ መቼም ልረሳው አልችልም። ለኔ ሁላችሁም ምርጥ ነበራችሁ፤ ትለዩብኛላችሁ። ሁሌ አብረን ብንሆን ምነኛ ደስ ባለኝ ግን መለያየት ልክ እንደመገናኘት ነው ፈልገሽ ሣይሆን መሆን ስላለበት ብቻ የሚሆን። እና ደግሞ ኢብቲ ሁላችንም እናከብርሽ ነበር ባቢም ማሂሮም ስለሌሉ እነሱንም ሁኜ ነው የምነግርሽ። በተለይ ለኔና ለባቢ በጣም ለውጠሽና፤ ብዙ ነገሮችን እንድናይ ረድተሽናል። የሰው ክብር ከምንም በላይ አሳውቀሽናል። ብቻ ብዙ ነገር.. ታዲያ ግን ይሄን ለኛ ባደረግሽ ጊዜ ካንቺ ሌላ ነገርን ጠብቀን ነበር። መጠበቅ ብቻ ሣይሆን ታደርጊዋለሽ ብለን ነበር..ግን ምን ያደርጋል፤ አንዳችን አርፍደናል አልያም ዘግይተናል። መቼስ ገብቶሻል አይደል? ስለ ማሂር ነው። በጣም እንድትቀራረቡ ከባቢ ጋር ብዙ ነገር ፈጣጥረን ነበር። እንድታወሩ ብዙ አጋጣሚ መሳይ ነገሮችን ስንፈጣጥር ነበር። የኛ ልፋት ውጤቱ ላይ ሳይደረስ ቀረ። ለምን? አንድም ማሂር ፈሪ ስለሆነ፤ ከዛሬ ነገ አወራታለሁ ሲል። ሌላው ደግሞ ያንቺ ትኩረት አለመስጠት ነው። እንዴ ኢብቲ ብዙ አጋጣሚዎች ላይ እኮ ማሂ ስለእምነቱ እንደማያውቅ ካንቺ መማር እንደሚፈልግ ነግሮሽ ነበር። ግን አንቺ ሁሌ ቀልድ እየመሰለሽ ታልፊዋለሽ። ከዛሬ ነገ ቀኑ እየሄደ ሲመጣ ማሂር ሁሉንም እንዲነግርሽ በግድ አሳምነን ላክነው። ግ'ና ምን ያደርጋል..እቸኩላለው ብለሽ ልታዳምጭው ፍቃደኛ አነበርሽም፤ ሌላ ስብራት ፈጠርሽበት። ትዝ ይልሻል አይደለ? ከቀናት በአንዱ ቅዳሜ ቀን ነበር። የዛኔ ያየሁትን የማሂን ተስፋ ማጣት ምንም ላይ ደግሜ የማየው አይመስለኝም። ሁላችንም ባንቺ እምነት ነበረን፤ ነገራቶችን ታስተካኪያለሽ ብለን... ደግሞ እኔ ወይ ባቢ ከምንነግርሽ ራሱ ቢነግርሽ እንደሚሻል አስበን ነው። ብቻ ኢብቲ አውቃለሁ፤ በጣም ጎበዝ ልጅ ነሽ፤ በትምህርትም በእምነታችሁም። እኔ በአስራ አራት አመቷ ወንድ አልጨብጥም የምትል ሴት ካንቺ ውጪ አላውቅም። በዛ ላይ በጣም ተግባቢም ልጅ ነሽ። ግን አንድ ነገር ይጎልሻል፤ ሰዎችን ማድመጥ፣ በዙሪያሽ ላሉት ትኩረት መስጠት.. ይሄን ባህሪሽ በናትሽ እንደምንም አስተካኪው። ድጋሚ የማሂን አይነት ሰው ትኩረት እንዳትነፍጊ። ኢብቲ የምር በጣም አመሰግናለሁ። ያው እኔ ከባቢ ና ማሂሮ ተለይቼ ያለፍኩት ካንቺ ስለሰራሁ ነው። የዛሬውን ቀን እንዲ አልጠበቅናትም ነበር። ከነ ማሂሮ ጋር ፈታ እንላለን ብለን ነበር አልሆነም። የስምንተኛ ክፍል ላይፍ ለኔ ከየትኛውም የትምህርት ቤት ላይፍ በላይ ነው። ፈጣሪ መልካሙን ያድርግልን፤ ምን አልባት በሆነ አጋጣሚ እንገናኝ ይሆናል።>> ከተቀመጠበት ተነሳ። እኔ ምን አይነት ስሜት ውስጥ እንደሆንኩ አላውቅም... አቤላ እንዲህ ቁም ነገራቶችን ያወራል ብዬ አልጠበኩም ነበር። እኔም ተነሳሁ። <<ቻው ኢብቲ በቃ>> <<አቤላ..>> <<ወዬ>> ፊቱን ሙሉ ለሙሉ ወደኔ አዞረ። <<በጣም ይቅርታ ስለሁሉም..>> ታምቆ የተያዘው ዕንባዬ ቀደመኝ። እኔ ከዕንባዬ ጋር ስታገል አቤላ እየሮጠ ወደ በሩ ሸሸ። ከአቤላ መሸሽ ጋር የኔም ህልምና ተስፋ ላይመለስ አብሮ ሸሸ፤ ፀፀቱ እኔው ጋር ቀረ። . አንድ አመት ሙሉ ከኔው ጋር እየዋለ ለሚሄድ፤ በየቀኑ ከጎኔ ለማገኘው.... ተስፋውን በኔ ላይ ጥሎ መሰበሩን ለሚያሳየኝ ሰው.... መጠገን ትቼ ተስፋውን ገደል መክተቴ... ምን ያህል የባከኑ ቀኖች.... ከኔ ጋር እንደነበሩ አሁን ገባኝ ....ቢገባኝስ ምን ሊፈይድ... ከነስብራቱ ተስፋውን ጥሎ... ማሂሬ ሄደ እኮ!.. . . #ክፍል_13 ይቀጥላል...
2331Loading...
27
የባከኑ ቀናት ክፍል አስራ ሶስት (ሂባ ሁዳ) . . (ከአምስት አመታት በኃላ) * * <ምንም የምወደውም የምጠላውም ነገር የለኝም። የወደድኩትን ጠልቼ፣ የጠላሁትን ወዶጄ ተምታቶብኛል። ማንንም ስለማልወድ ሌሎች እኔን አይወዱኝም ብል፤ ፍቅር ሰጥቶ መቀበል ነው ማለት ይቻለኛል?> የዛሬው የፌስቡክ ጥያቄዬ ነው። . ዛሬ ቀኑ ድብልቅልቅ ብሎብኛል፤ ምን እያሰብኩም ሆነ እየሰራሁ እንደሆነ ራሱ አልገባኝም። ለዛም ነው በደመ ነፍስ እንዲህ ፌስቡክ ላይ ፖስት አድርጌ የወጣሁት... ምን አልባት ሰሞኑን እቤት ስለዋልኩ ተጫጭኖኝ ይሆናል ብዬ ወጣ ለማለት ወሰንኩ። ከሰፈሬ ስወጣ ወደ ዊንጌት ታክሲ ለመያዝ አስፋልቱን ለመሻገር ከፊት የሚመጣ መኪና ለማየት ዞር ዞር ስል አንድ የማውቀው የሚመስል ሰው ፊት አየሁ። ከብዙ ሰው ጋ ተመሳሰለብኝ ወደ እሱ እየቀረብኩ ስመጣ ግን ልቤ ምቷን ከእርምጃዬ ጋር ጨመረች። * <<ይ..ቅር.ታ አ..ቤ..ላ..ማለቴ አቤል?>> <<እንዴ እንቺ! በፈጣሪ ኢብቲሳም ነሻ>> <<እእ አዎ ወዬኔ ግን እንዴት ነህ በአላህ?>> <<አለሁልሽ... በስማም! በሂወት ግን አለሽ ኢብቲ? ተዐምር ነው የሆነብኝ..>> <<በጣም ተቀይረሃል። ትልቅ ሰው መሰልክ እኮ ፂም ምናምን እየሞካከርክ ነው.. ሃሃሃሃሃ>> ፊቱ ላይ ጣል ጣል ያሉትን ፀጉሮች እያየሁ ሳኩበት። <<እና አሁንማ ግብዲያ ሆነናል አንቺ ራሱ.. አይ ግን ለኔ ምንሽም አልተቀየረብኝም። ነይ እንግባ ቦታ አለ..>> ሁለታችንም ገቢና ገብተን ማውራታችንን ቀጠልን። <<እና ከየት ወዴት ምናምን በናትሽ እስቲ አውሪኝ>> <<እኔ ከሰፈር ወደ ጓደኛዬ ሰፈር እያሄድኩ ነው ..አንተስ..>> <<ጓደኛ ስቲ.. እነዛ ሁለቱ ደህና ናቸው? በናትሽ ማን ነበር ስማቸው?..ያቺ እብዷ ..ራቢያ ነበረች መሰለኝ>> ፊቱን ጭምድድ እያረገ። <<ሃሃሃሃ አሁንማ እብድ አደለችም። እእ ደህና ናቸው በአምስት አመት ውስጥ አለመርሳትህ ሲገርም..>> <<ኧረ እንዴት ይረሳል ..ከማሂሮ ጋር እኮ በተገናኘን ቁጥር ነው የምናነሳው ያን ጊዜ..>> ማሂ ስሙ ሲጠራ የሆነ ንዝረት ነገር ተሰማኝ። <<ማሂርን ታገኘዋለህ? ደህና ነው?>> <<አዎ ብዙም ባይሆን ደህና ነው ኧረ እሱ ተመችቶታል..>> <<ስታገኘው ሰላምታዬን አድርስልኝ እሺ በናትህ..>> <<ኧረ አያሳስብሽ..አባ ወራጅ! አልፌው መጣሁ እኮ። ኢብቲ በቃ እናወራለን እሺ>> የገቢናውን በር ዘግቶ ከመኪናው ወደ ታች መራመድ ጀመረ። . <<አንድ ሰፈር አደላችሁም እንዴ?>> ሹፌሩ በጎን በኩል ሊያየኝ እየሞከረ። <<አይ አይደለንም..>> <<እና ትምህርት ቤት ነው የምትተዋወቁት? ከገባቹ ጀምሮ ኮ ስታወሩ በጣም ቅርብ መስላችሁኝ ሁኔታችሁ..>> <<ሳይሆን ስምንተኛ ክፍል አብረን ነበር የምንማረው እና ዛሬ ተገናኘን ከአምስት አመት በኃላ>> <<ዋው! ደስ ስትሉ አምስት አመት ረጅም ነው እኮ..>> <<አዎ ረጅም ጊዜ ነበር>> ብዙ ነግራቶች እንደየጊዜው ተቀያይረዋል። አንዳንድ ሰዎች መጥተዋል፤ ሌሎች ሰዎች ደግሞ ሄደዋል። እኔ ጋር በራሱ ስንት ነገር ተቀያየረ... ራቢ ስራ ጀምራለች፤ ኢክሩም ስራ ና ክላስ አንድ ላይ እያጧጧፈች ነው፤ ዩሲ ደግሞ ዩንቨርስቲ ሄዳ የጊቢ ተማሪ ሆናለች። ነገራቶች ምን ያህል እንደተቀየሩ ለአፍታ ውልብ ውልብ አሉብኝ። <<እና አምስት አመት ማለት አንቺ አሁን የጊቢ ተማሪ ነሽ ማለት ነዋ ምንድነው የምትማሪው?>> <<አይ እዚሁ ኮሌጅ ነው የምማረው ፋርማሲስት..በዛው እዚህ ጋር ያዝልኝ..>> <<ደረሽ እንዴ? በቃ ቆንጅዬ መልካም ቀን..>> እጁን አውሎብልቦልኝ ጉዞውን ቀጠለ። * ዊንጌት መናፈሻው ውስጥ ቁጭ እንዳልኩ አንድ ቴክስት ደረሰኝ <<ኢብቲ በጣም ይቅርታ.. ክላስ አስቸኳይ ፈተና እንዳለብን ነግረውን ወደዛ እየሄድኩ ነው..>> ከሰፈር እሷን ለማግኘት ቢሆንም የመጣሁት እዛው ትንሽ ሰዐታት ለማሳለፍ ወሰንኩ። በመሃል አቤላ ትዝ አለኝ ኡፍፍፍ ለካ ስልክ ቁጥር አልተቀያየርንም ኦህ ሲያበሽቅ!! በቃ እንደውም ወደ ቤት ብመለስ ይሽለኛል። ሂጃቤን አስተካክዬ ከመናፈሻው ወጣሁ። * እቤት እንደደረስኩ ለአመታት ልቤን ሲያስጨንቀኝ የነበረው ነገር እንደ አዲስ ነገራቶችን ይመላለሱብኝ ጀምሯል። ማሂር ለመጨረሻ ጊዜ ሲያየኝ የነበረው ቅፅበት ታወሰኝ። ወደ ግንባሩ ድፍት ካለው ፀጉሩ ጋር ትላልቅ አይኖቹ ከነሽፍሽፍታቸው፣ ፈገግ ሲል ስርጉድ ከሚለው ዲንፕሉ ያ ውብ የሆነው ፈገግታው አሁንም አይኔ ላይ ይመላለሳል። አሁንም እንደዛ ይሁን ወይንስ ተቀይሮ? ማሂሬ በአንድ አጋጣሚ ለአፍታ ብቻ ባየው ብዬ ተመኘሁ። በተቀመጥኩበት ብዙ አሰብኩ ነገራቶችን አለመርሳቴ ለራሴ አስገረመኝ። ዛሬ ከአቤላ ስልኩን እንዴት አልተቀበልኩም?..ግን ብቀበለውስ ደውዬ ምን ልለው ነበር? <ማነሽ? ምን ፈለግሽ?> ቢለኝስ?...እንደምንም ስለትናንት ይቅርታ መጠየቅ ብችል ና ልቤን ከፀፀት በገላገልኳት። * #ዕለተ_እሁድ_ከምሽቱ_3:30 * <<ሃይ እንዴት ነሽ ሰላም ነዋ?>> <<እኔ ደህና ነኝ>> ከማላውቀው አካውንት የተላከልኝን መልዕክት እየመለስኩ። <<ኢብቲዬ ሰላምታሽ ደርሶኛል እ የኢሜል አካውንትሽን በግድ ነው ያገኘሁት በዚህ ስልክ ቁጥር በቴሌግራም ከተመቸሽ መልዕክትሽን ላኪልኝ እጠብቃለሁ። ማሂር ..>> የደረሰኝን መልዕክት ማመን አቃተኝ። ማለት ማሂር..? ማሂ.. እንዴት? ወይኔ ደስ ሲል... ቆይ ምንድነው ያለኝ? ደግሜ አነበብኩት። ልክ የዛሬ ስድስት ቀን አካባቢ ነበር አቤላን ያገኘሁት ሰሞኑን ስለ ማሂ ሳስብ ነበር፤ አሁን ደግሞ መልዕክት ደርሶኛል። ወድያውኑ በመልዕክት መለስኩለት። <<ሰላም ማሂ ኧረ ቆይ ቲጂ መጣሁልህ...>> ጊዜ አልፈጀሁም ስልኩን መዘገብኩና ቴሌግራም ላይ አካውንቱን አመጣልኝ። ምን አልባት ያለበትን ሁኔታ ከገለፀልኝ ብዬ ፕሮፋዬሉን በረበርኩ ምንም የሚገልፅልኝ ነገር ሳጣ መበርበሬን ተውኩት። ልቤ ፈራ ምን ልለው ነው?...ምንስ ሊለኝ ይሁን?..... ለአመታት ባገኘሁት ስል እንዳልነበር አሁን ግን አመነታሁ ....ልክ እንደ "ግራጫ ".... ግራጫ የራሱ የሆነ ቀለም እንደሌለው ሁሉ ....እኔም ውሳኔ የለኝም ...ግራጫ ልክ ሁለቱንም በአንድ አጣምሮ እንደያዘ.. የኔም ሃሳብ አንዱ ላይ አረጋም.... ግራጫ ለአንዱ እንደሚያዳላ ሁሉ ...የኔም ሃሳብ ላውራው አላውራው ብሎ ሁለቱንም ቢይዝም... እንደ ግራጫ ወደ አንዱ አዳልቶ አዘንብሏል። . . #ክፍል_14 ይቀጥላል...
2330Loading...
28
✝ለመላው ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ መልካም በአል @ethioleboled
2550Loading...
29
✝ለመላው ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ መልካም በአል @CryptoUtopia2nd
40Loading...
30
የባከኑ ቀናት ክፍል አስር (ሂባ ሁዳ) . . የስምንተኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና መፈተኛ ጊዜ ደርሰ፤ እንደ አጋጣሚ ረመዳንም አብሮ ገባ። የፈተናችን ቀን የጀመረው በረመዳን የመጀመሪያ ቀን ነበር። . የጠዋቱን ከተፈተንን በኃላ ለዙሁር ሰላት ወደ መስጂድ አመራን፤ ድባቡ ልዩ ነበር። ግማሹ ጥግ ጥግ ይዞ ቁርዐኑን ይቀራል ሌላው ደግሞ ሱና ሰላቶችን ይሰግዳል። ሰግደን ወደ ምንፈተንበት ትምህርት ቤት አመራን መንገድ ላይ እነ አቤላን አግኝተን ስንተራረብ ት/ቤት ደረስን። ከማሂ ጋር እንደበፊቱ ባይሆንም እናወራለን። እሱ በጣም ሊቀርበኝ ቢፈልግም እኔ ግን ከላይ ከላይ ነው የማወራው፤ በአገኘሁት ጊዜ ያኔ እያውራሁት ጥሎኝ የሄደው ቀድሞ ይታወሰኛል። እስካሁን ተናድጄበታለሁ፤ እሱ ግን ረስቶት መሰለኝ ኩርፊያውን ትቶ ምንም እንዳልተፈጠረ ያወራኛል። የመጀመሪያ ቀን ፈተናችንን ደስ በሚል ሁኔታ አጠናቀቅን። ብዙዎች ቀላል ነው ብለዋል፤ አቤላ ከዘጠና በላይ አመጣለው ብሎ ይፎክራል። ከእኔ ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ነው የምንፈተነው ሙሉ መልሳችን አንድ አይነት ሣይሆን አይቀርም። ማሂ፣ ዩሲና ራቢ ግን ሌላ ሌላ ክፍል ነው የሚፈተኑት። ከምንፈተንበት ትምህርት ቤት እስከምንማርበት ትምህርት ቤት ርቀት ቢኖረውም እያወራን ስለነበረ ሳይታወቀን ደረስን። ሁሉም በየአቅጣጫው ተበታተነ እኛም ስለ ነገው ፈተና እያወራን ሰፈራችን ስንደርስ ተለያየን። * ዛሬ ፈተናው ትንሽ ከበድ ይል ነበር፤ ግን እንደምንም የጠዋቱን ጨርሰን ወጣን። ከአቤላ ጋር ውጪ ላይ ቁጭ ብለን ስንዛዛግ ማሂና ባቢ መጥተው ተቀላቀሉን። ፈተናውን ስላልሰሩ ተናደዋል። <<እና ፈተና እንዴት ነበር?>> እንዳገኘኋቸው ያቀረብኩት ጥያቄ ነበር። <<አቦ ተይን ቀናችን አይደለም የሆነ ገገማ ፈታኝ ነበር ምንም አላሰራንም>> ባቢ ብስጭት ብሎ መለሰ። <<ማሂ አንተስ አልሰራህም?>> <<ባክሽ ከኃላ ላሉት አስኮረጅክ ብሎኝ ቀማኝ ያውም ሣልጨርስ በቃ>> <<የከሰዐቱን ትሰራላችሁ። እእ.. አይዟችሁ እሺ...>> ሁለቱም አሳዘኑኝ አቤላም እነሱ ስላልሰሩ ደበረው። <<አቦ በቃ እዚው ዱቅ እንበል ሙዳችን ተከንቶማ ወዴት እንቀየሳለን>> አቤላ ከአንዱ ዛፍ ስር ሲቀመጥ አብረውት ቁጭ አሉ። <<ኢብቲ ነያ ተቀመጪ>> ባቢ እንድቀመጥ ተጠጋልኝ። <<ኧረ መስጂድ ልሄድ ነው ባቢ..>> <<እንዴ ምን ልትሰሪ?>> ማሂ በመገረም እያየኝ። <<ሃሃሃ አንተ ደግሞ ልጫወት ልበልህ..>> አጠያየቁ ገርሞኝ እያየሁት። <<ጀለሶችሽ መጡ>> አቤላ ወደነ ዩሲ እየጠቆመኝ። <<ደግሞ እዳትቆዪ አብረን እንገባለን>> <<እሺ በቃ ቻው..>> ተሰነባብተናቸው ተለያየን። * ከነ ዩሲ ጋር መስጂድ ደርሰን ተመለስን። የመጨረሻውን ፈተና ለመፈተን ሁሉም ጓጉቷል መፈተኛ ጊቢ ጋር ስንደርስ ተማሪው ጢቅ ብሏል። ጭራሽ የሚገባው በፍተሻ ነው፤ ሰልፉ ደግሞ ረዘም ያለ ነበር። መጨረሻ ላይ እኛ ነበርን አቤላ መጥቶ ጠራኝና ከፊት ሊያስገበኝ እነባቢ ወደ ተሰለፉበት መሄድ ጀመርን። <<እኔ ምልሽ ኢብቲ>> <<ወዬ አቤላ>> <<ከዛሬ በኃላ በቃ አንገናኝም ማለት ነው?>> <<ኧረ ለምን? ውጤት ሲወጣ እንገናኛለን እኮ..>> <<እስከዛስ አንቺም ጀለሶችሽም ስልክ የላችሁ ..ከነ ማሂ ጋ እኮ እያወራን ነበር እሱም ደብሮታል ልንለያይ መሆኑ...>> <<እህ አቤላ...ዘጠኝም አብረን እንመዘገባለን አያሣስብም ኮ....>> <<እሱማ አዎ ግን ያው...>> የምናወራውን ሳንጨርስ እነ ባቢ ጋ ደረስን << እነዚያው እነባቢ.. ነይ በዚህ ጋ>> ባቢ የሃይላንድ ሚሪንዳ እየጠጣ ነበር። አቤላን ሲያየው ለማሂ አቀበለው። <<ኧረ አልሰማቹም ብትጨርሱት>> አቤላ ፈጠን ብሎ ወደ ማሂ ሲንደረደር፤ ማሂ ለአቤላ ወይስ ለባቢ ሊያዳላ ነው ብዬ የሚሆነው ስጠብቅ... ያላስብኩት ነገር ተፈጠረ። <<እንዴ ማሂ!!>> ሚሪንዳውን የሚጠጣውን ማሂን አይቼ ከድንጋጤ ጋር ስጮህ ሶስቱም ወደኔ ዞሩ። መደንገጤን ሲያዩ መጨቃጨቃቸውን አቆሙና ማሂ ላይ አፈጠጡበት። ማሂ ግራ ገብቶት <<እእ ምን ሁነሽ ነው አስደነገጥሽኝ እኮ>> የተደፋበትን ሚሪንዳ እየጠራረገ ከኔ ምላሽ ይጠብቃል። <<እህ በረመዳኑ ትጠጣለህ እንዴ! ፆመኛ ነሃ ረስተኸው ነዋ...>> አይን አይኑን ሳየው አንገቱን ደፋ። እነ አቤላ ዝም ብለው ፊት ፊታችንን ያዩናል። <<እናንተ ልጁን አሳሳታቹታ...ሃሃሃሃ ቀልበ_ቢስ ሁላ። ማሂ በል ተጉመጥመጥ>> ማሂ ካቀረቀረበት ሲነሳ አይኑ በእምባ ተሞልቶ ነበር። <<እህ ማሂ ምን ሆነህ ነው?>> ጥያቄን ሳይመልስ ከመሮጥ ባልተናነሰ መልኩ ከአጠገቤ ራቅ ብሎ ሄደ። <<ምንድነው ባቢ ንገረኝ?>> ግራ እብደገባኝ በሚያሳብቅ አስተያየት። <<ኧረ ምንም አላውቅም..>> ፊቱን አዞሮ መለሰልኝ። <<አቦ ተናገር በናትህ ምንም እየገባኝ አይደለም ችግር አለ እንዴ? ማሂ ለምንድነው እንዲህ የሚሆነው?>> <<እሺ ለሱ አትናገሪውም እእ ብንግርሽ? ማይልኝ..>> <<ኡፍ ባቢ አዎ ተናገር...>> እስክሰማው ጓጓቻለው። ምን ይሁን? ማሂ ምንድነው ያልነገረኝ? ለምንስ ይፈራኛል? የራሴ ጥያቄ ነው። <<ምን መሰለሽ ኢብቲ...>> ባቢ ንግግሩን እንዲቀጥል በጭንቅላቴ ምልክት ሰጠሁት። <<ማሂር እንዳንቺ አይደለም>> <<ማለት?>> ምንም ለማለት እንደፈለገ አልገባኝም። <<ስልሽ አለ አይደል... ምንም አያውቅም>> <<ባቢ በግልፅ ንገረኝ። እሱ ህጻን አይደለም እኮ ምንድነው የማያውቀው?>> <<ማሂሮ ኮ አይሰግድም፣ አይፆምም በቃ ስለ እምነታቹ ምንም አያርፍም... እንዳንቺ ቁርዐን ቤት ምንናምን እሱ ጋ ወፍ የለም! አላ በቃ ማወቅ ይፈልጋል፤ ግን ደግሞ የሚረዳው ሰው አላገኘም። አንቺ ደግሞ በጣም ጎበዝ ነሽ እኔ ከማውቃቸው.. እሱም ደግሞ ለዛ ነው አንቺን መቅረብ የሚፈልገው። ብዙ እንደምትረጂውና እንደምትለውጪው አምኖ ነበር። ግን አንቺ ልታዳምጭው አልፈለግሽም፤ ስለሱ እኮ ምንም አታውቂም። ሊነግርሽ ቢፈልግም መንገዱን ትዘጊበታለሽ፤ በፊት ሙስሊም ጀለሶች ነበሩን እነሱ ከማሳወቅ ይልቅ ሙድ መያዣ አደረጉት። ለምን? ባለማወቁ ምክንያት! ምንአልባት አንቺ ታስተካኪዋለሽ ብለን ነበር፤ ግን ምን ያረጋል...በቃ ምንም ነው ልትረጂው ያልቻልሽው... ኢብቲ እንደነገርኩሽ ካወቀ ያልቅልኛል። የነገርኩሽም አንቺም ሳታውቂ እንዳሁኑ በሞራሉ ከምትጫወጪበትና እሱም ባንቺ ቅስሙ ከሚሰበር ብዬ ነው። በቃ ሁሉንም ባላየ እለፊው አታስጨንቂው፤ በናትሽ አሁንም በቃ እያለቀሰ ነው የሚሆነው እስቲ ልየው...>> ባቢ ከአይኔ እስኪጠፋ በሄደበት መስመር ፈዝዤ ቀረሁ። ምንድነው የሆነው? እኔስ ምንድነው ያደረኩት? ምንድነው የሰማሁት? ሁሉም ድንግርግር አለብኝ። ጭራሽ ያልጠበቁት ነገር በአንዴ መዐት የወረደብኝ ያህል ከበደኝ። ከየት መጣ ያላልኩት እምባ ሂጃቤ ድረስ አበስብሶኛል። መሬትና ሰማዩ እየተሽከረከረ መሰለኝ፤ አይኔ ብዥዥዥዥ አለብኝ። ምን ያህል ደቂቃ እዛው እንደነበርኩ አላውቅም ብቻ አቤላ መጥቶ ፊቴን እንዳስታጠበኝ ትዝ ይለኛል። ከዛም መፈተኛ ክፍል ውስጥ ምን ሁና ነው ብለው ሲጠይቁትም ይሰማኝ ነበር። አጠገቤ ቁጭ ብሎ አይዞሽ ምናምንም ሲለኝም ነበር።
2340Loading...
31
ከደቂቃዎች በኃላ ተረጋጋሁ፤ ወደራሴ ስመለስ የማጠቁርበት እርሳሴን መፈለግ ጀመርኩ። . <<አቦ አስቦክተሺኝ ነበር እኮ...ሆ... ወይ አትናገሪ ወይ ነቃ አትዪ.. በስማም የሌለ ክብድ ብሎኝ ነበር ኮ። ባለቀ ሰዐት ጉድ ልንሆን? ዘጠና ብዬ ስጎርር ዘጭ ልታስብዪኝ!? ፈጣሪ ሆይ ተመስገን>> ብሎ ብርክክ ሲል ክላሱ ሁላ በሳቅ አጥለቀለቀው። <<ሃሃሃ...አንተ በቃ ፈታ አልክብኛ? ኧረ ግን አቤላ ተቀየምኩህ>> እንደማኩረፍ ብዬ እያየሁት። <<ማሪያምን ኢብቲዬ ጭንቅ ብሎኝ ነበር.. >> <<ኧረ ፈታኙ መጣ>> <<ስድስት ስድስት>> ሲል ሁሉም ተስተካክሎ ቁጭ አለ፥ ፈታኙ። * <<የዛሬው ደግሞ ከስከዛሬው ሁሉ ቀላል ነበር ደስ ሲል አ አቤላ? ደግሞ በጣም ቀላል..>> ከመፈተኛ ክፍል ወደ ውጪ እየወጣን። <<ኧረ ምን አውቄ.. ቀለሜዋ አንቺ ..ብቻ ላጥ ላጥ ስታረጊው እኔም ከስር ከስርሽ ኮፒ አደረኩልሽ>> ደስ እንዳለው ከፊቱ ላይ ይነበባል። <<ደግሞ ማንም አልወጣም እኮ... አባቴ.. ቸኮልን መሰለኝ>> ዞር ዞር ስንል ከሁለታችን ውጪ ማንም አልነበረም። <<እና የዛሬው ፈተና ኮ ያንቺ ስለሆነ ነው። ቲቸር ራሱ ባይሎጂን ከኢብቲሳም ገልብጡ አልነበር ያለው? አንቺና ባይሎጂ ኮ በቃ ቤተሰብ ሆናችሁዋል።>> <<ሃሃ አንተ ደግሞ አታመሳስል እኮ.. ስማማ... ማሂ ና ባቢ ሰርተው ይሆን?>> <<ኧረ እንጃ በናትሽ፤ ካልሰሩ የመጭ ነው ሚደብረኝ... ደግሞ ማሂሮ ሲገባ ከፍቶት ስለነበረ ተረጋግቶ የሚሰራም አይመስለኝም።>> እንዲሁ እየተነጋገርን የተወሰኑ ተማሪዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። ከተማሪው መሃል ባቢ ወደኛ መጣ። <<እእ እንዴት ነበር ተሰራ?>> አቤላ አይን አይኑን እያየ ይጥይቃል። <<ባክህ ያው ነው ትንሽ ነው የሰራሁት..>> <<እና ብራዘርስ እየሰራ ነው..?>> <<ማ? ማሂሮ? እሱኮ ሄደ>> <<ወዴት?>> ሁላታችንም ሳናስበው ጮክ ማለታችን አስደንግጦት <<እህህ... ቀስ በሉ፤ እቸኩላለው ብሎ ላጥ አለ። ምንም አላናግር ብሎኝ ሄደ ወዲያው እንደወጣን...>> <<በቃ ቻው እሺ>> ብዬ እኔም ትቻቸው ሄድኩ። አቤላ ቢጠራኝም እየፈጠንኩ በሌላ አቅጣጫ ሄድኩ። እነዩሲ ሲመጡ በነኢክሩ ሰፈር አድርገን ሄድን፤ ሁላችንም ደብሮናል። እንደ ሌላው ቀን ፈታ ብለን ማውራት አልቻልም። ያው ትምህርት ከተዘጋ ሁሌ ስለማንገናኝ አብረን ስለ ማንውል እንጂ መድረሳ ለአጭር ሰዐት እንገናኛለን፤ ግን እንደ ልብ የምናወራበት ሰዐት አናገኝም። እሱን እያስብን ለመለያየት በቆምንበት መንገድ ላይ ብዙ ከቆየን በኋላ እንደምንም ተቃቅፈን ተለያየን። እኔና ዩስ እሰከ ሰፈር አንድ ላይ ብንጓዝም በሃሳብ ግን ሁለታችንም ለየብቻ ነበርን። . . #ክፍል_11 ይቀጥላል...
1560Loading...
32
የባከኑ ቀናት ክፍል አስራ አንድ (ሂባ ሁዳ) . . እነ ዩሲ በር ጋር ደርሰን ሁለታችንም ቆምን። እኔ ዝም ብያት ወደ ቤታቸው ስገባ ተከተለችኝ፤ ሳሎን በግማሽ በኩል በተነጠፈው መጅሊስ ላይ ዘፍ አልኩ። ዩስሪ ከደቂቃዎች ቡኃላ ልብሷን ቀያይራ አጠገቤ ቁጭ አለች፤ ዝም ብላ እኔ እስክነግራት ትጠብቃለች። ሁሌም በከፋኝ ሰዐት እነሱ ቤት ሄጄ ነው የሚወጣልኝ... ሁሉንም ዝርግፍግፍ አድርጌ እነግራታለሁ። ከኔ በላይ እሷ ትጨነቃለች፤ ዛሬ ግን ዝምታዬ በዛባት መሰለኝ ለማውራት ተገደደች። <<ኢብቲዬ ሀቢብቲ ምንድነው የሆንሽው? ቅድም ጀምረሽ ልክ እንዳነበርሽ እኮ አውቃለሁ፤ ብቻችንን ስንሆን እናወራለን ብዬ ነው ዝም ያልኩት>> ምንም ሳልመልስላት ስቀር አላስቻላትም ድጋሚ ሌላ ቃላት ሰነ ዘረች... <<ማሂ ነው አይደል? እንዲ ያስከፋሽ.. እእ ኢብቲ ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ በአላህ እያስጨነቅሽኝ ነው>> <<ዩሲ እሱኮ ምንም አላደረገም እኔ ነኝ እንጂ የጎዳሁት። ልቡን ስብርብር ነው ኮ ያደረኩት ምን አይነት ልጅ ነኝ!? አመት ሙሉ አጠገቤ ከችግሩ ጋር ሲታገል የነበረን ሰው እንዴት እገፋዋለሁ?...ዩሲ ንገሪኝ እስቲ ምን አይነት ግዴለሽ ሰው እንደሆንኩ..>> በመሃል ትንፋሼ መቆራረጥ ጀመረ፤ ከዚህ በላይ ማውራት አልቻልኩም። ዩሲ አቅፍኝ ማልቀስ ስትጀምር ይባሱኑ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። ሰዐቱ ወደ መምሸት ሲጠጋጋ ፊቴን ታጥቤ ወደ ቤት ገባሁ። ወንድሜ ፈተና ያልሰራሁ መስሎት ቢጨነቅም ትንሽ እንደደከመኝ ተናግሬ ከኢፍጣር ቡኃላ ወደ መኝታዬ ሄጄ ከራሴ ጋር ብዙ ተጨቃጨቅኩ። ከረጅም የድካም ሰዐታት በኃላ እንቅልፍ አሸለበኝ። * * ከሁለት ወራት ቡኃላ የሚንስትሪ ውጤት ለመቀበል ትምህርት ቤት ተሰብስበናል። ከረጅም ጊዜ የናፍቆት ወሬ በኃላ ተማሪዎቹ ውጤት ለመቀበል ተሰለፉ፤ እኛ መጨረሻ ላይ እንቀበላለን ብለን ጥግ ላይ ቁጭ አልን። እነ አቤላ ተሰልፈዋል እሱ ዘጠና አመጣለሁ ብሎ አሲዟል፤ ባቢም ከኃላው ነበረ፤ ማሂን ግን አላየሁትም። ዛሬ ደግሞ በጣም እፈልገዋለሁ... ብዙ ነገር ላወራው ተዘጋጅቼበት ነው የመጣሁት፤ በዛ ላይ ናፍቆኛል። ባቢ ጋር ሄጄ ስጠይቀው እንደማይመጣ ነገረኝ። ለምን ምናምን ሣልል ቀጥ ብዬ ስሄድ ከኃላ ሂጃቤ ሲጎተት ለማስለቀቅ ዞር ስል በአየሁት ነገር ድንግጥ አልኩኝ <<ኢብቲዬ>> ብሎ እጁን ሲዘረጋ እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ስጠጋው እቅፍ አደረገኝ፤ ምናልባት መተቃቀፋችን የመጀመሪያም የመጨረሻም መሰለኝ... ትንሽ እንደቆየን ድንግጥ ብዬ ከእቅፉ ወጣሁ። <<እእ ይቅርታ ሳላስበው ነው...>> እንደመሳቀቅ ሲል አሳዘነኝ። <<ኧረ ችግር የለውም ማሂ ...>> <<እና ደህና ነሽ? እንዴት ነሽ ተጠፍፋን ኣ?>> <<አለሁ አልሃምዱሊላህ አንተ እንዴት ነህ እእ ሁሉ ሰላም ነው?>> <<አዎ ሰላም ነው። ደግሞ ረፍቱ ተስማምቶሻል እእ አምሮብሻል..>> <<ሙድ አትያዝብኛ አንተ ነህ ያማረብህ እኮ...>> <<ሃሃሃ ኧረ ባክሽ... ስገባ እኮ ሳይሽ ወዳንቺው መጣሁ፤ ጀለሶችን አላገኘዃቸውም ከመጣሽ ቆየሽ እንዴ?>> <<ኧረ እዛ ጋር ተሰልፈዋል። አንተን ፈልጌ እኮ ባቢ አይመጣም ሲለኝ ወደዚህ ስመጣ ነው ያገኘሁህ አላወቁም መሰለኝ እንደምትመጣ...>> <<ኧረ ያውቃል ሊያዝግሽ ፈልጎ ነው ይሄ ዱዝ..እና ፈልገሽኝ ነው እእ?>> ፊቱ ላይ ፈገግታ ሞላ ሞላ ብሏል። <<አዋ! ማሂ እፈልግሃለው ..እንዲ ቁመን አይደለም በቃ እንጨርስና እናወራለን።>> <<ኧረ ደስ ይለኛል..በቃ እነ ባቢ ጋ ልሂድ እስኪ ..>> ፈጠን እያለ ወደ ተሰለፉት ልጆች አመራ። እሱ ወዳዛ ሲሄድ እነኢክሩ ወደኔ መጡ። ኢክራም ቸኩላ ሰለነበረ ካልተቀበልኩ ብላ ሄድን፤ እኔ ግን ፈራሁ። ውጪ ላይ ቆሜ እነሱ ገቡና እየሳቁ ወጡ እንደምታልፍ እርግጠኛ ነበርኩና ጥምጥም አልኩባት፤ ወዲያው ሸኝተናት ተመለስን። * እነ ባቢ ለመቀበል እየገቡ ነበር እኔን ሲያዩ ቆም አሉ፤ እኔም ወደነሱ ሄድኩ። <<ባቢ ምነው? እእ..>> ሶስቱም የተጨነቁ መሰለኝ። <<ኢብቲ ሁላችንም እናልፋለና? ፈራን እኮ..>> አቤላ ቀጠለ <<እኔ እኮ ምንም አልመሰለኝም ነበር ኡፍፍ አሁን ግን እነዚህ አንቦቆቦቁኝ>> አቤላ እንዲህ ማለቱ አስገርሞኛል። <<አቦ ፈታ በሉ እናልፋለን። አሁን ግቡ በቃ..>> <<ኢብቲ አንቺ ለምን አሁን አትቀበይም ነይ አብረን እንግባ እእ..>> ማሂ። <<አይ ቀስ ብዬ እቀበላለው እስቲ የአቤላንም ልየው። ያው አንዳይነት ነገር ነው እኮ ውጤታችን የሚሆነው...>> <<በናትሽ ነይ አብረሽኝ ..እንደውም የቅድሙን አሁን እናውራና በኃላ አብረን እንቀበላለን እእ..>> <<ኧረ አያሣስብክ እሱ ይደርሳል ..>> <<እኔ ግን አሁን ብናወራ ይሻለኝ ነበር..ደግሞ አሁንም ስልክ የለሽማ?>> <<አዎ ምነው? ልትገዛልኝ ነው? ሃሃሃሃ>> <<የኔን ውሰጂው እኔ ኮ ሌላም አለኝ እቤት ...ሲሙን ላውጣውና ስልኩን ይዘሽው ትሄጃለሽ በቃ እሺ..>> <<አንተ ደግሞ አታምርራ .. እኔ እኮ ቀፎ ስለሌለኝ አይደለም እቤት አይፈቀድልኝም። ገና በስምንተኛ ክፍል ነው የምባለው..>> <<እንዳዛ ከሆነ እሺ፤ ግን እኮ ቁጥሬ ራሱ የለሽማ? ነይ ልፃፍልሽ ..>> <<በኃላ ትሰጠኛለህ ኧረ ግባ እነ ባቢ አስጠበካቸው እኮ..>> እሺ ብሎ ወደ በሩ አመራ። በሩ ጋር ሲደርስ ዞር ብሎ አየኝ፤ በጣም ፈርቷል። አስተያየቱ አሁንም አይኔ ላይ አለ። ርቆ እንደሚሄድ ሰው ፍዝዝ ብሎ ነበር፤ እንዲገባ በአይኔ ምልክት ስሰጠው ገባ። * ከነ ራቢ ጋር ባቢ ማሂ ና አቤላ ስንት እንደሚያመጡ እየገመትን፤ የሶስቱንም ግምት ያገኘ ሎሊፖፕ እንደሚገዛለት ተስማምተን እስኪወጡ ዛፍ ስር ቁጭ ብለን መጠበቅ ጀመርን። ከደቂቃዎች ነኃላ የሆነች ልጅ እያለቀሰች ስትወጣ ደንግጠን ወደ በሩ ሄድን። ወደ ዘጠነኛ ክፍል ስላላለፈች ወደ አንዱ ጥግ ሄዳ ማልቀሷን ቀጠለች። ፍርሃታችን ይባሱኑ ጨመረ፤ ራቢ እጄን ጭምድድ አድርጋ <<ኧረ ፈራሁ እኛስ እናልፋለን ወይይ?>> አለች። <<እንጃ አላውቅም። ራቢ እነ ማሂ ለምን ቆዩ?>> ዩሲ ነበረች በር በሩን እያየች። ወዲያው ማሂ እየሮጠ ወጣ ከተቀመጥኩበት ብድግ ብዬ በፍጥነት ወደሱ ስሄድ እነ አቤላም ከኃላው እየሮጡ መጡ። እሱ ጋር ከመድረሴ በፊት ወደ ጊቢው መውጫ እየፈጠነ መራመዱን ቀጠለ ከኃላ ባቢ ቢጠራውም ሊቆም አልቻለም። እንደምንም ልደርስበፍት ሁለት እርምጃ ያህል ሲቀረኝ የጊቢውን በር በእግሩ ጠልዞ ወዲያው ወጣ። ተከትዬው ብወጣም እሱ ላይ መድረስ አልቻልኩም። ብጠራውም እጁን እያወናጨፈ ርቆ ሄደ። እኔም ባለሁበት ከአይኔ እስኪጠፋ ተከተልኩት። እነ ዩሲ መጥተው ወደ ውስጥ ገባን አቤላና ባቢ ተመልሰው መጡ። <<በናትሽ ማሄሬ ኮ ወደቀ በአንድ ነጥብ ቲሽሽሽ ብሽቅ ነው ያኩት>> አቤላ ተናዶ ያወራል፤ ሌላው ዝም ብሎ ቁጭ ቁጭ ብሏል። ዛሬም ያልሆነ ስህተት ሰራሁ፤ ምን አለ መጀመሪያ ብናወራ እሱም እናውራ ሲለኝ እሺ ብለውስ? በቃ ሁሌ የራሴን ሃሳብ ብቻ ነው የምፈፅመው። ለዛሬ እንኳን እሱን ብሰማውስ እንዴት ከስህተቴ አልማርም? እሺ ካሁን ቡኃላ የት ነው የማገኘው? ጭራሽ ስልኩ ቁጥሩን ሲሰጠኝም አልተቀበልኩትም! ኧረ ኢብቲሣም ምንድነው ያደረግሽው? የነበረኝን አንድ እድል ባልሆነ መንገድ አጣሁ እኮ። ሁለት ወር ሙሉ ስጠብቀው የነበረው ቀን በአንዴ እንዲህ ምንም ሳላደርግ ሊያልፈኝ ነው እንዴ? እነዚያ የባከኑ ቀናቶችን በዛሬ አስተካክላው ብዬ ምንም ሳላደርግ እንዲሁ ባክነው ቀሩ ማለት ነው?
2480Loading...
33
. <<ኢብቲ ተማሪው እኮ ተቀበለ እኛ ብቻ ቀረን እእ እንቀበል በቃ ቁርጣችንን እንወቀው>> ራቢ ከገባሁበት ሃሳብ መለሰችኝ እሺ ተባብለን ለመቀበል ተስማምተን ወደ በሩ ጋ ስንደርስ አቤላ እየወጣ ተገጣጠምን የውጤቱን ካርድ ሳይ ልቤ ምቱን ጨመረብኝ። <<እእ አቤላ እ.ን.ዴ.ት ነው..>> <<አቦ ተይኝ እኔ ደግሞ አልፋለው ማለቴ ድሮም ካንቺ ሰርቼ>> <<ማለት?>> ዩሲ ደንገጥ ብላ ወረቀቱን ለማየት ስትጠጋው። <<ቲ! ያው ናችሁ። ምን የወደኩበትን ለማየት ምን አስቸኮለሽ ዞርበይ ከዚህ ሲያስጠሉ>> ሶስታችንንም ገልመጥ አድርጎ አየን። <<በናትህ አቤላ ንገረኝ ወደቅን ነው የምትለኝ? ድምፄ ከፍ እያለ መጣ።>> <<አቤላ አትበይኝ ዱዝ! አቤል ነው ስሜ። አው እንኳን ደስ አለሽ እኔ ወደኩኝ ከሌላው ብሰራስ አንቺን አምኜ ሙሉ ካንቺ መስራቴ..>> ከዚህ በላይ አልሰማሁትም፤ እየተቻኮልኩ ወደ ቢሮው ገባሁ <<ይቅርታ የኔን ወረቀት ..>> <<እንዴ ኢብቲሳም የት ጠፍተሽ ነው እስካሁን?>> ባይሎጂ አስተማሪያችን ስሜን እየፈለገ። <<እሲቲ ቁጭ በይ እስከዛው>> እንድቀመጥ ጋበዘኝ። ቢለኝም እዛው መቆምን መረጥኩ... እስኪያገኘው ጨነቀኝ። አንድ ወረቀት ነጥሎ እንደያዘ። <<ምን ነክቶሽ ነው ግን ምን ሁነሽ ነበር?>> <<ማለት ቲቸር? መቼ?>> ግራ እየተጋባሁ ጠየኩት ... <<መቼ? ለፈተናው ነዋ። ጥሩ ጎበዝ ልጅ አልበርሽ እንዴ? በአንዴ ምንድነው እንደዚህ የቀየረሽ>> አስተማሪው አፈጠጠብኝ <ምነው ባልገባሁ> አልኩኝ በውስጤ። <<ቲቸር ም.ን.ድ.ነው እ ውጤቴ?>> የሞት ሞቴን ጠየኩት። <<እኛማ ብዙ ተስፋ የጣልንብሽ ልጅ ነበርሽ፤ የትምህርት ቤቱንም ስም ታስጠሪያለሽ ብለን ጠብቀን ነበር አዝናለሁ ኢብቲሳም። አሉኝ ከምላቸው ዋነኛዋ ተማሪ እንዲህ አልጠበኩም ነበር አፍሬብሻለው...>> አይኖቼ በዕንባ እየተሞሉ ልቤ ምቱን ላይ በላይ ሲደጋግመው በሰማሁት ነገር ልዘረር ምንም አልቀረኝም። <<እና ወ.ድ.ቀ.ሻ.ል ነው..>> <<በሚያሳዝን ሁኔታ አዎ>> በተቀመጠበት ወንበር ወደ ኃላ ለጠጥ ብሎ እየተቀመጠ የምሆነውን ያያል። በምን ሃይል እንደሆነ ባይገባኝም ወረቀቴን ስጠኝ ብዬ ጮኽኩበት። በር አካባቢ የነበሩት ዩሲና ራቢ ገቡ። እሱ ከቦታው ሳይንቀሳቀስ.. <<ብሰጥሽስ ምን ያደርግልሻል>> ብሎ የሹፈት ፈገግ አለ። እነ ራቢ ደንግጠው እርስ በርሳቸው ይተያያሉ። ይባሱኑ ብሽቅ አልኩና <<ወረቀቴን ስጠኝ ብወድቅስ ምን አገባህ>> ብዬ ከእጁ ላይ መንትፌው ወደ ውጪ ወጣሁ። ራቢ ተከትላኝ ወረቀቱን ተቀበለችኝ፤ ራቢ ለዩሲ <<ነይ! ነይ!ቶሎ በይ>> ስትል ዩሲ ምንድነው ብላ ራቢ ጋር መጣች። እኔ መቆም አቅቶኝ ከዚህ ወደዚያ እሽከረከራለሁ፤ በመሃል ራቢ <<የስሥሥሥሥሥሥሥሥ>> ብላ ስትቀውጠው ከዩሲ ጋር ተቃቀፉ። <<ኢብቲ ነይማ አፍጥኝው>> ብላ ወደኔ መጣች። እጇን ወረቀቱ ላይ እየጠቆመችኝ ትስቃለች፤ 96 ይላል ፁሁፉ። <<እእ.. ደስ ይላል ራቢ። ያንቺ ነው የዩሲ?>> ብዬ ሁለቱንም አፍራርቄ ሳይ ይስቃሉ አብራቼው ፈገግ ለማለት ስሞክር <<ኢብቲ እይማ>> ብላ ድጋማ ከወረቀቱ ላይ ሌላ ነገር አስነበበችኝ። <ኢብቲሳም ማህሙድ> ይላል። <<ማለት?>> ሁለቱም ላይ አፈጠጥኩባቸው። <<ያንቺ ኮ ነው 96 የኔ ውድ ነቀነቅሽው ኮ!>> ብላ ጥምጥም ስትልብኝ ደግሜ አየሁት ዩሲም ተጨመረች። በመሃል <ሰርፕራይዝ> ሚል ድምፅ ሰማን። ዞር ስል አቤላ እየሳቀ ነበር፤ እኔ አልፌ እሱ መውደቁ ትዝ ሲለኝ ወረቀቱን ለራቢ ሰጥቻት ወደሱ ሄድኩ፤ <አቤላ..> ስለው ምንም ሣይመልስልኝ ወረቀቱን ሰጠኝ የማየውን ማመን ስላቻልኩ እሱን አየሁት <<አዎ ነቀነቅነው 92>> ብሎ ሳቀ <<ውይኔ ደስ ሲል>> ብዬ ስጮኽ <<ተጫወትንብሻ ከቲቸር ጋ!>> ብሎ ከት ብሎ ሳቀብኝ። ብሽቅ አልኩና ልመታው ማሯሯጥ ጀመርኩ። . . #ክፍል_12 ይቀጥላል...
2400Loading...
34
የባከኑ ቀናት ክፍል ዘጠኝ (ሂባ ሁዳ) . . <<በቃ እደጠረጠርኩት... ይወድሻል..>> ራቢ ነበረች። <<አንቺ ደግሞ ሁሌ መጠርጠር.. እንደዛ እንኳን አይሆንም ዝም ብለሽ ነው።>> ምንም ልትሰማኝ አልቻለችም። <<አንቺ እኮ ቆየ ይወዳታል ማለት ከጀመርሽ፤ አይደለም ይሄ ተጨምሮ>> ዩሲ የቀረውን ምግብ እየጎረሰች። <<እሺ ካላመናችሁኝ የባለፈው ብቻ እኮ በቂ ማረጋገጫ ነበር እኮ እእ ምን ልትሉ>> ሁለታችንም ተያይተን <<የቱ?>> አልናት ለማስታወስ.. <<ባለፈው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ጊቢ ውስጥ ሲከበር ማሂር ስልኩን ክፍል ውስጥ ቻርጅ ላይ አድርጎ <ማንም እንዳይነካው!> ብሎ ወጣ። ቻርጅ አስቸግሮት አናዶት ነበር... አቤላ ላይ ሁላ <ለምን ነካኸው> ብሎ ጓ! ብሎ ነበር። እሱ ሲወጣ ኢብቲ ገባች። ስልኩ የማሂ እንደሆነ ስታውቅ ጋላሪ ላይ ገብታ ስትመሰጥ የሆነ ሰው ሄዶ ለማሂር ነገረው። ከውጪ ሲገባ በዛ አካሄዱ ላየውሟ የሌለ ያስፈራ ነበር፤ በሩን እንዴት ብርግድ እንዳደረገው ኢብቲም ደንግጣ ስልኩን ለቀቀችው፤ ማሂር ሄዶ እነሣውና <አንቺ ነሽ እንዴ የነካሽው? ደግሞ ተይው ግላሱ ነው አልተጎዳም> ቢላትስ፤ ከኋላ የነበረው ተማሪ እኮ ከአሁን አሁን አጋጫት እያለ... ሃሃሃሃ... አጅሬው ኢብቲ መሆኗን ሲያውቅ ምንም እንዳልተፈጠር <ስጨርሺ ቻርጅ ላይ አድርጊው ካስቸገረሽ ደግሞ ጥሪኝ> ብሎ ላሽ ቢልስ። እኔ ደግሞ ለኢብቲ ያለውን ቦታ ማየት ቻልኳ! እእ ምን ልትሉ ነው?>> <<እኔ ግን ምንም እንዳዛ አላስብም ራቢ። ምን አልባት ሌላ ነገር ይሆናል እኮ ማን ያውቃል ..>> ሃሳቧ የሚያሳምን ነገር አለው፤ ግን ለመከላከል ሞከርኩ። <<እኔም ኢብቲ እንዳለችው ነው። ራቢ እኛ በዚህ እድሜያችን እንዴት ይሄን እናስባለን? ማይሆን ነገር እኮ ነው። እንርሣው ባይሆን የቅድሙን ጥያቄዎች እንስራቸው ምን ትላላችሁ?>> ዩሲ ጉዳዩን ለማስቀር ተባበረችኝ። <<ካላችሁ ምን ይደረጋል ግን እኔ ያልኩት እውነት መሆኑን በቅርቡ ታረጋግጣላችሁ ጠብቁ ብቻ <ራቢ ብለሽ ነበርሽ> ስትሉ መስማቴ የማይቀር ነው>> <<አንቺ ደግሞ አንዴ ነገር ከጀመርሽ ቡኃላ አትፋቺም ዩሲ እንጀምር በቃ!!>> ነገሩን ዘጋሁት። * ያን ቀን ከትምህርት ቤት መልስ ጥያቄዎችን ሰርተን ከተለያየን በኃላ ዛሬ መገናኘታችን ነው። እንደተለመደው ክፍል ገብተን መማር ከጀመርን ሰዐታት አልፈዋል። ምሳ ሰዕት ላይ ዩሲ ማሂን እንዳወራው አስታወሰችኝና የተቀመጠበት ሄድኩኝ። <<ሰላም ማሂሬ>> ለማውራት እንዲመቸኝ ከጎኑ እየተቀመጥኩ። <<እእ እንዴት ነሽ?>> <<አልሃምዱሊላህ አለሁልህ.. ምነው አሞሃል እንዴ?>> ፊቱ ልክ አለመሰለኝም። <<ብታመምስ...ማንም ለማከም ፍቃደኛ ካልሆነ..>> <<ማለት እንዴት?>> <<ካልገባሽ አንድ ቀን ይገባሻል...>> ምንም ማሂ አልመስልሽ አለኝ። ቢያንስ የቅዳሜውን ባወራው በዛው ወሬ መቀየሻ ይሆነኛል ብዬ አሰብኩ። <<እኔ ምልህ ማሂ..>>ምን ብዬ እንደምጀምርለት ሃሳብ ስፈልግ። <<ምን ነው ችግር አለ?>> ከአይኔ ላይ ፍርሃቴን ያነበበው መሰለኝ። <<ሣይሆን... ቅዳሜ በጣም ቸኩዬ ስለነበረ ነው የሄድኩት እሺ ..>> <<እሺ>> እሱ በግድ ፈገግ ለማለት ይሞክራል፤ እኔ ደግሞ እያባበልኩት መሰለኝ። ትንሽ ዝም ካልን በኃላ <<እና አሁን ንገረኛ ምንድነው ማሂ ...>> <<ኧረ.. አሁንስ ጊዜ አለሽ ማለት ነው?>> <<ያኔ እኮ...>>አላስጨረሰኝም <<ነገርሽኝ እኮ በቃ!>> <<እህህህ ማሂ አሁን ንገረኝ እያልኩሃ>> ንግግራችን ወደ ጭቅጭቅ መስመር መቀየር ጀመረ። <<ምን እንድነግርሽ ነው የምትፈልጊው?>> ድምፁ ላይ ቁጣ ታክሎበታል። <<ልትነግረኝ የነበረውን ነዋ ቀስ ለማለት እየሞከርኩ ...>> <<ተውኩት በቃ!>> <<እህህህ ማሂር አታድርቀኝ እንግዲ...>> <<ሁሉም ነገር ላንቺ ቀልድ ነዋ የሚመስልሽ..ለማንኛውም ማርፈድ ከትምህርት ቤት ይልቅ ህይወት ላይ ዋጋ ያስከፍላል!>> ሲቃ በተሞላበት ድምፅ። <<አመሰግናለሁ>> ብሎኝ እየፈጠነ ወደ ውጪ ወጣ። እኔም ምንም መናገር አልቻልኩም ነበር እዛው ቁጭ አልኩ። <ያ ኢላሂ ምን ጉድ ነው? ኡፍፍፍ ኢብቲሣም ምንድነው ያደረግሽው.. ቲሽሽሽ> በራሴ ተናደድኩ። ያኔ ጥዬው ባልሄድ ይሄ ሁሉ አይፈጠርም ነበር። ምናለ ባዳመጥኩት... በራሴ ተናድጃለው፤ ከፍቶኛልም። እዛው ወንበሩ ላይ ድፍት ብዬ ባለቅስ ደስ ይለኝ ነበር። * <<ምንሼ እስካሁን እእ? ስሚ አታዝጊ ተነሺና ተናገሪ...>> አንገቴን ቀና አድርጋ እስክነግራት ትጠብቀኛለች፤ ራቢ። <<ምንም አላለኝም>> <<ሃሃሃሃ ኧረ ባኪ እስካሁን አብራቹ ስትጫወቱ ነበራ ታዲያ ማን አሸነፈ? ሃሃሃ>> ራቢ የሚያበሽቅ ሳቋን ለቀቀችው። ምንም መናገር ስላልፈለኩ ዝም አልኳት። እሷ ግን ምንም ልትረዳኝ አልቻለችም። <<ኧረ ይሄ ነገር ምንድነው እእ? ሚስጥር ነው እንዴ እህቴ..>> አላስጨረስኳትም <<ኡፍፍፍ አንቺ ደግሞ ችግር አለብሽ አትፋቺም! ዞር በይ በናትሽ .. >> <<እህህ ኢብቲ በአላህ ምን ሁነሽ ነው?>> ድምጿ ይሰማኛል ላዳምጣት ግን አልፈለኩም። <<ውዴ ወዴት ነው ጥድፊያው?>>ዩሲ ነበረች። <<መጣሁ። እንዳትከተይኝ!>> ፈርታኝ <እሺ> ብላ እዛው ቀረች።ብቻዬን አንድ ጥግ ስር ቁጭ ብዬ ደቂቃዎች አለፉ። ልቤ መረጋጋት አልቻለም፤ ላስብ ብሻም ራሴን መሰብሰብ ግን አልቻልኩም። ከራሴ ጋር ስወዛገብ ጊቢው ጭር አለ። እኔም ወደ ክፍል ሄድኩኝ፤ ብዙ አልፎኛል መሰለኝ አስተማሪው እያረመ ነበር። ስገባ አላየኝም... ሄጄ ተቀመጥኩ። ወደ ኃላ ስዞር ማሂን አየሁት፤ መልሼ ዞሬ ተቀመጥኩ። ራቢ ፈርታኝ ፊቷን አዙራ ተቀመጠች። የመውጫ ሰዐታችን ደርሶ እስክንለያይ ድረስ ምንም ሳንነጋገር ተለያየን። . . #ክፍል_10 ይቀጥላል...
2540Loading...
35
የባከኑ ቀናት ክፍል ስምንት (ሂባ ሁዳ) . . ጥናቱን እንዳጠናቀቅን መሸምደድ ያለብኝን የመድረሳ ሃዲስ ለራሴ ማነብነብ ጀመርኩ። <<ኢብቲ ግን ምንድነው እንዲ ያጨናነቀሽ? ታውቆሻል ብቻሽን የምትለፈልፊ ነው የምትመስዪው እኮ ...>> ማሂ ግራ በመጋባት እያየኝ። <<ወይ መለፍለፍ... ባክህ እየሸመደድኩ ነው የግድ መጨረስ ስላለብኝ ነው እኮ ማሂ>> <<እህ ምንድነው የደበቅሽው እስቲ አሣይኝ ቦርሣሽን አንሺው...>> <<ይኸው አርበኢን ኪታቤ ነው እዚህ ስለማይፈቀድ ነው በቦርሣዬ ከልዬ የምሃፍዘው>> <<እና እቤትሽ አታፍዢም ደግሞ ምን ይጠቅምሻል?>> <<ማለት ምን ይጠቅምሻል? ዛሬ መድረሣ ፈተና ስላለን ነው የቸኮልኩት።>> ማሂ ግራ ተጋባ። <<መድረሣ? የምን መድረሣ?>> <<ሃሃ አታድርቀኝ ዞር በል ሰዐት አትሻማብኝ..>> <<የምሬን ነው እኔ እኮ አላውቅም መድረሣ ምናምን>> <<ውይ ማሂ በአላህ ዞር በል አልኩሃ>> ትኩረቴ ሁሉ መሸምደዱ ላይ ስለነበር እሱ ላለኝ ነገር ቦታ አልሰጠሁትም። <<እእ እ..ሺ..>> ብሎ ከአጠገቤ ራቅ አለ። እንደምንም ሸምድጄ ጨረስኩ። የትምህርት ጊዜው እንዳበቃ፤ እነኢክሩ ቀድመውኝ ሸምድደው ስለ ነበር ከነሱ እየተጠያየቅን ወደ መድረሣ መንገዳችንን ጀመርን። አንዳንዴ ከረፈደ ወይንም ፈተና ከሆነ ከትምህርት ቤት በዛው ነው የምንገባው፤ ቅርብ ስለሆነ ቶሎ ደረስን። ብዙ ተማሪ ስላልነበረ እኛ የመጀመሪያዎቹ ተፈታኝ ነበርን። እንደ ፈራነው አልነበረም እኛ ከሸመደድነው ጥቂት ነበር ፈተናው ላይ የነበረው፤ ሰዐታችን ሲደርስ ወደ ቤት አመራን ። * ጊዜው ከምንም በላይ ይፈጥናል፤ ሰሞኑን ስለሚኒስትሪ ፈተና ነው ጭንቃችን። አስተማሪዎችም የተለያዩ ጥያቄዎችን ያሰሩናል፤ በዛ ላይ ቅዳሜ ማጠናከሪያ ተብሎ መግባት ተጀምሯል። አስተማሪዎቹ ከሌላ ትምህርት ቤት እየመጡ ነው የሚያስተምሩን በጣም ምርጥ አስተማሪዎች ናቸው፤ ረባሹ ተማሪ ሣይቀር ነው በደንብ የሚከታተላቸው። ተማሪን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው በደንብ የገባቸው ይመስለኛል፤ ለዛም ነው የሚያስተምሩት ተማሪ የሚወዳቸውና የሚከታተላቸው። . ዛሬ ግን ከሌላው ቀን ትንሽ አቆይተውናል እኔ ደግሞ አዛን እስኪል እቤት መድረስ አለብኝ። ቅዳሜ ቅዳሜ አክስቴ ጋር ተሰብስበን እንሄዳለን፤ ዙሁር ሁሉም ቤተሰብ አክስቴ ጋር ነበር የሚሰግደው አሁን እኔ ስለማረፍድ ጥለውኝ ይሄዳሉ። ታላቅ ወንድሜ ይጠብቀኝና ከእሱ ጋር እሄዳለው፤ እሱም ግን አዛን ካለ አይጠብቀኝም... ስለዚህ አስፈቅጄ ለመውጣት አሰብኩ። አስተማሪው <<በፍላጎት መማር እንጂ ተገዶ መማር ጊዜ ማቃጠል ነው>> ይላል፤ ስለዚህ በፈለግነው ጊዜ መውጣት እንችላለን ማለት ነው። አስፈቅጄ እንደወጣሁ ማሂ ተከትሎኝ ወቶ አስቆመኝ። <<እንዴ አንተም ወደ ቤት ልትሄድ ነው?>> እኔ ስለቸኮልኩ ላለመቆም እያልኩ... <<አይ ኢብቲ ላናግርሽ ምፈልገው ነገር ስላለ ትንሽ ጊዜ ስጪኝ ..>> <<ኧረ ማሂ አሁን አልችልም ሌላ ቀን አይሆንም..?>> <<አሁን ነው መሆን ያለበት በናትሽ ኢብቲ አትሂጂ>> ድምፁ በሲቃ ታፍኗል። <<ማሂ ምነው ችግር አለ?>> ደንግጫለው። <<አዎ ኢብቲ ታስፈልጊኛለሽ ካንቺ ብዙ ነገር ማወቅ ና ማግኘት እፈልጋለው ተረጂኝና ሁሉንም ልንገርሽ>> አይኖቹ እንባ አቅርረዋል። ለተወሰነ ሰዐት ዝም እንዳልኩ ቆየሁ። ብዙ ሃሣብ ተመላለሰብኝ ግን እሱ እንዲነግረኝ እዚህ መቆየት አለብኝ፤ እሱ ደግሞ አይሆንም። <<እ...ማሂ ሰኞ ትነግረኛለህ ቻው..>> ይሄን ቃል በደመነፍስ እንደተናገርኩት ጥዬው ሄድኩ ዞር ብዬ እንኳን አላየሁትም። . ወደ ቤቴ እየተቃረብኩ መጣሁ... መንገዴን ከጀመርኩ ጀምሮም ግን ምንም ላርፍ አልቻልኩም። ጭንቅ ብሎኛል፤ ምን ሊለኝ ነበር የሚለው ጥያቄ እረፍት ነስቶኛል፤ እንዲሁ ስወዛገብ ሰፈሬ ደረስኩ። መንገድ ላይ ወንድሜን አገኘሁት። <<በመጨረሻ መጣሽ አፍጥኝው በቃ አዛን ስላለ መስጂድ ሰግደን እንሄዳለን ቤት ደርሰሽ ነው ወይንስ በዚሁ እንሂድ ?>> ድምፄ ሲጠፋበት ከእቅፉ አወጣኝ፤ <<ምነው አሞሻል እንዴ?>> ለካ እስካሁን እቅፉ ውስጥ ነበርኩ። ሁሉንም ሰምቼዋለሁ መልስ መስጠት ግን አልቻልኩም። ብዙ ጊዜ ራስ ምታት ሲይዘኝ ስለማልናገር ዝም ባልኩ ቁጥር አሞሻል እንዴ የሁል ጊዜ ጥያቄው ነው። <<ትንሿ ምንድነው?>> <<ኧረ ምንም>> <<አሞሻል አይደል?>> ትኩር ብሎ እያየኝ። <<እእ አዎ ትንሽ.. በቃ ሂድ እኔ ልተኛ ነው።>> <<ኧረ አልሄድም አሞሽማ ብቻሽን>> ብሎ ድርቅ አለብኝ። ትንሽ ተጨቃጭቀን እሱ ሄደ እኔም ወደ ቤት ገባሁ። . እንዲሁ ሃሳብ አጨናንቆኝ እንጂ ደህና ነበርኩ። ወንድሜ እንደሄደ ሰግጄ ቁጭ አልኩ። ብዙም ሳይቆይ የጊቢው በር ተንኳኳ። <ኡፍፍ ምናለ ማንም ባይመጣ> እያልኩ ወደ በሩ አመራሁ። ስከፍት ግን ደነገጥኩ፤ ዩሲ ና ራቢ ነበሩ። መደንገጤ እንዴት እዚህ መጡ? ወይ እንዴት ቶሎ ወጡ? ይሁን.. ለራሴም አልገባኝም። <<ምነው ምሳ የለም እንዴ ፈዘዝሽ እኮ አሣልፊኝ ባክሽ>> ዩሲ ገፍትራኝ ገባች። ለካ ግቡም አላልኳቸውም። <<አንቺ እንደወጣሽ እኮ አስተማሪውም ሄደ። ለትንሽ ቀደምሽን አብረን ምንመጣውን>> ራቢ ግራ መጋባቴን ተመልክታ ከመጠየቄ በፊት ትመልስልኝ ጀመረች። <<ከዛ ደግሞ ጫፍ ጋር ወንድምሽ እቤት ናት ሲለን በዚሁ ከች አልንልሽ...ገባሻ ሃሃሃሃ ሣታስቢው ሰርፕራይዝ አደረግንሽ።>> <<አቦ ርቦኛል የሚበላ እፈልጋለው!!>> ዩሲ። <<እሺ በቃ ስገዱ ላቀራርብ>> እስኪሰግዱ ምሳ አቀረብኩ። እንዳጋጣሚ ዩሲ የምትወደው ምግብ ነበር እኛን አላስበላ እያለችን ትንሽ ከበላች ቡኃላ አንድ ላይ መብላት ጀመርን ። በዚህ መሃል ዩሲ <<ማሂ ምን ሆነው ይሁን?>> ስትል ደነገጥኩ። <<ምን ሆነ?>> <<ምን እንደሆነማ እኛም አላወቅንም ብቻ አልቅሶ አይኑ ቀላልልቶ ነበር። በዛ ላይ እነ ባቢንም አላናግር ብሏቸው ብቻውን ሄደ።>> እንዲህ ስትል ትን አለኝ ራቢ ጀርባዬን ስትደበድብ ዩሲ ውሃ ምናምን ስትል ለትንሽ ሰዐት ተዋከብን... ትንታው ለቀቀኝ። ስረጋጋ ሁሉንም ነገር ነገርኳቸው፤ በዚህ ጊዜ ነበር ራቢ ያልጠበቁት ነገር የተናገረችው። <<በቃ እንደጠረጠርኩት...>> . . #ክፍል_9 ይቀጥላል...
3041Loading...
36
<<ኦውው ለዚህ ነው ፊትሽን የጣልሽው? ዛሬ ቶሎ መሄድ ስላለብኝ ነው ነገ በጊዜ መጥቼ እናካክሣለን። ተማሪዎች ባይ ባይ>> እየነጠረ ክፍሉን ለቆ ወጣ። እኔም ወደ ማሂ ጋር ሄድኩኝ ..ሌሎች ተማሪዎችም ተቀላቅለውን ጥያቄዎችን መስራት ጀመርን። አልገባኝም ሲል የነበረው ማሂ ጥያቄዎቹን በቀላል መንገድ መልስ ሲያስቀምጥላቸው ነበር። ተማሪዎቹ ስንጨርስ ተበታተኑ እኔ ና ማሂ ብቻ ቀረን። <<ስማ ምኑ ነው ያልገባህ እንዲ እያስረዳህ?>> <<ኧረ ኢብቲ ይሄ አጋጣሚ ነው። ባይሆን ከመጀመሪው ማስረዳት ጀምሪ>> <<ኧረ ዛሬ እኔም ልስማሽ... እስቲ ሎጋው ተጠጋ>>አቤላ መልስ ሣይጠብቅ ገፍቶት ተቀመጠ። ትንሽ ከሰማኝ በኃላ በቃኝ ብሎ ተነሣ። እኔ ማሂን ማስረዳቴን ቀጥያለሁ <<እሺ ማሂ ጨረስና፤ ጥያቄ አለህ?>> <<አይ የለኝም>> ደንግጧል ለምን እንደሆነ ግን አልገባኝም። . . #ክፍል_8 ይቀጥላል...
3111Loading...
37
<<እ ኢብቲ አልተመቸሽም?>> <<አሪፍ ነው ግን የማሂ ቡድን የቱ ጋር ነው?>> <<የሱ ቡድን ስንት እንደሆነ አልታወቀም። ነገ ስሙ ያለበትን አይተን ከነ ራቢ ቡድን አጠገብ ወይም ከአንቺ ቡድን አጠገብ ይሆናል አይሻልም ሎጋው>> ወደ ማሂ ዞረ። ማሂ የጫማ ክሩን እያሰረ <<እስቲ እናያለን...እንውጣ እንጂ ይሄኔ ጥለውኝ ሄደዋል ..>> ሁላችንም ለመውጣት ወደ በሩ አመራን። እስከ ጊቢ አብረን ከወጣን በኃላ ተለያይተን በየመንገዳችን መሄድ ጀመርን.. . . #ክፍል_7 ይቀጥላል... ሼር
2411Loading...
38
የባከኑ ቀናት ክፍል ሰባት (ሂባ ሁዳ) . . ዛሬ ራቢ ቆይታብናለች። እኛም በጣም ሲረፍድ ጥለናት ሄድን። ጊቢ ስንገባ በማርፈዳችን ተቀጥተን የተመታውን እጃችንን እያሻሸን ወደ ክፍል አመራን። አስተማሪው ገብቶ ማስተማሩን ጀምሮ ነበር፤ ትንሽ ካስቆመን ቡኃላ እንድንቀመጥ ፈቀደልን። ሁሉም በቡድን ቡድን ተቀምጦል ራቢም አለች። እንዴ እስካሁን እሷን ስንጥብቅ አርፍደን እሷ ግን እዚህ ናት የተመታሁትም አሞኝ ስለነበር ተናድጄ ራቢን ገፍቻት አለፍኩ። ትናንት በተነጋገርነው ቦታ ላይ ቁጭ አልኩኝ። ደብተሬን ሣወጣ ባቢን አየሁት በእጁ ሃይ አለኝ ብናደድም ፈገግ አስባለኝ ከእሱ አጠገብ ዩሲ አለች እሷ ግን አልተናደደችም ነበር። ከእነሱ ፊት ደግሞ የነ ራቢ ቡድን አለ ከራቢ ጋር አይን ለአይን ስንገጣጠም ዞር አልኩባት። አጠገቧ አቤላ አለ... ባቢ እንዳለውም አልተራራቅንም፤ ፊት ለፊት ለመተያየት እንዲመች አድርገው ነው ያስተካከሉት። <<ትምህርቱን ረሣሁት እኮ እናንተን ሣይ ብዙ ጻፋቹ እንዴ?>> ብዬ ወደ ብላክቦርዱ ሣይ ከማሂ ጋር ተገጣጠምን። እስካሁን አላስተዋልኩትም ነበር፤ ስገባም ከአጠገቡ ነበር ያልፍኩት። ደግሞ ርቀት አለን እንዴት እዛ ሊሄድ ቻለ? ..ወይ ጉድ ብዙ ነገር ሳብሰለስል አስተማሪው ሳልፅፍ አጠፋብኝ። ቀጣዩን መፃፍ ጀመረ፤ በቃ አንደኛዬን በኃላ እፅፈዋለሁ ብዬ ተውኩት። ሲያስረዳ ከደብተሬ ጀርባ አጭር ማስታወሻ መያዝ ጀመርኩ፤ ዛሬ ደግሞ አስተማሪዎች ላይ በላይ ነው የሚገቡት ምንም ክፍተት አልተፈጠረም። ይኸው የእረፍት ሰዐት ደርሶ አስተማሪው ወጣ። <<ኡፍፍፍ ጭንቀት ሊገለኝ ነበር እኮ..>> ባቢ ከቦታው እየተነሣ። <<ድሮም እኮ የትምህርት ነገር አይሆንልህ>> ራቢ ሂጃቧን እያስተካከለች ትመልስለታለች። ደብተሬን አስገባብቼ ወደ በሩ በችኮላ መሄድ ጀመርኩ። ራቢ ቦርሣዋን እየዘጋች <<ኢብቲ በአላህ ጠብቂኝ...>> አለችኝ። ማሂ ወደነ ባቢ ጋር እየሄደ ነበር፤ መሃል ላይ ተገጣጠምን። ራቢም ወደኛ እየመጣች ነበር። <<በናትህ እንዳታሣልፋት>> ራቢ እንዲያስቆምላት ጠየቀችው። ማሂ ከፊቴ እንደቆመ ገፍትሬው አለፍኩ። ከክፍል ስወጣ ኢክሩ እየመጣች አገኘኋት። ተቃቅፈን ሰላም ስንባባል ራቢ መጣች... ሁለታችንንም አቀፈችን ምንም አላኳትም። ግንባሬን ሣመችኝ፤ እንደማኩረፍ እያልኩ <<በቃ አረሳሳሽ?>> <<ኢብቲ ደግሞ ይቅርታ.. ቆይ ልንገርሽ ለምን እንዳልመጣሁ..>> <<ኧረ ተይው ላለፈ ነገር። በርግጥ ተናድጄብሽ ነበር ግን አሁን አስጠፋሽብኝ በሰላም ከሆነ ጣጣ የለውም።>> ለማብረድ እየሞከርኩ። <<ለዚህ እኮ ነው ልዩ ነሽ የምልሽ። ነይ በዚህ>> ዘላ ጉንጬን ሣመችኝ። እርቋት አይደለም መዝለል ስለምትወድ እንጂ.. ዩሲ ብንጠብቃትም ከክፍል ስላልወጣች ተያይዘን ወደ ክፍል ገባን። በሩን ተደግፎ የቆመው ባቢ <<ቅድም ስትጨቃጨቁ ወታቹ አሁን ተቃቅፎ መግባት ጠላትን ለማናደድ ይመስላል።>> <<ገና ከመታረቃችን ልታጣላን ነው እንዴ ሆ!>> ራቢ ከአጠገቡ ቆማ መልስ ሰጠችው። እኔና ኢክሩ ወደ ውስጥ ገባን። ኢክሩ ዩሲን ሰላም ብላት አዲሱን ቦታችንን አሳይቻት ያለፈኝን ልትፅፍልኝ ተቀመጠች። ዩሲም እየፃፈች ነበር፤ አብረው መፃፍ ጀመሩ። እኔም እነ ባቢ ጋር ሄጄ ተቀላቀልኳቸው። * እንዲህ እንዲህ እያል ጊዜው ሄደ... ቁምነገር ያልተሰራባቸው ቀናት ተቆጠሩ። ከሙሉ ተማሪው ጋር ተግባባን ከነ ባቢ ጋር ደግሞ በጣም ተቀራረብን። ላየን እንደ አዲስ ተማሪ ሳይሆን ከድሮ ጀምሮ የምንተዋወቅ እንመስል ነበር። የክፍል ሃላፊያችን ካልገባ በቀር በቡድን አንቀመጥም። ሶስታችንም ከፊት ካለው ወንበር አብረን እንቀመጣለን አስተማሪ እስኪ ገባ ባለን ክፍተት እንጠያየቃለን። ዩስራ ሂሣብ ትምህርት ነፍሷ ነው፤ እኔ ደግሞ ብዙም አይደለሁም ባይሎጂ ግን የሚችለኝ የለም። ራቢ ደግሞ ኬሚስትሪ የግሏ ነው፤ በየትምህርቱ ላይ የተለያየ ቦታ መስጠታችን እኛን ጠቅሞናል። ሶስታችንም አንድ ላይ ስለምንሰራ የክፍሉ አሪፍ ውጤት እንድንይዝ ረድቶናል። * <<ኧረ ልጅት ምንድነው እናቷን ከገበያ እስክትመጣ የምትጠብቅ ልጅ የመሰልሽው>> ባቢ ወደኔ እየመጣ ንግግሩን ቀጠለ። ከነሱ ቀድሜ ክፍል ተቀምጬ ነበር የመጡት። በቀናት ሂደት ያልተቀየረው የባቢ ተጫዋች ምላስ ነው። <<እእ እሱ ካልተመቸሽ ደግሞ ፎንቃዋን የምትጠብቅ አፍቃሪ የመሰልሽው ይሁና>> <<ባቢ ይሄ ከፎንቃም በላይ ነው። ከትምሮ ይሁን ከአስተማሪው አልተለየም እንጂ!>> አቤላ ተከትሎት እየገባ ጭንቅላቱን ከግራ ወደ ቀኝ ያዞራል። እንዲ የሚያደርገው እኔን ለማናደድ ሲፈልግ ነው። የምርም ግን ያናድደኛል፤ ይኸው ተሣካለት። <<እስቲ አቤላ ነገር ከምትበላ ሂድ ብላክቦርዱን አፅዳው>> ያናደደኝን ልመልስለት እየሞከርኩ። <<ባክሽ አልሰማሽም፤ ዛሬ እኔ አላፀዳውም>> <<ነው?>> <<እናቴን አዎ ኢብቲ ምን ታመጪያለሽ>> <<ኧረ.. ምንም እንዴት እንደማስጠፋህ አሳይሃለው ...>> <<ይኸው እየነጠረ መጣልሽ>> ባቢ ወደ ቦታው ተመለሰ፤ የባይሎጂ አስተማሪ ገባ። <<ሄይ ሄይ ተማሪዎች ዛሬ ማን ነው የሚያፀዳው?>> <<እኔ አፀዳለው ቲቸር>> <<ኦውው ዛሬ ኢብቲሣም ናት>> ሲያቀብለኝ ተቀበልኩት። ለማፅዳት ወደ ብላክ ቦርዱ ከዞርኩበት ወደ ተማሪው መለስ ብዬ <<ኧረ ችግር የለውም>> አልኩ፤ አቤላን እያየሁ። ከባቢ ጋር ተጠቃቀስን። <<ምን?>> አቤላ ግራ እየተጋባ ያየኛል። ባቢ ወደ አቤላ በመዞር <<ኢብቱ አንቺ ጥቁር ሂጃብ ስላደረግሽ ብናኙ እንዳያበላሽብሽ ብሎ ነው>> <<እሺ አቤላ አመሰግናለው ይኸው ና አጥፋ>> ዳስተሩን አስቀምጬው ተቀምጥኩ። አቤላ እየበሸቅ አጥፍቶ ጨረሰ። <<እናቴን ባልሰራላቹ>> ብሎኝ ወደ ቦታው ሄደ። ባይሎጂ መምህራችን የእለቱን ትምህርት ጀመረ . የዛሬው ትምህረት ትንሽ ውስብስብ ያለ ነው፤ በዛ ላይ አስተማሪው ቸኩሏል። <<ኡፍ ምንድነው የሚደበላልቀው?>> ራቢ ትነጫነጫለች። <<ራቢ ዝም ብለሽ ከተከታተልሹ ግልፅ ይሆንልሻል።>> <<ባክሽ ዛሬ ምን እንደሚል ሁላ መረዳት አልቻልኩም በቃ ኢብቲ እንደለመደብሽ በኃላ ታስረጂኛለሽ>> ደብተሯ ላይ ጋደም አለችበት። ዩሲ እየተደገፍቻት <<ስሚ ቀጣይ ኬሚስትሪ እኮ ነው እንቅልፍ እንዳይወስድሽ ..>> <<እሱ መች ጠፋኝ.. ነቃ ብዬ እንድማር አሁን እረፍት ላድርግ እንጂ፤ ባይሆን ዝም በሉ ና ተከታተሉት።>> አለችና ተጋደመች። ትንሽ እንደተማርን <<ለዛሬ ይበቃል ጥያቄ ያለው አለ?>> ሶስት ልጆች ጥያቄ አቀረቡለት። የነሱን ከመለሰ በኋላ.. <<ቲቸር>> ማሂ ፀጉሩን እያሻሸ ጠራው። <<ወዬ>> ጋወኑን ለማውለቅ እየተቻኮለ <<ኧረ ምንም አልገባኝም አትደግምልኝም?>> ባይሎጂ መምህራችን ፈታ ያለ ስለሆነ ነገር አያከርም። <<በጣም አሪፍ ኢብቲሣም ታስረዳሃለች። የናንተንም ጥያቄ እሷ ትመልስላችሁ፤ የቀረ ካለ ደግሞ ነገ እናያለን በሉ ተማሪዎች ባይ ባይ>>.. ቲቸር ፊቱን ወደኔ አዞረ። <<ኢብቲሣም እንቺም ዛሬ አልገባሽም?>> <<አይ ገብቶኛል ግን ሰዐት አለን አላለቀም እኮ>>
2761Loading...
39
⭐ከገርልፍሬንዴ ጋ ስለኤክሶቻችን እያወራን ። ይገርምሻል ኤx እንዴት እንደምታምር ፣ ፀጉሯ እርዘመቱ ጥቁረቱ ግን ሰውነቷ የበለጠ ያምራል ከለሯም ንጣቱ እያልኩ በስሜት ከወንድ ጓደኛዬ ጋ እንደማወራ ሁሉ ብዙ ዘበዘብኩ ሳያት ኮስተር ብላለች አንቺ ከxሽ ጋ በምን ተለያያቹ ስላት "አይ አልተለያየንም " ማለት ? "መሃላችን ላይ ትንሽ ግጭት ነገር ተፈጥሮ ነበር አሁን እንፈታዋለን"
2641Loading...
40
የባከኑ ቀናት ክፍል ስድስት (ሂባ ሁዳ) . . << <እንዲው እንዳማረብህ ይቅርታ ልጠይቅህ> ፈገግ አለልኝ፤ በዚህ ቅፅበት ጥሬ እህል እንደሆነ ተሰማኝ። ወደ ተማሪዎች ዞር አልኩ የሚሆነውን ለማየት የቸኮሉ ይመስላሉ። ራቢ እንደተናደደችብኝ ታስታውቃለች፤ ባቢ አጠገቧ አለ... ብዙ ጥያቄ እንዳለው አይኖቹ ይናገራሉ። ፊቴን ወደ በረከት መለስ አደረኩ ምን አልባት ይህ ቅጽበት ለሱ ድል ከማድረግ በላይ በሃሴት የተሞላ ነበር። ከታች ወደ ላይ ተመለከትኩት ትልቅ ድብ የማይ መሰለኝ... ግዝፈቱ አላስፈራኝም። ወደ ኃላ ሄድኩ፤ ከበረከት ጀርባ ቆምኩኝ። ከየት ባመጣሁት ሃይል እና ግፊት እንደሆነ ባላውቅም በቀኝ እጄ አንገቱን እንቅ አድርጌ እንዴት መሬት ላይ እንደተዘረረ አሁንም ድረስ ይገርመኛል፤ ክፍሉ በአንዴ ወደ ሁከት ተቀየረ፤ ክብ ሰርተው መሃል አስገቡን። ከወደቀበት ተነስቶ አንድ ቦክስ ሰነዘረብኝ አልሣተኝም ነበር እኔም በርግጫ አልኩት። ታውቃላቹ ያኔ አምስተኛ ክፍል እያለን ከወንዶች ጋር እንደባደብ የነበረው ጠቅሞኛል... ግን ቦክሱ አቅም አሣጥቶኝ ነበር እናም ከኃላ አንድ ልጅ ሲገፋኝ ወደኩኝ። በረከት አጋጣሚውን ለመጠቀም በጉልበቱ ተንበረከከ በቦክስ ሊደግመኝ ሲል ከኃላ ተገፋና ወደቀ፤ ሲዞር ራቢ ናት። እኔን ትቶ ሲነሣ አብሬው ተነሣሁ፤ ወደ ራቢ ተጠግቶ እጁን ሲሰነዝር እጁን ጋም አድርጋ በቴስታ መለሰችው። ትዝ ይለኛል የተማሪው ፉጨት ምናምን.. ቴስታውን መቋቋም አልቻለም እኛም አጋጣሚውን ተጠቅመን ለሁለት ቀጠቀጥነው። ከስር የተደረቡም ነበሩ.. በቃ ክፍሉ ፉጨት በፉጨት ሆነ። ከዛ እኛ ክፍሉን ለቀን ወጣን፤ በንጋታው ትምህርት ቤት ስንገባ በቃ የሌለ አከባብደው አዩን። ከዛ ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ክብሮ ነን፤ በረከትም ይቅርታ ጠየቀን ግን አሁንም ድረስ ይፈራናል በቃ ይኸው ነው።>> <<በለውውው የኔ ውዶች አኮራቹኝ>> ኢክሩ ዩሲን ስታቅፍት እኔ ራቢን አቀፍኳት። <<አሪፍ አድርጋቹ ነው የቀጣቹት የኔ ጀግናዎች። አሁንም ቢሆን ማንም ከልኩ አያልፍም፤ በየትኛውም መንገድ እኛ ላይ እንዲደርሱብን አንፈቅድላቸውም። ነገራቶችን በቅን መንገድ እንፈታቸዋለን፤ ድንበሩ አልፎ ለሚመጣብን የሚገባውን እንሰጠዋለን። አይደል ውዶቼ >> ሶስቱንም አፈራርቄ አየሁዋቸው። ኢክሩ ከውብ ፈገግታዋ ጋር አይን አይኔን እያየች <<ኢብቲ አንቺ እኮ አትናገሪ.. ንግግሮችሽ ሁሌም ወደ ልባችን ይገባሉ፤ ደግሞ አራት ነን አላህ እስካለያየን ድረስ..>> <<እንዴ ሰዐቱን እዩትማ!>> ራቢ ሰዐቷን አየት አደረገች። <<ወይኔ ሰላት ረፈደብን ገና አንድ ምሣቃ ይቀረናል እኮ.. እዛ ከሄድንማ አንደርስም በቃ እዚው እንስገድ እእ ውዶች>> ዩስራ ምሣቃዎቹን ዘጋጋች። በዩስሪ ሃሣብ ተስማምተን የክፍላችንን በር ዘግተን ሂጃብ አንጥፈን ወደ ሰላታችን ገባን፤ ስንጨርስ ከክፍል ወጥተን ዞር ዞር ማለት ጀመርን። በዛው ሎሊፖፕ ገዝተን ተመለስን። እንደለመድነው ኢክሩን ሸኝተን ወደ ክፍላችን ገባን። * እኛ ቦታችን ጋር ተቀመጥን እነ ባቢ ደግሞ ከፊታችን ተቀምጠው እየተተራረቡ ፈታ ያረጉናል፤ እኛ እንስቃለን ሙድ እንይዛለን። እንዲህ እያለን አስተማሪው መጣ፤ ብዛት ያላቸው ወረቀቶች ይዟል። የክፍል ሃላፊያችን እንደሆነና በቡድን ሊከፋፍለን እንደሆነ ነገረን። ጎበዝ ተማሪዎችን የቡድን መሪ እንዲሁም ጸሃፊ እንደሚሆኑ እያስረዳን አምና የሚያውቋቸው ጎበዝ ተማሪዎችን ስም መጥራት ጀመረ። አራት ተማሪዎች ተጠሩ ስምንት ቡድን ስለሆነ ተጨማሪ አራት ተማሪ እንደሚፈልግ ነገረን። <ከሌላ ትምህርት ቤት የመጣችሁ ከሰማንያ በላይ ነጥብ ያላችሁ..> ሲል ሁሉም ዝም ሲሉ መጣሁ ብሎ ከክፍል ወጣ። ራቢ <ለምን አትሆኚም?> ብላ ተቆጣችኝ። እንደማልፈልግና ባይሆን እነሱ ለምን እንደማይሆኑ ስጠይቃቸው እነሱም እንደማይፈልጉ ነገሩኝ። ሶስታችንም የቡድን መሪ ከሆንን አንድ ላይ መሆን ስለማንችል ነው። ባቢ <<ዱዝ ሁነሽ ነዋ ከዛ ትምህርት ቤት የተባረርሽው.. እኛማ ጠጋ ጠጋ ያልነው ቀለሜ መስለሽን አይይይይ ተበላን!>> <<ሃሃ ባክህ አላወካትም ሚኒስትሪ በሷ ነው የምታልፈው ለዛውም ሰቅለህ>> ራቢ ጥብርር እያለች መለሰችለት። ራቢና ባቢ እየተከራከሩ አስተማሪው መጣ። <<እሺ አሁን ስማቹን የምጠራቹ ወደዚህ ትመጣላችሁ>> ብሎ ስም መጥራት ጀመረ። ከአራቱ ተማሪዎች ሶስቱን ጠራ አንዱን ቀነሰው ከዛም ራቢያና ዩስራ ጠራ <<እንዴት እናንተን እረሳለሁ? እናንተስ እንዴት ዝም ትላላችሁ? አምናም የቡድን መሪ ነበራቹ አይደል>> ብሎ ሌላ ተማሪዎችን ጠራ... ሁለቱ አዲስ ነበሩ፤ የፈሩ ይመስላሉ። ቀጥሎ ኢንቲሣር ብሎ ተጣራ ራቢ <<ኢብቲሣምን ነው?>> ጠየቀችው። ድጋሚ ወረቀቱን አይቶ <<ይቅርታ ኢብቲሣም የት አለች?>> <<ኢብቲ ነይ>> ዩሲ ከነሱ ጋር በመጠራቴ ደስ ብሏት፤ እኔ ግን መውጣት አልፈለኩም። ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ቲቸር ይቅርታ <<እኔ የቡድን መሪ መሆን አልፈልግም>> አልኩት። <<ለምን?>> <<በቃ ስለማልፈልግ ነው ...>> አስተማሪው ቆጣ እያለ <<መጀመሪያ ከሰማንያ በላይ ነጥብ ያላችሁ ስል ዝም አልሽ። ዘጠና አራት ነጥብ ይዘሽ በዚህ መሪ አልሆንም ትያለሽ?>> <<እሺ በቃ ጸሃፊ እሆናለው በዩስራ ወይም በራቢያ ቡድን>> እየፈራሁ ነበር የተናገርኩት። <<እኔ መች ምረጪ አልኩሽ?>> አስተማሪው ተቆጣ። ምንም አማራጭ እንደሌለኝ ሣውቅ ወጥቼ ከነ ዩሲ ጋር ተቀላቀልኩ። መዳድቦ ከጨረሰ ቡኃላ የቡድን አባላት ያለበትን ወረቀት ለየግል ሰጠን ወረቀቱን ይዘን ወደ ቦታችን ተመለስን። . አስተምሮ ሲጨርስ ከነገ ጀምሮ ሁሉም ተማሪ በየቡድኑ እንዲቀመጥ ካልሆነ እርምጃ እንደሚወስድ ነግሮን ወጣ። ባቢ ወረቀቶቹን ተቀብሎን የቡድኖቹን ክፍፍል ማየት ጀመረ <<በለው አቤላ ከራቢያ ጋር ነህ ብዙም አልራክም፤ እኔና አንተን የት ከቶን ይሁን>> ማሂን እያየ። የነሱን ስም ፍለጋ ቀጣዩን ወረቀት ማየት ጀመረ። <<በለውውው እኔ ደግሞ ከዩስራ ጋር ዋው>> <<እኔን ከኢብቲ ጋር አርጎኝ ነዋ እየው እስቲ>> ማሂር ለማየት እየቸኮለ። ባቢ ለኔ የተሰጠኝን ወረቀት ማየት ጀመረ። <<ቲሽ ሎጋው እዚህም የለህም>> ማሂ ከፋው ከጓደኞቹ ጋር ስለተለየ መሰለኝ እኛም ዝም አልን። የሱ ስም የሌላ ቡድን መሪ ወረቀት ላይ ስለሚሆን የት ቡድን እንደሆነ ለማወቅ አልቻልንም። <<ቆይ እንዲ የደበራችሁ የተለያየ ቡድን ስለሆናቹ ነው? እህ... ክፍል ሁላ ባለመለያየታቹ አመስግኑ>> ቀለክ ላደርገው እየሞከርኩ። ማንም ምንም አልተናገረም ባቢ ንግግሩን ቀጠለ <<እሺ ለምን እዚው ቅርብ ቅርብ አናደርገውም እእ.. አስተማሪው ቦታ ከሚመርጥልን እኛ እንደምንፈልገው እናድርገው እእ.. በናታችሁ ዝም አትበሉ ከቀጣዩ ክላስ ቡኃላ እናስተካክላለን እሺ>> ራቢም ተስማማች። <<እሺ>> ቀጣዩን ክላስ ከተማርን ቡኃላ ወደ ቤት ሰዐት ላይ ሁሉም ተማሪ ሲወጣ እኔና ዩስራ ውጪ ሆነን እነሱ ለአራት አስተካክለው ጠሩን። ስንገባ ሌላ ክፍል ነው የሚመስለው። ስምንት ቡድን ሰርተው የቡድን ቁጥር ከፋፍለው ነበር። እኔ ቡድን አምስት፣ እነዩስራ ስድስት፣ ራቢ ደግሞ ሰባት አደረጉን፤ ያው እንዳንራራቅም ነው ቅርብ ለቅርብ ነን
2962Loading...
መደነቅ የምናቆምበት ጊዜ አለ ስላገኘነው የማንቦርቅበት ስላጣነው የማንቆዝምበት የመጣን አንደ አመጣጡ የምንቀለበልበት ልሂድ ያለን እንደ ፍላጎቱ የምንሸኝበት አንዳንድ ጊዜ አለ. . . . . መታገል የምናቆምበት @Meki3
Показать все...
👍 3🏆 2🎉 1
መደነቅ የምናቆምበት ጊዜ አለ ስላገኘነው የማንቦርቅበት ስላጣነው የማንቆዝምበት የመጣን አንደ አመጣጡ የምንቀለበልበት ልሂድ ያለን እንደ ፍላጎቱ የምንሸኝበት አንዳንድ ጊዜ አለ. . . . . መታገል የምናቆምበት @mejnun_me
Показать все...
🔻::::::::::::::ሚስኪኑ አፍቃሪ::::::::::::🔻 ፀሀፊ✍✍ መሐመድ ክፍል 🔟 ባታውቀኝም የሆነ ፍንጭ እያገኘች ይመስላል። እኔም ሀሳቤን ቀይሬ እንድታውቀኝ ፍላጎት አደረብኝ።የት ትምርት ቤት ነበር ምትማረው? እናንተ ጋ ። እኔ አቅሀለው ? በጣም። ኧረ እኒጃ እኔ 12 ኛ ክፍል ማስታወሰው ሰው የለም አለች። እስቲ ትምርት ቤት ቤስት ጓደኛዬ የምትያቸውን 5 የወንድ ጓደኞችሽን ንገሪኝ አልኳት። ነገረችኝ ።አብዱ፣ኢብራሂም፣ .......... ፣እና ማሜ እነዚ የኔ ምርጥ ጓደኞቼ ናቸው አለች።ከነገረችኝ ውስጥ የሁለቱን ስም ረስቻቸዋለው። የኔ ስም መኖሩ ገርሞኛል። በቃ ከነዚ አንዱ ነኝ አልኳት።ማወጣጣቷን አላቆመችም። እሺ ለምን ስምህን በሴት ስም አደረከው ? አንቺን ለማግኘትናበወንድ ስም ባረገው አታናግሪኝም ብዬ ነው። ለምን እኔን ማግኘት ፈለክ ? እዚጋ ነበር ብሶቴን በሙሉ የዘረገፍኩት። በጣም እንደምወዳት፣ግን ለሷ እንደማልገባ ወይም እንደማልመጥናት። እሷ አግብታ ብትወልድ ራሱ እሷን መውደዴን እንደማልተው ።እሷን በማውራት እርካታና ደስታን እንደማገኝ።እንዲ ራሴን ደብቄ የማናግራትም ለዚህ እንደሆነ ነገርኳት።( ፍቀር ማለት የወደዱትን የራስ ማድረግ ማለት ብቻ እንዳልሆነ አምናለው)። ስለዚ s ዬን ማውራትና ጓደኛ መሆን እንጂ የግድ የኔ ትሁን አላልኩም። የኔ ብትሆን ደስተኛ ነኝ። ይህን ስላት "ማልመጥን የሚለውን እርሳው መማንም ለማንም ማይመጥን የለም" አለችኝ። ልክ ነበረች ።ኮንፊደስ የለኝም አላልኳቹም? ለዛ ነው ። ጥያቄዋን ቀጠለች። ስምህን ሀሊማ ለምን አልክ ሀሊማ ማናት? በነገራችን ላይ ይሄ ቃለ ምልልስ የአንድ ቀን አይደለም ። ከአንድ ወር በላይ ሆኖናል። ነሀሴ ወር አልቆ መስከረም ገብቶዋል ። እኔም ፈተና አልፌ አማራ ሀገር (ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ) መመደቤንም አውቂያለው። አልሀምዱሊላህ። ወደ ቃለ ምልልሱ ስመልሳቹ። ሀሊማ በጣም የምወዳት እህቴ መሆኗን ነገርኳት። (ሚስኪን) ስለዚች እህቴ የምታውቀው ታሪክ እንዳለ ረስቼዋለው። "እንደው የሆነ ቀን የነገርከኝ" ብላ አሾፈችብኝ። እኔ ግን አልገባኝም።ምክንያቱም ስለ እህቴ እንደነገርኳት ተረስቶኛል። አሁን አስራ አንደኛው ሰአት የደረስን ይስላል። እንዲህም አለችኝ ።"""አብዲንና እነዛ ስማቸውን የረሳኋቸውን ልጆች ጠቅሳልኝ እነሱ ከኔ እኩል 11ኛ ክፍል ናቸው። ኢብራሂም ና ማሜ 12 ናቸው። ኢብራሂም ደግሞ እንዲ አዋርቶኝ አያቅም። ስለዚ ካሁን ቡሀላ ብዙም አናወራም። እኔ ማላውቀው ሰው ሲያስለፈልፈኝ አልወድም። አሪፍ አወጣጭ ነኛ?""""" ብላኝ ከ fb ወጣች ደነገጥኩ፣ ተናደድኩ፣ ጬስኩ ፣ተቃጠልኩ።ውርደትና የበታችነት ተሰማኝ። እንዴት አይሰማኝም ። እኔ መሆኔን ስታቅ ካሁን ቡሃላ እንደማናወራኮ ነው የነገረችኝ።እየተጠላሁ የምወድ ፣እየተገፋሁ የምቀርብ አሳዛኝ ሚስኪን። ደሜ ፈልቶ ፣ እልህ እስከ አናቴ ተናንቆኝ ፣ ፍም እሳት የዋጥኩ ይመስል ሆዴ እየተቃጠለ ረጅም መልእክት ፃፍኩላት።የመሰናበቻ መሆኑ ነው።ደንታም እንደማይሰጣት አቃለው። የመልእክቱን መደምደሚያ በሚከተለው ጥያቄያዊ ትእዛዝ አደረኩት እንዲ ይላል።""""""ይኸውልሽ s እኔ አንቺን ማገኝባቸው መንገዶች በሙሉ ተዘግተዋል ።የቀረው fb ብቻ ነው። አሁን እኔ ብሎክ ባደርግሽ ስትናፍቂኝ የ fb ስምሽን ስለማውቀው ዳግም ሌላ fb ከፍቼ ልበጠብጥሽ እችላለው። እናም አንድ ነገር ብቻ ተባበሪኝ ።አንቺ ብሎክ አድርጊኝና የ fb Hilwan የሚለውን ስምሽን ቀይሪው። ከዛ የትም ብፈልግሽ ኬትም አባቴ አላገኝሽም።""""""""" ብያት k fb ወጣሁ በማግስቱ ዳታ አብርቼ ስገባ "" በጣም አዝናለው እንዲ ይፈጠራል ብዬ አላሰብኩም """"" መልካም ህይወት። የሚል መልእክት ልካልኝ ብሎክ አደረገችኝ። ግልግል። ከዚ ቀን አንስቶ ሳልረሳት ረስቺያት፣ ዳግም ስለሷ ላላስብ ለራሴ ቃል ገባሁ። ትንሽ የመረጋጋት ነገር ይታይብኛል።ምክንያቱም ከሷ በግልፅ እስክሰማና ብዙ ሙከራዎችን እስከ ማደርግ ድረስ ሁሉ ነገሬን የተውኩላትን እንስት ላለመተው የዛኔ ላይብረሪ እያለው ወስኜ አልነበር?አሁን ሁሉም ነገር ስለተገለፀልኝ ለቆራጥነት አልተቸገርኩም። እነሆ እኔ ወደ ካምፓስ መግቢያዬ ደርሶዋል ። ጥቅምት ዘጠኝ ነው ምሄደው።ቢያንስ ሳምንት ቢቀረኝ ነው። ከአዲሳበባ ስወጣ ይበልጥ እሷን እንደምረሳ ና አዲስ እኔነቴን እንደማገኝ ውስጤ እያጫረብኝ ነው። ዛሬ ቀኑ ሐሙስ ከቀኑ 11 ሰአት ነው። ፆመኛ ስለሆንኩ በጣም ደካክሞኛል።መንገድ ላይ ነኝ። ወደ ሰፈሬ በቢላል መስጊድ በኩል የተጎሳቆለ ሰው መስዬ፣ ከድካም የተነሳ እግሮቼን ከመሬት እያንፏቀቅኩ፣ ቲሸርቴ ተዝረክርኮ ከፊል ደረቴን እያሳየ፣የለበስኩት ትልቅ ነጠላ ጫማ አቧራ አያነሳ እግሬን ሌላ ጫማ አስምሎት፣ ልቤ በሀዘን፣ እምሮዬ በትካዜ ፣ሆዴ በረሀብ ተቃጥሎ በመንገዱ ግራ ጠርዝ ወደታች እየተራመድኩ ነው። ድንገት ቀና ስል s ዬ ኬት መጣች ሳይባል አይን ለአን ተጋጨን። እሷ ከታች እየመጣች ነበር ። እኔ ከላይ።ያየሁትን ማመን ከበደኝ፣ደርቄ ቀረሁ ፣ አምላኬ ግን ምን አርጌ ነው? ምን አጥፍቼ ይሁን? እንዲ የማልወጣበት ማጥ ውስጥ የገባሁት?ምናለ የዛኔ እዛ ቁራን ቤት አስቀራ ስባል እምቢ ባልኩ። #ክፍል_11 ✍✍ይቀጥላል
Показать все...
👍 4❤ 1
🔻:::::::::::::::ሚስኪኑ አፍቃሪ:::::::::::🔻 ✍ፀሀፊ መሐመድ ክፍል 9⃣ኝ በዚህ እቅዴ መሰረት ነበር sዬን ዳግም የማገኝበትን ተስፋ የሰነቅኩት።እሱም አዲስ የ fb acount ከፍቼ ፣ስሜን በሴት ስም አድርጌ የsዬን fb ስሟን ስለማውቀው friend request ልልክላት ። ከዛ ሴት መስዬ ላዋራት ። ብዙ ከተግባባን ቡሀላ ወንድ መሆኔን እነግራትና ከዛ ቀስ እያልኩ ማንነቴን አሳውቂያት እሷን ለማግኘት መሰዋት መክፈሌን እንድትረዳ ለማድረግ ነው ።አሪፍ ሀሳብ ነው ፣ግን ትግስትና ጊዜ ይጠይቃል። የ fb ስሜን በታላቄ ታላቅ እህቴ ስም ነው ያደረኩት።ሀሊማ ትባላለች ስለዚች እህቴ ለsዬ ስሟንና ከቤታችን ቀይና የሁላችንም ታላቅ እንዲሁም እኔ በጣም የምወዳት እህቴ መሆኗን ትምርት ቤት እያለን አጫውቻት ነበር።sዬ እህቴን በአካል ባይሆንም በደንብ ታቃታለች። አሁን የረመዳን ወር አልቆ ፣ፈተናም ጨርሰን፣እኔም በ 15 ቀን አንዴ ምመላለስበት የነበረው ጉዳዬን ከግብ አድርሼ የተቀመጥኩበትና ቀጣይ የፈተና ውጤት የምጠባበቅበት ወቅት ነበር።ዝናቡና ደመናው ክረምቱ በደንብ መግባቱን ያሳብቃሉ።ለብርዱ እንደልብስ ለደመናው እንደ ብርሀን የምትሆነኝ እንስት በአካልም በስልክም ከተለየኋት ግንቦት አልፎ ሰኔ ፣ሰኔ አልፎ ሀምሌ ገብቶዋል። ሁለት የሀዘን ወራቶችን ካሳለፍኩ ቡሀላ ነበር እቅዱን ያቀድኩት።አሁን fb frind ሆነናል ።sዬ ብዙ ነገር ትፖስታለች ፣በጣም ብዙ ኮሜንት ይሰጣታል።ከምትፖስታቸው ነገሮች አብዛኞቹ ስለ ጋብቻ መልእክት የሚያስተላልፉ ናቸው።ትንሽ ግራ ያጋባሉ ። የሚሰጣትን ኮሜንት ሳነብ አንድ የገረመኝ ነገር አነበብኩ።ምን ይላል መሰላቹ። " አንቺ ልጅ ምን አስበሽ ነው?" አላት የሆነ ልጅ። እሷም ቀጠለች " አቆላምጣው እገሊዬ ምንላርግ ማግባት አምሮኝ እኮ ነው" አለች።ትንሽ ደነገጥኩ።እንደዛ ችላ ምትለኝ የነበረው ልታገባ አስባ ይሆን? ራሴ ራሴን የጠየኩት ጥያቄ ነበር። መልስ የለም።እኔ ስለ ትዳር ለማሰብ ገና አስር አመት ይቀረኛል።ብዙ ነገራችን አራምባና ቆቦ እየሆነብኝ ተቸግሬያለው።እኔም በበኩሌ ኮሜንት ሰጠኋት።ግን በውስጥ ሚሴጅ ነው።የማግባት ፍላጎት ያለሽ ተመስያለሽ ።አልኳት ። አዎ ሀሉዬ አለችኝ ።እቺ ልጅ ሁሉንም ነው እንዴ ምታቆላምጠው? በሌላ ጊዜም ጥያቄዬን አቀረብኩላት "የወንድ ጓደኛ አለሽ"?ሴት መስያት ስለነበር በግልፅ ነበር ምትነግረኝ። የለኝም አለችኝ።ትንሽ ተረጋጋው። ጥያቄዬን ቀጠልኩ"ወንዶች ባንቺ እይታ ምን ይመስላሉ?" "አይ ሀሉዩ ሁሉም የሚፈልጉትን እስኪያገኙ ድረስ ንግግራቸው ሁሉ ማሬ ፍቅሬ ነው ። ሚፈልጉትን ሲያገኙ ፀባያቸው ይቀያየራል" እሷ ነበር የተናገረችው።ደነገጥኩ ደሞ እኔ ምን አድርጊያት ነው? አይ እኔን አይወክልም።ታዲያ የጎዳት ሰው አለ ማለት ነው? ልክ ነሽ Hilu አልኳት። የ fb ስሟ Hilwan ነው ብያቹ አልነበር? በኔ ቤት ማቆላመጤ ነበር። ቀጠለች "አንቺስ ሀሉዬ አግብተሻል?" አለችኝ ። አንቺ ስትለኝ በውስጤ እተዝናናሁ ኧረ Hiluye እኔም እንዳንቺ የተጎዳሁ ነኝ ። አልኳት። አልዋሸሁም በሷ የተጎዳሁ ነኝ። "አይዞሽ ሀሉዬ አላህ ያቃል" አለችኝ።ጥያቄዬን ስጠይቃት እሷም ስትመልስ። ተግባባን እኔ ዱባይ ሀገር ለስራ መሄዴንና በቅርቡ እንደምመለስ አድርጌ ነው የነገርኳት። በደንብ ተግባብተናል አንዳንድ ያልገቡኝ ሚስጥሮችን አወጣጥቼያት ነበር።ከዱባይ ስመለስ እንደምንገናኝም አውርተናል። በዚ አጋጣሚ ድጋሚ አንድ ነገር ብልጭ አለልኝ ። በፊት ቁርአን ቤት እያለን አንድ በጣጣጣም የምታምር ቁርአን ሰጥታኝ ነበር። ይህ ቁርአን ነጋ ጠባ sዬን ያስታውሰኛል ።እንዲ ከመራራቃችን በፊት እሷን በአካል ለማግኘት ስል ብዙ ጊዜ ቁርአንሽን አትፈልጊውም ልስጥሽ ስላት እሷ ግን ማሜ አንተ ጋር ይቀመጥ ትለኝ ነበር።ምናልባት ለመገናኘት ከተቀጣጠርን ከሩቅ ሆኜ በህፃን ልጅ ቁረአኑን አቀብያት በfb በሴት ሆኜ ሳዋራት የነበርኩት እኔ መሆኔን አሳውቄ ላስደነግጣትም አሰቤ ነበር።ግን አልተሳካም ልንቀጣጠር አልቻልንም። የአረፋ በአል ተቃርቦዋል።ጥቂት ቀናት ነው የቀሩት እኔም ከዱባይ መጥቻለው sዬ እንኳን ደህና መጣሽ ብላኛለች። ጉዴን አላወቀች አይፈረድባትም።አሁን ወደ ሁለየኛው እቅዴ ምሸጋገርበት ሰአት ነው።እሱም ወንድ እንደሆንኩና ዱባይም እንዳልነበርኩ ልነግራት። ትንሽ ፈርቻለው ።ብሎክ ብታደርገኝስ፣ ማንነትህን ካልነገርከኝ እንዳታዋራኝ ካለችኝስ?፣የኔ ሀሳብ ደሞ አሁን ማንነቴን እንድታውቅ አልፈለኩም ። የኔ ፍላጎት ወንድ መሆኔን ብቻ ካወቀች ቡሀላ በ fb የተዋወቀችው የወንድ ጓደኛዋ ለመሆን እና በጓደኝነት ከተጣጣምንና ከተመቻቸን ቡሀላ እንደ ሰርፕራይዝ ማንነቴን ለመንገር ነው። ከቀኑ አስር ሰአት ነው ።fb ገባሁ online ላይ አለች ።አሰላሙ አልኩም ሒሉ ።ወአለይኩም አሰላም ሀሉዬ። እንዴት ነሽ? አለሁ። አንቺ እንዴት ነሽ? አልሀምዱሊላህ ደና ነኝ። ሒሉ አንድ ሚስጥር ልንገርሽ አትቆጭም? ኧረ ሀሉዬ የምን ሚስጥር ነው ንገሪኝ ችግር የለውም።አትጣይኝም? ለምን እጣላሻለው ንገሪኝ? ብሎክ እንደማታደርጊኝ ቃል ጊቢልኝ? እሺ ቃል እገባለው ንገሪኝ። እኔ ሴት አደለሁም ወንድ ነኝ😧😳። አፈረጥኩት። " ወይ ዘንድሮ እሺ ማነህ ደሞ አንተ?" አለች። የኧኧኧኧፈራሁት ደረሰ። እሱንማ አሁን አልነግርሽም። አልኳት ቃል ስላስገባኋት ብሌክ አታደርገኝም ብዬ። "ይቅርታ እኔ ከማላውቀው ወንድ ጋር ማውራት አልደልግም። አለች። እንደምንም ብዬ እኔ አንቺን ማናገር ብቻ ነው ምፈልገው ፣ መተዋወቁ ምንም አይሰራም አንቺን ብቻ በማናገሬ ደስታን አገኛለው አልኳት ።እንደፈለክ ። አለችኝና ከfb ወጣች። ደስ አለኝ። በሌላ ቀን fb ገባሁ። እህቴ ቤት ነው ያለሁት። ሀይ ሒሉ አልኳት። ሀይ አለችኝ።ማቆላመጥ አቆመች። ብዙ አወራን ፣ብዙ ተጨዋወትን።ያለ የሌለውን ሳወራ ፣ስቀልድ ስተስቅ፣ቀየን። በመጨረሻም " ማን ብዬ ልጥራህ" አለችኝ።እንደተመቻቸን ገመትኩ።ግንኙነታችንን ወዳዋለች ማለት ነው አልኩ በሆዴ። ከዛ መለስኩላት" ፈላጊዬ ወይም F እያልሽ ልትጠሪኝ ትችያለሽ አልኳት። ሳቀች hhhhhh ። አሳሳቅሽ ደስ ይላል ።አላኳት። እንዴት? አለች። መለስኩላት HaHaHaHa እያሉ መሳቅ ሰርአት ያጣ ነው። ያንቺው ደስ ይላል አለኳት።አመሰግናለው F. አለችኝ። አውሽኝ እመልስልሻለው? አይ እምቢ ። ቋጣሪ ብተሰጭኝ ምን አለበት። እሺ ውሰደው። ባንዳፍ hhhhhh አልኩ።ከዚ ጊዜ ቡሀላ ሳታውቀኝ ቢሆንም በጣም ደስተኛ ነኝ።ሁሌም በደንብ እናወራለን።እኔ መሆኔን ብታቅ ግን እንዲ ታወራኛለች? አይ አታወራኝም ። ከዚ ቀደም የነበረውን አስታውሳለው ከሌላ ወንድ ጋ እያወራች ከኔ ጋ ሲሆን ለምን ከበዳት?አላቅም።ወንድ መሆኔን ከነገርኳት ገዜ አንስቶ ማንነቴን ለማወቅ ማትፈነቅለው ድንገይ አልነበረም።እስቲ ካደረግናቸው ቃለ ምልልሶች መሀከል ጥቂቱን ላውጋቹ። ተከተሉኝ። አሷ ነበረች ጀማሪዋ ........................................... ....ተማሪ ነክ?ነበርኩ ።ዘንድሮ ካምፓስ ነኝእኔን የት ነው ምታቀኝ?ትምርት ቤት።የትሰፈር ነክ? ኧረ እሱንማ ከነገርኩሽ ታቂኛለሽ። እንዴት አቅካለው አንተ ብቻ ነክ በሰፈሩ ወንድ። እናንተ ሰፈር አልኳት።አሪፍ ነው አንድ ሰፈርነና አለች። #ክፍል_10 ይቀጥላል✍✍
Показать все...
👍 2
🔻:::::::::::::::ሚስኪኑ አፍቃሪ::::::::::🔻 ክፍል::::::::8⃣ት ግን ተስፋ አልቆረጥኩም በሶስት ቀን አንዴ ምናምን መደወሌን ተያይዤወለው ።እሷግን ሚስኮልም አርጋ አታቅም።ዛሬ ቀኑ በማያቃጥል ፀሀይ ደምቆ ላየብረሪው በሰው ጢም ብሎ ከጠዋት ጀምሮ በአሪፍ ድባብ ላይ ነው።ያሁሉ አንባቢ ተሰብስቦ ከፀጥታው ብዛት የተነሳ የትንፋሽ ድምፅ ራሱ ይሰማል ። በዚ መሀል አስር ሰአት አካባቢ ስልኬ ጠራ ያልገመትኩት ስልክ ።sዬ ነበረች እየፈጠንኩ ከላይብሪው ወጥቼ ስልኩን አነሳሁት። ሃሎ ማሜ ላይብረሪ እየመጣን ነው። ቦታ አለ? አለችኝ።ዛሬ ማውቀው የ sዬ ድምፅ ነው። ደስ ያላት ትመስላለች። ልታጠኑ ነው? አልኳት።ምክንያቱም ትምርት እንደማትወድ ነበር ምገምተው። አደለም አሳይመንት ልንሰራ ነው አለችኝ ።ብቻዋን አደለችም ።ቦታ እንደማይጠፋ ነግሪያት ስልኩን ዘጋችዉ።ወደ ውስጥ ገብቼ ቦታዬ ላይ ቁጭ አልኩ። ከጎኔ ክርስቲያን ሴቶች አሉ። ከፊት ለፊቴ ደሞ ወንዶች ናቸው ምንም ቦታ ላገኝላቸው አልቻልኩም ።ትንሽ እንደቆየሁ ከፊይ ለፊት ያሉት 3 ልጆች መፃፋቸውን ይዘው ተነስተው ሄዱ።ማመን ከበደኝ እንዴት ሊሆን ቻለ።3ወንዶች ለ3ሴቶች ቦታ ለቀው ሄዱ። ለዛውም እኔ ፊት።ቦታውን ያዝኩላቸው።ብዙም ሳይቆዩ sዬ ከባለ መነፅሯና ከዛች ከእንደራሷ አይነት ቀጫጫ ልጅ ጋር ላየብረሪ ገቡ።እነዚ ጓደኞቿ ትምርት ቤት እኔን ከsዬ ጋር ሲያዩኝ የተለየ ስሜት ፊታቸው ላይ አይባቸው ነበር። ይኮሳተራሉ፣እንደማፈር ይላሉ ፣ፊት ያዞራሉ፣ ወይም ካሉበት ቦታ ተነስተው ይሄዳለው። እኔ የትም አላውቃቸውም።አንድ ቀን ግራ ሲገባኘኝ s እቺ ባለመነፅሯ ማናት? በጣም ነው ምፈራት ብዬ ጠየኳት። ቁራን ቤት ትቀራ ነበር አለችኝ። አስቀርቻትም አቃለው ማለት ነው። ወይ ውርደት አልኩ በሆዴ ።ለካ አስቀሪ መሆኔን አውቃ ነው እንዲ ምትሆነው። እናም ላይብረሪ ውስጥ ከዛ ሁሉ ሰው መሀል እኔን እስኪያዩኝ ባለመነፅሯ ውር ውር አለች።sዬ ለየት ያለ ጅልባብ ለብሳለች ። በጣም አምሮባታል ።የኔ ታናሽ ሳይሆን ታላቅ ነው ምትመስለው።ጅልባቡ ከግርማ ሞገሷ ጋ ተደምሮ ትልቅ ሰው አስመስሏትል።በእጄ ምልክት ስሰጣቸው sዬ በኔ አቅጣጫ በኩል ባለው ወንበር ስትቀመጥ ሁለቱ ደሞ ከጎኔ ከነበሩት ሴቶች አቅጣጫ ተቀመጡ። ገና ሲገቡ ጀምሮ ያ የሚያጠና ወንድ በሙሉ አአአአአአአ ብሎ ሊጎርሳቸው ይመስል በስስት ሲመለከታቸው አስተውያለው። ዛሬ ከሳምንታት ቡሀላ አየኋት ።ውስጤ እየከዳኝ ነው። ከገባች ሰአት አንስቶ ማጠና እየመሰልኩ ሰርቄ እያየኃት ነው። የማጠናው አደለም መስመሩ ገፁም ጠፍቶብኛል። እነሱ ግን ብዙም ሳይቆዩ ወዲያው ነበር አሳይመንታቸውን መስራት የጀመሩት። ማንበብ ሲያቅተኝ ጠረጴዛ ላይ ያስቀመጠችውን ስልኳን አንስቼ ቀጥታ ጋላሪ ውስጥ ነበር የገባሁት ።እቤት ሆና በከፊል ተገላልፃ የተነሳቻቸውን ፎቶዎች ወደራሴ መላክ ጀመርኩ። የስልኬ የሚሴጅ ድመፅ የፍየል ጩኸት ስለነበር ፎቶው ሲገባ ጮኸ የላይብረሪው ሰው ሁሉ ነበር በአንድ ድምፅ የሳቀው ። ሶስት ፎቶ ላኩኝ ሶስቴ ሚእእእእእ አለ። ይሳቁልኝ ይሳቁብኝ ማውቀው ነገር የለም።እሷም ሳትቀር እሳቀች ነበር። ግን ፎቶ እየላኩኝ መሆኔን እሷም አልባነነችም። መግሪብ ሲደርስ ተነስተው ሄዱ። ስለ ፎርሙላው ከነ አካቴው ጠይቃኝ አታቅም። ረስታዋለች። ከላይብረሪው ቡሃላ ድጋሚ ግንኙነታችን በስልክ ብቻ ሆነ።አንድ ቀን ነው ትዝ ይለኛል በጣም እየተጨዋወትን በስልክ ከ30 ብር ካርድ የሚበልጥ አወራን ። የዛኔ ነበር fb ፈሬንዷ እንድታደርገኝ የጠየኳት ።fb ላይ ማውራት ከጀመርኩ ጀምሮ በጣም ተቀዛቅዘናል። ሲላት ትንሽ ታወራኝና ዝም ፣አንዳነዴ ጭራሽ አታናግረኝም።አሁን እኔም ፋራ መሆን የለብኝም ሰው በይሉኝታ እንዲያደርግልኝ ስለማልፈልግ ማቆም እንዳለብኝ ወሰንኩ።ለራሴም ቃል ገባሁ መርሳት መቻል እነዳለብኝ ። ካሁን ቡሃላ በምንም አይነት መንገድ ማግኘት እንደማልችልና ተስፋ መቁረጥ እንዳለብኝ ቆራጥ ውሳኔ ወሰንኩ። ምክንያቱም እንደጠላችኝ በብዙ ነገሮች ምልክት አየሁዋ።ከዚ በላይ መለመን የለብኝም።ስልኳን ከስልኬ አጥፍቼ የራሴን ህይወት መኖር ጀመርኩ።ሳልነግራት መደወል ተውክ ።ጠፋሁ ።አንድም ቀን ደውላ አታቅም።ግን ከተወሰኑ ጊዚያት ቡሀላ ግን ናፍቆቱን መቋቋም አቃተኝ ለመደወል ብዬ ስለኳን ኬት ላምጣው፣ ደሞ fb ላይም ብሎክ አረጊያታለው። በማስታውሰው መጠን የተለያዩ ቁጥሮችን ሞከርኩ ግን የደለትኩትን ስልክ ቁጥሯን ላገኝ አልቻልኩም። ማን ደልት አለኝ? ድጋሚ ራሴን መውቀስ ጀመርኩ። (ሚስኪኑ ማሜ) ።በዚህ ሀዘን ውስጥ ሆኜ፣ሳልናፍቃት ናፍቃኝ፣ሳትወደኝ ወድጃት፣ሳትደውል ደውዬላት፣ አንድ እጅ ብቻውን ማጨብጨብ አይችልምና አንድ ብቻዬን ሆኜ ምንም መፍጠር እንደማልችል በድምፅ አልባ አዋጅ እየተነገረኝ ነው። እኔ ግን ተስፋ አልቆርጥም ።ትግሌን እቀጥላለው ማንንም አላማክርም።በአንድ እጅ ማጨብጨብም እንደሚቻል በተግባር አሳያለው እያልከኩ ውስጤ እየነደደ ሀሳብ ማፍለቅ ጀመርኩ።ያለ እቅድ ማይሆን የለምና አንድ በጣም የሚያምር ሀሳብ ከመጋደሚያዬ ላይ ሆኜ መጣልኝ። ወዲያው ነበር ለመተኛት ካሰብኩበት ብድግ ብዬ የተነሳሁት።በዚ እቅዴ መሰረት sዬን ዳግም የማገኝበትን ተስፋ የሰነቅኩት። ምን ይሆን እቅዱ ቀጣይ ክፍል ላይ እንገናኝ። #ክፍል_9 ✍ይቀጥላል።።።
Показать все...
👍 2
🔻::::::::::::::ሚስኪኑ አፍቃሪ::::::::::::🔻 ክፍል: :::::::::7⃣ት መርዶው ባጭር አረፍተ ነገር በ3 ቃላት ብቻ የሚገለፅ እኔን እንክትክቴን ያወጣኝ ንግግር ነበር። አሱም እንዲህ ይላል "12 ቶች መግባት አትችሉም"።ለኔ ብቻ ነበር መርዶው ለሌላውማ ብስራት ከብስራትም በላይ ነበር ።ተማሪው ግማሹ ያፏጫል ፣ከፊሉ ይጮሀል፣ከፊሉ ደሞ እንደኔ አይነቱ ፊቱን አጨፍግጎ ነገሩን በትዝብት ይከታተላል። 11 ዶች መታወቂያ እያሳዩ አየገቡ ስለነበር ምናልባት ስትገባ ካገኘኋት ብዩ ባይኔ በር በሩን ስመለከት ቆይቼ አይኔ ደከመው።እሷም ቀድማ ገብታለች። አይኔ ከግቢው አጥር አሻግሮ ወደ ውስጥ እያየ ድመት ወተት አይታ ለመጠጣት እንደምትቋምጠው እኔም ጊቢ ውስጥ ለመግባት እቋምጥ ነበር። ግን ምን ዋጋ አለው አልችልም😢😢😢😢😢። ልክ የዛኔ sዬ የፎርሙላውን ትርጉም ሰላልነገርኳት በቀዘቀዘ መንፈስ ጥላኝ እንደሄደችው፣ ዛሬ እኔም ስሜቴን የምነግርበትን አጋጣሚ ስላከሸፉብኝ በቀዘቀዘ መንፈስ ዳግም እዚህ ትምርት ቤት ላልመለስ ወደ ቤቴ አቀናሁ። ከተዋወቅን አንድም ቀን በስልክ አውርተንአናውቅም ምክንያቱም ቀን በቀን በአካል እንገናኝ ስለነበር አላስፈለገም።አሁን ግን የቤት ምርኮኛ ሁኛለው።ከዚ ቀደም እንደነገርኳቹ ብቸኛ ነኝ ከሰው መቀላቀል ብዙም አይደላኝም።ከራሴ ጋር ማውራት አበዛ ነበር።አሁን ግን ከብዶኛል ጭርታ እንዳልወደድኩት አስጠልቶኛል።ወላጁን በሞት እንደ ተነጠቀ ታዳጊ ዝም ብሎ ብሶት ብሶት ይለኛል። ከጥቂት ቀናት ቡሀላ ትንሽ ወደ ራሴ መመለስ ጀምሪያለው። አእምሮዬ ላይም የፈተናው ነገር ብልጭ ብልጭ ይልብኛል።ከቤታችን ጥሩ ደረጃ ላይ እንድደርስ ምጠበቀው እኔ ነኝ።ታላላቆቼ ሁሉም ከታች ክፍል ነው ትምርት ያቆሙት። 12 ከመግባቴ በፊት በነበረኝ የማጥናትና ጎብዞ የመማር ባህሪዬ ነው ቤተሰቤ ሚያውቁኝ።በፍፁም አንድም ቀን ባልባሌ ቦታ ይገኛል ብለው ጠርጥረውኝ ስለማያውቁ አይቆጣጠሩኝም የትዋልክ የት አደርክ እያሉኝም።እናም ዩኒቨርስቲ የመግባት ህልሜ ጨልሞ እየታየኝ የቤተሰቤ ሸክም መሆኔ ደግሞ ይበልጥ አያበገነኝ ሲመጣ ድንገት የማላወቅ ሀይል ገፍትሮ ላይበረሪ አስገባኝ።የቀረችኝን አንድ ወር እረፍት የሌለው የ24 ሰአት ጥናት ማጥናት ተያያዝኩት።በ sዬ ናፍቆት የቆሰለው ማንነቴ ድብርቱን ሚያስረሳው ነገር ሳያገኝ አይቀርም።አሁን ከጥናቱ ጋ በጣም ተጣጥመናል፣ያለችኝ አጭር ጊዜ ስለሆነች ትኩረቴን ቀላልና የሚሰሩ ሳብጀክቶች ላይ አድርጊያለው።በተጨማሪም የትምርት ቤታችን ሰቃይ ተማሪዎችንም የመግባባት እድሉንም ስላካገኘሁ።ውስጤ ፈተናውን የማለፍ ተስፋው እያንሰራራልኝ ነው።ቁርስ በላው ላይብረሪ፣ምሳ በላው ላይብረሪ፣ ምሽት 3 ሰአት ሲል እቤት እገባለው።ታዲያ በዚ ሙድ ወስጥ ሆኜ ድብርቴ ቢጠፋም sዬን መርሳት አልቻልኩም። ከዚ በላይ መቆየት አልቻልኩም መደወል እንዳለብኝ ይሰማኛል።ውስጤ ደግሞ እሷ ለምን አልደወለችም? ይለኛል።አንተ ብቻ ነህ ምትወዳት? እንድጠራጠር እያረገኝ ነው። አይ እሷ እንደምጠላኝ ካፏ እስክሰማ መጠበቅ አለብኝ እያልኩ ከራሴ ጋ አመነታለው። ደወልኩ ሰአቱ ከመግሪብ ቡሀላ ነው።ቀኑን ሙሉ በነሻጣ ሳጠና ውዬ ውስጤ እርካታና ተስፋን በጥናቱ ምክንያት ተላብሶ በአሪፍ ሙድ ሆኜ ነበር። ለመግሪብ ሰላት ወጥተን ስንመለስ ነበር የደወልኩት ስልኩ ተነሳ።ልቤ መብረቅ የመታው መሬት ይመስል ሲሰነጠቅ ይሰማኛል። (ሚስኪን)።ሄሎ ቀጥሎ የሰማሁት ቃል ነበር። ግን ዝግ ያለ፣የመኮሳተርም ባህሪን የሚያንፀባርቅ ፣ ከምንም በላይ ደግሞ በቀዘቀዘ ስሜት የተለቀቀ ድምፅ ነበር።እኔ ደሞ ሰው ሲንቀኝ፣የበታች አርጎ ሲያየኝ ከማይ ምንም ነገር ቢቀርብኝ እመርጣለው።ሰው ሰው ሆኖ እንዴት ሰውን ከራሱ በታች አድርጎ ይመለከታል? ???እናም ይህን ድምፅ ከሰማሁ በኃላ ቀኑን ሙሉ የገነባሁት ሙዴ ድምጥማጡ ጠፋ።በዚም አላበቃም ሄሎ ሳልላት በመደወሌ ፀፀተኝ።ለነገሩ አንዴ ደውያለውና በጆሮዋ አልዘጋው። ሄሎ ሰላሙ አለይኩም ።እኔ ነበር ያልኩት። ዋለይኩመሰላም ።ማን ልበል? የሚል ድምፅ ተመለሰልኝ። ስልኬ እንደተራራ ነበር የከበደኝ ምለው ጠፋኝ።መጀመሪያ ሰልኩ ሲጠራ ድንጋጤ ሲወረኝ፣ሃሎ ሲባል ነሻጣዬ ደስታዬ ሲነፈግ፣አሁን ደግሞ ማን ልበል ስባል ንዴት አገንፍሎኛል። ማን ልበል እንዴት ልትል ቻለች? በደስታ ላወራ የነበረው ስልክ አሁን ንዴት በተላበሰ መንፈስ ሊሆን ነው። s መሀመድ ነኝ። አልኩ እንደምንም እራሴን አያረጋጋሁ። እንደፍሪጅ ውሀ በቀዘቀዘው ድምፇ ።እእእእ ማሜ እንዴት ነህ ሰላም ነው አለችኝ። ዘገነነኝ ።ማሜ ስባል ዛሬ አስጠላኝ።ማላውቃት ሆነችብኝ።በራሴ አፈርኩ።አፌ ሁሉ ተሳሰረ።እንደምንም 3 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተሰነባብተን። ስልኩ ተዘጋ ግያለው ፣መፃፌን ይዤ ወደ ቤቴ አመራሁ።እንደሰከረ ሰው ያረገኛል።ምን ሆና ይሁን እንደዛ ምትስቅ ምትጫወት ልጅ? በስልክ ለተፈጠረው ነገር ምንም መልስ አጣሁለት።ምክንያቱ ባልታወቀ ነገርማ ዝም ብዬ ማንነቴን ሁሉ የረሳሁባትን እንስት አልፋታም ። ብዙ ማረጋገጫዎችን ለመሞከር ወሰንኩ ።ቀን ቀን እያጠናው ማታ ወደ ቤት መግባት ሆኖዋል ስራዬ ጥሩም ተጉዣለው።ውስጤ ምንም ፈተናውን የመውደቅ ፍራቻ የለም አልሀምዱሊላህ ጭንቀቴም ፍራቻዬም ወደሷ ዞሮዋል። በየቀኑ አልደውልም ሙዴና ነሻጣዬን መምጫቸውን ጠብቄ ነው መደወል ምፈልገው ምክንያቱም ደስተኛ ሆኜ ለማውራት እንዲመቸኝ ።ደወልኩ ከቀኑ 11 ገደማ ይመስለኛል ።ተነሳ የዛሬው ድምፅ ይሻላል ።አወራን ፣አሁንም ትምርት ቤት እየሄደች እንደሆነ ነገረችኝ። ማልዋሸው ነገር ቢኖር በአካል ማቃት sዬ ግን አደለችም።ፍፁም በስልክ ተቀይራለች ። ሁሉም ሰው ይሆን በስልክ ሚቀያየረው።ወይስ ቴሌዎች ሊያጣሉን ፈልገው የሌላ ሰው ድምፅ አያሰሙኝ ነው ?። ምለው ጠፍቶኛል መደወል ለመተው ባላስብም ግን ቅፍፍ ብሎኛል ።የሆነ በማልፈልገው ነገር ላይ ተገድጄ ምደውል ምደውል እየመሰለኝ ነው። #ክፍል_8 ይቀጥላል::::::✍
Показать все...
👍 2
🔻::::::::::::::ሚስኪኑ አፍቃሪ:::::::::🔻 ክፍል 6⃣ ዛሬ ትላንትና ነገ እያልን ስለሱ እያወራንለት የነበረው ቀን ነው።sዬ ልታገኘኝ የፈለገችበት ጉዳይ እስካውቅ ጓጉቻለው። ረፍት ላይ ተገናኘን።ለምን በድንገት መምጣት እንደተወች አልጠየኳትም።እኔ በባህሪዬ ሰው በይሉኝታ ምንም ነገር ለኔ ብሎ እንዲያደርግ አልፈልግም። ውስጡ ያዘዘውን እንዲያደርግ ነው ፍላጎቴ።እሷም ጠፋች ።የራሷ ምክንያት ይኖራታል ብትነግረኝም ባትነግረኝም እንደፈለገች። ምንም እንዳልተፈጠረ ፈገግ እያልኩ። አሰላሙ አለይኩም s ። መልስ ሰጥታኝ ።" ማሜ ቁራን ቤት አዲስ የገባው ውስታዝ ኪታብ ሲያስቀራ አይገባኝም። አንተ ከተመቸህ እዚ በምሳ ሰአት እየተገናኘን አስቀራኝ" አለችኝ ። ገርሞኛል።እንዲሁም አስፈርቶኛል። የተወደድኩም እየመሰለኝ ነው። ብዙ ጊዜ ሰው ሲስቅልኝ፣ሲያቆላምጠኝ እና እኔ በምችለው እርዳታዬን ሲፈልግ የወደደኝ ይመስለኝ ነበር።(ሚስኪን) ።ሁኔታዋ በኪታብ ሰበብ በየቀኑ ለመገናኘት ዘዴ እየዘየደች ይመስላል። እርግጠኛ ነሽ መቅራት ትፈልጊያለሽ? አልኳት። እንደምትፈልግ ስትነግረኝ። ከነገ ጀምሮ እንደምንገናኝና መቅራት እንደምንችል ፈቃደኛ መሆኔን ነግሪያት ተለያየን። ከዛ ቀን ጀምሮ የተቋረጠው ግንኙነታችን እንዳዲስ ቀጥሎዋል። እሷም እኔም የየራሳችን ኪታብ ይዘን የትምርት ቤቱ ሜዳ ጋ አንድ ጥግ ስር የመጀመሪያ ቂራት ለመቅራት ተቀመጥን።የየራሳችን ኪታብ ያስፈለገው ያልተገባ ቅርርቦሽና ንክኪ እንዳይፈጠር ነበር። እኔ ማስረዳቴን ቀጠልኩ የሷ ሁኔታ ግን ግራ ሚያጋባ ነበር። አይኗ ኪታቡ ላይ ሳይሆን እኔ ላይ ነው ።እየሰማችኝ አደለም ።ሼም ያዘኝ።ገባሽ ?አልኳት ቀና ብዬ እያየኋት። አንገቷን እየነቀነቀች አይኗን እኔ ላይ ተክላ አው አለችኝ። ፌቴን አዙሬ አነብላት ቀጠልኩ ከተወሰነ ደቂቃቡኋላ ዳግም ዞሬ ሳያት አሁንም እያየችኝ ነው።ይሄ ነገር ወዴት ወዴት እያመራ ነው? በውስጤ አጉረመረምኩ። አሁን የጠረጠርኩት ነገር እውነት መሰለኝ። ስሜቷን ለመረዳት በማሰብ ከአንድ መሰረመር ያልበለጠ ቀርተን ኪታቡን ዘግቼ ለዛሬ ይበቃናል አልኳት።አወራን ፣አወራን፣አወራን፣ ትፈነድቃለች፣ትስቃለች ፣እኔ በሷ ሳቅና ደስታ እረካለው።ለሞራሏ እገለፍጣለው ።ተጨዋውተን ተለያየን።ግን በውስጤ እየተገረምኩ ነው። ኪታቡንስ ልንተወው ነው? በነጋታው መቅራት እንደምትፈልግ ለማረጋገጥ ብዬ ላስቀራት ብሞክርም ፊቷ ላይ ምንም የመቅራት ፍላጎት ማንበብ አልቻልኩም። ትንሽ ታዘብኳት ግን ደስ ብሎኛል ።ከኔ ጋ ለመሆን ፍላጎት እንዳላት ራሴን አሳመንኩት። ኪታቡም ተረሳ እኔም እሷን በሙሉ አይን ማየት አብዝቻለው።ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ፀጉሯ የመመልከት አቅሙን አግኝቻለው።ግን ከመዳፏና ከፊቷ በቀር ሌላ የሚታይ ቦታ አልነበራትም።ረጅም ጉርድ፣ ካልሲ ትለብሳለች።አይን ትልቅ ተፅዕኖ አለው።ያያል ለልብ ማሳሰቢያ ይሰጣል።ልብ ደሞ ይሸፍታል።አእምሮ ብዙ ነገር ያስባል፣ብዙ ነገር ያቅዳል። አልሀምዱሊላ ከማየት የዘለለ አእምሮዬ ሌላ ምንም አላዘዘኝም። ሁሌም ስትመጣ የምትይዘው ደብተር ነበር ከለታት አንድ ቀን አንዴ ልየው? ብያት የማየት እድሉን ስትሰጠኝ እውስጡ በርካታ የፍቅር ግጥሞችና ከጀርባው ደግሞ ስሟን፣ስልኳን፣ ሆቢዋን፣ ባጠቃላይ ስለሷ ብዙ ኢንፎርሜሽን የሚናገር ፅሁፍ አለ። ጌም ነገር ነው የሚሞላ ። ግጥሞቿ አብዛኞቹ በፍቅር የተጎዳ ሰውን የሚገልፁ ናቸው። በግጥሞቿ አንድ በጣም የምትወደው ሰው እንዳለ ተረድቻለው።ግን ማን ነው? እኒጃ ራሴን በፍፁም አልጠረጥርም ።ከተዋወቅን አመት ሳይሞላን፣ከማውራት በቀር ምንም ነገር ሳናደርግ እንዴት ሊሆን ይችላል?ጠየኳት" እቤት ወስጄ ደብተሩን ላንብብ?" አሷም አለችኝ "ውሰደው በዛውም ሚሞላውን ሙላ " አለችኝ። እኔም ግጥሞቿን አነበብኩ በቃሌም የሸመደድኩት ነበር። በዛውም ሚሞላውን ሞላሁ። በዚ አጋጣሚ ነበር ስልክ የተለዋወጥነው።እንዲ እንዲ እያልን የግቢ ላይፋችንን እያሳለፍን ነው።ግጥም ታነብልኛለች ።እኔ ደሞ ልክ Bed story ይመስል ተመስጬ ሳዳምጣት። እሷ ስጦታ ስታመጣልኝ እኔ ደሞ ልቤን በስጦታ መልክ ስሰጣት።ወሩ ሚያዝያ ነው ።በቀጣይ ወር የ 12 ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወሳጅ ነኝ ። ግን አደለም ስለ ፈተና ላስብ ተማሪ መሆኔን ራሱ ሳልረሳው አልቀርም። አሁን ያስጨነቀኝ ትምርት ቤታችን ለፈተና ዝግጅት እንድናደርግ በሚል ከፈተና አንድ ወር ቀደም ብሎ ነው ትምርት ሚዘጋልን።እሷ 11 ኛ ክፍል ስለ ሆነች እስከ ሰኔ እዚው ትቆያለች።ከዚ ቡሀላ የት አባቴ ነው ማገኛት? ሰፈሯን አቅጠጫውን እንጂ የት እንደሆነ አላቅም።ባውቅስ እንዴት ብዬ ነው ሰፈሯ ምሄደው።የለመድኩት እሷ መጥታ እንደምትወስደኝ ነው።ግራ ገባኝ ።እሷም መለያየታችንን ብታውቅም ምንም ነገር አላለችኝም። 12 ቶች ትምርት ጨርሰን ግቢውን ለቀን ለመውጣት 2 ቀን ሲቀረን እንደሌላው ጊዜ ሜዳ ስር ተቀምጠን ማውራቱን ትተን ከግቢ ወጣን። በበርበሬ ወይምበጨው በረንዳ አርገን አቧቦራ መስጊድን አቋርጠን በኳስ ሜዳ በኩል አድካሚ የሆነ ወክ አድርገን ወደ ጊቢ ገባን።ሁለታችንም ደስተኛ እንመስላለን።የዛኔ የማረሳወ አጋጣሚ ቢኖር ልክ ወካችንን ጨርሰን ግቢ ከመግባታችን በፊት መናኸሪያ አካባቢ አንድ መኪና ሊገጫት ወይም ሊገፈትራት ሞክሮ ነበር።ግን አላህ አተረፋት። ከዛ ቢገጨኝስ ስትል ተከትዬሽ ነበራ ጎማ ውስጥ ምገባው አልኳት።ተገርማ" እነዴለምን? አለችኝ። ወክ እናርግ ብዬ ይዤሽ የወጣሁት እኔ ነኝ ስለዚ አንቺ በመኪና አደጋ ብትሞቺ እኔ እንደገደልኩሽ ነበር ምቆጥረው። ከፀፀቱ ለመዳን አብሬሽ ብሞት እመርጣለው ለማለት ፈልጌ ነበር አባባሌ። ያ ቀን የማጄላንን የመሬት መዞር ታሪክ ያስታወሰኝ ነበር።ደክሞናል እነሱ ክፍል ጀርባ ቆምን።የእኛ ክፍል ተማሪዎች ከሰአት ላለ መማር አድማ አድርገው ከግቢው እየጨፈሩ ወጡ። ከነሱጋ ለመሄድ እየቸኮልኩ s ቻው በቃ፣ስለ ወኩ በጣም አመሰግናለው ደስስስስ ብሎኛል አልኳትና ።እጇን ይዤ የሆነ ፎርሙላ ፃፍኩላት። እኔና እሷ ከተዋወቅን ዛሬ ተሳስቼ በደስታ መንፈስ እጇን ነካኋት።የፎርሙላው ትርጉም ሲፈታ "አፈቅርሻለው" ነበር ሚለው። ምንድነው ስትለኝ ሰው ጠይቀሽም ቢሆን ትርጉሙን ፈልጊው ብያት እንደ ህፃን እያረገኝ ከክፍል ጓደኞቼ ጋ ከግቢው ወጣን
Показать все...
👍 5
በነጋታው እረፍት ሰአት ሲደወል እየከነፈች ክፍል ድረስ መጥታ ማሜ ኧረ ምን ማለት ነው ንገረኝ አለችኝ።አቤት ቀልብ ስትስብ ትንፋሿ እየተቆራረጠ፣ክንፍ እያለች ፣ፈገግታና ጉጉት በሞላበት ያ ውብ ፊቷ በአይኗ እየተማፀነችኝ ነበር ትርጉሙን የጠየቀችኝ።በሰአቱ ከሁኔታዋ አንፃር ትኩር ብዬ ሳያት አንዲት እናት ያአንድ አመት ህፃን ልጇን አቅፋ በስስት አይን አይኑን እንደምታየውና ወድያና ወዲ እያረገች እንደምታጫውተው እኔም sዬን ባደረኳት ብዬ ተመኘሁ። ትከሻዋን ደገፍ አድርጌ ይዣት ወደ ክፍሏ ግማሽ መንገድ ከሸኘኋት ቡሀላ አርብ ከዚ ትምርት ቤት ስንወጣ እነግርሻለው አልኳት።እንድነግራት በጣም ጓጉታ ስለነበር አልነግርሽም ስላት ሞራሏን ሳልሰብረው አልቀርም።በቀዘቀዘ መንፈስ ሆና ትታኝ ሄደች ።እለቱ አርብ ነው ገና ከጠዋቱ ከቤቴ ሳልወጣ ነበር የዘነበው።መንገዱ ሁላ ጭቃ ሆኖዋል ።ትምርት ቤትም ባልሄድ ያስብላል ።ግን ከምንም በላይ ለsዬ ፍቅሬን ምነግርበት እንዲሁም ትምርትቤታችንን ምንሰናበትበት ቀን ነው። ዲንጋይም ቢዘንብ የመሄድ አቋሜን አልቀይርም!!!!! እየተጓዝኩ ነው ዛሬ ልክ የዛኔ የመጀመሪያ ቀን sዬን ለማግኘት ስጓዝ እንደነበረው አይነት ስሜት እየተሰማኝ ነው። ትምርት ቤት እየተቃረብኩ ሰመጣ በር አካባቢ ብዙ ፖሊሶች ተሰልፈው ቆመዋል።የመኪና መንገዱ ደሞ በተማሪዎች ተጥለቅልቆዋል። ከትርምሱ መሀል ገብቼ ነገሩን ሳጣራ። ፀፀትን ሚያለብስ፣አልቅስ አልቅስ ያስባለኝን፣ብጮህ የሆዴን የእልህ ቃጠሎ የማያሰታግስ የሆነ መርዶ ተነገረኝ ። #ክፍል_7 ✍✍✍ ይቀጥላል
Показать все...
👍 5❤ 1
🔻:::::::::::ሚስኪኑ አፍቃሪ::::::::::::🔻 ክፍል 5⃣ት እኔም ፊቴን ወደሷ ሳላዞር አልቀርም። ቀጣዩ ላይፌ ምን ሆነ? ከተሰናበተችኝ ሰአት አንስቶ ሆዴ እየሳቀ ፣የተወዳጅነት ስሜት እየተሰማኝ፣በዛ በሚያስጠላው ፈገግታዬ እየተፍነከነኩ ወደ ዙሁር ሰላት አመራሁ።በነገራችን ስስቅ ሰው እንዳያየኝ እጄን አፌ ላይ አደርጋለው ወይም አነገቴን እደፋለው።ላለ ማስፎገር።ለምዶብኛል። አንዳንዴ ግን እየረሳሁት ሰው ፊት እገለፍጣለው። ወይኔ ካለፈ ቡሀላ እንዴት እንደምሸማቀቅ። ግን እኮ እኔ እንደ ማስጠላ ምንም ማረጋገጫ የለኝም ግን እንዲው ስስቅ ሚያስጠላብኝ ስለሚመስለኝ ነው። ለዚ ሁሉ ምክንያቱ ደሞ ታላቅ እህቴ ናት።ታሪኩ እንዲህ ነው። ይመስለኛል የ15 አመት ጎረምሳ እያለሁ እኔና ሁለት ታላላቅ እህቶቼ አንበሳ ጊቢ ለመዝናናት ሄደን ነበር። እዛ ያሉትን አንበሳና የተለያዩ እንስሶችን እስኪሰለቹን በአይን ከሰለልናቸው ቡሀላ።እንደተለመደው ሴቶች ዛፍና አበባ ባለበት ሁሉ ፎቶ ያምራቸው አደል? ስልካቸው ቦታ እስኪያጥረዉ ድረስ መነሳት ጀመሩ። እኔም ጣል ጣል እየተነሳው ነበር ።በዚህ መሀል ነበር የታላቄን ታላቅ እህቴን አቅፌ ታላቄን አንሽን ብለናት ልታነሳን ስትል ለፎቶው ውበት ብዬ ፈገግ ስል ምን ብትለኝ ጥሩ ነው? እስቲ ገምቱ። ኮስተር በል አንተ ስትስቅ አያምርብህም!!!!! የፈጣሪ ያለህ እንዴት ሞራል ሚሰብር ንግግር ነው።ይኸው ከዛ ጊዜ ጀምሮ በገዛ ጥርሴ እንደ ኪራይ ቤት እየተጠነቀክኩ ነው ምጠቀመው።ወደ ጉዳዬ ስወስዳቹ:-- እስቲ ተከተሉኝ-------------------------------------------------------መስጊድ ደረስኩ። ሰገድኩ።ምሳ ሳልበላ የከሰአት ትምርት ለመማር ክላስ ገባሁ ።አሁን ውስጤ በጣም ረክቶዋል።ልክ በከፍተኛ ጥም ውስጥ ሆኜ ቀዝቃዛ ወሀ እንደጠጣሁ፣ ለቀናት ሳልበላ በድንገት ተመግቤ እንደረካሁ ያህል የመንፈስ እርካታ ይሰማኛል።በዛ መንግስት በሰራው ሰባራ ዴክስ ተቀምጬ በባለ ስልጣን ዙፋን ላይ የተቀመጥኩ ያህል እየተሰማኝ፣አእምሮዬ ቀጣይ በሚያሳልፋቸው ጣፋጭ ጊዜያቶች ምራቅ አያስዋጠኝ በሀሳብ ባህር እያስዋኘኝ ነው።አቤት የባህሩ ጥልቀት!! መጨረሻውን ሳላይ ከሰመጥኩበት ሀሳብ የቀሰቀሰኝ የትምርት ቤቱ ደወል ነው። ደብተሬን ይዤ ሳልማር እንደተማረ፣ሳይገባኝ እንደ ገባው ተማሪ ሆኜ ከተማሪ እኩል ወደ ቤት ለመሄድ ተነሳሁ። ከግቢ ወጥቼ ቀኝ ግራዬን ስመለከት በሁለተኛው በር መግቢያ ዳር ላይ አጅሪት ቆንጂት ጅልባብ ለብሳ ቆማለች። አሁን ነው በባለፈው ከኃላዬ ስትከተለኝ የነበረችውን መላእክት ያየኃት። ዋው በጅልባብ እንዴት እንደምታምር።ይህንን ደግሞ ደጋግሜ ነግሬያታለው።ምናልባት ጅልባብ ለመተው ሀሳብ ከሰነቀች ለሀይማኖቷ ባይሆንም ለውበቷ ስትል እንድትለብስ ብዬ ነበር አነጋገሬ። እሷን ብቻ እያየሁ ባልበላ ባልጠጣ ምመርጥበት ደረጃ ደርሼ ነበር በሰአቱ።ሚስኪን እኮ ነኝ። ውስታዟ መሆኔን ከነ አካቴው ጠፍቶኛል። ሁሉ ነገሬ እሷ ሆናለች። በእጇ የጠብቀኝ ምልክት አሳየችኝ ። አብረን ወደ ቤት እያወራን አመራን ። መንገዱ ለካ እንዲ አጭር ነው ሳላውቀው ሰፈር ደረስን ።መንገድ ላይ አብረን ሆነን ሚያየን ሁሉ አቤት ስታምሩሩሩሩ ሚሉን ወይም ከኃላ በቅናት መንፈስ ማጅራቴን ብለው ሚደፉኝ ነበር የሚመስለኝ። ብቻ ውስጤ ኩራትን ተላብሶ ፣ ቀናም ብዬ በሙሉ አይን ሳላያት መንገዳችን አልቆዋል። ሁለት መንታ መንገድ መገንጠያ ላይ ቆምን ።የሷ ሰፈር በቀኝ መገንጠያ ላይ ባለው መንገድ በኩል ሲሆን የኔ በግራ ባለው ነው። እሺ s ቻው ስላት ።ቻው እሺ ማሜ አለች ። ደስስስ አለኝ ።እንዴት ደስ አይለኝ ማሜ እኮ ነው ያለችኝ። የተወሰኑ እረምጃዎችን ወደኃላ እየተራመድኩ በሚያስጠላው ፈገግታዬና በአይኔ ሸኘኃትና ዞሬ ወደ ቤቴ አመራሁ። የዛን ቀን መኪና ራሱ እንዲ በፍጥነት ሚያደርሰኝ አይመስለኝም።መንገዱ እንዴት አባቱ ነው ያጠረው።ወይስ ፀሀይ ሲመታው እሳት እንደነካው ፌስታል ኩምሽሽ ማለት ጀምሮዋል? የወቀሳ ጥያቄ መንገዱን እየጠየኩት ቤቴ ገባሁ ።ጠግቤ ነበር ምግብም አላሰኘኝም ። ግን እኮ ከቁርስ ቡሀላ ምንም አልቀመስኩም። ካሁን ቡሀላ እኔ ሁለት ሰው ሆኚያለው። ስበላ ፣ሰተኛ፣ስቀራ ፣ስማር፣ስቀመጥ ፣ስቆም በሁሉም ቦታና ጊዜ sዬ አለች። ሲመስለኝ ግን ከጭንቅላቴ ባንዱ ጎን በመንፋስ ጠጋ በል ብላ ሳትቀመጥ አትቀርም። ዋናው ፍቅር ነው ይበቃናል ።ትቀመጥ ለዘላለም።መጃጃል ጀምሬያለው።ብቻዬን ሆኜ ፈጌ መጫር አብዝቻለው። በሀሳብ የህንድ ፊልም ከሷጋ እየሰራሁ ነው። እጆቼን ዘርግቼ እንደ ሻሩክ እያረገኝ ነው። ሰማይ ላይ እየተንሳፈፍኩም ይመስለኛል።ጋንጃ በኦክስጅን መልክ ወስጃለው እንዴ? ግራ ገብቶኛል። የሆነ የሆነ ሰአት ላይ እንደ መባነን ስል ራሴ በራሴ ላይ እስቃለው።አንዴ አንታርቲካ የበረዶ ተራራ ላይ ስንሯሯጥና ልብሷን ንፋስ ፊቴ ላይ ሲያለብሰኝ፣ አንዴ ደግሞ በጣም ንፁህና በጣም አረንጓዴ በሆነ ጀነት ውስጥ ተቀምጠን በፍቅር አለም ቅልጥ ስንል ይታየኛል ።ከዚ በላይ መጃጃል አለ እንዴ?በነጋታው በረፍትና በምሳ ሰአት እክፍሌ ድረስ መጥታ አብረን ከሰው ገለል ምንልበትን ቦታ መርጠን አወራን ፣ተጨዋወትን ።ለካ ከተቃራኒ ፆታ ሲኮን በማያስቅ ይሳቃል?ፍቅር ለካ መጃጃል ነው።የኔና የሷ ክፍል ከግቢው በዳርና በዳር በኩል ስለነበር ትንሽ ይራራቃል።ሁልጊዜም እሷ ነበረች ክፍሌ ድረስ ምትመጣው እኔ ደሞ ያቺ ኮሪደር ላይ ቆሜ እጠብቃታለው። አንድም ቀን ክፍሏ ሄጄ አላውቅም። እኔ እንደምፈራና እሷ ክፍል መምጣት እንደማልችል እነግራት ነበር። እሷም ችግር የለውም ብላኛለች። በቃ ከዚ ቀን አንስቶ ለትምርት ሳይሆን በምሳና በረፍት ሰአት ከሷ ለማውራት ብዬ ብቻ ነበር ምሄደው። ቅዳሜና እሁድን እየጠላሁዋቸው መጣሁ። የተዋወቅነበት ሳምንት አልቆ በቀጣይ ሰኞ ከረፍት ስንወጣ ትመጣለች ብዬ ነበር ።ግን ስለቀረች ከክፍል ወጥቼ ግቢ ውስጥ ወክ ሳረግ ከኃላዬ እየሮጠች መጣች። የመጣችበትን አቅጣጫ ዞሬ ሳይ ባለመነፅሯ ና አንዲት እንደ sዬ ቀጠን ያለች ልጅ ዶናት ቤቱ ፊት ለፊት ቆመዋል ።ከጓደኞቿጋ ዶናት እየበሉ እንደነበር ገመትኩ ።በእጇም ዶናት ይዛ ነበር። እንዴት ነሽ ሰላም ነው? ውይ እነዚ ቃላቶች ሚሸጡ ቢሆን ኖሮ አንደኛ እኔ ነበርኩ በነፃ ማከፋፍለው። ቅዳሜና እሁድ እንዴት እንደረዘመብኝ አልኳት።የውነቴን ነበር። "እኔም" አለች አይን አይኔን እያየች።አፍራታለው፣አከብራታለው በሙሉ አይን አላያትም።በጨረፍታ እያየሁ ጎንበስ ነው ስራዬ።ምክንያቱም ቁራን ቤት እያለሁ በአእምሮዬ የምስላት መላእክት ስለምትመስለኝ።እኔም ያለችው ቃል ግን በረፍት ሰአት ከመቅረቷ ጋር አልስማማ ብሎኛል። እንካ ዶናት ባላህ ስትለኝ እየተቅለሰለሰች። ዛሬ ሰኞ አደል ረሳሽው? ፆመኛ ነኝ አላኳት። ከዚም በፊት ምሳ እንደማልበላ ከነገርኳት ቡሃላ ምሳ ልተጋብዘኝ ስትጠይቀኝ እንደምፈራ ነግሬያት ስለነበር ነው ዛሬ በአላህ ያለችኝ። እሺ ብላኝ እሷም ወደ ጓደኞቿ ተመለሰች እኔም ወደ ፊት አመራሁ።እኔና እሷ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሁነን መስከረም አልቆ፣ጥቅምት ፣ጥቅምት አልቆ ህዳር፣ህዳር አልቆ ታህሳስ ገባ። ይህን ጊዜ ሁላ ስንገናኝ እሷ ነበረች ክፍሌ ድረስ እየመጣች ምትወስደኝ።ረፍት ላይ መምጣት ካቆመች ቆይታለች።የትምህርት ቤታችን ሜዳ ጋ አሪፍ መከለያ ዛፍ ስር ተቀምጠን እሷ በብዛት እያወራችልኝ እኔ በብዛት አንገቴን ደፍቼ ሳደምጣት 3 ወር ገደማ ሞላን።
Показать все...
👍 2❤ 1

👍 3