cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Bilal Media & Communication

Рекламные посты
236
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
-930 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
#ቻሌንጅ ቀን ሶስት አልሀምዱሊላህ የቻሌንጅ ቀን ሶስት ንጋት ጀምሯል ቀናችሁን በሰደቃ በመጀመር ለ100 ህፃናት #እንደ_እናት_እንደ_አባት ለኢድ በአዲስ ልብስ የህፃናት ደስታ ሰበብ እንሁን .👇👇👇👇👇 1000451773759 .©Darul Arqem Development and charity . ሰደቃ አፍንጫ ሊያሸተው የማይችል ነገር ግን ልብ ዉስጥ ልዩ ስሜትን የሚፈጥር ልዩ መዓዛ አለው ዐሊ ጠንጣዊ ረሂመሁላሁ
Показать все...
አያምሩም በረቢ?! አምና ያለበስናቸው ሴት ህፃናቶች እኮ ናቸው ያኔ እኛም ሆንን ልጆቹ በጣም ተደስተን የዋልንበት ድንቅ ጊዜ ነበር ታድያ ዘንድሮስ ያን ጊዜ እንድንደግመው ከጎናችን አትሆኑምን? 👇👇👇👇👇 1000451773759 ©Darul Arqem development and charity
Показать все...
Repost from ቢላል ሚዲያ
ግብዣ 👇👇👇👌 @venuee13
Показать все...
Repost from Venue
Фото недоступноПоказать в Telegram
<< አንቱ ሰው እንዴት ያለ ፍቅር ነው ጊዜ የማያስረጀው? >> << የኔ ልጅ ካለመጠን ከፍ የማታደርገው፣ ከወሰኑ የማታሳንሰው፣ ሀቁን የምትጠብቅለት ፍቅር በጊዜ ውስጥ ፈገግታው ይጨምራል። ፍቅር አደራ የመጠባበቅ ቃል ኪዳን ነው። ሀቁን ለባለ ሀቁ ስታደርስ ሀቅህ አይጓደልም። >> << ፍቅሮን እንደምን ጠበቁ? >> << ፍቅር የሚቸረውን የፍቅር ባለቤትን ሀቅ ለመጠበቅ ሞከረን እንጂ የፍቅር ምንጩን እየዘነጋን ፍቅራችንን ለመጠበቅ አልሞከርንም። ፍቅራቸውን ብቻ ለመጠበቅ የሚታገሉቱ የሚስቱት ይበዛል። የኔ ልጅ የፍቅር ምንጩን ሀቅ ጠብቅ ፍቅርህ ንፁህ ይሆናል። >> << አንቱ ሰው እወዶታለሁ! >> << የፍቅር ምንጩን ከማጣት ይጠብቅህ! >> << አሚን! >> (አብዱልሀኪም ሰፋ) : @Venuee13 @Venuee13
Показать все...
Repost from Venue
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንባዋን ከልላ ሳቄን ምታጎላ መንገዴን አስታዋሽ መካሪዬ እንዳልዋሽ! እሷ ውቧ አይነ ’ርግቧ። ሳልደግፋት ካክራ ሆና ፀንታ የኖረች ተፈትና ቃል ቆጥባ የሰከነች ስትገፋ የጀገነች እሷ ፅኑ ባለ ልቧ አይነ ’ርግቧ። አርማ ክብሯ ንግስ ድንበሯ መታወቅያ ምልክቷ መሰተሯ ጥልቅ ውበቷ እንኳን ገላ ሲወርድ ላቧ ሀያዕ አለው ያ’ይነ ’ርግቧ። ዘመናይት በከፍታ ሽሙንሙን ነች በዝምታ ክፍት ሲላት አላት ኸሊል ሽሽት ውሽቅ ወደ ጀሊል። ሰናይ ሰብር ሰርክ ቀለቧ አብሪዋ ጌጥ አይነ ’ርግቧ። [ አብዱልሀኪም ሰፋ ] : @Venuee13 @Venuee13
Показать все...
04:22
Видео недоступноПоказать в Telegram
6.62 MB
(( « ከናንተ በስተፊት የነበሩ ሰዎችን መንገድ ስንዝር በስንዝር ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ ! "ዳባ" (የምትባለው እንሰሳ) ጉርጓድ ውስጥ ቢገቡ እንኳን ተክትላቹ (ትገባላችሁ‼️" እኛም ( እንዲህ በማለት) ጠየቅናቸው። " አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! የሁዳና ነሳራን ማለቶት ነውን ?! " "ታዲያ ምንን ነው ?‼️( እነሱን ቢሆን እንጂ ) » )) 👉 ከሃዲያንን የመከተላችንና የመውደዳችን ታማኝነት በመልዕክተኛው አንደበት በዚህ ደረጃ ነው የተገለፀው !!! ❤ አዎ ! ስሜት አሸንፎን በመታወራችን የተነሳ መልካም አስከታይ ሳናጣ ... መጥፎ ተከታይ ሆነን ቀራን !!! አዎ ክፉዎች እየመሩን 🔥 ውስጥ ሊከቱን እያሮጡን ነው‼️ደጋጎቹ ቀደምቶች ደግሞ የውለታቸውን ክፍያ በትዝብት ከኛ እየተጠባበቁ ነው። « ወይ ! የኛ ነገር ... ውለታ በዪ ሆነን መቅረታችን ... ያሳዝናል !!! ምን ይሆን ፍፃሜያችን ???‼️» 👉 የቂያማ ዕለት አምላካችን አላህ ዘንድ እውነቱን ሳንጨምር ሳንቀንስ "ዒድ" ብለን አክብረን አሳይተን አደራችንን ተወጥተናል ሲሉ... አደራውን ቆረጣጥመን የበላነው እኛ መልሳችን ምን ይሆን ??? ❤ قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله : ( وأما اتخاذ موسم غير المواسم الشرعية كبعض ليالي شهر ربيع الأول التي يقال : إنها ليلة المولد , أو بعض ليالي رجب , أو ثامن عشر ذي الحجة , أو أول جمعة من رجب , أو ثامن من شوال الذي يسميه الجهَّال عيد الأبرار : فإنها من البدع التي لم يستحبها السلف , ولم يفعلوها. والله سبحانه وتعالى أعلم). ا.هـ. مجموع الفتوى لشيخ الإسلام ابن تيمية (25/298). 👉 አላህ ይዘንለትና ሸይኸል ኢስላም ኢብን ተሚያ እንዲህ ነበር ያለው ፦ « ሸሪዓው ካደረገው የክብረ-በዓል ውጪ መያዝን ከሆነ ... ልክ ከፊል የረቢዓል-አወል ወር ሌሊቶችንና የነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የልደት ቀን በማለት ማክበር ፤ ከፊል የ"ረጀብ" ወር ሌሊቶችን ፥ የዙል-ሒጃ 18ኛውን ቀን ፥ ከ"ረጀብ" ወር የመጀመሪያውን "ጁምዓ"ና እነዚያ መሀይባን የሆኑ ሰዎች ደሞ "ዒዱል አብራራ" ( የምርጦች ዒድ) በማለት የሰየሙት የሆነው ከ"ሸዋል"ወር 8ኛውን ቀን "ዒድ" አድርጎ ማክበር ቀደምት ደጋግ ሰለፎች ያልወደዱትና ያልተገበሩት የሆነ "ቢድዓ" (አዲስ ፈጠራ) ነው !!! » ጥራት የተገባውና ከፍ ያለው አላህ የበለጠውን ዐዋቂ ነው !!! መጅሙዓ ፈታዋ (25/298) 👉 ታዲያ ለምን አንመከርም ?? ስለምንስ አንገሰፅም ?! የኛ ባልሆነ ነገር መጌጥ እየፈለግን እውነተኛው ኢስላም ያወጀልንን የ"ዒድ" ገፅታ እናበላሻለንን ?!‼️ አዎ ! ኢስላም ያወጀልን ዓመታዊ ባህላችን (ሁለት ነው !!!) « ومما أحدث الناس اليوم بدعة عيد الأم، عيد فلان، عيد فلانة، تشبه بأعداء الله، هذه الأعياد تشبه بالنصارى واليهود، هم أهل الأعياد، وليس لنا إلا عيدان نحتفل بهما: عيد الأضحى، وعيد الفطر، وليس لنا أن نحدث احتفالات بأعياد أخرى،...» (دروس و محاضرات) (التعليقات على ندوات الجامع الكبير) الإمام ابن باز رحمه الله  👉 « በአሁን ጊዜ ሰዎች የፈጠሩት ከሆነው አዲስ ነገር ውስጥ የ" እናት ዒድ" ፥ የእከሌ "ዒድ" ፥ የእከሊት "ዒድ" ፥ የሚባለው ነገር ሲሆን በአላህ ጠላቶች መመሳሰልም ነው‼️ 👉 እነዚህን በዓላቶች (ማክበር) በነሳራና በየሁዳዎች መመሳሰል ነው !!! እነሱ የበዓላት ባልተቤቶች ናቸውና። 👉 ለኛ ደሞ የምናከብራቸው የሆነው ሁለት ዒዶችን እንጂ ሌላ የለንም !!! 👉 እነሱም ፦ "ዒድ አል-አድሓ"ና "ዒድ አል-አፍጥር" ናቸው። ❌ እኛ ሌላ ዒዶችን (በዓላቶችን) ለማክበር ስንል "ቢድዓ" መፍጠር የለብንም !!! ... » (( ሰማሓቱ ሸይክ ኢማም ዐብዱላዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ )) በጣም የሚገርመኝ ነገር ...👇 👉 መረጃ ያልመጣበት መሆኑ አንድ ነገር ሆኖ ሳለ ካፊሮችን መመሳሰልና መፎካከር ካልሆነ ለምን ከ"ሸዋል" ፆም ውጪ የሚፆሙትን እንደሁም አጅር በማስገኘት ወይም በጊዜው በላጭነት ወይም ወንጀልን በማሳበስ ወይም ከረመዳን ፆም ቀጥሎ ባለው ደረጃ ... ከ6ስቱ የሸዋል ፆም የሚበልጡ ሱና ፆሞች አሉና ለምን ዒድ አድርጎ ከመያዝ ተቆጠብን ?!!! መልሱ ግልፅ ነው !!! የእውነት ዲናችንን እንገንዘብ !!! ከስሜት እንውጣ !!! በዕምነታችን አንፈር !!! አላህ ሆይ ቀናውን መንገድ ምራን !!! ወንድም እህቶች ለአላህ ብላቹ "ሼር" አርጉት !!! https://t.me/amr_nahy1 https://t.me/amr_nahy1 https://t.me/amr_nahy1 … ኢስማኤል ወርቁ …
Показать все...
الأمر بالمعروف والنهي عن المنكر

ይህ ቻናል በመልካም ማዘዝንና ከመጥፎ መከልከልን ዓላማው በማድረግ ቁርኣንና ሐዲስን በሰለፎች ግንዛቤ በመመርኮዝ የተለያዩ አስተማሪና ገሳጭ ምክሮች የሚተላለፍበት ነው። አስተያየት ለመስጠት= @esmael9

የአብራሮች "ዒድ"ና ኢስላም... بسم اللــــه الرحمـــن الرحيم. (( " اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ وَلَا تَتَّبِعُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ ۗ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ " )) « ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ፡፡ ከአላህም ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ፡፡ ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ፡፡ » (( " وَاتَّبِعُوا أَحْسَنَ مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ بَغْتَةً وَأَنتُمْ لَا تَشْعُرُونَ " )) « እናንተ የማታውቁ ስትኾኑም ቅጣቱ በድንገት ሳይመጣባችሁ በፊት ከጌታችሁ ወደናንተ የተወረደውን መልካሙን (መጽሐፍ) ተከተሉ፡፡ » 👉 ከነዚህ የተቀደሱ የአላህ ንግግሮች የምንረዳው ከፈጣሪያችን አላህ እንዲሁም ከመልዕክተኛው ዘንድ የመጣውን ብቻ መከተል እንዳለብን ነው። (( ... ما رواه أبو داود في سننه عن أنس رضي الله عنه قال قدم رسول الله صلى الله عليه وسلم المدينة ولهم يومان يلعبون فيهما فقال: "ما هذان اليومان؟ قالوا: كنا نلعب فيهما في الجاهلية ، فقال رسول إن الله قد أبدلكم بهما خيراً منهما يوم الأضحى ويوم الفطر " ... )) 👉 ሱነን ውስጥ አቡ ዳውድ እንደዘገበውና አነስ ቢን ማሊክ እንዳወራው ፦ (( « ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ "መዲና" የሄዱ ጊዜ (ለመዲና) ሰዎች ሁለት የሚጫወቱባቸው የሆነ ዕለቶች (ክብረ-በዓል) ነበራቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉ ፦ « ምንድናቸው እነዚህ ሁለት ዕለቶች ? » እነሱም እንዲህ አሏቸው ፦ « እኛ በጃሂሊያ ጊዜ (በነዚህ ቀናቶች) ውስጥ የምንጫወትበት ነበር። » ረሱልም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ ፦ « አላህ በእርግጥም ከነዚህ ቀናቶች ይልቅ የተሻለን የ"ዒድ አል-አፍጥርና የዒድ አል-አድሓን ቀናቶቾ ቀየረላቹ። » )) 👉 ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው ከነዚህ ሁለት ዒዶች ውጪ ሌላ ቢኖር ኖሮ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለባልደረቦቻቸውና ለህዝባቸው ባሳወቁ እንደነበረ ነበር !!! 👉 ስለዚህ ከዚህ በመነሳት ከነዚህ (2) ዒዶች (በዓላት) ውጪ ሌላ ተጨማሪ "ዒድ" በዓል ማክበር አዲስ ፈጠራ "ቢድዓ" ይሆናል ማለት ነው‼️ 👉 ሌላውም የመልዕክተኛው ንግግር የሚያመላክተው ይህንኑ ነው ፦ (( " وقد قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: "من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد " أخرجه مسلم في صحيحه، " )) (( " በዚህ ጉዳያችን (ዕምነታችን) ውስጥ ከሱ ያልሆነን አዲስ ነገርን የፈጠረና የሰራ የሆነ ሰው ስራው ተመላሽ ይሆንበታል !!! " )) (ሰሒሕ ሙስሊም) ታዲያ ሊሆን የሚገባው እውናታ ይህ ሆኖ ሳለ እኛ በተለይም በዚህ ዘመን ላይ ያለን ሙስሊሞች እጅግ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ ከአላህ በመቀጠልም ከመልዕክተኛው ዘንድ በመጣልን ነገር ከመብቃቃት ይልቅ የተሟላውን እስልምና ጎዶሎ አርጎ ሊያሳይ በሚችል መልኩ አዳዲስ... በደጋግ ቀደምቶቻችን የማይታወቁ ነገሮችን በማምጣትና የዚንጀሮ ቆንጆ ዓይነት በማስመሰል ተፈጥሮአዊ የሆነውን እስልምና ጥላሸት ቀብቶ ማግማማቱን እየተካነው ነው‼️ግን ለምን ??? ባለውለታው እስልምና አይፋረደንም ይሆን ??? ግን ለምን ?! ለእያንዳንዱ ድርጊታችን ከጌታችን አላህ ከወረደልን ድንጋጌ ይልቅ ከሀዲያኖችን ሞዴል ማድረጋችን ??? ውርደትን በገዛ እጃችን በመፈለጋችንም አይደለም ??! 👉 ተጠያቂው ማነው ??? አዎ ! ተጠያቂውማ እምቢተኛና አጥፊው ነው‼️ 👉 እኔ ግን ከተጠያቂነት ለመዳን ስል እቺን ተግሳጽ አድርሼሃለሁና አድርሱልኝ ብያለሁ !!! አደራ !!! አማና !!! ታላቁ " ኢማም ኢብን ባዝ " ከተጠያቂነት ለመዳን ሲሉ የሰጡትን ዕውቀታዊና ጥበበኛ ግሳፄያቸውንና አደራቸውን እንዲህ በማለት አድርሰውም ነበር። ❤ فالذين يحدثون أعيادًا ما أنزل الله بها من سلطان إنما كانوا بهذا في الحقيقة معارضين ومشاقين لما شرعه الله ورسوله، ومتشبهين بأعداء الله من اليهود والنصارى فيما أحدثوا من الأعياد الباطلة التي لا أساس لها في شرعنا، بل غيروا وبدلوا وأحدثوا، فغضب الله عليهم سبحانه وتعالى، فعلينا أن نحذر أن يغضب الله علينا كما غضب عليهم في الإحداث والبدع والمعاصي والمخالفات. ونسأل الله للجميع العافية والسلامة، ولا حول ولا قوة إلا بالله. (دروس و محاضرات) (التعليقات على ندوات الجامع الكبير) الشيخ الإمام ابن باز رحمه الله ❤ « እነዚያ አላህ ከመረጃ ምንም ያላወረደበት የሆነውን "ዒድ " የሚፈጥሩ የሆኑ ሰዎች በትክክልም እነኚህ ሰዎች አላህና መልዕክተኛው ከደነገጉት ድንጋጌ አፈንጋጮችና ሰንጣቂዎች ናቸው‼️እንዲሁም ከአላህ ጠላቶች የሁዳና ነሳራ ጋርም እየተመሳሰሉም ነው !!! 👉 እነሱ በሸሪዓችን መሰረት የሌላቸውን ውድቅ የሆኑ ዒዶችን በማስገኘት (ከካዲያኖች) ጋር ተመሳሰሉ። ቀየሩ ! ለወጡ ! ፈጠሩ‼️ጥራት የተገባውና ከፍ ያለው አላህም ተቆጣባቸው ‼️!!! 👉 (ታዲያ) አላህ በእነሱ ላይ በአዲስ ነገር ፥ በ"ቢድዓ" በወንጀልና በተቃርኖ እንደተቆጣባቸው ሁላ በኛም ላይ እንዳይቆጣብን ዘንዳ ልንጠነቀቅ ይገባል‼️!!! 👉 አላህ ለሁላችንም ጤናንና ሰላም መሆንን እንጠይቀዋለን !!! « በአላህ ቢሆን እንጂ ዘዴ ብልሃትም ይሁን ኃይል የለም !!! » (( ሰማሓቱ ሸይክ ኢማም ዐብዱላዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ )) 👉 ካፊሮች የ2 ወር ፆማቸውን ጨርሰው " ትንሳዔ" ይላሉ። ከዚያም በሳምንቱ ዳግማዊ " ትንሳዔ" ይሉና የሚያረጉትን ያረጋሉ‼️ ለበዓላቸው ህግ ደንብና ስርዓትን የሚያበጅለት የሆነ መለኮታዊ ትዕዛዝ ያልመጣበትና መመሪያ የሌለው ስለሆነ ማንም እንደፈለገውና እንደተመቸው ተነስቶ ደስ ያለውን አፅንቶ ደስ ያላለውን ይሽራል‼️ እነሱ ጋር ...የፈለጉትን "ዲን" አርጎ መያዝ አያስጠይቅምም !!! 👉 ታዲያ እኛጋስ ??? እኛጋማ ጥርጥር የለውም !!! ምናልባት "ዳባ" የምትባለው እንሰሳ ምሳ የገባችበት ጉርጓድ ውስጥ ካልገባው ብሎ እነሱን የተከተላቸው ካልሆነ በስተቀር... ያለድንጋጌና ያለመረጃ አምልኮት የሚባል ነገር እንደሚያስጠይቅ ጠንቅቆ ያውቃል !!!... فعن أبي سعيد الخدري أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: ((لتتبعُنَّ سَنَنَ من كان قبلَكم، شبرًا بشبرٍ، وذراعًا بذراعٍ، حتى لو دخلوا جُحْرَ ضبٍّ تبعتُمُوهم))، قلنا: يا رسولَ اللهِ، اليهودُ والنصارى؟ قال: ((فمَنْ؟)) [البخاري: 7320]. አቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ ረሱል (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አሉ በማለት እንዲህ አለ ፦
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር ከ1816 - 1824 በአልጄሪያ ቆንስላ ተመድቦ የነበረው ትውልደ አሜሪካዊው ዊልያም ሻለር እንዲህ ይላል፡- "በአልጄሪያ ባሳለፍኳቸው ተከታታይ ስምንት ዓመታት የአልጄሪያዊያንን ሙስሊም ሴቶች ቅርፅና መልክ በህይወቴ ተመልክቼ አላውቅም። ኒቃብ ባህላቸው አይደለም በሙስሊም ሴቶች ልብ ላይ የታተመ ሀይማኖታዊ መመርያ ነው" @yesheh_kalidrashid_daewawoch @yesheh_kalidrashid_daewawoch
Показать все...
ሔንሪ መክው የተባለ የክርስትና እምነት ተከታይ ምዕራባዊ ፀሀፊ ስለ ኒቃብ እንዲህ ይለናል፦ Mahi Mahisho "በቢሮዬ ግድግዳ ላይ ሁለት የተሰቀሉ ምስሎች አሉ። አንደኛዋ ኒቃብ የለበሰች የሙስሊም ሴት ፎቶና ከጎኗ ደግሞ እራፊ ጨርቅ ላይዋ ላይ ጣል ያረገች እርቃኗን ለቁንጅና ውድድር የምትሳተፍ አሜሪካዊት። የመጀመሪያዋ ከዓለም ሁሉ ገላዋን የደበቀች ሽፍን ውድ ሴት ሁለተኛዋ ደግሞ ለዓለም ገላዋን ባደባባይ የምታሳይ ርካሽ ሴት! በምዕራቡና በምስራቁ ዓለም የሚደረገው ጦርነት በዋናነት ያነጣጠረው ዐረቦችም ሆኑ ሙስሊሞች ከሀይማኖታቸውና ከመልካም ባህላቸው ርቀው እርቃን እንዲወጡና ኒቃብን በአጭር ቀሚስ እንዲተኩ ነው። ስለሆነም እኔም ኒቃብ በሀይማኖቴ ውስጥ ካለው ቦታ በመነሳት ከሱ እከላከላለሁ። ሴት ልጅ ለባሏ እና ለቤተሰቧ ያላትን ክብር ማሳያ ናት። የነርሱ ብቻ እንደሆነች ማመላከቻ ነው። ውድ ዕቃ ናትና ማንም እንዳሻው ሊያያት አትፈቅድም። እርቃኗን ሆና ለሚሊዮኖች ገላዋን በቴሌቪዥን የምታሳየው የአሜሪካዋ የቁንጅና ንግስት ንብረትነቷ ለሁሉም ነውና የኔ ናት ብሎ የሚከራከር የለም። ሁሉም እንዳሻው ያያታልና" የምዕራቧ ሴት የክብሯን መገለጫ የሆነውን ሐያዋንና ጥብቅናዋን አጥታለችና ምንም የሚስብ ነገር የላትም። ስሜትም ፍቅር አትሰጥም። አስቀድማ ፍቅርን ጨርሳለችና ለፍቅርም የታደለች አይደለችም። በምዕራቡ ዓለም ያለች እንስት የወንዳወድነትን ባህሪ በመላበሷ ሚስትም ሆነ እናት የመሆን ሞራልም ሆነ አቅም የላትም። እንስሳዊ የስሜት ፍላጎትን ከማርካት ውጪ ለፍቅርም ሆነ ልጅን ለማፍራት ምቹ አይደለችም" በርግጥ በራስ ላይ ከመመስከር የበለጠ ሌላ ምስክርነት አያሻም። አላህ ኒቃባችሁ ላይ ያፅናችሁ። @yesheh_kalidrashid_daewawoch @yesheh_kalidrashid_daewawoch
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.