የስንኝ ቋጠሮ
Открыть в Telegram
የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!
Больше2 046
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
2 046
🔜🔜 Inspirational Word
በህይወትህ መለወጥ የማትችለው ነገር ካጋጣመህ አንተ መለወጥ አለብህ ማለት ነው ።
እንደሰው ልጅ በህይወትህ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ትልቅ የለውጥ አቅም መኖሩ ግልፅ ነው ፡፡
ከእነዚህ የለውጥ አቅሞች መካከል ገንዘብ ፣ እውቀት የፖለቲካ ስልጣን ፣ ውበት ወይም ሌላ ነገር ሊሆን ይችላል ፡፡
፣
‼ እነዚህ ህይወትህን አንተ በምትፈልገው መልኩ ለመለወጥ የሚያስችሉ የለውጥ አቅሞች ናቸው ፡፡
ነገር ግን ሁሉንም ነገር መለውጥ ይችላሉ ማለት ግን አይደለም ፡፡
አንተ ካለህ የለውጥ አቅም በላይ ያጋጠመህ ጉዳይ ያለመለወጥ ትልቅ አቅም ሊኖረው ይችላል ፡፡
፣
‼ ስለዚህ እነዚህን የለውጥ አቅሞች ተጠቅመህ መለወጥ የምትችላቸው ብዙ ጉዳዮች የመኖራቸውን ያህል መለወጥ የማትችላቸው ጉዳዮችም የዛኑ ያህል ናቸው ፡፡
እነዚህ ሊለወጡ የማይችሉ የህይወት ጉዳዮችን ለመለወጥ መሞከር ግን ትክክለኛ ለውጥ ላይሆን ይችላል ፡፡
፣
በህይወት ውስጥ ለውጥ አስፈላጊ የሚሆነው በዙሪያችን ያሉ ነገሮችን በመለወጥ ብቻ አይደለም ፡፡
እርግጥ ነው፡ አንዳንዶቹ የምንለውጣቸው ናቸው ፡፡ ሌሎቹ ግን እኛ ራሳችንን የምንለውጥላቸው ናቸው ፡፡
የሞቱ እናትህን ወደህይወት መለወጥ አትችልም ።
የምትችለው ወደህይወት እንደማይለወጡ መቀበል በሚያስችል መልኩ ራስህን መለወጥ ነው ።
‼ ሁሉም ነገር ሊለወጥ አይችልም ፡፡ ለውጥ ማለት ሁሉንም ነገር መለወጥ ብቻ አይደለም ፡፡
መለወጥ የሌለባቸው የህይወት ጉዳዮች መኖራቸውን ተገንዝቦ ራስንም መለወጥ የለውጥ አካል ነው ፡፡
ስለዚህ በህይወትህ መለወጥ የማትችለው ነገር ካጋጣመህ አንተ ራስህን የምትለውጥለት የህይወት ጉዳይ ነው ፡፡
2 046
ከበረት ወደ በረት
****
ነገስታትን ትቶ ጠቢባንን ትቶ
ሀያላንን ትቶ ምሁራኑን ትቶ
ጤነኞቹን ትቶ ሀብታሞቹን ትቶ
የነፍሴን መባከን መቅበዝበዟን አይቶ
በእረኝነቱ ስር ሊያወጣኝ ሊያገባኝ
በበረት ተወልዶ ከበረቱ አስገባኝ
#ሄኖክ አሸብር
2 046
የሴት ልጅ"
የሴት ልጅ ይለኛል ያዋረደኝ መስሎት
ስድብ እና ሙገሳ መለየት ተስኖት
አው የሴት ልጅ ነኝ ያውም የጀግናዋ
ጉንበስ ቀና ብላ ለልጅዋ ኗሪዋ
ዘጠኝ ወር ሳልከፍል በሆድዋ ተኝቼ
በጀርባዋ አዝላኝ እሰክሄድ በእግሮቼ
ተደፍታ ስታነድ ምግቡን ለማብሰል
እንጀራ ስትጋግር ፊትዋ መስሎ ከሰል
ሳጠፋ ገስፃ እንዳልኩራ መክራ
በርታ እያለችኝ ሁሌም እንዳልፈራ
አይዞህ አልከፋም ሴት ያሳደገኝ ነኝ
ስድብ ከመሰለህ ደጋግመህ ስደበኝ
አልቀየምህም በስምዋ ስትጠራኝ
እውነቱን ልንገርህ አዎ የሴት ልጅ ነኝ
"መታሰቢያነቱ እናቱን ለሚወድ በሙሉ።"
ሎሬት ፀጋዬ ገ / መድህን
#like & #share
@Roviben @Roviben
