cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Nolawi ኖላዊ ኄር

ዘየአምን ለአማኑኤል በስሙ ፣ ኅቱም በማኅተመ ደሙ ፣ ውኩል በጸሎተ ማርያም እሙ ፣ ወለቅዱሳን ተላዌ ሃይማኖቶሙ ። ይህ ቻናል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነወ ። #ለሃሳብ ለአስተያየት 👉 @Nolawiher1 Facebook :- https://www.facebook.com/estifanos.dejene.94

Больше
Рекламные посты
11 659
Подписчики
+11924 часа
+677 дней
+1430 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከቅዱሳን ባሕታውያ ጋርበአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡-ከዕለታት አንድ ቀን በሀገረ ስብከቴ ሥር በነበሩ በሜዲትራኒያን ባሕር በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ምእመናንን ለመጎብኘት አሰብሁ፡፡ ከእኔ ጋር ቀሳውስትንና ዲያቆናትን አስከትዬ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዝሁ፡፡ በደሴቱ ውስጥ ስንዘዋወር የሰው ዱካ ብንመለከትም ምንም ሰው ማየት አልቻልንም ነበር፡፡ በአሸዋው ላይ ታትሞ የነበረውን የሰው ዱካ ተከትለን ስንጓዝ ካልተፈለፈሉ ዐለቶች የተሠራ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ዋሻ ላይ ደረስን ፡፡ ዋሻው በርም ሆነ መስኮት የለውም፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ ልክ እንደ ሰባቱ ደማቅ ከዋክብት እጅግ በጣም አንጸባራቂ ብርሃን ቆመው ከሚጸልዩ ሰባት አባቶች ዘንድ ሲወጣ ተመለከትን፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ለመጸለይ ባለንበት ቆምን። አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ እኛ ዞሩና በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ። በመቀጠልም ሰላምታ ሰጡን፡፡ እኔ ዮሐንስም 'እኔ አባታችሁና ፓትርያርካችሁ ዮሐንስ ነኝ' አልኳቸው፡፡ ቅዱሳኑ እንደገና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በፊቴ ሰገዱ እና እኔን ደካማውን እንዲህ አሉኝ፡- "የምንወደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትባርከንና እኛም አንተን በማየት እንድንበረታ ወደዚህ አመጣህ" አሉ። እኔም 'እባካችሁ ታሪካችሁን ንገሩኝ'' አልኋቸው ፡፡ ሰባቱ አባቶችም “ከብዙ ዓመታት በፊት ሰባታችንም ከቍስጥንጥንያ ወጥተን በአንድነት ተሰባስበን ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና በአምልኮ ብቻ ለማሳለፍ ወደዚህ ደሴት መጣን፡፡ ከዚህ ደሴት በደረስንበት ዕለት ከባሕሩ ከሚመጣው አስቸጋሪ ነፋስ ራሳችንን ለመከላከል ዋሻዎችን ለመገንባት ዐለቶችን ሰበሰብን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ ይህን ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጀመርን። በዐለቶች መካከል ከሚበቅለው ሣር እንበላለን፤ ውኃም ከባሕሩ እንጠጣለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን የከበቡትን እነዚህን የአሸዋ ክምሮች ለማስወገድ ፈልገን ነበር፤ ግን አእምሯችንና አሳባችን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስለተያዘ ጊዜ አጣን" በማለት ታሪካቸውን ነገሩኝ ። እኔም ''መንፈሳዊ አባታችሁ የት ነው?' ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ ይህን ጥያቄ ከመጠየቄ ወዲያውኑ አንድ ሽማግሌ በትሩን ተደግፎ ወደ እኔ ቀረብ አለና "እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ'' አለኝ፡፡ አረጋዊው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ራቁቱን ነበረና “ሰውነትህን የምትሸፍንበት ትንሽ ልብስ ትፈልጋለህ?'' ስለው እሱም ''ጌታ ከክረምቱ ቅዝቃዜ፣ ከበጋው ሙቀት ይከላከልልናል፤ ይጠብቀናልም'' በማለት መለሰልኝ፡፡ “ምግብ ያስፈልጋችኋል?" ብዬ ስጠይቀው እርሱም "የሚበቃንን ያህል ከእነዚህ ዕፅዋት እንመገባለን ከዓለም የሆነ ምንም ነገር አያስፈልገንም'' በማለት መለሰልኝ፡፡ እኔም ''አባቶቼ እባካችሁ ለእኔ እና ስለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ጸልዩ" አልሁት። የእነዚያን ቅዱሳን ባሕታውያን አባቶች በረከት ከተቀበልን በኋላ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ምሥጋና የሚገባውን የምንወደውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ወደ መጣንበት ተመለስን" ይለናል ቅዱሱ አባታችን ዮሐንስ አፈ ወርቅ ። የሰላም ሌሊት ይሁንላችሁ ! ግንቦት 18 ምሽት 2016 ዓ.ም
Показать все...
57🙏 17👍 14🥰 5👏 3😍 3 2
"ቃለ እግዚአብሔር ተንሥአ ወሥጋሁኒ ኢማሰነ፤ የእግዚአብሔር ቃል ተነሣ ሥጋውም አልጠፋም (መበስበስን አላየም)" ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ - ፪፻፲፮ ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቷል በእውነት ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቷል ! ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን መካከል ተለይቶ በመነሳቱ ፤ ሰይጣን ታሰረ እኛ የአዳም ልጆች ነፃ ወጣን እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን አደረሳችሁ። "ቃል" መጀመሪያ በሌለው መጀመሪያ ከጥንት ጀምሮ ገና ሰማይና ምድር ሳይፈጠሩ፤ ቀላያት ገና ባልነበሩበት ደግሞም ባልተደነገጉበት ፤የውሃ ምንጮች ሳይፈልቁ፣ ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረ፤ እግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ በእርሱ የተገኙ ከሆነው ሁሉ እንኳን አንዳች ያለ እርሱ ያልሆኑ የሁሉ ጌታ፤ የሁሉ አስገኝ ፤አምጻኤ ዓለማት፤ መጋቤ ፍጥረታት የአብና የመንፈስ ቅዱስ ቃል፤ ክርስቶስ ኢየሱስ ለአባቶቻችን ስለ ገባው ኪዳን እራርቶ አስቦ ቃል ሥጋ ሆነ ፤ ሕገ ሰብእን ጠብቆ በመካከላችን ተመላለሰ በምኞታችን ተስበን በምርጫችን ብንጠፋ ወደ ገዛ ሐሳባችን አዘንብለን በነፋስ እንደሚንቀዋለል ቅጠል ረግፈን ብንፍገመገምም ከዚህ መከራ ሊታደገንና ሊያድነን ከእስራታችን ሊፈታን ከአቤል ጀምሮ በእኛ ላይ ሠልጥኖ በግፍ ሲገዛን ከኖረው ሞት አርነት ሊያወጣን የሕይወት አስገኝ፥ ሕይወታችን ክርስቶስ ስለ መተላለፋችን ቆስሎ ፤ስለ በደላችን ደቅቆ ኃጢአት ሳይኖርበት ወደ ወረድንበት መንደር ወደር በሌለው ፍቅሩ ወርዶ ፈለገን ከቤተልሔም ግርግም እስከ ቀራንዮ ለቤዛነት ያለ ቅሬታ የዕዳችንን ዋጋ ከፈለ ። ተወዳጆች ሆይ ! መድኃኒታችን ክርስቶስ በእኛ ወገን የነበረውን ነቀፌታ መናቅና መሰደብ መነወርን ተሸክሞ ገንዘቡ የሆነውን ክብር አለበሰን ስለ እኛ ከኃጢአት በቀር ሁሉን ሆነ እስከ ሞት ድረስ እኛ በቁጣና በንቀት እየጎተትነው እርሱ ግን በፍቅር ተከተለን ሞት የማይገባው ስለ እኛ ሞተ ተሸናፊ መስሎ በሞት መንደር ለሦስት መዓልትና ለሦስት ሌሊት አድሮ የሞትን ኃይል ሽሮ ፤ የግዛቱንም ከተማ መዝብሮ፤ በቀንበሩ ሥር የነበሩትን ነፍሳት ነፃ አውጥቶ፤ በአዋረዳቸው ፊት አዋርዶ ፤ አሰቅቆት ኃይል አሳጥቶት በታላቅ ግርማ ተነሣ። በሆነ ጊዜ እንድናምነው ከመሆኑ አስቀድሞ እንዳለው ነፍሴን ስለ ወዳጆቼ ላኖራትም ላነሣትም ሥልጣን አለኝ ያለው ክርስቶስ በእግዚአብሔርነት ገንዘቡ የነሃሱን ደጆች ሰብሮ፤ የብረቱን መወርወሪያ ቆርጦ ፤ ሲኦልን ድል ነስቶ በክብር በኃይል በሥልጣን ተነሣ በትንሣኤውም ጨለማችንን አበራ፤ እስራታችንን ፈትቶ ነፃነታችንን አወጀ። የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ! "ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር " ይህች ዕለት እግዚአብሔር ሥራውን የሠራበት ዕለት ናትና "ንትፈሣህ ወንትሐሠይ ባቲ " መዝ ፻፲፯፥፳፬ እንዳለው በዚህች ዕለት እንደሰት በእርሷም ፍፁም ደስ ይበለን ሐሴት እናድርግ ለእኛ ላመንነው ሁሉ የእረፍታችን የሰላማችን ቀን ጨለማ ተወግዶ የብርሃን ጎርፍ የጎረፈበት በመሆኑ ክርስቶስ በምስኪኗ መንደራችን በጎስቁልናችን ከተማ ተገልጾ ታሪካችንን እንደቀየረ ሁሉ በድኅነት በመከራ በሥጋ እስራት ላሉት መጽናናት ይሆን ዘንድ እንድንጎበኛቸው በዙሪያችን ያሉ አቅመ ደካሞችን እንድንመለከት የተጠቁትን አርነት እንድናወጣ በተወደደችው በእግዚአብሔር ቀን ቸርነትን እንድናሳይ በክርስቶስ ፍቅር አደራችን የጸና ነው ። በትንሣኤው ትንሣኤችን የተረጋገጠበት እኛም ከእርሱ ጋር በልቡና ትንሣኤ አብረን ተነስተን የምንኖርበት ዘመን ይሁንልን ለሀገራችንም ትንሣኤ ይሁንላት ። መልካም የበረከት በዓል በያላችሁበት ይሁንላችሁ ። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ ! ብፁዕ አቡነ ሄኖክ
Показать все...
34👍 17🙏 7👏 1🕊 1😍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
አቅም ስጠኝ ጌታዬ ሆይ ሳላውቅ ብዙ ጊዜ እወድቃለሁ ። ፍጹም ነኝ ብዬ ስለማስብ መልካሙን ለማድረግ ጥረት አላደርግም ። በዚህም ፍቅርህን የማልረዳ ሆዳም ሆኛለሁ ። እባክህ እኔን ስለማቀር መቁሰልህን አስብ ዘንድ አቅም ስጠኝ ። እኔን ስለማዳን መድማትህን አውቅልህ ዘንድ አቅም ስጠኝ ። ጌታዬ ሆይ እኔ ከአንተ ብዙ እሻለሁ አንተ ከእኔ ምን ትፈልግ ይሆን ? እባክህ ሀሳብህን አውቅልህ ዘንድ አቅም ስጠኝ ። ለእኔ የሆንከውን አውቅ ዘንድ አቅም ስጠኝ ። ለእኔ ያለህን ጥልቅ ፍላጎት አውቅልህ ዘንድ አቅም ስጠኝ ። አንተ ሕይወቴን ካስተካከልከው ህልውናዬ ጤናማ ይሆናል ። ንጉሤ ሆይ ስለ እኔ ኃጢአት በመስቀል መዋልህን እውቅ ዘንድ አቅም ስጠኝ ። ልዑል ሆይ አንተን በማመን እንደ ፈቃድህ እኖር ዘንድ አቅም ስጠኝ ። የሆንክልኝን አስብ ዘንድ አቅም ስጠኝ። ጌታዬ ሆይ የዚህ ዓለም ኑሮ እንድ ምንም ያልፋል። የማያልፈውንና የወዲያኛውን ዓለም ማሰብ እችል ዘንድ አቅም ስጠኝ ። እኔ ለራሴ ዋስ መሆን አልችልም በዚህም ዓለም በዛኛውም ዓለም ዋሴ አንተ ነህና እባክህ አከብርህ ዘንድ አቅም ስጠኝ። መልሕቄ ክርስቶስ ሆይ  አባቴ ብዬ እወድህ ዘንድ አቅም ስጠኝ። አዳኜ ብዬ እታመንብህ ዘንድ አቅም ስጠኝ። ጌታዬ ብዬ እገዛልህ ዘንድ አቅም ስጠኝ። እረኛዬ ብዬ እከተልህ ዘንድ አቅም ስጠኝ። አዳኜ ብዬ እታመንልህ ዘንድ አቅም ሰጠኝ ። ለስምህ ክብር ይሁን ! ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ ሚያዝያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም
Показать все...
🙏 50 23👍 7😭 7 3🥰 2❤‍🔥 1🕊 1
"በሠላሳ ብር በርካሽ ዋጋ የተሸጠው እርሱ ዓለምን በውድ ዋጋ ገዛ ፤ ይኸውም ክቡር ደሙ ነው ።" (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ)
Показать все...
79👍 9🙏 8🥰 2🕊 2💯 2😍 1🤗 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ንጉሰ ሰላም ጨርሰህ የምትጀምር ፣ ቃለ ሕይወትን የምትሰጥ የቃል መፍለቂያ ፣ ንጉሰ ሰላም ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አመሰግንሃለሁ ። ደብረዘይትና ቤተ ፋጌ እንደሚቀራረቡ ልቤን ወደ ቃላህ አቅርብልኝ ። ከመንደር ውስጥ የምትገለገልባቸውን አህያና ውርጫይቱን እንዳገኘ የልቤን መንደር ፈትሸውና አረሙን አቃጥልልኝ። አህያና ውርጫይቱ ላይ መቀመጥህ ተአምር ነው ደንቆኛል ! እኩል የሆኑ አህዮች ላይ መቀመጥ በራሱ ከባድ ነው ፤ አንተ ግን ውርጫይቱ ላይ ተቀመጥከ ። አንዷ ትንሽ ናት  አንዷ ከፍ ያለች ናት ። አንዷ ልምጥ ነች አንዷ ደልዳላ ነች አንተ ግን በተአምራት ሁለቱም  ላይ ተቀመጥክባቸው። ምግባሬ ትንሽ ትዕቢቴ ብዙ ፣ ለትዕዛዝህ ልምጥ ለኃጢአት ብርቱ የሆንኩ ነኝ ። ሚገድብህ ድንበር የሌለ ንጉሰ ሰላም ክርስቶስ ሆይ የማልመቸውን ልጅህን ስራኝ ። በእስራኤላውያን ልማድ ሀገር ላይ ጦርነት ሲኖር ንጉሱ በፈረስ ላይ ጦር ይዞ በመንደር ውስጥ ይመላለሳል። ሀገሪቱ ሰላም ከሆነች በአህያ ላይ ተቀምጦ መንደሩን በሙሉ እንደሚመላለሳል አንተ ንጉሰ ሰላም ነህና ውርጫይቱ ላይ ተቀምጠህ ወደ ከተማው ገባህ፤ ጌታዬ ሆይ ሀገሬ ኢትዮጵያ አትገባም ወይ ? ወደ ታወከው ልቤስ አትገባም ወይ? የኔ ጌታ ቀርበህ ለከተማይቱ አዘንክ አይደል! ኢትዮጵያን ስትቀርባት ስንቴ አዝነህ ይሆን? የሰላም ንጉሷን አንተን ገፍታ መሳሪያን ስትደገፍ ለኢትዮጵያ አታዝንም ወይ ? አንተን አምላክ ብሎ ሌላ ለሚሚመኘው ልቤስ ስንቴ አዝነህ ይሆን ? ንጉሰ ሰላመቸውን ትተው የዓለማዊያንን ዕቅድ ለሚያራምዱ አገልጋዮች እንዴት አዝነህ ይሆን? ብቻ ሆሳዕና በአርያም ለአንተ ይሁን።ስባዝን በሚሰበስበኝ ፍቅርህ ፣ ስደክም በሚያበረታኝ ድምፅህ ፣ ስታሰር በሚፈታኝ ቃልህ ለዘለዓለሙ አሜን ! ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ ሚያዚያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም.
Показать все...
🙏 42 22👍 13🥰 4🕊 4🔥 2🫡 2 1❤‍🔥 1🤗 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
አስተምረኝ ጸዳልህ ግሩም፣ ክብርህ ትልቅ፣ ፍቅርህ ድንቅ የሆነ ፤ ሙት ለሆንኩት ሕይወትን የዘራህ ጌታዬ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አመሰግናለሁ። ፍቅርህ መሸሻዬ፣ ክንድህ አቅሜ ፣እቅፍህ መሸሸጊያዬ ሆኖልኝ የማይታለፈውን አልፍኩ። የማይጀመረውን ፈጸምኩ። የማይወጣውን ወጣሁ ተመስገንልኝ። ታላቁን ሽንፈቴን በድል የለወጥክህ ሹመት አክሊሌ አንተ ነህ። ዘለዓለማዊ የምትሆን አምላኬ ሆይ እውቀት ያልኩት መና ሆኖ ፣ጥበብ ያልኩት ከንቱ ሆኖ ልቤ ቆስሎብኛል። ዘለዓለምን አስተምረህ ዘመኔን አለምልም። የፈጸምኩ መስሎኝ ስጀምር፣ የጸናው ምስልኝ ስናወጥ  እንድፈፅም አድርገህ አስተምረኝ እንድፀና አድርገህ አበርታኝ። ጌታዬ ሆይ እንደ ልብህ አልሆንኩምና እንደ ልቤ እየሆንኩ ነው። እንደ ሃሳብህ አልሆንኩምና እንደ ሀሳቤ እየፈረጅኩ ነው። እንደ ፍቃድ አልሆንኩምና እንደ ፍቃዴ አየተጓዝኩ ነው። እባክህ ከዚህ ጥም ቃጠሎ በቃልህ ትምህርት አርካኝ።በሆሳዕና አጅቤህ በቀራንዬ የማልሸሸው አንተ ስታስምረኝ ነው ።  ዕለት ዕለት በኃጢአት አንተን ከመስቀል የምድነው እንተ ስታስተምረኝ ነው። እንደ ኒቆዲሞስ አንተን ከመስቀል ላይ ለማውረድ የምታደለው አንተ ስታስተምረኝ ነው ። በቃልህ ብርሃን ጨለማ ኑሮዬን አብራው።ቅጥ አልባ ውድቀቴን አርመው። ለዝና የሚያደለው ልቤ ለፍቅርህ  ይደንግጥ። አስተምረህ ልቤን በፍቅርህ ማርከው። እየበደልኩ በጥፋቴ እንዳልኖር አስተምረኝ።በሰጠኸኝ ቀን ውስጥ ቀኔን የምኖር ብሆንም ፣ ቸርነትህ በዝቶ በነውርና በአመጽ ብዳክርም አንተ ብቻ አስምረኝ ከእንግዲህ የዓለም አልሆንም። ዘለዓለማዊው ቃልህ ዘለዓለሜ ነው። የዛሬ ትህምርትህ የዓመት ቀለቤ ነውና እባክህ እንደ ኒቆዲሞስ እኔንም አስተምረኝ። በማላፍርበት ደግነትህ ለዘለዓለሙ አሜን ። ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ ሚያዝያ 16ቀን 2016 ዓ.ም.
Показать все...
49👍 11🙏 11🥰 3😍 2 1🔥 1
አቤቱ አንተን የሚመስል ማነው ? “መኑ ይመስለከ፡ እምነ አማልክት እግዚኦ፡ አንተ ውእቱ ዘትገብር መንክረ፡ አርአይኮሙ ለሕዝብከ ኀይለከ፡ ወአድኀንኮሙ ለሕዝብከ በመዝራዕትከ ሖርከ ውስተ ሲኦል፡ ወአዕረገ ጼዋ፡ እምህየ ወጸጎከነ ምዕረ ዳግመ ግዕዛነ እስመ መጻእከ ወአድኀከነ፡፡ በእንተ ዝንቱ ንሴብሐከ፡ ወንጸርሕ ኀቤከ እንዘ ንብል፡ ቡሩክ አንተ እግዚኦ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እስመ መጻእከ ወአድኀንከነ፡፡” (ሥርዓተ ቅዳሴ) አቤቱ ፈጣሪያችን፡ መድኀኒታችን እግዚአብሔር ሆይ፤ “አማልክት” ከተባሉ፡ አማልክት ከሆኑባቸው ከእነ ዜውስ፡ ከእነ አርጤምስ አንተን የሚያህል፡ አንተን የሚተካከል ማነው? አማልክት ከሆኑብን ከአምሮት፤ ከስስት አንተን አንተን የሚተካከል እውነተኛውን ደስታ መስጠት የሚችል ማነው? እኒህ ሁሉ አማልክት ሕዝብህን ከክፉው እና ከክፋት ማዳን አይችሉምና፤ ሕዝብህን ከክፉ በማዳንም ድንቅን አላደረጉምና፤ እንዲያውም ሕዝብህን ወደ ሞት ይወስዳሉና፡፡ አንተ ግን በከበረች ኀይልህ፡ እኛን ልታከብር፡ እኛ ከገባንበት ደይን (ሲኦል) ለማውጣት፡ ወደ ሲኦል ሄድኽ፡፡ እኛን ለመፈለግ በፍቅርህ ብዛት ወደ ምድር መጣህ፡፡ ፍቅርህ እውነተኛ ናትና “ወደ ምድር መጣሁላቸው፤ እሱ ይብቃቸው” ብለህ ፍቅርህን ሳትቆጥር፤ በደላችን ከምድር በታች (ሲኦል) ወስዳናለችና፡ እዚያም ሄድኽ፡፡ ክቡር እና ልዑል ለሆነ አባትህ ምርኮን ማረክህ፤ እኛን ወደ እርሱ አቀረብከን፡፡ እኛን ከከፋችው ቦታ አወጣኸን፡፡ ለዘለዓለም የሚሆን ነጻነትን (ጸጋን) ዳግመኛ ሰጠኸን፡፡ ጥንት የሰጠኸንን ነጻነት አንተን ላለመውደድ፤ ሕግህንም ላለማድረግ በጥመት ተጠቅመንበት ነበርና፡፡ አሁን ግን ወደን፡ ፈቅደን ለአንተ እንድንገዛ ከሰይጣን ባርነት፤ ያንተን ወደምትመስል ነጻነት መለስከን፡፡ ታዲያ እኛ ምን ብለን፡ ምን አድርገን እንመልስልህ? “የቡሩክ አብ ልጁ፡ ቡሩክ ወልድ” ብለን እናመስግንህ እንጂ፡፡ “እኛን ክፉ ከተባለው ሁሉ ጠብቀን” ብለን እንለምንህ እንጂ፡፡ “እኛን ከራሳችንም ጠብቀን፤ አድነን” ብለን እንለምንህ እንጂ፡፡ አንተ መጥተህ (ሰው ሆነህ) አድነኸናልና፡፡ አሁንም በመምህራን ትምህርት፤ በካህናት መሥዋዕት፤ በምዕመናን ጸሎት መጥተህ ታድነናለኽና ፡፡ አቤቱ ከአማልክት አንተን የሚመስል ማነው? አቤቱ ማረን ! https://t.me/Nolawiiher
Показать все...
Nolawi ኖላዊ ኄር

ዘየአምን ለአማኑኤል በስሙ ፣ ኅቱም በማኅተመ ደሙ ፣ ውኩል በጸሎተ ማርያም እሙ ፣ ወለቅዱሳን ተላዌ ሃይማኖቶሙ ። ይህ ቻናል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነወ ። #ለሃሳብ ለአስተያየት 👉 @Nolawiher1 Facebook :-

https://www.facebook.com/estifanos.dejene.94

👍 20 15🥰 4🙏 4🕊 3🤗 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የክርስትና ፍሬ ከአንደበታቸው ይነጥባል ፣ ኦርቶዶክዊነት በትምህርታቸው ጎልቶ ይነበባል ። ኢየሱስ ክርስቶስ በሕይወታቸው ልቆ ይታያል ። በፁዕ አቡነ ማር ማሪን ክርስቶስ ይዳብስልን ።
Показать все...
🙏 136 33😢 6👍 3👎 3🥰 3😡 3🕊 2🤗 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ለምጽአትህ ፍቅር ከልብህ የሚያበራ ፣ ምሕረት ከአንደበት የሚነጥብ ፣ ርኅራኄ የስብከትህ ርዕስ፣ ቸርነትህ ድንበር አልባ የሆነ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሆይ አመሰግንሃለሁ ። አምላኬ ሆይ ግፍ በሰፈነበት አመጻም ጌጥ በሆነበት በዚህ መሥፈርት በሌለው ዘመን ማኩረፊያዬ ምጽአትህ ነው ። የሞተ ሰው ዓለም ከንቱ መሆኗን ያስተምር ይሆናል ። የአንተ ዳግም መምጣት ግን ሰማይና ምድርን ይጠቀልላል ። ዓለም በካህዲዎች  ባለቤት አልባ ስትሆን አንተ ግን ወዳልተለየሃት ዓለም ትመጣለህ ። በዚህ ረግረግ ዘመን የሚያሰምጡ ክፋቶች፣ ነውሮች፣ አመጻዎች መንሰራፋታቸው ቢያስፈሩኝም ምጽአትህን ሳስብ ግን ልቤ ያርፋል። የመምጣትህ ብሥራት ዜና የኑሮዬ ብርታት ነውና ተመስገን። አንተን እምቢ ያሉ ጉዳዮች ልክ እንደጽድቅ አደባባዩን አጣበዋልና እባክህ ናልን። ሙሉ ድኅነቴ  ምጽአትህ ነው ። ፍቅርን እቢ ያለው ልቤ፣ መውደድን ያጎደለው አክብሮቴ፣ የወገብ ስብከት ያጠቃው ትሕትናዬ በምጽአትህ ድምፅ ስፍራ ይያዝ። በምትፈርድብኝ ነውር ሳይሆን በምትፈርድልኝ ምግባር እንዳጌጥ፤ ከዚህ ዓለም ወረት ክብርህ ይጋርደኝ። መድረኩን የያዙ ሀሰተኞችን  ከመድረኩ ከኮበለሉ እውነተኞ ለሚለየው ለምጽአትህ ሰላምታ ይገባል። የምስክርነት ልክ ሳይሆን የምግባርን ልክ ለሚያጣራው ምጽአትህ ስላምታ ይገባል። በምድር የተራቆቱ ለሚያጌጡበት በምድር የበለጸጉ ለሚሟሽሹበት ምጽአትህ ሰላምታ ይገባል። ወደ ላይ ያዳጠው ለሚዋረድበት ወደታች ያዳጠውም ለሚገመገምበት ምጽአትህ ሰላምታ ይገባል።የስብከትን ርዕስ ሳይሆን የክርስትናን ፍሬ ለሚያበጥረው ምጽአትህ ሰላም እላለሁ። በዛች ዕለት ፈርደህልኝ እንዳርፍ እንጂ ፈርደህብኝ እንዳልወድቅ በመምጣትህ ተስፋ እማጸንሃለሁ ። በማለፍርበት ደግነትህ ለዘለዓለሙ አሜን ! ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ መጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም
Показать все...
55👍 12🙏 10🥰 5🕊 3 2🤗 2🫡 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
አቅም ስጠኝ የንፍሴ ብርሃን ፣ ታላቁ ንጉሥ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ አመሰግንሃለሁ ። ተስፋዬ ሆነህ መርተኸኛልና ፣  አባቴ ሆነህ አቅፈኸኛልና ፣ ወዳጄ ሆነህ ደግፈኸኛልና ፣ ጉልበቴ ሆነህ አጽንተኸኛልና ፣ ምግቤ ሆነህ አጥገበኸኛልና ፣ መጠጤ ሆነህ አርክተኸኛልና ፣ መድህኔ ሆነህ አኖረኸኛልና ልቤ ያመሰግንሃል ። ጌታዬ ሆይ ሳላውቅ ብዙ ጊዜ እወድቃለሁ ። ፍጹም ነኝ ብዬ ስለማስብ መልካሙን ለማድረግ ጥረት አላደርግም ። በዚህም ፍቅርህን የማልረዳ ሆዳም ሆኛለሁ ። እባክህ እኔን ስለማቀር መቁሰልህን አስብ ዘንድ አቅም ስጠኝ ። ጌታዬ ሆይ እኔ ከአንተ ብዙ እሻለሁ አንተ ከእኔ ምን ትፈልግ ይሆን ? እባክህ ሀሳብህን አውቅልህ ዘንድ አቅም ስጠኝ ። ለእኔ ያለህን ጥልቅ ፍላጎት አውቅልህ ዘንድ አቅም ስጠኝ ። አንተ ሕይወቴን ካስተካከልከው ህልውናዬ ጤናማ ይሆናል ። ብርታቴ ሆይ የውጭውን ጠላት ስከላከል የውስጡ በልቶ እንዳይጨርሰኝ አቅም ስጠኝ ። ልዑል ሆይ አንተን በማመን እንደ ፈቃድህ እኖር ዘንድ አቅም ስጠኝ። በዚህ ዓለም ላይ ያለኝ ቆይታ እንደ ፀሐይ ዕድሜ አጭር ነውና እባክህ ከእቅፍህ እንዳልኮበልል አቅም ስጠኝ። ጌታዬ ሆይ የዚህ ዓለም ኑሮ እንድ ምንም ያልፋል። የማያልፈውንና የወዲያኛውን ዓለም ማሰብ እችል ዘንድ አቅም ስጠኝ ። እኔ ለራሴ ዋስ መሆን አልችልም በዚህም ዓለም በዛኛውም ዓለም ዋሴ አንተ ነህና እባክህ አከብርህ ዘንድ አቅም ስጠኝ። መልሕቄ ክርስቶስ ሆይ  አባቴ ብዬ እወድህ ዘንድ አቅም ስጠኝ። አዳኜ ብዬ እታመንብህ ዘንድ አቅም ስጠኝ። ጌታዬ ብዬ እገዛልህ ዘንድ አቅም ስጠኝ። እረኛዬ ብዬ እከተልህ ዘንድ አቅም ስጠኝ። አንተ መተኪያ የሌላህ የማይቀይሩህ ልዩ የሆንክ እውነተኛ ሰላም ነህ። በማላፍርበት ደግነትህ ለዘለዓለሙ አሜን! ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም
Показать все...
59👍 18🙏 13🥰 3🕊 3 1😁 1