cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

አጫጭር ወጎች

Let us be family @imvsp and read and share what we have..

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
282
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ምርመራ (በእውቀቱ ስዩም) በቀደምት ቴክሳስ ከተማ የበረዶ ውሽንፍር ጥሎ የከተማው መብራት ተቁዋረጠ፤ በማግስቱ የከተማው አስተዳዳሪ ደውሎልኝ ለከተማው ህዝብ ልምድ እንዳካፍል ጋበዘኝ፤ “ ያለመብራት የመኖር ጥበብ “ እሚል ጥናታዊ ፅሁፍ አዘጋጀሁና ናሙናውን ላክሁለት፤ በጣም ተደስቶ መጠኑን እዚህ ገፅ ላይ የማልገልፀውን ቀብድ ላከልኝ ፤ በህይወቴ ለመጀመርያ ጊዜ የኢትዮጵያ መብራት ሃይል ውለታ እንደሰራልኝ ገባኝ ፤ ጭራሽ ቴክሶች፥ ፅሁፍህን ከማቅረብህ በፊት ቢልቦርድ ላይ ልናወጣህ እንፈልጋለንና ፎቶ ላክ አሉኝ፤ ፓስፖርት ሳይዝ ላክሁላቸው፤ ጊዜው ደርሶ ነድቼ ሄድኩ፤ ከተማው በር ላይ የኾቪድ መርማሪ ግብረሃይል ተቀበለኝ፤ “ከየት ነህ?” አለኝ ዶክተሩ “ከኢትዮጵያ “ አልሁት’ “ የጠራኸው አገር ከደቡብ አፍሪካ ምን ያህል ይርቃል? ” “ እረ ጎረቤት ነን ፤ እሳት እንጫጫራለን” “ እዚህ ስራህ ምንድነው?” አለችኝ ነርሲቱ፤ “ ቻተም የተባለ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እሰራለሁ” በማለት በደፈናው ላልፍ ስል “ የስራ መደብህ ?’ ብላ አፋጠጠችኝ፤ ፤“ የዩንበርሲቲውን ማህበረሰብ በየአቅጣጫው አሰማራለሁ” “ ኦ! የዩንቨርሲቲው አስተዳዳሪ ነህ?” “ በምን እድሌ! የካምፓሱ አውቶብስ ሹፌር ነኝ” ወድያው ዶክተሩ የትኩሳት መለኪያ አነጣጠረብኝ ፤ “በምን መንገድ?” “ የሆነ ምግብ ስጡኝና የምግቡ ጣእም ከጠፋብኝ ተይዣለሁ ማለት ነው” “ እሺ ምን ይምጣልህ? ” “ እኔ ነኝ ያለ የጣልያን ቲማቲም ስልስ ይምጣልኝ ፥ በላዩ ላይ የህንድ ቂጣ ጣል አድርጉበት ! የተጠበሰ የቬትናም አሳ ከተገኘ እሰየው ነው ! ካልተገኘ ሰለሞን ፥ ማለቴ ሳልመን ጥበሱልኝ ! ደረቅ ይበል ታድያ! በቀኝ ጎኑ አቮካዶ ሳንዱች ፥ በግራ ጎኑ የበቆሎ እሸት ቅቅል ሻጥ አድርጉበት ፥ ድንች ዝልዝሉ አያስቸኩልም፥ ከላዛኛው ቀጥሎ ሊመጣ ይችላል፤’” ነርሲቱ አድምጣኝ ስታበቃ ትንሽ ተካክዛ እንዲህ አለች “ አሁን ከተናገርከው ተነስተን hyperphagia የሚል በሽታ እንዳለብህ መገመት ችለናል፤ የዚህ በሽታ ዋና ምልክት ጅብ የሚያስንቅ የምግብ ፍላጎት ነው ! ለማንኛውም ለጊዜው ጣእም መለየት አለመለየትህን ቼክ ለማድረግ በጀታችን የሚፈቅደው ይሄንን ነው” አለችና አንድ ዘለላ ጦር ማስቲካ አውጥታ ሰጠችኝ ፤ ከዚያ ምን አጋጠመኝ? የፊጥኝ ይዘው መረመሩኝ ? ወይስ እንዴት ሆንኩ? ተከታዩን በሚቀጥለው ፅሁፍ ይጠብቁ ይሆናልኮ መቸም እርም የለዎትም..... @imvsp @imvsp
Показать все...
‹‹ ኦቨር ዶዝ ›› (አሌክስ አብርሃም ) @AlexAberham ------------- // ----------- ትላንት ጎረቤቴ ሚስቱን ሊገላት ለትንሽ ተረፈች !! ትላንት ማታ ሲጮሁና ሲንጫጩ ሰምቸ …‹‹ዘራፍ…ያንበሳው ግልገል ›› ብየ መቀረቀሪያ ነገር ይዠ ሮጥኩ …እና ጎረቤቴ ቤት ስደርስ ‹‹ምንድነው ሌባ ነው የታለ …›› እያልኩ ቀውጢ ሳደርገው ‹‹ኧረ ተረጋጋ እትየ አልማዝ እራሷን ስታ ወድቃ ነው ›› አሉኝ ….እውነትም እትየ አልማዝ ሶፋው ላይ ዝርግትግት ብላ ወዟ ፍልቅ ፍልቅ እያለ ….አንዱ ‹‹ፀበል እርጩባት ›› ይላል ሌላው ‹‹አውድቅ ይሆናል ክብሪት አምጡ ›› ሌላኛው ‹‹አምቡላስ ይጠራ ›› አለ … ዓለሙ የሚባለው የላዳ ታክሲ ባለቤት ‹‹አምቡላንስ እስኪመጣ ትሙት እንዴ …ባይሆን በኩንትራት ታክሲ እንውሰዳት ›› እያለ ስራውን ያመቻቻል …. ደግነቱ እትየ አልማዝ ወዲያው አይኗን ገልጣ ፈገግ አለች !ጎረቤቴን ካወኳት ጀምሮ ፈገግ ስትል አይቻት አላውቅም ..ምን ታያት …መለዓክት ተገልጦ ምን ሹክ አላት …እያልኩ አሰብኩ ! በኋላ ዛሬ ጧት ላይ የአልማዝ ልጅ ሚጢ ትምህርት ቤት ስትሄድ አግኝቻት ‹‹ምን ሁና ነው እትየ አልማዝ እራሷን የሳተችው ›› ብየ ብጠይቃት … ‹‹አባቴ ተናግሯት ›› አለችኝ …በጣም ተበሳጨሁ ይሄ ሰውየ አበዛው… ሁልጊዜ ሚስቱን እትየ አልማዝን እንደነዘነዛት እንደሰደባት አንዳንዴም እንደነረታት ነው በቃ…ጭራሽ እንዲህ ራሷን እስክትስት ደግሞ ይናገራታል እንዴ ያበሻ ወንድ ሲባል …ሴት እናት ናት ሴት እህት ናት …ሚስት ናት …ብየ በቃ ተብከነከንኩ ! ‹‹ሚጢ ለመሆኑ አባትሽ ምን ቢናገራት ነው እንዲህ ራሷን እስክትስት … ›› ብየ ሳልጨርስ ‹‹አይይይ የማታው እንኳን ትንሽ ይለያል… እኔም ልዘረር ነበር …አባባ ሁልጊዜ ሲገባ ..አንች ከርፋፋ ጀሪካውን ውጭ የጣልሽው ምናባሽ ሁነሽ ነው …አንች ደነዝ ድመቷ ላይ ለምን በር ዘጋሽባት …ውሃውን አትዘጊውም እንዴ ለነገሩ ምን ታረጊ ብሩን የምገፈገፍ እኔ ….ተጎልተሸ ቴሌቪዥን ታያለሽ ….ነበር የሚለው ….ማታ ግን …ድንገት ገባና ማሚ ሶፋው ላይ እንደተቀመጠች ….‹የኔ ፍቅር ደህና አመሸሽ ›ብሎ ጉንጯን ሲስማት በቃ ራሷን ሳተች፡)ብላኝ ፈገግ ሚጢ !! ‹‹ኦቨር ዶዝ››፡)ከንፈሯን ቢስማት …አበባም ይዞ ቢገባ ኑሮማ ዛሬ ቀብር መዋሌ ነበር፡) !! ከምር ግን ዝም ብየ ባልና ሚስት ጎረቤቶቸን ስመለከት …. አንዳንድ ሚስቶች መፈቀር መከበር የናፈቃቸው ይመስለኛል …ቀልዱን ከነግነቱ በቁም ነገር እዩልኝና ባሎች በናታችሁ አፍቅሯቸው አትከፍሉበት …አንዳንዱ ባል ሚስቱን አቢዮት ሲፈነዳ እወድሻለሁ ያላት እስከዛሬ ደግሞት አያውቅም ! ውጭ ፖለቲካውን ሲያወራ ኳሱን ሲጠርቅ ዘና ሲል አምሽቶ ቤት ሲገባ ፊቱን የሚጥል ስንት ባል አለ … በቃ ፈገግታውን ‹‹ሚስት የማትደርስበት ቦታ አስቀምጥ ›› ብሎ ሃኪም ያዘዘለት ነው የሚመስለው ! ‹ባል ፊት› አለች ያች ልጅ …ምናይነት ባል ማለቷ እንደሆነ እንጃ ! @imvsp @imvsp @imvsp
Показать все...
ምክር እስከመቃብር (ከኣልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) (በእውቀቱ ሥዩም) . እንደምነሽ ሸገር እንደምነሽ ሸገር የቤት ኣከራየ የጋሽ ጣሰው ኣገር እየመጣሁ ነው፡፡ወደ ኣዲስ ኣበባ እየመጣሁ ነው፡፡እናቶች ኣባቶች ልጆች ኦርጅናሎች ሰልቫጆች! እኔ ሳልመጣ ውጊያውን እንዳትጀምሩት ኣደራ፡፡ ኣጭርና ጣፋጭ ይሁን እንጂ በማንኛውም ትግል ላይ ለመሳተፍ ዝገጁ ነኝ፡፡የጥይት መከላከያ ቆብ ሹራብና ሱሪ እንዲሁም ፈንጅ የማይበትነው ጫማ ከተሰጠኝ ኣንድ ሻለቃ እመራለሁ፡፡ኣነሰ ከተባለ ኣንዲት ኮረብታ እቆጣጠራለሁ፡፡ በጦር ምህንድስና ላይ እሳተፋለሁ፡፡ ባሩድ ኣገነፋለሁ፡፡ የታንክ ጎማ እነፋለሁ፡፡በሰላሙ ቀን ለሞባይል፤ በቀውጢው ቀን ለሽጉጥ ማስቀመጫ የሚሆን ሰገባ እሰፋለሁ፡፡ ይሄም ኣላዋጣ ካለ የኤፍሬም ይሳቅን ቡድን የሚፎካከር ኣስታራቂ ቡድን ኣቋቁሜ” ኣንተም ተው ኣንተም ተው፤ ያስታረቅሁበትን ኪሴ ውስጥ ክተተው” የሚል ኣገልግሎት እሰጣለሁ፡፡ቃሌ ነው፡፡የተናገርኩት ከሚጠፋ በቅርቡ የገዛሁት ጋላክሲ ሙባይል ይጥፋ(በዝች ንግግር ውስጥ የተደበቀ ጉራ እንዳለ እናንተ ሳትሉኝ ኣውቀዋለሁ) ገና ለገና ካሜሪካ ሊመጣነው በማለት ማጅራቴን ለመመታት እያሟሟቃችሁ ያላችሁ ዱርየዎች እንዲሁም ከዱላ የተረፈች ማጅራቴን በማሸት ትርፍ ለማጋበስ የተሰናዳችሁ ወጌሻዎች ተስፋ ቁረጡ ፡፡ ቤሳቢስትን የለኝም፡፡(ማጅራት መምታት ሲነሳ ፋሲል ደመወዝ ትዝ ኣለኝ፡፡እንኳን እግዜር ማረህ ልለው ብደውል ከዲሲ በርሮ ኣትላንታ እንደገባ ነገረኝ፡፡ለኮንሰርት ይሁን ለስልታዊ ማፈግፈግ ኣልነገረኝም፡፡ ወይ ኣበሳ!እኛ ኢትዮጵያውያንኮ ምስኪን ነን ፤ ኣገር በቀል- ዱላ ሸሽተን ስንሄድ የውጭ ኣገር ዱላ ይጠብቀናል፡፡ ኣሜሪካ ሁለት ወር ስቆይ ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ግብዣና ምክር ነው፡፡ዲታው ቢራ ጋብዞ ወደ ኣገርቤት ይዣት የምመለስ ቦርጭ ያወጣልኛል፡፡ቺስታው ቦርጬ እንዴት እንደምቀንስ ይመክረኛል፡፡ ኣሜሪካ ፍሪሽ የሆነ ሰው ኑሮው ምክር እስከመቃብር ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ወደ ኣሜሪካ ገንዘብ የተላከለት የመጀመርያው ሰው ሳልሆን እቀራለሁ? ለምሳሌ ጺም ለመቆረጥ ኣስር ዶላር መከስከስ ነበረብኝ፡፡ ፈርዶብኝ ኣሜሪካ ስገባ ጺሜ ያለወትሮው ቶሎቶሎ ማደግ ጀመረ፡፡ኣዲኣበባ እያለሁ ጺም ኣልነበረኝም፡፡እንዲያውም” ይሄ ልጅ ጺሚ የሚባል ነገር የለውም ስልብ ነው እንዴ?” የሚል ኣሜት በመንደራችን ይናፈስ ነበር፡፡ስልብ ኣለመሆኔን ለማሳየት ኣንድ ሁለት ቀን መንገድ ዳር ሸንቻለሁ፡፡ እንደልማዴ ከቀናኝ የሚጋብዘኝ ከፈረደብኝ የሚመክረኝ ኣላጣም በማለት Fenton መንገድ ላይ ወደሚገኝ ያበሻ ምግብ ቤት ጎራ ኣልኩ፡፡ ኣንዱ መድረክ ላይ የሱዳን ዘፈን ይዘፍናል፡፡ ከተስተናጋጆች ውስጥ ኣንድም የሚያዳምጠው የለም፡፡ሁሉም ሙባይሉ ላይ ኣቀርቅሯል፡፡የታደለው ከፍቅረኛው በቫይበር የተላከለትን የክንፈር ምስል እያየ በደስታ ይዋኛል ፡፡ ያልታደለው”የትምርት ቤት ክፍያ እየደረሰብኝ ስለሆነ ቶሎ ላክልኝ እንጅ”የሚል ካገር ቤት የተላከ መልክት እያነበበ ተክዟል፡፡ ሌላው ግድግዳው ላይ በተንጠለጠለው ቲቪ ላይ የሚተላለፈውን ያሜሪካ እግርኳስ እየተመለከተ ምድር ጠቦታል፡፡ ያሜሪካ እግርኳስ ቢሏችሁ እንደ ዋናው እግርኳስ እንዳይ መስላችሁ፡፡ ኣንዱ ጠብደል ጥቁር ሙልሙል ኳስ ይዞ ይሮጣል፡፡ሌላው ኣሳድዶ ይደርስበትና ዘርጥጦ ይጥለዋል፡፡ ለኔ ይህ ጨዋታ ሳይሆን ህጋዊ እውቅና ያለው ኣምባጓሮ ነው፡፡ በዚህ መሃል ዘፋኙ “ከ እኔ ጋ ናችሁ?” እያለ ኣስሬ ቢጣራም ማንም ተጉዳይ ኣልጣፈውም፡፡ ልምምድ ላይ ያለ ይመስል ለራሱ ዘፍኖ ወረደ ፡፡ስላሳዘነኝ ባንኮኒውን እንደመቋሚያ ተደግፌ በጥሞና ኣዳመጥሁት፡፡ድምጹ ከዛፍ ላይ ኣምፖል ያረግፋል፡፡ ቢሆንም ዘፈኑን ኣለቅጥ ያስረዝመዋል፡፡የሱን የሱዳን ዘፈን ታግሶ መጨረስ ሱዳንን በእግር እንደማቋረጥ ነው፡፡ ጥግ ላይ ክበበው ገዳ ተቀምጧል፡፡ ወንበር ስቤ ኣጠገቡ ተሰየምሁ፡፡ ራት ይጋብዘኛል ብየ ስጠብቅ ከራት ጋር የተያያዘ ገጠመኝ ጋበዘኝ፡፡ ክበበው ገዳ ጎረምሳ እያለ የለቅሶ ቤት እራት ኣያመልጠው ነበር፡፡ እንድያውም እንዲያባላኝ እያለ ቃሪያ በኪሱ ይዞ መዞር ጀምሮ ነበር፡፡ ኣንድ ለቅሶ ላይ ታድያ እራት ሲቀርብ ክበበው ከቤቱ ይዞት የመጣውን ቃርያ ከኪሱ ኣውጥቶ ኮርሸም ሲያደርግ የተመለከተ የሰፈር ልጅ ወደ ኣስተናጋጆች እያጨበጨበ “እዚህ ጋ ቃርያ ኣልደረሰኝም” ብሎ ጮከ፡፡ ኣለፍ ብሎ፤ የጃንሆይ ኣምባሳደር ዘውዴ ረታና ያሬድ ጥበቡ ቁጭ ብለዋል፡፡ያሬድ ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ ሲሆን ዘውዴ የተንቀጠቀጠው ተራራ ነው፡፡ኣሁን ዲማሚቱና ተራራውም ባንድ ጠረጴዛ ዙርያ ተቀምው ሳያቸው ገረመኝ፡፡ ከማጅራቴ ኣካባቢ “ልትጽፍ ነው የመጣህ ኣይደል”የሚል ሹክሽክታ ሰማሁ፡፡ወይንሸት ናት፡፡ ባለፈው ኣመት ከባህል ቡድናችን ጋር ስትመጣ ኮከብ ድምጻዊ ነበረች፡፡ኣሁን እዚሁ ቀርታ ኮከብ ኣስተናጋጅ ሆናለች፡፡ኣፍንጫዋ ላይ የወርቅ ቡግር የመሰለ ሎቲ ለጥፋለች፡፡እዚህ ኣገር ሴቶች ሎቲ የሚያንጠለጥሉት ጆሮኣቸው ላይ ሳይሆን ኣፍንጫቸው ላይ ነው፡፡ ስለወይንሸት በሌላ ምእራፍ እተርካለሁ፡፡ በሩ ኣጠገብ ተኬን ኣየሁት፡፡ ተኬ በደርግ ዘመን ካይሮ ላይ ከጠፋው የብሄራዊ ቡድናችን ገንዘብ- ያዥ ነበር፡፡ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ባደረገችው በግጥምያ ዋዜማ ላይ በረኛውን ጨምሮ ብዙ ተጫዋቾች ስለኮበለሉ እሱ የበረኛውን ቦታ ተክቶ ተሰልፏል፡፡ ከተቃራኒ ቡድን የተለጋች ኳስ ወደእሱ ኣቅጣጫ ስትመጣ በገንዘብ ቆጠራው ለምዶበት ጣቱን በምላሱ እያጣቀሰ ሲርበደበድ ፤ ኣስራ ሰባት ጎል ገበቶበታል፡፡ (ምንጭ፡ የይድነቃቸው ተሰማ ሪፖርት)ተኬ ጉዳዩ ሲነሳበት ያማርራል፤“ይሄ ውለታ ቢስ ህዝብ የገባብኝን ኣስራ ሰባት ጎል እንጂ ያዳንሁትን ሰባት መቶ ጎል ኣላሰበልኝም” ይላል፡፡ካገሩ ወጥቶ መቅረት ኣሳብ ፈጽሞ ኣልነበረውም፡፡ይሁን እንጅ ይህን ሽንፈት ይዞ ጓድ መንግስቱ ፊት መቆም የሚያመጣውን ነገር ኣስቦ በዛው” ነካው“፡፡ ኣሁን በሩ ኣጠገብ ቁጭ ብሎ ”ብሉ ሙን“ ቢራ ይጠጣል፡፡ የቢራ ጠርሙሱን በጥርሱ ከፍቶ ቆርኪውን ጠረጴዛ ልይ ተፋው፡፡ ቢራ መክፈቻ ቢቀርብለትም ተጠቅሞበት ኣያውቅም፡፡እግዜር መንጋጋን የፈጠረው ሲርብህ ኣጥንት እንድትቆረጥምበት ሲጠማህ የቢራ ጠርሙስ እንድትከፍትበት ነው ይላል፡፡ . @imvsp @imvsp @imvsp Read and share if u like it!!!
Показать все...
#ስለ_ፎቶ (በእውቀቱ ስዩም) . . ልጅ እያለሁ ፎቶ ብርቅ ነበር ፤ ከእናቴ ጋራ የሆነ ግብዣ እሄዳለሁ፤ የቤት እመቤቲቱ ቡናው እስኪፈላ ከግድግዳው ላይ መስኮት የሚያህል ባለፍሬም ፎቶ መስቀያ አውርዳ በዳንቴል ወልወል አድርጋ ትጋብዘናለች:: በፎቶው ውስጥ ሚስት ጥበብ ቀሚስ ለብሳ ፤ገብረክርስቶስ ጫማ አድርጋ ቁጢጥ ብላ ትታያለች ፤ ባል ሱፉን ግጥም አድርጎ አጠገቧ ቆሞ ይታያል ፤ በሰሌዳው ውስጥ ያለውን ብዙ ቦታ የሚቆጣጠረው የባልና ሚስቱ ፎቶ ነው ፤ ቴምብር የሚያካክሉ የልጆች ፎቶዎች ፍሬሙን ተጠግተው ጣል ጣል ይደረጋሉ ፤ አንዳንዴ እናቴና ጋባዧ ሳያዩኝ መስታውቱን ከፍቼ እበረብራለሁ ፤ ያልተዋጣላቸው ፎቶዎች ከጀርባ ተደብቀው አገኛለሁ፤ በጊዜው ዴሊት ማድረግ እሚባል ነገር ስላልነበረ ያለሽ አማራጭ የከሸፉ ፎቶዎችሽን ሰብስቦ መደበቅ ነው፤ አስራሁለተኛ ክፍል ስደርስ የፎቶ አልበም መጣ፤ ግን በጊዜው የነበሩት አልበሞች ከአምሳ ገፆች በላይ አልነበራቸውም ፤ ከዚያ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሆነው ቦታ፤ ያገለገለ የሰርግ ጥሪ ካርድ ፤ የከሸፈ ሎተሪ እና የመፅሄት ቅዳጅ ይቀመጥበታል ፤የፎቶ አልበም ሲቀርብልን የምናየው በታላቅ ተመስጦ እንደነበር ትዝ ይለኛል ፤ ያኔ የጎረቤት ፎቶ በምናይበት ጥሞና ዛሬ ፊልም የምናይ አይመስለኝም ፤ እያንዳንዱ ፎቶ ደግሞ የራሱ ታሪክ ነበረው፤፤ በከተማችን የነበረው ብቸኛ ፎቶ ቤት እነማይ ፎቶ ቤት ይባላል ፤ የስቱዲዮዋ ባክግራውንድ ሁሌም የዘንባባ ዛፍ ነው፤ ካሜራው የቅየሳ መሳርያ ይመስላል፤ ከጎኑና ከጎኑ ሁለት ትልልቅ ባለ ባርኔጣ አምፕሎች ያጅቡታል፤ አንዱ አምፖል ብቻ የሚለቀው ጨረር ድፍን ጎጃምን ራት ሊያበላ ይችላል፤ ሲመስለኝ ከተማው መብራት ሃይል የለህዝቡ የሚያከፋፍለው ከነማይ ፎቶ ቤት የተረፈውን መብራት ሳይሆን አይቀርም ፤ በጊዜው “ ፊትዎትን በሳሙና በመታጠብ አይንዎን ከትራኮማ ይጠብቁ” የሚል መፈክር በሬድዮ ይነገር ነበር፤ የእነማይ ፎቶ ቤት አምፖል ባጨናበሰው አይን፤ ትራኮማ ተጠያቂ መሆኑ ያሳዝነኛል፤ ብዙ ጊዜ የተነሳነው ፎቶ ለመድረስ በትንሹ አምስት ቀን ይፈጃል፤ ጉጉታችን አይጣል ነበር:: በተለይ ሴቶች የቀጠሮ ቀናቸው እስኪደርስ ድረስ እየተቁነጠነጡ ፎቱዋቸውን ቢያንስ ሁለቴ በህልማቸው ያዩታል፤ ሲኒማ ወደ ከተማው ከመግባቱ በፊት ቅዳሜ ከሰአትን የምናሳልፈው እነማይ ፎቶ ቤት በር ላይ የተለጠፉትን የሳምንቱን ፎቶዎች በማየት ነበር ፤ አልፎሂያጁ የከተማዋ ቆንጆ ሴት የተነሳችውን ፎቶ ከብቦ እያየ “ እዩዋትማ!! እመብርሃንንኮ ነው እምትመስል ” እያለ ያደንቃል ”፤ አንዳንዱ ጎረምሳ በማየትና በማድነቅ ብቻ አይወሰንም፤ ፤ ለፎቶ አንሽው ጉርሻ ሰጥቶ የቆንጆይቱን ፎቶ አጥቦ እንዲሸጥላት ያግባባዋል፤ ከዚያ ፎቶዋን በኪሱ ይዞ በከተማው በመዞር 'ገርሌኮ ' ናት እያለ ጉራውን ይነሰንሳል ፤ ማርክ ዙከርበርግ የሰው ፎቶን Share የማድረግ ሀሳብ የወሰደው ከነማይ ፎቶ ቤት ይሆን??? @imvsp @imvsp @imvsp
Показать все...
#ለራስ_የተፃፈ_ውዳሴ ስላንቺ ቁንጅና ስላንቺ ቁመና ከንፈር እና ዳሌ ጥርስና ተረከዝ ፥ ፀጉር ገለመሌ ለጡት ለወገብሽ ፥ ለፀባይሽ ጭምር በግጥም በዝርው ፥ ባድናቆት ስዘምር እስከዛሬ ድረስ... ውበትሽን አግንኜ ፥ ሰርክ መለፈፌ እኔ ስለራሴ አንዳች ቀን እንኳ ፥ ግጥም አለመፃፌ ሲትጠዪኝ ቆጨኝ ቢሆንም ቆንጆ ነኝ፡፡ እርግጥ ነው ብዙዎች ስለኔ ሳወራ ፥ ድንገት ያኮርፉኛል "ያንተን ሌሎች ያውሩ” ፥ ብለው ይነግሩኛል እኔ ግን እላለሁ! “እኔን ከኔ በላይ እርግጠኛ ሆኖ ፣ ሌላ እንዴት ያውቀኛል?!” እናም እኔ ማለት ቁመቴ ከአክሱም ፥ በእጥፍ ይረዝማል ጣፋጭ አንደበቴ መስማት ለተሳነው ፥ ለስልሶ ይሰማል ውብ አረማመዴ እንኳን መንገደኛን ፥ መንገድን ያቆማል፡፡ የከንፈሬ ወዙ ፥ ጥፍጥናው አያልቅም ጥርሴ ሺ ገዳይ ነው! ሺ ሟች ላለማየት ፥ ኗሪ ፊት አልስቅም፡፡ ከዐይኖቼ ብሌን ውስጥ ፥ ብርሐን ይፈልቃል አይኔን ያየ ሁሉ ብርሃን እንዳይጎዳው በእጆቹ መዳፍ ; ዐይኑን ይደብቃል። የገላዬ ጠረን ፥ ከሽቱ እጥፍ ነው መልካም ጠረን ሁሉ አለ ባሉት ስፍራ ፥ እኔ አለሁ ማለት ነው፡፡ ፀባየ ትሁት ነኝ ፥ ምጡቅ ነው እውቀቴ ግርማ ሞገሳም ነው ፥ ተክለ ሰውነቴ ሁሉ ይወደኛል የወደየኝ ሁሉ ፥ መቼም አይጠላኝም ከዚ በላይ እንኳን ብዙም ስለራሴ ፥ የማውቀው የለኝም፡፡ እንደውም እንደውም... አልጎርርም እንጂ ! ያ'ፈር ሰውነቴን ፥ በቁንጅና አብየው ቆንጆ ማየት ሲያምረኝ ፥ ራሴን ነው ማየው፡፡ ቢሆንም ቆንጆ ነኝ! 🔘በላይ በቀለ ወያ🔘 Share @imvsp @imvsp @imvsp
Показать все...
#ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት መልዕክቱን አንብበው ሲጨርሱ #Share ያድርጉት (Social Rules ተብለው የተዘረዘሩ የማኅበራዊ ሕይወት ሕግጋትን ስመለከት ለኛስ አትጠቅምም ወይ ብዬ ነው ወዲህ ማምጣቴ) ================== 1. ይሰለቹሃል አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ! 2. 'ሼም ነው' ነው የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ! 3. አይባልም "... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም። 4. ክፈል አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ። 5. ነውር ነው ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ። ============ 6. አታቋርጥ ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ። ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው። 7. አታብሽቅ ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው። ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ። 8. አመሥግን ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመሥግን። 9. ያለስስት አድንቅ ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው። 10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ። =================== 11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል። 12. ስነ ስርዓት ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው። 13. ክብር ለሁሉም ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም። 14. ስልክህን አስቀምጥ ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው። 15. አድብ ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው። ========================== 16. ተቆጠብ ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ። 17. መነጽርህን አውልቅ ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው! 18. አትሳሳት በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ። 19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው። ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው። 20. ዕቃ መልስ የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ። 21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። ሌሎች እንዲወያዩበትና እንዲተቹት ክፍት አድርገው፤ አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ። ነገርህን ደገፉትም አልደገፉት ምንጊዜም ቢሆን ላነሳኸው ሐሳብ ጥሩ ግብዓት አይጠፋም። ልክ አልሆን ወይ እያልክ ወይም ሐሳቤ ያንስ ይሆን ወይ ብለህ አትሸማቀቅ፤ ተሸማቀህ ትቀራለህ! @imvsp @imvsp @imvsp
Показать все...
ጋሽ አዳሙ ዘ ብሔረ አዲስ አበባ ! (አሌክስ አብርሃም) ‹‹እያንዳንድሽ ›› የሚለው ድምፅ የሰፈራችንን ጨለማ ሰነጣጥቆ አየር ላይ ሲናኝ …. ጋሽ አዳሙ የሰፈራችን ታዋቂ ሰካራም ልክ በሰዓቱ ከምሽቱ 4; 00 ሰዓት ደረሰ ማለት ነው ….ሳር ቅጠሉን እየተሳደበ የተኛውን እየቀሰቀሰ …እናም ደስ ሲለው እያንጎራጎረ … ለግሩ ጫማ የለው ለራሱ ባርኔጣ የጭንቅሎ አባት አሁን ገና መጣ ! ….ጭንቅሎ የጋሽ አዳሙ ልጅ ነው ! ሰፈሩ ጭጭ ይላል …ሁሉም በየቤቱ ሲያንጫጫው የነበረውን ዘፈን ነሽ ዜና …ወሬ ነሽ ክርክር ዘጋግቶና አቁሞ ጆሮውን ወደሰካራሙ አዳሙ ያቆማል … ‹‹ፈሪ ሁሉ … አንድ ሰፈር ፈሪ ቦቅቧቃ …እያንዳንድሽ ወጥተሸ ከሰንሰለትሽ በላይ አትጩሂና ጭጭ ብለሽ እኔን አዳምጭ … ለነገሩ ….ፈሪ መንደርተኛ ራሱን አንዴ በእብድ አንዴ በሰካራም እየደበቀ ብሶቱን ካላስነገረ ማን ይናገርለታል …. መቶ ፐርሰንት የመረጣቸው ተወካዮቹ እንደሆነ …. ፓርላማ ላይ ለሽ ሁኗል ስራቸው ….እኔ የምለው መንግስት ለህዝብ ተወካዮቹ ደመወዝ የሚከፍላቸው በእንቅልፍ ኪኒን ነው እንዴ ….ሃሃ ›› ጋሽ አዳሙ ዝም ይላል መንደርተኛው ጆሮውን አቁሞ ለሳቅ ተዘጋጅቶ በየቤቱ ያቆበቁባል … ውው …ውው የሰፈራችን ውሾች ጋሽ አዳሙ ላይ ይጮሁበታል...አመል ሁኖባቸው ‹‹ህ …ጩሁ …ካልጮሃችሁ ጌቶቻችሁ ነገ ቅንጥጣቢ አያቀምሷችሁም …ለነገሩ ከኋላ ተደብቀው እናተን ከሚያስጮሁት ባለቤቶቻችሁ እናተ ትሻላላችሁ ... ሰፈሩ ዝም ከሚል ውሻም ቢሆን ይጩህበት …ችግሩ አዲስ መጭው ትውልድ የውሻ ሰፈር ብሎ እንዳይሰይመው ነው ….ደጋግሞ ውሻ ሲጮህ ባለቤቶቻችሁም የሰውን ንግግር እረስተው የውሻ ጩኸት እንዳይወርሱ ነው ….›› ውው ….ውሻዎቹ ይጮሃሉ ‹‹ው .. አለች ቡችላ እንደውሻ መጮህ እለማመድ ብላ ግደለም ው ትበል ው ትበል ካሁኑ የእውነት ጩኸት የለም ጅራት ቆይ ውሻ ተከታይ ከሆኑ ው ትበል ካሁኑ ! ›› ሃሃሃሃ ጋሽ አዳሙ በጎርናና ድምፁ በሳቁ ጨለማው ላይ ይነግስበታል ! … ‹‹አረጋሽ›› ብሎ ድንገት ይጣራል …አረጋሽ የቀበሌው ምክትል ሊቀመንበር ናት ….እሷን ካልጠራ አይሆንለትም … ‹‹አረግየ ስዊት ….ሃሃ ባለፈው ወተት በየቤታችሁ በቧንቧ ይልክላችኋል ብለሽ የመረጥነው ሰውየ ምነው በድርቅ ምክንያት ከነላሞቹም ወተታቸው ሲደርቅ ዝም አለ ….ሃሃሃሃ መጣፈጡ ቀርቶ እጀን በለቀቀኝ አለች አሉ ሴትዮዋ …እኔኮ ግርምምም የሚለኝ መንግስት ምን ቢያበላችሁ ነው ‹‹ኮንፊደንሳችሁ›› 11 በመቶ ያደገው …በቃ አፋችሁን ሙልት አድርጋችሁ በያዝነው የበጀት ዓመት ምንትስ ቅብርጥስ ሰርተን ገንብተን ትሉናላችሁ … በጀቱ እና አመቱ ያልቃል… ልማት ኢንጅሩ !! ምነው ብለን ስንጠይቅ ‹‹እቅዱ ተለጥጦ ነው …›› ይሄ ነገር ቅኔ ነው እንዴ ….መጭው ትውልድ የሚፈታው የብድር ቅኔ .... እዚች አገር ላይ እቅዱ ተለጠጠ ትሉናላችሁ ….ትሉናላችሁ….ኧረ ይሄ የልማት እቅድ ተለጥጦ ተለጥጦ ሱዳን እንዳይገባና ‹‹ካለፍላጎታችን አለሙን ›› ብለው ጦር እንዳይመዙብን ብለን ስንፈራ … በአንድ ጀምበር የከበረ ልጥጥ ባለሃብት እና ኮምታራ አገርና ህዝብ ….እጃችን ላይ ቀረ ! አረግየ ነገር አለ …ግን ማን ይናገር ….እንደነዚህ ውሾች እንኳን የሚጮህ ጠፋ ! ጋሽ አዳሙ ዝም ይላል …የነፍሳት ሲርሲርታ የውሾች ጩኸት ….ጨለማው ሰፈር ላይ ነግሶ ዝም እንዳለ ….ድንገት ‹‹እያንዳንድሽ›› ብሎ ይጮሃል !‹‹እያንዳንድሽ አሁን ከአረብ አገር የመጣ ብርድ ልብስሽን ተጀቡነሽ ከአረብ አገር በመጣ ቬርሙዝ አጥሚትሽን አቅርበሽ ፊልምሽን እያየሽ ነው ….ድንዙዝ ሁሉ ዛሬ ከክንብንብህ ወጥተህ ለምን ካላልክ ነገ ከየትም ውጣ ስትባል ትተነፍሰው ቃል የለህም ‹‹ ውጡ …ካገራችን ውጡ ›› ተባልን አዎ አረቦቹ ውጡ አሉን …ዝም !! እሱ ያመጣውን እያልሽ ! ድህነት ከገዛ አገራችን ‹‹ውጡ›› ሲለን ስንወጣ ....ባለአገሮቹ ከዛ ‹‹ውጡ›› ሲሉን ስንወጣ … መውጣትና መግባት የሚባለው የተፈጥሮ ህግ ቀርቶ መውጣትና መውጣት እጣው የሆነ ሚስኪን ትውልድ አፍርተን እንረፍ !! ደግሞኮ በየቴሌቪዥንና ሬዲዮ በየስብሰባና ምናምኑ ዋናው ‹‹ሰልፍ ኮንፊደንስ ነው… ባገር ላይ ሰርቶ መቀየር ››ይባልልኛላ ….ወይ ሰልፍ ኮንፊደንስ … ይሄ ትውልድኮ ሳይመከርም በፊት ያላነበበው የሰልፍ አይነት የለም ጓዶች ….አገር ምድሩን የሞላው የ‹‹ሰልፍ ›› መፅሃፍ ነው …ወገኖቸ እውነቴን ነው ሴት ወንዱ ‹‹ሰልፍ ኮንፊደንስ …ሰልፍ ስቲም …ሰልፍ ኮንትሮል ….ሰልፍ አክቸዋላይዜሽን ….የሚል መፅሃፍ አይኑ እስኪቀላ ካነበበ በኋላ ቀና ሲል የሚጠብቀው የታክሲ ሰልፍ …የዘይት ሰልፍ …እና የስኳር ሰልፍ ነው !! … ይሄ ሁሉ ‹‹የሰልፍ›› መፅሃፍ አንድ ነብስ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ እንኳን ያደርግ ዘንድ ያረዳው ትውልድ ቢሰደድ ምን ይገርማል …. አሁን አሁን ደሃው ኢትዮጲያዊ ብቻ ሳይሆን ከበርቴውም አሜሪካና ኤሮፕ ወጣ የሚለው ለስራ ብቻ አይመስለኝም … የሰልፍ አምሮቱን ተወጥቶ ለመመለስም ይመስለኛል…. ቀልድ ይመስላል እንዲህ ሲወራ … ሰው አትተነፍስም ከመባል በላይ ምን እርስት መነጠቅ አለ !! ቢሆንም የእብድና ሰካራም እንዲሁም ዘበናይ መብታችንን ለመጠቀም ስንል ….በጀመርነው መጠጥ ይሄው ሰካራም ሁነን ቀረን ….እቅዳችን ተለጥጦ ለቅምሻ ያልነው መጠጥ ጎርፍ ሁኖ አጥለቀለቀን ….›› ጋሽ አዳሙ ….በጨለማው ውስጥ …ድምፁ እየቀነሰ …እየቀነሰ …እ…የ …ቀ…ነ…ሰ ….‹‹እ …ያ …ን…ዳ…ን…ሽ ›› ሲል ይሰማናል ከሩቁ … እየቀነሰ …እ…የ …ቀ…ነ……………..ሰ …… @imvsp @imvsp @imvsp
Показать все...
ከስራ በሁዋላ አየሁዋት ሄድኩና" (በእውቀቱ ስዩም) ኢትዮጵያ ውስጥ ስራ እንዲከበር ያደረገ ደርግ ነው፤ ከዛ በፊት ስራ የተናቀ ተግባር ነበር፤ “ዋይ ዋይ ባላባት እንግዲህ ቀረ ሳይሰሩ መብላት “ ይሉ ነበር የዩኒቨርስቲ ፋኖዎች! ደርግ ስራን አስከበረ፤ አንዳንዶች እንደውም ባንድ ጊዜ ሁለት ስራ ደርበው እሚሰሩ ነበሩ ! ለምሳሌ አትሌት ምሩፅ ይፍጠር ሩጫ ልምምድ ሲያደርግ እግረመንገዱን በየቤቱ ፖስታ ያድል ነበር! በደርግ ብር ኖቶች ላይ ያሉትን ምስሎች ተመልከቷቸው ! ሰፌድ የምትሰፋ ሴት፤ የሚመራመር ሳይንቲስት ! ቡና የሚለቅም ገበሬ! የቦዘነ የለም! መንግስቱ ሃይለማርያም እልል ያለ አምባገነን ነበር ፤ በስራ ግን ቀልድ አያውቅም! የሆነ ጊዜ ላይ መንጌ፤ አለማየሁ እሸቴንና ጥላሁን ገሰሰን ወደ ቢሮው አስጠራቸው ! “ ወጣት አለማየሁ! “ “አቤት ጏድ ሊቀመንበር “ “እጅ እግሩ ተቆርጦ አከላቱ ጎሎ ይኑር አባብየ እየበላን ቆሎ አርባራቱን ታቦት ጠርቶና ለምኖ ብለው የዘፈንከው ምን አስበህ ነው? አባትህ ካልሰራ ማን የቆላውን ቆሎ ነው የሚበላው?" “ ጏድ ሊቀመንበር ይሄን ዘፈን የዘፈንኩት ካብዮቱ በፊት ባድሃሪው ስርአት ውስጥ ነው! አሁን ንቃቴ ከጨመረ በሁዋላ የገዛ ዘፈኔን ሳደምጠው ሼም ይጨመድደኛል” አለ አሌክስ ዞማ ፀጉሩን በጣቶቹ እየቆፈረ ! “ ሂስህን ከዋጥህ ላይቀር፤ ጥቂት ስንኞችን አስተካክለህ በድጋሚ ብትዘፍነው ምን ይመስልሃል?” “ ጥሩ አሳብ ነው ጏድ ሊቀመንበር ! ምኑጋ ላስተካክለው? ” መንጌ በመስኮቱ አሻግሮ ትንሽ ሲያስብ ከቆየ በሁዋላ ፤” እጅ እግሩ ተቆርጦ የሚለው ስንኝ በጣም ዘግናኝ ነው ! የምር አባትህ ከሆነ ትንሽ አስተያየት አድርግለት ! ወይ እጁን ወይ እግሩን አስቀርለት ! " “ የትኛውን ላስቀርለት?” አለ ለሌክስ ! “ እንደኔ እንደኔ እጁን ብታስቀርለት ጥሩ ነው፤” ቀጠለ መንጌ” የለመነውን ቆሎ ለመያዝ ራሱኮ እጅ ያስፈልገዋል፤ እንደ ሁኔታው አይተን፤ ብሄራዊ ውትድርና ላይም ልናሳትፈው እንችላለን ፤ ሻእቢያ ናቅፋ ላይ የረፈረፈችን እግር የሌላቸው ሸሽተው እማያመልጡ ወንበዴዎችን የቀበሮ ጉድጏድ ውስጥ ወትፋ ነው፤ ‘ ይገርምሃል መጀመርያ ፈንጅ በእግራቸው ያስጠርጏቸዋል! ከዛ ደግሞ በባሊ ተሸክመው ወስደው ሽምቅ ውጊያ ላይ ያሰማሯቸዋል! አገር መገንጠል የተለማመዱት የገዛ ወንድሞቻቸውን እግር በመገንጠል ነው! ርጎሞች!" ቀጥሎ መንጌ ወደ ጥላሁን ገሰሰ ዞር ብሎ " እሺ ጃል ጥላሁን! ወዳንተ ስመለስ፤ -ያላየሁሽለታ በማዘን፤ በጭንቀት በድቀት ተክዤ ሌሊቱን ሳልተኛ እያደርኩኝ፤ ቀኑን እውላለሁ ፈዝዤ- ብለህ የዘፈንከውን አዳምጫለሁ! አሁን ያለንበት ሁኔታ የሙሉ ጊዜ አፍቃሪነትን የምናበረታታበት አይደለም!! ወጣቱ ቀን በስራ ተስማርቶ ማታ ላይ በሃሳብ መፍዘዝ መብቱ ነው! በተረፈ ኢትዮጵያ ሌትም ቀንም በፍቅር የሚጃጃል ወጣት የምትሸከምበት ጫንቃ የላትም! የወዝ አደር እንጂ የውዝዋዜ አደር ፓርቲ ለመገንባት አልተነሳንም! ተግባባን?” ከጥቂት ሳምንታት በሁዋላ ጥላሁን ገሰሰ “ ፈልጌ አስፈልጌ “ የሚለውን ዘፈን ሰራ! ዘፈኑ የመንጌ ተፅእኖ እንዳለበት ለማወቅ እኒህን ስንኞች ብቻ ማየት ይበቃል! “ አየሁዋት መርካቶ ሲሉኝ ትናንትና ከስራ በሁዋላ አየሁዋት ሄድኩና ከስራ በሁዋላ ብቅ ብል በማታ የለችም ካዛንችስ እሱዋ የት ተገኝታ እሷ የት ተገኝታ ! “ @imvsp @imvsp @imvsp Share to your beloved ones!!!
Показать все...
ሴት ጓደኞች አሉኝ። (ዋቃ ገለታ ይግባውና እጣ ፈንታዬ ሴቶች ናቸው) ሳወራቸው አንተ እያልኩ ነው። ብሮ ስላቸው አይከፋቸውም። አንዳንዴ ሳት ሲያደርገኝ "ወንድምህ ነኝኮ" ይሉኛል። ሌላ ደግሞ ማውቃቸው ሴቶች "ሴት ጓደኛ የለኝም ሴቶች አይመቹኝም" ምናምን ማለት ይቀናቸዋል ወንድ ጓደኞቼ እህቴ ብላቸው የሚረሽኑኝ ይመስለኛል። ደግሞም ወንድ ጓደኛ የለኝም ወንዶችን አልወድም የሚል ወንድ ልጅ ገጥሞኝ አያውቅም። ዝም ብዬ ሳስበው ይህ ነገር በዘወርዋራ የሚነግረን ነገር ያለ ይመስለኛል። ወንድነትን ሚያገዝፍ ሴትነትን ሚያኮስስ ስውር ዝንባሌም ይመስለኛል። .... ምናልባት ፀጉር ሰንጣቂ አቃቅራም ሆኜ ይሆን? ምንጭ --ወግ በኛ @imvsp @imvsp @imvsp
Показать все...
,,ድሮ እና ዘንድሮ,, ድሮ ..... ሀያቶቻችን ሕክምና ሳይማሩ ሐኪሞች፣ቀይ ጋውን ተከናንበው በሕግ ሳይመረቁ ድንቅ ዳኞች፣ በኢንጂነሪንግ ሳይመረቁ ቀያሾች፣ የቋንቋ ዲግሪ ሳይጭኑ የብዙ ቋንቋ ተናጋሪዎች ፣ያለ ጥቅማጥቅም ፍቅር አዋቂዎች፣ ያለ ጦር ትምህርት ተዋጊዎች፣ያለ ሰባኪ ሀይማኖተኞች ነበሩ። አባቶቻችን ትንሽ ቀለም ቆጠሩና እውቀት ሞልቶ ቢፈሳቸው ምሁርነት አቁነጥንጦአቸው የፖለቲካ ርዕዮት አለም አብዝተው፣ እርስ በእርስ ተጋደሉ ተጨራረሱ ... ዛሬ በየአመቱ በየዩኒቨርሲቲው በሺህ የሚቆጠሩ ቆብ ደፍቶ ተመርቆ ሲወጣ ጭራሽ አእምሮው ጠቦ በሱስ ሲደነዝዝ ውሎ ያድራል። ከድሮ ከሀያቶቻችን ያረጀችና የተዛመመች የእንጨት ቤት ጎን ፎቅ ይገትራል፣ ታዲያ የተዛመመችው አንድም ምርጊቶ ሳይረግፍ በዘመነኞች መሐንዲስ የተሰራው ፎቅ ፍርክስክሱ ወጥቶ የፍራሹ ፍንጣሪ የተዛመመችውን ይደረምሳል። ግም ያገማል አይደል? ታሞ ሊታከም ሆስፒታል የሚገባው ህሙማን በሽታው ከሚገለው ይልቅ ሐኪሙ የሚገለው ይበዛል። ገበሬው በራሱ ልምድ አርሶ ያመርት ከነበረው የተማረው ከመከረው ወዲህ የምርት ውጤቱ ያሽቆለቆለ ነው። እውነት ጠፍታ ውሸት ነግሳለች፣ ድሮ የሰው ገንዘብ መመኘት፣ በሰው መጋበዝ፡ ውርደትና የበታችነት ነበር፣ ዛሬ ሁሉም በአገኘው አጋጣሚ ያገኘውን መዝረፍ ይፈልጋል። መጪውስ እንዴት ይሆን?🤔🤔 ✍✍.... @imvsp @imvsp @imvsp
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.