cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

🌷❤️🌹 ውብ ፍቅር🌹❤️🌷

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
562
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼ቸሩ የእኔ ጌታ መሃሪ ይቅር ባይ 🌼 🌼ከክፉው ወረርሽኝ ከኮሮና ቫይረስ 🌼 🌼ከባህሩ ስጥመት ድልድይ ሆነህ🌼 🌼ከጥፋት ከልለህ ትላንት ካሻገርከኝ🌼 🌼በሰላም በጤና ዛሬ ላይ አኑረህ 🌼 🌼ተመስገን ጌታዬ ነገም አንተ አለህ🌼 🌼የዘመናት ሠሪ የዓመታት አባት 🌼 🌼ሁሉን አሳላፊ አልፋና ኦሜጋ 🌼 🌼ያለፈውን ዘመን ደግሞ እንዳይመጣ 🌼በምሕረትህና በቸርነት ይለፍ 🌼 🌼እውነተኛ መሪ መንጋውን ሰብሳቢ🌼 🌼ከሃሳዊ መሲህ ተዋህዶን ጠባቂ 🌼 🌼አሁንም አድለን እንባ አባሽ መሪ 🌼 🌼 🌼 🌼ዘመነ ማቴዎስ ዘመነ ፍሥሃ ! ፡፡ 🌼 🌻 🌻 🌼 🌻 🌼 🌻 🌻 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌹@Yewqetabugida67🌷🌼
Показать все...
. #እንቁ_ጣጣሽ🌼💐🌷🌹 ​​🌼 "የዕንቁጣጣሽ" ሥያሜ አመጣጥ? ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው áŠ ááˆŞá‰ƒ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የሀገራችን ንግሥት áŠ•áŒáˆĽá‰° ሳባ á‹¨áŠ•áŒ‰áˆĽ áˆ°áˆŽáˆžáŠ•áŠ• ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡ ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡ ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡ አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡ #መልካም_አዲስ_አመት_ይሁንልን #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር 🌼@Yewqetabugida67🌼
Показать все...

🗣ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ትላንትና የድርጅቱ ሰራተኞቹን ሰብስቦ የማነቃቂያ ንግግር አደረገ በንግግሩም ደጋግሞ የተጠቀመው ቃል የማይቻል ነገር የለም #ይቻላል ብሎ ንግግሩ ቋጨ፡፡ በመጨረሻም ጥያቄ ያለው ሲል በመስሪያ ቤቱ አዝግ በሚል ቅጽል ስም የሚጠራ ሰራተኛ እጁን አወጣ ኃይሌም እድሉን ሰጠው፦ "አመሰግናለሁ ሻለቃ እንደው ደፈርከኝ አትበለኝና ብሎ በንግግርህ ደጋግመህ ይቻላል ይቻላል ስትለን ነበር ግን ከምር ሁሉ ነገር ይቻላል???? " ሲል ኃይሌም ቀበል አርጎ "ከሞከርክ ሁሉም ይቻላል" አለው፡፡ ሰራተኛው ግን አልተዋጠለትም እንግዳው ሁሉም የሚቻል ከሆነ አንድ ነገር አድርግልኝ እኔ አልቻል ስላለኝ ነው ሲል ፣ ሻለቃ ኃይሌም፦ ኮስተር ብሎ ምንድነው እሱ አለው?? ሠራተኛው ፦ "ይቻላል የሚለው ቃል ይበልጥ እንዲገባን እዚህ ግድግዳ ላይ ውኃን በፕላስተር አጣብቀህ/አንጠልጥለህ ይዘህ አሳየን"ሲል ሻለቃ ኃይሌ፦ ከመልሱ በፊት "እኔ ምለው አንተ የእኔ ሠራተኛ ነህን ??? 🤔🤔 አላለም ፡፡ መልካም የእሁድ ቀትር Join & shsre @yewqetabugida67
Показать все...
#በዓለም_ላይ_3_ዐይነት_ሰዎች_አሉ! 1, የተቀመጡ ሰዎች 2, የተሰረቁ ሰዎች 3, ባለ ራዕይ ሰዎች #የተቀመጡ_ሰዎች የሚባሉት ህይወትን በ TV ነው የሚያዩት፣ ትችትን ፣ ነቀፌታን ፣ተግዳሮት የማይፈልጉ ፣ አሸናፊነትንም ሆነ ሀላፊነትን አይወዱም ባአጠቃላይ [Challenge Life] አይፈልጉም። #የተሰረቁ_ሰዎች ሌላዉን መስሎ መኖር ምኞታቸው ነው። የራሳቸው የሆነ አቋምም ሆነ ማንነት የላቸውም። የተሰረቀ ሰው ራሱን ከሌላ ጋር እያወዳደረ ነው የሚኖረው። #ባለራዕይ_ሰዎች ነፃ እና ተፈጥሯዊ ሰዎች ናቸው። የበታችነት ስሜት አይሰማቸውም!! መተባበር፣ ፍቅር እና ማህበራዊ ተቆርቋሪነት መገለጫቸው ነው።እነዚህ ሰዎች በቅድሚያ፦ 🔹ማህበረሰቡን 🔹ሲቀጥል ቤተሰባቸው 🔹 በመጨረሻ ራሳቸዉን የሚያስከትሉ ናቸው። እንዲህ አይነት ሰው ካርታውን ያለማጭበርበር የሚጫወት እንጂ የሚያሸንፍ አይደለም። 👍ሁሉም ጥሩ ይሆናል ዋናው ነገር ሰላምና ጤና 🕊@Yewqetabugida67🌹
Показать все...
ባለ ጊዜ ጉልበተኛ አልጠግብ ባይ ስትሆንና ቀን ሲጥልህ መራመድ ሲያቅትህ @Yewqetabugida67
Показать все...
✤ሰው እንጂ እግዚአብሔር አልረሳኝም✤ መርሣት የባህሪውም አይደለምና፦ በጸሎት ኃይል የሚያምን አምኖም የሚተጋ አንድ ፅኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደኃ ፣የሚበላውን የሚቸገር ረሃብተኛ ፣ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርብ ሆኖ ይታዘብ የነበረው ወዳጁ እንዲህ አለው ‹ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማስገኘት ካልቻለ የመጸለይህ ትርጉም ምንድር ነው? በቃ ፈጣሪህ አልሰማህም ማለት ነው!› ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያ ምስኪን ክርስቲያን ግን እንዲህ ሲል መለሰለት ተሣስተሃል ‹እግዚአብሔርማ አልረሳኝም! ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ ነግሮት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን አደራ የተቀበለው ሰው ዘነጋኝ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይሆን ይህ ሰው ረስቶኛል!!!› ክርስቲያኖች ለምን አንዳንዶች ከዕለት የሚተርፍ ብዙ እንጀራ ሲያገኙ፤ አንዳንዶች ደግሞ ለዕለት እንኳን የሚሆን ቁራሽ እንጀራ ያጣሉ? መቼም ‹ለሰው ፊት የማያዳላ› እግዚአብሔር አድልዎ ኖሮበት ነው አትሉም?! (ሐዋ. 10፥34) ይህስ የሆነው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት አትርፈው ያገኙት ምንም የሌላቸውን በመርዳት እና በመመገብ በባሕርይው መግቦትን ገንዘብ ያደረገውን አምላክ በጸጋ እንዲመስሉትና በፈጠራቸው ሰዎች መካከል ያለውን ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ነው፡፡ ስለዚህ ‹የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ› ብለን የለመንነው አምላክ ከዕለት እንጀራችን አትርፎ የሚሰጠን ይህን አምላካዊ አደራ እንድንወጣም ስለሚፈልግ እንደሆነ ብንረዳው እንዴት መታደል ነበር!!! ★በዚህ ዓለም በዚህ ዘመን ሰው ዝም ብሎ ራሱ ተስፋ ቆርጦ ሰውን ተስፋ ቢስ የሚያደርግ ሙሉ ነው፡፡ ነገር ግን ወዳጄ ምንም ጊዜ ምንም ይሁን ምን ሰውን ያለቦታው የሚያውሉ ያላዩትን የሚናገሩ ዝም ብለው ስም የሚያወጡ በመሰለኝ የሚናገሩ አሉና እንዳትሰማ ፦ " #ሰው ሲጨርስ እግዚአብሔር እንደገና ይጀምራል፤ #ፈጣሪ ሰው አይደለማ " ፡፡ ተስፋ ሕይወት ነው ተስፋ ጠል ነው ተስፋ አያልቅም ጅረት ነው .... ደስ የሚል የተስፋ ቀን ይሁንልን ፡፡ #የእውቀት አቡጊዳ 🌹@Yewqetabugida67🌷
Показать все...
. #ድንቅ_እናት ባለቤቷ ከሞተ በኋላ ልብሱን ቁም ሳጥን ውስጥ አንጠልጥላው በየጊዜው ገንዘብ ታስቀምጥበታለች ። ልጆቿ ለተለያየ ጉዳይ ወጪ ሲጠይቋት ሂዱ ቁም ሳጥን ውስጥ ከአባታችሁ ደረት ኪስ ውሰዱ ትላቸዋለች " እነሱም የሚያስፈልጋቸውን ብቻ ቆጥረው ከአባታቸው ኪስ ይወስዳሉ ከዕለታት አንድ ቀን ልጆቹ እናታቸውን ለምን እንደዚህ እንደምታረግ ሲጠይቋት የአባታችሁ ሩህሩህነትና ለጋስነት እንድታውቁትና አባታችሁ እዛም ሆኖ ለእናንተ እንደሚጨነቅ እንድታውቁ (አባት የሞተበት ) ነን ብላችሁም እንዳታስቡ ለማስታወስ ነው!:: #አስተዋይ_እናት_ትምህርት_ቤት_ናት_የምንለው_ለዚህ_ነው!:: 🌹@Yewqetabugida67🕊
Показать все...
#እኛ_አበሾች_ስንተባበር @Yewqetabugida67
Показать все...
#ሁሉም_የሞላለት_ስለሌለ_ሁሉም_የጎደለበትም_የለም በአንድ የቻይና የገጠር መንደር የሚኖሩ አንድ ጎልማሳ ሰው ነበሩ ሁሌም ታዲያ ማልደው በመነሳት ውሃ ሊቀዱ ወንዝ ይወርዳሉ፣ሆኖም ያሉዋቸው ሁለት ከሸክላ የተሰሩ የውሀ ማሰሮዋች ሲሆኑ አንደኛው አዲስ ሲሆን ሌላኛው ግን ሰባራ ነው በዚህ ምክንያት ውሃ ቀድተው ቤት ሲደርሱ አዲሱ ሙሉ ውሃውን እነደያዘ ቤት ሲደርስ ሰንጥቅ ያለበት አሮጌው ግን ግማሹን አፍሶ ግማሹን ደግሞ ይዞ ነው የሚገኝው በዚህ ምክንያት የሚያፈሰው አሮጌ ማሰሮ ሁሌም እኚህ ሰውዬ ለምን እንደማያድሱት እያጉተመተመ ከጓደኛው በማነሱ እየተሸማቀ ይኖር ነበር :: አንድ ቀን የራሱ ተፈጥሮው በጣም ስላስጠላው ይህ እንዲሆን ለምን እንደፈቀዱ አፍ አውጥቶ ጌታውን በምሬት ጠየቀ :: አዛውንቱ ሰውዬም ሲመልሱለት ” ተፈጥሮህን ለምን ታማራለህ የምንሄድበትን መንገድ ተመልክተኸው ታውቃለህ በአንተ አቅጣጫ ያለው መሬት ሁሌም ለምለም ነው በሚያምሩ አበቦች የተሸፈነ ነው በጓደኛህ በኩል ያለው ግን ደረቅና አቧራማ ነው ይሄ አንተ በማፍሰስህ ምክንያት የመጣ ነው እነዚህ አበቦች ለአካባቢው ጌጦች የሳሎን ማድመቂያ ናቸው ህይወትን ያድሳሉ :: በዚህ አለም ሁላችንም ብንሆን ከጉደለት ጋር ነው የተፈጠረነው አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን ዋናው ነገር ከሌላው በማነፃፀር የራስን ተፈጥሮ በመጥፎ መሳልና ማማረር ተገቢ አይደለም ከዛ ተፈጥሮ የሚገኝን በጎ ነገር ማየትና ያንን ማድነቅ ያስፈልጋል “ ብለው መለሱለት ። ሞራል : — ሁሌም ቢሆን አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን ራስን ዝቅ አድርጎ ተፈጥሮን ማማረር ተገቢ አይደለም ። #ሁሉም_ሙሉ_የሆነለት_የለም_ሁሉም_ደግሞ_የጎደለበት_የለም_ሙሉውን_በጎዶሎ_ጎዶሎውን_እየሞሉ_መኖ 🌹👇🌷#የበለጠ_ያግኙ🌷👇🌹 @Yewqetabugida67
Показать все...
#ምክር_ለወዳጅ❗️ 🖋 በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል። ሰምቶ ማመን፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል። 🖋 ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው! በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው። ብልህ ከሆንክ በሰው ከደረሰው ትማራለህ፤ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ። 🖋 የታየህን አሳይ፣ ያልታየህን አጥራው። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል። 🖋 ዓይንህ የፊቱን ቢያይ፤ ልብህ የኋላውን ያስብ። ነገ ላይ እንድትደርስ፤ የትናንቱን አትርሳ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ። 🖋 የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው። 🖋 ክፋት አይሙቅህ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት። 🖋 ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ። ላለው አትሩጥ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው። 🖋 ለሀብታም አትሳቅ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን፣ ነገርህን በልክ፣ ቃልህን በጣዕም፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው። 🖋 እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ። 🖋 ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም። 🖋 በዓላማ ኑር፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ። 🖋 የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ነገ ከመምጣቱ በፊት ቀድመህ አስብ ። 🌹@Yewqetabugida67🌷
Показать все...