cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

🌹firdews islamic gallery 🌹

🌱قال رسولﷲ صلیﷲ عليه وسلم (( الدنيا سجن المؤمن وجنۃ الكافر))🌱 📚رواه مسلم 🥀የአሏህ መልዕክተኛ ሰለሏሁ አለይሒ ወሰለም እንዲህ ብለዋል ፡- ❗️ዱኒያ ለሙዕሚኖች እስር ቤት ናት፡ ለካፊሮች ደግሞ ጀነት ነች፡፡ 🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱 ሀሳብ አስተያየት ካለዎት⤵️ @firdews_bot

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
622
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

#አላገባምተውኩት!! ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ትዳር ልመሰርት አስቤ ነበረ፡ በቃ ሰርዣለሁ ተውኩት መና ቀረ፡ ጥምረቴ ከሆነ አሰልች ስብሰባ፡ ጭቅጭቅ ንዝንዝ ጧት ማታ ትረባ፡ ክፉ ፊት ካየሁኝ ስወጣ ስገባ፡ ምላሷ ከጠቃኝ እንደ ጃርት ወለባ፡ በቅፅበት ከረገፍኩ እንደ አደይ አበባ፡ ትዳር ምርቱ ጠፍቶ ከሆነ ገለባ፡ በብቸኝነቴ ዘንቸ እኖራለሁ፡ አላገባም እኔ በቃ ትቸዋለሁ፡ ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ በትዳር ህይወት ውስጥ ግልፅነት ከሌለ፡ በአብሮነታችን ውስጥ እምነት ከጎደለ፡ አጥፊ ከጥፋቱ ካልተስተካከለ፡ እንደዚህ እያለ ህይወት ከቀጠለ፡ ፍቅራችን ተረስቶ ጥላቻን አግዝፈን፡ መተሳሰብ ቀርቶ ጥቁር ታሪክ ፅፈን፡ በትንሽ ትልቁ ንዝንዝን ለምደን፡ ጭካኔን አስርፆ ልባችን ሆኖ ደን፡ የሁቡን ጎዳና ሸይጧን ከጋረደን፡ እንደዚህ ከሆነ የትዳር ጎዳና፡ የአእምሮ ውጋት መጥፎ ፍልስፍና፡ ከስህተት ካልተማርን ከጠፋ ምክክር፡ ዘወትር ጧት ማታ ከሆነ ክርክር፡ በቁርስም በምሳ ጥላቻን ስንዘክር፡ በሀሳብ ስጨነቅ በጭንቀት ስዳክር፡ ከትንሽ ትልቁ ከሁሉም ብግባባም፡ እንደዚህ ከሆነ ወላሒ አላገባም፡ በለጋው እድሜዬ ሀሳብ ከሚቀጣኝ፡ ይቅርብኝ ትዳሩ ምነው ምን በወጣኝ፡ ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ይህን አይነት ህይወት ከቶ አልፈልገውም፡ አላህ ይጠብቀኝ እኔ አልሞክረውም፡ የቁጭትን ሙሾ ዘውትር እንዳልቀኝ፡ ከጭቅጭቅ ትዳር አሏህ ይጠብቀኝ፡ ቅመም የለም ብላ ነገር ከምትገጥም፡ መልኳ ከሚያስጠላ ከላሟ ከማይጥም፡ አንድ ስህተት ነክሳ ከምትቆረጥም፡ እንደዚህ ከሆነ ትዳርን አልመርጥም፡ ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ካገባሁ በኋላ ካላገኘሁ ፍቅር፡ ወላሒ አላገባም አልፈልግም ይቅር፡ መውለድም አልሻ ሁሉም ይበል ጥንቅር፡ ነገር ከምትጠባው ተስባ እንደ ዘንዶ፡ ራዕይ ከሌላት ከሆነች በረዶ፡ ከንደዚች አይነቷ ጨቅጫቃ ተወልዶ፡ በንዝንዝ አድጎ ለማን ምን ሊጠቅም፡ ማግባቱ ይቅርብኝ በትዳር አልፀድቅም፡ ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ በርሷ መጥፎ ፀባይ ጓደኛ ከሸሸኝ፡ ሰው በመጣ ቁጥር ጭንቀት እኔን ካሸኝ፡ ከስሜት ስብራት ሁሌም ላላገግም፡ ይቅርብኝ ማግባቱ ተውኩት አልፈልግም፡ ከሱና ወንድሜ ፍቅር እየዘመርኩ፡ መንሀጀን በደሊል ሁሌ እየመረመርኩ፡ ራሴን በራሴ እኔው አጋብቼ፡ ሰላም እኖራለሁ ሁሉን ነገር ትቼ፡ አልጨቃጨቅም ትዳርን መስርቼ፡ እብድማ አልባልም አእምሮየን ስቼ፡ ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ረጂም እቅደን ባጭሩ ሰረዝኩት፡ ብዙ ጊዜ አጥፍቼ ለልቤ አማከርኩት፡ ከዚያም ውሳኔየን ለአካሌ ነገርኩት፡ ከመላ አካሌ ጋር እኔው አፀደኩት፡ አያስፈልገኝም ብዙ ጊዜ አሰብኩት፡ እየተሸማቀቅኩ ምኑን ኑሮ ኖርኩት፡ ምድርን ከምጭር ጧት ማታ እንደኩኩት፡ ትዳር ይህ ከሆነ አላገባም ተውኩት፡ ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ በኑረዲን አል አረቢ 2014 ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ http://t.me/nuredinal_arebi http://t.me/nuredinal_arebi http://t.me/nuredinal_arebi ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
Показать все...
شـبـاب السـلـــفــــيــــيــن

#ሰለፍያ_ቀጥተኛ_የሀቅ_መንገድ_ብሎም_አይነኬ_ፅኑ_ተራራ_ነው ለአስተያዬትና እርማት @Nuredin_al_arebi_Bot

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ የፍቅር አስከ ጀነት ቤተሰቦቺ ዛሬ በተለየ መልኩ ወደ እናንተ መተናል ወሎ ላይ እንደሚታወቀው ለወራት ያክል ጦርነት ሲካሀድ ቆይቶል በዚህ የተነሳ የብዙ ሙስሊም ወንድምና እህቶቻቺን ቤተሰቦቺ ሙሉ ለሙሉ ንብረታቸው ተዘርፎባቸው ለማረፊያ እንኳን የሚሆን ነገር የላቸውም በዛ ላይ ኑሮ ውድነት አለ ፡፡ ከዛ አልፎ በዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ልጆቻቸውን መርዳት አልቻሉም ሰለዚህም እነዚህ በዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ሙስሊም ወንድምና እህቶቻቺንን ተቸግረው ነው ያሉት፡፡ ሴቶቺ ራሳቸውን የሚጠብቁበት ሞዲየስ እንኳን መግዛት አልቻሉም ሴት የሆነ በደንብ ያቀዋል ብየ አስባለሁ ምን ያክል እንደሚቸገሩ ፡፡ የቻልኩትን ያክል አስከ አሁን ለመርዳት ጥረት እያደረኩ ቢሆንም ተጨማሪ ሰው አስፈልጎኛል ፡፡ ሰለዚህም እነዚህን ሙስሊም ወንድምና እህቶቻቺን ባለቺን እንተባበራቸው ስል ጥሪየን አቀርባለሁ ፡፡ ለመርዳት ያሰባቺሁ ከታቺ ባለው ሊንክ አናግሩኘ 👇 @sundus_mediabot 👆 አላህ ሰጭዎቺን ይስጣቸው ይዘንላቸው አሚን !! አላህ ሱብሀነ ወተአላ ምን ይለናል ፡- وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ምጽዋትንም ስጡ፡፡ መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ ለእናንተ ሊታዘንላችሁ ይከጀላልና፡፡ ሼር አድርጉ መልካምነት ለራስ ነው ፡፡
Показать все...
, #አላፊዋ_ዱንያ ! ~~~~~~~~~~~~~~~~ አይ የዱንያ ነገር በጣም ይገርምሀል ትልቅ ትንሽ ክስተት ሥንቱ ታይቶ ያልፋል ሁሉም እንደ ቧልታ ያለፈ ይሆናል ደስታና ጭንቀቱ ለቅፅበት ይረሳል የትናንት አይመስልም ጌዜያት ያስቆጥራል / ደግሞ ሌላ ታሪክ ይመጣና እንደ አድሥ ከፊቱ የሚሻል ወይንም የሚብሥ በደሥታ የሚያሥቅ ወይም የሚያሥለቅሥ ወይ ራስ የሚመልጥ ወይ አንጀት የሚያርሥ ባጭር የሚያቋርጥ ወይ ምኞት የሚያደርሥ / #ያም_አለ #ያም_ሆነ ተከናውኖ ያልፋል #መልካም_ሥራ #መጥፎ ሁለቱ ይቀራል አሏህ በጥበቡ ፅፎ ያስቀምጣል እኩልኛው ሚዛን ያዛኔ ይቀርባል ሁሉም በየ ሥራው ዋጋውን ያገኛል / ታድያ ለዚህ ሂዎት ለሆነ ትርምስምሥ ይዞን ለሚጋልብ እንደ ሜዳ ፈረሥ ኋላን ሥናበጃጅ ፊት ለሚገሰግሥ በሩጫ ላይ ያለን ጥሎ ለሚያሥነክሥ ሥለዚህ መንቃት ነው ቀንጣጤ በመንከስ መፋዘዝ አይሻም መሞቻ ቀን ድረሥ ቶሎ መፍጠን ይሻል ወደ አሏህ መመለሥ ________________________ © https://t.me/FKR_ESKE_JENET
Показать все...
ፍቅር አስከ ጀነት

ሀላሌ ነሺ አሉ !! ከወንዶቹ ሁሉ አይንሺ ለኔ አድልቶ ልብሽ ከወደደኝ ሁሉን ነገር ትቶ ወላጅም ከሰጠ ሽማግሌ መጥቶ ኒካህ ከታሰረ ሁሉም ተመቻችቶ ልቤም ይረጋጋል ያሰብኩት ተሞልቶ፡፡ በዚህ ቻናል የሚለቀቁ ማንኛውም ጰሁፋ ሀላሎቺን የሚወክል በመሆኑ ጰሁፎቹን ሀራም ላይ ባለመጠቀም ከወንጀል ራስወን ይጠብቁ (ለባለ ትዳሮቺ ብቻ ነው ፡፡) ለአስታያየትዋ ☞ @Fkr_Eske_Jenet_bot

sticker.webp0.21 KB
የዘመናችን ነሺዳህ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 31፥6 ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْتَرِي لَهْوَ الْحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًا ۚ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ የዘመናችን ነሺዳህ በሙዚቃ እና በመሳሪያ የታጀቡ እንጉርጉሮ ነው፥ ዘፈን ሙዚቃ፣ የሙዚቃ መሳሪያ እና እንጉርጉሮ የታጀበት ስለሆነ ከሸይጧን ነው፦ 31፥6 ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት ”አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ”፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْتَرِي لَهْوَ الْحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًا ۚ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 31፥6 “ኢብኑ መሥዑድ እንደተናገረው፦ *”ከሰዎችም ከአላህ መንገድ ሊያሳስት ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ” የሚለው ወሏሂ እርሱ “ዘፈን” ነው”*። كما قال ابن مسعود في قوله تعالى : ( ومن الناس من يشتري لهو الحديث ) قال : هو – والله – الغناء . “ለህወል ሐዲስ” لَهْوَ الْحَدِيث ማለትም “አታላይ ወሬ” ማለት ሲሆን “ጊናእ” ነው፥ “ጊናእ” غِنَاء የሚለው ቃል “ገና” غَنَّى‎ ማለትም “ዘፈነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ዘፈን” ማለት ነው። አምላካችን አላህ ኢብሊሥ የሚከተሉትን በድምጹ እንደሚያታልላቸው ተናግሯል። ይህም ድምጹ መደበሪያ፣ ዘፈን፣ ላግጣ እና ስላቅ ነው፦ 17፥64 *ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል*፡፡ وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 17፥64 *”ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል” የተባለው እርሱ ዘፈን ነው፥ ሙጃሒድም አለ፦ “ድምጽ የተባለው መደበሪያ፣ ዘፈን፣ ላግጣና ስላቅ ነው”*። واستفزز من استطعت منهم بصوتك قيل هو الغناء قال مجاهد باللهو والغناء أي استخفهم بذلك "ሐላል” حَلَال ማለት “የተፈቀደ” ማለት ሲሆን “ሐራም” حَرَام ማለት “የተከለከለ” ማለት ነው። ዝሙት እና አስካሪ መጠጥ ሐራም እንደሆነ ሁሉ ሙዚቃም ከዝሙት እና ከአስካሪ መጠጥ ጋር ተያይዞ ክልክል መሆኑ በነቢያችን”ﷺ” ሐዲስ ተነግሯል፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 16 አቡ ዐሚር ወይም አቡ ማሊኩል አሽዐሪይ እንደተረከው፦ “ወሏሂ አልዋሸውም! ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦ *”ከኡመቴ ውስጥ ጥቂት ሰዎች ለራሳቸው ዝሙትን፣ ሐር ልብስን፣ አስካሪ መጠጥን እና የሙዚቃ መሣሪያ ሐላል የሚያደርጉ ይሆናሉ”*። قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو عَامِرٍ ـ أَوْ أَبُو مَالِكٍ ـ الأَشْعَرِيُّ وَاللَّهِ مَا كَذَبَنِي سَمِعَ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ “‏ لَيَكُونَنَّ مِنْ أُمَّتِي أَقْوَامٌ يَسْتَحِلُّونَ الْحِرَ وَالْحَرِيرَ وَالْخَمْرَ وَالْمَعَازِفَ የዘመናችን ነሺዳህ ከፕሮቴስታንት መዝሙር የተኮረጀ ፈሣድ ነው፥ ትተን የመጣነው የጴንጤ እምነት ትዝ ያስብሉኛል። ዜማው፣ የሙዚቃ መሣሪያው እና ጭፈራው ምንም ልዩነት የለውም፥ ከዚህ ፈሣድ እራሳችንን መጠበቅ አለብን። አሏህ በሙዚቃ መሣሪያ የሚነሽዱትን ሰዎች ሂዳያህ ይስጣቸው! አሚን። "ይህ ፈሣድ መጋለጥ አለበት፥ ለሌሎች ሠበቡል ሂዳያህ ይሆናል" ካላችሁ እንግዲያውስ ሼር ማድረግ ግድ ይላል። 🔗SHARE 🔗SHARE https://t.me/thegoldenss
Показать все...
🌹የረሱልصلیﷲ عليه وسلمወዳጆች 🌹

በገዛ ሃገርህ እንደ እንግዳ ኣትኑር እኛ እኮ ፅድት ያልን የቢላል ዘሮች እኮ ነን

sticker.webp0.21 KB
ውሸታሟ ጉንዳን 🍗🍗🍗🍗🍗 አስገራሚ ታሪክ 🥕ኢማሙ ኢብኑል ቀይም, በአንድ ወቅት ከአንድ ዛፍ ስር ተቀምጠው ሳሉ ያዩትን ድንቅ ታሪክ ሚፍታሑ ዳሪ ሰዓዳህ በተሰኘው ድንቅ መጽሐፋቸው እንደሚከተለው አስፍረውታል። 🥕አንዲት ጉንዳን እርሳቸው ካሉበት ዛፍ አቅራቢያ የአንበጣ ክንፍ ታገኝና ለመሸከም በጣም ተጣጥራ ሞክራ ሞክራ ሲያቅታት ወደ ጉንዳኖቹ መኖሪያ ጉድጓድ በማቅናት ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ጉንዳኖቹ በሰልፍ አስከትላ ክንፉ ወደ ሚገኝበት ስፍራ አመጣቻቸው። 🥕አሏህ ስለእውነታው ይበልጡን ያውቃል ለጉንደኖች ሁኔታውን ነግራቸው በሰልፍ ወደ ክንፉ እንዲመጡ ያዘመተቻቸው ነው የሚመስለው። 🥕መንጋው ወደ አንበጣው ክንፍ ሲቃረብ ሸይኩ ክንፉን ያነሱታል። ጉንዳኖቹ ክንፉን ፍለጋ ተራውጠው ሲያጡት ወደ መጡበት ጉድጓድ ይመለሳሉ ። አንዷ ጉንዳን ብቻ በስፍራው ቀርታ ያንን ያየችውን የአንበጣውን ክንፍ መፈለጓን ትቀጥላለች !! 🥕 ኢብኑል ቀይም ረሒመሁሏሁ ክንፉን በመመለስ ቦታው ሲያስቀምጡላት በፍጥነት ወደ መንጋዋ ትሄዳለች ። መንጋው አሁንም እንደ መጀመሪያው በመመትመም በሰልፍ ሲመጣ ሸይኩ መልሰው የአንበጣውን ክንፍ ያነሱታል። መንጋውም እንደመጀመሪያው ለፍለጋ ተበታትኖ የተባለውን የአንበጣ ክንፍ ፈልጎ ያጣዋል። ሲያጡትም ወደ ጉድጓዳቸው አሁንም ተመልሰው ይሄዳሉ። 🥕 አንዷ ጉንዳን ግና አሁንም አልተመለሰችም በአካባቢው ሆና ያንን በእርግጠኝነት አይታው የነበረውን የአንበጣ ክንፍ መፈለጓን ቀጠለች ሸይኩ መልሰው ለሶስተኛ ጊዜ ሲያስቀምጡላት ተንደርድራ በመሄድ አሁንም ለመንጋው መገኘቱን ትነግራቸዋለች መንጋውም ተግተልትሎ መጣ። 🥕 በአቅራቢያው ሲደርስ ሸይኩ መልሰው አነሱት። አሁንም ፈልገው ሲያጡት መንጋው በሙሉ ተረባርቦባት በመክበብ አንገቷን ቀንጠሰው ገድለዋት። ወደ ጉርጓዳቸው ተመልሰው ሲሄዱ ሸይኩ የአንበጣውን ክንፍ መንጋው ላይ ወረውርኩት ይላሉ። 🥕ክንፉን እንደተመለከቱት ውስጣቸው በሐዘን የተነካ ይመስላል በፍጥነት እየተጣደፉ አንገቷን ወደ ቀነጠሷት ጉንዳን ተመልሰው ዙሪያዋን በመክበብ በስፍራው ለሰዓታት ቆሙ። 🥕 በጣም ተገርመው ሸይኩ ይህን እውነታ ለመምህራቸው ለሸይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ ረሒመሁሙሏሁ ሄደው ሲያወጓቸው 🥕"ሱብሐነሏህ ጥራት ለአሏህ ይገባው ያ ነፍሳትን እንኳን የውሸትን አስነዋሪነትና አጸያፊነት ያሳወቀ አምላክ !!" ካሉ በኋላ •🥕ይህን ዓይነት ግፍ በመስራትክ አሏህ ይማርክ ዳግመኛ እንዲህ ዓይነቱ ስራ እንዳይለመድክ !!" ብለው ገሰጿቸው። ይባላል። https://t.me/thegoldenss

Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.