ru
Feedback
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

Открыть в Telegram

💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።

Больше
9 048
Подписчики
Нет данных24 часа
+317 дней
-6630 день
Архив постов
#تلاوة ما تيسر من سورة طه 🍃🌺

🔹 تجد كثير من النّاس يعرف أشياء كثيره الا دينه !. 🎙الشيخ عبدالرزاق البدر وفقه الله تعالى

ኢላሂ!!    ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር መታመሙን ስሰማ በጣም አዘንኩ ተጨነቅኩም። ትላንት ስልክ ደውየ ድምፁን ስሰማው ብረጋጋም ጉዳቱ የደሰበት የሰውነት ክፍል spinal cord ጋ መሆኑን ሲነግረኝ ግን በሃሳብ ተዋጥኩ። የጀርባ አጥንት ጉዳት አላህ ያቅልለት እንጅ ክፉ ቦታ ነው። የጉዳቱ ደረጃ ከፍ ካለ ሰውነት paralyzed ሁሉ ሊያደርግ ይችላል። ኢላሂ በሰፊው እዝነትህ ይሁንብህ ኡስታዛችንን አንተው አሽርልን። ሀኪም ቤት ሂዶ እንደነበርና ወደፊትም ቀጠሮ እንዳለው አሳውቆኛል። እናማ የሱና ቤተሰቦች ከልባቹህ ዱዓ አድርጉለት። ኢብኑ ሙነወር ማለት አንድ ግለሰብ ሳይሆን እስካፍንጫው የታጠቀ ሙሉ ክፍለ-ጦር ነው። በአቅሙ ልክ በሙሉ ፅናት ለሱና ዘብ ቁሞ ቢድዓና የቢድዓ ሰዎችን አንገት ሲያስደፋ የኖረ ጀግናችን ነው። እኛ ሰዎች ስንባል የተሰጠንን ፀጋ ታላቅነት የምንረዳው ስናጣው ስለሆነ እንጅ በአለንበት የፊትና ዘመን እንደ ኢብኑ ሙነወር አይነት የተሰላ ሰይፍ ከመታደል በላይ ትልቅ ፀጋ የለም። ካስተዋላቹህ የእርሱ እና መሰሎቹ ከሚዲያ መራቅ ለቀናትም ቢሆን እንኳ ትልቅ ተፅዕኖ አለው። t.me/Abu_lmran_Alaseriy

የተለያዩ ውዥንብሮችና ብዥታዋችን ለማስወገድ ግልፅ ለማድረግ ያክል፡ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ከእንጨት [ከከበሊቶ] ላይ ወድቆ የጀርባ አጥንቱ ላይ ጉዳት ደርሶበታል። ጉዳቱ መንቀሳቀስ ሀታ በመኝታ መገለባበጥ እስከማይችል ድረስ ነው ያደረገው። አሁን የተወሰኑ መሻሻሎች አልሉት። የአጥንትና የነርቭ ህክምና እየተከታተለ ነው። የቻለና ቤቱን የሚያውቅ በአካል ይዘይረው፡ ዋናው ለሱ የሚጠቅመው ግን ከልባችን የምናደርግለት ዱዓእ ነው። በተረፈ አቤት ሆስፒታል ውስጥ የሚሰራ የነርቭ ስፔሻሊስት የሚያውቅ ሰው ካለ በ @YunusHassen ያናግረኝ። جزاكم الله خيراً.

~አንዲት ሴት አለች… እራሷን እየጠበቀች ለማይገባት ሰው ልትዳር የምትታጭ። አንዲት ሴት አለች ከማግባት የበለጠ ሊያገቧት የፈለጓት የሚያስፈራት። አንዲት ሴት አለች ብን ብላ ከቤተሰቦቿ መለየት ፈልጋ ሀያዕ ይዟት የተቀመጠች። አንዲት ሴት አለች በልጅነቷ ጥቃት ደርሶባት ለማንም ትንፍሽ ሳትል ኖራ በቤተሰብ በኩል ትዳር ሲመጣላት የምትበረግግ። አንዲት ሴት አለች ከገላዋ በቀር ምንም መስጠት የማትችልበት ሁኔታ ላይ ያለች። አንዲት ሴት አለች ልጅ አምሯታል፣ እናት መሆንን አጥብቃ ትፈልጋለች ግና ለልጇ አባት ለሷ ባል የሚሆናትን ትክክለኛው ሰው እስከሚመጣ ድረስ ስለምትጠብቅ የሆነ የደበቀችው ነውር አለባት ተብላ የምትታማ። ~ አንድ ወንድ አለ ከስሜቱ ጋር እየታገለ የሚኖር፣ ትዳር ፈልጎ ትዳር የተወደደበት። አንድ ወንድ አለ የሚረዳው ያላገኘ፣ ልፋ ብቻ የሚል ፍርድ የተፈረደበት። አንድ ወንድ አለ ልቡ ተሰብሮ ምንም እንዳልሆነ ጠንክሮ የሚንቀሳቀስ። አንድ ወንድ አለ ከዘመድ መጠጋት፣ ከሰው መቀላቀል የሚያስፈራው፣ እራሱን ለሁሉም ኃላፊነት በታትኖ ለራሱ መሆን ያቃተው። አንድ ወንድ አለ እናት እና ሚስት መሆን የምትችል ሴት የሚፈልግ፣ የልጆቹን እናት በጥንቃቄ የሚመርጥ። አንድ ወንድ አለ የሚወደውን ሰው ክብር ስለሚጠብቅ ሞኝ የተሰኘ፣ ድንበር አልፎ ስለማይባልግ ፈሪ የተባለ። አንድ ወንድ አለ ጉዳዮቹን ለራሱ መስጥሮ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈፀም ደፋ ቀና የሚል። አንድ ወንድ አለ ኃላፊነቶቹ ያጎበጡት፣ የሚንከባከባቸው ነፍሶች በዝተው የራሱን ነፍስ የረሳ አንድ ወንድ አለ። ስለ ሰዎች የልብ ጉዳይ በእርግጠኝነት በፍፁም አታውቁም። ሁሉም የራሱ ቁስልና ህመም አለው። ቆሞ የሄደ ሁሉ ደስተኛ አይደለም። በበሽታ የሚማቅቅ ሁሉም አልከፋውም። የተቆነጀ ሁሉም ያማረ ታሪክ የለውም። አስጠሊታ የተባለ ሁሉም ቆንጆ ታሪክ የለውም ማለት አይደለም። ስለ ሰዎች የውስጥ ትግል አታውቁምና አጓጉል አትፍረዱ።… t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan

الحمدُ للهِ الَّذي بِنعمَتِه تَتمُّ الصَّالحاتُ . አልሐምዱሊላህ! በፀጋው መልካም ነገሮች ሁሉ ይሳካሉ፡፡ ~

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ገባ ገባ በሉ ደርስ ሊጀመር ነዉ

🍂  إِنَّ ٱلَّذِینَ یَتۡلُونَ كِتَـٰبَ ٱللَّهِ 🍂 🎙  القارئ #عبدالرحمن_الحسينان

ከትክክለኛው መልስ ጀርባ ጠቃሚ ነገር አለ ጥያቄ1,  አላህ የት ነው??🌷

«ከኒካህ በፊት ያለ የፍቅር ቅዠት ማእከላዊ እስር ቤት ሲሆን ከኒካህ በኋላ ያለው ንፁህ ፍቅር ግን ምድራዊ ጀነት ነው።!! በተለይ ዲን እና አኽላቅን መስፈርት በማድረግ ላይ የተመሰረተ ትዳር ከሆነ ኒዕመል መታዕ...

የሰው ልጅ በህይወቱ ያሳለፋቸውን ከባባድ የጭንቀት እና የችግር ቀናት ሊረሳ ይችላል። በችግሩ ጊዜ ፊቱን ያዞረበትን ሰው እና በችግሩ ጊዜ አይዞህ ያለውን ባለውለታውን ግን አይረሳም።

🛑👉ኡስታዝ ሳዳት ከማል ሙአዝ ሀቢብን አስጠነቀቀ! አላህን ፍራ ነብዩን የሚወድ ከአስቴር አይኮርጅም ! የምንቃወመዉ በማስረጃ ነዉ! =

አስመሳይ አግብቼ ግራ ከምጋባ፣ ተደብቄ ልኑር ልቅር ሳላገባ። ተመሳሳይ ኮፒ በመቅረቷ አልባባም፣ እምነት አሰዳቢ ፍፁም አላገባም። የአላህን ትዕዛዝ ሂጃቧን አድርጋ፣ ከተጨማለቀች ከአጂነብይ ሰው ጋ፣ እሷን አላገባም ከቶ ቁሜ ልቅር፣ በብቻየ አለም ውስጥ ተደብቄ ልኑር። አቂዳየ እያለ ምን አለው ካለችኝ፣ እስልምናየን ይዤ ድሃ ካረገችኝ፣ መስፈርቷ ከሆነ ቤት ና መኪና፣ ኒቃቢስትም ብትሆን ብትሄድ ተሸፍና፣ ትቅርብኝ ይች ልጂ እኔ አላገባትም፣ ኪታቤን አዝየ ሄዳለሁ የትም። እውቀት ፍለጋየን አቀጣጥላለሁ፣ እምነት አሰዳቢ ለምን አገባለሁ። ጀግና የጀግና ልጂ በመንሀጂ ያደገች፣ በሰለፎች አሰር አምራ የደመቀች፣ አላህ ከገጠመኝ ውብ ትዳር ፈላጊ፣ አስተዋይ መካሪ ንደት አረጋጊ፣ የሙብተዲ ጥላት ጦረኛ ተዋጊ፣ ሽርክን አፈራራሽ የተውሂድ ምርኮኛ፣ የቢድአ ካንሰር የሱና ሱሰኛ፣ እምነቷ ሲደፈር የሚያንዘረዝራት፣ ከእግር እስከ ራሷ ንደት የሚወራት፣ በአቂዳዋ ታጋይ ጀግና አርቆ አሳቢ፣ የእህቶቿ ሞደል በሂጃብ ተዋቢ፣ ከመጥፎ ከልክላ በመልካም ላይ አዛዢ፣ ውድ ባልተቤቷን በፍቅር አደንዛዢ። ለረጂሙ ጉዞ ስንቋን የሰነቀች፣ በተውሂድ በሱና በሀቅ የደመቀች። ከመንሀጀ ሰለፍ ሁሌ የማትለወጥ፣ ያወራ ቢያወራ ልቧን የማትሰጥ። ይህችን መሳይ ሞደል ታስፈልገኛለች፣ እህትም ፣ባልተቤት እናት ትሆናለች። ችግሩ እሷ ግን የት አለች የት አለች፣ ልፈልግ በዱኣ ከአላህ ተስፋ አልቆርጥም፣ እምነት አሰዳቢ አልለማመጥም፣ ተውሂድ ያልገባት ልጂ አርፋ አትቀመጥም። ያ አላህ እኔንም አድርገኝ ከነጓደኞቼ፣ ቀጥ ብየ የምሄድ አንተኑ ፈርቼ። ሀቅ የምገልፅበት ስጠኝ እምቅ ወኔ፣ ተውሂድ ላስተምረው ይጠቀም ወገኔ። ጀግናይቱ የት አለች ለባሽ ጥቁር ካባ፣ ብቸኝነት ይብቃኝ አትፈትነኝ ላግባ   ✍ከወንዶቹ  መንደር

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ “ከሰባት አጥፊ ወንጀሎች ራቁ። አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!  እነሱ እነማን ናቸው ብለው ሶሃቦች ጠየቁ፦ ❶ /‘ሺርክ’ በአላህ ላይ ማጋራት፣ ❷/ድግምት፣ ❸/ ያለ አግባብ አላህ እርም ያደረገውን የሰዎች ነፍስ ማጥፋት፣ ❹‘/አራጣ’ ወለድ መብላት፣ ❺ /‘የቲምን’ የሙትን ልጅ ገንዘብ መብላት፣ ❻/ከተፋፋመ ውጊያ ወደ ኋላ ማፈግፈግ፣ ❼ /ጥብቅ የሆኑ ሙስሊም ሴቶችን በዝሙት ማጉደፍ ናቸው።” Ergamaan Rabbii (صلى الله عليه وسلم) akkana jedhan: “Dilii balleessituu torba irraa fagaadhu Yaa Ergamaa Rabbii Sahaabonni ni gaafatan: Maal isaan: ❶ /‘Shirk’ (Rabbiin shariika gochuu), . ❷/.sihrii'. ❸/ Nama Rabbiin dhoowwe haqa malee ajjeesuu, . ❹/Araaxaa' dhala nyaachuu ❺/Maallaqa yatiima nyaachuu, . ❻/Lola irraa duubatti deebi'uu, . ❼/Dubartoota Musliimaa qulqullootaa irratti zinaa hujjachuu.” 🌐 https://t.me/ASTU_MSJ

ሴቶች እህቶቻችን ሆይ ፡- በየ ሶሻል ሚዲያው አግቡን አጋቡን በማለት ራሳችሁን አታርክሱ ! አሏህ ባዘዘው መንገድ ቀጥ በሉና በቀጥተኛ በር ለመግባት ሞክሩ ።  አሁን ያለችሁበት መንገድ በሰዎች ላይ ፈተና ከመፍጠርና እናንተን ከማርክስ ውጭ ሌላ ጥቅም የለውም ደሞም የ ዘራፊዎችና የ" ሞካሪዎች " ሲሳይ መሆናችሁን ብትጠነቀቁ ጥሩ ነው ! የተቆርቋሪ ወንድም ምክር አድርጋችሁ ብታስቡት መልካም ነው ! https://t.me/Muhammedsirage