cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የኦርቶዶክስ መዝሙሮች እና ጥቅሶች (pp)🙏🙏

የ ኦርቶዶክስ ጥቅሶች ብቻ⛪💒💒 እየሱስም። አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አይውቁምና ይቅር በላቸው አለ። ልብሱንም ተከፋፍለው እጣ ተጣጣሉበት።😭 🙏🙏🙏 የሉቃስ ወንጌ. 23:34

Больше
Не указана странаНе указан языкНе указана категория
Рекламные сообщения
364Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ወቀሳ ከብዶህ ባቆምስ ብለሀል? በጣም ለፍተህ እየሰራህ ባለህበት ሁኔታ ውስጥ ባለማወቅ ትንሽ ስህተት ብትፈጠርና በሷ ምክንያት ከፍተኛ ወቀሳ ቢደርስብህ ወቀሳው በጣም ያማል አይደል? ምክንያቱም አውቀህ አይደለም ያጠፋኸው ፣ ጥፋቱ በመከናወኑ አንተ ራስህ ከፍቶሀል በዚያ ላይ ደግሞ በጣም ወጥረህ ከልብህ እየሰራህ ነው ስለዚህ መወቀስ አይገባህም አይደል? ግን ሰው ነህና ሁሌ ትክክል አትሆንም ትሳሳታለህ፣ ሰዋች ይናደዱብሀል የደከምክበት ሁሉ ባዶ እንደሆነ አስኪሰማህ ድረስ ትደርሳለህ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ልትቆጣጠራቸው አትችልም ስለዚህ ወደምትቆጣጠረው አተኩር ስህተትህ ስላስተማረህ ነገር በልፋትህ ያገኘኸውን ውጤት ጥፋቶችኽን የምታስተካክልበትን ጥበብ ለማስተዋል ሞክር! ለምን እንዲህ ሆነብኝ አይገባኝም እኮ በሚል ጥቅም የለሽ ሀሳብ ጊዜህን አታባክን ወንድሜ አንተ ብቻ አይደለህም አለም ላይ ያለ ሰው በሙሉ ይሄ ነገር ያጋጥመዋል ታድያ ግን ልዩነቱ ሁሉም የሚቀበሉበት መንገድ ነው! መልካም ቀን ተመኘን 🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ ☺️
Показать все...
Показать все...
የዘማሪ አብርሃም ተገኔ/Zemari Abraham Tegene የጉዞ ላይ አስደናቂ ዝማሪዎች ከከተማው ወጣጣቶች ጋር: Timeket/Ketera/ kanazegelila

ዛሬም ሌላ ልዩ ቀን በባሌ ጎባ ጥር 13 ቀን 2014 ዓ.ም የእግዚአብሔር አብን የቃል ኪዳን ታቦት ስናስገባ የነበረውን ልዩ ደስታ ተመልከቱልኝ።በእውነት ገና ትደመማላችሁ እናንተ ብቻ ሰብስክራይብ ላይክና ሼር እያደረጋችሁ መከታተሉን አትዘንጉ።

እንዳሰብነው ባይ ሆን እንኻን እንዳሰበልን አኑሮናል ከዘመን ዘመን አድርሶናል መጪውንም እሱ አብሮን ይሁን 😍 ፈጣሪ 🙇🏽 ይህቺ የጳግሜ ቀናት የይቅርታ እና የምስጋና ቀናት ናቸው ስለሆነም ❣ሳላውቅ በስህተት❤ 💙አውቄ በእህል💔 አስቀይሜ አሳዝኜ አስከፍቼ 💜ከሆነ ከጉልበቴ በርከክ ብዬ💗 💞ይ 💞ቅ 💞ር 💞ታ ጠይቃለው💕 🖤በችግሬ በሃዘኔ ስከፋ ተከፋታችው ሳዝን አዝናችው💘 💖በደስታዬ ተደስታችው ሃሳቤን በመካፈል መፍትሄ ለሰጣችውኝ❣ 💚ስሜታዊ ሆኜም 💙መታግስትን ላስተማራችውኝ💜💗 💖💕💞በዙሪያየ 💓💗💖ያላችው 💙💜❤ሁሉ 💝አ 💝መ 💝ሰ 💝ግ 💝ና 💝ለ 💝ው ❣💝💕💞💓💗 መልካም አዲስ አመት 🌻🌻🌻🌻💐💐💐🌼🌼🌼ላንተ/ቺ ይሁንላችሁ ለጓደኞቻቹ ኣድርሱ እኔም🙋🙌 ከነዛ ውስጥ ከሆንኩ forward ኣድሩጉልኝ😙💕💕💕💕💕💕💕💕💕
Показать все...
"እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ" ዕብ 11:13 ዛሬ ማለዳ ወደ ፌስ ቡክ መንደር ጎራ ስል መጀመሪያ ያየሁት የወንድሜን የመምህሬን የትጉሁን አገልጋይ የመጋቤ ሐዲስ አስራት አያንሳ ዜና እረፍትን ነበር። በእውነት ካለው የአገልግሎት ፍቅር ከነበረው ትጋት በተለይ ክፍለ ሀገር ላይ ከከተማ እስከ ገጠሪቱ አንዲት ቤተክርስቲያን የነበረው ወንጌልን ለሕዝብ ሁሉ የማድረስን ተልዕኮ ስለማውቅ ቤተክርስቲያን ድምጿ ሚሰማበት ወንጌልን የምታዳርስበት አንዱንና ምርጡን የክርስቶስ አገልጋይ ማጣቷን ስረዳ አዘንኩ። ሆኖም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አምነውና አገልግለው ስላለፉት ቅዱሳን ምስክርነት በሰጠበት ኃይለ ቃል "እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ" ያለውን እያሰብኩ ተጽናናው። ወንድሜ አስራት እንዳመነ : ክርስቶስን እንደገለጠ : እንዳገለገለ ሞተ!!! ምን መታደል ነው እንዳመኑ እንዳገለገሉ መሞት??? እንዴ እየሰረቁም መሞት እየገደሉም መሞት እንደካዱም መሞት አለ እኮ ጎበዝ! ስንቱ ከነኃጢአቱ ከነበደሉ ሊሞት ወረፋ እየተጠባበቀ ይሆን? ስንቱ እንደካደ ሊሞት ተራውን እየጠበቀ ይሆን? ቸሩ መድኃኔዓለም የወንድሜንስ ሞት ተመኘሁት ለንስሐ ሞት በቅቼ እንዳመንኩህ እያገለገልኩህ እየሰበኩህ ልሙት!!! ነፍስ ይማርልን! ለቤተሰቦቹና ለወዳጆቹ ሁሉ መጽናናትን ተመኘሁ! ለቤተክርስቲያንም ተተኪዎችን ያብዛልሽ አልሁ!!! ዲያቆን መሰለ ሞላ ከባሌ ጎባ
Показать все...
ብጹዕ አቡነ ሰላማ ዘባሌ በረከታቸው አይለየን!!!
Показать все...
ስለነበሩበት ገዳም ሲናገሩ ማኅበረ ሥላሴ ጥሬ በጸሐይ የሚበስልበት፡ የእንስሳ እንስት ፆታ እንኳ የማይገባበት፡ ላሞችና አንበሶች አብረው የሚኖሩበት ነው ራሳቸው ሲሉ ሰምቻለው።አቡነ ሰላማን የተከተሏቸው ብዙ መናንያን አሉ። በዚያ ጊዜ እርሳቸው በመሰረቱት ጎለ ብሕንሳ ገዳም ውስጥ የመነኮሱ ወጣንያን ዛሬ ብርቱ ብርቱ ዐሠረ ፍኖታቸውን የተከተሉ አባቶች (መነኮሳት) አሏቸው። በግሩም መምህርነታቸው የሚመስሏቸውንም አባቶችም ለማየት እድሉን አግኝቻለሁ (አባ ጌዴዎንን ) ። የመሰሉ አባቶችን። አሁን ሲያትል ያሉ አባት። ቦታውን ገዳሙን ለመርዳት የምትሹ አዲስ ቤተ ክርስቲያን እየተሰራ በመሆኑ ልታግዙ ትችላላችሁ። ሰላማ በሕይወት ዐሠረ  ፍሎታቸውን የተከተሉ ብዙ ልጆቸ አሏቸው። አክብረው ያስከበሩ። ፍጻሜያቸውን ያሳምርልን። አብዝተው መነኩሴ ይወዱ ነበር። አንድ ወቅት እጅግ ተቆጪ ተማቺ መነኩሴ ሥራ አስኪያጅ ነበራቸው(አባ ገብረ ሥላሴ) ። ከወረዳ ለሥራ ስመጣ ብፁዕነታቸው ቢሮአቸው ተቀምጬ ሳለ አንድ አባት ገብተው አባ ገብረ ሥላሴ (ሥራ አስኪያጁን) ባናግራቸው ሰዳቡኝ ውጣ ከፊቴ ዞር በል ከዚህ ብለው አባራሩኝ ብለው ለሰላማ ሲነግሯቸው አንገታቸውን አቀርቅረው “አይ እንደው አመክሮ ያልነካው ምንኩስና ይኽው እኮ ነው ችግሩ” ሲሉ ሰማኋቸው። ++ ትምህርታቸው ሰላማ እጅግ የሚያስገርም ስጦታቸው የማስተማር ዘያቸው እና ለማስተማር ያላቸው ፍቅር ነው። የመጀመሪያው አንድም ሁለትም ሰው ይኑር ያስተምራሉ። የሰው መሰብሰብ መብዛት ማነስ ጉዳያቸው አይደለም። ጠዋት በአዘቦት ኪዳን ላይ መጥተው ወንጌል ያስተምራሉ። ጎባ መድኅኔ ዓለም ጠዋት ከኪዳን በኋላ አጠር ያለ ትምህርት ይሰጣል። በዓል ሆኖ ለኪዳን ከመጡ ያስተምራሉ። ከጊኒር ስመጣ እንዳደረሰኝ እሳተፋለሁ። ርዕስ እዚያው መድረክ ላይ የሚሰጡ ይመስለኛል። አንድ ቀን በኪዳን ሰዓት ዕለቱ ሐሙስ ነበር ታድያ “ሐሙስ የቀን ቅዱስ” የሚለውን ትምሕርት ያስተማሩትን ከ 18 ዓመት በኋላ ዛሬም አስታውሳለሁ።       + ሁለተኛው አይረሴነቱ በዚህች ሚጢጢዮ ጽሑፌ ላይ ያስተዋልኩት አስተያያየት እንኳ ሰው ትምህርቱን ምክሩን አለመርሳቱ ነው። በቃ የሰላማ ትምህርት አይረሳም። ዘልቆ የሚገባ ዝናም ነው። ታዲያ ያለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታ ይኽ እንዴት ይሆናል። “አንተ ልጅ” የሁል ጊዜ ጥሪያቸው ናት። ዛሬ ከደቂቃ በፊት የተጣሩ እስኪመስል ድረስ ይሰማኛል። ድምጻቸው ልዩ በመሆኑ ፍንትው ብሎ ይሰማል። ትምህርታቸው በየትኛውም ዘመን ቢሆን ማስታወሻ ሳይያዝ እንኳ ከነድምጻቸው፣ ከነ ሰውነት እንቅስቃሴያቸው፣ ከነፈገግታቸው ምንም አይጠፋም። አይረሴ ነው። ሙቀት ፈጥሮ አስቆ የሚያልፍ ትምህርት የለም።   የሚያወጡት ቃላት ጥንካሬው በአንድ ወቅት የጎባ መድኅኔ ዓለም ሰንበት ትምህርት ቤት ዓመታዊ መጽሔት ላይ ይህንን ቃል ተጠይቀው ነበር። እነዚህን እያስተማሩ የሚናገሯቸው ንግግሮቸ ከየት ነው የሚያመጡት ተብለው። ዛሬ ሼክስፒር፣ ፕላቶ፣ አርስቶትል፣ አብርሃም ሊንከን …..ተናገሯቸው የምንለው ቃላት ይልቅ ሰላማ በትምህርታቸው ውስጥ እንደ ውሃ ያዝጎደጎዱታል።ንግግራቸው ሁሉ ልዩ ቃል አለው። ሰምተህ የምትሄደው ሳይሆን ተሸክመህ የምትኖረው ነው። በጎባ ተክለ ሃይማኖት ገዳሙ የታተመውን ታሪካቸውን የያዘ መጽሔት ፈልጎ ማንበበ ይሻላል በአጭሩ። +                                                በሁሉም ሰው ልክ ማስተማራቸው ሰላማ የሁሉንም ሰው ልክ ያውቁታል። ሕጻናት ሰንበት ትምህርት ቤት ገብተው ያስተምራሉ አምስቱ አዕማደ ሚስጢርን በ 30 ደቂቃ ሳይሞላ ያስተማሩንን ሳስብ ግርም እሰኛለሁ። በጥያቄ ይጀምራሉ እያሳሳቁ ቁም ነገሯን ይግታሉ። ለምሳሌ። ጥምቀት ማለት ምን ማለት ነው? ለምን እንጠመቃለን? ባንጠመቅ ምን እንሆናለን? ማነው ተጠመቁ ያለን? ለምን እንቆርባለን? ባልቆርብ ምን እንሆናለን? በፍጹም የማይረሳ ትልቅ መነሻ ማዕዘን ነው የሚመሰርቱት። ከዚያ በኋላ ምንም ብትማር ያንንው ነው የምታስፋፋው።   + የትምህርቱ ስሜት ሰላማ በትምህርት የሚያስለቅሱት ተናግረው ሳይሆን አልቅሰው ነው። ትዝታዬን ላጋራችሁ። ወርኅ ታኃሳስ ዓመተ ምሕረቱን እርግጠኛ አልሆንኩም በ90-92 ዓ.ም ይሆናል። እንዳንድ ሰዎች የይቀየሩልን ፊርማ ያሰባስባሉ። ቅዳሴ አልቆ ማስተማር ጀመሩ። የሳምንቱ መዝሙር “ብርሃን” ነበር። በትምህርት መካከል “የብርሃን ልጆች በጨለማ አይፈራረሙም፣ አያድሙም፣ አውቃለሁ ምንም እንዳልሰራሁ ለምን በዓት አጸና ነው የምትሉት? ለመነኩሴ ደግሞ ሥራው አጽንኦ በዓት ነው። ግድ የለም በፊርማ መቀየር ቢቻል እኔም ከናንተ ጋር ብፈርም ደስ ባለኝ ነበር”….. ሲሉ። ያ ሁሉ ቤተክርስቲያኒቱን የሞላው ሕዝብ በአንድነት ዕንባውን አረገፈው። ሰላማን የሚሰማ ሰው የሚያሳዝን ነገር የሚገልጡት በንግግር ቅላጼ በመሆኑ ሳታውቁት ታለቅሳላችሁ። ደስታም ከሆነ ገና ጥርሳቸውን ፍልቅ ሲያደርጉ ውስጥህ ይገባሉ። እንደ ማዕበል ወደ ሰማይም ወደ ምድርም ትጓዛለህ።ልባችን ድረስም በቁም ነገር ዓይን እንዳፈጠጠ ቅንድብ ሳይርገበገብ ትኩረት ይይዛሉ። ልብን በቁም ነገር ቀጥ ያደርጋሉ። በአንድ ወቅት መድኅኔ ዓለም በሠራተኛ ጉባኤ ላይ ሲያስተምሩ ከጀርመን እንደተመለሱ፦ የሀገራችንን ገበሬና የአውሮፓን ሰው ሲያነጻጽሩ “ የሀገራችን ገበሬ በጾም አንጀቱ በጠዋት ጠምዶ ሲያርስ ውሎ ማታ ይገባል። ፈረንጅ በጠዋት አንድ ቁና ዳቦ ጎርሶ ረፋዱ ላይ ያፋሽካል ” ይኽ ምን መሰላችሁ። ሀገሪቱ የረድኤት ናት፤ ሕዝቡ ሃይማኖተኛ ነዋ” ይሉ ነበር። ሮቤ መምህራን ማሰልጠኛ ላይም “ይኽንን አንዣቦ ቀላልቶ የመጣውን የአውሮፓ የክሕደት ደመና፤ በሃይማኖት ነፋስ ሰይፍ እያሳደድክ እየበተንክ እየበተንክ ወደ መጣበት መልሰው” እያሉ ሰንበት ተማሪውን ወጣቱን ቁጭት ይፈጥሩበት ነበር። አቤት ጥበብ። ጊኒር ለመጀመሪያ ጊዜ በ1985ዓ.ም. ወጣቶች በዝተው ሌሊቱን ሙሉ በቀድሞ ሰንበቴ ቤት አዳራሻችን ውስጥ ሲያስተምሩ ያደሩ ቀን እንዲህ አሉ፦”ከዚህ በፊት ስመጣ አዚህ ቦታ ማንቆርቆሪያ እና ኩባያ ጠላ እየተቀዳባቸው ቂጭል ቂጭል ይሉ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ የተዋሕዶ ወጣት ሞልቶት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያለ ሲዘምር ማየቴ በእውነት እጅግ ደስ ያሰኛል” ታዲያ በዚያ ሌሊት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሚለው መዝሙር እጅግ ለበርካታ ደቂቃዎች ያለማቋረጥ ተዘመረ። ++ መምህራንን፡ ሰባክያንን የሚያሰለጥኑበት መንገድ በእሳቸው ምኞት ሰንበት ተማሪ ሁሉ መምህር እንዲሆን ነው የሚሰሩት። ሁሌም ሰንበት ትምህርት ቤት መርሐ ግብር  ላይ ይሳተፋሉ። ሊያስተምሩ እንዳይመስላችሁ። እርሳቸው ተቀምጠው የተመደበው መምህር ያስተምራል። ያያሉ። ዓይናቸውን በጣታቸውን መካከል አድርገው በትኩረት ያያሉ። በሚያስቀው ይስቃሉ። አሜን ሲያሰኝ አሜን ይላሉ። በቃ በደንብ ይሰሙሃል። ሲሰሙህ በራሱ ይፈውሱሀል። ሲያልቅ ያሳርጋሉ ምክራቸውን ይሰጣሉ። ማስታኮት (የማት ጉባኤ) ይመጣሉ። መምህሩ ሲያስተምር ቁጭ ብለው ይሰማሉ። መምህር ስላችሁ የደብሩ አልያ ከአካባቢው ካህን፣ዲያቆን፣ አልያ ሰንበት ተማሪ ሊሆን ይችላል። የዛሬን የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ በጃቸው ያደጉ መምህራን ናቸው።
Показать все...
በመ/ር ንዋይ ካሳሁን      (አሜሪካ) ብፁዕ አቡነ ሰላማ ሰኔ 18 ቀን 1996 ዓ.ም.  ዕለት የእረፍታቸው  ነው። ማሳሰቢያ (ጳጳሳት በየትኛውም ቀን ይረፉ እንደ ሌላው ሙት አመት ቀናቸው በእለቱ አይታሰብም። ይልቁንም የሁሉም ያረፉ ጳጳሳት መታሰቢያ በመዝገበ ሙታን ተጽፎ በጥቅምት ወር ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከመጀመሩ ቀድሞ ያለው እሁድ የመታሰቢያ ስማቸው እየተጠራ ይታሰባሉ) ይኽንን ቀን ልጆቻቸው እናዘክረው በማለት ብቻ ነው። ብፁዕነታቸው ከጵጵስና በፊት መሪጌታ ሐዋዝ ወይም አባ ሐዋዝ ይባሉ ነበር።ሰሜን ሸዋ ሰላሌ አውራጃ ጎሐ ጽዮን ወረዳ በ1931 ዓ.ም. ተወለዱ። በአቅራቢያቸው ንባብን ዜማን ተማሩ። ከብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ዲቁናን ተቀበሉ። ከዚያም ቅኔን ከመምህር ጥበቡ ገሜ ተማሩ። የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ትልቅ ፍላጎት ስለነበራቸው ወደ ጎንደር አቅንተው ፋርጣና ጋይንት አካባቢዎች በመዘዋወር ቁም ዜማን አቋቋምን ተማሩ። በዚያው ጎንደር አቋቋምን አስመሰከሩ።ዐቢየ እግዚእ ቤተ ክርስቲያን በመሔድ ብሉይን ተማሩ። በ1961 ዓ.ም በመሔድ ማኅበረ ሥላሴ ገዳም ሔደው ምንከስናን ፈጸሙ። በ1964 ዓ.ም ቅስናን ተቀበሉ። በወቅቱ ወደ አዲስ አበባ ኮርስ እንዲወስዱ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ተልከው ሳሉ በየአድባራቱ እየተዘዋወሩ ወንጌል ሲሰብኩ የብዙዎችን ቀልብ ይስቡ ጀመር። (አቤት የሰላማ አንደበት) ማር ይፈልቅበት ነበር። ታድያ ቅድስት ማርያም አካባቢ ሰው እየሰበሰቡ ያስተምሩ ነበር። ድምጻቸው ቀጭን በጣም የምትስብ ናት። ታድያ ወዲያው ገነተ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆነው ተመደቡ። ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያንም አገልግለዋል። በዚያው ተያይዞ መናኝ መሆናቸውን ያዩ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ለኤጲስ ቆጶስነት በ1971 እጩ ሆነው በ1971 ብፁዕ አቡነ ሰላማ የባሌ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ ተብለው በሶስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ ተሾሙ። “ሰላማ እና ባሌ” ለኦርቶዶክሶች ሰላማ ማለት ባሌ፤ባሌ ማለት ሰላማ ማለት እስኪመስለን ድረስ አንነጣጥልም። ብዙ ቢጻፍ አያልቅም። ወደባሌ የመጡበት ወቅት አደገኛ የደርግ ዘመን ነበር ቢሆንም ሐዋርያ ሰው ይወዳሉ። ቄስ ጌጡን፣ መጋቤ ትፍስህት አንዳርጌ ዘውዴን ፣ ሊቀ ኅሩያን ሰርፀ አበበን የመሰሉ ትንታግ ሰባኬ ወንጌል ሥራ አስኪያጆችን አስይዘው ወጣቱን ያስተምሩ ጀመር። አቡነ ሰላማ ቢሮ የሚውሉበት ቀን ውሱን ነው። ገጠር ለገጠር እንደ ዞሩ ነው ያሳለፋት። እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየኋቸው ጊንር ከተማዋን ሊባርኩ ሲመጡ በታህሳስ ወር 1985 ሲሆን በዚያንው ጊዜ ዲቁናን ከእርሳቸው ተቀበልኩ። ሰላማ የሁሉም ሰው የሙስሊሙም የክርስቲያኑም አባት መሆናቸውን በቃልም በተግባርም የገለጡ የተራራ ላይ መቅረዝ ነበሩ። ማንንም በደረጃው ሳይንቁ አክብረው ማናገር ይችላሉ። በጣም ለካህን የሚያዝኑ አባት ነበሩ። ትምህርታቸው የማይስበው የማይማርከው ፍጥረት አልነበረም። ሰላማ የሰውን ጸጋ የመለየት ስጦታም አላቸው። ለምግብ ቅባት ነገር በአፋቸው አትዞርም። ዳቦና በደረቅ እንጀራ በበርበሬ፣ ጥሬ ሽንብራ ምግባቸው ሲሆን አጋንንት ገና ከቤት ሳይወጡ በያሉበት ይርድ ነበር። የመሠረቱትን ጎለ ብህንሳ ት የጻድቁን የተክለ ሃይማኖት ገዳሙን እጅግ ከመውደዳቸው የተነሳ ሁሌም ያዘወትራሉ። አዲስ አበባ እንኳ መጥተው ቤት ሳይገቡ ደብረ ሊባኖስ ሔደው ያድራሉ። ሰላማ ሌሊት እንቅልፍ የላቸውም የስግደቱ ምልክት የእጃቸው ጣት መጅ አውጥቶ እግራቸው እንደ እንጨት ደድሮ እንደነበር ለማጠብ ጎንበስ ስንል እናይ ነበር። ሁሌም የማልረሳው ምክራቸው ለክፉው ቀን ስንቅ ሆኖናል። ብፁዕ አቡነ ሰላማ ጎንደር ተዛውረው ለተወሰነ ጊዜ ሰርተው ወደ እንግሊዝ ተቀየሩ። እዚያም በሐዋርያነት አገልግለዋል። በኋላም በፅኑ ህመም ደዌ ዘእሴት ታመው በሕክምና እየተረዱ ቆይተው ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው እንዲታከሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ሲወሰን ወንድም የሚሏቸው ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ተቀብለዋቸው አስታመዋል። ነገር ግን ሕክምናው መፍትሔ ስላልነበረው ወደ ሀገር ቤት ተመልሰው በሐያት ሆስፒታል እየተረዱ ቆይተው  ሰኔ 19 ቀን 1996 ዓ.ም.ዐርፈው በሚወዱት ገዳም በደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ።ሰላማ ከጽሑፍ በላይ ናቸው። ስለ እርሳቸው ለመናገር የሚችሉ ብዙ ልጆች አሏቸው። ሰላማ እንደ ጸሐይ ለድሃውም ለሐብታሙም፣ ለመስሊሙ ለክርስቲያኑም፣ ለትንሹም ለትልቁም እኩል የሚደርስ ፍቅር ሰጪ ናቸው። በተለይ ጎባ ከተማው ላደጉ ልጆች ትውስታው ቀላል አይደለም። ባሌ እኔ እስከምገነዘብ ድረስ ሕዝብ በሚወዳቸው ጳጳሳት እድለኛ ነው። ከሁሉም አባቶች ግን ረጅሙን ዘመን ያገለገሉት አቡነ ሰላማ ናቸው። እንደ ልጆቻቸው ጥሪ “ሰላማ” ሰላምችን፣ ሰላማዬ ይባላሉ። ከጊኒር ለሥራ መጥቼ ስለ ሥራና ቦታው ሁኔታ ሳወራቸው። “እኔ እኮ እናንተ ሳትወለዱ ነው ባሌ የመጣሁት” ይሉኝ ነበር። ለማንኛውም ሁሉም ትዝታውን ቢጽፍ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር። ስሜቴ ወደ ብዙ ጉዳዮች እየገባብኝ ብዙ ማንነታቸውን እያሰብኩ ለመጻፍ እየተቸገርኩ መከተቤን ያዝኩት……..  ብፁዕ አቡነ ሰላማ + ብኅትውና የብፁዕነታቸው ብኅትውና የጻድቁን የተክለ ሃይማኖትን ዐሠረ ፍኖት እንደተከተሉ የኖሩት ሕይወት ይናገራል። ከወገባቸው ቅንዓተ ዮሐንስን አልፈቱም። አልጋ ላይ አልተኙም። መኝታ ቤታቸው ሰው አይገባም። ለመጀመሪያ ጊዜ እርሳቸው ሔደው አቡነ ዜና ማርቆስ ሲመጡ ቤቱ ሊጸዳ ሲገባ የሚተኙት ቁርበት ላይ መሆኑን ታወቀ። አቡነ ዜና ማርቆስ “እኔ የጻድቁ ሰላማ ያህል ትጉህ አይደለሁም አልጋ አስገቡልኝ” ብለው ነበር ይባላል። ማታ ላይ ውዳሴ ማርያም የሚዘልቁት በዜማ ነበር። ይህንን እርሳቸውን ለማነጋገር ወደ ቤት ስሔድ በር ላይ ሆኜ በተደጋጋሚ ሰምቻለሁ። ወዳሴ ከንቱ እጅግ ከሚጸየፏት ነገር አንዷ ናት። ቅኔ ሲደረግ ሙገሳው ሲጀመር ተው ተው ይላሉ። ምግብ መመገብ መቼ ትዝ እንደሚላቸው አላውቅም። አንድ ጊዜ እንዲህ ሆነ:- ለአገልግሎት ወደ ሲናና ወረዳ የካቲት አጋማሽ ላይ በሔድን ቀን ከቅዳሴ ወጥተን ቀድመን እኛ አስተማርን፣ ከዚያም ቄስ ከተማ የተባሉ ትንታግ የኦሮምኛ ሳበኪ አስተማሩ። መጨረሻ ብፁዕነታቸው ቀጠሉ። በቦታው ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ ነበረችና “አካ ሰሎሜ ኦቶታኔ “ (እንደ ሰሎሜ በሆን ጌታ ሲወለድ ባየን ) የሚለውን መዝሙር ዘመረች። ማንም ከቦታው ሳይነሳ ጉባዔው ሳይበተን ምሽቱ መጣ። ምንም አልበላንም አልጠጣንም እኛ ረሃብ ሊጨርሰን ሆነ። መሽቷል እራት ብሉ ሲባል መንገዱ አመቺ አይደለም እንሄድ ብለው ስንነሳ የኛ አለመብላታችን ትዝ ብሏቸው “ልጆች ምን በላችሁ” አሉን። ሹፌራቸው መዝገቡ “እረ አባታችን ምንም አልበላንም” ቢላቸው። “ልጆች ዛሬ ሞታችሁ” ብለው ዳቦ እንድንይዝ ተደረገ።ከሰላማ ጋር መኖር ሆነ ማገልገል በቃ ከምግብ ተራራቅህ ማለት ነው። ደክሞኛል ልረፍ፣ ርቦኛል ልብላ የለም። ሹፌር አንኳ ይርበዋል አይሉም። ለዚኽ ነው መመገብ እንኳ ትዝ የማይላቸውን ያነሳሁት። (አንጋፋዋ ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ ለጎለ ብኅንሳ ገዳሙ የቁጥር 6 ካሴቷን አበርክታለች። በዚያም ላይ ባሌን ከወር በላይ ከእርሳቸው ጋር ገጠር ለገጠር እየዞረች አገልግላለች። ትልቅ አገልግሎት ነው። እንደውም አቡነ ቀሲስ አይበረክትላቸውም ይባላል። አይበሉ አይጠጡ። በቃ ባኅታዊ ካልሆንክ አልያ ቆራጥ መነኩሴ ካልሆነ አይቻልም።
Показать все...
++መጨራሻ አካባቢ አንድ ሸምገል ያሉ የቀድሞ ሰራዊት ወታደር የነበሩ ሰው ሹፌር ነበሯቸው። በጣም ቀልጣፋ ናቸው። በጣም ታዛዥ ናቸው። እሺ አባታችን ብሎ መታዘዝ ብቻ ነው የሚያውቁት። ጠዋት ቀድመው መጥተው መኪና አዘጋጅተው ይጠብቃሉ። መቋሚያ ተቀብለው ቦታ ያመቻቻሉ። አንድ ቀን ጠዋት ላይ ወደ አዲስ አበባ ልንሸኝ ቆመናል። የሰውየውን መዘጋጀት አይተው። ሊሸኙ ለተሰበሰቡትን ካህናት “አንድ ካህን ከመምራት መቶ ወታደር መምራት ይቀላል” አሉ። ካህናቱ ሳቁ። አይደል እንዴ አባቶች አሉ። ካህናቱም በራሳቸው አዝነው አዎን አባታችን ትክክል ነው አሉ። ሰላማ ማብራሪያ ጨመሩበት ቆም ብለው። ወታደር ወደፊት ሲባል ወደፊት ነው። ተቀመጥ ሲባል ተቀመጥ ነው፤ ሩጥ ሲባል ሩጥ ነው። እኛኮ ስንታዘዝ እንደ ግመል ሽንት ግራ ነን። ብለው በር ዘጉ። ታዲያ ይህ አይነት ተግሳጽ እንዴት ከአዕምሮ ይጠፋል። ሁሌም የሚገርመኝ አባባል ይናገራሉ “አንድ ተራ መነኩሴ ነኝ አኮ” ሰላማን የሚያህል ተጫዋችም አላየሁም። ትልቅ፤ ትንሽ፣ ተማረ፣ አልተማረ የለም ከኔቢጤው ጋር ቆመው ነው የሚያወሩት። እንደ ዮሐንስ አፈወርቅ የድሃ ጠበቃ ነበሩ። ጊንር ላይ ሲያስተምሩ “እግዚአብሔር በሐብታም አድሮ ይሰጣል፤ በደሃ አድሮ ይቀበላል” “ለድሆች መመጽወት በሰማይ ቤት ባንክ መክፈት ነው” ብለው አስተማሩን። ዛሬ ላይ የድሆች መርጃ ማኅበር በሰንበት ትምህርት ቤቱ ከተቋቋመ 218 ዓመቱን አስቆጥሯል። ++ሰላማና ንባብ አቡነ ሰላማን እኔ ለማየት እንደታደልኩት ትልቁ መጽሐፏቸው አዘውትረው የሚመረምሩት መጽሐፍ ቅዱስ እና ሃይማኖተ አበው ነው። ምንም ቢሆን ለንባብ አይቦዝኑም። ++ሰላማና መታሰቢያቸው * መታሰቢያ አንድ ብፁዕነታቸው ብዙ ወዳጅ እንዳላቸው አውቃለሁ። መታሰቢያም ለማድረግ ብዙ የተጣረ ይመስለኛል። በተለይም ባቋቋሙት ገዳም አካባቢ። ወደ ገዳሙ ከሔድኩ ከ 14 ዓመት በላይ ስለሆነኝ ምንም መረጃ የለኝም። ከዚህ ጽሑፍ በኋላ የማገኝ ከሆነ እጠብቃለሁ። ነገር ግን እጅግ ደስ የሚለኝ ቆራጥ መንፈሰ ጠንካራ ትጉህ ባህታዊ፣ ገዳማዊው አባት ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የደብረ ሊባኖሱ መናኝ። ዛሬ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ናቸው። ወደ ሀገረ ስብከቱ እንደመጡ ምንም የልማት ሥራ እንዳልተሰራ ሲያዩ በማዘናቸው ለመስራት ወጠኑ። እኔም እንደተመደቡ ቡራኬ ልቀበል ቤታቸው ስሄድ መስራት እንደሚፈልጉ ነገሩኝ። ደስ አለኝ እኛም እናስተባብራለን አልኳቸው። በቃ የሰላማን ልጆች ያዙ። ከአቡነ ባስልዮስ ጀምሮ ምንም ያልተለወጠውን ያረጀ መንበረ ጵጵስና ለመስራት አሰቡ። በተለይም ታላላቆቹ አባቶች የኖሩበት ቤት እንዲህ ሆኖ ማየት አልሻም በማለት ቁጭት ፈጠሩ። ጎባ ላይ የቢሮ ሰራተኛውን አዘጋጁ። ሥራ አስኪያጁን ሊቀ ስዮማን ንጋቱ ዘውዴ፣ ቀሲስ ፍቃዱ ለገሰ፣ መ/ር ወጋየሁን በተርታ አሰለፉ… (ሁሉም የሰላማ ልጆች የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ምሩቃን ናቸው ፣የሀገረ ስብከቱ ሰራተኞች ናቸው)። ወደ ወረዳ ዘመቱ፣ አዲስ አበባ ሊቀ ትጉሃን ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ፣ እኔ አሰተባባሪ ሆንን። ሰላማ መታሰቢያ መንበረ ጵጵስና ተገነባላቸው። የሰላማ መታሰቢያ ክፍል ይሰየማል። ያገለገሉበት ንዋያተ ቅድሳት፣ ልብስ፣ መስቀል ይቀመጣል። አሁን ሥራው ተጠናቋል። አቡነ ዮሴፍ የስራ አባት ናቸው። ሁለቱም የደብረ ሊባኖስ ፍሬ ናቸው። (ባሌ ጎባ) * መታሰቢያ ሁለት ሁሌም ለአቡነ ሰላማ መታሰቢያ አመታዊ ጉባኤ በጎባ መድኅኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ይደረጋል። ይዘከራሉ። ደስ ሲል። ዘንድሮ በኮቪድ ምክንያት የሚኖር አይመስለኝም። * መታሰቢያ ሦስት የጎባ መድኅኔ ዓለም ሰንበት ትምህርት ቤት እጅግ ዘመናዊና ትልቅ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ አሰርቷል። ይህ የስብከተ ወንጌልም መታሰቢያነቱ ለአቡነ ሰላማ ነው። *መታሰቢያ አራት በእረፍታቸው ዕለት አዲስ አበባ ያሉ ልጆቻቸው በቦታው እንደሚሄዱና እንደሚዘክሯቸው አውቃለሁ። ዘንድሮን ባላውቅም። በቀጣይ ጽሑፍ ሰላማና የሕመማቸው ወቅት፣ ሞትና ቀብራቸው በተለይም ከአቡነ ጳውሎስ ጋር የነበራቻው ጉዳይን እንዳስሳለን። በረከታቸው አይለየን!!!
Показать все...