ru
Feedback
HiTech

HiTech

Открыть в Telegram

HiTech | Learn. Fix. Create. 📱💻🎨 Your Ethiopian tech hub! We teach: ✅ Smartphone Repair ✅ Laptop & Chip-Level Repair ✅ Graphics & Motion Design ✅ Coding & Web Development ✅ Tools, Tips & Tech Reviews Join the HiTech family — grow your skills & build

Больше
1 635
Подписчики
+224 часа
+127 дней
+2630 день
Архив постов
HiTech
1 636
#​​Cloud_Storage ◽️[Cloud_Storage]ክላውድ ስቶሬጅ የምንለው በኮምፒውተር ወይም በሞባይል ስልክዎት የትኛውም ክፍል ላይ የተቀመጠ ፋይልና ዳታ በሌላ ድርጅት በተዘጋጀ የዳታ ማስቀመጫ ላይ የኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የምናስቀምጥበት ነው፡፡ ◽️ በአሁን ሰዓት ይሄን አገልግሎት የተለያዮ ድርጅቶች እየሰጡ ሲሆን በዋናነት #Microsoft, #Google, and #Amazon ትልቁን ቦታ በመያዝ የሚጠቀሱ ሲሆኑ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ለማስቀመጫ ድርጅቶቹ ለመጠቀሚያ የሚያስፈልግ ስም እና የይለፍ ቃል በማዘጋጀት የተወሰኑ ፋይሎችን በነፃ እንዲሁም በክፍያ እንድናስቀምጥ ያደርጋል፡፡ ◽️ መጠባበቂያ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ክላውድ ስቶሬጂ አገልግሎትን መጠቀም ፍላጎት እየጨመረ የመጣ እና የተለያዮ ጥቅሞች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፋይሎች ጥብቅ በሆነ ቦታ መቀመጣቸው፣ የምናስቀምጠውን ፋይል ከየትኛውም ቦታና በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ ሆነን መጠቀም እንችላለን እንዲሁም የግል ፋይሎቻችን የተቀመጠበት ኮምፒውተር ቢሰረቅ፣ ቢበላሽ ወይም በእሳት ቢቃጠል ካስቀመጥንበት ድርጂት ፋይሎቹን ካለምንም ችግር እናገኛለን፡፡ ◽️ 'ባክአፕ ክላውድ' በመጠቀም ፋይል እና ዳታ ስናስቀምጥ ኮምፒውተራችን የተገናኘበት የኢንተርኔት ግንኙነት ፍጥነት የሚወስነው ይሆናል ትልቅ መጠን ያላቸውን ፋይሎች ለማስቀመጥ ቀናትን ሊፈጅ የሚችል ሲሆን አገልግሎቱን ለመስጠት Amazon S3፣ Google Mozy እና Microsoft Sky Drive የሚሉ ሶፍትዌሮችን አዘጋጅተዋል፡፡ ◽️ ማክሮሶፍት ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Sky Driveን በመጠቀም እስከ 25 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡  ◽️ በተጨማሪም Google ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Google Driveን በመጠቀም እስከ 15 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ከስልክዎ ላይ ያሉትን ፎቶና የመሳሰሉት መረጃዎች ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን ስቶሬጅ በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው:: @cellphonetechnology @cellphonetechnology

HiTech
1 636
✅ #parts_of_computer ❖አንዳንድ የኮምፒውተር #ክፍሎች ማብራሪያ ❶. #RAM (Random Access Memory) ራም (RAM) ፕሮግራሞችን እና ዳታዎችን ይይዛል የሚኖረው መጠን ትልቅ በሆነ መጠን ውስብስብ የሆኑ ፕሮግራሞችን በቀላሉ ለመጠቀም እና ብዙ ዳታዎችን ለማገናዘብ ይችላል:: የራም ብቃት በሜጋ ባይት ይለካል:: (1 MG= 1 Million character) በአሁኑ ሰአት የምንጠቀምባቸው የግል ኮምፒዎተሮች (Personal computer) ከ512MB በላይ ራም ይኖራቸዋል:: ❷. #ኤክስፓሽን_እስሎት (Expansion slot) ማዘር ቦርድ የምንለው የኮምፒውተሩ አካል ላይ የሚገኝ ሶኬት ሲሆን Expansion card በቀላሉ በላዩ ላይ ለመሰካት ያገለግላል የምንጠቀምበት ኮምፒውተር ብዙ Expansion slot ባሉት ቁጥር ብዙ ተጨማሪ የኮምፒውተሩን አገልግሎት የሚጨምሩ ሁኔታዎችን ለመጠቀም ይረዳል:: Expansion slot ሌላው መጠሪያ Expansion bus እንለዋለን:: ❸. #Heat_sinker ሂት ሲንከር የምንለው ማዘርቦርድ ላየሚገኝ ሲሆን ስራውም #Fan በተባለ Divice አማካኝነት ንፁ አየርን ተቀብሎ #CPU ስራውን በስርአቱ እንዲሰራ ያደርገዋል:: ይህ ማለት Cpu ብዙ ስራዎችን ሲሰራ ሙቀት ይፈጥራል Heat sinker ደግሞ ያቀዘቅዘዋል:: ❹.#Fan ፈን ብለን የምንጠራው ደግሞ ያው ከላይ እንዳየነው ንፁ አየር ወደ ኮምፒውተራችን ያደርጋል:: ይህ ማለት ቬንትሌተር እንደሚሰጠው ጥቅም ማለት ነው:: ❺ #CPU #CPU ስለ ተባለው ዋነኛ እና ዋነኛ Divice እንመለከታለን:: #CPU (the brain of computer) ወይም የComputer አእምሮ እየተባለ የሚጠራው ይሄ Divice የኮምፒውተራችንን ሙሉ ስራ የሚሰራልን ነው::የትኛውንም አይነት ስራ ኮምፒውተር ላይ ከፍታቹ ስትሰሩ እና የምትፈልጉት ውጤት ወደናንተ የሚመጣው በተአምረኛው # CPU በተባለ Divice ነው:: ይህም የሚከናወነው በማይክሮ ሰከንድ ውስጥ ነው:: #CPU (Central procssing unit) ሶስት ዋና ክፍሎች አሉት እነሱም : ▫️1. #Control_unit ይሄ የCpu ክፍል የሚሰራ ስራ ሁሉንም የኮምፒውተር ስራ መቆጣጠር ነው::ይሄ ማለት አንድ ሰው Computer ላይ ቁጭ ብሎ የሚፈልገውን ሙሉ ትእዛዝ የሚፈፀምለት በዚሁ control unit ውስጥ ነው:: : ▫️2. #Arthmatic and # logic_unit ሌላኛው ደግሞ arthmatic and logic unit በመባል የሚጠራው ሲሆን የተለያዩ ሂሳብ ነክ ነገሮችን ለመስራት ያገለግላል:: : ▫️3. #Regster ይሄ ደግሞ # Cpu ላይ የሚገኝ ትንሽዬ ሚሞሪ ነው:: ይሂም #Cpu የሚሰራቸውን ስራዎች ይመዘግብልናል ማለት ነው:: ❻ #Port (ፓርት) : port ከኮምፒውተሩ ጀርባ የሚገኝ አገናኝ ሶኬት ነው:: በዚህም መሰረት ማንኛውም ውጫዊ የኮምፒውተር ክፍል የሚገናኙበት ቦታ ነው:: መመሪያዎችና መረጃዎች በዚሁ መስመር አማካኝነት ከኮምፒውተር አካላት መሀከል ኪቦርድ,ፕሪንተር,ማውስ, እና ሌሎችም ዩተለያዩ አካላት በየራሳቸው የማገናኛ ገመድና ሶኬት ከኮምፒውተር አካል ጋር በማገናኘት አስፈላጊውን ስራ ያከናውናሉ:: የኮምፒውተሩ ስርአቱ ያለ ችግር እንዲሰራ እነኝህ ክፍሎች በትክክል እርስ በራሳቸው ከተያያዙ በህዋላ ከሀይል ጋር መገናኘት አለበት:: ከሀይ ምንጭ ጋር ማገናኘት ስንፈልግ ሁል ግዜ #ኤሌክትሪክ #ጠፍቶ መሆን አለበት ይህም በተለያዩ ክፍሎች ላይ ብልሽትን ለመከላከል ነው:: ❼ #Power_Supply (የኤሌትሪክ ሀይል) power supply በኮምፒውተሩ አካል የሀይል ሰጭ ክፍል ነው ይህም ክፍል የኤሌክትሪክ ሀይል ለኮምፒውተሩ አቅም በሚመጥን ለውጦ ለኮምፒውተሩ አገልግሎት ያቀርባል:: በሌላ አነጋገር Power supply convert Alternative current (AC) to Direct current (DC). Aalternative current ማለት የኤሌክትሪክ ሀይሉ ከሶኬቱ (ከማከፋፈያው) የሚመጣው ያልተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ሲሆን Direct current ደግሞ Power supply የሚቀበለው የተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ነው ማለት ነው:: የኤሌክትሪክ ሀይል መለክያ ዋት (Watt) ይባላል::ለአንድ ኮምፒውተር አገልግሎት 200 ወይም 230 ዋት በቂ ሀይል ነው::ይህንንም የኤሌክትሪክ ሀይል ለሴቶች የፀጉር ማድረቂያ ማሽን (ካስክ) ጋር ስናመዛዝነው ኮምፒውተሩ ከሚፈልገው የኤሌክትሪክ መጠን ሰባት እጥፍ ይፈልጋል:: ❽#ሞደም (Modem):- ይህ መሳርያ አገልግሎቱ ኮምፒዪተሩን ከስልክ መስመር ጋር በማያያዝ ለመረጃ ልውውጥ ያገለግላል::ሞደም በኤሌክትሪክ ለሚተላለፍ መልእክቶች (E-mail) በተለያዩ ቢሮ ውስጥ ኮምፒዩተሮች በማገናኘት መረጃን ለመለዋወጥ ያገለግላል::የተለያዩ የሞደም አይነቶች ሲኖሩ ፍጥነታቸውም እንዲሁ የተለየ ነው:: : ❾#ኪቦርድ Keybord:- መረጃን ወደ ኮምፒዪተር ለማስገባት በፅሁፍ መሳርያነት የሚያገለግል መሳርያ ሲሆን ለዚህም አገልግሎት ይረዳ ዘንድ ፊደላት ቁጥሮች ምልክቶችና ሌሎች ቁልፎች በመጫን የተፃፈውን በምስል ማሳያው (Screen) ላይ እናያለን:: ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩ @cellphonetechnology

HiTech
1 636
✴️ የተወሰኑ ICT ታክኒካዊ ስያሜዎች እናሳውቃችሁ፡፡👏🙌 🎈1. ጥቁር መዝገብ (Blacklist) - በገዳቢ የክልከላ ፖሊሰ የታገዱ ድረ ገጾች እና ሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶች ዝርዝር ነው። 🎈2. ብሉቱዝ (Bluetooth) -አልባ ከሞባይል እና ከባለመስመር ስልኮች በአጭር ርቀት ዳታ ለመላላክ የሚያስችል ገመድ የግንኙነት ደረጃ ነው። ቡሉቱዝ ዳታ ለመለዋወጥ አጭር ሞገዶችን ይጠቀማል 🎈3. ቡቲንግ (Booting) - ኮምፒውተርን ሥራ ማስጀመር ወይም ማስነሳት ነው። 🎈4. አቫስት (Avast) - ጸረ ቫይረስ መሣሪያ 🎈5. መሠረታዊ የግብአት/ውጤት ሲስተምሶፍትዌር (Basic Input/Output System-BIOS) - የኮምፒውተር ሶፍትዌር የመጀመሪያው እና መሠረታዊው ደረጃ ነው። ባዮስ የኮምፒውተራችንን ሐርድዌር ደኅንነት ለማረጋገጥ የሚረዱ የተለያዩ አማራጮችን ይሰጠናል፤ ኮምፒውተራችን ሲከፈት በይለፍ ቃል ብቻ እንዲገባ ማድረግ ከእነዚህ አንዱ ነው። 🎈6. ሲክሊነር (CCleaner) - በነጻ የሚገኝ ሶፍትዌር ነው። በቅርብ በተጠቀምንባቸው ፕሮግራሞችና በዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲሰተም አማካኝነት በሐርድ ዌራችን ላይ የተተዉ ጊዜያዊ ፋይሎችን ዱካ የሚያሳዩ መረጃዎችን የሚያጸዳ ሶፍትዌር ነው። 🎈7. ሲዲ በርነር (CD Burner) - በባዶ ሲዲዎች ላይ መረጃ ለመጻፍ የሚችል የኮምፒውተር ድራይቭ ነው። ዲቪዲ በርነር (DVD burners) በተመሳሳይ መንገድ በባዶ ዲቪዲዎች ላይ ይጽፋል። ሲዲ-አርደብሊው (CD-RW ) እና ዲቪዲ-አርደብሊው ድራይቮች (DVD-RW drives) ደግሞ በሲዲ/ ዲቪዲ ላይ የተጻፈውን አጥፍተው ከአንድ ጊዜ በላይ መልሰው መጻፍ ይችላሉ። 🎈8. ሰርከምቬንሽን (Circumvention) - በኢንተርኔት አፈና የታገዱ ድረ ገጾችን እና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለማግኘት እገዳውን ማለፍ። 🎈9. ክሌም ዊን (Clam Win) - ለዊንዶውስ የተሠራ የኤፍኦኤስኤስ ጸረ ቫይረስ 🎈10. ኮቢያን ባክአፕ (Cobian Backup) - የኤፍኦኤስኤስ የመጠባበቂያ ማከማቻ መሣሪያ ነው። የቅርብ ጊዜዎቹ የኮቢያን አይነቶች ምንጫቸው የማይገለጽ ነገር ግን በነጻ የሚገኙ ናቸው፤ የቀድሞዎቹ ግን በኤፍኦኤስኤስ ብቻ የሚለቀቁ ነበሩ። 🎈11. ኮሞዶ ፋየርዎል (Comodo Firewall) - ምንጩ (ውስጣዊ መዋቅሩ) ለምርመራ ክፍት የሆነ፣በነጻ የሚገኝ የፋየርዎል መሣሪያ ነው። 🎈12. ኩኪ (Cookie) - የኢንተርኔት ማሰሻ (browser) በኮምፒውተር ላይ የሚተዋቸው የጎበኘነውን ድረ ገጽ እና ተያያዥ መረጃዎችን መዝግቦ የሚይዝ አነስተኛ ፋይል ነው። 🎈13. ዲጂታል ፊርማ (Digital signature) - ኢንክሪፕሽንን በመጠቀም አንድ ፋይል ወይም መልእክት ከትክክለኛው ሰው የተላከ መሆኑን የማረጋገጫ መንገድ 🎈14. የዶሜይን ስም (Domain name) - በቃላት የሚገለጽ የድረ ገጽ ወይም የኢንተርኔት አገልግሎት አድራሻ 🎈15. ኢንክሪፕሽን (Encryption) - የተራቀቀ ሒሳባዊ ስሌትን በመጠቀም ኢንክሪፕት (encrypt) ማድረግ፤ ትክከለኛው መረጃ ማለትምያለው የይለፍ ቃል ወይም የኢንክሪፕሽን ቁልፍ (encryption key) ሰው ብቻ ኢንክሪፕት የተደረገውን መረጃ ዲክሪፕት ማድረግ/መክፈት (decrypted) እንዲችል የሚያደርግ 🎈16. ኢንጂሜይል (Enigmail) - የታንደርበርድ የኢሜይል ፕሮግራም አጋዥ መሣሪያ (add-on) ነው፤ ተጠቃሚዎቹ ኢንክሪፕት የተደረገ ወይም በዲጂታል ፊርማ የታተመ መልእክት ለመላክና ለመቀበል የሚያስችል 🎈17. ኢሬዘር/መደምሰሻ (Eraser) - ከኮምፒውተር ወይም ከሌሎች ተንቀሳቃሽ የመረጃ ማከማቻዎች ላይ የሚገኝ መረጃን በአስተማማኝ እና በዘላቂነት ከነጭራሹ ለማጥፋት (delete) የሚያከማይክሮሶፍት 🎈18. ፋየርፎክስ (Firefox) - የታወቀ የኤፍኦኤስኤስ ማሰሻ (FOSS Web browser) ነው፤ ከማይክሮሶፍት ማሰሻ “ከኢንተርኔት ኤክስፕሎረር” የተለየ አማራጭ ነው። 🎈19. ፋየርዎል (Firewall) - ኮምፒውተርን አስተማማኝ ካልሆኑ የኢንተርኔት እና የቤት ውስጥ መረቦች ግንኙነት የሚጠብቅ መሣሪያ ነው። 🎈20. ነጻና ቀመሩ የሚታይ ሶፍትዌር- ኤፍኦኤስኤስ (Free and Open Source Software-FOSS) - ያለክፍያ በነጻ የሚገኙ እንዲሁም ተጠቃሚዎች የሶፍትዌሮቹን አሠራር እንዲመረምሩ፣ እንዲፈትሹ፣ እንዲያሻሽሉና ለሌሎች አሳልፈው እንዲሰጡ የሚፈቅዱ ሶፍትዌሮች ምድብ 🎈21. ፍሪዌር (Freeware) - በነጻ የሚገኙ፣ ነገር ግን ተጠቃሚዎች መሠረታዊ የፈጠራ አወቃቀሩን (source code) እንዳያገኙ ሕጋዊና ቴክኒካዊ ክልከላዎችን የሚያደርጉ ሶፍትዌሮች 🎈22. ጂኤንዩ/ሊኑክስ (GNU/Linux) - የኤፍኦኤስኤስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ነው፤ ለማይክሮሶፍት ዊንዶውስ አማራጭ ሲስተም ነው። 🎈23.ጂፒኤስ (Global Positioning System - GPያደረገ በስፔስ/ምህዋር ላይ መሠረት ያደረገ በሳተላይት በመታገዝ ቦታንና ጊዜን ለመለየት የሚያስችል፤ በማንኛውም የአየር ሁኔታ፣ በየትኛውም የምድራችን ወይም በአቅራቢያዋ ባሉ ቦታዎች የሚሠራ፤ ከሞላ ጎደል በምንም ነገር የማያደናቀፍ ከሰማይ ከፍታ ለመመልከት የሚያስችል የሳተላይት መመልከቻ ነው። 🎈24. ሐከር/ሰባሪ (Hacker) በዚህ አገባቡ፣ ከርቀት ኮምፒውተራችንን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ወይም ስሱ መረጃዎቻችንን ለመስረቅአይፒ የሚሞክር ወንጀለኛ 🎈 25. የኢንተርኔት ፕሮቶኮል አድራሻ-( አድራሻ) (Internet Protocol address -IP address) - ማንኛውምሰጪ ኮምፒውተር ከኢንተርኔት ጋራ ሲገናኝ የሚሰጠው ልዩ መለያ 🎈26. ኢንተርኔት አገልግሎት (አይኤስፒ) (Internet Service Provider-ISP) - የኢንተወይም ግንኙነት መስመር አገልግሎት የሚሰጥ ኩባንያ ወይም ድርጅት። የብዙ አገሮች መንግሥታት ኢንተርኔትን በጣም ይቆጣጠራሉ፤ እነዚህን አገልግሎት ሰጪዎች (አይኤስፒ) በመጠቀምም የኢንተርኔትአሶሲዬሽን ክልከላ፣ ስለላ እና እገዳ ያደርጋሉ። 🎈27. ኢንፍራሬድ ዳታ (Infrared Data Association) (ኢርዳ/IrDAአልባ በአጭር ርቀት የኢንፍራሬድ ስፔክተረም ጨረሮችን በመጠቀም መረጃ/ዳታ ለመለዋወጥ የሚያስችል ገመድ አልባ የግንኙነት መንገድ ነው። በዘመናዊ መገልገያዎች ውስጥ ኢርዳ/IrDA በብሉቱዝ ተተክቷል። 🎈28. ጃቫ አፕሊኬሽንስ (Java Applications) (አፕልትስ/Applets) - በብዙ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ላይ የሚሠሩ አነስተኛ ፕሮግራሞች ናቸው። ብዙውን ጊዜ በድረ ገጾች ውስጥ የተሻሻሉ አገልግሎቶችን (functionalities) ለመስጠት ጥቅም ላይ ይውላሉ። 🎈29. ኪይሎገር (Keylogger) - ለስለላ ተግባር የሚውል የስፓይዌር አይነት ነው፤ በኮምፒውተሩ የመተየቢያ ገበታ (keyboard) ላይ የነካናቸውን/ የተጫንናቸውን ቁልፎች/ፊደሎች በሙሉ መዝግቦ ለሦስተኛ ወገን ይልካል። ኪይሎገሮች የኢሜይሎችን እና የይለፍ ቃሎችን ለመስረቅ በብዛት ጥቅም ላይ ይውላሉ። 🎈30. ኪፓስ (KeePass) - የአስተማማኝ የይለፍ ቃል ማከማቻ (database) ፍሪዌር ነው። ════❁✿❁ ═══════ Joi

HiTech
1 636
🚩ሰላም ሰላም MPS ቤተሰቦች .. 🚩 ዛሬ ማንኛውንም አይነት የ Software ችግር ያለበት የአንድሮይድ ስልክ እንዴት እንደምናስተካክል አሳያቹሀለው። 🚩 በመጀመርያ ODIN የተሰኘ የኮምፒውተር መተግበርያ በኮምፒውተርአችን ላይ እንጭናለን። ( መተግበርያውን ከዚህ ጽሁፍ ስር ታገኙታላቹህ ) 🚩 ከዚህ በመቀጠል የ Software ችግር ያለበትን ስልክ ፍላሽ እናደርጋለን። ፍላሽ ለማድረግ ከስር የተቀመጡትን መንገዶች ይከተሉ። 1. በመጀመርያ የስልካችን #setting ውስጥ በመግባት ሞዴሉን እና አንድሮይድ ቨርዥኑን እናያለን። 2. በመቀጠል የ SAMSUNG OFFICIAL FIRMWARE WEBSITE ላይ እንሄድና የስልካችንን ሞዴል በመጠቀም ፍላሽ ፋይሉን ዳውንሎድ እናደርገዋለን ። 3. የስልካችንን power button ➕volum up button ➕ home button ስንጫነው እራሱ ስልኩ ወደ ዳውንሎድ ሞድ ይገባል ። 4. ከዛም ኬብል ተጠቅመን ስልካችንን ከኮምፒውተራችን ጋር እናገናኛለን 5. odin ንን ከከፈትን ቡሓላ ዳውንሎድ ያደረግነውን ፍላሽ ፋይል #Browse እናደርግለታለን ። 6. በመቀጠል #Start እንለውና ከዛ ሁሉን ነገር ጨርሶ #Pass እስኪለን እንጠብቃለን ። ከዛ ስልኩ በራሱ ሰአት restart ያደርግና ይከፍታል ማለት ነው ። 🚩🚩 ማስጠንቀቂያ 🚩🚩 🚩 ስልካችንን ፍላሽ ካስጀመርን ቡሓላ በፍጹም መንቀል የለብንም 🚩ያወረድነው ፍላሽ ፍይል የራሱ የስልኩ ሞዴል መሆኑን ማረጋገጥ አለብን።

HiTech
1 636
አይሲዎች እና ግልጋሎታቸዉ 1. ሲፒዉ:- የስልኩን ሁለተናዊ እንቅስቃሴ ይቆጣጠራል ። ይህን ስንል ስልካችን ዉስጥ የሚደረጉ ስራዎችን በሙሉ ለምሳሌ ቻርጅ ማድረግ : መደወል : መቀበል : አላርም : ካልኩሌተር : ካሌንደር የመሳሰሉት ይቆጠራል። 2. ፓወር አይሲ :- ለእያንዳንዱ የስልክ አካል የሚገባዉን ያህል ከባትሪ ወስዶ ያከፋፍላል ። ለምሳሌ :- ለአንቴና ስዊች : ለሲፒዩ : ለክሪስታል ኦሲሌተር : ለኔትወርክ አይሲ እና ለሌሎች ክፍሎች በሙሉ የሚፈልጋቸዉን ሀይል ይሰጣል ። 3. ኦዲዮ አይሲ :- የኤሌክትሪክ ሲግናልን (ሞገድን) የማጉላት ስራ ይሰራል ። የኤሌክትሪክ ሲግናሉ የድምጽ መረጃ የያዘ ነዉ ። ኦዲዮ አይሲ ስልካችን ዉስጥ የሚከናወኑ የድምጽ ሂደቶች በሙሉ ያጎላል ። ለምሳሌ :- እኛ የምናወራዉን ድምፅ እና የመሳሰሉትን በሙሉ በበቂ ሁኔታ እንዲሰሙ ያደርጋል ። 4. ቻርጅ አይሲ :- ስልካችን ቻርጅ የሚደረግበት ጊዜ ከቻርጀር የሚመጣዉን ቮልቴጅ ወይም ሃይል መጥኖ ለባትሪ የማድረስ ስራ ይሰራል ። ቻርጅ አይሲ በቻርጅ እና ባትሪ መሀል ሆኖ ቮልቴጅ በተመጣጣኝ ሁኔታ ከቻርጀር ወደ ባትሪ እንዲሄድ ያደርጋል ። ቻርጀር—>ቻርጀር አይሲ—–>ባትሪ 5. ሚሞሪ አይሲ :- ሚሞሪ አይሲ የተለያዩ መረጃዎችን የሚይዝ አይሲ ነዉ ። ሚሞሪ አይሲ በሁለት ይከፈላል ። ሁለት ክፍሎች ራምና ሮም በመባል ይታወቃል ። 5.1 ራም:- ራም የሚለዉ የሚሞሪ ክፍል ጊዜያዊ /ቋሚ ያልሆኑ / መረጃዎችን ያስቀምጣል ። ለምሳሌ ሚስኮል የተደረገን ቁጥር ፣ የደወልንበት ቁጥር እና ጥሪ የተቀበልንበት ቁጥር የሚቀመጥበት ክፍል ነዉ ። ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎችን የምናገኛቸው እስከ ተወሰነ ቁጥር ብቻ ነዉ ። ከአንድ ወር ወይም ከሁለት ወር በፊት የደወልንባቸዉን ቁጥሮች አናገኛቸዉም ምክንያቱም የስልኩ ራም መያዝ እስከሚችለዉ ይይዝና ቀሪዉን በራሱ ያጠፋዋል ። ይህን መረጃ የመያዝ አቅም ደግሞ እንደ ስልኩ ሞዴል ይለያያል ። 5.2 ሮም:- ሮም የሚባለዉ ደግሞ ቋሚ የሆኑ እና እስካላጠፋናቸዉ ድረስ በፍጡም የማይጠፋ መረጃዎችን ይይዛል ። ለምሳሌ ፎቶ ግራፍ ፣ ሙዚቃ ፣ ቪድዮ ፣ የስልክ ቁጥሮችና የስልካችን ሶፍትዌር የሚቀመጡት ሮም ዉስጥ ነዉ ። ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች እስከፈለግነዉ ጊዜ ድረስ ማቆየት እንችላለን ። በአንድ ወቅት የተነሳነዉን ፎቶ ካላጠፋነዉ እስከፈለግነዉ ጊዜ ሳይሰረዝ ማቆየት እንችላለን ። ምክንያቱም ፎቶ ግራፍ የሚቀመጠው ሮም ዉስጥ ነዉ ። 6. ዩአይ አይሲ :- 1. ሪንገርን 2. ቫይብሬተርን 3. የስክሪን ብርሃንን እና 4. የኪፓድ ብርሃንን ይቆጣጠራል ። 7. ረዳት ፓወር አይሲ :- ቢቢ ቫይቭ (BB 5) ስልኮች ዉስጥ ሁለት ፓወር አይሲ እንደሚገኝ ከላይ ተጠቅሷል ። ከአር ቲ ሲ አጠገብ የሚገኘዉ ዋና ፓወር አይሲ ሲሆን ከቡስተር ኮይል አጠገብ የሚገኘዉ ረዳት ፓወር አይሲ ነዉ ። ይህ አይሲ የቻርጅን እንቅስቃሴ እና የቮልቴጅን ሂደት ይቆጣጠራል ።

HiTech
1 636
​​💥 እንዴት አድርገን የተበላሸ ሚሞሪ ካርድን እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል እንችላለን⁉️ 💥 እነዚህን 12 ስቴፓች ይጠቀሙግን ሚሞሪ ካርዱ ውስጥ የነበሩት ፋይሎች መጥፋታቸው የማይቀር ነገር ነው። ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ ◉step_1➹ ሚሞሪ ካርዱን የኮምፒውተርዎ “USB port” ላይ ይሰኩት። ♡┈┈┈••✦ ◉step_2➹ ከዚያም “my computer” ውስጥ ገብተው ኮምፒውተሩ ሚሞሪ ካርዱን እንዳነበበው ቼክ ያድርጉ። ♡┈┈┈••✦ ◉step_3 ➹ ከዚያም “Start” በተኑን በመጫን “cmd” ብለው በመፃፍ “Enter”ን ይጫኑ። ♡┈┈┈••✦ ◉step_4 ➹ ከዚያም “Command prompt” ውስጥ ብለው “DISKPART” ይፃፋና “Ok”ን ይጫኑ። ♡┈┈┈••✦ ◉step_5 ➹ ከዚያም “list disk there” ብለው ይፃፋና የሚቀርቡ አማራጮችን ይዩ። ♡┈┈┈••✦ ◉step_6➹ ከሚመጡት አማራጮች ውስጥ ሚሞሪ ካርዱን ከነ ቁጥሩ ያገኛሉ። ♡┈┈┈••✦ ◉step_7➹ ከዚያም “select disk (disknumber)” ብለው ይፃፋና “Enter”ን ይጫኑ። ♡┈┈┈••✦ ◉step_8 ➹ ከዚያም “clear” ብለው ይፃፋና Enterን ይጫኑ። ♡┈┈┈••✦ ◉step_9➹ ከዚያም “create partition primary” ብለው ይፃፋና “Enter”ን ይጫኑ። ♡┈┈┈••✦ ◉step_10➹ ከዚያም “active” ብለው ይፃፋና “Enter” ይጫኑ። ♡┈┈┈••✦ ◉step_11➹ ከዚያም “format fs=fat32” ብለው ይፃፋና “Enter” ይጫኑ። ♡┈┈┈••✦ ◉step_12➹ ከዚያም ኮምፒውተሩ ሚሞሪ ካርዱን ፎርማት ያደርገዋል። ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈         🗣➹share &Join Us                      👇🏾👇🏾👇🏾 ☄ @cellphonetechnology       ┗━ ••• ━ ••• ━━•••━━━┛

HiTech
1 636
የ አንድሮይድ ስልካችንን ፈጣን ለማድረግ የሚረዳ ዘዴ እናያለን ⏸⏸⏸⏸⏸⏸⏸⏸⏸ በመጀመርያ 👉 Go to setting በመቀጠል 👉 about phone ወይም about device Step 3 👉 build number የሚለውን 7 ጊዜ ይንኩት በዚህን ጊዜ deveoper option የሚል setting ውስጥ ይከፈታል Step 4 👉settings 👉 developer option ከዛ Developer option በመግባት ON ካረጋችሁት Step 5👉👉👉 ↪️Window animation scale የሚል ይፈልጉ 1.0 ወይም 1.5 ከሆነ 0.0 ወይም off ያርጉት ↪️Transition animation scale የሚል ይፈልጉ 1.0 ወይም 1.5 ከሆነ 0.0 ወይም off ያርጉት ↪️Animator duration scale የሚል ይፈልጉ 1.0 ወይም 1.5 ከሆነ 0.0 ወይም off ያርጉት 🚫 🚫Developer option ውስጥ ሌላ ከላይ የተጠቀሰው ውጪ ሌላ ነገር ባይቀይሩ ይመከራል በመጨረሻም Settingን ዘግተው ይውጡ ። ✔️✔️ 💯 ፈጣን የ አንድሮይድ ስልክ ይኖረውታል💯✔️✔️ 📶📶📶📶📶📶📶📶📶 ♻️የተመቸ ው 👍 Share በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ

HiTech
1 636
📍Easy Eyes📍 🖲 Blue light filter አድርጎ አይናችን እንዳይጎዳ የሚጠቅም ምርጥ አፕሊኬሽን ነው ይጠቀሙት። @cellphonetechnology

HiTech
1 636
👉ዋይፋይ እንዴት ይሰራል.? WiFi የሚለው አህጽሮተ ቃል Wireless Fidelity ማለት ሲሆን ከ ገመድ አልባ አከባብያዊ መረብ (WLAN) ተመሳሳይ ነው። WiFi የሚሰራበት መርህ ከሌሎች ሽቦ አልባ መሣሪያዎች ጋር ይመሳሰላል፤ የራድዮ ፍሪኮንሲ(ድግግሞሽ) በመጠቀሞ ምልክት(ሲግናል) በመሳርይዎች መካከል ይልካል። ለምሳሌ ያህል የመኪናዎ ራድዮ በሺዎች እና ሚልዮኖች ኸርዝ(Kilohertz, Megahertz) ክልል (ኤ ኤ ም እና ኤፍ ኤም ጣቢያዎች) ውስጥ ያሉትን ድግግሞሽ(frequency) ይቀበላሉ፤ WiFi ግን በቢልዮን ኸርዝ (Gigahertz)ክልል ውስጥ የሚያሰራጭ ውሂብ(ዳታ) ይቀበላል እንዲሁም ይልካል። ኸርዝ (Hz) የድግግሞሽ አሃድ ነው፤ ልክ ሊትር የፈሳሽ ነገሮች መለክያ አሃድ ብለን እንደምንጠራው ማለት ነው። ኸርዝን ለመግለጽ አንድ ምሳሌ እናንሳ፤ በባህር ዳርቻ ቁመው የውሃ ሞገድ ሲመጣና ሲሄድ እያዩ ነው እንበል። ውሃው ጸጥ ብሎ ይቆይና ሞገድ ይፈጥራል፤ ያቺ የተነሳች ሞገድ እየተንከባለለች እግርዎ ስር ትደርሳለች። የሚያዩት ውሃ አሁን ረጋ ብሏል፤ ትንሽ ቆይቶ ተመሳሳይ ነገር ይከሰታል፤ ሞገዱ እየተንከባለለ ወደ እርሶ ይመጣል። በእያንዳንዱ ሞገድ መካከል ምን ያህል ሰከንዶች እንዳለፉ ከቆጠሩ፤ ይህ የሞገዱ ድግግሞሽ(ፍሪኮንሲ) ይሆናል። በተመለከትናቸው ሞገዶች መካከል የነበረ የግዜ ልዩነት አንድ ሴኮንድ ከሆነ የሞገዱ ድግግሞሽ 1 ኸርዝ ወይም በሴኮንድ አንድ ዑደት ነበር ማለት ነው። WiFi እና ሌሎች በራድዮ ድግግሞሽ የሚሰሩ መሳርይዋች የአየር ሞገድን ይጠቀማሉ፤ እነዚህ ሞገዶች በሰኮንድ ከሚልዮን እስከ ቢልዮን ግዜ ይርገበገባሉ ማለት ነው። WiFi የሚጠቀምበት ድግግሞሽ 2.4 እና 5 ቢልዮን ኸርዝ ነው። ዋይፋይ በምንጠቀምበት ግዜ በዚህ ድግግሞሽ አካባቢ የሚሰራ ሌላ እቃ ካለ ሞገዶች እርስ በራሳቸው ስለሚጠላለፉ(interfe rence ስለሚፈጥሩ) የ ኔትዎርክ መቆራረጥ ልያጋጥመን ይችላል። ምግብ ለማብሰል የምንጠቀምባቸው ማይክሮዌቭ የሚፈጥሩት ድግግሞሽ ከ WiFi ድግግሞሽ ጋር ስለሚቀራረብ ብዙ ግዜ የ የራዲዮ መሰናክል(interference) ልያመጡ ይችላሉ። እናም WiFi እምቢ ሲሎት በ ማይክሮዌቭ ምግብ እያበሰሉ አለመሆንዎን ያረጋግጡ።

HiTech
1 636
ከአንድሮይድ ስማርት ስልኮችና ታብሌቶች ላይ የጠፉብንን ፎቶግራፎች መልሰን ለማግኘት… --------------- ከስማርት ሰልካችን እና ታብሌታችን ላይ ሆን ብለን ያጠፋናቸው አሊያም በድንገት የጠፉብንን ፎቶግራፎች በዚህ መልኩ በቀላሉ ማግኘት እንችላለን። በተለያየ ምክንያት የጠፉብንን የምንወዳቸውን ፎቶግራፎቻችንን እነዚህን ቅደም ተከተሎች በመከተል መልሰን ማግኘት አንችላለን። ከአንድሮይድ ስማርት ስልካችን ላይ የጠፉ (የተሰረዙ) ፎቶ ግራፎችን መልሶ ለማግኘት በዚህ ክፍል ከሳምሰንግ ጋላክኢና ኖት፣ ሞቶሮላ፣ ኤል.ጂ፣ ዋን ፕላስ፣ ሶኒ እና ሌሎች አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀሙ ስማርት ስልኮች ላይ የጠፉ ፎቶ ግራፎችን መልሰን የምናገኝበትን መንገድ እንመለከታለን። ይህንን ለማድረግ በዓለም ዙሪያ ከ600 ሺህ ለሚበልጡ አንድሮይድ መገልገያዎች መፍትሄ የሆነውን የአንድሮይድ መልሶ ማግኛ (Android Data Recovery) ያስፈልገናል። 1. በመጀመሪያ “Android Data Recovery” መተግበሪያን ኮምፒውተራችን ላይ ካወረድን (ደወንሎድ) ካደረገን በኋላ ኢኒስቶል ማድረግ ይጠበቅብናል። 2. መተግበሪያውን ከጫንን በኋላ “Data Recovery” የሚለውን መጫን ያለብን ሲሆን፥ በዚህ ጊዜም በርካታ አማራጮች ይመጡልናል። በዚህ ጊዜም የጠፋብንን ፎቶግራፍ መልሰን ማግኘት የምንፈልግበትን ስማርት ስልክ በኬብል አማካኝነት ከኮምፒውተራችን ጋር ማገናኘት አለብን። 3. ስልካችን እና ኮምፒውተራችን ጋር መናበቡን በትክከል ማየት ያለብን ሲሆን፥ ከዚህ ቀደም ስልካችን ከኮምፒተር ጋር እንዲናበብ አድርገን የማናውቅ ከሆነ የሚመጣልንን ቅደም ተከተል በማየት ማገናኘት እንችላለን። 4. ስማርት ስልካችን በተሳካ መልኩ ከተገናኘ በኋላ መልሰን ልናገኛቸው የምንችላቸውን በርካታ ፋይሎች ኮምፒውተራችን ላይ የሚመጣልን ሲሆን፥ ሌሎቹን በመተው “Gallery” መምረጥ ቀጥሎም “next” የሚለውን መንካት አለብን። 5. በዚህ ደረጃ ላይ ሁለት አይነት አማራጮች የሚመጡልን ሲሆን፥ ይህም “Standard mode” እና “Advanced Mode” የሚሉ ናቸው። ከእነዚህም በብዛት የሚመከረው “Standard mode” የሚለው ሲሆን፥ የሚጣልንን የማስጠንቀቂያ መልእክት በመቀበል ለመቀጠል “next” የሚለውን መንካት አለብን። ይህ አልሰራ ካለን ግን “Advanced Mode” ወደ ሚለው በመቀየር መጠቀም እንችላለን። 6. አሁን ስካን የማድረጉ ሂደት የሚጀምርበት ደረጃ ላይ ነን፣ ይህ ሂደት እስኪያልቅ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፤ በዚህ ጊዜም ስማርት ስልካችን አሊያም ታብሌታችንን ከኮምፒውተራችን ጋር እንደተገናኘ እንዲቆይ ማድረግ አለብን። 7. ስካን የማድረጉ ሂደት የሚያበቃ ሲሆን፥ በዚህ ጊዜም ጋላሪያችን ውስጥ የተገኙ ፎቶ ግራፎች በሙሉ ይመጡልናል፤ በስተግራ በኩል “gallery” የሚለውን በመምረጥም ፎቶ ግራፎቹን መመልከት እንችላለን። አሁን የምንፈልጋቸውን ፎቶዎች እየመረጥን “Recover” የሚለውን አማራጭ እየተጫንን ፎቶ ግራፎቹን መልሰን ስማርት ስልካችን አሊያም ታብሌታችን ውስጥ ማኖር እንችላለን።

HiTech
1 636
የሞባይል ኢንተርኔትን በላፕቶፕ ላይ ለመጠቀም (በኬብልና ያለኬብል ለማገናኘት) ክቡራን የዚህ ቻናል ታዳሚዎች… እንዴት አርገን ሞባይላችንን ከኮምፒውተር ጋር በማገናኘትና የሞባይላችንን የኢንተርኔት ዳ
የሞባይል ኢንተርኔትን በላፕቶፕ ላይ ለመጠቀም (በኬብልና ያለኬብል ለማገናኘት) ክቡራን የዚህ ቻናል ታዳሚዎች… እንዴት አርገን ሞባይላችንን ከኮምፒውተር ጋር በማገናኘትና የሞባይላችንን የኢንተርኔት ዳታ ለኮምፒውተራችን መጠቀም እንደምንችል እንደሚከተለው አቅርቤላችኋለሁ። ❶. የሚከተሉትን steps ማዛነፍ አይፈቀድም ➢step ① የሞባይሎን ኢንተርኔት ዳታ ያብሩ ➢step ② ሞባይሎን ከኮምፒተሮ ጋር በUSB cable ያገናኙ ➢step ③ የሞባይሎን setting ይክፈቱ ➢step ④ more በሚለው ይግቡና ከሚመጣሎ አማራጭ tethering and portable hotspotን ይክፈቱና USB tethering የሚለውን on ያድርጉ ➢step ⑤ ወደ ኮምፒውተሮ በመመለስ የፈለጉትን browser (chrome, Firefox or opera) በመጠቀም በኮምፒተሮ ኢንተርኔት ማግኘት ይችላሉ ------- ❷. other method Internet sharing የሚል ሴቲንግ ያላቸው ሞባይሎች ያለ ኬብል መጠቀም ይችላሉ፡፡ •► መጀመሪያ ዳታ ማብራት •►ከዚያ ኢንተርኔት ሼሪንግ የሚለውን ኦን ማድረግ፤ ከዚያ ሄደው ላፕሮፕ ላይ ልክ እንደ ዋይ ፋይ የሞባይሎን ዳታ ያገኙታል፡፡ •► ኢንተርኔት ሼሪንግ የሚለው ሴቲንግ ውስጥ የተቀመጠውን የፓስዋርድ ቁጥር ላፕቶፑ ላይ ማስገባት •► ከዚያ መጠቀም መጀመር ነገር ግን በሞባይል ከምታገኙት ኢንተርኔት ይህ ዋጋው ከፍ ይላል፡፡ የሞባይሎን ካርድ ቶሎ ነው የሚበላው፡፡ ⌘ሌላው ማወቅ ያለብዎ ሞባይሎን ነቅለው መልሰው ከኮምፒውተሮ ጋር ሲያገናኙ ከላይ የተጠቀሱትን steps እንደአዲስ መከተል ግድ ይላል በርግጥ ይህንን አጠቃቀም ምታውቁ እንደምትኖሩ አልጠራጠርም። ጥያቄ ካልዎት 👉 @tekle21

HiTech
1 636
#የውጪ_ሀገር ጥሪዎች📲 ለምን በኢትዮጵያ 🇪🇹 ቁጥር ይወጣሉ? 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ✍ለዓመታት ከተለያዩ ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚደወሉ የስልክ ጥሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ቁጥር እንዲቀየሩ ያደረጉ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች የመታሰራቸው ዜና ይሰማል። ኢትዮ-ቴሌኮም ማግኘት የሚገባውን ጥቅም ከሚያሳጡ ወንጀሎች መካከል የውጪ ጥሪዎችን በሀገር ውስጥ የስልክ ቁጥር ማስተላለፍ ይገኝበታል። ✍ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የሚያዩት #የኢትዮጵያ ስልክ ቁጥር ከሆነ ጥሪው የሀገር ውስጥ እንደሆነ ያስባሉ። ሆኖም ጥሪው ከጣልያን ወይም ከከሳዑዲ ሊሆን ይችላል። ቢሆንም ግን በጣልያን ወይም በሳዑዲ ሀገር የኮድ ቁጥር (ኤርያ ኮድ) ሳይሆን #በኢትዮጵያ ቁጥር ይታያል። ✔️ለመሆኑ የውጪ ሀገር ጥሪዎችን #የሀገር ውስጥ ማስመሰል ለምንና በማን ይሰራል? ቢቢሲ ያናገረው አቶ ተክሊት ኃይላይ ከሶስት ዓመታት በፊት በኢትዮ-ቴሌኮም የክራውድ ማኔጅመንት የአይቲ ባለሙያ ነበረ። ✍አሁን በግሉ የማማከር ስራ የሚሰራው አቶ ተክሊት፤ ቴሌ ሳለ ትራንጉላይዜሽን በሚባል መንገድ የውጪ ሀገር ጥሪን ወደ ሀገር ውስጥ ቁጥር የሚቀይሩ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ያሉበትን ቦታ ይለይ ነበር። ✔️እንዴት የውጪ ሀገር የስልክ ጥሪዎች #በኢትዮጵያ ቁጥር እንዲወጡ ይደረጋል? ሲም ቦክስ ክራውድ ይባላል። ከተለያዩ ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚደወሉ የስልክ ጥሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ቁጥር እንዲቀየሩ ለማድረግ የሚፈልጉ ግለሰቦች ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው የኢትዮጵያ ሲም ካርድና የኢንተርኔት መስመር ይገዛሉ። በሌላ ወገን "ኢንተርኮኔክት" የተባለ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋሞች ከኢትዮጵያ ውጪ ይገኛሉ። ከያሉበት ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ጥሪዎች በኢትዮጵያ ቁጥር እንዲታዩ ማድረግ ይችላሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ከተቋሞቹ ጋር ስምምነት ላይ ይደርሳሉ። ከዛም ተቋሞቹ የውጪ ሀገር የስልክ ጥሪዎች (ራውቲንግ) ወደ ቴሌ ሳይሆን ግለሰቦቹ ወዳዘጋጁት ሲም ካርድ (አይፒ አድራሻ) አንዲላክ ያደርጋሉ። "እነዚህ ጥሪዎች በቴሌ በኩል መተላላፍ ሲኖርባቸው ግለሰቦቹ ወደገዟቸው ሲም ካርዶች (የስልክ ቁጥሮች) ይሄዳሉ" ሲል ተክሊት ይገልጸዋል። ስልክ የሚደወልላቸው የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ምን እየተከናወነ እንደሆነ አያውቁም። በእርግጥ ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ ደዋዮችም ሆነ ሀገር ውስጥ የሚገኙ የጥሪው ተቀባዮች ስለ ሂደቱ አያውቁም። የሚያገኙት ጥቅምም የለም።❌ ✔️የስልክ ቁጥሩን #መቀየር ለምን አስፈለገ? አንድ ጥሪ ከውጪ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ሲደረግ በደቂቃ ወደ 11 ብር ገደማ ያስከፍላል። በአንጻሩ የሀገር ውስጥ ለሀገር ውስጥ የስልከ ጥሪ በደቂቃ ወደ 75 ሳንቲም ገደማ ያስከፍላል። ግለሰቦቹ በሚጠቀሙበት መንገድ ለውጪ ሀገር ጥሪ 75 ሳንቲም ብቻ በማስከፈል፤ ከ 11 ብር ላይ የቀረውን ገንዘብ ኢንተርኮኔክት ከሚሰሩ ተቋሞች ጋር ይቀራመቱታል። ግለሰቦቹ ጥሪውን ለማስተላለፍ የሚያወጡት የኢንተርኔት ወጪ ብቻ ነው። #በኢትዮጵያ ህግ መሰረት የግለሰቦቹ ተግባር ህገ ወጥ ቢሆንም፤ ሂደቱን ህጋዊ አድርገው የሚገለገሉበት ሀገሮች ብዙ ናቸው። አቶ ተክሊት እንደምሳሌ የሚጠቅሰው የሳዑዲ ቴሌኮምን ነው። የሳዑዲ ቴሌኮም የአለም አቀፍ ጥሪ ወጪ ለመቀነስ ሲም ቦክስ ክራውድን በይፋ ይጠቀማል ይላል። በብዙ ሀገሮች ሲም ቦክስ ክራውድ መጠቀም ህጋዊ ስለሆነ ጥሪው የሚደረግባቸው ሀገሮች መንግሥታትን በህግ መጠየቅ አይቻልም። ግለሰቦቹ ከውጪ ተቋማት ጋር የሚቀራመቱትን ገንዘብ ማግኘት የነበረበትን ቴሌ እንደሆነ የሚያስረግጠው ባለሙያው "ሂደቱ ህጋዊ ቢሆን ኖሮ #ቴሌ ይጠቀም ነበር" ይላል። ✔️ #መፍትሔው ምንድን ነው? አቶ ተክሊት እንደሚለው ከተለያዩ ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ🇪🇹የሚደወሉ የስልክ ጥሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ቁጥር እንዲቀየሩ የሚያደጉት ግለሰቦች ወይም ቡድኖች በብዛት የሚሰሩት አዲስ አበባ፣ መተማና ሞያሌ ነው። የስልክ ጥሪዎቹ በዋነኛነት የሚነሱባቸው ሀገሮች ደግሞ ቻይና፣ ጣልያንና ሳዑዲ ናቸው። ከተለያዩ ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚደወሉ የስልክ ጥሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ቁጥር እንዲቀየሩ የማድረጉ ሰዎች በተደጋጋሚ ቢታሰሩም ብዙም ሳይቆይ ሌላ ቡድን ስራውን ይጀምራል። "ቴሌ በምሰራበት ወቅት ተቋሙ በየወሩ ወደ ሶስት #ሚሊየን ዶላር ያጣ ነበር" ይላል። 👉ባለሙያው እንደሚለው አሰራሩ ሀጋዊ ቢሆን #የውጪ ተቋማት ከግለሰቦች ጋር ሳይሆን በቀጥታ ከቴሌ ጋር መደራደር ይችላሉ። ግለሰቦቹ በህገ ወጥ መንገድ የሚያገኙት ጥቅምም የተቋሙ ይሆናል።      

HiTech
1 636
🖥️ፍላት ስክሪን ቲቪዎችን የሚያበላሹ 5⃣ ነገሮች 1⃣. ቮልቴጅ ⚠️ሁሉም እቃዎችን የሚያበላሸው የተለመደው የቮልቴጅ መጨመር እና መቀነስ ነው😡 አብዛኛው ቲቪዎች የራሳቸው መቆጣጠሪያ #ስለሌቻው ቦ
🖥️ፍላት ስክሪን ቲቪዎችን የሚያበላሹ 5⃣ ነገሮች 1⃣. ቮልቴጅ ⚠️ሁሉም እቃዎችን የሚያበላሸው የተለመደው የቮልቴጅ መጨመር እና መቀነስ ነው😡 አብዛኛው ቲቪዎች የራሳቸው መቆጣጠሪያ #ስለሌቻው ቦርዳቸው ቶሎ ለመቃጠል ይዳረጋል ስለዚህ 500 V Stabilizer ገዝተው ይጠቀሙ። 2⃣. የቲቪ የጀርባ መብራቶች (Backlight) #መቃጠል ⚠️ላይቶቹ ሚቃጠሉበት ወቅት ቲቪዎቹ ምስል ማሣየት አቁመው ድምፅ ብቻ ማሠማት ይሆናል ይህ ነገር እሚከሠተው የባክ ላይቶቹ እድሜ (life span) ሲያልቅ እና #ከፍተኛ ሀይል ሲመታቸው ይቃጠላሉ በቶሎ ማስቀየር ያስፈልጋል። 3⃣. ፅዳት ⚠️ስክሪኑ ላይ #Spray ረጭቶ ማፅዳት በፍፁም ሊደረግ እማይገባ ነው። ስክሪኑ በጣም Sensitive ስለሆነ ውስጥ ውሀ ገብቶ በቀላሉ ይበላሻል። ለማፅዳት ሲፈልጉ በንፁ ለስላሣ ጨርቅ ላይ ስፕሬውን በትንሹ በመርጨት ማፅዳት ይችላሉ። 4⃣. ኬብል ⚠️በክረምት ወቅት #HDMI ኬብል አይጠቀሙ መብረቅ በዲሹ ኬብል አልፎ በHDMI አማካኝነት ቲቪዎን ቀጥታ ያገኘዋል በዚ ጊዜ Av ጃክ መጠቀም የተሻለ ነው። ⚠️በዚ ጊዜ Av ጃክ መጠቀም የተሻለ ነው። 5⃣. የስክሪን መሰበር ነው። ⚠️በተለያዩ አጋጣሚዎች ስክሪን ይሰበራል ይሰነጠቃሉ ማሰቀየር #በጣም_ውድ ነው፤ ስለዚህ ልንጠነቀቅላቸው ይገባል። ⚠️ቲቪዎን #ከፍ አርጎ ግድግዳ ላይ መስቀል ያስፈልጋል። ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካሎት Comment ላይ ፆፉልን እስኪ ቻናላችን የተመቻቹህ የ👍 ምልክቷን ተጫኗት

HiTech
1 636
ሲም ካርድ ምንድን ነው? 🔷 ሲም ማለት ነው የተመዝጋቢ ማንነት ሞዱል. SIM stands for Subscriber Identity Module ከማንኛውም የሞባይል ስልክ በጣም አስፈላጊ አካል ነው ፡፡ በአንዳንድ አገሮች ICC (Integrated Circuit Card ) and UICC ( Universal Integrated Circuit Card ) በመባልም ይታወቃል ፡፡ በቀላል አነጋገር ሲም ካርድ በመሠረቱ SIM Card is a or ማይክሮ መቆጣጠሪያን መሠረት ያደረገ የመዳረሻ ሞዱል (microcontroller-based access module) ወይም የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ መረጃን የሚያከማች (a small portable memory chip) ፣ የ 16 አኃዝ ወይም የ 17 አኃዝ ኮድ ያለው ሲሆን ግን እንደየሀገሩ ይለያያል የኔትወርክ አጓጓዥ መረጃን እና የሚያከማች አነስተኛ ተንቀሳቃሽ የማስታወሻ ቺፕ ነው ፡፡ ልዩ የተጠቃሚ መታወቂያ / የሞባይል ስልክ ቁጥር ነው። ✅ የሲም ካርድ ሲም ካርዶች በ 3 መሠረታዊ መጠኖች ይገኛሉ መደበኛ ፣ ማይክሮ እና ናኖ ፡፡ ከነዚህ ሶስት መጠኖች ውስጥ መደበኛ መጠኑ የመጀመሪያው ነው ፡፡ ማይክሮ እና ናኖ ሲም ካርዶች ከመደበኛው ሲም ካርድ ዙሪያ ያለውን ተጨማሪ ፕላስቲክን በመቁረጥ አነስተኛ እንዲሆኑ ተደርገዋል ፡፡ ለተሻለ ግንዛቤ የሚከተለውን ምስል ይመልከቱ ፡፡ ✅ የሲም ካርድ ዓይነቶች ሲም ካርዶች በዋናነት 2 አይነቶች ናቸው - GSM (ጂ.ኤስ.ኤም) እና CDMA (ሲዲኤምኤም) ናቸው። ✅ GSM ማለት (Global System for Mobiles) SIM ለሞባይል ዓለም አቀፍ ስርዓት ማለት ነው፡፡ በማንኛውም የሞባይል ስልክ ውስጥ ሊገባና ሊወጣ ይችላል፡፡ CDMA ማለት ሲተነተን Code Division Multiple Access ማለት ነው፡፡ አንዴ ከመጀመሪያው ስልክ ውስጥ ሊወገድ ወይም ሊወጣ አይችልም። ✅ eSIM ካርድ በአሁኑ ጊዜ eSIM Card ተብሎ የሚጠራ አዲስ የሞባይል ስልክ ግንኙነት ቴክኖሎጂ አለ ፡፡ eSIM ማለት Embedded ሲም ማለት ነው፡፡ እንደ GSMና CDMA SIM አይነት አይደለም ገና ስልኩ ሲሰራ አብሮ ከስልኩ ጋ ተጣብቆ የሚመረት ነው እንዲሁም በ eSIM ላይ ያለው መረጃ እንደገና ሊፃፍ ስለሚችል የኔትወርክ ኦፕሬተርዎን መለወጥ ይችላሉ ፡፡ ✅ ሲም ካርድ ክፍሎች እና ተግባር በሲም ካርድ ላይ የተለያዩ የወረዳ ክፍሎች የተለያዩ ተግባራት አሏቸው ፡፡ የሚከተለው የአንድ ሲም ዋና ዋና ክፍሎች ናቸው ፡፡ 🔷 1. VCC ( Power Supply ) የሲም የኃይል አቅርቦት ፒን ነው ፡፡ 5V DC ኃይልን ይደግፋል ፡፡ ሲም ካርዱ እንዲሰራ ይህ የቪ.ሲ ፒን ከ 5V DC ጋር መቅረብ አለበት ከዚያም በሲም ካርዱ ውስጥ የተካተተው IC(Integrated Circuit) ብቻ ነው የሚሰራው ፡፡ 🔷 2. RST ( Reset ) የሲም ካርዱን Signal እና ግንኙነቶችን (Communication) እንደገና ለማስጀመር የሚያገለግል ፒን ነው ፡፡ ይህንን ፒን ሲጠቀሙ ሲም ሁሉንም የወቅቱን Signal ዳግም በሚያድስ ነባሪው ሞድ ያደርገዋል ፡፡ የ RESET ፒን በሞባይል መሳሪያዎች ወይም በሲም ካርዱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ይሠራል። በአጠቃላይ ሲም ተጠቃሚዎች ይህንን ተግባር እንዲጠቀሙ አነስተኛ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡ 🔷 3. CLK ( Clock ) ሰዓት-ሲምውን ለprocessor የሰዓት Signal ይሰጣል፡፡ 🔷 4. GND (Ground) ሲም የIntegrated Circuit ያለው አነስተኛ የኤሌክትሮኒክስ ሃርድዌር እንደመሆኑ Ground ተብሎ ተሰይሟል ፡፡ GND አሁን ለሲም ካርዱ ትክክለኛ ሥራ ወረዳውን ያጠናቅቃል ፡፡ 🔷 5. VPP ( Voltage Programming Power ) ቀደም ሲል ይህ ፒን በሲም ካርዱ ማህደረ ትውስታ ውስጥ ያለውን ውሂብ ለመፃፍ ወይም ለመሰረዝ የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ቮልት ለመሸከም ያገለግላል ነገር ግን አሁን ይህ ስራ በVCC የሚሰራ ስለሆነ በጣም ጠቃሚ አይደለም፡፡ 🔷 6. SIM Data I/O Pin ግብዓት / ውጤት-በሞባይል ስልኮች በሲም ካርድ ውስጥ ያለውን data ለማንበብ እና ለመፃፍ ጥቅም ላይ ይውላል ፡፡ እንደ የdata ማስተላለፊያ ፒን የሚሰራ ግማሽ ባለ ሁለትዮሽ የግንኙነት ፒን ነው። ሲም ካርዱ እያነሰ እና እየቀነሰ ሲመጣ አፈፃፀሙ እና አቅሙ በየቀኑ እየጨመረ ሲሆን በአዲሱ ቴክኖሎጂ እና ምርምርም ምስጋና ይግባው ፡፡

HiTech
1 636
🔘ኮምፒውተሮት ላይ ምንም አይነት USB ሲሰካ ማንም ሳያቅ AUTOMATICALLY ሁሉንም ፋይል እንዴት መገልበጥ እንችላለን‼️ ✍ COPY DATA AUTOMATICALLY FROM USB 📤 TO YOUR PC 🖥 ON INSERT 1. open cmd 2. type copy filename.bat 3. now type xcopy i: f:\copied /h /s /c /q /i remove 4. type Exit 5. press f6 6. now it will create a batch file named filename.bat xcopy is a command which dataset used to copy file and folder i: is the name of your pen-drive name replace with your drive name f:\ copied is the name of folder where you wish to copied data is to be placed replace with your own folder or path /h is used to copy hidden files also Now copy this file on desktop. Whenever someone insert his/her USB into your system, then click on this file. His/Her data will automatically copied into the folder specified by you. ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

HiTech
1 636
ስለ ስልክ ቫይረስ ምን ያህል ያቃሉ ▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁ What is Virus ?? #Virus ማለት የ Computer Code ወይም Program ሲሆን ብዙ ግዜ የሚሰራው ወይም የሚፈጠረው የ Computer እውቀት ባላቸው ሰወች እና ስለ Computer ጠልቀው በ ተማሩ ሰወች ነው ቫይረስ ስንል ብዙ አይነት ቫይረሶች አሉ ➲Spyware Virus ➲Malware Virus ➲Ransonware Virus ➲Adware Virus ➲Trojan Horse Virus ናቸው እንደ ስማቸው ሁሉ ስራቸውም ይለያያል የ#Virus ዋና አላማው እና ስራው ምን ምን ናቸው ⓵ ስልካችንን ማበላሸት (Damage) ማድረግ የስልኩን Software ቫይረሱ በሚያጠቃበት ግዜ ስልኩ Dead ይሆናል ይህ ማለት ስልካችን Samsung ከሆነ ስንከፍተው Samsung ይልና ቀጥ ብሎ ይቆማል አይከፈትም ማለት ነው ⓶ በጣም ጠቃሚ ፋይል ማጥፋት እና መደበቅ ስልካችን ላይ ሆነ MemoryCard ላይ ያሉትን ማንኛውም (File) ለምሳሌ Music Photo Video Application Document ያለ ምንም ምህረት ያጠፋል (Format) ያደረጋቸዋል ያለኛ ትዛዝ እና ፍቃድ ⓷ ስልካችንን በማናውቀው Password ወይም Pattern መቆለፍ እና መዝጋት ይህ ማለት ስልካችንን የዘጋንበትን የሚስጥር Password ይቀይርና የራሱን Password በማስገባት ይቆልፍብናል ማለትም ስልካችንን ሙሉ በ ሙሉ በራሱ ቁጥጥር ስር ያደርገዋል እኛ ስልኩን ማዘዝ አንችልም ማለት ነው ⓸ ስልካችንን(OS)Operating System ስራ ማዛባት እና ስልኩ እንዲዘባርቅ ማድረግ ይህ ማለት ስልካችን ስራውን በትክክል እንዳይሰራ እንቅፋት ይሆናል ይህ ማለት እኛ ስልኩን ሳንነካው ሳናዘው በራሱ (File)መክፈት መዝጋት ስልኩን Flight Mode ላይ ማድረግ ስልኩን Switch Off ማድረግ ከዛ ስልኩን መልሶ መክፈት. ሌላም ብዙ ብዙ ነገሮችን በራሱ ይሰራል ⓹ Software File ማጥፋት የ ስልካችንን Software File Delete ማድረግ => Software File Delete ከሆነ ስልኩን ማስተካከል ከባድ ይሆናል ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉ ያለ ባለቤቱ ፍቃድ በራሱ መብት ይሰራል. ስለ #ቫይረስ አደገኛነት ጉዳት እና አላማ ይህን ካልን ስለ መከላከያው እና ስለ መፍትሄው ደግሞ እናያለን እንዴት አድርገን ስልካችንን ከአደገኛ ቫይረስ መጠበቅ እና መከላከል እንችላለን ⓵ ካልታወቀ እና #Fake ከሆነ ዌብሳይት ማንኛውንም ነገር ከ ማውረድ መቆጠብ ለምሳሌ ካልታወቀ እና #Fake ከሆነ ዌብሳይት Application ወይም File (Download) በምናደርግበት time #ቫይረሱ Download ከምናረገው Application ወይም File ጋር አብሮ ወደ ስልካችን በቀላሉ ይገባል ለምን ቢባል Fake የሆኑ #ድረገጾች ላይ #ቫይረሶች ብዙግዜ ስለሚለቀቁ ነው ሰለዚህ ከታወቀ እና ታማኝነት ካለው ዌብሳይት ብቻ የምንፈልገውን File ማውረድ ይጠበቅብናል ⓶ Bluetooth Email እና G-mail ክፍት አድርጎ አለመተው ተጠቅመን ከ ጨረስን በኋላ መዘጋቱን #Check Up ማድረግ ⓷ የስልካችንን #Software Update ማድረግ በሰአቱ እና በግዜ ስልካችን የSoftware Update ጥያቄ ሲጠይቀን #ችላ አለማለት ወድያውኑ ስልኩን Update መድረግ የስልካችን Software Update ከተደረገ ስልካችን በ ቫይረስ የመጠቃት እድል በጣም ዝቅተኛ ነው የ ስልካችንን Software Update ለማድረግ መጀመሪያ #Setting ውስጥ እንገባለን ከዛ መጨረሻ ላይ #About Phone የሚል አለ እሱን እንዴ #Click እንላለን ከዛ Software Update የሚለውን #Click ማለት ⓸ ትክክለኛ እና #Original Antivirus መጠቀም ስልካችን ላይ ያለውን ሁሉኑም Application እና File #Scan ማድረግ Scan በምናደርግበት ግዜ Virus ያለበት Application ወይም File ከተገኘ ወዲያውኑ ማጥፋት #Remove ማድረግ እነዚህን Original Antivirus ከ PlayStore በ ማዉረድ ተጠቀሙ ➷➷➷➷➷➷ ➊ #Norton Antivirus ➋ #KasperskyAntiVirus ➌ #BT Virus Protect: Mobile Anti-Virus & Security App እነዚህ Antivirusሶች የሚሰሩት በ Data እና በ Wifi Connection ⓹ ቫይረስ በዋናነት ከሚገባበት መንገድ አንዱ በ #Email ለምሳሌ በ #G -mail ነው Email ለምሳሌ በ G-mail በምንጠቀምበት ግዜ ከማናውቃቸው ሰወች #Link ሲላክልን ቶሎ መክፈት የለብንም ምክንያቱም የተላከው ከ #Hackerሮች (Linkኩም) ቫይረስ ሊሆን ስለሚችል በፍፁም መክፍት የለብንም ⓺ ስልካችን ላይ ያሉትን ሁሉኑም Application # Update ማድረግ ለምን ቢባል አንዳንድ Applicationኖች ከ ቆይታ ብዛት የተነሳ ወደ ቫይረስ ይቀየራሉ ስለዚህ ሁሉኑም Application በየጊዜው Update ማድረግ አለብን ስልካችን ላይ ያሉ Applicationኖችን Update ለማድረግ መጀመሪያ ወደ PlayStore ላይ እንገባለን ከዛ (My APP) ዉስጥ እንገባለን ከዛ Update መሆን ያለበት Application ካለ እራሱ ይህን Application Update አድርግ ብሎ ይጠቁመናል ከዛ Update የሚለውን #Click ማድረግ ⓻ Wifi በምንጠቀምበት ግዜ ከባድ ጥንቃቄ ማድረግ Wifi ከፍተን በምንጠቀምበት ሰአት ብዙ Notification ወደ ስልካችን ይገባሉ በዚህ ግዜ ወድያውኑ Notificationኑ ፍቃድ ይጠይቀናል (Allow or Decline) ብሎ ይጠይቀናል ? Notificationኑ ቫይረስ ይሁን አይሁን እኛ አናውቅም ነገርግን እኛ ችላ በማለት ወይም ትኩረት ባለመስጠት (Allow) ብለን እንፈቅዳለን በዛን ሰአት Notification መስሎ የመጣው #ቫይረስ በፍጥነት ወደ ስልካችን በመግባት ስልካችንን ያበላሻል ስለዚህ ማንኛውንም Notification ወደ ስልካችን ሲመጣ ዝምብለን ከመክፈት መታቀብ አለብን ⓼ ማንኛውንም Application ከሰው ስንቀበል ስለ Applicationኑ ምንነት እና ስራ በደንብ መረዳት አለብን ይህ ማለት Applicationኑ ጎጂ ሆነ ጥሩ የሚለውን እንድናውቅ ይረዳናል ስለዚህ ማንኛውንም Application ስልካችን ላይ ከመጫናችን እና ከ መቀበላችን በፊት ስለ Applicationኑ በደንብ መገንዘብ ያስፈልጋል ▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁

HiTech
1 636
#ካፓሲተር_ምንድን_ነው❓/ #What_is_Capacitor❓ ==================== 👉ካፓሲተር የኤሌክትሪክ ሀይልን(Electrical Energy) በኤሌክትሪካል ቻርጅ (Electrical change) መልክ ማከማቸት የሚችል የኤሌክትሪካል ኮፖነንት ነው። 👉ካፓሲተሮች በአይነት በጣም ብዙ ሲሆኑ ከበጣም ትናንሽ እስከ ትላልቅ ለፓወር ፋክተር ማስተካከያነት እስከሚያገለግሉት የሚገኝ ሲሆን ሁሉም ግን ተመሳሳይ አገልግሎት ነው ያላቸ፤ እሱም ኤሌክትሪክ ቻርጅ ማከማቸት(Store Electrical changes) ነው። 👉ካፓሲተር ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ትይዩ ኮንዳክቲቭ (ብረት) ሳህኖች እርስ በርስ የማይገናኙ ወይም የማይነካኩ ነገር ግን በኤሌክትሪክ የሚለያዩት በአየር ወይም በሌላ መከላከያ ቁሳቁስ ለምሳሌ በሰም በተሰራ ወረቀት፣ ሚካ፣ ሴራሚክ፣ ፕላስቲክ ወይም ሌላ የፈሳሽ ጄል እንደ ኤሌክትሮላይቲክ ካፓሲተር የሚያገለግሉ ናቸው። 👉በካፓሲተር ሰሌዳዎች(Capacitor plates) መካከል ያለው የኢንሱሌሽን ንብርብር በተለምዶ ዳይኤሌክትሪክ (Dielectric) ይባላል። 👉ካፓሲተሮች የተለያየ አይነት ያላቸው ቢሆኑም ሁሉም የተለዩ ቢያንስ ሁለት የኤሌክትሪክ ሊዶች (ሳህኖች) ይይዛ 👉ሊዶቹ የብረት ፣ የአሉሚኒየም ፎይል ወይም ዲስኮች ወዘተ ቀጭን ፊልሞች(thin films) ሊሆኑ ይችላሉ 👉ዳይኤሌክትሪክ (Dielectric) መስታወት ፣ ሴራሚክ ፣ የፕላስቲክ ፊልም ፣ አየር ፣ ወረቀት ፣ ማይካካ ፣ ወዘተ ሊሆን ይችላል። 👉 ከተቃዋሚ በተቃራኒ ፣ አንድ ካፓሲተር ኃይልን አያጠፋም። 👉ይልቁንም አንድ ካፓሲተር ኃይል በውስጡ ሳህኖች መካከል በኤሌክትሮ ስታቲክ መስክ መልክ ሃይልን ያከማቻል። 👉ካፓሲተር በኤሌክትሪክ አስተላላፊ እቃዎች ላይ ሊፈጠር የሚችል የሃይል ልዩነት ሲኖር (ለምሳሌ ፣ አንድ ካፓሲተር ከባትሪ ጋር ሲያያዝ) ፣ የኤሌክትሪክ መስክ በዳይኤሌክትሪክ ላይ ይገነባል ፣ ይህም ፖሰቲቭ የኤሌክትሪክ ቻርጅ (+Q) በአንድ ሳህን ላይ እንዲሰበሰብ እና ኔጌቲቭ የኤሌክትሪክ ቻርጅ (-Q) በሌላ ሳህን ላይ እንዲሰበሰብ ያደርጋል። 👉አንድ ባትሪ ከካፓሲተር ጋር ለተወሰነ ጊዜ ከተያያዘ ፣ ምንም የኤሌክትሪክ ፍሰት በካፓሲተሩ ውስጥ ሊፈስ አይችልም። ነገር ግን ፣ የተፋጠነ ወይም ተለዋጭ ቮልቴጅ በካፓሲተር ሊድ ላይ ከተተገበረ የመፈናቀያ ኤሌክትሪክ ፍሰት ሊፈስ ይችላል። #የካፓሲተር_አገልግሎት/ #Applications_of_Capacitor ➖የኤሌክትሪክ ኢነርጂ ለማከማቸት፣ ➖አላስፈላጊ ድግግሞሽን/frequency ለማስወገድ ➖የቮልቴጅ ለውጥን ለማዘግየት ➖እንደ ሴንሰር መሳሪያ(Sensing device) ሆኖ ያገለግላል። ➖ለተሽከርካሪዎች ድምፅ ለማውጣት ያገለግላል ➖AC እና DC ቮልቴጅን ለመለየት ያገለግላል።

HiTech
1 636
Adobe Photoshop CS6 Portable Full Version 13.1.2 64 bit Extract File @cellphonetechnolgy

HiTech
1 636
Advanced System Repair Pro 1.9.4.1 + License Key https://telegram.me/cellphonetechnology

HiTech
1 636
👉 ሲም ካርድ ምንድን ነው? - ሲም ማለት የተመዝጋቢ ማንነት ሞዱል SIM Stands for Subscriber Identity Module ከማንኛውም የሞባይል ስልክ በጣም አስፈላጊ አካል ነው፡፡ - በአንዳንድ አገሮች ICC (Integrated Circuit Card ) and UICC ( Universal Integrated Circuit Card ) በመባልም ይታወቃል፡፡ በቀላል አነጋገር ሲም ካርድ በመሠረቱ SIM Card is a or ማይክሮ መቆጣጠሪያን መሠረት ያደረገ የመዳረሻ ሞዱል (microcontroller-Based Access Module) ወይም የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ መረጃን የሚያከማች (A Small Portable Memory Chip) የ 16 አኃዝ ወይም የ 17 አኃዝ ኮድ ያለው ሲሆን ግን እንደየሀገሩ ይለያያል... የኔትወርክ አጓጓዥ መረጃን እና የሚያከማች አነስተኛ ተንቀሳቃሽ የማስታወሻ ቺፕ ነው፡፡ ልዩ የተጠቃሚ መታወቂያ/የሞባይል ስልክ ቁጥር ነው። - የሲም ካርድ ሲም ካርዶች በ 3 መሠረታዊ መጠኖች ይገኛሉ መደበኛ ማይክሮ እና ናኖ ከነዚህ ሶስት መጠኖች ውስጥ መደበኛ መጠኑ የመጀመሪያው ነው፡፡ - ማይክሮ እና ናኖ ሲም ካርዶች ከመደበኛው ሲም ካርድ ዙሪያ ያለውን ተጨማሪ ፕላስቲክን በመቁረጥ አነስተኛ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ ለተሻለ ግንዛቤ የሚከተለውን ምስል ይመልከቱ ፡፡ 📍የሲም ካርድ ዓይነቶች ሲም ካርዶች በዋናነት 2 አይነቶች ናቸው - GSM (ጂ.ኤስ.ኤም) እና CDMA (ሲዲኤምኤም) ናቸው። 👉 GSM ማለት (Global System for Mobiles) SIM ለሞባይል ዓለም አቀፍ ስርዓት ማለት ነው፡፡ በማንኛውም የሞባይል ስልክ ውስጥ ሊገባና ሊወጣ ይችላል፡፡ 👉 CDMA ማለት ሲተነተን Code Division Multiple Access ማለት ነው፡፡ አንዴ ከመጀመሪያው ስልክ ውስጥ ሊወገድ ወይም ሊወጣ አይችልም። 👉 eSIM ካርድ በአሁኑ ጊዜ eSIM Card ተብሎ የሚጠራ አዲስ የሞባይል ስልክ ግንኙነት ቴክኖሎጂ አለ፡፡ eSIM ማለት Embedded ሲም ማለት ነው፡፡ እንደ GSMና CDMA SIM አይነት አይደለም ገና ስልኩ ሲሰራ አብሮ ከስልኩ ጋ ተጣብቆ የሚመረት ነው እንዲሁም በ eSIM ላይ ያለው መረጃ እንደገና ሊፃፍ ስለሚችል የኔትወርክ ኦፕሬተርዎን መለወጥ ይችላሉ ፡፡ 📍 ሲም ካርድ ክፍሎች እና ተግባር በሲም ካርድ ላይ የተለያዩ የወረዳ ክፍሎች የተለያዩ ተግባራት አሏቸው ፡፡ የሚከተለው የአንድ ሲም ዋና ዋና ክፍሎች ናቸው ፡፡ 1. VCC ( Power Supply ) - የሲም የኃይል አቅርቦት ፒን ነው ፡፡ 5V DC ኃይልን ይደግፋል፡፡ ሲም ካርዱ እንዲሰራ ይህ የቪ.ሲ ፒን ከ 5V DC ጋር መቅረብ አለበት ከዚያም በሲም ካርዱ ውስጥ የተካተተው IC (Integrated Circuit) ብቻ ነው የሚሰራው ፡፡ 2. RST ( Reset ) - የሲም ካርዱን Signal እና ግንኙነቶችን (Communication) እንደገና ለማስጀመር የሚያገለግል ፒን ነው ፡፡ ይህንን ፒን ሲጠቀሙ ሲም ሁሉንም የወቅቱን Signal ዳግም በሚያድስ ነባሪው ሞድ ያደርገዋል ፡፡ የ RESET ፒን በሞባይል መሳሪያዎች ወይም በሲም ካርዱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ይሠራል። በአጠቃላይ ሲም ተጠቃሚዎች ይህንን ተግባር እንዲጠቀሙ አነስተኛ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡ 3. CLK ( Clock ) - ሰዓት-ሲምውን ለ processor የሰዓት Signal ይሰጣል፡፡ 4. GND (Ground) -ሲም የ Integrated Circuit ያለው አነስተኛ የኤሌክትሮኒክስ ሃርድዌር እንደመሆኑ Ground ተብሎ ተሰይሟል ፡፡ GND አሁን ለሲም ካርዱ ትክክለኛ ሥራ ወረዳውን ያጠናቅቃል፡፡ 5. VPP ( Voltage Programming Power ) - ቀደም ሲል ይህ ፒን በሲም ካርዱ ማህደረ ትውስታ ውስጥ ያለውን ውሂብ ለመፃፍ ወይም ለመሰረዝ የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ቮልት ለመሸከም ያገለግላል ነገር ግን አሁን ይህ ስራ በVCC የሚሰራ ስለሆነ በጣም ጠቃሚ አይደለም፡፡ 6. SIM Data I/O Pin - ግብዓት / ውጤት-በሞባይል ስልኮች በሲም ካርድ ውስጥ ያለውን data ለማንበብ እና ለመፃፍ ጥቅም ላይ ይውላል ፡፡ እንደ የ data ማስተላለፊያ ፒን የሚሰራ ግማሽ ባለ ሁለትዮሽ የግንኙነት ፒን ነው። ሲም ካርዱ እያነሰ እና እየቀነሰ ሲመጣ አፈፃፀሙ እና አቅሙ በየቀኑ እየጨመረ ሲሆን በአዲሱ ቴክኖሎጂ እና ምርምርም ምስጋና ይግባው ፡፡ ⚡️Share And Support Us. Telegram chanal @cellphonetechnology