cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Mind programming

Business and personal development opportunity 👇👇👇👇 @Gech1921 t.me/purposoflife

Больше
Рекламные посты
216
Подписчики
Нет данных24 часа
+37 дней
+830 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

1:32:19
Видео недоступноПоказать в Telegram
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟     #THE_SECRET - #ምስጢሩ -›ወርቃማው ሕግ low of attraction -›መጠየቅ :ማመን :ማመስገን -›ከአውንታዊ ሃሳቦች ጋር መቆራኘት -positive thinkers. እነዚህና ሰፊ ተጨማሪ ነገሮችን በመያዝ በ •The Secret - ምስጢሩ •The Sower ታላቁ ኃይል •Magic - ታላቁ ምስጢር •Hero - ጀግና •How to use the secret - ምስጢሩን መጠቀም ሚቁአጨው አስደናቂው መፅሐፍ በ ፊልም መልክ ቀርቦላቹአል:: ከመፅሐፉ ባይደርስም ፊልሙን ወደዛው ይጠጋልና እስኪ ተጋበዙልኝ 🙏      
Показать все...
31.51 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
በፍጹም አታቁም! “አንድ ጊዜ ነገሮችን በቀላሉ የማቆም ልምምድ ከጀመርክ ሁኔታው ልማድ ይሆንብሃል” - Vince Lombardi በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ! ጠቃሚና ዋጋ ያለው ግብን የምትከታተል ከሆነ፣ የሆነ ጊዜ ላይ ከዚህ በታች ያሉትን ሃሳቦች ማስተናገድህ አይቀርም፡ •  “ይህ ነገር ካሰብኩት በላይ ከባድ ነው፡፡” •  “ለምንድን ነው ይህ ነገር ይህን ያህል ረጅም ጊዜ የወሰደብኝ?” •  “ይህ ነገር ወደፊት አላራምድ አለኝ፡፡” •  “ይህ ግብ ደጋግሞ እየተበላሸብኝ ነው፡፡” •  “ይህንን ነገር መቀጠል የምችል አይመስለኝም፡፡ ምን አስቤ ነው የጀመርኩት?” በእዚህና በመሰል ስሜቶች ከጀመርከው ነገር እንዳትገታ ከፈለክ “በፍጹም አላቆምም” የሚልን አመለካከት አዳብር፡፡ ተስፋ አለመቁረጥ የአመለካከት ጉዳይ ነው፡፡ ይህም አመለካከት ልታዳብረው የምትችለው አመለካከት ነው፡፡ ይህንን አመለካከት ለማዳበር ከሚረዱህ ልምምዶች መካከል የሚከተሉትን ሃሳቦች ደግመህና ደጋግመህ ለራስህ መናገር ነው፡- •  ነገሮች ሲከብዱብኝ በዓላማዬ ጸንቼ እቀጥላለሁ፡፡ •  መንገድን እፈልጋለሁ ወይም እፈጥራለሁ፡፡ •  ማንኛውም ችግር መፍትሄ አለው፣ እኔ ደግሞ መፍትሄውን ለማግኘት ብቃቱ አለኝ፡፡ •  በየቀኑ የሚሰራውንና የማይሰራውን የመለየትን እውቀትና ግንዛቤ እያገኘሁ ነው፣ ይህም ማለት በጥንካሬና በጥበብ እየጨመርኩኝ ነው ማለት ነው፡፡ •  መሰናክሎች ጊዜያዊ ናቸው፡፡ ከላይ ያሉትን ሃሳቦች ለራስህ ከተናገርክ በኋላ ቆም ብለህ አስብ! እንደገናም ወደፊት ቀጥል! (“ጀምሮ መጨረስ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)
Показать все...
ለ.......(ሰው) ስትል አንተ ብትጠነክር አንተን አይቶ የሚጠነክር አለ - አንተ ብትወድቅ አንተን አይቶ ተስፉ የሚቆርጥ አለ - ልጅህ ሊሆን ይችላል ወይ እናት ፣ አባት ፣ እህት ወንድም ወይም ጓደኛ ወይም ደግሞ ላታውቀው ትችላለህ ግን ያንተን ጥንካሬ አይቶ እሱ ከቻለ እኔስ ለምን ያቅተኛል የሚል ሰው አይጠፉም - በተቃራኒው እሱ እንኳን ተስፉ ቆርጦ የለ ብሉ ተስፉ የሚያጣ ሰው አለ - ለራስህ መበርታት ቢያቅትህ እንኳን ለእነዚህ ሰዎች ስትል በርታ። - ለእናትህ ስትል ፣ ወይ ለልጅህ ፣ ወይ ለወንድምህ ፣ እህትህ ፣ ጓደኛህ ስትል ጠንከር በል።   መልካም  ቀን
Показать все...
🙅‍♂ አእምሮን መቆጣጠር አእምሮአችን ብዙ ጊዜ እኛን ይቆጣጠረናል የእኛም አለቃ ይሆናል። ሳንፈልግ እንድንዋሽ እንድንሰርቅ እንድናጭበረብር ይገፉፉናል Ego ይሉታል አንዳንዶች። ተመልሶ ይመጣና እንደ ፖሊስ 👮 ለምን ይሄን አደረክ ? ይለናል። መጀመርያ ሌባ ያደረገን ያ አስተሳሰብ መልኩን ለውጦ ጨዋ መስሎ ይመጣል። ልብ ብላችሁ አስተውሉ የማትፈልጉትን እንድታረጉ የሚገፉፉችሁ ድምጽ አለ። ይህንን በአእምሮአችሁ ያለ ድምጽ የራሳችሁ መስሏችሁ ከራሳችሁ ጋር ትጣላላችሁ። ይህ ግን ውሸት ነው ያ ድምጽ አለም አእምሮአችሁን ፕሮግራም ያደረገው ነው። አሁን ያ ፕሮግራም ⏯️ play/ ሲል መጫወት ሲጀምር ነው የምታደርጉትን ምታደርጉት። -
አእምሮአችሁ ውስጥ ያለውን ውግያ ካሸነፉችሁ ብቻ ነው በአለም ላይ ምትፈልጉትን ስኬት ምታገኙት!
ጠንክራ ሁኑ!!! አላማችሁ ትልቅ እስከሆነ ድረስ ገና ከዚህ በላይ... ፈተና ይመጣልና ተዘጋጁ
Показать все...
ስራ-ፈት አትሁኑ! ፨፨፨//////፨፨፨ ለምንም ነገር እራሳችሁን ካልሰጣችሁ በሁሉም ነገር መረበሻችሁ አይቀርም። ስራፈትነት ከውጤት አልባነት በዘለለ ብክነትንም ያስከትላል። የማይረባ ሃሳብ መነሻው ከስራፈት አዕምሮ ነው። ስራ ፈቶ መቀመጥ ለማንም ከባድ አይደለም፣ ማንንም የሚፈትን አይደለም። ስራፈት መሆንን መምረጥ መብት ነው፣ ህይወት ግን ለስራፈቶች ቦታ የላትም። እንኳን ያለስራ ተቀምጦ ይቅርና ቀኑን ሙሉ እየሰሩም ህይወት ክብደቷን አትቀንስም። መጥፎ ሀሳቦች የሚቆጣጠሩን መቼ ይመስሏችኋል? በቀላሉ ለሱስና ለአሉታዊ ልማዶች የምንጋለጠው መቼ ይመስላችኋል? በእርግጥም ያለስራ የምናሳልፈው ጊዜ ብዙ ሲሆን ነው። የሰው አዕምሮ በስራና በፈጠራ ሀሳቦች ካልተወጠረ በቀላሉ ለውዳቂና ጥቃቅን ሀሳቦች መጋለጡ አይቀርም። ሁሌም እድገት በሌለው ኋላቀር ሀሳብ ስትሞሉ ልባችሁ እየደነደነ፣ ግዴለሽና ተስፋቢስ እየሆናችሁ ትመጣላችሁ። ስራ ገቢ ከማምጣቱም በላይ የህሊና እረፍትን ይሰጣል። ያለምንም ስራ ቁጭ ብሎ መዋልና እራስን በስራ መወጠር የሚሰጡት የህይወትና የሀሳብ ነፃነት እኩል አይደለም። አዎ! ስራ-ፈት አትሁኑ! አዕምሯችሁን በሚያሳድጓችሁ ሀሳብና ስራ ወጥሩ፣ ነፃነትን በሚነፍጓችሁ ብዙ ነፃና የእረፍት ጊዜያት ህይወታችሁን አትሙሉ። የተገደበ እረፍትና የተገደበ የስራ ሰዓት ያስፈልጋችኋል። ስራፈት አዕምሮ የሰይጣን መነሃሪያ ነው። ሰይጠናን እንደፈለገው ይመራዋል፣ የፈለገውን ያስደርገዋል፣ ያሰኘው ነገር ውስጥ ይከተዋል። ስራፈት ስትሆኑ ሰይሰን ብቻ ሳይሆን የሰውም መጫወቻ ትሆናላችሁ። ይብዛም ይነስም ስራ በእራሱ ክብር ነው፣ አንድ መዋያና አዕምሮን ማሳረፊያ ነገር ማግኘት በእራሱ ስኬት ነው። ምንም ቢሆን ካለመስራት መስራት ይሻላል፣ የማይረባ ሀሳብ ከማሰብ ጠቃሚና ህይወት ቀያሪ ሀሳብን ማሰብ ይሻላል። ሁን ብላችሁ እራሳችሁን ጫና ውስጥ ክተቱት፣ ስራፈት በመሆን በማያሳድጋችሁ ምቾት ውስጥ አትቀመጡ። ወጣ በሉ፣ እራሳችሁን ፈትኑት፣ አቅማችሁን መዝኑ፣ እውቀታችሁን በተግባር ግለጡት። ተቀምጦ መናን ከሰማይ መጠበቅ አያዋጣም። ምንም ቢሆን መናው እስከሚወርድበት ቦታ መጓዝ የግድ ነው። "ሳይሰሩ የሚበሉ እጆች የተረገሙ ይሁኑ" እንደሚል መፅሀፍ ቅዱስ እራሳችሁን የወጣት ተጧሪ አታድርጉ። አዎ! ጀግናዬ..! ተንቀሳቀስ፣ ዞር ዞር በል፣ ለእድገትህ መሱዓትነት ለመክፈል ተዘጋጅ። አርሶ፣ ዘረቶ፣ አርሞ፣ አጭዶ፣ ወቅቶ ሰብሉን ለገበያ የሚያቀርበውን የብርቱውን ገበሬ ታታሪነት ተመልከት። መስራት ብቻ ሳይሆን ጠንክሮ መስራት በራሱ ዲኤንኤው (DNA) ውስጥ ነው። ማንነቱን ለስራ አሳልፎ ሰጥቷልና በቀላሉ የማይሰበር ጠንካራ ልብ አለው፣ የእጆቹን ስራ ፈጣሪው እንደሚባርክለት ከልቡ ያምናል፣ ፅናቱና ታታሪነቱ እንደሚከፍለው ያውቃል። ስራ ስትፈታ እጆችህ የሰይጣን መጠቀሚያ ይሆናሉ። ለመብላት መዝረፍ ትጀምራለህ፣ ስራፈትነትህን ለመርሳት ወደ ሱስ ትገባለህ፣ በአጭር ጊዜ ገንዘብ ለማግኘት ወንጀልን ጨምሮ የተለያዩ አቋራጭ መንገዶችን ትጠቀማለህ። ስራ አትናቅ፣ ከሚያስገኝልህ ገንዘብ በላይ የሚሰጥህን የሰራተኝነት ነፃነት አስብ። ስራ እየናቁ ተንቀው የቀሩ ብዙ ሰዎች አሉ፣ ስራ እየመረጡ ምራጭ ሆነው የቀሩ ብዙ ሰዎች አሉ። ዛሬ በገቢው ያነሰ ስራን ብትሰራ ሁሌም እርሱን እየሰራህ አትኖርም። የሰው ልጅ ምንም ሰርቶ ምንም ገቢ ቢያገኝ አጠቃቀሙን ካወቀበት በሂደት እራሱን ማሳደጉ አይቀርም። ጠንቃቃ ሁን፣ ስራህን አክብር፣ ልብና አዕምሮህን አስገዛለት፣ ጠንክረህ ስራ የነገው ህይወትህንም ዛሬ እራስህ ወስን። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
Показать все...
#ዋጋህን_እወቀው! መነበብ ያለበት አስተማሪ ታሪክ "ትናንት ማታ አንድ ቪዲዮ እያየሁ ነበር። ሰባኪው የመቶ ብር ኖት ይዟል። እንዲህ ሲል ሰማሁት 'ይህ የብር ኖት እንደታተመ ምንም ዓይነት መጨማደድ አልነበረበትም። ከዚያ በኋላ ግን ሰዎች፦ 👉እጽ ለመግዛት ተጠቅመውታል። 👉 ለዝሙት ከፍለውታል። 👉ጭቃ ውስጥ ነበር። 👉ተቀዷል፣ 👉ጠርዞቹ ተቆርጠዋል። ከዚህ ሁሉ ቀኋላ ይህ የመቶ ብር ኖት አሁን ዋጋው ስንት ነው? አሁንም ዋጋው ያኔ አዲስ በነበረበት ጊዜ የነበረው ዋጋ ነው። አምላካችንም እኛንም የሚያየን እንደዚህ ነው። ያለፈው ታሪካችን ምንም ሆነ ምንም፣ የቱንም ያህል የተጎዳን እንሁን፤ ለእሱ ዋጋችን ያኔ ሲፈጥረን እንደነበረው ነው።' "
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ያስቸገረኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር! ተወልዶ ካደገበት ሃገሩ በተፈጠሩ ማሕበራዊ ቀውሶች ምክንያት ወደሌላ ሃገር በስደት ለመሄድ የቆረጠ አንድ ሰው ረጅም፣ አድካሚና አስፈሪ የሆነን በረሃ ለቀናት በእግሩ በመሄድ ካቋረጠ በኋላ እጅግ ደክሞና ዝሎ ነበር፡፡ በመጨረሻም በደረሰበት አንዲት ከተማ ውስጥ በተሰጠው እርዳታ ትንሽ አገገመ፡፡ የዚህን ሰው ጉዞ የሰማና ለሕብረተሰቡ ለማቅረብ የፈለገ አንድ ጋዜጠኛ አገኘውና አንድን ጥያቄ ጠየቀው፡፡ “ተጉዘህ የመጣኸው በረሃ ብዙ ሰው የማይደፍረው በረሃ ነው፡፡ ለመሆኑ በመንገድህ ላይ በጣም የጎዳህና ያስቸገረህ ውኃ ጥም ነበር? ምግብ ማጣት ነበር? አውሬ ነበር? ሽፍቶች ነበሩ? ወይስ . . . ? የዚህ ስደተኛ መልስ ለጋዜጤኛው ያልተጠበቀ ነበር፡፡ በዚህ አደገኛ በረሃ አቋርጬ ስመጣ በጣም ያስቸገሩኝ የጠቀስካቸው ትልልቅ ነገሮች አልነበሩም፡፡ ጉዞየን በጣም አድካሚና አስቸጋሪ ያደረገብኝ በእርምጃዬ ወቅት ጫማዬ ውስጥ እየገባ የሚቆረቁረኝና አላራምድ ያለኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር፡፡ የሕይወት ጉዞም እንዲሁ ነው! አብዛኛውን ጊዜ የሚያስቸግረን፣ የሚቆረቁረን፣ አላራምድ የሚለንና ከዓላማችን የሚጎትተን ችግር ትልልቁ አይደለም፡፡ በየቀኑ የሚያጋጥሙን ጥቃቅን “አሸዋዎች” ናቸው፡፡ ትንንሽ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ባህሪይ፣ ትንንሽና አናሳ ወሬን የሚያወሩ ሰዎች ሁኔታ፣ ትንንሽና ስሜትን የሚነካኩ የየቀን ገጠመኞች . . . ጉዟችንን አዳጋችና አድካሚ ያደርጉታል፡፡ “በትንንሽ” ሰዎችና ሁኔታዎች ሳትበገሩ ትልቁ የሕይወት ስእልና ዓላማችሁ ላይ በማተኮር ወደፊት መገስገስን ያወቃችሁበት ጊዜ ዋናውን የሕይወት ድል የተጎናጸፋችሁበት ጊዜ ነው፡፡ በርቱ!
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
መፍራትን አትፍራው! እንደ ፍርሃት፣ ድንጋጤና ስጋት አይነት ስሜቶች ሰው ከአደጋ እንዲጠነቀቅ ከፈጣሪው የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ስሜቶች በአግባቡ ልንጠቀምባቸውና ከአደጋ ልንጠበቅባቸው ሲገባን ለአንዳንድ ሰዎች የኑሮ ዘይቤ ሆነዋል፡፡ የመውደቅ ፍርሃት፣ የመክሰር ፍርሃት፣ ያለመወደድ ፍርሃት፣ ብቻ የመቅረት ፍርሃት፣ … ጣጣችን ብዙ ነው፡፡ በፍርሃት ስንወረስ፣ ሕይወታችንን በራእይ መምራት እናቆምና ለፍርሃት ምላሽ በመስጠት መምራት እንጀምራለን፡፡ ከአንዱ ራእይ ወደሌላኛው በማለፍ ሕይወትን “ልናጠቃት” ሲገባን የመጣው ሁሉ የኑሮ ገጠመኝ የሚያጠቃን ቋሚ ኢላማዎች እንሆናለን፡፡ ቆመን ለመጣው ወይም የመጣ ለመሰለን ጥቃት ምላሽ በመስጠት ጊዜአችንን እናባክናለን፡፡ ይህ ሲሆን የቆመ ኢላማ ሆንን ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ከአንዱ ግብ ወደሌላኛው በአላማ የምንንቀሳቀስ ሰዎች ስንሆን አይኖቻችን ከችግሩ ላይ ይነሱና መፍትሄው ላይ ማረፍ ይጀምራሉ፡፡ የፍርሃትህ ጥልቀት አእምሮህ የፈቀደለት ያህል ነው” - Unknown Source ፍርሃት በሕይወትህ ብቅ ጥልቅ ማለቱ አያስፈራህ፡፡ በዚያ ፍርሃት ምክንያት ግን መንቀሳቀስ እስኪያቅትህ ድረስ እንዳትታሰር ፍራ፡፡ ማንኛውም ሁኔታ አንተን የማስፈራራት ሙከራ የማድረግ ሙሉ መብት አለው፡፡ አንተ ካልፈቀድክለት ግን ሊያስፈራራህ አይችልም፡፡ ትፈራለህ፣ ፈሪ ግን አይደለህም፡፡ “በፍጹም አልፈራም” ብለህ ካሰብክና ከተናገርክ ከፍርሃት የተደበቅህ ሰው እንደሆንክ አመልካች ነው፡፡ በሌላ አባባል፣ የፍርሃት ስሜት እንዳይመጣ መከልከል አትችልም፣ ይህንን ስሜት ለማስተናገድ የተፈጠረ ማንነት ስላለህ፡፡ ሆኖም፣ የፍርሃትን ጥልቀትና በአንተ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ጉዳት የመወሰን ሙሉ መብትም ሆነ ብቃት አለህ፡፡
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ግንቦት 23 ,24,25/2016 ዓ.ም May 31/2024- June 1,2/2024     የአልፋ ጥቅል ስልጠና       📍በአሶሳ  የኃያል ሂደት ስልጠና በአማርኛ የሚሰጥበት ቦታ፦   - ባንቡ ፖራዳይዝ   ሆቴል     📍በአዋሳ   የኃያል ሂደት ስልጠና በአማርኛ የሚሰጥበት ቦታ፦ -ሳውዝስታር  ሆቴል 📍 በሆሳዕና የሃያል ሂደት ስልጠና በአማርኛ የሚሰጥበት ቦታ፦ -  ቪክትሪ ሆቴል 📍በባሌ ሮቤ   የልምድ ግንባታ  ስልጠና በኦሮሚኛ የሚሰጥበት ቦታ፦   ዪኒየን አዳራሽ 📍በመቀሌ የሃያል ሂደት ስልጠና በአማርኛ የሚሰጥበት ቦታ፦ -  አክሱም ሆቴል - ዘማሪያስ ሆቴል -ካራሜል ሆቴል ✨ባለራዕይ፣ ቅን፣ ጤናማ እና ባለፀጋ ትውልድን መፍጠር!✨ 📍አዲስ አበባ፣ ቦሌ  ክፍለ-ከተማ፣ ወረዳ 3 ሽልም ህንፃ 4ተኛ ፎቅ 🌐 www.alphagenuine.com ☎️ +251930020395 Bole Branch        +251903441155 Adama Branch
Показать все...
who is ready
Показать все...