ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Открыть в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 16 126 подписчиков, занимая 5 230 место в категории Религия и духовность и 2 226 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 16 126 подписчиков.

Согласно последним данным от 31 октября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 520, а за последние 24 часа — 7, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 22.41%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 10.30% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 3 597 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 653 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 28.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 01 ноября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

16 126
Подписчики
+724 часа
+197 дней
+52030 дней
Архив постов
#ቅዱስ_ፊልሞና_ሐዋርያ_(_ጥዑመ_ቃል) ✤ከ72ቱ አርድእት አንዱ የኾነና 'ጥዑመ ቃል (አንደበቱ የሚጣፍጥ) በመባል የሚታወቅ ሲኾን፤ በዘመነ ሐዋርያት በጣም ልጅ በመሆኑ እየተሯሯጠ ለአበው ይታዘዝ ነበር፡፡ ከቅዱስ እንድርያስ ጋር ለስብከት ወጥቷል፤ ሃገረ ስብከቱም ልዳ ነበረች፤ እርሱ ሲያስተምርና ሲያነብብ ሰው ሁሉ በተመስጦ ይሰማው ነበር፤ አንዳንድ ቀን ደግሞ ወፎችና ርግቦች ያደምጡት ያዋሩትም ነበር፡፡ ሊገድሉት የመጡ ወታደሮች እንኳን በተደሞ መግደላቸውን ይረሱት ነበር፡፡ ይህ ታላቅ አርድእትና ሐዋርያ በዛሬው ዕለት ነው ያረፈው፡፡

#ያዕቆብ_ዘግሙድ_፤_የፋርሱ_ኰከብ፤ 42 አካላቱ ተቆራጠው ሰማዕት የኾነ፡፡ *ከክርስቲያን ቤተሰብ የተወለደው ቅዱስ፤ ሚስት አግብቶ በዘመኑ የነበረው ንጉሥ ሠክራድ ጋር በጣም ይዋደዱና አማካሪውም ነበርና በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ሹም አድርጐ አስቀመጠው፤ በሒደትም ንጉሡ የሚለውን ሁሉ የሚፈጽም ሰው ሆነ፤ ንጉሡም "ለእሳትና ለፀሐይ ስገድ፤ እነሱንም አምልካቸው" ሲል ጠየቀው:: ያዕቆብም ገና በእምነት ያልጠነረ በመኾኑና ከንጉሡ ጋር ወዳጅ ስለነበረ ንጉሡን ለማስደሰት ብሎ የክርስትና እምነት የማይፈቀድወን ለሌሎች አማልክት (ለፀሐይ ሰገደ፤ እርሷንም አመለከ)፤ ክርስቲያኖቹ ይህንን ሲሰሙ እጅግ አዘኑ ይልቁኑ ደግሞ የቅርብ ወዳጆቹ የሆኑት እናቱ፥ እኅቱና ሚስቱ ይህንን ሲሰሙ እጅግ በማዘናቸው ደብዳቤ ጽፈው ተፈራርመው ላኩለት፤ የደብዳቤው ይዘት እንዲህ ይላል፤ "አንተ ክርስትናህን መካድህን ሰምተን አዘንን፤ በዚህም ምክንያት ከዚህ በኋላ በአካባቢህ መኖርን አንፈልግም፤ ከቅዱሳት መጻሕፍትም እየጠቀሱ፤ ለሞተልህ ለክርስቶስ ካልታመንሀ እኛ አንተን እንደ ልጅ፣ እንደ ወንድምና እንደ ባል ልናምንህ ይከብደናል፡፡››፤ ይህንን ደብዳቤ ልከውለት እነርሱ አካባቢውን ለቀቁ፤ ቅዱስ ያዕቆብ ደብዳቤውን ተቀብሎ ወደ ቤቱ ገብቶ ሲያነበው ደነገጠ፤ በዚህ ምድር ያሉት ዘመዶቹ ሚስቱ፣ እናቱና አንዲት እኅቱ ብቻ ናቸውና ውስጡ ተሸበረ፤ ተደፍቶም ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡ *በመሸም ጊዜ ጸሎት ሲያደርግ ከንጉሡ ጋራ ያደረገውን ያልተገባ ቅርርብና ስህትት እግዚአብሔር ግልጽ ብሎ እንዲታየው አደረገ፤ እርሱም ‹‹ጌታ ሆይ፤ በምድር ካሉ የሥጋ ዘመዶቼ መለየት እንዲህ ካሸበረኝ፤ ካንተ ፍቅር መለየትማ እንደ ምን ይጨንቅ ይሆን፡፡ በሰማያዊ ዙፋንህ ፊትስ እንዴት ብዬ እቆማለሁ፡፡›› እያለ ሌሊቱን ሙሉ በእንባና በጸሎት አድሮ በጠዋት ንስሐ ገባ፡፡ ከዚህች እለት ጀምሮም ፍፁም በክርስቶስ ፍቅር ተጠመደ፤ ጾምና ጸሎትንም ወዳጆቹ አድርጐ ከንጉሡ እልፍኝና አደባባይ ቀረ፡፡ *ንጉሡም ይህንን በሰማ ጊዜ ጠርቶ ለምን እንዲህ አደረግክ ሲለው፤ ‹‹የፈጠረኝን ክርስቶስን ትቼ አንተን በባዕድ አምልኮ አስደስትህ ዘንድ የሚገባ አይደለም›› ሲል ተናገረው፤ ንጉሡም በብዙ ሽንገላ ሊያታልለው ቢሞክር እምቢ ስላለው ብዙ መከራን አደረሰበት ደሙ በመሬት ላይ እስኪንፈስ ድረስም አስገረፈው፣ አስደበደበው:፤ ጭንቅ መከራዎችንም አደረሰበት፡፡ **ቅዱሱ ግን በፍቅረ ክርስቶስ ጸና፤ በዚህ የተበሳጨው ንጉሡ በየቀኑ አካሉን እንዲቆራርጡት ግን ቶሎ እንዳይገሉት አዘዘ፡፡ ቀን በቀን እየገቡ ከአካሉ ይቆርጡ ጀመር፡፡ መሐል አካሉ (ወገቡና ራሱ) ብቻ እስኪቀሩ ድረስም ከጣቶቹ ተነስተው እጆቹን እስከ ክንዱ፤ እግሮቹን እስከ ታፋው ድረስ፤ ደረቱና አካሉ ግንድ እስኪመስል ድረስ ቆረጡ፤ ቅዱሱም እንዲህ እያለ በትጋት ይጸልይ ነበረ ‹‹የወይን ግንድ ሆይ፤ እኔን ቅርንጫፍህ አድርገኝ›› /ዮሐ. 15፥:5/ ይለው ነበር፤ ከአካሉ እየቆረጡ የጣሉትም ሲቆጠር 42 ሆነ:: 43ኛ ደግሞ የተረፈ ደረቱና አካሉ ነበርና፤ ተቆንጽሎ በቀረው ግማሽ አካሉ ‹‹አቤቱ ወደ አንተ የማነሳው አካል የልቀረልኝምና ነፍሴን ተቀበል›› እያለ ይጸልይ ነበር፤ ጌታችንም ተገልጾ ካረጋገው፣ ካጽናናውና ብዙ ቃልኪዳንን ከሰጠው በኋላ ከንጉሡ ጭፍሮች መካከል አንዱ መጥቶ አንገቱን በሰይፍ ቅረጠውና የሰማዕትነቱ ፍጻሜ ኾነ፡፡ ጌታችንም ነፍሱን ታቅፎ ወደ ሰማይ አሳረገው፡፡ እናቱ፣ እኅቱና ሚስቱ ይህንን ሲሰሙ እያለቀሱና እየዘመሩ አካሉን ሰብስበው በክብር ቀበሩት፤ በደጋጎቹ ክርስቲያኖች በአኖሬዎስና በአርቃዴዎስ ዘመን ምዕመናን ውብ ቤተ ክርስቲያን ሰርተው በዚያ ሥጋውን በክብር አኖሩ፡፡ ✤#_አቡነ_ተክለ_ሐዋርያት_ዘደብረ_ጽሙና_(_ዘገበርማ) **በምድረ አፋር(ለ14ዓመታት)፣ እንዲሁም በምድረ ሸዋና ጐጃም የሰበኩና ያስተማሩ አባት ናቸው፡፡ ከአባታቸው እንድርያስ (የአናዕርት ሃገረ ገዥ)ና ከእናታቸው እሌኒ፤ በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተወለዱና በዘመኑ ካሉ ዐበይት ጻድቃን አንዱ ናቸው፡፡ ገና በእናታቸው ማኅጸን ሳሉ አጋንንትን ያቃጥሉና ያጠፉም ነበር፡፡ *በዲቁናም ከቆዩ በኋላ፤ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመግባት እስከ ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ ደርሰዋል፤ ሥውራን የኾኑ ቅዱሳንም እየተገለጡ ምሥጢራትን ይነግሯቸው ነበር፡፡ ከስግደታቸው ብዛት የተነሣ የእጆቻቸው አጥንቶች እስከ መሠበር፥ ከቁመታቸውም ብዛት የተነሣ እግሮቻቸው እስከማበጥ ደርሰዋል፡፡ *ሲቀመጡና ሲሰግዱ የጌታችንን መከራ እንዲያስቡ፤ 8 ጦሮች ያሉበትን ሰንሰለት በአራቱ አቅጣጫ በወገባቸው ታጠቁ፡፡ ከልደት፣ ከጥምቀትና ከትንሣኤ በቀርም ከወገባቸው አይፈቱም ነበር፡፡ *ቅዱስ ሚካኤልም ዕፀ ገነት አምጥቶ ካሸተታቸው በኋላ ምድራዊን ነገር ለመቅመስ የሚጸየፉ ኾኑ፡፡ *ቅስናን እንዲሾሙ አበምኔቱ ሲጠይቃቸው እምቢ በማለታቸው ወደ ሊቀ ጳጳሱ መልእክት አድርሱልኝ ብለው በላኳቸው ጊዜ ጳጳሱ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት ቅስናን ሹሟቸዋል፡፡ *ወደ ደብረ ጽሙና ጻድቁ አቡነ አትናቴዎስ መቃብር ሂደው በሚጸልዩበት ጊዜም ብርሃን ይወርድላቸው ነበር፤ እግራቸው በረገጠበት ቦታም ጸበል ፈልቆላቸው ቦታውን ላሳየቻቸው እግዚእ ክብራ ለተባለች ጻድቅት በጽዋ ሞልተው ሰጧት እርሷም መካን ለነበረችው አገልጋይ ብትሰጣት ልጅ ወለደች፤ ይህ ጠበላቸው እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ገቢረ ተዓምራትን እየሠራ በገዳማቸው ገኛል፡፡ መልአኩም ወደ በረሃ እንዲወርዱ በነገራቸው መሠረት ወደ ምድረ ሐጋይ በመሄድ ለ41ዓመታት በጽኑ ተጋድሎ ቆይተዋል፡፡ **ወደተለያዩ ገዳማት በመሄድም 40 ቀን (ከሰንበት ውጪ ሳምንቱን ሙሉ እያከፈሉ) ይጾሙና ይጸልዩ ነበር፡፡ ወደ ታላቁ ገዳም ወደ ዋልድባ ገብተው ሲወጡም ወደ ድባብ ገዳም ገዳም ሄደው 40ቀን ሲጾሙ ጌታችን ወዳልተጠመቁ ሄደው እንዲያስተምሩ አዝዟቸው አስተምረዋል፡፡ * ጻድቁ 3ት ነገሮችን እፈልጋለሁ፤ እነርሱም፤ ከሐሜት መራቅን፤ ክፉ ነገርን ከማየት መራቅን፤ ከንቱ ነገርን ከመስማት መራቅን፤ እያሉ ይናገሩ ነበር፡፡ *ሰማዕት እንዲኾኑም ይለምኑ ነበረ፤ እመቤታችንም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በመምጣት ‹‹የጳውሎስ አበባ፥ የጴጥሮስ ፍሬ፥ የልጄ ተክል›› የለመንከውን ታገኛለህና በርታ አለቻቸው፤ አርሳቸውም በነገረ ሠሪ ከንጉሡ ጋራ እንዲጣሉ አደረጓቸው፤ በንጉሡ ዘርዐያዕቆብና በሠራዊቶቻቸው ብዙ መከራን ተቀብለው በ71 ዓማታቸው በሰማዕትነት አረፉ፤ ከ14 ዓመት በኋላም በንጉሡ ዘርዐያዕቆብ ወንበር ልጁ በዕደ ማርያም በነገሠ ጊዜ ሥጋቸውን አፍልሶ በደብረ ጽሙና በክብር አሳረፈው፡፡ ጻድቁ በታላቁ ገዳማቸው በደብረ ጽሞናና በደብረ ሊባኖስ አጠገብ በሚገኘው በአጋት መድኀኔ ዓለም ክብረ በዓላቸው ይከበራል፡፡ ***ጻድቁ በተባሕትዎም ኾነ በትሩፋት እጅግ የተደነቁ አባት ነበሩ፡፡ ለአብነትም ያህል፤ * በትራቸው እንደ ሙሴ በትር ተዓምራትን ታደርግ ነበር፡፡ በብርሃን ሠረገላም ይጓጓዙ ነበር፡፡ * ክርስቶስን በመከራው ይመስሉት ዘንድ ዘወትር ይተጉ ነበር፤ *ሥጋ ወደሙ የተቀበለ አንድ ሰው በመንገድ ላይ ሲያስመልሰው ተመልከተው ሁሉ ተጸይፎ ሲሸሽ እሳቸው ግን የፈጣሪን ሥጋና ደም በመመልከት ደስ እያላቸው እንደ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ተመግበውታል፤ በዚህ ጊዜም ጌታ ከሰማይ ወርዶ በግንባራቸው ላይ ፀሐይን ስሎባቸዋል፤ በዚህ ምክንያትም ፊታቸው ያበራ ነበር፡፡ *በገዳማቸው አንድ ዶሮ ለእንግዳ ሊያርዱት ሲሉ አፍ አውጥቶ ‹‹በአባ ተክለ ሐዋርያት ተማጽኛቹሃለሁ›› በማለቱ ትተውታል፡፡

#✤#መድኀኔዓለም ተወከፍ እንተ አቅረብኩ ንስቲተ፤ ዘሰተይከ በእንቲአየ ከርቤ ወሐሞተ፤ በሞተ ዚአከ ከመ ትቅትል ሞተ፡፡ ✤ፈጣሪዬ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ሆይ፤ በሞትህ ሞትን ታጠፋው ዘንድ ከርቤ የተቀላቀለበትን መራራ ሐሞትን ስለኔ ሕይወት የጠጣህ የአቀረብኳትን አነስተኛ የምስጋና መባዕ በቸርነትህ ተቀበል፡፡ ***በፎቶ የምታይዋቸው አብያተ ክርስቲያናት #✤#ደብረ_ቀራንዮ_መድኀኔ_ዓለም፤ #በ1826_ዓ.ም. #በንጉሥ_ሣህለ_ሥላሴ የተመሠረተ፤ ጠፍነት ሳያጋጥመው በመቆየት በአ.አ የመጀመሪያው ቤተ ክርስቲያን (በአ.አ. ላይ ከቀራንዮ የሚቀድሙ ጠፍነት ያጋጠማቸውና ኋላ መልሰው የተሠሩ ግን በርካታ አብያተ ክርስቲያናት መኖራቸውን ልብ ይሏል፡፡) #✤#ቀጨኔ_ደብረ_ሰላም_መድኀኔዓለም፤ #በ1903ዓ.ም. #በአቤቶ_(#ልጅ_ኢያሱ_የተመሠረተ፤ በአዲስ አበባ በመድኀኔዓለም ስም ከተመሠረቱት አብያተ ክርስቲያናት 2ኛው፡፡

#_ኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_አቡነ_ሀብተማርያም፡፡ በሽዋ (የራውዕይ) ከአባታቸው ፍሬ ቡሩክ ከእናታቸው ቅድስት ዮስቴና ነው የተወለዱት፡፡ ወላጆቹ በተለይም እናቱ ከማግባቷ በፊት መናኝ ነበረች፡፡ ጻድቁን እንደምትወልድ በበቃ ባሕታዊ ተነግሯት ጻድቁን ወልዳ በጽድቅ ኑሮ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ በክብር አርፋለች፡፡ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ›› ሲባል ይሰማሉ፤ በሕፃን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ ‹‹ማረን እባክህን›› እያሉ ይሰግዱ ነበር፡፡ ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ፡፡ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል፤ የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል፡፡ ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው ትምህርትን ከቀሰሙ በኋላ መንነዋል፤ ከታላቁ አባት በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በኋላም ብዙ ትርፋትንና ተጋድሎን ሠሩ፡፡ ለአብነትም፤ *ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ *በየቀኑ 4ቱን ወንጌልንና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ *በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ *ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው *በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ *ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ፤ ክቡር ደሙን ይጠጣሉ *በልባቸው ውስጥ በፍጹም ቂምን፣ መከፋትን አላሳደሩም፡፡ *"ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" ጌታችንም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ተለያዩ ቦታዎች ይሔዱ ነበር፡፡ ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በኋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው:: +"*ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: *ስለ ምናኔሕ: *ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: *ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: *ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: *ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: *ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::" +"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን: 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ: በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ በርእስየ' ብዬሃለሁ" አላቸው:: +ቅዱሳን መላእክትም "ሀብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት:: ✤ ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነሱም፤ 1. #_መብረቅ፣ 2. #_ቸነፈር፣ 3. #_ረሃብ፣ 4.#_ወረርሽኝ፣ 5.#_የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ቦታውን ሲባርክ ሦስት አጋንንት በጸሎቱ ሥልጣን የታሠሩለት ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡ በዛሬው ዕለት በኅዳር 26 ባረፈ ጊዜ፤ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማህሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በጻድቁ መቃብር ቀበሩት፡፡ (ከወርቅ ንፁህ ከብርም የጠራ ከሁሉ የሚበልጥ የተመረጠ ሃብተማርያም መልአክ ዘበምድር ነው መልካሙ ዜናው እስከ አጽናፍ ተሰማ፡፡) #_በዛሬዋ ዕለት #በናግራን ያሉ ክርስቲያኖች በ6ኛው ክፍለ ዘመን ሰማዕታት የኾኑበት ዕለትም ነው፡፡

#አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ፤ #_የወርቃማ_ዘመን_መሥራች፤ በሐይቅ የኖረ፥ እንደ እስጢፋኖስ ጸጋን ጽድቅንና ሞገስን የተመላ፥ በሥራው ፍጹም የኾነ፥ #_ወላዴ_አእላፍ_ቅዱሳን_የኾነ አባት *በበጌምድር ዳኅና(አሁን ስማዳ) ገብርኤል በተባለ ቦታ ከአባታቸው ዘክርስቶስና ከእናታቸው እግዚእ ክብራ ነሐሴ 26 ሰኞ ተጸንሰው፤ ግንቦት 26/1205 ዓ.ም. ረቡዕ በቅዱስ ነአኵቶ ለአብ ዘመነ መንግሥት ተወለዱ፡፡ ወንድሞቻቸው ገብረ ጽዮንና ስቡሕ አምላክ ይባላሉ፡፡ *እስከ 30 ዓመታቸው ድረስ በእናት አባታቸው ቤት እያገለገሉና ትምህርት እየቀሰሙ ቆዩ፤ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጾላቸው ወደ 5ኛው የደብረ ዳሞ አበምኔት ዳግማዊ አቡነ ዮሐኒ ዘንድ እንዲሄዱ በራዕይ ነገራቸው፤ በመንገድም ሲሄዱም የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አግኝተው ይምጻአ ምሕረት የሚባል ዲያቆንን አስከትለው ወደ ደብረ ዳሞ እንዲሄዱ መልአኩ ባዘዛቸው መሠረት ወደ ገዳሙ አቀኑ፡፡ *በደብረ ዳሞ ቆይታቸውም እህልን በመፍጨትና ለገዳሙ ንግድን (ሩቅ መንገድንና አስጨናቂ ኹኔታዎችን በማለፍ ) ይነግዱ ነበር፡፡ እንዲሁም ቅዱሳት መጻሕፍትን በመጻፍ (በመገልበጥም) ትጉህ ጸሓፊ ናቸው፤ ይህ ይታወቅ ዘንድ በቅርብ የደብረ ዳሞ ዕቃ ቤት እስከተቃጠለበት ድረስ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በእጃቸው የጻፉት ወንጌል ይገኝ ነበር፡፡ *37ዓመት ሲኾናቸው ከአባ ዮሐኒ ሥርዐተ አስኬማ ዘመላእክትን ከተቀበሉ በኋላ መልአኩ ወደ ሐይቅ እንዲሄዱ በገለጻላቸው መሠረት በ1237ዓ.ም. ወደ ሐይቅ በመምጣት በሐይቁ ዳር በሚገኘው ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤ.ክ. ለ6ወራት አገለገሉ፤ በዚሁ ደብር የሚገኘው ‹‹ሔር አምላክ›› የተባለ ካህንም የጻድቁን ታሪካቸውን ጠይቆ ከተረዳ በኋላ ወደ ደሴቱ አስገባቸው፤ የአካባቢው ሕዝብም አገልግሎታቸውንና መንፈሳዊ ተጋድሏቸውን አይተው ንጉሡ ይትባረክ ዘንድ በመሄድ የገዳሙ አበምኔት እንዲያደርገው ጠየቁት እርሱም ሾመው፡፡ ጻድቁም ይህን ገዳም በዮዲት ጉዲት ከጠፋ ከ300 ዓመታት በኋላ ዳግም አቅንቶታል፡፡ *እርሳቸውም ደሴቲቷም ስለወደዷት ከገዳሟ ላለመውጣት፤ የባሕሩን ወደብም ላለመርገጥ ብፅዓት ገብተው 20 ዓመታት ያህል እንደኖሩ፤ አፄ ይኵኖ አምላክ እንደነገሠ ጻድቁ ወደ ንጉሡ እንዲመጡ ላከበቸው፤ እርሳቸው ግን ከሐየቅቁ እንደማየወጡ ብፅዓት እንዳለባቸው ንጉሥ ወደእርሳቸው እንዲመጣ ላኩበት፤ ንጉሡም በበቅሎ እስከ ጉልበቱ ድረስ ወደ ባሕሩ ገብቶ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ኂሩተ አምላክና ኀረየነ ክርስቶስ ከሚባሉ ደቀመዛሙርቶቹ ጋር በታንኳ (በጀልባ) መጥተው ተጨዋወቱ፤ ንጉሡም ምን ላደርግልህ ትወዳለህ ሲላቸው፤ * ገዳሟ የወንዶች ገዳም እንድትኾን ነው አሉት፤ ንጉሡም በቦታው ያሉትን ሴቶች ይህ ቦታ የወንዶች ገዳም ብቻ እንዲኾን ስለወሰንኩ የፈቀዳችሁ ከእኔ ጋር በከተማዬ መኖር አሊያ በፈቀዳችሁትና በመረጣችሁት ቦታ መኖር ትችላላችሁ የምትፈልጉትንም ኹሉ እሰጣችኋለሁ በማለት ሥርዐት አበጁለት፡፡ ደሴቲቱን ለቀው እየሄዱ ካሉት ሴቶች መካከልም አንዲቷ ምጧ ደርሶ ነበረና በደሴቱ ጫፍ ወለደች ቦታውም ‹‹ምጥ ገበታ›› ተባለ፡፡ ዛሬ ክብረ በዓል የሚከበረው በዚሁ ምጥ ገበታ በተባለው ቦታ ነው፡፡ (ከምጥ ገበታ በስተምዕራብ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ፤ በስተሰሜን ምዕራብ መካነ አእምሮ (University)፤ በስተሰሜን የሴቶች ገዳም ይገኛል) * በንግግራቸው ሳሉም እባብና አለቅት በንጉሡን በቅሎ እግር ላይ ተጠመጠሙ፤ ጻድቁም መርዛማነት ያላቸውን እንስሳት በዚህ ገዳም ሰውን እንዳይጎዱ አወገዟቸው፤ የደወልም ድምፅ ተሰማ ንጉሡም አሁን ስንት ሰዐት ነው የደወል ድምፁስ ምንድን ነው ብሎ ጻድቁን ጠየቀ፤ ጻድቁም ፱ኝ ሰዐት በመኾኑ ደወሉ ከገዳሙ የተደወለ መኾኑን ነገሩት ንጉሡም ለጻድቁ የዐቃቤ ሰዐት ማዕርግን ሰጣቸው፡፡ (ምንም እንኳን እርሳቸው በሹመቱ ለመጠቀም ባይፈልጉም)፤ ከተከታያቸው ከአባ ዘኢየሱስ አንስቶ እስከ 16ኛው መጀመሪያ አጋማሽ ድረስ በሐይቅ መምህራን እጅ ቆይቷል፤ ኋላ የንጉሦች መናገሻ ከሸዋ ወደ ጎንደር ሲዛወር በቦታ ርቀት ምክንያት ይህ ሹመት በገጽ የሚሰጥ ሹመት ሁኗል፡፡) ✤ንጉሡ ይኵኖ አምላክ ለገዳሟ የሚከተለውን ሥርዐት ሠርተው መደ መናገሻቸው፤ ጻድቁም ወደ ደሴታቸው ተመለሱ፤ **መኳንንት፣ መሳፍንትና ነገሥታት የሰጡትን ገዳሙን ርስት ጉልት ማንም እንዳይነካ፤ **ሴቶች ወደ ገዳሙ እንዳይገቡ (የአባቶች መነኰሳትና የባሕታውያን ብቻ መኖሪያ እንዲኾንና እኅቶች እንዳይቀላቀሉ በማሰብ) **መነኰስ ያልኾነ ማንም በሐይቅ ገዳም ቤትን እንዳይሠራ፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በሃገራችን አንጋፋና ቀደምት በኾነው ደብረ ዳሞ መካነ አእምሮ (University) የተማሩ እንደመኾናቸው፤ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሲመለሱም በሃገራችን በትምህርት መካነ አእምሮነቱ ዋናና ግንባር ቀደምቱን፤ በርካታ ሊቃውንትን ቅዱሳንን ያፈለቀውን የሐይቅ እስጢፋኖስ መካነ አእምሮ መሠረቱ፤ በዚህም የኢትዮጵያን ወርቃማ ዘመን መሥራች ነው፤ ልጆቻቸውም ይህን ወርቃማ ዘመን አስቀጥለውታል፡፡ በቆብ የወለዷቸው ቅዱሳን ሊቃውንት ብዙ ቢኾኑም ለአብነት ያህል ዐበይቶቹ፤ ✤ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ዘደብረ ጎል (ምድረ ዐማራን፣ ሸዋንና ደቡብን፤ ምድረ ትግራይን ያስተማሩ፤ የአቡነ ተክለሃይማኖት የመጀመሪያ መምህር የኾኑ) ✤ አቡነ ተክለሃይማኖት (ሐዲስ ሐዋርያ ተብሎ የተሰየመ፤ ከመመነኰሳቸው በፊት 7 ዓመታት፣ ከመነኰሱ በኋላ 3 ዓመታት ተቀምጠዋል) ✤ አባ ሕዝቅያስ (ከምድረ ወግዳ ይዞ እስከ ጎጃም ያስተማሩ) ✤ አባ ገብረ እንድርያስ ዘደብረ ቆዘት (በጸበላቸው የእንጨት ቅርፊትን እንደ ደንጊያ መቁጠሪያ የሚያደርጉ፣ በድንጋይ ሠረገላ የሚጓጓዙ) ✤ እጭጌ አባ አሮን ዘደብረ ዳሪት (ከምድረ ዋድላ አንስቶ እስከ ዳውንት፤ ከበጌምድር እስከ ደምቢያ የሰበከ) ✤ አባ ገብረ ናዝራዊ ዘበለሳ (ምድረ ትግሬን ያስተማረ) ✤ አባ ኂሩተ አምላክ ዘዳጋ (እንደ መምህሩ በእስጢፋኖስ ስም በጣና ላይ የዳጋ እስጢፋኖስ ገዳምን የመሠረተ፤ ምድረ ሳርክን ይዞ እስከ ጋዝጌ፤ መላዋን የአላፋና ጣቁሳ እና የአገው ምድርን ያስተማረ) ✤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ዘደብረ ባሕርይ) (የኢትዮጵያ መብራት)፤ አብዛኛዋን የኢትዮጵያ ምድር ያስተማረና ቤተ ክርስቲያንን ከ40 በላይ በሚደርሱ ድርሳናቱ ያስጌጣት፡፡ ✤ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ፡፡ ✤✤ እንዲሁም ንጉሡን ይኵኖ አምላክ (ከንግሥናው በፊት በልጅነቱ ያደገውና የተማረው ከጻድቁ ዘንድ ነው፡፡) በአጠቃላይ 44 ዓመታትን ማለትም፤ *20 ዓመት በይትባረክ ዘመነ መንግሥት *15 ዓመት በይኵኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት *9 ዓመት በአግብዓ ጽዮን ዘመነ መንግሥት የኖሩ ሲኾን፤ ለ44 ዓመታት በገዳሙ ቆይታቸው ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም፤ ለሰውነታቸውም(ለጎናቸውም) ምኝታን አላስለመዱትም፡፡ ‹‹እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ፤ መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ፡፡›› እንዲል፡፡ ጻድቁ በሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩም የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር፡፡ የማረፊያው እለት በደረሰ ጊዜ ደቀመዛሙርቱና ሰዎች ተሰባሰቡ፤ በደብረ ነጐድጓድ ያደገውን ተክለ ኢየሱስን መምህር አድርጎ ሾመላቸው እነርሱንም ባርኳቸው፤ ኅዳር 26 በ1286ዓ.ም. በእለተ እሑድ ጧት ፀሐይ ስትወጣ ዐረፈ፤ ደቀ መዛሙርቱም እንደሚገባ አድርገው በፍየል ሌጦ አድርገው ገንዘው በክብር ቀበሩት፡፡

በሃገራችን ከሚገኙ የቅዱስ መርቆሬዎስ ክብረ በዓል ከሚከብርባቸው ዋነኞቹ፡፡ ✥1. ደብረ ጽባሕ ጸዶየ መርቆሬዎስ፤ በአጼ ይኵኖ አምላክ ዘመን የተመሠረተ፡፡ ✥2.ደረስጌ ደብረ ጽዮን ማርያም፤ ‹‹ደጃች ውቤ ደረስጌ ደብረ ጽዮንን በወርቅና በዕንቊ ከመሥራታቸውም በላይ ታቦተ መርቆሬዎስን ማምጣታቸው ተብሎ የሚነገርለት›› ተዓምር አድራጊ ስዕል የሚገኝበት ቤ.ክ (ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የነገሠበት)፤ ራስ ደጀን አጠገብ፤ ጃናሞራ (መካነ ሰላም ከተማ) ✥3. ጎንደር ደብረ ፀሐይ ቊስቋም ማርያም፤ የቅዱስ መርቆሬዎስ ታቦት ከጥንት ጀምሮ በድርብነት አለ ✥4. ጋሹ አምባ አርማንያ ቅዱስ መርቆሬዎስ (ሰሜን ሸዋ፤ ደብረ ሲና)፤ ስዕሉ በበዓለ መርቆሬዎስ ቀን የሚያሸበሽበው፡፡ ✥5. ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኡል (አ.አ)፤ የቅዱስ መርቆሬዎስ ታቦት ከጥንት ጀምሮ በድርብነት አለ ✥6. ደብረ ሲና ቅ.እግዚአብሔር አብ(አ.አ)፤ የቅዱስ መርቆሬዎስ ታቦት ከጥንት ጀምሮ በድርብነት አለ ✥7. አዲስ አበባ ጎፋ ደብረ መዊዕ ቅዱስ መርቆሬዎስ ወዮሐንስ መጥምቅ ቤ.ክ (በአዲስ አበባ በመርቆሬዎስ ስም የጠሰየመ ብቸኛው ቤ.ክ.) LIKE & INVITE our Facebook Page <<የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት››

መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች በውስጧ አስገባውና ከእርሱ ተሰወረ፡፡ ይህም ወጣት በኋላ አምኖ ተጠምቆ ብዙ ሰማዕትነት ተቀብሏል፡፡ ገዳምም ገብቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ እንደገና ወደ አገሩ ተመልሶ ብዙዎችን ወደ ክርስትና አምጥቷል፡፡ በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ አበ ምኔትም ሆኖ ብዙ መነኰሳትን አፍርቷል፡፡ /ምንጭ፤ ከገድላት አንደበት/ ✣✤✣ ቅዱሳት ሥዕላት በቅዱሳት መጻሕፍት -‹‹የስርየት መክደኛ ስራ ፣ ሁለት ኪሩቤልን ከተቀጠቀጠወርቅ ስራ፣ በምስክሩ ታቦት ላይ በሁለቱ ኪሩቤል መካከል መክደኛውም ላይ ሆኜ አነጋግርሃለሁ፡፡›› ዘጸ25፣18-22፤ 37፣7-9 -በቅድስቲቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል መለያ በሆኑት መጋረጃዎች “ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤልን አድርጉባቸው” ዘጸ 26፥31፤ 36፣ 8-35፡፡ -እግዚአብሔር ማዘዝ ብቻ ሳይሆን በጥበብና በማስተዋል መንፈሱን እንደመላባቸው፤ የኡሪ ልጅ ባስልኤል፥ የአሂዳምኒክን ልጅ ኤልያብን ዘጸ 31:1-6 -‹‹እስከ መነነቶ ሜልኮል ቅድመ ታቦተ ሕግ ከመ ዘፈነ፣ንጉሠ እስራኤል ኪያኪ ዘጸገየ ሥነ፣ቅድመ ሥዕልኪ ድንግል እዘፍን አነ. . .፤ የዓለም የድኅነት ጌጥ የሆነ ጌታን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ አንቺን ያስገኘ የእስራኤል ንጉስ ዳዊት ሚስቱ(ሜልኮል) እስከምትንቀው ድረስ በእግዚአብሔር የቃልኪዳን ታቦት ፊት እንዳመሰገነ እኔም በሥዕልሽ ፊት ቆሜ እዘምራለሁ፤. . .›› ‹‹ኢየኀፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ ወርኀ ጽጌረዳ አመኀ ኀልቀ . . .፤ማርያም ሆይ የጽጌረዳ ፣የአበባ ወራት ባለፈ ጊዜ ብዙ ምስጋናሽን ሳመሰግን በሥዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም፣ ስምሽን መጥራት የወደቀውን ያነሣል ፣ኀጥኡንም ጻድቅ ያደርጋልና።›› /አባ ጽጌ ድንግል/ ኅዳር ፳፭ የምናከብረው ክብረ በዓል፤ ፨ ታላቁ ሰማዕት (‹‹ካልዕ ሊቀ ሰማዕታት››) ቅዱስ መርቆሬዎስ(ፒሉፓዴር) ዓመታዊ የዕረፍት በዓሉ ፨ ቅዱሳን ታቦትና ኖኅ (ወላጆቹ) ፨ ቅዱስ ሮማኖስ በዓላቸው ነው፡፡

#ፒሉፓዴር_መርቆሬዎስ_ስዕሉ_የሚያሸበሽበውን_ቪዲዮ_ይመልከቱ፠፨ ገባሬ ተአምር፥ ገባሬ ተአምር፥ ገባሬ ተአምር፤ መርቆሬዎስ መርቆሬዎስ ገባሬ ተአምር፡፡ ቪዲዮውን ሁሉም ሊያየው የሚገባ የተዓምር ተዓምር፡፡ የቻላችሁ በአካል ሰሜን ሸዋ (የ100ብር የትራንስፖርት መንገድ ነው) ሂዳችሁ፤ ያልቻላችሁ ቪዲዮውን እንድታዩት አቅርበንላችኋል፤ ዛሬም ድረስ ተዓምር አድራጊውና በበዓለ መርቆሬዎስ እለት የሚያሸበሽበው የቅዱስ መርቆሬዎስ ስዕል፤ (ቀድሞም ባስልዮስና ጎርጎርዮስ ዑልያኖስ የሚባል ጠላት ሲመጣባቸው ወደ ቅዱስ መርቆሬዎስ ስዕል ጸለዩ፤ ቅዱስ መርቆሬዎስም ከስዕሉ ላይ ወጥቶ ዑልያኖስን ገደለላቸው)፤ ዛሬም ድረስ የቅዱስ መርቆሬዎስ ስዕል ተዓምራትን ያደርጋል፡፡ በጻድቃን ሰማዕታት፤ በመላእክት በእመቤታችን ላይ አድሮ እግዚአብሔር እንደሚመሰገን አስተውሉ፡፡ ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ፤ የወላጆቹ አገር አስሊጥ የምትባል ስትኾን እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡ አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ ከለባት ወገን የሆኑ ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት፡፡ አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡ ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡ በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተወለደና ስሙ ፒሉፓዴር ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸውም በእርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፡፡ አባቱን ኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፡፡ ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ አቆማቸው፡፡ እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡ ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሯቸውን ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ ጊዜ ተፈጥሯቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን አይቶ አከበረው፡፡ ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡ መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባቱ አብረውት ነበሩ፡፡ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሯቸውን እግዚአብሔር ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠውና ዜናው በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፡፡ በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በጦሩ መሀል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ›› አለው፡፡ መልአኩም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና ‹‹ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው›› አለው፡፡ ጦርነቱን ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት ‹‹ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት እረሳህ?›› አለው፡፡ ከጦርነቱም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በዚያ ስላልተገኘ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረጉ እንዳልተባበረ ንጉሡ ሲያውቅ መልእክተኞችን ልኮ አስመጣው፡፡ ንጉሡም ‹‹ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?›› ባለው ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ ‹‹ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፣ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም›› አለው፡፡ ንጉሡም ተናዶ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡ ንጉሡም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የአገሩ ሰዎች እንዳይነሱበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጰዶቅያና የእስያ ክፍል ወደሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡ በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ኅዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፡፡ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፡፡ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡ እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡ ✤ከብዙ ተአምራቱም አንዱ የቂሳርያውን ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስን እንዲሁም ጎርጎርዮስን ረድቶ ከሃዲውን ዑልያኖስን የገደለበት ነው፡፡ ዑልያኖስ ነግሦ የክብር ባለቤት ጌታችንን ክዶ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሠቃየት ጀመረ፡፡ የቂሳርያው ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስም አስተምሮ ሊመልሰው ወደ ንጉሡ ቢመጣ ክብር ይግባውና ዑልያኖስ ጌታችንን ሰድቦ ባስልዮስንም አሰረው፡፡ ባስልዮስም በእሥር ቤት ሳለ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ጸለየ፡፡ ሥዕሉም ወዲያው ተሰወረው፡፡ ያንጊዜም ወደ ከሃዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ዘንድ ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለውና ወዲያው ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡ በስዕሉ ላይ ያለው የቅዱስ መርቆሬዎስ ይዞ ከተሳለው ጦር ጫፍ ላይም ደም ይንጠፋጠፍ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ከሃዲውን ንጉሥ እንደገደለው ዐውቆ ‹‹የክርስቶስ ምስክር ጌታዬ ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን?›› አለው፡፡ ሥዕሉም ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አደረገ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡ ✤ሌላው ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በተአምሩ ከእስልምና እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ እስላም ሰው አለ፡፡ ይኸውም የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያኑ በተሠራችበት በምስር አገር የሚኖር ከመሳፍንት ወገን የሆነ ወጣት ነበረ፡፡ ከብዙ ሰዎችም ጋር ሆኖ ወደ መሐመድ መቃብር ለመሄድ እንዳሰበ ለአባቱ ሲነግረው ስንቅ ሰንቀው በሰላም ወደ መካ መዲና ሸኙት፡፡ መካ ደርሰውም ሥራቸውም ፈጽመው ወደቤታቸው እየተመለሱ ሰባት ቀን ተጓዙ፡፡ በሌሊትም ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ ግዳጁ ያ እስላም ወጣት ከግመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ፡፡ እነርሱም አብሯቸው የሚጓዝ መስሏቸው ስለነበር ባልንጀሮቹም በበረሃው ውስጥ ትተውት ሄዱ፡፡ እርሱም ወዴት እንደሚሄድ ስላላወቀ አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ እጅግ ደነገጠ፡፡ በዚያም ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ ቅዱስ መርቆሬዎስን እንዲያድነው በመለመን ተሳለ፡፡ ወዲያውም ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈረሱ ተቀምጦ ወደ እርሱ መጣና ‹‹ከወዴት ነህ? ከዚህ በረሃ ውስጥስ እንዴት ጠፋህ?›› አለው፡፡ ወጣቱ እስላምም የሆነውን ነገረው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም ‹‹ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ›› አለውና በአየር ላይ እየበረረ በምስር አገር ወዳለች የቅዱስ መ

ዛሬ ኅዳር 24 #የ24ቱ_ካህናተ ሰማይ (የሱራፌል)ና በቆብ አያትና የልጅ ልጅ የኾኑት #አቡነ_ተክለሃይማኖትና_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑበት ዕለት ነው፨ ፨ካህናተ ሰማይ የዐውዶ ሡራሄ፤ ሎቱ ለባህቲቱ ይደሉ ስባሔ፨ /ሰዐታት/ ፨ ብፁዕ ሳሙኤል መንበረ ልዑል የዐጥን።

እንዳያመልጥዎ!!!!! በ፻ ዓመት አንዴ የሚገኝ፥ የማይደገምየእግር ጉዞ፨ shareeeeeee ✤✤#ተጓዡን_ቅዱስ_በጕዞ_እንዘክረው!!!፨ ✣ ኑ ከእመቤታችንና ከልጇ ጋራ በስደቷ አብሮ የተጓዘውን አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍን በጕዞ እንዘክረው፡፡ በጕዟችንም ከእመቤታችንና ከልጇ እንዲሁም ከአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ በረከት ረድኤት ማግኘታችንን እንዳትዘነጉ፡፡ ✤✤#ኅዳር_23 ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ፨ መርሐ ገብሮቹም፤ * ከሌሊቱ 11:00-1:30 ጸሎተ ቅዳሴ፤ * ከ1:30-2:00 ልዩ ልዩ እንግዶች የጉዞ ማስጀመሪያ ንግግር ያደርጋሉ፤ * 2:00 ቅዱስ ዮሴፍ በምዕመናን ታጅቦ በቀለበት መንገድ ወደሳሪስ አቦ ቤ/ክነወ ደርሶ ይመለሳል፤ * ከጉዞው መልስ በቅዱስ ዮሴፍ ቤ/ክን በተጣሉ ድንኳኖች ልዩ ልዩ ሥነ ሥርዐቶች ይከናወናሉ፤ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከትራፊክ ጽ/ቤት የተወከሉ፣ ከፖሊስ የተወከሉ ትምህርትና መልዕክት ያስተላልፋሉ። ✤#_የእግር ጕዞው #_"ከትራፊክ አደጋ ራሳችንንና ሌሎችን መጠበቅ መንፈሳዊ ግዴታችንም ነው" በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል፨ ✤✤✤#_አጭር_ስለ_ደብሩ_ታሪክ፤ ከ፻ ዓመት ዓመታት በፊት በ፲፻፱፲ ዓ.ም. በሰብዮን ኀይለ ማርያም የተመሠረተው ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርቲያን የ፻ኛ ዓመት የምሥረታ ክብረ በዓሉን ከግንቦት 23/2010ዓ.ም. ከዋይዜማው ጀምሮ፤ እየተከበረ መኾኑም የማይዘነጋ ነው፡፡ ደብረ ናዝሬት ተብሎ የተሠየመው ጌታ በቤተ ልሔም ተወልዶ ወደ ግብጽና ኢትዮጵያ ተሰዶ ሲመለስ ወደ ቤተ ልሔም ሳይኾን ናዝሬት ገብቶ ነው ያደገው፤ እንዲሁም ናዝሬት አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ የተቀመጠባትና ብዙ ምሥጢራት ያየባት በመኾኗ ደብረ ናዝሬት ተብሎ ደብሩ ተሰይመሟል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ በደጃዝማች መርዕድ መንገድ ላይ፤ ከቦሌ ወደ ሳሪስ አቦ በሚወስደው ቀለበት መንገዱ ዳር ላይ ይገኛል፡፡ (የታክሲ ትራንስፖርት፤ ከላጋር፣ ከፒያሣ፣ ከ4ኪሎ ቃሊቲ መናኸሪያ በቦሌ /በቀለበት መንገድ/ ብለው በሚጭኑት በቶሎ ቤተ ክርስቲያኑ በር ድረስ ያደርስዎታል፡፡) ✤#_ሊቁ_አባ_ጽጌ_ድንግልም_በሰቈቃወ_ድንግል ድርሰቱ ቅዱሱን እንዲህ ብሎ አንስቶታል፡፡ ጐየ ዮሴፍ ብሔረ ግብጽ ተንሢኦ እምንዋሙ፤ መልአከ እግዚአብሔር ሌሊተ በከመ ነገሮ በሕልሙ፡፡ ነሢኦ ሕፃነ ዘምስለ ማርያም እሙ፤ ይእቲ ትበኪ ወትቤ ቀቲሎትየ ይቅድሙ፤ እምእርአይ ለወልድየ ዘይትከዐው ደሙ፡፡ (የእግዚአብሔር መልእክተኛ የኾነ ቅዱስ ገብርኤል ሌሊት በሕልሙ እንደነገረው ዮሴፍ ከእንቅልፉ ነቅቶ ሕፃኑን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋራ ይዞ ወደ ግብፅ ሃገር ሸሸ፤ ድንግል ማርያምም የልጄ ደም ሲፈስ ከማይ ይልቅ የሄሮድስ ሠራዊት እኔን አስቀድመው ይግደሉኝ እያለች አለቀሰች፡፡ / ሰቈቃወ ድንግል፣ ማቴ.2፥13/

ጽዮንን ክበቧት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦቿንም ቅጠሩ፥ አዳራሿን ተመልከቱ፥ በብርታቷ የልባችሁን ተስፋ አኑሩ፡፡ /መዝ. 47፥12/ #ታቦተ_ጽዮንና #ጽዮን_ ድንግል ማርያም፤ ✤ ታቦተ ጽዮንን ሌዋውያን ከበዋት ውዳሴ፥ ዝማሬ ያቀርቡላት እንደነበረው፤ ዛሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካህናትና ምእመናን ከሩቅ እና ከቅርብ ተሰብስበው በማኅሌት፥ በዝማሬ፥ በቅዳሴና በውዳሴ ያከብሯታል፡፡ ✤ ታቦተ ጽዮን በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የኖረች፣ የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች /ኢያሱ 3÷14-17/፤ ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች /ኢያሱ 6÷1-21/፤ ዳጎን የተባለ የፍልስጥኤማውያንን ጣዖት የቆራረጠች /1ኛ ሳሙ. 5÷1-5/፤ በድፍረት ሊነካ የሞከረውን ኦዛን የቀሰፈች /1ኛ ሳሙ. 6÷6/፤ በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች /2ሳሙ 6÷12/፣ ዳዊት የዘመረላት /2ሳሙ 6÷14/፤ ጠቢቡ ሰሎሞን በቤተ መቅደስ በክብር ያኖራት /1ኛ ነገ፣ 8÷1/፤ የእግዚአብሔር የክብር መገለጫ ናት፡፡ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ንጽሐ ጠባይዕ ሳያድፍባትና የቅድስና ባሕርይ ሳይጎድፍባት፤ (በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰሰ፣ በማሽተት አንዳችም እድፍ ጉድፍ ሳያገኛት) በንጽሕናና በቅድስና ጸንታ በኀጢአት ሳትለወጥ ኖራለች፡፡ /ውዳሴ ማርያም፣ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም፤ አንቀጸ ብርሃን፣ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ/ እንዲሁም ‹‹ምክንያታዊ ነውር ኃጢአት የሌለብሽ የኀጢአት ሸታ ያልደረሰብሽ ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና ክብርት በልዕልና አንቺ ነሽ» ብሏታል ጠቢቡ ሰሎሞን /መሓ. 4÷7፣/ ✤ ታቦተ ጽዮን በከበረ ወርቅ እንደተሸለመች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ እና በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ያጌጠች መሆኗን ያጠይቃል፡፡ ✤ ታቦተ ጽዮን የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ እንደሆነችው ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ለአካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ኾናለች፡፡ «ድንግል ማርያም ሆይ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ ለእርሱ ማደሪያ ሆንሽ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀንሸ ቻልሽው ተሸከምሽው ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ለመወሰን የታመንሽ አንቺ ነሽ» /ውዳሴ ማርያም፣ ቅዱስ ኤፍሬም/ ✤ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል ጥልቅ የሆነ ምሥጢራዊ ትምህርት አለ፡፡ /ዘፀ. 25÷9-20/፡፡ ✤ «ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ፤ ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ፡፡ አመ ነገደት ቊስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ፤ ወድቁ አማልክተ ግብፅ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ፤ ወተኀጉሉ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ፡፡ ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የሔደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦተ ጽዮን የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፡፡ ድንግል ማርያምም ሁሉን ማድረግ ከሚችለው ከልጇ ጋር ግብፅ ወደሚባል ሀገር በሔደች ጊዜ የሐሰተኛ ሰይጣን ዙፋኖች የሆኑ የግብፅ ጣዖታት ፈረሱ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ሁሉ ዐፈሩ» /ኢሳ 19÷1፣ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል/ #ኅዳር 21 የታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን ወይም ታቦተ ሕጉ) ዓመታዊ ክብረ በዓል የምናከብርበት ምክንያቱ፤ ፩ኛ. በሊቀ ካህናት ኤሊ ዘመን በሕዝበ አስራኤል(በአፍኒን ፊንሐስ) ኀጢአት ምክንያት፤ ታቦተ ጽዮን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካ፤ ዳጐን የተባለ የአሕዛብ ጣዖትን ቀጥቅጣ አድቅቃ ወደ እስራኤል የተመለሰችበት በመኾኑ፡፡ (1ሳሙ. ከ1-6) ፪ኛ. ታቦተ ጽዮን መፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን ወዳሠራው ቤተ መቅደስ (በዓለም ላይ እስካሁን ያልታየ ድግስ ደግሶ) የገባችበት እለት በመኾኑ፡፡ / (1ኛ ነገ. 8፥2፣ 2ኛ ዜና. 5፥1፣ ስንክሳር ዘሐምሌ 23) ፫ኛ. በቀዳማዊ አፄ ምኒልክ (ዕብነ ሐኪም) አማካኝነት ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር በ318ቱ ሌዋውያን ካህናት በሊቀ ካህናቱ አዛርያስ እየተመራች ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ የገባችበት በመኾኑ፡፡ /ክብረ ነገሥት፣ መጽሐፈ ምሥጢር፣ መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ አንድምታ መቅድም፣ …/ ፬ኛ. ነቢያትና ቅዱሳን ስለ እመቤታችን በተለያየ ኅብረ መልክእና አምሳል (ዕዝራ በቅድስት ሃገር መንፈሳዊት፥ በአምሳለ ብእሲት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተ መቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ማኅቶት፥ በወርቅ መቅረዝ፣ እረኛው ጻድቅ ሔርማ በአምሳለ ብእሲት……) ያዩበት በመኾኑ፡፡ /ሕዝ. 44፥1፣ መጽ. ዕዝራ/ ፭ኛ. በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱሳን ጻድቃን ነገሥታት አብርሐ ወአጽብሐ አማካኝነት መሥዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት የቆየችው አኵሱም ጽዮን፤ ጽዮን ማርያም ተብላ ባለ 12 መቅደሶች ባሏት በወርቅና በዕንቊ ያሸበረቀች ቤ.ክ ሠርተው ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበትና ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ የታወጀበት፡፡ ፮ኛ. በንጉሥ አፄ ባዜን (በ4 ዓ.ም. አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ዋልድባን፣ ደብረ ዐባይን፣…… ሌሎችንም የኢትዮጵያ መካናት በስደት ከልጇ ጋር ባርካ አኵስም ጽዮን ላይ መጥታ የገባችበትና የባረከችበት፤ በወቅቱም አኵስምና አካባቢዋ በብርሃን ጎርፍ የተጥለቀለቁበት በመኾኑ፤ /ታሪከ ዋልድባ፣ ታሪከ አኵስም፣ ድርሳነ ዑራኤል፣ ....) ፯ኛ. በየጊዜው (በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ) ወደ ዝዋይ፣ ወደ ጣና ቂርቆስ፣ …… ተሰድዳ ቆይታ፤ ተመልሳ (ከዮዲት በኋላና ከግራኝ በኋላ በአፄ ፋሲል የታነጹት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን) ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበት በመኾኑ፡፡ ፰ኛ. ወደ አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም በቦታው ርቀት ለመሳለም ላልቻሉ ክርስቲያኖች ዳግሚት ደብረ ጽዮን በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አዲስ አለም ላይ የተሠራችበት በመኾኑ፡፡ ፱ኛ. ሴቶችም ወንዶችም የሚያስቀድሱበትና ያለ ዐምድ ዕፁብ ድንቅ በኾነና በሃግያ ሶፍያ ቤ.ክ. አምሳል የተሠራው የጽዮን ቤተ ክርስቲያን ኅዳር 21 ጾም በመኾኑ ቅዳሴ ቤቷ የተከበረው ግን ጥር 30 ቀን 1957 ዓ.ም ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ፣ እቴጌ መነን፣ የታላቋ ብሪታንያ ንግሥት ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥና ልዑል ፊልፕ በተገኙበት ነው፡፡ ፨፨፨ #በጽዮን ስም የተመሠረቱና ዐቢይ ዓመታዊ ክብረ በዓላቸው ኅዳር 21 የኾኑ፤ ✣ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም ✣ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አዲስ ዓለም ደብረ ጽዮን ማርያም (በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ተመሠረተች) ✣ዝዋይ ደብረ ጽዮን ማርያም (ደቡብ ሸዋ) ✣ሳዶቅ አምባ ማርያም (በ1670 ዓ.ም. በአባ ሳዶቅ የተመሠረተች፤ ሰሜን ተራሮች) ✣እንፍራንዝ ደብረ ጽዮን ማርያም (ጥንታዊዋ ደብር) ✣ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ደረስጌ ደብረ ጽዮን ማርያም (በወርቅና በዕንቊ ተደርጋ በራስ ውቤ የታነጸች፤ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የነገሠባት፤ ስሜን፣ ራስ ደጀን አጠገብ) ✣ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ማርያም (እንግሊዝ፣ ለንደን) #ሥርዐተ ማኅሌቱን የላይ ቤቱን (ዘግምጃ ቤት)ና የታች ቤቱን (ዘበዓታ) እንዲሁም የአዲስ ዓለምንና የእንጦጦ ማርያም የየቤታቸውን የወረብ ቀለም አብረን አዘጋጅተንላችኃል፨ በጸሎታችሁ ሰ/ት/ቤታችንን አትርሱን፨ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/joinchat/AAAAAE2hgYCjGkwz9N1jIw /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/