ru
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Открыть в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 389 подписчиков, занимая 5 582 место в категории Религия и духовность и 2 199 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 389 подписчиков.

Согласно последним данным от 02 июля, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 23, а за последние 24 часа — -3, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 21.38%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 10.20% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 3 290 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 569 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 17.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 03 июля, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

15 389
Подписчики
-324 часа
+207 дней
+2330 день
Архив постов
ለ5ኛ ጊዜ ደብሩ ለሰ/ት/ቤቱ የቀድሞውን የሰ/ት/ቤቱን ቦታ እንዲሰጥ ከአ.አ ሐገረ ስብከት በብጹዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ አመራር ሰጪነት መምህር አካለወልድ ተሰማ ውሳኔ አስተላለፉ፡፡ ከዚህ በፊት በብጹዕነታቸው ለደብራችን የተላከውን ደብዳቤ ተከትሎ የደብራችን አስተዳደር የተወሰነውን ውሳኔ ከህግ አንጻር ማስፈጸም አልችልም በማለት በደብዳቤ ቁጥር…በቀን 18/08/2013 ዓ.ም ለአ.አ ሐገረ ስብከት አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን አቤቱታውንም ተከትሎ በዛሬው እለት ለ5ኛ ጊዜ ውሳኔው እንደጸና ደብዳቤ ለደብራችን አስተዳደር ተልኳል፡፡ በደብዳቤውም መሰረት ውሉ አሁን እንዲቋረጥ ወይም እንዲሻሻል እና በዚህ ዓመት የትምህርት መጨረሻ ድረስ የመዋዕለ ህጻናት ተማሪዎች እንዲማሩ የተወሰነውን ውሳኔ ያጸና ነው፡፡ ሰንበት ት/ት ቤታችን ምንም እንኳን በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ ያለ ቢሆንም ነገር ግን መድኃኔዓለም እየቀደመ ፈተናዎቹን እያስወገደ በሰከነ እና በበሰለ መንገድ እየሄደ በገዳማውያን አባቶቻችን እና በሕጻናቱ ጸሎት እዚህ ደርሷል፡፡ የደብራችን አስተዳደር አሁንስ ለ5ኛ ጊዜ የመጣውን ውሳኔ ይፈጽም ይሆን? ደብራችንስ ወደ ቀደመ ሰላሙ ይመልስልን ይሆን? ወይስ ከእንደገና አቤቱታ ለሀገረ ስብከቱ ያቀርብ ይሆን ? ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን!!!

ግንቦት_16 ተዛካር ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በእንተ ስብከቱ ቅዳሴ ቤቱ ውስተ ሀገረ እስክንድርያ ወሶበ ጽሕፈቱ ወዕረገቱ ውስተ ሰማያት ወርእዮቱ ለሠራዊተ ሰማያውያነ ፡፡ ✤ወደ ሰማይ ወጥቶ በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሰራዊትን ሥራዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ፡፡ ✤ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ነው ፡፡ ✤በእስክንድርያም ሀገር ቤተክርስቲያን የከበረችበት ዕለት ነው ፡፡ ሰላም ለቅደሴ ቤትከ በእለ እስክንድርያ ሀገር ፡፡ እለ ሐነፅዋ ኬነውት ወጠበብታ ምክር፡፡ ወእንዘ ትበውእ ዮሐንስ ውስተ መቃብር ፡፡ ተኀባዕከ ወተሠወርከ በሥልጣን ኀይል መንክር ፡፡ ባሕቱ ልብሰከ ዘተተፈ ለዝክር ፡፡ #በተለያዩ_ቅጽል_ስሞች_የሚጠራ፤ (100 አካባቢ ከሚጠጉ ስሞቹ ጥቂቶቹን /21ዱን ስሞች ከጽሑፍ በስተመጨረሻ ይመልከቱ) #ሰዓሊ_የኾነ፤ የጌታችንን ስነ ስቅለት የሳለ፡፡ #ከ81ዱ_የመጽሐፍ_ቅዱስ_ክፍሎች_5ቱንና_ሌሎች_መጻሕፍትንም_(ነገረ ማርያምን ..) የደረሰ፤ #ብዙ_ደቀ_መዛሙርትን_ያስተማረ፤ ወደ ሰማይ ወጥቶ በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሰራዊትን ሥራዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ፡፡ ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ነው ፡፡ በእስክንድርያም ሀገር ቤተክርስቲያን የከበረችበት ዕለት ነው ፡፡ #share እና #Like ማድረግ እንዳይረሱ ጌታ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው፡፡ ✤ዮሐንስ ንጹሕ በአምሳለ ትጉሃን፤ (#ዮሐንስ_እንደ_መላእክት_ንጹሕ_ነው፤) ✤ዮሐንስ ድንግል ምክሐ ቅዱሳን፤ (#ዮሐንስ_ድንግል_የቅዱሳን_መመኪያ_ነው፤) ✤ዮሐንስ ስርግው በቀጸላ ሥን በሜላተ ብርሃን፤ (#ዮሐንስ_በብርሃን_መጐናጸፊያና_ሻሽ_የተጌጠ_ነው፤) ✤ዮሐንስ አርጋኖነ ዘቤተ ክርስቲያን፤ (#ዮሐንስ_የቤተ_ክርስቲያን_በገና_ነው፤) ✤ወበቃለ ቀርን ዘይኬልህ በኤፌሶን፥ ይስአል ለነ ስርየተ ለኀጥኣን፡፡ (#በኤፌሶን_ዐዋጅ_የሚናገር_ዮሐንስ_ኀጥኣን_ለምንሆን_ለኛ_ይቅርታን_ይለምንልን፡፡ /እመጽሐፈ ሰዐታት/ ፨ ‹‹ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ፤ ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ›› /መልክአ ኢየሱስ/ ፨ ሰላም ለሥዕልኪ ወለሥዕለ ወልድኪ ዘሰዓሞ፤ ዮሐንስ ርኄ ዮሐንስ ቀናንሞ፤ ለዝ ወልድኪ መሐሪ ኅሩመ በቀል ወተቀይሞ፤ ማርያም ሀብኒ በእዴኪ እንዘ ትጼውዒ ስሞ፤ ሥጋሁ ቅዱሰ ወክቡረ ደሞ፡፡ /መልክአ ሥዕል/ ፨#100_አካባቢ_ከሚጠጉ_ስሞቹ_ጥቂቶቹን_21ዱን_ስሞች_እነኾ፤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ዮሐንስ፤ ዮሐንስ #ፍቁረ እግዚእ፥ (የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት (ጴጥሮስ ፣ ናያዕቆብ ) ዮሐንስ ቀዳሚዉ ነዉ፡፡ ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት ፣ ምሥጢረ መንግስትን (መለኮትን) በደብረ ታቦር፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት ፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም ‹‹ጌታ ይወደዉ የነበረ ደቀ መዝሙር ››ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ዮሐ 13፡ 23 ፡፡ ወልደ #ዘብድዮስ ፥ ዮሐንስ #ነባቤ መለኮት ፥ ዮሐንስ #ቦኦርኔጌስ ፥ ዮሐንስ #አብቀለምሲስ ፥ (ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነዉን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብሏል፡፡ትጉሙም የራዕይ አባት ማለት ነዉ፡፡) ዮሐንስ #ወንጌላዊ ፥ ዮሐንስ #ድንግል ዮሐንስ #ታዎሎጎስ ቅዱስ ዮሐንስ ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን አስፍቶ በመጻፉ (ታዎሎጎስ) ተብሏል፡፡ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር)ማለት ነዉ፡፡ 1. #ዮሐንስ_ብፁዕ (ብፁዕ ዮሐንስ) 2. ዮሐንስ ድንግል 3. #ዮሐንስ_ፍንው 4. #ዮሐንስ_ካህን 5. #ዮሐንስ_ኅሩይ 6. ዮሐንስ ሥርግው 7. #ዮሐንስ_ምዑዝ 8. ዮሐንስ ቅኑይ 9. #ዮሐንስ_ማኅቶት 10. ዮሐንስ ቤዛ ሰማይ 11. #ዮሐንስ_ክቡር 12. ዮሐንስ ጻድቅ 13. #ዮሐንስ_ረድእ 14. ዮሐንስ ማኅቶት 15. #ዮሐንስ_ድንግል 16. ዮሐንስ ንጹሕ 17. #ዮሐንስ_ለባዊ 18. ዮሐንስ መረግድ 19. #ዮሐንስ_ዕንቈ 20. ዮሐንስ መልአክ 21. #ዮሐንስ_ኪሩብ 22. #ቁጽረ ገጽ ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል፡ በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን አሜን የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/ .....share Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem www.Finotehiwotsundayschool.com ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ

‹‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡ ›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት ግንቦት ፩ 2013 ዓ.ም በ
‹‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡ ›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት ግንቦት ፩ 2013 ዓ.ም በቀ.ደ.ሰላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉኀን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ በሥርዐተ ተክሊል ጋብቻህን የፈጸምከው የሰ.ት.ቤት ወንድማችን ዲ/ን ኤልያስ ፀጋ እና፤ የፈጸምሽው የሰ.ት.ቤት እኅታችን ኢየሩሳሌም አየለ ፤ የፈጸማቹሁት ጋብቻ፤ የይሰሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ ÷ ያጣምራቹ ÷ ያዋህዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኃላ ይከተላቹ፡፡ †<<ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንደሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡>> ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበስ ለፓሊካርፐስ በላከው መልእክቱ፡፡ †<<ከተጋባቸሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፈ አጼ ዘርዓያዕቆብ፡፡ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም እና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት

/የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/
+7
/የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

#ግንቦት 𝟏𝟐፤ ፍልሰተ አጽሙ ለሐዲስ_ሐዋርያ_ፀሐይ_ማር_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፠ ‹‹አባቴ ተክለ ሃይማኖት የሚለኝ ሁሉ፤ በፍልሰቴ ቀን በገዳሜ ይገኝ እኔም ልጄ እለዋለው ከቅዱስ ሚካኤልና ከልጄ ፊልጶስ ጋር እባርከዋለው።›› /ገድለ ተክለ ሃይማኖት/ ፠ አባታችን ባረፉ በ54ኛ ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም በአፄ ሰይፈ አርዕድ ዘመን ለ4ኛው እጨጌ ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡ ፠ ግንቦት 12 በደብረ ሊባኖስ ትልቁ በዓል ነው፡፡ ጥንተ መሠረቱም፤ 12ቱ እጨጌዎች ከያሉበት ቦታ እየመጡ 1ድ 1ድ ወር ሙሉ በፈረቃ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ቅዱስ አጽም ተራ ገብተው ያጥኑ ነበር፡፡ ግንቦት 12 ግን ሁሉም ከያሉበት ተሰባስበው በአንድነት ያከብራሉ፡፡ #የጻድቁ_ዋና_ዋና_የታሪክ_ሂደቶች፤ ፠ከአባታቸው ከቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከቅድስት እግዚዕ ኀረያ፤ መጋቢት 24 ቀን ተጸንሰው፤ በታኅሣሥ 24 ቀን በ1190 ዓ.ም. በእቲሣ ተወለዱ፡፡ ፠በተወለዱ በ3ኛው ቀን አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመሠገኑ፡፡ ፠በተወለዱ በ40ኛው በደብረ አጋዓዚት ማርያም ፍስሐ ጽዮን “የጽዮን ደስታ” ተበለው ተጠሩ፡፡ ፠እስከ 7 ዓመታቸው ድረስ ከአባታቸው ከጸጋዘአብ ዘንድ እየተማሩ ፠በ15 ዓመታቸው ዲቁናን ከጌርሎስ ዘንድ ተቀበሉ፡፡ ፠በ22 ዓመታቸው ከአቡነ ጌርሎስ ዘንድ ቅስናን ተቀበሉ፡፡ ፠በከተታ አውራጃ 3 ዓመት ወንጌልን እያስተማሩ ብዙ ድንቅ ነገርን አደረጉ፡፡ ፠በኅዳር 24 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ወደ ላይ ነጠቃቸው ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር 25ኛ ካህን ሆነው የሥላሴን መንበርን አጠኑ ፠በሐይቅ እስጢፋኖስ 10 ዓመት፥ በደብረዳሞ 12 ዓመት ኖረዋል፡፡ ፠በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች እየተዘዋወቱ አስተምረዋል፤ በአኵሱም ጽዮን፣ በዋልድባና በዙሪያቸው ባሉ ገዳማት እየዞሩ ተሳልመዋል፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም በመውረድም ተሳልመው ተመልሰዋል፤ ሲመለሱም ብዙ ቅዱሳን አብረዋቸው ተመልሰዋል፡፡ /እነ እጨ ዮሐንስ ዘጎንድ (ዘጠገሮን) ልብ ይሏል፡፡ ፠በ1267 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስን በአት አድርገው ኖሩ፡፡ ለ22 ዓመት ቆመው በመጸለይ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሠበረ ደቀ መዝሙሮቻቸው በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡ በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመት በጸሎት ቆሙ በጠቅላላው ለ29 ዓመት በጸሎት ከቆሙ በኋላ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን ነሐሴ 24 ቀን 1290 ዓ.ም አረፉ፡፡ ፠፠፠አባታችን ባረፉ በ54ኛ ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም በአፄ ሰይፈ አርዕድ ዘመን ለ4ኛው እጨጌ ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡ ፠የደብረ ሊባኖስንም ቦታ የሰጠው ሐኖ (ተክለ ሃይማኖት) /የግራርያ ሰው/፤ ሲሆን ዓፄ ልብነ ድንግል በነገሠ በ8ኛው ዓመት ‹መርሕ› ከምትባል ስፋራ ታቦቱ ከነዋየ ቅድሳቱ ጋር ‹ከምድኃሬ› ተዛውሯል፡፡ ይህንንም ያደረገው እጨጌው አባ ጴጥሮስ ነበር፡፡ #የጻድቁ_ክብረ_በዓላቶቻቸውም፤ #ኅዳር 24፤ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑበት #ታኅሣሥ 24፤ የአባታችን ልደት #ጥር 24፤ የአባታችን ስባረ አጽም #መጋቢት 24፤ የአባታችን ጽንሠት #ግንቦት 12፤ የአባታችን ፍልሰተ አጽም #ነሐሴ 24፤ የአባታችን በዓለ እረፍት ናቸው፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/ .....share ፠ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ፤ እስመ በውስቴታ ተገብረ ፍልሰተ ሥጋሁ ወአጽሙ፡፡ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem www.Finotehiwotsundayschool.com ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ

ሐ. በሥርዓተ ጸሎት፤ ከዓመት እስከ ዓመት ለሚከናወኑ (የዘመናትና የሳምንታትን ጨምሮ) ማንኛውም ሥርዐተ ጸሎት ዋና መሪው የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ነው፡፡ ማኅሌቱ፣ ቅዳሴው፣ ፍትሐቱ፣ ጥምቀተ ክርስትናው ሁሉ በዜማው መሪነት የሚከናወኑ አገልግሎቶች ናቸው፡፡ መ. ለቱሪዝም ሀብት (መስህብነት)፤ ክርስቲያናችን በየወሩና በየዓመቱ ከምታከብራቸው በዓላት ላይ ከሚቀርቡት ዝግጅቶች አብዛኛውን ክፍል የሚይዘው በቅዱስ ያሬድ ዜማ የሚቀርበው የዝማሬና የቅዳሴ አገልግሎት ነው፡፡ #ማሕሌቱን_ለማሕሌት_አባት_እናቅርብለት:: Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem www.Finotehiwotsundayschool.com ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ