ru
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Открыть в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 457 подписчиков, занимая 5 521 место в категории Религия и духовность и 2 192 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 457 подписчиков.

Согласно последним данным от 02 августа, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 75, а за последние 24 часа — 4, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 23.81%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 7.58% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 3 681 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 172 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 25.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 03 августа, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

15 457
Подписчики
+424 часа
-17 дней
+7530 день
Архив постов
‹‹ሐምሌ 10›› በዚህ ዕለት ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል ነው። ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ ሐዋርያ ነው:: ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእስራኤላውያን ወላጆቹ ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው:: ይህ በምን ይታወቃል ቢሉ እርሱ ሕፃን እያለ ሔሮድስ 14,000 ሕፃናትን ሲፈጅ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል:: እናቱ በቅርጫት ውስጥ አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው ነበር:: ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል:: በባልንጀሮቹ ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና አካባቢ ስላደገ) አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር:: ምሑረ ኦሪት ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር:: በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል የአጎት ልጅ ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ የጠራበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው:: ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ: ከበለስ ቁጭ ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ?" እያለም ይተክዝ ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን አውቆ በፊልጶስ አማካኝነት ጠርቶታል:: ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በኋላ ግን የጌታችንን ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እስራኤላዊ" ሲል አመስግኖታል:: ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር ምሥጢረ መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ ቅዱስም ሰክሮ: ብዙ አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ ክርስቶስ) መልሷል:: እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል:: የጌታችን ወንድም የተባለ ቅዱስ ያዕቆብ በአይሁድ ከተገደለ በኋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም ሁለተኛ ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ አገልግሏል:: ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ ደርሶበታል:: በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት አልፏል:: የሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል በረከቱ ይደርብን🙏

በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡ ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት ለአባቶች መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡፡ አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡ አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡ ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል፡፡ አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር፡፡ ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ›› በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡ ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ›› ብለው ገዝተው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው ‹‹እግዚአብሔር ይፍታሽ›› ባሏት ጊዜ ጠልቃለች፡፡ ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡ በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ መልክአ መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ ጸሎት አለቻቸው፤ እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ፡፡ ጸሎቷም የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች፡፡ በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ አቡነ ዘበሰማያት ይደግማሉ፡፡ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ጸሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም፡፡ ይህንን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት የምናገኘው ከገድላቸው ላይ ነው፡፡ ጻድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልው ሚያዝያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈሰ ቅዱስ ስም አሜን ሐምሌ 9-አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ እራሳቸው ተዘቅዝቀው ባሕር ውስጥ መቆም የጀመሩበት እና ከዘጠኝ ዓመት በኃላ ጌታችን ተገልጦላቸው "ኢትዮጵያን ምሬልሃለሁና ና ከባሕሩ ውስጥ ውጣ" በማለት ከባሕር ካወጣቸው በኃላ ለአባታችን ቃልኪዳኑን ያጸናበት ዕለት ነው፡፡ + የአምስቱ አሕጉር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ቴዎድሮስ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ + የቆጵሮሱ ቅዱስ ታኦድሮስ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ከታኦድሮስም ጋራ ሦስት ሴቶችና እርሱን ያሠቃዩት የነበሩት ሁለቱ መኳንንት ሉክያኖስና ድግናንዮስ በጌታችን አምነው መስክር ሆነው ዐረፉ፡፡ + መሥተጋድል አባ ኅልያን ዕረፍቱ ነው፡፡ + የግብፃዊው የቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ዕለት ነው፡፡ + ከአባ ኤሲ ጋራ በሰማዕትነት ያረፉ 5504 ሰማዕታት መታሲቢያቸው መሆኑን ስንክሳሩ ይጠቅሳል፡፡ ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት፡- ዲዮቅልጥያኖስ በካደና ጣዖታትን ባመለከ ጊዜ ምአመናን ያስሩና ይገድሉ ዘንድ መኳንንቱን ሁሉ ወደ አገሮች ሁሉ ላከ፡፡ ስሙ ፍላጦስ የሚባል መኮንንም ወደ አፍራቅያ አገር ላከው፡፡ በዚያም ለክርስቲያኖስ ወገን መምህር የሆነውን ቅዱስ ቴዎድሮስን ወደ እርሱ አስጠርቶ ለጣዖታት እንደሠዋ አዘዘው፡፡ ቅዱሱም ‹‹ሰማይንና ምድርን ለፈጠረ ለእውነተኛው አምላክ ለኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው የምሠዋው እንጂ በሰው እጅ ለተሠሩና ለረከሱ ጣዖታት አልገዛም›› አለው፡፡ መኮንኑም ይህንን ኃይለ ቃል ከቅዱስ ቴዎድሮስ አንበት በሰማ ጊዜ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ለ40 ቀን በፍርፋትና በስቅላት፣ በእሥራትና በመንኮራኩር እንዲያሠቃዩት አዘዘ፡፡ እንዳዘዘውም ለ40 ቀን በእጅጉ ካሠቃዩት በኋላ በመጨረሻ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና ሰማዕትነቱን በድል ፈጽሞ የክብርን አክሊል ተቀዳጀ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን! + + + ሰማዕቱ ቅዱስ ታኦድሮስ፡- ይኽንንም ቅዱስ ክርስቲያን በመሆኑ ይልቁንም የቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ በመሆኑ ብቻ በመኳንንቶቹ በሉክያኖስና በድግናንዮስ ዘንድ ከሰሱት፡፡ መኳንንቱም ወደ እነርሱ አስቀርበው በመረመሩት ጊዜ ቅዱስ ታኦድሮስም በጌታችን ታመነ፡፡ እነርሱም እየደበደቡት ለጣዖት እንዲሠዋ ባስገደዱት ጊዜ ቅዱሱ ከወደቀበት እየተዳኸ ሄዶ ጣዖቱን ረገጠውና ከመንበሩ ላይ ገልብጦ ጣለው፡፡ መኳንንቶቹም የሚያመልኩትን ስላቃለለባቸው በዚህ ተቆጥተው ቅዱስ ታኦድሮስ በእጅጉ አሠቃዩት፡፡ ሥጋውንም በማቅ ጨርቅ፣ ጨውና ኮምጣጤ ነክረው ፋቁት፡፡ እርሱም ጣዖታቱን ይረግም ነበር፡፡ የሚናገርበትንም ምላሱን ቆረጡት፡፡ አንዲትም ሴት የተቆረጠች ምላሱን አንሥታ ሆዱ ላይ ቢያደርጋት በተአምራት ተዘርግታ አፉ ውስጥ ገባችና እንደቀድሞው ሆነች፡፡ አንዲት ነጭ ርግብ መጥታ በቅዱሱ ላይ ስትዞር ሌላም ሶሪት ወፍ መጥታ በላዩ ተቀመጠች፡፡ በዚህም ጊዜ መኮንኑ ሉክያኖስ በጌታችን አመነ፡፡ ድግናንዮስ ግን ተቆጥቶ ቅዱስ ታኦድሮስን ይከተሉት የነበሩትን ሦስት ሴቶች በሰማዕትነት ገደላቸው፡፡ ቅዱስ ታኦድሮስም ነፍሱን አሳልፎ በሰጠ ጊዜ ርግቧና ሶሪት ወፏ በርረው ሄዱ፡፡ ሉክዮስም ድግናንዮስን የክርስቲያኖች ሃይማኖት የቀናችና እውነትም እንደሆነች መከረው፡፡ እርሱም የተመለከታቸውን ተአምራት አስተውሎና የጓደኛውን ምክር ሰምቶ በጌታችን አመነ፡፡ ከዚህም በኋላ ሉክያኖስና ድግናንዮስ ከቆሮንቶስ አገር ወደ ቆጵሮስ በመርከብ ሄዱ፡፡ በዚያም ሌላኛው መኮንን ክርስቲያኖችን ሲያሠቃይ ሉክያኖስ ከጓደኛው ተሠውሮ በመሄድ በመኮንኑ ፊት የጌታችንን ክብር በመመስከር የጣዖታቱን መንበር ገለበጠው፡፡ መኮንኑም ራሱን በሰይፍ አስቆረጠውና የሰማዕነት አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ድግናንዮስም ሥጋውን ወስዶ ገንዞ ቀበረውና እርሱም በተራው በመኮንኑ ፊት ቀርቦ ጣዖታቱን በመርገም የጌታችንን አምላክነት መሰከረ፡፡ አሁንም ከሃዲው መኮንን የድግናንዮስን ራስ በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ የክብር አክሊልንም ተቀበለ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን! + + + መሥተጋድል አባ ኅልያን፡- የዚህም ቅዱስ አገሩ ዐይነ ፀሐይ ይባላል፡፡ አባቱ ዲስጣ እናቱ ካልሞና ይባላሉ፡፡ ኅልያንም በወጣትነት የተገሰገነ የወርቅና የብር አንጥረኛ ነበር፡፡ በአንዲት ዕለት ከዐረብ አገልጋዮች የሆነች ሴት መጥታ የጆሮ ጉትቻ ከሠራላት በኋላ ዋጋውን ቢጠይቃት ‹‹ወንዶች ከሴቶች የሚሹትን ብትሻ እነሆኝ አለሁ ሌላ ገንዘብ ግን የለኝም›› አለችው፡፡ እርሱም ይህንን በሰማ ጊዜ ‹‹አንቺ የጨለማው አበጋዝ ልጅ ከእኔ ራቂ›› ብሎ ገሠጻት፡፡ ከዚህም በኋላ የነፍሱን ድኅነት አስቦ ገንዘቡን ለእናቱ ሰጥቶ ራቅ ወዳለ ገዳም ይሄድ ዘንድ ተነሣ፡፡ እግዚአብሔርም መንገዱን አቅንቶለት ረጅሙን መንገድ አቅርቦለት ወደ ኤርትራ ባሕር ዳርቻ በአንዲት ቀን ደረሰ፡፡ በዚያም ቆሞ ሳለ ነጭ ልብስ የለበሱና እንደፀሐይ የሚያበራ መስቀልን የተመረኮዙ ሦስት ሰዎች ተገለጡለትና ከእነርሱ ጋራ ወሰዱት፡፡ ወደ አትክልት ቦታም በደረሱ ጊዜ በትርና የዕንቁ መስቀል ሰጡት፡፡ በዚያም በአንድነት ጸለዩና ሰገዱ፡፡ ቅዱስ ኅልያንም ሰግዶ ቀና ሲል እነርሱን አጣቸው፡፡ በመለየቱም አዝኖ አለቀሰ፡፡ በዚያም በአትክልቱ ቦታ ቅጠል እየተገመበ ልብሱም ቅጠል ሆኖ ኑሮውን በብሕትውና አደረገ፡፡ ወደ ዋሻዎችም ለመሄድ ባሰበ ጊዜ የሰጡት በትረ መስቀሉ ታበራለት ነበር፡፡ ሰይጣንም መልካም ተጋድሎውን ስላየ ቀናበትና በፈተና ሊጥለው በማሰብ በሰው ተመስሎ ወደ ክፉዎች ሰዎች ዘንድ ሄዶ ‹‹እዚህ ቦታ የተሠወረ ገንዘብ አለ፣ ጠባቂውም አባ ኅልያን ነው፣ እርሱን ከያዛችሁት ያለበትን ያሳያችኋል›› አላቸው፡፡ ሰዎቹንም እየመራ አመጣቸውና ከወንዝ ማዶ በደረሱ ጊዜ መሻገሪያ አጡ፡፡ ውኃም እጅግ ተጠምተው ነበርና ሰይጣንም ወደ አባ ኅልያን በመሄድ ‹‹ውኃ ተጠምተውና መሻገሪያ አጥተው ተቸግረው ሳለ ውኃ የማታጠጣቸው ለምንድነው? አለው፡፡ እርሱም ሲሄድ ሰዎቹ የሚይዙት መስሎት ነበር፡፡ አባ ኅልያን ሄዶ ውኃ ቀድቶ አጠጣቸው፡፡ እነርሱም ባዩት ጊዜ ምንም የሌለው ድኃ መሆኑን ዐውቀው ተውት፡፡ ሰይጣንም ተንኮሉ ስለከሸፈበትና ስላፈረ ዳግመኛ በደጋግ በመሆኑ መነኮሴዎች ተመስሎ አባ ኅልያንን ሊያስተው ወደ በዓቱ ሄደ፡፡ ቅዱሱም በብርሃን መስቀሉ ባማተበ ጊዜ እንደትቢያ መነው ጠፉ፡፡ የአባ ኅልያንም የዕረፍቱ ሰዓት በቀረበ ጊዜ እነዚያ መጀመሪያ የተገለጡለት ሦስት ሰዎች ዳግመኛ ተገለጡለትና ገድሉን ጻፉለት፡፡ ቅዱሱ ባረፈም ጊዜ በክብር ቀበሩት፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን! +++ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ፡- አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናቱ ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል፡፡ የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል፡፡

#ሐምሌ_7_የቤተ_ክርስቲያን_ማኅቶት ፥ #አፈ_በረከት_ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ፤ #ወልዱ_ለአቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል_ልደቱና_እረፍቱ_ነው፡፡ ዕረፍቱ የኾነው በሐምሌ 7 (6,705 ዓመተ ዓለም፥ በ2ት እንድቅትዮን፥ በአልቦ አበቅቴ፥ በ7ት ጥንተ ዮን፥ በወንጌላዊው ማቴዎስ ዘመን በዕለተ ረቡዕ) ነው፡፡ ያረፈውም በአፄ ይስሐቅ ጥያቄ የጋራ መናገሻ መድኀኔ ዓለም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ባርኮ ሲመለስ በደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም ሲኾን ፤ አርድዕቱ ሥጋውን ይዘው ሂደው በአባቱ መካን በደብረ ጎል (አሁን በደብረ ባሕርይ) አሳርፈውታል፡፡ ፠ይህ አባት ከ40 በላይ መጻሕፍትን የደረሰና ብዙ መጻሕፍትን እያጻፈ ለመላው ገዳማት ያዳረሰ፤ ጸሓፊ፥ ቅዱስና ጻድቅ፥ ፈላስፋና ደራሲ፥ መናኝና ባሕታዊ፥ ሊቅና ተመራማሪ፥ ገጣሚና በለቅኔ፥ የመጻሕፍት ተርጓሚና የዘመን አቈጣጠር (የአቡሻህር) ሊቅና ተንታኝ፥ አርክቴክትና መሐንዲስ ነው፤ በዚህም ምክንያት በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፤ ፠ዳግማዊ ቄርሎስ (ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ)፥ ፠ ዐምደ ሃይማኖት ፠ ዳግማይ ቅዱስ ያሬድ፤ ፠ የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት፥ ፠ አፈ በረከት ፠ የከሃድያን ዘላፊ፥ የቅዱሳን ፀሐይ …….ተብሏል ከ40 በላይ ድርሰቶቹ መካከል በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚታወቁት 34ቶቹ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፤ 1.  ✼  ኆኀተ ብርሃን 2.  ✼  መዝሙረ ኢየሱስ (ሰላመ ማርያም) 3.  ✼  መዝሙረ  ድንግል 4.  ✼  የማርያም የምስጋና ሰላምታ 5.  ✼ ውዳሴ መላእክት 6.  ✼  ውዳሴ ነቢያት 7.  ✼ ውዳሴ ሐዋርያት 8.  ✼  ውዳሴ ሰማዕታት 9.  ✼  ውዳሴ ጻድቃን 10.  ✼  መጽሐፈ ብርሃን 11. ✼ መጽሐፈ ምሥጢር 12. ✼ መጽሐፈ ሰዐታት ዘመዓልት ወዘሌሊት 13. ✼ መጽሐፈ አርጋኖን 14. ✼ አርጋኖነ ውዳሴ 15. ✼ መሰንቆ መዝሙር 16. ✼ እንዚራ ስብሐት 17. ✼ ውዳሴ መስቀል 18. ✼ ፍካሬ ሃይማኖት 19. ✼ ፍካሬ ሐዋርያት 20. ✼ መጻሕፍተ ቅዳሴያት 21. ✼ ቅዳሴ እግዚእ ካልዕ 22. ✼ መዐዛ ቅዳሴ 23. ✼ ሕይወታ ለማርያም (ሕይወተ ማርያም) 24. ✼ ውዳሴ ስብሐት 25. ✼ ውዳሴ ማርያም ካልዕ 26. ✼ ውዳሴ ስብሐት ወሰላምታ 27. ✼ ማኅሌት ዘነቢያት ወዘሐዋርያት 28. ✼ የሰባቱ ጊዜያት ጸሎት (መልክአ ሕማማት) 29. ✼ ጸሎተ ፈትቶ (ጸሎተ ማዕድ) 30. ✼ ጸሎት ዘ(ቤት)ውስተ ቤት 31. ✼ መልክአ ቊርባን 32. ✼ ተአምኆ ቅዱሳን 33. ✼ ተአምኆታ ለእግዝእትነ ማርያም 34. ✼ ክብረ ቅዱሳን (በፎቶ ላይ የምታዩት ገዳም፤ በዓለም ብቸኛው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ገዳም የኾነው ደብረ ባሕርይ ነው፡፡ የቦታው አቀማመጥ እጅግ በጣም ማራኪና እንደ ደብረ ዳሞ ሲሆን የሚወጣው በመሰላል ነው፡፡)፤ ገዳሙ የሚገኘው #በደቡብ_ወሎ_በቦረና_አውራጃ ነው፡፡ (አስተጋባኢ /ይህንን ጽሑፍ ከአባቶች በመጠየቅ ፥ መጻሕፍትን በማንበብ ፥ ከታላቁ ገዳም ደብረ ባሕርይ ጋሥጫ ድረስ ሂዶ ያዘጋጀው የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነው፡፡) አምላከ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሀበነ በረከተ ወረድኤተ፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

✤✤✤ #ሐምሌ_ቅድስት_ሥላሴ ቅድስት ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣና ትርጕሙም ልዩ ማለት ሲኾን የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ልዩ (የሥላሴን አንድነትና ሦስትነትን የሚመስል ስለሌለ፤ ቢመስልም ምሳሌ ዘየኀጽጽ) ስለኾነ ሥላሴን ቅድስት በሚል ቅጽል እንጠራለን፡፡ #ሐምሌ_7_ቀን_ቅድስት_ሥላሴ_ለአብርሃም_የተገለጹበት_ነው፡፡ ይኸውም ስለ ፫ት ምክንያቶች ነው፤ #፩ኛ) ለመልካም ነገር /በአብርሃም አንግዳ መቀበል ፀር የኾነ ሰይጣንን ለማሳፈር/ (ሰይጣን በምቀኝነት አብርሃም እንግዳ እንዳይቀበል የውሸቱን ወደ አብርሃም ቤት በሚወስድ መንገድ ላይ ግንባሩን ገምሶ፥ ደሙን አፍስሶ ሰዎች አብርሃም እንዲህ መጥፎ ነውን እንዲሉና እንግዶች ወደ ቤቱ ሂደው እንዳይስተናገዱ አድርጓል፤ አብርሃምም ለ3 ቀናት እንግዳ እየጠበቀ ጾሙን ውሎ ነበር፡፡ ይህን የሰይጣን ክፋት የአብርሃምን እምነትና እንግዳ መቀበል የተመለከቱ ፥ ምግብን የማይመገቡ ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው እሳት ቅቤን እንደሚበላ ተስተናግደዋልና ነው፡፡ መስተናገዳቸውንም መምህረ ጋሥጫ የኾነው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ እንዲህ በግጥም አስቀምጦታል፤ ለንግሥክሙ ሰገደ አብርሃም በርእሱ፡፡ ቤተ ገብርክሙ እንዘ ይብል ገሐሡ፤ አጋዕዝትየ ዘትሤለሱ ግናይ ለክሙ፡፡ እዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባው አምላካችንም ኾነ ቅዱሳን መላእክት ለአብርሃምና ለሌሎችም ቅዱሳን በተለያየ አምሳል መገለጻቸውን ልብ ይሏል፡፡ ለአብነትም፤ ፠ ለአብርሃም በአምሳለ አረጋዊ፤ ፠ ለሕዝቅኤል በዘባነ ኪሩብ፤ ፠ ለዳንኤል በአረጋዊ፣ ፠ ለዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ በተለያየ አምሳል፤ ፠ ለደብረ መጕናው (ሞጊና) ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን አቡነ አብሳዲ ደግሞ ራሱ መድኀኔዓለም ተገልጾላቸውና ተቀብለውት እንደ አብርሃም እግሩን ያጠቡት መኾኑን ልብ ይሏል፡፡ #፪ኛ) ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛልሃለሁ ያሉት ሥላሴ ቃሉ የማይታበይ መኾኑን ለማሳየት (ሰማይና ምድር ያልፋል ፥ ቃሌ ግን አያልፍም ብሎ በኋለኛው ዘመን ጌታችንም እንዳረጋገጠው)፤ ለአብርሃምና ለሣራ ልጅ ሊሰጧቸው፡፡ አባታችን አብርሃም 99 ዓመት ፥ እናታችን ሣራ 89 ዓመት መልቷቸውና የመውለጃ ጊዜያቸው ባለፈበት ሰዐት እንደሚወልዱ ለማብሰር፡፡ #፫ኛ) ምግብ ተመግበን ካበቃን በኋላ አምላካችንን ማመሰገን እንደሚገባን ለማስተማር፡፡ (የታረደው ወይፈንም በተዓምራት ተነሥቶ ስብሐት ብሎ አመሰግኗል፤ ይህንንም መምህረ ጋሥጫ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ በግጥም እንዲህ አስቀምጦታል፤ ድኅረ በላዕክሙ ላሕመ እንበይነ ፍቅረ ሰብእ ፍጹም ፤ ዘበኀይልሙ ሐይወ ላሕም፤ ሥላሴ ክቡራነ ስም፡፡ ግናይ ለክሙ፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

#ልደተ_ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_ወሥርዐተ_ማኅሌት በሃገራችን የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ክብረ በዓል የሚከበርባቸው አብያተ ክርስቲያናት ጥቂቶቹ (በጽሑፉ መጨረሻ ላይ ይመልከቱ) ልደቱና ብሥራቱ አባቱ ዘካርያስ (ከአብያ ምድብ የኾነ ሊቀ ካህን ነው)፤ እናቱ ኤልሳቤጥ (ከአሮን ነገድ ነበረች)፤ ሁለቱም የጌታን ትእዛዝና ሥርዓት ሁሉ ጠብቀው ያለ ነቀፋ የሚኖሩ፣ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ ኤልሳቤጥ መካን በመሆኗ ልጅ አልነበራቸውም፡፡» /ሉቃ.1÷5-7/፡፡ ካህኑ ዘካርያስና ቅድስት ኤልሳቤጥ ልጅ እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን ዘወትር በጸሎት ይጠይቁ ነበር፡፡ አንድ ቀን ዘካርያስ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሥርዐት /ዘጸ.3ዐ÷6-8/ ወደ ቤተ መቅድስ ገብቶ ዕጣን የማጠን ተራ ደርሶት /ዕጣ ወጥቶለት/ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ መልአከ እግዚአብሔር ከዕጣን መሠዊያው /ከዕጣን መሥዋዕት ማቅረቢያው/ በስተቀኝ ቆሞ ታየው፡፡ ዘካርያስም ባየው ጊዜ በፍርሃት ተዋጠ፡፡ መልአኩ ግን «ዘካርያስ ሆይ አትፍራ ጸሎተህ ተሰምቷል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፤ በእርሱ ተድላና ደስታ ታገኛለህ ብዙዎቹም በእርሱ መወለድ ደስ ይላቸዋል፤ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና» በማለት ብሥራት ከነገረው በኋላ ስለሚወለደው ልጅ አራት ነገሮችን ነገረው /ሉቃ.1÷13-17/፡፡ ሀ. የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፡ ለ. በእናቱ ማኅፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል፡፡ ሐ. ከእስራኤል ወገን ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል፤ መ. ለጌታ የሚገባ ሕዝብ ለማዘጋጀት በኤልያስ መንፈስና ኃይል በጌታ ፊት ይሔዳል፡፡ ዘካርያስ ይህንን ከመልአኩ በሰማበት ወቅት እርሱ ሸምግሎ፥ ሚስቱም አርጅታና የመውለጃ ዕድሜዋ አልፎ በዚያም ላይ መካን ነበረችና «ይህን በምን አውቃለሁ? እኔ ሽማግሌ ነኝ ሚስቴም በዕድሜ ገፍታለች» በማለት ጥርጣሬውን በጥያቄ መልክ አቀረበ፡፡ በዚህን ጊዜ መልአኩ እንዲህ አለው «እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፡፡ ይህን እነግርህና ይህን የምሥራች አመጣልህ ዘንድ ተልኬያለሁ፤ እነሆ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ ይህ እስከሚፈጸምበት ቀን ድረስ ድዳ ትሆናለህ፤ መናገርም አትችልም» አለው፤ በዚህም መሠረት ዘካርያስ አገልግሎቱን ፈጽሞ ሲወጣ መስማትም ሆነ መናገር አልቻለም ነበር፡፡ መልአኩ እንደነገረውም ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰች፡፡ ይህ ከሆነ ከስድስት ወር በኋላ የቅዱስ ዮሐንስን መፀነስ ለዮሐንስ ያበሠረው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ጌታችንን እንደምትወልድ አበሰራት፡፡ መልአኩ እመቤታችንን ሲያበስራት ኤልሳቤጥ መፀነስዋንም ነግሯት ነበር፡፡ «... እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥ በእርጅናዋ ወራት ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን የተባለችውም ስድስተኛ ወሯን ይዛለች፤ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና» ብሏት ነበር፡፡ እመቤታችንም መልአኩ ስለ ኤልሳቤጥ የነገራትን ለማየት በዚያው ሰሞን ፈጥና ወደ ኤልሳቤጥ ሄደች፡፡ ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ለኤልሳቤጥ ሰላምታ ስታቀርብላት እጅግ የሚያስደንቅ ነገር ተከሰተ፤ ኤልሳቤጥ የእመቤታችንን ሰላምታ በሰማች ጊዜ በማኅፀኗ ያለው ጽንስ ዘለለ፡፡ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች ድምጽዋን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፡- «አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ የሰላምታሽ ድምፅ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ጽንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሏልና፡፡... »፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይህንን አስመልክቶ በድጓው ላይ ባስተማረው ትምህርት «አእሚሮ እምከርሠ እሙ ሰገደ ወልደ መካን ለወልደ ድንግል» «ገና በእናቱ ማኅፀን ሳለ አውቆ የመካኒቱ /የኤልሳቤጥ/ ልጅ ለድንግሊቱ /ለእመቤታችን/ ልጅ ሰገደ» ብሏል፡፡ #የቅዱስ_ዮሐንስ_ልደት_(ሉቃ.1÷67-80) ኤልሳቤጥ የመውለጃዋ ቀን ደረሰ፤ ወንድ ልጅም ወለደች፡፡ በስምንተኛውም ቀን ጎረቤቶቿና ዘመዶቿ ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፤ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ፈለጉ፤ እናቱ ግን ለዘካርያስ በቤተ መቅደስ «የሕፃኑ ስም ዮሐንስ ይባላል» ብሎ ያናገረ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት መንፈስ ቅዱስ ገልጦላት «ዮሐንስ መባል አለበት» አለች፡፡ ዘካርያስን ለልጁ ምን ስም ሊያወጣለት እንደሚፈልግ ሲጠይቁት መጻፊያ ሰሌዳ እንዲሰጡት ጠይቆ «ስሙ ዮሐንስ ነው» ብሎ ጻፈ ወዲያውም አንደበቱ ተፈታ፡፡ (ዮሐንስ ማለትም ፍሥሐ ወሐሴት፣ ርኅራኄ ማለት ነው፡፡)፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ይናገር ጀመር፡፡ በዚህም ምክንያት ጎረቤቶቹ ሁሉ በፍርሃት ተመሉ፡፡ ነገሩም በይሁዳ አውራጃ ሁሉ ተወራ፡፡ የሰሙትም ሁሉ «ይህ ሕፃን ምን ይሆን?» እያሉ በመገረም ጠየቁ፡፡ ካህኑ ዘካርያስም በመንፈስ ቅዱስ ተመልቶ ስለ ሕፃኑ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ትንቢት ተናገረ /ሉቃ.1÷67-79/ «አንተ ሕፃን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፤ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና፤ እንደዚሁም የኃጢአታቸው ሥርየት የሆነውን የመዳን ዕውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ» በማለት ቅዱስ ዮሐንስ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ጠራጊ እንደሚሆን ማለትም ከእርሱ ቀድሞ የሕዝቡ ልብ ጌታችንን እና ትምህርቱን እንዲቀበል የሚያዘጋጅ ትምህርት እንደሚያስተምር ተናገረ፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ መንገድ ጠራጊነት በቅዱስ ገብርኤልና በአባቱ በዘካርያስ ብቻ ሳይሆን ቀድሞም በሌሎች ነቢያት ትንቢት የተነገረለት ነበር፡- ነቢዩ ኢሳይያስ «የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንዲህ ይላል «የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ አዘጋጁ...» /ኢሳ.4ዐ ÷3/ በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ ✼ የቅዱስ ዮሐንስ ዕድገት ✼ የቅዱስ ዮሐንስ ስብከትና አገልግሎት ✼ ጌታችን እና ቅዱስ ዮሐንስ ✼ የቅዱስ ዮሐንስ እረፍት (ሰማዕትነት) ✼ የቅዱስ ዮሐንስ ቃልኪዳኑና አማልጅነቱን …. የሚመለከቱ ርዕሶችን በወርኃ መስከረም የተለጠፈውን የሰሌዳ መጽሔት ይመልከቱ፡፡ በሃገራችን የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ክብረ በዓል የሚከበርባቸው አብያተ ክርስቲያናት ጥቂቶቹ፤ ✤ ደብረ ቢዘን ዘንባባ ዮሐንስ (መካነ ቅዱሳን ወፈዋሴ ድውያን)፤ ከደብረ ብርሃን በኩክየለሽ መንገድ የ2ሰዓት መንገድ እንደተጓዙ የሚገኝ ጥንታዊ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ገዳም፡፡ ✤ ጎንደር ደብረ ጽጌ ዮሐንስ፤ ጎንደር ከተማ የሚገኝ፤ ✤ ሸንኮራ ዮሐንስ (ጠበሉ ፈዋሽና አስደናቂ ዕፁብ ዕፁብ በሚባል ሁኔታ የሚወርድ)፤ ምንጃር /ከሞጆ ወደ ሳማ ሰንበት የሚወስደውን መንገድ ትተው በመገንጠያው ገባ ብሎ የሚያገኙት) ✤ ወደ ሸንኮራ መሄጃ መንገድ ላይ (ከሞጆ አለፍ ብሎ) የሚገኝ የዮሐንስ መጥምቅ ቤ.ክ. ✤ አ.አ ቦሌ ደብረ ሳሌም ዮሐንስ መጥምቅ፤ (ኋላ ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኀኔዓለም ወዮሐንስ መጥምቅ ወአረጋዊ በሚል መጠሪያ እየተጠራ የሚገኝ)፤ ✤ ደብረ አናጕግ ቅዱስ ሚካኤል ወዮሐንስ መጥምቅ (አኵሱም አጠገብ) ✤ መርሐቤቴ ዮሐንስ መጥምቅ ✤ አዲስጌ (እንሳሮ/ሰላሌ/) ዮሐንስ መጥምቅ ✤ አ.አ ገዳመ ኢየሱስ (በድርብነት ይገኛል) ✤ አ.አ ሸጎሌ ኪዳነምሕረት (በድርብነት ይገኛል)

✤ #እረፍታቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ምድራዊ የአገልግሎት ዘመኑ ሊፈጸም ሲቃረብም እንዲህ ኾነ፤ በዘመኑ የክርስቲያኖች ጠላት የነበረው የሮም ንጉሥ ወደ አካይያ ዘምቶ ድል አድርጎ በደስታ ወደ ሮሜ ሲመለስ መኳንንቱን ለማስደሰት፤ ጣዖታቱንም ለማክበር ሲል በቅዱስ ጴጥሮስና በሌሎችም ክርስቲያኖች ላይ የሞት ፍርድ ዐወጀ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም በሮም ሲያስተምር ቆይቶ የሮም መኳንንት እንዳይገድሉት ትጥቁን ለውጦ ከሮም ሲወጣ ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ተገለጸለት፡፡ በዚህ ጊዜ ‹‹አቤቱ ጌታ ሆይ ወዴት ትሔዳለህ?›› ሲል ቢጠይቀው ጌታችንም ‹‹ልሰቀል ወደ ሮም እሔዳለሁ›› አለው። ‹‹ዳግመኛ ትሰቀላለህን?›› ባለው ጊዜም ‹‹አንተ ስትፈራ ጊዜ ነው እንጂ›› ሲል መለሰለት፡፡ ያን ጊዜም ‹‹ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን ታጥቀህ ወደ ወደድኸው ትሔድ ነበር። ስትሸመግል ግን እጅህን ታነሣና ሌላ ሰው ያስታጥቅሃል፤ ወደማትወደውም ይወስድሃል፤›› (ዮሐ. ፳፩፥፲፰) በማለት ጌታችን የነገረው ቃል አሟሟቱን የሚያመለክት መኾኑን አስታውሶ ወደ ሮም ተመልሶ ስብከቱን ቀጠለ፡፡ በሮማውያን ሕግ ቅጣት የተፈረደበት ወንጀለኛ የሮም አገር ተወላጅ ከኾነ የወንጀሉ ክብደትና ቅለት እየታየ ግርፋት ወይም ሞት ይፈረድበታል እንጂ በአንድ ወንጀል ሁለት ቅጣት አይቀጣም ነበር፡፡ ወንጀለኛው የውጪ አገር ዜጋ (ከሮም ውጪ) ከኾነ ግን ለምሳሌ ቅጣቱ ግርፋት ከኾነ ከተገረፈ በኋላ እስራት ይጨመርበታል፤ ቅጣቱ ሞት ከኾነም ከገረፉት በኋላ በመስቀል ወይም በሌላ መሣርያ ይገድሉት ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ዜግነቱ ሮማዊ አልነበረምና በግርፋትም፣ በእስራትም በሞትም እንዲቀጣ ተፈረደበት፡፡ እንደ ሥርዓታቸውም ቅዱስ ጴጥሮስን ከገረፉት በኋላ ሊሰቅሉት ሲሉ ወታደሮቹን ‹‹እንደ ክብር ንጉሥ እንደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አቁማችሁ ሳይኾን፣ ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም እንዳላቸው አድርገው ሐምሌ ፭ ቀን ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ በመስቀል ላይ ሳለም ተከታዮቹን በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ ካዘዛቸው በኋላ ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጠ፡፡ ሥጋውንም መርቄሎስ የሚባለው ደቀ መዝሙሩ ሽቱ ቀብቶ፣ በነጭ ሐር ገንዞ ዛሬ ቫቲካን በምትባለዋ ስፍራ በክብር ቀብሮታል፡፡ ✼ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ ከእዚያም እግዚአብሔር በሞቱ እንደሚያከብረው ነግሮት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ በጨካኙ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት ቁልቁል (እንደ አምላኬ አልሰቀልም ብሎ) በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡           ✼ #ሐዋርያው_ቅዱስ ጳውሎስ ለ 2 ዓመት ከ6 ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ከቆየ በኋላ በ74 ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት አንገቱን በሠይፍ ተሠይፎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት አረፈ፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ረድኤት በረከታቸው ይክፈለን፤ አሜን፡፡ #አቢያተ_ክርስቲያናቱ #ብርሃናተ_ዓለም_ጴጥሮስ-ወጳውሎስ፤ ከፒያሳ ወደ አስኮ በሚወስደው መስመር መንገድ ላይ የሚገኝ፡፡ #ሰዋስወ_ብርሃን_ቅዱስ-ጳውሎስ_ገዳም፤ ከ3ቱ መንፈሳውያኝ ኮሌጆች አንዱና ዋነኛው የሚገኝበት፡፡ ከመርካቶ አውቶቡስ ተራ 18ት ማዞሪያ ብላችሁ ስትሄዱ የሚገኝ፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

እንኳን ለሐዋርያት (የሰኔ) ጾም ፍቺ፤ እንዲሁም ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ፡፡ ✤✤ #ብርሃናተ_ዓለም_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ_ወሥርዐተ_ማኅሌት_ዘሐምሌ_፭፡፡ ✼ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ፤ በገሊላ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው በቤተሳይዳ ተወለደ፡፡ የአባቱ ስም ዮና የእናቱ ስም ሃውኒን ይባላል፡፡ ከ 5 ዓመቱ ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ነው የመጀመሪያው ስሙ ስምዖን ሲሆን ይህንንም እናቱ በነገዷ ስም እንዳወጣችለት ይነገራል፡፡ ✼ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ፤ ነገዱ ከዕብራውያን ከብንያም ነገድ ነው አባቱ ዮስአል ሲሆን የተወለደውም በጠርሴስ ከተማ ነው፡፡ ጠርሴስ በንግድ የታወቀች የኬልቅያ ዋና ከተማ ናት፡፡ ሮማውያን በሥራቸው ለሚተዳደሩት ሕዝቦች ሮማዊ ዜግነት ይሰጡ ስለነበር የቅዱስ ጳውሎስ አባት በዜግነት ሮማዊ ነበር፡፡ ይህም ለቅዱስ ጳውሎስ ተላልፎለታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ  በ15 ዓመት ዕድሜው ወደ ትውልድ ሐገሩ በመመለስ በኢየሩሳሌም ከነበረው የታወቀ የገማልያል ትምህርት ቤት ገባ፡፡ በዚያም የአይሁድን ሕግና ሥርዐት እየተማረ እስከ 3ዐ ዓመቱ ቆየ፡፡  በ3ዐ ዓመቱ የአይሁድን ሸንጐ አባል ሆኖ ተቈጠረ፡፡ ✤ #ለአገልግሎት_አጠራራቸው ✤✼ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በጐልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ ማሥገር ጀመረ፡፡ ለደቀመዛሙርትነት ሲመረጥ እድሜው 55 ዓመት ሲሆን ወደጌታችን ያመጣውም ወንድሙ እንድርያስ ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረውን መረቡን ታንኳውን እንዲህም አባቱን ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው፡፡ በቂሳርያ ከተማ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቀ ጊዜ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ ለአይሁድ ሊቃውንት የተሰወረ ምሥጢረ ተዋሕዶ ገልጦ በመመስከሩ ጌታችን አንተ ጴጥሮስ ነህ ብሎታል ይህን በጽርዕ ቋንቋ «ዐለት» ማለት ነው በአረማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ይወድ ነበር፡፡ ፍቅሩ ግን ቅንዓት የተቀላቀለ በመሆኑ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የሞቱን ነገር ቀድሞ ሲነግራቸው አይሁንብህ በማለት ተከራክሯል፡፡ ማቴ 16፥23 በኋላም ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም ብሎ በራሱ ቅንዓት ተማምኖ ተናግሮ ነበር፡፡ ጌታችን ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው እንኳን ከአንተ ጋር መሞት እንኳ የሚያስፈልገኝ ቢሆን ከቶ አልክድህም በማለት የተናገረ ሐዋርያ ነው፡፡ (ማቴ 26፥34) ነገር ግን 3 ጊዜ ጌታችንን አላውቀውም ብሎ ካደ፤ ዶሮ በጮኸና አምላኩን መበደሉን እንዳወቀ ከግቢው ወጥቶ አለቀሰ ንስሐ ገባ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በዕድሜው ታላቅነት በሐዋርያት ዘንድ እንደ አባት ይታይ ስለነበር ጌታ በተለየው ጊዜ ሐዋርያቱን ሊመግብ ወደሚያውቀው ሙያ ዓሣ ወደማስገሩ ተሠማራ ጌታም አስቀድሞ የመረጠው እርሱ ነውና ቢከዳው እንኳን በንስሐ በመመለሱ ንስሐውን መቀበሉን ዛሬም እንደሚወደው ይገልጽለትም ዘንድ በጥብርያዶስ ባሕር ተገለጠለት፡፡ ሦስት ጊዜ ክዶት ነበርና ቀኖና ሰጠው፡፡ አሁን ቅዱስ ጴጥሮስ በራስ መተማመኑ እንዳላዋጣው አውቆ ትወደኛለህ ተብሎ ሲጠየቅ አንተ ታውቃለህ ነበረ መልሱ የራሱ እውቀት የት እንዳደረሰው ያውቃልና ጌታችንም ኀዳጌ በቀል /በቀልን የሚተው/ ነውና ዛሬም እንደሚወደው በንሰሐ ተመልሷልና ዛሬም ለእርሱ የሰጠውን ክብር እንደማያጐልበት ሲነግረው ግልገሎቼን አሠማራ ጠቦቶቼን ጠብቅ በጐቼን አሠማራ በማለት አደራውን አስረከበው፡፡ ዮሐ 21፥15-17 ✼ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ስለነበረ በአይሁድ ሸንጐ አባልነት ለ2 ዓመታት በሠራበት ወቅት እምነቱ ቀናተኛ ፈሪሳዊ በመኾኑ ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣሚ ይቃወም ነበር፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ሲያርፍም የወጋሪዎችን ልብስ ይጠብቅ የነበረው እርሱ ነው፡፡  በ32 ዓመት ዕድሜው ከኢየሩሳሌም 223 ኪ.ሜ ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀርቦ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የሚያስችለውን የፈቃድ ደብዳቤ ጠይቆ ካገኘ በኋላ ጭፍሮችን አስከትሎ ወደ ደማስቆ አመራ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ከተማዋ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው ነበር ከሰማይ የወረደው ብርሃን አካባቢውን ያለበሰውና ሳዖል፥ ሳዖል ስለምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ የሰማው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስም ጌታ ሆይ ማን ነህ? ብሎ ጠየቀ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል ሲል መድኀኒታችን ተናገረው፡፡ ያንን በወደቀበት ሆኖ እየተንቀጠቀጠ ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ ሲል ጠየቀው ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ወደ ደማስቆ እንዲገባ ተነገረው፡፡ የሐዋ 9፥1 የሐዋርያው ዓይኖች ለማየት አልቻሉም ነበር፡፡ እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ ለ3 ቀናት ያህልም እህል ሳይቀምስ ቆየ በዚያች ዕለት እግዚአብሔር አምላክ በደማስቆ ለሚገኘው እና ሐናንያ ለተባለው አባት በራዕይ ተገለጠለት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ያለበትን አድራሻ ነገረውና  እንዲያጠምቀው አዘዘው፡፡ ሐናንያ አስቀድሞ የቅዱስ ጳውሎስን ማንነት ያውቃል፡፡ አብዛኞቹ በደማስቆ የሚገኙት ክርስቲያኖች ከኢየሩሳሌም በስደት ጊዜ የመጡ ናቸው፡፡ ያን ስደት ያስነሳው ደግሞ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ የደረሰው መከራ ነው፡፡ በዚህ በቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ደግሞ ዋናው ተዋናይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነበርና ነው፡፡ ሐናንያ ቅዱስ ጳውሎስን ካጠመቀውና ካስተማረውም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዓረብ ሐገር ሄደ፥ ለሦስት ዓመታት በዓረቢያ በረሃ ከቆየም በኋላ ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ። በዚያም በነበሩ አይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ፡፡ ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱና ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰብክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት፡፡ በዚያም የተነሣ የደማስቆ ክርስቲያኖች በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ አይሁድ ጳውሎስን እንደሚያውቁት እና እንደለመዱት ሆኖ ስላላገኙት ሊገድሉት ተነሱ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቲያኖች የቅዱስ ጳውሎስን መመለስ ሊያምኑ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻ ግን በርናባስ ወደ ሐዋርያት ዘንድ ወስዶ የጳውሎስን መመለስ በመተረክ እንዲያምኑት አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም በድፍረት በማስተማሩ አይሁድ ስለተቃወሙት ከተማዋን ትቶ በቂሳርያ በኩል ወደ ትውልድ ሐገሩ ጠርሴስ ተመለሰ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጠርሴስ ከተማ ለ9 ዓመታት ቆይቷል፡፡ ከኢየሩሳሌም ውጭ የአሕዛብ ከተማ በነበረችው በአንጾኪያ የክርስትና ሃይማኖት ተስፋፋ፡፡ ከዚህም በኋላ ሐዋርያው ሦስት ታላላቅ ሐዋርያዊ ጉዞዎችን አድርጓል፡፡ በመጀመሪያው ጉዞው ወደ 2,ዐዐዐ ኪ.ሜ የሚደርስ መንገድ በእግር ተጉዟል፤ ይህም የተከናወነው በ46 ዓ.ም. ነው፡፡ በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከ18 በላይ ከተሞችን ሸፍኗል፤ ጉዞውም በ5ዐ ዓ.ም. የተደረገ ነው፡፡  በሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከ2ዐ በላይ ከተሞችን ሸፍኗል፤ ጉዞውም በ54 ዓ.ም. የተደረገ ነው፡፡ ብዙም ጊዜ በቁም እሥር በብዙም መከራ ሥቃይ እንግልት ያሳለፈ ታላቅ ሐዋርያ ነው፡፡