ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Открыть в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 784 подписчиков, занимая 5 335 место в категории Религия и духовность и 2 221 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 784 подписчиков.

Согласно последним данным от 11 октября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 71, а за последние 24 часа — 0, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 8.70%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 5.07% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 1 360 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 792 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 12.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 12 октября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

15 784
Подписчики
Нет данных24 часа
+1017 дней
+7130 дней
Архив постов
ደብራችንን ለረጅም ዓመታት በዋና አስተዳዳሪነት ያገለግሉት መልአክ ሰላም ዘለዓለም እሰይ ነሐሴ 5 ቀን ፣ 2014 ዓ.ም ፤ በ81 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አረፈዋል ። ሥርዓተ ቀብራቸውም ብፁዓን
ደብራችንን ለረጅም ዓመታት በዋና አስተዳዳሪነት ያገለግሉት መልአክ ሰላም ዘለዓለም እሰይ ነሐሴ 5 ቀን ፣ 2014 ዓ.ም ፤ በ81 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አረፈዋል ። ሥርዓተ ቀብራቸውም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ነገ ነሐሴ 6 ፤ በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከሥርዓት ቅዳሴ በኃላ ይፈጸማል።

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: ꔰ #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot .YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w www.finotehiwotsundayschool.com ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት . Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)

እንኳን ደስ አላቹሁ ፡፡ ጾመ ፍልሰታ #ጾም_በሐዲስ_ኪዳን፡- የሐዲስ ኪዳን ጾም ከብሉይ ኪዳን ጾም የተለየ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበረው ጾም ሥጋዊ ችግርን የሚመለከት ሲኾን፤ በሐዲስ ኪዳን ግን የምንጾመው ለጽድቅ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የመጀመሪያ ሥራ ያደረገው ጾምን ነው፤ እንደዚሁም ያስተማራቸው ደቀ መዛሙርት ከሥራቸው በፊት ጾምን እንደ ጌታቸው አስቀደሙ፡፡ የሚከተሉት ጥቅሶች በሐዲስ ኪዳን ጾም እንደታዘዘ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ማር.፱፣፳፱፣ ማር.፪፣፳፣ ማቴ.፮፣፮፣ ሉቃ.፮፣፳፩፣ የሐ.ሥራ.፲፫፣፫፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያናችን እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አብነት በማድረግ ጾምን በአዋጅ እንድንጾም በቀኖናዋ (በሥርዐቷ) ደንግጋለች፡፡ በቤተክርስቲያናችን የአዋጅ ጾም የሚባሉት ሰባት ናቸው፡፡ እነርሱም፡- 1. ✣ ዐቢይ ጾም (ጾመ ኩዳዴ) 5. ✣ ጾመ ነነዌ 2. ✣ ጾመ ድኅነት (የረቡዕና ዐርብ) 6. ✣ጾመ ጋድ 3. ✣ ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) 7. ✣ #ጾመ #ፍልሰታ 4. ✣ ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) #ጾመ_ፍልሰታ ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ #ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገን፤ ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የምንጾመው ታላቅ ጾም ነው። እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለኾነ፤ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት፤ ዕዝራ በመሰንቆ፥ ዳዊት በበገና እያጫወቷት፤ በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን #በ48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች። ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት (ከየሀገረ ስብከታቸው) ወደ መኖሪያ ቤቷ (የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቤት) ተሰባስበው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች ሥጋዋን ገንዘውና ሸፍነው ወስደው ለመቅበር ወደ #ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤ ይህንንም ማድረግ የፈለጉበት ምክንያት፤ የሐዋርያት ትምህርት (የጌታችን ከሞት መነሳትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት)ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። ‹‹የፈሩት ይነግሣል፥ የጠሉት ይወርሳል›› እንዲሉ አበው፤ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት አይቀሬ ሁኗል። አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፋኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ የእመቤታችንን ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር፤ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ (ቆርጦ) ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነት (የአምላክ እናት መሆኗ)ና ክብርን ለመመስከር በቅቷል። የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ #በዕፀ ሕይወት ሥር መቀመጡ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ እመቤታችን ሥጋ ነገራቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ለዮሐንስ ተገልጾ ለኛ ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለመኑ ከጥር 21 አንስተው ለስድስት ወራት ከዐሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህም በኋላ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ፥ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን አምጥቶ ስለሰጣቸው፤ ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች። ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ.፪፥፲/። እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ሐዋርያው #ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ (ሕንድ) ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ ከደመናው ላይ ሊወድቅም ፈለገ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን/የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው። ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት አስረዱት። እርሱ ግን ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን ለማሳመንና ለማሳየት ወደ መቃብሯ ወሰዱት፤ ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት የነበረውን ጨርቅ/ አሳያቸው፤ የራሱን ድርሻም አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው፤ #ዛሬም_ካህናት ከእጅ መስቀላቸው ጋር የሚይዙት እራፊ ጨርቅ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው። ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለ፪ኛ ጊዜ ሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል። በአጠቃላይ #የእመቤታችን ለሐዋርያት በተለያዩ ጊዜያት መታየት፣ የሥጋዋና የነፍሷ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፍልሰት ሲባል ከዚህ የተነሣ #የነሐሴ ጾም በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዐት መሠረት ሐዋርያት ያገኙትን በረከት ለማግኘት ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን።