cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Nur'amba mesjid jemaa፦ኑር አምባ መስጂድ ጀመአ

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
133
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ጂብሪል ዐ ሰ አንድ ቀን ያለወትሮው ረሱል ሰዐወ ዘንድ ፊቱ ጠቁሮ መጣ። ረሱል ሰ ዐ ወ በዚህ ሁኔታ ሲያዩት ግዜ፦"አንት ጅብሪል ምነው ፊትህ እኮ ተቀየሯል?" አሉት። ጅብሪልም፦"አንተ ሙሀመድ አሁን የመጣሁት ሰዐት የጀሀነም አቀጣጣዮችን አላህ እንዲያቀጣጥሏት ባዘዛቸው ሰዐት ነው። ጀሀነም እውነት መሆኗን ላወቀ፣እሳትም እውነት መሆኗን ላወቀ፣የቀብር ቅጣት እውነት መሆኑን ላወቀ፣የአላህ ቅጣት ትልቅ መሆኑን ላመነ ሰው ከሷ መትረፉን ሳያረጋግጥ መረጋጋት የለባትም" ብሎ መለሰላቸው። ረሱል ሰ ዐ ወ፦"አንተ ጅብሪል እስቲ ስለጀሀነም ንገረኝ" አሉት። ጅብሪልም ዐ ሰ፦"አዎ አላህ ጀሀነምን 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ቀይ እስክትሆን ድረስ ከዚያም 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ነጭ እስክትሆን ድረስ ከዚያም 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ጥቁር እስክትሆን ድረስ.....አሁን /ጀሀነም ጥቁር ጨለማማ ናት።ነበልባሏ እና ፍሟ አይጠፋም ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ. የመርፌ ቀዳዳ ያህል ጀሀነም ብትከፈት ዱንያ ላይ ያለ ነገር ሁሉ ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር። ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ.ከጀሀነም ሰዎች ልብስ አንዷ በሰማይና በምድር መሀከል ብትንጠለጠል ከግማቱ የተነሳ ምድር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ ይሞት ነበር። ያ በዕውነት ነቢይ አድርጎ በላከህ አላህ እምላለሁ...አላህ ቁርአን ላይ የጠቀሰው የጀሀነም ሰንሰለት አንዷ እንኳን በተራራ ላይ ብትቀመጥ ተራራው እስከ ሰባተኛው መሬት ድረስ ይቀልጣል። ያ በዕውነት በላከህ አላህ እምላለሁ. በምዕራብ አንድ ሰውዬ በጀሀነም ቢቀጣ ኖሮ በምስራቅ ያለው ሰው ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር። ሙቀቷ ጠንካራ ነው፣ጥልቀቷ እሩቅ/ስምጥ ነው፣ጌጧ ብረት ነው፣መጠጧም የፈላ ውሀ እና ምግል ሲሆን፣ልብሷም ከእሳት የተለካ ነው። 7 በሮች አሏት። ለያንዳንዱ በር የተለያዩ በሮችም አሏቸው ለሴቶችም ለወንዶችም" ብሎ መለሰላቸው። ረሱልም ሰዐወ፦"እኛ እንደምንጠቀመው አይነት በር ነው?" ብለው ሲጠይቁት ጅብሪልም ዐ ሰ፦" አይ አይደለም ከላይ ወደ ታች የተደረደረ በር ነው።ከአንደኛው በር ወደ ሌላኛው በር ያለው ርቀት 70 አመት ያስኬዳል። እያንዳንዱ በር ከሌላኛው በር ግለቱ በ70 እጥፍ ይበልጣል። የአላህ ጠላቶች ወደጀሀነም ይነዳሉ። ልክ በሯ ላይ እንደደረሱ ዘባኒያ የተባሉ የጀሀነም ወታደሮች በሰንሰለት ይቀበሏቸዋል። ሰንሰለቱን በአፋቸው አስገብተው በመቀመጫዎቻቸው ያስወጡታል። ግራ እጁ ከአንገቱ ጋር ይጠፈራል ቀኝ እጁም ከልቡ ጋር ተጠፍሮ ይታሰራል። እያንዳንዱ ሰው ከሸይጧን ቁራኛው ጋር በሰንሰለት ይጠፈራል። ከዚያም በፊቶቻቸው እየተጎተቱ መላዕክት ደግሞ ከብረት በሆነ መዶሻ ይመቷቸዋል። ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት ሲሞክሩ ወደዛው ይመልሷቸዋል"ብሎ መለሰላቸው። ነቢያችንም ሰ ዐ ወ፦"በነዚህ በሮች የሚገቡት እነማን ናቸው?" ብለው ጠየቁት። ጅብሪልም ዐ ሰ፦ "በታችኛው በር የሚገቡት 1፦ሙናፊቆች 2፦በዒሳ ዐሰ ማዕድ የካዱት 3፦"የፊርዐውን ቤተሰቦች...ሲሆኑ የበሩ ስም ሀዊያ ይባለል። ሁለተኛው በር ስሙ ጀሂም ሲሆን በሱ የሚገቡት ሙሽሪኮች ናቸው። ሶስተኛው በር ሳብያኖች ነው የሚገቡበት ስሙም ሰቀር ይባላል። በአራተኛው በር ኢብሊስ እና ተከታዮቹ መጁሶችም ይገቡበታል ስሙም ለዟ ይባላል። አምስተኛው በር የሁዶች የሚገቡበት ሲሆን ስሙም ሁጠማ ይባላል። ስድስተኛው በር ስሙ ዐዚዝ ሲሆን የሚገቡበት ክርስቲያኖች ናቸው።"ብሎ ከዘረዘረላቸው በኋላ ሰባተኛውን ለመጥቀስ ፍርሀት ያዘው። ነቢያችንም ሰ ዐ ወ፦"ሰባተኛውን በር ለምን አትነግረኝም?" ብለው ሲጠይቁት ጂብሪልም ዐ ሰ፦"በሱ በር የሚገቡት ካንተ ዑመት የሆኑ ትላልቅ ወንጀሎችን ሰርተው ሳይቶብቱ/ሳይፀፀቱ የሞቱ ናቸው" ብሎ ሲመልስላቸው ረሱል ሰ ዐ ወ እራሳቸውን ስተው ወደቁ። ከዚያም ጅብሪልም የረሱልን ሰ ዐ ወ ጭንቅላት ታፋው ላይ አሳረፈ።ልክ ሲነቁ ቀና አሉና፦"አንተ ጅብሪል ችግሬ በዛ ሀዘኔም በረታብኝ ከኔ ኡመት ጀሀነም ሚገባ አለ እንዴ?" ብለው ሲጠይቁት ጅብሪልም ዐ ሰ፦" አዎን ካንተ ኡመት የትላልቅ ወንጀል ባለቤቶች ይገባሉ"ብሎ መለሰላቸው፣ የዐይናችን ማረፊያ ከእናት ከአባት በላይ ለኛ አዛኝ የሆኑትም ነቢይ ይሄን ሲሰሙ ተንሰቅስቀው ማልቀስ ጀመሩ።ጅብሪልም አብሯቸው አለቀሰ። /ፊዳከ አቢ ውኡሚ ያ ረሱለላህ/ ረሱል ሰ.ዐ.ወ ይህኔ፦"ያጅብሪል አንተም ታለቅሳለክ?" አሉት ። ጅብሪልም፦"እንዴት አላለቅስ የኔንስ መጨረሻ በምን አውቃለሁ? እብሊስ እኮ ከመላእክት በላይ አላህን ይገዛ ነበር አላቸው ። __________________________________ አላህ ይሄን መልዕክት የፃፈውንም ያነበበውንም አንብቦ ለሌላው ያስተላለፈውንም ከዚህ አስፈሪ ቅጣት ይጠብቀው። አሚን...
Показать все...
عَنْ سَلْمَانَ بنِ عَامر رضي الله عنه قال قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: [ إِذَا أَفْطَرَ أَحَدُكُمْ فَلْيُفْطِرْ عَلَى تَمْرٍ فَإِنْ لَمْ يَجِدْ فَلْيُفْطِرْ عَلَى مَاءٍ فَإِنَّهُ طَهُورٌ ] 📚رواه الترمذي 🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸 ከሰልማን ቢን ዓሚር (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው) እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:– [ አንዳችሁ ማፍጠር ሲያስብ በቴምር ያፍጥር፤ ካላገኘ በውሃ ያፍጠር፤ እሱ ጦሁር(ንጹህ፣ የሚያጸዳ) ነውና።] 📚ቲርሚዚ ዘግበውታል። t.me/nurambamesjid
Показать все...
عن عبد الله بن عمر رضي الله عنهما قال: كان رسول الله صلى الله عليه وسلم إذا أفطر قال: [ ذَهَبَ الظَّمَأُ، وَابْتَلَّتِ الْعُرُوقُ، وَثَبَتَ الْأَجْرُ إِنْ شَاءَ الله] 📚 رواه أبو داود 🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸 ከዐብደላህ ቢን ዑመር (አላህ ከሁለታቸውም ስራቸውን ይውደድላቸው) እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲያፈጥሩ(ፆም ሲፈቱ) እንዲህ ይሉ ነበር:- "ዘሀበዝ-ዞመኡ ወብተል-ለቲል ዑሩቁ ወሠበተል-አጅሩ ኢንሻ አላህ" ትርጉሙ:- [ ጥሙ ተወገደ የደም ሰሮችም ረጠቡ በአላህ ፍቃድ ምንዳውም ፀደቀ።] 📚አቡ-ዳውድ ዘግበውታል። t.me/nurambamesjid
Показать все...
✒️ረመዷን አንዷ ቀን ለሰራባት ትልቅ ሀብት ናት። 🖋قال الإمام ابنُ الجَوزِيّ - رحِمه اللّه - : 《 تاللّهِ لو قِيل لأهلِ القُبور تَمنَّوا ،لتَمنّوا يومًا من رَمضان 》. 📚 |[ التّبصرة (٧٨/٢) ]|. ✒️ኢማሙ ኢብን አልጀውዚ ((ረሂመሁላህ)) እንዲህ ይላሉ ✒️በአላህ እምላለሁ መቃብር ውስጥ ላሉ ሰዎች ተመኙ ቢባሉ ኑሮ ከረመዷን አንድ ቀን በተመኙ ነበር ። ምንጭ ✒️✒️ 📚 ((التّبصرة ~٧٨/٢)) t.me/nurambamesjid
Показать все...
عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: [ إِذَا دَخَلَ رَمَضَانُ فُتِّحَتْ أَبْوَابُ الجَنَّةِ ، وَغُلِّقَتْ أَبْوَابُ جَهَنَّمَ ، وَسُلْسِلَتِ الشَّيَاطِينُ ] 📚 متّفقٌ عليه 🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸 ከአቢ-ሁረይረህ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው) እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:– [ረመዷን በገባ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፋፈታሉ፤ የጀሀነም በሮች ይዘጋጋሉ፤ ሸይጧኖች(ዋና ዋናዎቹ) በሰንሰለት ይታሰራሉ።] 📚ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል። t.me/nurambamesjid
Показать все...
ከአቢ-ሁረይረህ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው) እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:– [ የሀሰት ንግግርን፣ በሱ መስራትን እና የቂል ተግባርን ያልተወ ሰው ምግቡንና መጠጡን ከመተዉ አላህ ጉዳይ የለውም። ] 📚ቡኻሪ ዘግበውታል። t.me/nurambamesjid
Показать все...
ኮሮናን በተመለከተ‼ ============== ✍ መጪው ወር ረመዷን እንደመሆኑ መጠን በተለይም ከተራዊሕ ሶላት ጋር ተያይዞ ህዝብ ከህዝብ የመደባለቅ ነገር ስለሚኖር፤ ትናንት አባ ጅፋር መስጅድ በነበረው ሙሐደራው ላይ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ በዚህ ጉዳይ ላይ የተናገራቸውን ③ ጥቆማዎች ላጋራችሁ ወደድኩ። ♠ ①) የጠዋትና የማታ ዚክሮችን ማድረግ – ለምሳሌ፦ √ (أعوذ بكلمات الله التامات من شر ما خلق) √ بسم الله الذي لا يضر مع اسمه شيء في الأرض ولا في السماء وهو السميع العليم! • በርሱ ስም ከፈጠረው ነገር ሁሉ ተንኮል ከተጠበቅክና የርሱን ጥበቃ ከጠይቅ በምድርም ይሁን በሰማይ አንዳችም የሚጎዳህ ነገር አለመኖሩን ካመንክ፤ ኮሮና እንደት ያገኝሀል! * ②) ለኮሮና መከላከያ ዘዴ ናቸው ተብለው የሚመከሩ ነገሮችን በአግባቡ መተግበር – ለምሳሌ፦ ማስክ መልበስ፣ ሳኒታይዘር መጠቀምና መታጠብ፣ ከተቻለ የራስን መስገጃ፣ መያዝ፣ * ③) የተራዊሕ ሶላት ሱንና ስለሆነ ቤት መስገድ ይቻላል። አሰጋጆች ደግሞ በተለምዶ በአንድ ጁዝእ ያሰግዱ ከነበር ወደ ግማሽ ጁዝእ ቢቀንሱ፤ በተቻለ መጠን መቀነስ ይቻል ይሆናል። ለብዙ ደቂቃዎች አብሮ መቆዬት እና ለተወሰኑ ደቂቃዎች አብሮ መቆዬት ያለው ተፅዕኖ ስለሚለያይ! * በተጨማሪም ሶፍን አራርቆ መስገድን በተመለከተ በድጋሜ ተጠይቆ፤ እንደ ጥቅል ጉዳዩ የኢጅቲሀድ ጉዳይ ስለሆነ ሶፍ ተራርቆ በሚሰገድበት መስጅድ ውስጥ አንድ ሰው አቋሙ ይህን አይቻልም የሚል ቢሆን እንኳ ተራርቆ መስገድ አለበት። Vice Versa! ከተቻለ ደግሞ ሁለት ሁለት ሰዎች አንድ ላይ እየሆኑ፤ በሌሎች ሁለት ሰዎች መካከል የሆነ ርቀት ተበጅቶ እንደዛ ቢደረግ መልካም ነው። ምክንያቱም ሶፍን ማስተካከል ግዴታ ነው ወይንስ ሱንና የሚለው የኺላፍ ርዕስ ስለሆነ ነው። ዋጂብ ነው በሚሉት በነ አል-ቡኻሪይ አይነት ሊቆች፤ ተራርቆ መስገድ አይቻልም። ሱንና ነው በሚሉት መሠረት ደግሞ ይህ ለችግር (ለዾሩራ) ስለሆነ ሱንናውን በመተው ተራርቆ መስገድ ይቻላል ይላሉ። በርካታ የዘመናችን ዐሊሞች መፍቀዳቸውንም ጠቁሟል። ለማንኛውም እንዳለው ከተቻለ ሁለት ሁለት ሰዎችን አንድ ላይ በማድረግ ቢሰገድ፤ ለኮሮና ተጋላጭ የመሆን እድልንም በጣም ይቀንሳል፣ ምናልባትም ቢቀር ሱንናው እንጅ ዋጂብ ነው ከሚሉት ምሁራን አንፃር ያለውንም ኺላፍ መጠበቅ ይቻላል። t.me/nurambamesjid
Показать все...
«ረመዷን ከሪም» አትበሉ! «ረመዷን ሙባረክ» በሉ። ምክንያቱም (ከሪም ማለት ሰጪ ወይም ለጋስ እንደማለት ስለሆነ) ረመዷን ደግሞ "ከሪም" ለመባል በራሱ ሰጪ አይደለም። አላህ ነው የሚሰጥበት ወር የመሆንን ልቅና የሰጠው! ስለዚህ ተገቢው "የተባረከ (ሙባረክ)" የሚለው እንጅ "ከሪም (ለጋሽ)" የሚለው አይደለም። ፈታዋው የኢብኑ ዑሠይሚን ነው።
Показать все...
«ረመዷን ሙባረክ!»‼ ===================== ✍ በየትኛውም የዓለማችን ክፍል የምትኖሩ ሙስሊም ወንድምቼና እህቶቼ፣ አባቶቼና እናቶቼ እንዲሁም ጓደኞቼና ኡስታዞቼ በሙሉ፤ السلام عليكم ورحمة الله وبركاته እንኳን ለተከበረው የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ። አላህ ከነ ሙሉ ቤተሰባችሁ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቃችሁ። ይህን የተከበረ ወር በትክክል ጹመው ምንዳቸውን ከሚያገኙት ባሮቹ አላህ ያድርገን። ♠ ሁላችሁንም ለአላህ ብዬ እወዳችኋለሁ‼ مبارك عليكم الشهر، أعاده الله علينا وعليكم أعواما عديدة بالخير. ========= ረመዷን 01, 1442 H.C
Показать все...
عن أبي هريرة رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال: [ لا يَشْكُرُ اللَّهَ مَنْ لا يَشْكُرُ النَّاسَ] 📚رواه أحمد 🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸 ከአቢ-ሁረይረህ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው) እንደተወራው ነቢዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- [ሰዎችን የማያመሰግን ሰው አሏህን አያመሰግንም።] 📚አሕመድ ዘግበውታል:: t.me/nurambamesjid
Показать все...

Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.