cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ሃኒታዬ የጥበብ ማዕድ

👉ግጥም እወዳለሁ

Больше
Рекламные посты
203
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступно
የሰፈሬ -አድባር😥 ለቀን ቀን ባይኖረውም -ቀን በቀን ባይቀና፣ ስምሽ ያረፈበት- አለው ልዩ ቃና፤ ብዬሽ እንደነበር -እንዴት እረሳሽው? ማርያም ሆይ! በቀንሽ -ጥቁር የለበሽው! በዛ ድንቁ ውልደት- የልደትሽ ቀን ላይ... ማን ማመን ይችላል -ከምድር ከሰማይ! (ጥቁር እንደ ለበሽ😭) እኔው ማቁን ልበበስ -እኔ ልጥቆርልሽ! ቢገባቸውኮ ለአለም መዳኑ -የሰርጉ ልብስ ነሽ። እኔን እመቤቴ- የቀናት አፍ መፍቻ! አንቺኑ በጥቁር- እ'ኮ በአንቺው ዛቻ¡ እንዴት ያለ ድፍረት -ምን ይሉት ጋኔል ነው... ሰላማዊት አንቺን ደጅሽን ደፋሪው። እግዚኦ....😭 #ይታረቀን
Показать все...
Фото недоступно
00:59
Видео недоступно
11.50 MB
00:38
Видео недоступно
7.23 MB
00:34
Видео недоступно
5.81 MB
ስለ አንቺ ደከመኝ! እማማዬ የኔ -የቃላት ስብጥር፣ በአንቺ እንዳልተነሳ -ሰው የጣለው ፍቅር፣ ዛሬ ማንሳት ደክሞሽ- አቅምሽ ቢሟጠጥ፤ መተው ምርጫሽ ሆነ- ሰዎች መለማመጥ። ይሁና!.. ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋዩን ሰባሪ በከፋሽ ደቂቃ ለሆነሽ ዘማሪ ለዛ ምስኪን ልጅሽ ጡትሽን ላልጠገበው መታገስን መርጠሽ ጥቁር አለበሽው። #😭😭😭
Показать все...
Фото недоступно
00:20
Видео недоступно
9.72 MB
ናፍቀሽኛል! ስለሄድሽ ሳይሆን - አጠገቤ ሆነሽ፣ እንደ ምትናፍቂኝ- ብነግርሽ ታምኛለሽ? እጆቼ እየነኩሽ -መኖርሽ ሲገርመኝ፣ አካሌ ከአካልሽ -ተጣብቆ እያየሁኝ፣ የለሽ በሚል ቃል ...፣ ባለ መኖር ስሜት፣ አንቺን ናፋቂ ነኝ፤። ትናፍቂኛለሽ!! እያየሁሽ እኔ - እያዩኝ አይኖችሽ! ልሂድ¡ ባልሽኝ ቁጥር - ታሳምሚኛለሽ! ልክ መለያየት -ህመም እንደሚሆን፣ ሰአታቱ ሲሄደ -ቀን ሲተካ ቀኑን፤ እኔ የሚሰማኝ -ደርሶ እስከሚሰማሽ! እየፈራሁ እንኳን - ትናፍቂኛለሽ:: መቼስ ይገባሻል- በአንቺ የመሄድ ዳር.. ብዙ- ብዙ -ብዙ - አብሮሽ የሚዳክር ጥቂቱ ቀናችን -አመታት የሚያስንቅ ዛሬን ብቻ ሳንሆን - ነገን የሚያስናፍቅ! ሁሉንም ትዝታ - መሄድሽ ይወስዳል.. ታዲያ ይሄንን- ልቤ እንዴት ይቀበላል? እትሂጂ...እባክሽ።
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.