cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ቅድሚያ ለ ተውሂድ

አላህን በማስደሰት ላይ ራስህን ጥመደው! ካልሆነ ሸይጧን አላህን እንድታስከፋ ያጠምድሀል! ✒العلم قبل القول والعمل 👇👇👇 For any comment . @Gestureles . . . . . . . .

Больше
Рекламные посты
371
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Repost from فهم سلف
➷አንዳንዴ ውብ ቃላቶችን አትመኑ። እውነቱን ከክስተቶች አንደበት ውሰዱ። ነጂብ መህፉዝ አንዳንዶቹ ሲያደንቁህ ከሰማይና ከጨረቃ ውበት ጋር ያመሳስሉሃል፣ ውዴታቸውን ሲገልፁልህ ደግሞ ላንተ መስዋዕት እስከመሆን ያዘልቁሃል። ያ ሁሉ የቃል ውዳሴና ውዴታ በፈታኝ ተግባር ውስጥ ግን ኦና ይሆናል። ~ ሁሌም ከጎንህ እንደሆኑ ቢነግሩህም ሲፈልጉህ እንጂ በቁም ነገር ስትፈልጋቸው አታገኛቸውም። ✅ አጂብ ወሏህ ሀቅ‼️ ➷ክስተቶች እውነትን ይገልጣሉ። በቃላት የተከሸኑ ውዴታዎችም በአንድ ወቅት በተግባር ይፈተናሉ። ~ ብዙዎቻችን ያለንበት ይህ ነው እውነታው ከቃላት የማያልፍ ውዴታ‼️ አላህ ይዘንልን....! ↷⇣🌹⇣↷ https://t.me/Rim_Yee_Umi
Показать все...
فهم سلف

በምንማራቸው ኪታቦች(መፅሀፎች)ስፋት ክብደትና ትልቀት ብቻ ትልቆች ወይም ከባዶች አንሆንም ።እኛ ትልቆች መሆን የምንችለው የተማርነውን ተግባራዊ ማድረግ ስንችል ነው የተማርነውን ዐቂዳ(እምነት)ኢባዳ(አምልኮ)እና አኽላቅ(ሥነምግባር)ተግባራዊ ማድረግ ስንችል በሁቱም ሀገር ስኬታማ እንሆናለን ስህተቴን አይቶ ለነገረኝ የአላህ እዝነት በሱ ላይ ይሁን 👇👇👇 @Kun_Ala_Besira

Repost from فهم سلف
➷አንዳንዴ ውብ ቃላቶችን አትመኑ። እውነቱን ከክስተቶች አንደበት ውሰዱ። ነጂብ መህፉዝ አንዳንዶቹ ሲያደንቁህ ከሰማይና ከጨረቃ ውበት ጋር ያመሳስሉሃል፣ ውዴታቸውን ሲገልፁልህ ደግሞ ላንተ መስዋዕት እስከመሆን ያዘልቁሃል። ያ ሁሉ የቃል ውዳሴና ውዴታ በፈታኝ ተግባር ውስጥ ግን ኦና ይሆናል። ~ ሁሌም ከጎንህ እንደሆኑ ቢነግሩህም ሲፈልጉህ እንጂ በቁም ነገር ስትፈልጋቸው አታገኛቸውም። ✅ አጂብ ወሏህ ሀቅ‼️ ➷ክስተቶች እውነትን ይገልጣሉ። በቃላት የተከሸኑ ውዴታዎችም በአንድ ወቅት በተግባር ይፈተናሉ። ~ ብዙዎቻችን ያለንበት ይህ ነው እውነታው ከቃላት የማያልፍ ውዴታ‼️ አላህ ይዘንልን....! ↷⇣🌹⇣↷ https://t.me/Rim_Yee_Umi
Показать все...
فهم سلف

በምንማራቸው ኪታቦች(መፅሀፎች)ስፋት ክብደትና ትልቀት ብቻ ትልቆች ወይም ከባዶች አንሆንም ።እኛ ትልቆች መሆን የምንችለው የተማርነውን ተግባራዊ ማድረግ ስንችል ነው የተማርነውን ዐቂዳ(እምነት)ኢባዳ(አምልኮ)እና አኽላቅ(ሥነምግባር)ተግባራዊ ማድረግ ስንችል በሁቱም ሀገር ስኬታማ እንሆናለን ስህተቴን አይቶ ለነገረኝ የአላህ እዝነት በሱ ላይ ይሁን 👇👇👇 @Kun_Ala_Besira

Repost from فهم سلف
قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله:* *《 من تعصّب لأهل بلدته، أو مذهبه، أو طريقته، أو قرابته، أو لأصدقائه دون غيرهم؛ كانت فيه شعبة من الجاهلية 》.* *📚 |[ مجموع الفتاوى (٤٢٢/٢٨) ]|*
Показать все...
    ለምን ተገለበጥሽ እህቴ? አንተስ ለምን ተገለበጥክ? አንቺ ቅኑን መንገድ አውቀሽ የተስተካከልሽ ከዛም መንገዱን ለቀሽ የጠመምሽ ሁኔታሽም የተቀየረ ክልክል በሆነ መንገድ ደስታን እየፈለግሽ ያለሽ እህቴ ሃቁን ካወቅሽ በኋላ ለምን ዱንያ ልብሽን ቀየረችው ?እህቴ ምን አግንቶሽ ነው ምንስ ነው ምክንያትሽ!? ለምንድን ነው ለሊቱም ቀኑም እኩል የሆነብሽ ለምንድን ነው ደስታ በጣፋጭ ነገርና በስሜት ውስጥ እየፈለግሽ ያለሽው? ለምን ለምን እህቴ እስኪ ራስሽን ጠይቂውና መልሽልኝ እስኪ ንገሪኝ ምንድን ነው ምክንያትሽ ለምን ይሆን በዚህ ርካሽ ዱንያ የተታለልሽው የዱንያን ፈተና መውጣት የከበደሽ ለምንድን ነው ??? ምን አልባት የጀነትን ዋጋ አላወቅሽው ይሆን እና የአኼራን አሳማሚ ቅጣት ? ምን አልባት ዋናው መጨረሻ ነው ትሉኝ ይሆናል ግን መርሳት የሌለብን ነገር መጨረሻችን እንዲያምር ጥሩ ሁኔታ ላይ ሁነን መፅናት ይኖርብናል።!! ውድ እህቴ እስከመቼ ነው አላህ ማመፁ አላህ እድል እየሰጠሽ ነው ለምን ይሄን ውድ የሆነ እድል አትጠቀሚበትም? ወላሂ ብዙ የቀብር ነዋሪዎች ያላገኙትን እድል ነውኮ ። ካንቺ በፊት የሞቱት ሰዎች ልክ አሁን አንቺ እንደምታስቢው አሁን አልሞትም ብለው እያሰቡ ነበር ሞት የቀደማቸው ታዲያ ለምን ካለፉት እህቶችሽ ትምህርት አትወስጂም? ለምን ለምን እሰኪ በሩን ዝጊና ራስሽ ጋር ተሳሰቢ ምን ይዘሽ ነው ጌታሽ ፊት ምትቀርቢው? አይበቃም? አረዘመም ከአላህ መራቁ? ልብሽ አልናፈቀችም ጀነትን? አላህ ሆይ ከተውበተኞች አድርገን ከተጥራሪዎችምና ከደጋግ ባሪያዎችህም አድርገን ከነዚያም ፍርሃትና ሃዘን የለባቸውም ከተባሉት አድርገን አላሁ አሚን!! የምትወጃት እህት/ጓደኛ አለችሽ? ላኪላት ይሄ ውዴታሽን የሚገልፅ ምርጥ የማንቂያ ስጦታ ነው አሁኑ ሼር አድርጊላትና ውዴታሽን በተግባር ግለጭላት። Share Share Share -------------------- mohammed ebnu seid
Показать все...
ቀልብ የፅድቅም የጥፋትም የእዝ ማዕከል ~ ጀነት ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተከባለች፤ ጀሀነም ደግሞ ነፍስ በምትወዳቸው ሸይጧን በሚያስውባቸው አማላይ ነገሮች፡፡ በብዙ ሁኔታዎቻችን ከአረሕማን ይልቅ ለሸይጧን የቀረብን ነን፡፡ ዐይኖቻችን፣ ጆሮዎቻችን፣ እጆቻችን፣ እግሮቻችን፣ እንዲሁም ምላሳችን ለሸይጧናዊ ተልእኮ የሰሉ ናቸው፡፡ ቀላሉን አምላካዊ ክልከላ መታገስ አቅቶን ከባባድ ሸይጧናዊ ልፋት ላይ እንተጋለን፡፡ ሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ለጥፋት ሲተባበሩ፣ አንዳቸው ብቻ ለሚበቁት ኸይር ግን ተባብረውም ይዝላሉ፡፡ ይሄ ሁሉ የሚሆነው እንግዲህ ማዕከሉን “ዋግ” ሲመታው ነው፡፡ ቀልብ በሺርክ፣ በቢድዐ፣ በስሜት፣ ለሙስሊሞች በምታረግዘው ክፋት፣ … ከተበከለች ታማ፣ ታውካ፣ አመርቅዛ ትሞታለች። ታዲያ ቀልብ ስትሞት ሞቷ ለኸይሩ እንጂ ለሸሩማ ኢንኩቤተር ትሆናለች - ክፉ የሸር መፈልፈያ። ብቻ ሂወቷ በኢማን ካልኩሌተር ሲሰላ ያለ ኢማን ሂወት የለምና ሞታለች - የምር ሞት! ከዚያስ? ከዚያማ ቀልብ ተበላሽታ ሌላው ሰውነት ምን ጤና ሊኖረው? የአካል እንቅስቃሴ በሙሉ ደመ-ነፍሳዊ ይሆናል። ተንቀሳቃሽ ሙት! ግድግዳ የተጠጋ እንጨት ሆኖ ሂወት እንዳለው ያስባል፡፡ ከዚህ በኋላ ዐይንም ዐይን ጆሮም ጆሮ አልሆነም፡፡ የሰማያትና የምድር አፈጣጠር፤ የሌሊትና የቀን መተካካት ለሱ ከታክሲዎች መተላፍ፣ ሽንት ቤት ደርሶ ከመመለስ ብዙም ልዩነት የለውም፡፡ ችግሩ ከማዕከሉ ነዋ! (أَفَلَمۡ یَسِیرُوا۟ فِی ٱلۡأَرۡضِ فَتَكُونَ لَهُمۡ قُلُوبࣱ یَعۡقِلُونَ بِهَاۤ أَوۡ ءَاذَانࣱ یَسۡمَعُونَ بِهَاۖ فَإِنَّهَا لَا تَعۡمَى ٱلۡأَبۡصَـٰرُ وَلَـٰكِن تَعۡمَى ٱلۡقُلُوبُ ٱلَّتِی فِی ٱلصُّدُورِ) "ለነርሱም በነርሱ የሚያውቁባቸው ልቦች ወይም በነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች ይኖሩዋቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን እነሆ ዐይኖች አይታወሩም። ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ፡፡" [አልሐጅ፡ 46] በሌላ በኩል ልብ ከተስተካከለች፣ በኢማን ከተዋበች፣ በተቅዋ ካሸበረቀች መላ ሰውነት ጤና ይኖረዋል፡፡ ፊትም ኑር ይላበሳል፡፡ ዐይኖች በሐራም አይገግሙም፡፡ ጆሮዎች ለሙዚቃ አይቆሙም፡፡ ምላስም የሀሜት ማሽን አትሆንም፡፡ ከውጭ ሙስሊም ያልሆነ ገፅታ እየተስተዋለ ምላስ “ዋናው ልብ ነው” እያለች አታሽቃብጥም፡፡ ማዕከሉ ነቅቶባታላ! ልብ ስትስተካከል እውነተኛ ማንነት ይገኛል፡፡ ከውስጥም ሙስሊም፣ ከውጭም ሙስሊም! በሐያእ የለሰለሰ፣ በውጭ ገፅታው ያልተኮፈሰ፣ በልቡ የመጠቀ፣ ከእንቶ ፈንቶ የራቀ ልዩ ስብእና! አቡበክር ሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ ከሌሎች በተለየ የላቁት በሶላትና በፆማቸው ብዛት አልነበረም፡፡ ይልቁንም ልባቸው ውስጥ በፀደቀ ነገር ነበር። ኢማን! የቀልብ ልዩ ክብር! ባጭሩ ጥፋታችንም ልማታችንም ከልብ ጋር የተሳሰረ ነው ማለት ነው፡፡ ታዲያ እኔና እርሶ የቱጋ ነን? ሰገነት ወይስ ጫማ ተራ? ነው ወይስ መሀል ሰፋሪ? በሌላ አነጋገር ልባችን ጤነኛ ነው? በሽተኛ ነው? ወይስ ሞቷል? ለካ ይህንንም ለማወቅ ልብ ያስፈልጋል፡፡ "ባለ ልቦናዎቹ እንጂ አይገነዘቡም" አይደል ያለው ኻሊቁ? አንተ ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታችን ሆይ! ልቦቻችንን ወደ ትእዛዝህ አዙርልን። በዲንህም ላይ አፅናን፡፡ አላሁመ ኣሚን፡፡ (ኢብኑ ሙነወር፣ 2001) https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

"إِنَّ اللّهَ لاَ يَغْفِرُ أَن يُشْرَ.كَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَلِكَ لِمَن يَشَاءُ ". “አላህ በርሱ ማጋራትን በፍፁም አይምርም፡፡ ከዚህ በታች ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡” [ኒሳእ፡ 48] ሌላው ቀርቶ ነብዩ ﷺ እንኳን ያን ሁሉ ከመድከማቸው ጋር እንዲህ ብሏቸዋል፡- " لَئِنْ أَشْرَ.كْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ " “ብታጋራ ስራህ በእርግጥ ይታበሳል፡፡ በእርግጥም ከከሳሪዎቹ ትሆናለህ!!” [ዙመር፡ 65] . ለማንኛውም “ለጳጳሱ አላህ እንዲምረው ዱዓ እናደርጋለን” ያለበትን ለዲን ከሚከላከሉት በላይ ለግለሰብ የሚከላከሉ ተከታዮቹ ሊያድበሰብሱ ስለሚችሉ ይሄው ድምፁን ሰምታችሁ ፍረዱ፡- https://youtu.be/508PxByYJcM ቀርዳዊ ኋላ ጫጫታው ሲበዛበት በቃላት እየተጫወተ እንደዛ አላልኩም ሊል ሞክራል። ይሄ ግን ግልፅ ውሸት ነው። በአልጀዚራ የተላለፈውን ድምፁን ሰምታችሁ ማረጋገጥ ትችላላችሁ። በሰራው መልካም ስራ መጠን እንዲያዝንለት ማለቴ ነው ይላል። በክ^ህ^ደት ላይ የሞተ ሰው ለአኺራ የሚሻገር መልካም ስራ አለው? ነወዊ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “በክህ^ደቱ ላይ የሞተ ከ^ሃ^ዲ መልካም ቢሰራ በኣኺራ ምንዳ እንደማይኖረው ዑለማዎች #ተስማምተዋል፡፡ ዱንያ ውስጥ ወደ አላህ ለመቃረብ ብሎ በሰራው በየትኛውም ስራ (በአኺራ) አይመነዳም፡፡” [ሸርሕ ሙስሊም፡ 17/150] ሸይኹል አልባኒይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ከ^ሃ^ዲ በመልካም ስራው ዱንያ ውስጥ ይመነዳል፡፡ ግና መልካም ስራዎቹ ለአኺራ አይጠቅሙትም፡፡ በነሱ ሳቢያም ከቅጣት ሊድን ይቅርና ጭራሽ አይቀለልለትም፡፡ ይህን እውነታ የሚጠቁሙ ሐዲሦች በጣም ብዙ ናቸው፡፡” [አሶሒሐህ፡ 53] በነገራችን ላይ ኢኽዋኒዩ ሙሐመድ ሙርሲም የግብፁ ጳጳስ ሲሞት ተመሳሳይ ጥፋት ፈፅፏል። ይሄውና ማስረጃው:- https://youtu.be/0cw-SAamPoI አላህ እንዲህ ይላል፡- " مَا كَانَ لِلنَّبِيِّ وَالّذين آمَنُواْ أَن يَسْتَغْفِرُواْ لِلْمُشْ.رِكِينَ وَلَوْ كَانُواْ أُوْلِي قُرْبَى مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُمْ أَصْحَابُ الْجَحِيمِ. وَمَا كَانَ اسْتِغْفَارُ إِبْرَاهِيمَ لِأَبِيهِ إِلاَّ عَن مَّوْعِدَةٍ وَعَدَهَا إِيَّاهُ فَلَمَّا تَبَيَّنَ لَهُ أَنَّهُ عَدُوٌّ لِلّهِ تَبَرَّأَ مِنْهُ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ لأوَّاهٌ حَلِيمٌ "(2)، “ለነብዩና ለነዚያ ላመኑት ሰዎች፡ ለአጋ^ሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶች ቢሆኑ እንኳን እነሱ (ከ^ሃ^ዲዎቹ) የእሳት ጓዶች መሆናቸው ከተገለፀላቸው በኋላ ምህረትን ሊለምኑ የሚገባ አልነበረም፡፡” [ተውባ፡ 113] = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
القرضاوي يترحم على بابا... الفاتيكان

በሌላ እምነት ላይ ለሞተ ሰው የምህረት ዱዓእ አይደረግም ~ ከኢስላም ውጭ ባለ እምነት ላይ ለሞተ ሰው “አላህ ይማረው”፣ RIP /rest in peace/፣ “የጀነት ያድርገው” ማለት ከቁርኣንና ከሐዲሥ ጋር የሚጋጭ ነው። ሟቹ ምድር ላይ ሲኖር መልካም ስራ መስራቱ የሚቀይረው ነገር የለም። ምክንያቱም የመልካም ስራ መሰረቱ ኢማን ነውና። ኢማን ከሌለ ደግሞ የትኛውም መልካም ስራ ዋጋ አይኖረውም። አላህ እንዲህ ይላል፡- " وَقَدِمْنَا إِلَى مَا عَمِلُوا مِنْ عَمَلٍ فَجَعَلْنَاهُ هَبَاء مَّنثُوراً " “ከስራም ወደሰሩት እናስባለን። የተበተነ ትቢያም እናደርገዋለን።” [ፉርቃን፡ 23] ነብዩ ﷺ በአንድ ወቅት የእናታቸውን ቀብር ከዘየሩ በኋላ አለቀሱ። በዙሪያቸው የነበሩ ሰዎችንም አስለቀሱ። ከዚያም " استأذنت ربي في ان أستغفر لها فلم يؤذن لي" “ምህረትን እንድለምንላት ጌታዬን ፈቃድ ጠየቅኩኝ። ግን አልፈቀደልኝም!” አሉ። [ሙስሊም፡ 976] ከዚህ ሐዲሥ ከሚወሰዱ ቁምነገሮች አንዱ “ለከ^ሃ^ዲዎች ምህረት መለመን የተከለከለ መሆኑ ነው” ይላሉ ነወዊይ ረሒመሁላህ። [ሸርሕ ሙስሊም፡ 7/45] በተጨማሪም ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- "إنّ الله لا يظلم مؤمنا حسنة. يعطى بها في الدنيا ويجزى بها في الآخرة. وأما الكافر فيطعم بحسنات ما عمل بها لله في الدنيا. حتى إذا أفضى إلى الآخرة. لم يكن له حسنة يجزى بها ". “አላህ አማኝን በመልካም ስራው አይበድልም። በዱንያም በሷ ይሰጠዋል። በአኺራም በሷው ይሸልመዋል። ከ^ሃዲ ግን ለአላህ ብሎ በሰራቸው መልካም ስራዎች ዱንያ ላይ ያበላዋል። ወደ አኺራ ሲሄድ ግን የሚመነዳበት መልካም ስራ የለውም።” [ሙስሊም፡ 2808] እናታችን ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ኢብኑ ጁድዓን በዘመነ ጃሂሊያ ዝምድናን ይቀጥል፣ ምስኪኖችን ያበላ ነበር፡፡ ያ ይጠቅመዋልን?” ብላ ጠይቃ ነበር፡፡ የነብዩ ﷺ መልስ ግን እንዲህ የሚል ነበር፡- لا ينفعه. إنه لم يقل يوماً: ربّ اغفر لي خطيئتي يوم الدين “አይጠቅመውም፡፡ እሱ አንድ ቀን እንኳን ‘ጌታ ሆይ! በፍርዱ ቀን ሃጢኣቴን ማረኝ’ አላለምና፡፡” [ሙስሊም፡ 214] ስለዚህ አንድ ሰው “ሙስሊም” ሊያስብለው የሚበቃ ኢማን ባላስገኘበት የፈለገ መልካም ስራ ቢኖረው አላህ እንዲምረው ዱዓ ማድረግ ክልክል ነው፡፡ ከመሆኑም ጋር ብዙ ሙስሊሞች በዚህ ጉዳይ ላይ እየተዘናጉ ፀያፍ ግድፈት እየፈፀሙ ነው። ከዚህ ጥፋት ላይ ለመውደቃቸው ብዙ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ ጥፋቱ ኢስላምን ያውቃሉ፣ ምሳሌ ይሆናሉ ብለው በሚያስቧቸው አካላት እየተፈፀመ መሆኑ ነው። ዩሱፍ አልቀረዷዊ ለዚህ ጉዳይ ምሳሌ መሆን ይችላል፡፡ ቀረዷዊ የቀድሞው የሮማው ጳጳስ ዮሐንስ ጳውሎስ በሞተ ጊዜ አላህ እንዲምረው ዱዓ አድርጎለታል፡፡ ይሄ እጅግ የሚደንቅ ነገር ነው፡፡ ታዲያ ይህንን ጥፋቱን እንደ ጥፋት ቆጥሮ አላዋቂዎች እንዳይሸወዱበት ከመጠቆም ይልቅ በቡድናዊ መነፅር የሚመለከቱ ተከታዮቹ በስሜት በመነሳሳት ለመሸፋፈን ሲተጉ ይታያሉ፡፡ ከዚህ የቀርዷዊ አስደንጋጭ ጥፋት የሚከላከሉ ሰዎች ሁለት መልክ አላቸው፡፡ አንደኛው፡- ጥፋትነቱን አውቀው ማለፊያ ምክንያት የሚደረድሩ ናቸው፡፡ በእርግጥ መነሻቸው ወይ ደካማ ሐዲሦች ወይም ደግሞ የተሳሳቱ ተእዊሎች ናቸው፡፡ ቀዳሚው ትኩረቴ ስላልሆነ ለማሳጠርም ስል ወደ ውስጥ አልገባሁም፡፡ አቧራ የሚያስነሳ ካየሁ እመለሳለሁ ኢንሻአላህ። ሁለተኛው ክፍል፡- አይናቸውን በጨው አጥበው ቀርዷዊ ጭራሽ አላጠፋም የሚሉ ናቸው፡፡ “እንዴት?” ከተባለ “እሱ ማለት የፈለገው ጳጳሱ እዚሁ ዱንያ ውስጥ ሳለ በሰራው መልካም ስራ አላህ አዝኖለት አጣቅሞታል ማለት ነው” ይላሉ፡፡ እውን እንደዚያ ነው ያለው? ቀርዷዊ ጳጳሱ ሲሞት ስለሱ የተናገረውን ቀንጨብ አድርጌ ላስፍር:- فكان مخلصا لدينه وناشطا من أعظم النشطاء في نشر دعوته والإيمان برسالته وكان له مواقف سياسية يعني تُسجل له في حسناته مثل موقفه ضد الحروب بصفة عامة. فكان الرجل رجل سلام وداعية سلام ووقف ضد الحرب على العراق ووقف أيضا ضد إقامة الجدار العازل في الأرض الفلسطينية وأدان اليهود في ذلك وله مواقف مثل هذه يعني تُذكر فتشكر “ለዲኑ (ለክርስትናው) ኢኽላስ ያለው ነበር፡፡ እንዲሁም ስብከቱን በማዳረስና በተልእኮው በማመን ላይ ከታላላቅ ትጉሃን የሆነ ትጉ ነበር፡፡ ለሱ ከመልካም ስራዎቹ የሚመዘገቡ ፖለቲካዊ አቋሞች ነበሩት፡፡ ለምሳሌ ባጠቃላይ የጦርነቶች ተቃዋሚ ነበር፡፡ ሰውየው የሰላም ሰው፣ የሰላም ሰባኪ ነበር፡፡ በዒራቅ ላይ የተከፈተውን ጦርነት ተቃውሟል፡፡ በፍልስጤም ምድር የሚቆመውን አግላይ አጥር ተቃርኗል፡፡ በዚህ ላይ የሁዶችን አውግዟል፡፡ ይህን የመሰሉ የሚወሱና የሚመሰገኑ አቋሞች አሉት፡፡” "... لا نستطيع إلا أن ندعو الله تعالى أن يرحمه ويثيبه بقدر ما قدَّم من خير للإنسانية وما خلف من عمل صالح أو أثر طيب..." “… ለሰብአዊነት ባስቀደመው፣ በሰራው መልካም ስራ ወይም ጥሩ ቅሪት የተነሳ የላቀው አላህ እንዲምረውና እንዲመነዳው ከመለመን ውጭ ሌላን አንችልም!! …” ይሄ የቀርዷዊ ንግግር ነው፡፡ ዱዓው የተደረገው ለሮማው ጳጳስ ዮሐንስ አራተኛ ነው፡፡ ወንድሜ ንቃ! ከኢስላም ይልቅ የቡድናቸው ጥቅም የሚያሳስባቸው ከንቱ ሰባኪዎች ጩኸት ሰለባ አትሁን፡፡ ለማንኛውም ይሄ የቀርዷዊ ንግግር “ ‘በህይወት ሳለ አላህ አዝኖለት አጣቅሞታል’ እያለ እንጂ እንዴት ቀርዷዊን ያክል ሰው ሙስሊም ላልሆነ ሰው ያውም ለጳጳስ ዱዓ ያደርጋል?” እያሉ ለሚከላከሉ ሰዎች የማያፈናፍን መልእክት አለው፡፡ ምክንያቱም:- 1. ቀርዷዊ “አላህ አዝኖለታል” ሳይሆን ያለው “አላህ እንዲምረውና እንዲመነዳው ዱዓ እናደርጋለን” ነው ያለው፣ ለአኺራው! 2. ዱዓውን ያደረገውም ሰውየው ከሞተ በኋላ ነው፡፡ ሰውየው “ለጳጳሱ አላህ እንዲምረው ዱዓ አደርጋለሁ” እያለ “አይ ማለት የፈለገው ዱንያ ላይ አላህ አዝኖለታል ለማለት ነው” እያሉ መከላከል በስሜት የተለጎሙ ጭፍን ተከታዮችን ያስደስት ካልሆነ በስተቀር ማንንም አይሸውድም፡፡ ባጭሩ ሰውየው የፈፀመው ግልፅ የሆነ ጥፋት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ቀርዷዊ እንዳለው ጳጳሱ የካቶሊክ እምነቱን በማሰራጨት ላይ ትጉ ነበር፡፡ ምናልባትም በዚህ ሰውየ እንቅስቃሴ በአፍሪካ፣ በፊሊፒንስ፣ በኢንዶኔዢያ፣ በተይሙር፣ … ውስጥ ስንት ህዝቦች ከኢስላም ወጥተዋል! ለዚህ ነው እንግዲህ ከአላህ ምህረትን የለመነለት። ነብዩ ﷺ ግን ከለላ ለሆናቸው አጎታቸው አቡ ጧሊብ እና ለወለደቻቸው እናታቸው እንኳ የምህረት ዱዓእ እንዲያደርጉ አልተፈቀደላቸውም፡፡ አላህ ፍጡር እያመለከ በሱ ላይ የሚያጋራን አይምርምና፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
Показать все...
የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦ ” يَتْبَعُ المَيِّتَ ثَلاثَةٌ، فَيَرْجِعُ اثْنانِ ويَبْقى معهُ واحِدٌ: يَتْبَعُهُ أهْلُهُ ومالُهُ وعَمَلُهُ، فَيَرْجِعُ أهْلُهُ ومالُهُ، ويَبْقى عَمَلُهُ “ . "ሟችን ሶስት ነገሮች ይከተሉታል። ሁለቱ ይመለሳሉ፤ አንዱ ከሱ ጋር ይቀራል። ቤተሰቡ፣ ገንዘቡ እና ስራው ይከተሉታል። ቤተሰቡና ገንዘቡ ይመለሳሉ። ስራው ይቀራል።" [ቡኻሪ፡ 6514] = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

ድምፅ ከፍ በሚደረግበት ሶላት ላይ ዝቅ አድርጎ እየቀራ የነበረ ሰው ሲያስታውስ ጊዜ ወደ ኋላ መመለስ ሳይጠበቅበት ከደረሰበት ጀምሮ ከፍ አድርጎ ይቀጥላል። ዝቅ በሚደረግበት ላይ ከፍ አድርጎ እየቀራ ያስታወሰም እንዲሁ። መጨረሻ ላይ የማካካሻ ሱጁድ መውረድም አይጠበቅም። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

ለልጁ ማሳከሚያ ትብብር የጠየቀው ወንድማችን አመንሲስ ኢብራሂም ብሩ ስለሞላለት አሳውቅልኝ ብሎኛል። በየትኛም መንገድ የተባባራችሁ ሁሉ አላህ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይመንዳችሁ። አሁን ፌስቡክ ላይ መግባት ስለማልችል አሳውቁልኝ። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.