ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

Открыть в Telegram

👉plexiglass 👉engraving 👉orginal cosmotics 👉 natural face products like Kesil 👉Gift packages 📞0942410512 metis_bag 🏠🏠 Megenagna 3M Mall 1st floor

Больше
1 892
Подписчики
-124 часа
-37 дней
-2330 дней
Архив постов
photo content

photo content

photo content

ተመራቂ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ተቋማቸው እየተመለሱ ነው! የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዙር ተመራቂ ተማሪዎችን በተዘጋጀው መርኃግብር መሰረት በመቀበል ላይ ይገኛሉ፡፡ በመርኃ ግብሩ መሰረት
ተመራቂ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ተቋማቸው እየተመለሱ ነው! የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዙር ተመራቂ ተማሪዎችን በተዘጋጀው መርኃግብር መሰረት በመቀበል ላይ ይገኛሉ፡፡ በመርኃ ግብሩ መሰረት ከትላንት ጀምሮ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ተቋማቸው እያመሩ ነው፡፡ ተቋማቱም ተማሪዎቻቸውን ለመቀበል ትራንስፓርት ጭምር በየአቅራቢያው ማመቻቸታቸውን አየገለጹ ነው፡፡ ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ ተማሪዎች ጉዟቸው ጥንቃቄ የተሞላበት እንዲሆን ግንዛቤ ተሰጥቷል፣ የትራንስፖርት አቅርቦትንም በተመለከተ እጥረት እንዳይኖር ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተገልጿል፡፡ #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

ለተማሪዎች የተዘጋጀ ድንቅ ቻናል‼️ የትምህርት ደረጃዎን በመጫን የሚመጣሎትን ቻናል ይቀላቀሉ👇

✅ አሁን online ላላችሁ ብቻ ስፖርታዊ ጥያቄና መልስ ውድድር ልንጀምር ነው❗️ 1⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ 2⃣ ለወጣ 50 ብር ካርድ 3⃣ ለወጣ 25 ብር ካርድ 👉 ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ

ከክፍያ ጋር በተያያዘ እገዳ የተላለፈበት አንድነት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እንዲከፈት ተወሰነ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ያወጣውን የክፍያ መመ
ከክፍያ ጋር በተያያዘ እገዳ የተላለፈበት አንድነት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እንዲከፈት ተወሰነ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ባለመተግበሩ እና ወላጆች በተደጋጋሚ ለትምህርት ሚኒስቴር ባቀረቡት ቅሬታ እገዳ የተላለፈበት ትምህርት ቤት በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እገዳው ተነስቶለታል፡፡ትምህርት ሚኒስቴር ባደረገው የሱፐርቪዝን ስራ ትምህርት ቤቱ አስፈላጊውን ማስተካካያ ማድረጉ እና ከወላጅ ኮሚቴዎች ጋር ስምምነት ላይ የተደረሰ መሆኑንን ቢያረጋግጥም ትምህርት ቤቱ ትምህርት ሚኒስቴር የጣለበትን እገዳ ሳያነሳ እና ሳያሳውቅ ትምህርት በመጀመሩ ትምህርት ቤቱ በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እንዲከፈት መወሰኑ ተገልጿል፡፡ በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እገዳው የተነሳለት አንድነት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ከዛሬ ጀምሮ በመመሪያው መሰረት መደበኛ ስራውን ማከናወን እንደሚችልም ተነግሯል፡፡ከዚህ በኋላ ትምህርት ቤቱ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣውን ማናቸውም መመሪያዎችን ተላልፎ ከተገኘ ትምህርት ቤቱን እስከ መዝጋት የሚያደርስ እርምጃ እንደሚወሰድም ትምህርት ሚኒሰቴር አስታውቋል፡፡ሌሎች ትምህርት ቤቶችም ትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣቸውን መመሪያዎች በመከተል የመማር ማስተማሩን ሄደት ማስቀጠል እንዳለባቸው ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

ለተማሪዎች የተዘጋጀ ድንቅ ቻናል‼️ የትምህርት ደረጃዎን በመጫን የሚመጣሎትን ቻናል ይቀላቀሉ👇

✅ አሁን online ላላችሁ ብቻ ስፖርታዊ ጥያቄና መልስ ውድድር ልንጀምር ነው❗️ 1⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ 2⃣ ለወጣ 50 ብር ካርድ 3⃣ ለወጣ 25 ብር ካርድ 👉 ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ

ለተማሪዎች የተዘጋጀ ድንቅ ቻናል‼️ የትምህርት ደረጃዎን በመጫን የሚመጣሎትን ቻናል ይቀላቀሉ👇

በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የተገነባው ትምህርት ቤት ---------------------------------- በጎንደር ከተማ ቀይ አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እርጅና ተጭኖት፣ እንክብካቤ ርቆት
በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የተገነባው ትምህርት ቤት ---------------------------------- በጎንደር ከተማ ቀይ አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እርጅና ተጭኖት፣ እንክብካቤ ርቆት ከመማሪያ ክፍል ጎዳና ሊወጣ ጥቂት ቀርቶት ነበር፡፡ ኑሮዋን በአዲስ አበባ ያደረገችውና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሃንዲሷ አክሱማይት አብረሃ ወደ አካባቢው ባቀናችበት ወቅት ትምህርት ቤቱ የነበረበትን ጉድለት ማየትና መስማት ብቻ ለእርሷ በቂ አልነበረም፤ የቻለችውን ለማድረግ ተነስታ ያሰበችውን አሳክታለች፡፡ ቀይ አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ የሚያስተምር ትምህርት ቤት ነው፡፡ በክፍሎቹ ውስጥ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር ማግኘት ከባድ ነበር። ተማሪዎች እንጨትና ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ነበር ትምህርታቸውን የሚከታተሉት፡፡ ትምህርት ቤቱም ለመማር ማስተማር ሄደቱ ምቹ አልነበረም:: የቀድሞ ትምህርት ቤቷ ገጽታ ረፍት የነሳት አክሱማዊት ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅሞ ትምህርት ቤቱን ማደስ የሚል ዘመቻ ጀመረች፡፡ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም እና በ ሀገር ውስጥ እና ከ ሀገር ውጪ ያሉ ህብረተሰቦችን በማስተባበር 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በማሰባሰብ ስምንት የመማሪያ ክፍሎችን ማስገንባት ችላለች፡፡ ከዚህ በመቀጠል በፋሲል ክፍለ ከተማ ቀበሌ13 የንባብ ማዕከል ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗንም አክሱማይት ተናግራለች። ቀይ አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በዚህ አመት 670 ተማሪዎችን ተቀብሎ በፈረቃ ለማስተማር ወደ ተግባር ገብቷል፡፡ ዘመቻውን ያስተባበረችው አክሱማይት አብርሃ እና በዘመቻው ላይ የተሳተፉ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል ፡፡

photo content

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በጠቅላላ በሀገሪቱ በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁሉም ዘርፍ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሳይመለሱ በፊት የወጪ መጋራት ክፍያ ለመፈጸም እንዲያስችል የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር ( የቲን ቁጥር ) ማውጣት እንዳለባቸው የገቢዎች ሚኒስቴር በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ማስወቂያ እያስገነረ ነው። የየትኛውም ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ የቲን ነምበር ማውጣት እንደሚገባቸው እና በሚኖሩበት የከተማ አስተዳደር በሚገኝ የገቢዎች ቢሮ በመሄድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን ማውጣት እንደሚቻልም አስታውቋል፡፡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማውጣት ያስፈለገው የኮስት ሼሪንግ ( የወጪ መጋራት ) ለመክፈል ብቻ እንደሆነም አስታውቋል። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

እንኳን 1495ኛው የነቢዩ መሀመድ የልደት በዓል (መውሊድ)በሰላም አደረሳችሁ! ትምህርት ሚንስቴር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን መልካም በዓል ይመኛል። #JOIN & #SHARE @FD
እንኳን 1495ኛው የነቢዩ መሀመድ የልደት በዓል (መውሊድ)በሰላም አደረሳችሁ! ትምህርት ሚንስቴር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን መልካም በዓል ይመኛል። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

በአፋር ክልል በስራ ላይ እያሉ ህይወታቸውን ላጡ የትምህርት ሚንስትር ሰራተኞች ሽኝት ተደረገ። የትምህርት ሚኒስቴር ባልደረባ የነበሩ ሁለት ሰራተኞች በአፋር ክልል በስራ ላይ ሳሉ ባልታወቁ ሰዎች በተ
በአፋር ክልል በስራ ላይ እያሉ ህይወታቸውን ላጡ የትምህርት ሚንስትር ሰራተኞች ሽኝት ተደረገ። የትምህርት ሚኒስቴር ባልደረባ የነበሩ ሁለት ሰራተኞች በአፋር ክልል በስራ ላይ ሳሉ ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸውን አጥተዋል። የሰራተኞቹ አስክሬን ከአፋር ክልል ዛሬ ወደ አዲስ አበባ የገባ ሲሆን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች አቀባበል ተደርጎላቸው ወደ የአካባቢያቸው ሽኝት ተደርጎላቸዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ፒ ኤች ዲ) በሽኝቱ ላይ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን በመመኘት የአበባ ጉንጉን አኑረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም በሰራተኞቹ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለስራ ባልደረቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል።

ተአምር የሚመስሉት የብርትኳን ልጣጭ ጥቅሞች [ ካንሰር እና ሌሎችን… https://youtu.be/KHjz_bQb0sQ ቪዲዮውን ለመመልከት ሊንኩን ወይም ምስሉን ይጫኑ

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው አለፈ! የትምህርት ሚኒስቴር የስራ ባልደረባ የነበሩት አቶ ሙላት ጸጋዩ እና አቶ አበባው አያልነህ ለስራ ወደ አፋር ክልል በሄዱበት ድንገ
የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው አለፈ! የትምህርት ሚኒስቴር የስራ ባልደረባ የነበሩት አቶ ሙላት ጸጋዩ እና አቶ አበባው አያልነህ ለስራ ወደ አፋር ክልል በሄዱበት ድንገት "ባልታወቁ ሰዎች" በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸውን ማለፉ ተገለፀ። የሚኒስቴር መስሪያቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለስራ ባልደረቦቻቸው እና ለ ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል። (MoE) #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

እገዳ የተጣለበት ትምህርት ቤት እገዳው ተነሳለት - ትምህርት ሚኒስቴር --------------------------------------- ትምህርት ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ባለመከተል እና ወላጆች ባቀረቡት ተደጋጋሚ ቅሬታ እገዳ ከተጣለባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል የግሪክ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት እገዳው ተነሳለት፡፡ እገዳው የተነሳው ትምህርት ሚኒስቴር ባቋቋመው ቡድን ባደረገው የሱፐርቪዝን ስራ መሰረት ትምህርት ቤቱ አስፈላጊውን መስተካከያ በማድረጉ እና ትምህርት ለመጀመር የሚያስችለውን ዝግጅት በማጠናቀቁ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ትምህርት ቤቱም ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ስራውን ማከናውን እንደሚችል ተገልጿል፡፡ ሌሎች ትመህርት ቤቶችም ትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣውን መመሪያ በመከተል የመማር ማስተማር ሄደቱን ማስቀጠል እንዳለባቸውም ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ተፈታኞች በኦንላይን ምዝገባ ማካሄድ ጀምረዋል የኦንላይን ምዝገባውም በየአካባቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስ
የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ተፈታኞች በኦንላይን ምዝገባ ማካሄድ ጀምረዋል የኦንላይን ምዝገባውም በየአካባቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሀረጓ ማሞ ተናግረዋል። ተማሪዎችም በየአካባቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች በመገኘት በወቅቱ ምዝገባቸውን እንዲያከናውኑ ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል። ምዝገባውም እስከ ጥቅምት 30, 2013 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል። የ2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ዘንድሮ በኦንላይን የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላም አስከባሪ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሥልጠና እየወሰዱ ነው! በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላም ለማስጠበቅ በተለያዩ ዘርፎች ተመድበው የሚሰሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በኢት
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላም አስከባሪ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሥልጠና እየወሰዱ ነው! በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላም ለማስጠበቅ በተለያዩ ዘርፎች ተመድበው የሚሰሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሥልጠና እየወሰዱ ነው፡፡በ45 ዩኒቨርሲቲዎች እና በ15 ቅርንጫፍ ካምፓሶች የሚመደቡ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለሚፈጠሩ ግጭቶች ህግ ለማስከበርና በጤና ሚኒስቴር የወጣውን የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ ተገልጿል፡፡የሰላም ሚኒስቴር፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና የፌዴራል ፖሊስ በዩኒቨርሲቲዎች ግቢ ውስጥ በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላምና ፀጥታን ለማስከበር በጋራ እየሰሩ ነው ተብሏል፡፡በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፌዴራል ፖሊሶች መመደብ በ2012 ዓ.ም እና ቀደም ባሉ ጊዜያት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከሰቱ ግጭቶችን ለማስቀረት እንደሚረዳም ተጠቁሟል፡፡ #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁 - Статистика и аналитика Telegram-канала @korojobag