cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

The Startups

Inspiring Ethiopian Entrepreneurs Admin: @FekadeM

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
363
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
የሽክup ቤተሰዎች ተግባር      ሁሉም ሰው ሀሳብ አለው፣ ምንአልባትም ከኛ በጣም የተሻለ ሀሳብ። ገንዘብም ቢሆን ከእኛ ብዙ እጥፍ የተትረፈረፈ ገንዘብ ያላቸው አሉ። በእውቀትም እንበለጥ ይሆናል። ፉክክሩ ከባድ ነዉ። እናም እንደዚህ ፉክክር በበዛበት አለም ውስጥ ከሁሉ ልቀን ስኬታማ እንድንሆን የሚያስችለን ሀሳብን ወደ ተግባር የመለወጥ ቆራጥነት ነው። እኛ ጋር ያለችው ነገር ምንም ጥቂትና ከሁሉ ያነሰች ብትሆን፣ እሷን በድፍረት ወደ ተግባር ለውጦ መገኘት ትልቅ ዋጋ አለው።       እውቀት፣ ቴክኖሎጂ፣ እና ሌሎችም ሀብቶች በብዙሃኑ እጅ እያለ ለምንድን ነዉ ጥቂቶች ብቻ የነዚህ ተጠቃሚ የሆኑት? ሁሉም ሰው ጋር አሪፍና ትልቅ ቦታ ሊያደርስ የሚችል ሀሳብ ካለ ለምንድነው ሁሉም ሰው ስኬታማ ያልሆነው? መልሱ አጭር ነው፤ ተግባር! ምንም እንኳ ብዙ ሰው ሀሳብ እና እውቀት ቢኖረውም ወደተግባር የመለወጥ ቆራጥነት ግን ጥቂቶች ጋር ብቻ ነው ያለው። Google፣ Facebook፣ Ride፣ እና ሌሎችም ስኬታማ ድርጅቶች አጀማመራቸው እንደእኛው ትንሽ ነበረ። ነገር ግን ታናሽነታቸውን ሳይንቁ በተግባር ስለፀኑ ወደ ታላቅ ስኬት መድረስ ችለዋል። ለዛም ነው ከሌሎች ልቆ ለመገኘት ተግባር ወሳኝ ነው ያልነው። መልካም ሀሳብ ካልተተገበረ ዋጋ የለውም፤ እውቀት እና ሀብትም ስራ ላይ ካልዋሉ ኪሳራ ናቸው። በዚህ ዘመን የጠፋው የተግባር ሰው ነው። ለመተግበር ቆራጥ የሆነ ሰው፣ ጥቂቶች ጋር ብቻ ያለ ውድ ሀብት አለው።      ውድ አንባቢዎቻችን፣ ያላችሁን ሀሳብ እና እውቀት ቀብራችሁ አታስቀሩት። ባይሳካስ፣ ሰው ምን ይለኝ ይሆን ሳትሉ በጥቂቱም ቢሆን ወደተግባር ለውጡት። ከትልቅ ስኬት በፊት በጥቂቱ መጀመር ይቀድማል። ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ ከመፃፍ ወደኋላ አትበሉ። ሽክ @intrpreneurs
Показать все...
ዳግም 1896! About us:- ጥንትም ፈረንጅ አፍሪካን ለማንበርከክ ጦሩን ሸምቆ ሲመጣ የኢትዮጵያ ልጆች ሰይፋቸዉን ሳይመልሱ ሰንደቃቸውን ሳያጥፉ በኢትዮጵያ አምላክ ብቻ ተማምነው ቀን እና ሌሊት ተጋድለው ያን ጥጋበኛ አፈር አብልተው መለሱት፣ ታሪክ ሲደገም! ኢትዮጵያ ፈረንጅን አትለምንም የራስዋ ልብስ ይኖራታል ብለን ቆርጠን ዘምተናል። https://t.me/Tikurseww
Показать все...
ጥቁር ሰው

ዳግም 1896! About us:- ጥንትም ፈረንጅ አፍሪካን ለማንበርከክ ጦሩን ሸምቆ ሲመጣ የኢትዮጵያ ልጆች ሰይፋቸዉን ሳይመልሱ ሰንደቃቸውን ሳያጥፉ በኢትዮጵያ አምላክ ብቻ ተማምነው ቀን እና ሌሊት ተጋድለው ያን ጥጋበኛ አፈር አብልተው መለሱት፣ ታሪክ ሲደገም! ኢትዮጵያን ወደ ቀደመው ክብሯ ለመመለስ ቆርጠን ዘምተናል።

Фото недоступноПоказать в Telegram
የሽክup ቤተሰዎች ጉዞ ፬ አይፎን መስራት አይጠበቅብንም። ብዙ ሰዎች አዲስ ሃሳብ ይዘው ወደ ንግድ መምጣት ሲፈልጉ እጅግ የተወሳሰበ፣ ለመረዳት የሚያስቸግርና ምስጢራዊ ምርት ማቅረብ እንዳለባቸው ያስቡና ሊፈነቅሉት ከማይችሉት ድንጋይ ጋር መላተም ይሆንባቸዋል። የሚገርመው ግን በአለማችን ላይ ትልልቅ የሚባሉት ተቋማት የሚሰሩት ስራ በጣም ጠባብ የስራ ዘርፍ ክልል ላይ ያተኮረ መሆኑ ነው። እንደምሳሌ አፕልን እንይ። አፕል በእጅጉን ከሚታወቅባቸው ምርቶቹ መካከል አይፎን አንዱ ነው። ታድያ ለዚህ ምሳሌ እንዲመች አይፎን ፮ን (iphone 6) ነጥለን ብናወጣ ከላይ ባያያዝነው ምስል ልታዩ እንደምትችሉት አፕል የተለያዩ ክፍሎቹን በምንም ከማይገናኙ ከበርካታ ሃገራት ፋብሪካዎች ሰብስቦ አዋቅሮ ያቀርባቸዋል። የአፕል ስራ ማዋቀርና ማዋቀር ብቻ ነው። አፕል የአይፎንን ካሜራ አያመርትም፣ ስክሪኑን አይሰራም፣ ባትሪውን አይፈለስፍም...። በተቃራኒው ለእነዚህ ለተወሰኑ ተግባራት የተፈጠሩ ሌሎች ነጋዴዎች የገቡበት ገብተው የራሳቸውን ምርት ምርጥ አድርገው ያቀርባሉ። እያንዳንዳቸው እጅግ በጣም የተሳካላቸው ንግዶች ናቸው፤ ሁሉ ግን አይፎንን መስራት አይጠበቅባቸውም። የምንደፍናት ቀዳዳ በትልቅዬ ግድግዳ መሃል ያለች ትንሽዬ ስንጥቅ ልትሆን ትችላለች። ስኬታችን ለዚያች ስንጥቅ ያቀረብነው መፍትሔ ጥራት ላይ የተመረኮዘ ነው። ሽክ @intrpreneurs
Показать все...
የሽክup ቤተሰዎች ጉዞ ፫ የንግድ ቁማር የንግዶች ሁሉ ዋነኛ አላማ ትርፋማ መሆን ነው። ማትረፍ ደግሞ በምርታችን ተወዳጅነት ላይ የተደገፈ ነው። የንግዱ ቁማር አዲሱ ምርታችን ተጠቃሚ አልፎም ደምበኛ ያገኛል ወይስ አያገኝም የሚል ነው። የወደፊት ደምበኞቻችን ፍላጎት ምን ሊሆን እንደሚችል በደንብ አጥንተን ወደ ስራ ከገባን ቁማሩን በላነው ማለት ነው። በራሳችን አስተሳሰብ ብቻ ተመርተን ግን ብዙ ከለፋን በኋላ ማንም ማይወድልን ከሆነ ውሃ በላን ማለት ነው። ለዚህ መፍትሄው ለመጀመር ያክል አነስ ያለ ቁጥር ያላቸው፣ እምነት የሚጣልባቸው፣ የወደፊት ተገዳዳሪ የሌላቸው ደረጃ አንድ ደምበኞችን ይዞ ለነሱ የሙከራ ሃሳቦችን እያሳዩ፣ የልብ አስተያየታቸውን እንደቤተሰብ እንዲሰጡ እየገፋፉ፣ በብዙሃኑ ዘንድ ተወዳጅነትን የሚያገኝ ምርት እስኪሆን ድረስ ማሸት ነው። ለዚህም ነው ከብዙ ሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንድንፈጥር የሚመከረው። እናንተም ለሌሎች ሰዎች ምርቶች ግልጽ አስተያየታችሁን በመስጠት እንዲያድጉና እንዲበረቱ የራሳችሁን አስተዋጽኦ አድርጉ። ገና በዳዴ ላይ ያለ ንግድ ስታዩ "ሲያድግ እመለሳለሁ" ብላችሁ ጥላችሁ ከመሄፍ ይልቅ "አብረን እንደግ" ብላችሁ በመተባበር ግሩም የሆነውን ወደፊታችንን እንገንባ። እኛ የሽክup ቡድን አባላትም እናንት ቤተሰዎቻችን በዚህ እንደማታሳፍሩን እርግጠኞች ነን። አስተያየታችሁ ይደግፈናልና ያልወደዳችሁትን ነገር ከመንገር ወደኋላ አትበሉ። እናንተም የንግድ ሃሳቦች ሲኖራችሁ ወደ እኛ በመላክ እንድናቀርብላችሁና ሌሎች አስተያየት እንዲሰጡበት እናደርግላችኋለን። አብረን ሽክ @intrpreneurs
Показать все...
የሽክup ቤተሰዎች ልዩ ጉዞ ፭፻ መሸነፍ ቀላል ነው። ስኬት ውድ ነው። በብዙ የህይወት ሩጫዎቻችን ላይ ሁላችንም ተሳክቶልን እየፈነጠዝን አለመታየታችን ምክንያት አለው። ይህም ተስፋ መቁረጥ፣ እጅ መስጠት፣ መተውና እነዚህን የመሰሉት ነገሮች ለመወሰን ቀላል መሆናቸው ነው። ይልቁንስ በንግዱ አለም ደግሞ እደጃፋችን ላይ ቆመው ይጠብቁን ይመስል ነቅነቅ ባልን ቁጥር ይፈታተኑናል። በአዲስ መንፈስ ራዕይ አንግበን ለስራ የተነሳን ጊዜ እምብዛም ሳንቸገር እናልፋቸዋለን ያልናቸው ተግባራት ጫን ያለ ጥረት ሲጠይቁን፣ እስከናካቴው ያላሰብናቸው ችግሮች ከየት መጡ ሳይባሉ ፊታችን ድቅን ሲሉ፣ ከወዲያ ወዲህ ከላይ ታች ተሯሩጠን ትክት ሲለን፣ በአንዴ ይሞላል ይትረፈረፋል ያልነው ብር አድሮ ጠብ አልል ሲል፣ ... ይሄኔ... "አርፌ ብማርስ"፣ "አርፌ ተቀጥሬ ብሰራስ"፣ "ምን ማድረግ እንዳለብኝ አለቃዬ አዘጋጅቶ ያቀርብልኛል እኔ ያን ጽድት አድርጌ እተገብራለሁ። ምን እዚህ ናላዬን አዞረኝ" የሚሉ ሃሳቦች ይወርሩናል። መገዛት ቀላል ነው። ድል ግን ጽናትን ይጠይቃል። ያላሰለሰን ትግል ያሻል። ደረማምሶ፣ ገነጣጥሎ ማለፍን። ወደኋላ አለማየትን!!! ዛሬም ከሽክup ጋር ወደፊት! ሽክ @intrpreneurs
Показать все...
የሽክup ቤተሰዎች ጉዞ ፪ መድረሻው የማይታወቅ ጉዞ መቅበዝበዝ ይባላል። አስቀድመን ሞክረነው በማናውቀው አዲስ መንገድ እንኳን ብንሄድ በየት በየት ልናልፍና የት ልንደርስ እንደምንችል ተረድተን ካልጀመርን "አዙሪት ይዞታል"፣ "ጦሽ ያደርጋታል" ከመባል በቀር የምናተርፈው ቁም ነገር አይኖርም። አዲስ የንግድ ሃሳብ መጣልኝ ስንል ከዛ በፊት አይተነው የማናቀው መንገድ ታየን እንደማለት ነው። በዛ መንገድ የሄደበት ሰው ከኛ በፊት አለ ወይ? እሱ የሚጣራ ይሆናል። ምናልባት ሌሎች ሰዎችም ይኸው መንገድ ታይቶአቸው ገንዘባቸውን፣ እውቀታቸውን፣ ጉልበትና ጊዜያቸውን ሸክፈው ብዙ ተመራምረውና ተራቀው ያሉበት የንግድ ዘርፍ ሊሆን ይችላል። በተቃራኒው ደግሞ ማንም ያላለመው፣ እንዲያውም ሰዎች ከእናንተ ሲሰሙት "ምን ጉድ ነው!" ያሰኛቸው ድንግል ራዕይ ሊሆን ይችላል። ታድያ ይህን ሃሳብ ወደ ተግባር ለመቀየር ስንነሳ ልንከተለው የሚገባ ካርታ ካልቀረጽን ንግዱ ጉዞ መሆኑ ቀርቶ አዙሪት ይሆንብናል። ይህን፣ ከምን ወደምን እንዴት እንደምናድግ የሚገልጽልንን ካርታ መቅረጽ የሳምንታትና የወራት ስራ ሊሆን ይችላል። በሮችን ማንኳኳት፣ የካበተ ልምድ ያላቸውን ሰዎች ማናገር፣ ከምንም በላይ ደግሞ መሞከርንና መውደቅን ይጠይቃል። ግን አንዴ ያየናትን መንገድ በካርታችን ላይ አድምቀን ነድፈን ቀጣይ ሙከራችን ላይ ያለፈውን ውድቀታችንን ሳንደግም ከፍ ብለን መገኘት አለብን። ከዚህም በተጨማሪ ሐሳብን አበልጽጎ ምርጥ የሚባል ውጤት ለማግኘት የአለማችን ቁጥር አንዱ ቱጃር ኢሎን መስክ ከትንንሾቹ ንግዶቹ ጊዜ ጀምሮ ሲከተለው የኖረ አንድ አዋጭ አካሄድ አለ። "First Principle Analysis" ይሉታል ፈረንጆቹ። ይህም በቀላሉ ሲተነተን የምንሰራውን ስራ ከስር መሰረቱ ፈልፍሎ አጥንቶ ከወጪም ሆነ ከጥራት አንጻር ሊስተካከል የሚችለውን ነገር ሁሉ አስተካክሎ መነሳትን ያመለክታል። እንደምሳሌ ልብስ ላምርት ብለን ብንነሳና የዳበረ የልብስ ዲዛይን እውቀት ቢኖረን፣ እንደነገሩ ከዛ በፊት ከምናውቀው ጥሩ ጨርቃ ጨርቅ ሻጭ ጥሬ እቃ ገዝተን፣ ጓሮአችን ውስጥ መስፊያችንን ተክለን ጥሩ ደምበኞች አፍርተን ልንኖር እንችላለን። ነገር ግን የሃገራችንን ስም የሚያስጠራ፣ የሃብት ማማ ላይ የሚያቆናጥጥ፣ ትልቅ ለውጥ የሚፈጥር፣ ልዩ ልብስ ማምረት ከፈለግን የምንሰፋው ልብስ ከሚሰራበት ክር ጀምረን፣ ክሩ ከሚገኝበት እንስሳም ሆነ እጽዋት ጀምረን፣ ከመርፌያችን ውፍረት እና ቅጥነት አንስተን፣ እያንዳንዷን ጓዳ ጎድጓዳ አስተውለን መስራት አለብን። ከመጀመሪያዋና ከትንሿ መሰረታዊ መርህ ተነስተን የማምረት ሂደታችንን መገንባት ግድ ይላል። የኸ ሲባል ግን፣ ግራ እንዳይገባችሁ፣ ክሯንም እኛ እናምርታት ማለት አይደለም፤ ምርጡን ክር ከየት እንደምናገኝ እንወቅ እንጂ። ትምህርት ቤቶቻችንን የምንወቅሰው እንዲህ ያለውን ነገር ስለማያስተምሩን ነው። ዛሬም አብረን ሽክ እንበል። ብቻችንን ግን አይደለም፣ ላልሰሙ፣ ሽክ ላላሉ፣ ማሰማታችሁን አትዘንጉ። ሽክ @intrpreneurs
Показать все...
ሽክup እናንት ቤተሰዎቻችን በህይወት እስካለን ድረስ የመለወጥ፣ የማደግ፣ የመጨመር ተስፋ አለን። የሰው አእምሮ ከምንገምተው በላይ ጥልቅ የሆኑ ሃሳቦችን ማፍለቅ ይችላል። ቅድም ባይሳካ አሁን ልክ ይገባል፤ አሁኑኑ ባይደርስ ነገ ይፈታል። በስሜት ሳንናውዝ አስተውለን ከኖርን ካሰብንበት እንደርሳለን። ሽክup ጉዞ ቅዳሜ ትቀጥላለች። ሽክ በሉ። @intrpreneurs
Показать все...
የሽክup ቤተሰዎች ጉዞ ፩ ጉዞ ጊዜ ይጠይቃል። በንግድ ጉዞ ላይ በመጀመሪያ የሚገጥመን ትልቅ እክል ቢኖር የጊዜ እጥረት ነው። በማህበረሰባችን ዘንድ በእጅጉን ተወዳጅነትን ያተረፈ የኑሮ ሂደት አለ። መወለድ፣ በሶስትና በአራት አመት ትምህርት ቤት መግባት፣ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን ጨርሶ ዩንቨርስቲ መግባት፣ መመረቅ፣ ስራ መፈለግ። ስራ በዘመድም በምንም ተብሎ ይገኝና መቀጠር፣ ማስተርስ ይጀመራል፣ በመሃል ትዳርና ልጅ የሚባሉ ነገሮች ይሰነቀራሉ። ከዛ በኋላ የስራ እርከን እድገት እየጠበቁ፣ በተገኘው ብጣሽ ወረቀት "የወሩ ወጭዎች" እያሉ እየጻፉ መኖር ነው። የምናውቃቸው ሰዎች ሁሉ በዚህ ሂደት ላይ የቱ ጋር እንደደረስንና ምን ያክል እንደተሳካልን ባገኙን ቁጥር ያጣራሉ። መስመሩን ጠብቆ የሄደ ሲወደስ፤ አንዱ ላይ አልሳካ ያለው ደግሞ "አሰደብከን" ተብሎ ይነቀፋል። ሆነ ብሎ መንገዱን የቀየረ ደግሞ "ብዙ የማታውቀው ነገር ስላለ ነው" ተብሎ ይወቀሳል። እንዲስተካከልም ቁጣ አዘል ምክሮች ይደርሱታል። አያችሁ ንግድ ስንጀምር ሁለት አይነት የጊዜ ፈንጂዎች መቁጠር ይጀምራሉ። የመጀመሪያው በህብረተሰቡ ውስጥ ያለን አንድ ችግር አስተውለን፣ እንዴት እንደሚፈታ ተመራምረን፣ ሃሳባችንን ወደ ተግባር የሚለውጥ ቡድን አዋቅረን፣ ከሌሎች ተፎካካሪዎቻችን ቀድመን ምርታችንን ይዘን እስቅንቀርብ የሚቆጥር ጊዜ ነው። ሌላኛው ደግሞ ከላይ የጠቀስነውን ተወዳጅ የኑሮ ፍሰት ተቃውመን ባልተለመደ መንገድ በመሄዳችን ምክንያት የሚመጣብን መዘዝ ከመድረሱ በፊት ራሳችንንም ሆነ በአካባቢያችን ያሉ ሰዎችን የሚያሳምን የስኬት ጭላንጭል እስክናይ የሚቆጥር ነው። ይህንን ፈተና በተቻለ መጠን በልጅነት ብንጋፈጠው ውጤታማ እንሆናለን። ለምሳሌ አንድ ተቀጥሮ የሚሰራ፣ ያገባ፣ ልጅ የወለደ ሰው ንግዱን ለማሳካት ሲፍጨረጨር ስራውን፣ የተለመደውን ገቢውን፣ ቤተሰቡን ሁሉ አደጋ ላይ ጥሎ በመሆኑ ቁማሩ የከረረ ነው። አንድ የዩንቨርስቲ ተማሪ ቢሆን ግን ከንግዱ ውጪ የእርሱን እጅ የሚጠብቁ አካላት ቁጥር በመቀነሳቸው የሰፋ "የማሪያም መንገድ" ያገኛል ማለት ነው። በመጀመሪያው የሽክup ጉዞአችን የምናስተላልፈው መልዕክት ይህ ነው። በንግድ አለም እጅግ ውድና የማይገኝ ሃብታችን ጊዜ ነውና የጊዜን ነገር አደራ! አደራ!! ዛሬም ሽክ በሉ @intrpreneurs
Показать все...
ሽክup ጉዞ በአለማችንም ሆነ በሀገራችን ውስጥ ስላሉ ዝነኛ ቱጃሮች ሲነሳ ወደ ብዙ ወጣቶች ልብ የሚመጣ አንድ ነገር አለ። ይህም አብዛኞቹ ባለሃብቶች አንዲት ዲግሪ እንኳን የሌላቸው መሆናቸው ነው። ቢል ጌትስ፣ ስቲቭ ጆብስ፣ ማርክ ዙከርበርግ፣ ጄይ ዚ፣ ማይክል ዴል፣ ተቆጥረው አያልቁም። አብዛኞቹ ከኮሌጅ፣ የተቀሩት ደግሞ ገና ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳግም ዞረው ላያዩት የትምህርትን አለም የተሰናበቱ ናቸው። ይህን ካለትምህርት የተሳካውን የህይወት ታሪካቸውን ስንሰማ አድገን እኛ በየትምህርት ቤቱና በየዩንቨርስቲው በተጠገረርን ቁጥር ሊገነዘቡን ባልቻሉት ወላጆቻችን መብሰልሰል የእለተለት ተግባራችን ነው። አንዳንዶቻችን እንዲያውም እንዲሁ በግብናችን ትምህርት ቤት የምንመላለስ ብንመስልም ቅሉ ትምህርቱን ከአእምሮአችን እርግፍ አድርገን ተፍተነው ነገረ ስራችን ሁሉ ምን አይነት ንግድ ብንጀምር እንደሚያዋጣን ማውጣት ማውረድ ሆኗል። ተስፋ ያላት የምትመስል አንድ ሃሳብ ብልጭ ያለችልን ጊዜም ያለምንም ጥርጥር በዚህ ቢዝነስ አለምን አሽከረክራለሁ ብለን ከላይ ታች ኳትነናል። እኛ የሽክup አባላትም ታሪካችን ይኸው ነው። ትምህርት ምን ያደርጋል፣ የሚጠቅም የማይጠቅመውን ግሳንግሱን ሁሉ ማግበስበስ የት ያደርሳል ብለን ትኩረታችንን ወደ ንግዱ አለም ካደረግን ሰነባብተናል። ገና ዳዴ ላይ ብንሆንም በሃገራችን ስላለው የንግድ ስርዓት ብዙ ተረድተናል። ውድ የቴሌግራም ቤተሰዎቻችን በንግዱ አለም ውስጥ ባሳለፍናት ትንሽ እድሜ እጅጉን የተጎዳንበት ነገር ቢኖር ቀጣዩ እርምጃችን ምን መሆን እንዳለበት ማወቅ አለመቻል ነው። የሀገሪቷን የንግድ ስርዓት ተረድቶ ውሳኔዎችን በእውቀት ማከናወን ዋጋ የማይተመንለት ትርፍ ነው። ታድያ እኛ ከቀደሙን ታላላቆቻችን ያገኘናቸውን ጠቃሚ ልምዶች አፍነን ብንይዝ እንነወራለን ብለን እነሆ ሽክup ጉዞ ብለን ተመልሰን መጥተናል። ጥያቄዎቻችሁን፣ አስተያየቶቻችሁን ላኩልን። ለሌሎችም መልዕክቶቻችንን አካፍሉልን።    ሽክ ማለታችሁን እንዳትዘነጉ። @intrpreneurs
Показать все...
ህልም -ድርጊት(action) - ስኬት ብዙ ህልም አላሚዎች አሉ፡፡ ብዙ ባለ-ሃሳቦች አሉ፡፡ ብዙ እድለኞች አሉ፡፡ ነገር ግን ጥቂት ቢልየነሮች አሉ፡፡ ለምን? በቅርብ ቀን እንመለሳለን!!! @intrpreneurs
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.