cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

The White Future 👻

**ይህ The white future የተሰየው ቻናላችን ነው በዚ ቻናል በ አላህ ፍቃድ የተለያዪ ኢስላማዊ መልክቶችን በቻልነው መጠን እናስተላልፉለን ** #ሼር በማድረግ ተባበሩን **Is a channel that posts Islamic message as much as it can by the help of Allah **👉 #whitefuture #share #share #share

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
168
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

(☆.mp32.26 MB
ኒስፍ ሸዕባን ======== የዛሬዋ ለሊት የሸዕባን ወር ዐስራ አምስተኛው ለሊት ናት። የተባረከች ሌሊት ናት። ታላላቅ ትሩፋቶች እንዳላት የሚጠቁሙ በርካታ ሐዲሶች ተነግሮላታል። ሐዲሶቹ እርስ በእርሳቸው የሚደጋገፉ እና ሐሰን የተሰኘው የሐዲስ ደረጃ ላይ እንደሚደርሱ ዐሊሞች ተናግረዋል። ዶዒፍ የሐዲስ ዘገባዎችም ቢሆኑ በእንዲህ ባሉ የመልካም ስራን ትሩፋት በሚያብራሩ ጉዳዮች ላይ በቂ መረጃዎች መሆናቸው በዐሊሞች ዘንድ ስምምነት ያለበት ነጥብ ነው። የሸዕባን ዐስራ አምስተኛው ለሊትን ትሩፋት በማስመልከት የተዘገቡ ሐዲሶችን በጥቂቱ እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ: ‐ ⚀ ከምእመናን እናት ሰይዳ ዐኢሻ [ረዐ] እንዲህ ተዘግቧል: ‐ «በአንድ ሌሊት ላይ ነቢዩን [ﷺ] አጣኋቸው። ከዚያም እርሳቸውን ለመፈለግ ከቤት ወጣሁ። በቂዕ ላይ ጭንቅላታቸውን ወደ ሰማይ ከፍ አድርገውም አገኘኋቸው። እንዲህም አሉኝ: ‐ «ዓኢሻ ሆይ አላህ እና መልክተኛው ይበድሉኛል ብለሽ ፈርተሽ ነው?» እኔም «የአላህ መልክተኛ ሆይ ይህን ፈርቼ አይደለም። አንደኛዋ ባለቤትዎ ጋር ሄደው ከሆነ ብዬ ገምቼ ነው!» አልኳቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ: ‐ «አላህ በሸዕባን ወር ዐስራ አምስተኛ ሌሊት ላይ ወደ ቅርቡ ሰማይ (በእዝነቱ) ይወርዳል። ከልብ (ከሚሰኙ ጎሳዎች) የፍየል ፀጉር ቁጥር በላይ ለሆኑ ሰዎች ምህረትንም ይሰጣል።» ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህ እና አሕመድ ዘግበውታል። ⚁ ሙዐዝ ኢብኑ ጀበል [ረዐ] እንደዘገቡት ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «አላህ ሰዎችን በሙሉ [በእዝነት] ይመለከታል። ከአጋሪ ሙሽሪክ እና ከቂመኛ በስተቀር ሰዎችን በሙሉ ይምራል።» ጦበራኒ ዘግበውታል። ⚂ ዐሊይ ኢብኑ አቢጧሊብ [ረዐ] እንደዘገቡት ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «የሸዕባን ወር ዐስራ አምስተኛው ሌሊት ሲሆን ሌሊቱን ቁሙበት ቀኑን ፁሙት። ፀሀይ ከጠለቀ ጀምሮ አላህ [በእዝነቱ] ወደ ምድር ይወርዳል። 'ምህረት የሚለምነኝ የምምረው ማነው? ሲሳይ የሚለምነኝ ሲሳይን የምሰጠው ማነው? መከራ የደረሰበት ከመከራ የማወጣው ማን ነው? እንደዚህ እንዳደርግለት የሚለምነኝ የሚፈልገውን የማደርግለት ማነው?…' ንጋት እስከሚቀድ ድረስ እንደዚህ በማለት ይጣራል።» ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል። በዚህ ሌሊት: ⚀ ይቅር እንባባል። ቂምና ጥላቻን እናስወግድ። ⚁ ሌሊቱን በሶላት፣ ቁርኣን በማንበብ፣ በዚክር እናሳልፈው። ⚂ ቀኑን በጾም እናሳልፈው። ⚃ ለራሳችን፣ ለቤተሰባችን እና ለሀገራችን ዱዓ እናብዛ። ሌሊቱ ዱዓ ተቀባይነት ከሚያገኝባቸው ልዩ ቀናት መካከል አንዱ ነው! አላህ ተውፊቅ ይስጠን! https://t.me/fiqshafiyamh/228
Показать все...
Tofik Bahiru

❤️ፍቅር» ምን እንደሆነ ያውቁ ኖሯል??? . #እውነተኛ_ፍቅር_ማለት፦❤️ ☞ ነብዩ ﷺ ለባልደረባቸው ሰውባን ረዲየሏሁ ዐንሁ ምንድነው ፊትህን የቀየረው? ብለው ሲጠይቁት «በሽታም ሆነ ህመምም የለብኝም፤ ግን አንቱን ሳላገኝ ስቀር ከባድ የሆነ ብቸኝነት ይሰማኛል፤ አንቱን እስከማገኞዎ ድረስ» ማለቱ ነው። . #እውነተኛ_ፍቅር_ማለት፦❤️ ☞ አቡበከር አስ-ሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ ከነብዩ ጋር በሂጅራ ጉዟቸው ወደ ዋሻ ከመግባታቸው በፊት «ወሏሂ ካንቱ በፊት ካልገባው በስተቀር አትገቡም፣ የሆነ ነገር ቢኖር እንኳ ካንተ በፊት እኔን ይጉዳኝ» ማለታቸው ነው። . #እውነተኛ_ፍቅር_ማለት፦❤️ ☞ ዐሊይ ኢብን አቢ-ጧሊብ ረዲየሏሁ ዐንሁ በነብዩ ﷺ ፋንታ በፍራሻቸው መተኛታቸው ነው፤ የመካ ካፊሮች ነብዩን ﷺ ለመግደል መስማማታቸውና በዛ ፍራሽ ላይ ሊሞቱ እንደሚችል እያወቁ መተኛታቸው ነው። . #እውነተኛ_ፍቅር_ማለት፦❤️ ☞ ቢላል አል-ሐበሺይ ረዲየሏሁ ዐንሁ ነብዩ ﷺሲሞቱ የነብዩ ﷺ ፍቅር መዲና አላስቀምጥ ብሎት አዛን ማድተጉን መተዉና መዲናን ጥሎ መሄዱ ነው፤ ይህ ብቻም ሳይሆን ነብዩ ﷺ በህልሙ መጥተውበት ምንድነው እንዲህ መጥፋት? ለምን አትዘይረንም? ሲሉት ገና ሌሊቱ እንደነጋ የነብዩን ﷺ ቀብር ዚያራ ለማድረግ መጓዙ ነው፤ ከዛም አዛን እንዲያደርግ ለምነውት ያን ጣፋጩን አዛን ሲያደርግ የመዲና ህዝብ በሙሉ በእንባ መራጨቱ ነው። ነብዩ ﷺ ከሞቱ በኃላ እንጂ እንደዛ አይነት እልቅሻ አልታየም ተብሎ በታሪክ ኢስኪፃፍ ድረስ። . #እውነተኛ_ፍቅር_ማለት፦❤️ ☞ ከበኒ ዲናር የሆነች ሴት ባሏ፣ አባቷና ወንድሟ ወደ «ኡሑድ» ዘመቻ ወጥተው ሳለ ሙስሊሞች ከውግያው ሲመለሱ ሁሉም እንደሞቱ ሲነገራት «ነብዩ:ﷺ እንዴት ሆኑ? ብላ መጠየቋ ነው፤ ከዛም እሳቸው አልሞቱም ሲሏት እሳቸውን ካላየው ብላ ነብዩን ﷺ ስታያቸው «ካንቱ በኃላ ያለ ሙሲባ ሁሉ ለኔ ገር ነው» ማለቷ ነው። . #እውነተኛ_ፍቅር_ማለት፦❤️ ☞ ዙበይር ረዲየሏሁ ዐንሁ የ15 አመት ወጣት ሆኖ የነብዩን ﷺ መገደል የውሸት ወሬ ሲሰማ የመካ መንገዶች ላይ ሰይፉን እየጎተተ መውጣቱ ነው። . #እውነተኛ_ፍቅር_ማለት፦❤️ ☞ ረቢዐተ ኢብን ከዕብን ረዲየሏሁ ዐንዩ ነብዩ ﷺ ምንድነው ሓጃህ (ጉዳይህ) ሲሉት ካንቱ: ጋር በጀነት ጓደኛ መሆን ነው ማለቱ ነው። . «አንድ ሰው ከወደደው ሰው ጋር በቂያማ ይቀሰቀሳል» ማለቶን እናውቃለን፤ #እኔም_አንቱ የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! እንወዳችኃለሁ❤️ በአባቴ፣ በእናቴ፣ በቤተሰቦቼ፣ በንብረቴና በነፍሴ ፊዳዕ ልሁንሎ አንቱ የአሏህ መልክተኛ ﷺ
Показать все...
ጨረቃን ፍራቻ (ዳኒያ ሁሴን ) . ትንሹ ወንድሜ ፉአድ ገና ሲነኩት ሲጢጥጥ ብሎ የሚጮኸውን በራችንን ቀስ አርጎ ከፍቶ ከገባ በኃላ "ኢኩ ኢኩ ረመዳን እኮ ደረሰ!" አለኝ። እኔም የዛን ሰአት ድካምና የሰው ፊት ያደቃትን እናቴን ባለቀ ፍራሻችን ላይ ጋደም ባለችበት እግሯን እያሸሁዋት ረመዳንን እንዴት እሷ ሣትሰቃይብኝ ልናልፍ እንደምንችል እያሰብኩ ስለነበረ ግጥጥሞሹ ገረመኝና የሚቀመጥበት ቦታ እያመቻቸሁለት"የት ሰማህ ፉፉዬ" አልኩት። ከእማዬ ቀጥሎ አንድ አለኝ የምለው ሰው ፉፉ ወንድሜ ነው። ያስተካከልኩለት ቦታ ላይ ቁጢጥ አለና የልጅነት ለዛ ባልተለየው አንደበቱ "ቅድም ከነረያን ጋር ስንጫወት ነው የነገሩኝ" አለኝ። ወይ ጉድ !! እነሱም ደረሰ አልደረሰ እያሉ ቀን ይቆጥራሉ ማለት ነው። ፀጉሩን እያሻሸሁ "ዘንድሮ ከሁሉም የበለጠ ብዙ ቀን እንደምትፆም አልጠራጠርም የኔ ጀግና ወንድም" አልኩት። በዛች ትንሽዬ አይኑ እየተቁለጨለጨ እያየኝ "አዋ አምና እነ ረያን ባያመኝ ኖሮ አይበልጡኝም ነበር ዘንድሮ ግን እበልጣቸዋለሁ" አለኝ። አምና ግን ያልፆመው አሞት ሳይሆን ረመዳን በገባ በአምስተኛ ቀን ራሱን ስቶ ወድቆ ሀኪም ቤት ስወስደው ራሱን የሳተው ውስጡ ምንም የተጠራቀመ ሀይል ሳይኖር ስለፆመ እንጂ ምንም በሽታ ኖሮበት እንዳልሆነ ነግረውኝ ነበር።እኔ ግን ስላመመህ አትፆምም ብዬ ከለከልኩት። ለ 11 አመት ልጅ እንዴት ምግብ ስለማታገኝ ነው የወደቅከው እለዋለሁ። ይከብዳላ...........በጣም ያማል። "ኢኩ" የሚለው የወንድሜ ድምጽ ከሰጠምኩበት የሀሳብ ውቅያኖስ አወጣኝ። ፈገግ ብዬ "ወዬ ፉፉዬ" አልኩት። ምን ጊዜም የፈለገውን ነገር ባላሟላለት እንኳን ፈገግ ብዬ ተስፋ ልሰጠው እሞክራለሁ። "እነ ረያን ስለረመዳን ያስታወሱት በምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?".... "አልነገርከኝም እኮ በምንድን ነው?" "የረያን አባት የሆነ ሳጥን ነገር ይዞ ቤት ሲገባ አየነውና ረያንን ስንጠይቀው ረመዳን ስለደረሰ ቴምር ተገዝቶላቸው እንደሆነ ነገረን።" ፉፉ በቀን 3 ጊዜ እንኳን መብላት ሳይችል ጓደኞቹ ቤት ገና ለሚመጣው ረመዳን ቴምር ሲገዛ ሲያይ ምን ያህል ሊሰማው እንደሚችል አስቤ ውስጤ ደማ....ውስጥ ይደማል እንዴ እንዳትሉኝ ... የደረሰበት ያውቀዋል ። ፊቱን ድምን አርጎ "እኛም እኮ አባት ቢኖረን ቴምር ይገዛልን ነበር" አለኝ። ዝም ስለው አንጀት የሚበላ አስተያየት እያየኝ "በአሁኑ ረመዳን ግን እኛ ጋርም ሾርባና ሳንቡሳ ይሰራላ?" አለ። "አዎ ፉፉዬ ይሰራል!" ቃላቶቹን እንዴት ከጎሮሮዬ ፈልቅቄ እንዳወጣኋቸው የማውቀው እኔ ነኝ። ምክንያቱም ለዚህ ሚስኪን ህፃን የምሰጠው የውሸት ተስፋ ነዋ። ርእስ እንዲቀይር ብዬ ጨዋታ እንጫወት አልኩትና ሰአቱን እስከ መግሪብ ገፋነው። መግሪብ አዛን ሲል እማዬን ቀሰቀስናትና ሰግደን ከጎረቤት የመጣ ሰደቃ እራታችንን በላን። እኔ ደሞ ኢሻ ከሰገድኩ በኃላ ምን አልባት በዚ ሰአት ሚዘጉ ሱቆች ካሉ የወዳደቁ ቲማቲምና ሽንኩርቶች ለቅሞ ቤት ለማምጣት እላይ ሰፈር ሄድኩ። ሄጄ እስክመለስ ሳስብ የነበረው የወንድሜን ንግግር ነበር ። ሰዎች የረመዳንን ጨረቃ በናፍቆት እየጠበቁ ነው፤ እኔ ግን የረመዳንን ጨረቃ ፍራቻ መምጣቱ ላይቀር ምነው ባልደረሰ ብዬ እመኛለሁ ። ምክንያቱም ረመዳን ላይ ስቃያችን ይብሳል። ሌላውን ቀን ጎረቤትም ስንሄድ ሰውም ሰጥቶን ብቻ እንዲም እንዲያም እያልን የምንለቃቅመው ነገር ስለማናጣ ረሀቡ አይታወቀንም። ረመዳን ላይ ግን ኢፍጣር ሰአት ከደረሰ ብቻ ነው መብላት የሚቻለው። እዚም እዚያም ብለን የምናገኘው ምግብ ደግሞ እንኳን ለፆመኛ ሲበላ ለዋለም አትበቃም። እማዬንም ሳያት ታሳዝነኛለች። ጭንቀት ፣ማጣት ፣ድካምና የሰው ፊት ተደማምሮባት ያለእሜዋ አርጅታለች።እኔን በ20 አመቷ ነበር የወለደችኝ አሁን 19 አመቴ ነው። ግን ስትታይ የ39 አመት ሴት አትመስልም። የወጣትነት ወዝና ጉልበቷን እኛን ለማሳደግ ተፍ ተፍ ስትል አጥታ አሁን ደክማለች። ልጆች ቤት መጥተው "ነይና ልብስ እጠቢ ብላሻለች ማሚ" ብለዋት ተነስታ ስትሄድ ልቤ ምን ያህል እንደሚሰበር የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ ። ያውም እኮ የዕለት ጉርስ መሸፈን ለማትችል ክፍያቸው ነው በልጆቻቸው የሚያስጠሯት።ከአሁን በኋላ ግን እማዬን የማሣረፍ ሀላፊነት የኔ ነው...ፉፉዬንም ከጓደኞቹ እኩል አደርገዋለው..... ኢንሻአላህ እንደምንም ብዬ ህይወታችንን መለወጥ አለብኝ ። . . . . ኢክራም ይህን እያሰበች ሳታውቀው ለካ አስፓልቱ መሀል ነበር ስትሄድ የነበረው። የመኪና ክላክስ ሰምታ ፈጥና ወደዳር ስትወጣ ሌላ ከመንደር እየበረረ ሲወጣ የነበረ መኪና ተቀበላት ።.......ሲጢጥጥጥ የሚል የመኪና ጎማ ድምጽ ......... የሰዎች ጩኸትና ዋይታ .......... ጭልም ፀጥ......... ኢኩ እንደዛ የምትወዳቸው እናቷና ወንድሟን ስለነሱው እያሰበች ጥላቸው ላትመለስ ሄደች። አለቀ።።።።። ##ታዲያ በየቤቱ ስንት ኢክራሞችና ፉፉዎች የሰቀቀን ህይወት እየኖሩ ነው!!? የረመዳንን መምጣት ላያመልጡት እየሸሹ ነው!!?........ ቤት ይቁጠረው። #ምንም እንኳን የሁሉንም ችግር መቅረፍ ባንችል ጥቂቶችን እንኳን ባለን አቅም ለመርዳት እንሞክር። "ለበጎነት መስፈርት የለውም " "አንዲት ጉርሻ ከኛ..... ለእዝነቱ ወር ፆመኛ" ኡሚ የየቲሞች የልማት እና መረዳጃ ተቋም እንኳን ለተከበረው የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ! "አላህ ከሰጪዎች ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን ሰጪ ነው በላቸው።" [62:11] ኡሚ የየቲሞች የልማት እና መረዳጃ ተቋም "#አንዲት_ጉርሻ……ለእዝነቱ_ወር_ፆመኛ! በሚል መሪ ቃል ለ6ተኛ ዙር ዘንድሮ ለ300 ቤተሰቦች የረመዳን አስቤዛ ለመሸፈን እየተንቀሳቀሰ ይገኛል እርሶም የበኩልዎን ያደርጉ ዘንድ ጥሪውን ያስተላልፋል #ለአንድ ቤተሰብ ሙሉ ፓኬጅ 2000 ብር ግማሽ ፓኬጅ 1000 ብር በዐይነት መደገፍ ለምትፈልጉ ★ዱቄት ★የሾርባ እህል ★ዘይት ★ሩዝ ★ቴምር ለበለጠ መረጃ 0926688698 0980482001 0912927557 ንግድ ባንክ 1000278180388 TELEGRAM [ https://t.me/ummicharityinstitut ]
Показать все...
አንዳንዴ ዋጋቢስ እንደሆንክ፣ የትም እንደማትደርስ፣ መቼም ደስተኛ ለመሆን እንዳልታደልክና እንደማትረባ ሊሰማህ ይችላል። ግን አንድ ነገር አድርግ🤔 በየቀኑ ትናንሽ መስጠቶችን ተለማመድ፤ ጊዜህን ይሆናል፣ ገንዘብህን ይሆናል፣ ጉልበትህን ይሆናል ወይ ደግሞ ሀሳብህን ይሆናል። ለተቸገረ ገንዘብ መርዳት ብቻ አይደለም መስጠት፤ የከፋው ሰው ካለ የሆዱን ሲነግርህ ጊዜህን ሰጥተህ ማድመጥ ብቻ ለዛ ሰው ሰላም ሲሰጠው ታይና ልዩ ስሜት ይሰማሀል። ጉልበት የከዳው አቅም ያነሰው የምታውቀው ሰው ካለ ጉልበትህን ለደቂቃዎች አውሰው፤ ታላቅ ስጦታ እንደሰጠኸው አስቦ ሲያመሰግንህ ይውላል። ይሄን ስታደርግ እኔኮ የማልረባ ሰው ነኝ የሚለው ስሜትህ ጠፍቶ ማንነትህ በራስህ አይን ገዝፎ ይታይህና "ለዚህ ክብር ያሰብከኝ ተመስገን አምላኬ!" ትላለህ። ወዳጄ እንዳትጠራጠር ለክብር ነው የተፈጠርከው! የሚያረካ ሰንበት ተመኘንላችሁ🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
Показать все...
#አካል_ጉዳተኛ : ዉሃ መጠጣት ፈልጎ ኩባያዉ ይወድቅበታል። ማንሳትም አይችልም! #ሽባ/ፓራላይዝድ: ወዳጆቹ ሲወድቁ ደግፎ ሊያቆማቸዉ ይመኛል። ግን ለራሱም መነሳት አይችልም። #መስማት_የተሳነዉ: አፎች ሲንቀሳቀሱና ጥርሶች ሲገለጡ ያያል። ሰዎች ድምፅን በማዉጣት እየተግባቡና እየተጫወቱ እንደሆነ ቢገምትም በዙሪያዉ ስለሚነገረዉ አጀንዳ ምንም አያዉቅም!። #መናገር_የተሳነዉ: ሁሌም ከአፉ የሚወጡት (አ ኢ ኡ) አይነት ፊደሎች ብቻ በመሆናቸዉ አሞኛል ለማለትም ስሜቱን የሚገልጽበት ሌላ ቃል የለዉም። "ኣ ኣ ኣ!" ፊደሎቹ ሲወጡ ቢያመዉም (ምናልባት ከቤተሰብ በቀር) ሰዉ አይረዳዉም። #ማየት_የተሳነዉ: ሰዎች ከፊቱ ያሉ ነገሮች ምን እንደሚመስሉ ይገልጹለታል። "ዛፎቹ አረጓዴ ናቸዉ" ሲሉት: ከማያዉቀዉ የዛፍ ቅርጽ ባሻገር "አረንጓዴ ቀለም" ምን ዓይነት ይሆን? የሚለዉ ግራ እንደገባዉ ይኖራል። #የአዕምሮ_ዘገምተኛዉ: ሌሎች ሲያሾፉበት እያየ አብሯቸዉ በመሆኑ ደስ ብሏቸዉ የሚስቁ ይመስለዋል። በዚህ ሁኔታም እንኳን ተሳላቂዎቹ እርሱም ቅርታ አይሰማዉም(ከወለደችዉ እናቱ በስተቀር!)። የህጻናቶች እንግዳ አስተያየት ምክንያት ለእርሱም እንግዳ ነዉ(እንደነርሱ ማስተዋል ጎሎታል)። #ምን_ያህል_እድለኞች_ነን?? ربي أوزعني أن أشكر نعمتك التي أنعمت علي وعلى والدي وأن أعمل صالحا ترضاه ] #አልሓምዱ_ሊላህ!
Показать все...
7.11 KB
✨✨ዐይነ በሲሩ ህፃን 💜 ( ለጁመዐችን) ✍ ღ¸.✻´✻.¸¸ღ ኹፊያ በጢብሪዝ ከተማ እምብርት ላይ የምትገኝ የገበያ መዐከል ናት፡ ነጋዴዎች እቃዎቻቸውን ሸካክፈው እዚህ እዚያ ይንቀዋለላሉ ከተርታ መደብሮቹ ትይዩ መንገድ ላይ አንድ የተጎሳቆለ ልጅ ተቀምጧል፡ አይኖቹ ማየት የተሳናቸው ህፃን ነው ፊቱን እግሮቹ መሀል ወሽቆ ከፊት ለፊቱ ሳንቲም የሚቀበልባትን ባርኔጣ ገልብጦ አስቀምጧታል ከአጠገቡም እንዲህ ሲል የተፃፈባት ወረቀት የመንገዱን ጠርዝ ተደግፋለች " አይኖቼ ማየት ስለማይችሉ እርዳታችሁን እሻለሁ" አላፊ አግዳሚው አለፍ አለፍ እያለ 1 1 ሳንቲሞችን ጣል ያረግለታል፡ ምፅዋቱ በዚሁ ከቀጠለ ከአንድ ደረቅ ዳቦ መግዣነት አያልፍም ፡ አንድ የጢብሪዝ ነዋሪ በለማኙ ህፃን በኩል ሲያልፍ ሳንቲሞችን ከጣለለት በኋላ ወደ ልጁ ጠጋ ይልና መለመኛዋን ወረቀት ገልብጦ አዲስ ጽሁፍ ጽፎባት መንገዱን ቀጠለ፡ ይህ ሰው ከሄደ በኋላ ሰዎች ለእርዳታ ይጎርፉ ጀመር፡ ህፃኑ የእግር ኮቴ በሰማ ቁጥር ተከታይ የሳንቲም ኩሽኩሽታዎችንም ያጣጥም ነበር ፡ የወረቀቷን ፅሁፍ የቀየረው የጢብሪዝ ነዋሪ ተመልሶ ሲመጣ ህፃኑ በእርምጃዎቹ ዳና ይለየውና "አንተ ሰው እባክህን ቅድም በአዲስ ፅፈህልኝ የሄድከውን መለመኛ ምን እንደሆነ ንገረኝ" አለው በሚያሳዝን ድምጽ ፡ጢብሪዚዪ ወደ ልጁ ጆሮ አጎንብሶ አንሾካሾከለት፡አዲሱ ፅሁፍ ቀጣዩን ይመስላል 😔""ዛሬ ቀኑ ደስ ይላል እኔ ግን ላጣጥመው አልችልም"" ღ¸.✻´✻.¸¸ღ አንተስ ለዐይኖችህ አመስግነሃል?
Показать все...
#አኩራፊ_ሰው_ብዙ_ነገር_ያመልጠዋል! ሴት ልጅን በፀባይ ካለያዝካት ከሷ በላይ ተንኮለኛም የለም ነገሩ እንዲህ ነው ... ባል እና ሚስቱ በመሀላቸው ግጭት ተፈጥሮ አይነጋገሩም፡፡ ሁለቱም በረጅም ትዝታ ተውጠዋል፡፡ መጀመሪያ ማውራት ሽንፈት መስሎ ስለታያቸው ሳይነጋገሩ መተኛ ሰዓታቸው ደረሰ፡፡ ድንገት ግን ባል የሆነ ነገር ትዝ አለው፡፡ ነገ በጠዋት የስራ ስብሰባ ስላለው ወደ ሌላ ሀገር ለመሄድ በረራ አለው፡፡ ሁሌ ደግሞ ወደ ስራ ሲሄድ እንቅልፋም በመሆኑ የምትቀሰቅሰው ሚስቱ ናት፡፡ እናም የነገው ስበሰባ እንዳያመልጠው ለሚስቱ "11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በአፉ መናገር ሞት መስሎ ታየው፡፡ እና ወረቀት ላይ "ነገ የስራ ስብሰባ ስላለበኝ ወደ ሌላ ሀገር እበራለው፡፡ አደራ 11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በወረቀት ፅፎ እሷ የምታየው ቦታ አስቀምጦላት ምንም ቃል ሳይተነፍስ ተኛ፡፡ ጠዋት ባልዬው ከእንቅልፉ ሲነቃ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ሆኖ በረራውም ስብሰባውም አምልጦታል፡፡ "እንዴት እንደዛ አስጠንቅቄ ነግሪያት አትቀሰቅሰኝም?" ብሎ በጣም ተበሳጨ፡፡ ከአልጋው ለመነሳት ሲሞክር አንድ ወረቀት ኮመዲኖ ላይ ተቀምጦ አየ፡፡ "11 ሰዓት ሆኗል ተነስ ስብሰባ እንዳያመልጥህ" የሚል ፅሁፍ ተፅፎበታል፡፡ ማነው ስህተት የሰራው? ማነው ልክ? ወዳጄ ሴትን ልጅ በተንኮልም ሆነ በፍቅር ልትበልጣት አትችልም፡፡ ዝምታ ደግሞ መቼም መፍትሄ ሁኖ አያውቅም፡፡ "ከስጦታዎች ሁሉ ምርጥ ስጦታ #ይቅርታ" ይቅር በል አላህ ይቅር ይልሃል። "ለአላህ ስትል ክብርህን አሳልፈህ ስጥ። የሰደበህን አሊያም የመታህን ለአላህ ስትል ተውለት። ያጠፋህ እንደሆነም ከአላህ ምህረትን ለምን።" (አቡ አድደርዳእ ረ.ዐ)
Показать все...
😂😂የአምበሶቹ ገዳይ😂😂 ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ እነሆ በአንድ ጥቅጥቅ ባለ ጫካ ዉስጥ የተለያዩ እንስሳዎች (የዱር አራዊት ) በየጎሳቸዉ ተከፋፍለዉ እየተዝናኑ ነዉ፡፡ ሁሉም መጠጥ ይጎነጫል ፡ ጨዋታና ጭፈራዉም ደርቷል፡፡ ወደ ለሊቱ አጋማሽ ላይ ሁሉም እራስን በሚያስት ስካር ዉስጥ ገብቷል፡፡ ተፈራርተዉ የነበሩ እንስሳዎች በሂደት ተቀላቅለዉ አብረዉ መጨፈር ጀመሩ ፡፡ ለሊቱም ለንጋቱ ተራዉን በለቀቀ ጊዜ አዳኝ ከታዳኝ ጋር ተኝተዉ ተገኙ ፡፡ ጦጢትም ሳታስበዉ ከአንበሶች መንጋ መሃል ተኝታ ራሷን አገኘችዉ ፡፡ መጀመሪያ ህልም መስሏት ነበር ፡፡ ነገር ግን እዉነታዉ እንደዛ እዳልሆነ ቆይታ ተረዳች ፡፡ በዙሪያዋ ያሉትን አንበሶች ብትነካካቸዉም ሊነሸቀሳቀሱ አልቻሉም ፡፡ ማምለጫዋን አመቻችታ እዚህና እዝያ እየሮጠች መቀስቀሷን ቀጠለች ፡፡ ነገር ግን የአንበሶቹ መንጋ ጥምብዝ ብለዉ ሰክረዉ ስለነበሩ ሊነቁ አልቻሉም ፡፡ ጦጢትም የሞቱ መሰላት ፡፡ ምናልባትም ትላት ማታ ከእርሷ ጋር በተደረገ ፍልሚያ እደተሰዉ አሰበች ፡፡ ይህን ሁሉ አምበሳ ብቻዬን ገደልኩኝ እንዴ''? ስትል በአግራሞት ተዋጠች ፡፡ የስካር አንጎቨር ያለቀቀዉ ጭንቅላቷ '' ጀግና እኮ ነሽ ሲላት ፈገግ አለች ፡፡ ወዲያዉ ጩኸቷን ለቀቀችዉ ፡፡ ከዛፍ ዛፍ እየዘለለች 🤸‍♀😂 የአንበሶቹ ገዳይ '' ነኝ እያለችና እየፎከረች ሀገሩን አዳረሰችዉ 😂😂😂
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.