የኔ ግጥም በታገል በንቲ🌹📜❤️
✍️ ያዉ መቼም ብዕሬ የሚወልደዉ ያረገዝኩትን ብቻ አይደለም ፣ ሌሎች ያረገዙትንም ጭምር ነዉ፣ኑ ስሜታችንን በግጥም እንተንፍሰዉ 🦋✍ታገል ነኝ🦋 መሳጭ ግጥሞችና የህይወት ስንቅ ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ ለማንኛውም አስተያየትና ማስታወቂያ ያናግሩኝ @tagel_negn🙏☝😍😘https://telegram.me/afkarish
Больше752
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
+130 дней
- Подписчики
- Просмотры постов
- ER - коэффициент вовлеченности
Загрузка данных...
Прирост подписчиков
Загрузка данных...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ተይዤልሻለሁ
ቱ
እኔ አልመለስም ፡
ተፍቼ እንደዉሻ ትፋቴን አልስም ።
ተዉኩህ ፣
አፈቀርኩህ እንጂ መች እኔ ወለድኩህ ።
እናት መሆን በቃኝ እዘኝ ለጀርባዬ ፣
እስከምን ነዉ ምዘልቅ አንተን አባብዬ ።
ቱ
ትፋብኝ ብመለስ ፡
የባይተዋር ኑሮን በል እስቲ ልመደዉ ፣
''ደህና ሁን' እያለች ወዴት ነዉ ምትሄደዉ ?
አለም ላይ ያላንቺ ፡
ሰዉ መሆን እንዳልችል ለብቻ በልተሽኝ ፣
ፈዉሴ ሆይ በእስራት ወዴት ነዉ ምትሸሽኝ ።
እንደቀሳዉስቱ ፡
እግዚያር ይፍታህ ብለሽ እስራቴን ፍቺ ፣
የተያዝኩት እኔ ምን አለብሽ አንቺ ።
ደህና አድርጊኝ እንጂ ፡
ቅበጠጥ ወደ ነዳሽ ፡
በሄድሽበት ሁሉ እከተልሻለሁ ፣
ይልቅ ነይ ትፊብኝ ተይዤልሻለሁ ።
✨✨✨✨✨✨
✍️ታገል በንቲ
👍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ዉዴ ሆይ ፡ እዉነትን የሚሸሽ እንጂ የሚጋፈጠዉ ያለ አይምሰልሽ ፡ እንደ ዓለት የከበደን ነገር ፡ ማን ሊማረክለት ይችላል ?......ሊሸከመዉ የታደለ ጫንቃ ኢምንት ነዉ ። ሁሉም ቀላሉን ይመርጣል (ዉሸትን ) .....እዉነት ደግሞ ፡ በሰዎች አለመመረጡ በሽሽግ አያስቀረዉም ፡ ይልቁንም ጎልቶ ለመታየት ገሃዱን ይመርጣል ።
✨✨✨✨✨✨✨✨
❤❤❤❤❤❤❤❤
✍️ታገል ገጣሚው
tiktok.com/@tagelbanti
@afkarish
.....✍️አንዳንድ ሰዎች ይንቁኛል ፣ ለምን ናቁኝ ብዬ አጉል ፀብ ዉስጥ አልገባም፣ ነገር ግን ሁለት ነገሮችን እመለከታለሁ፣ አንድም ...የናቀኝ ሰዉ ከኔ የባሰ መንገድ ላይ ካለ ፣ እኔን መናቁ ትክክል እንደሆነ አስባለሁ ምክንያቱም ሰዉ የሚንቀዉ የቀናበትንና መድረስ ያልቻለዉን ቦታ ሌላ ሰዉ ሲደርስ ሲመለከት ነዉ ። ሁለተኛዉ ደሞ የናቀኝ ሰዉ ከኔ የተሻለ ከሆነ ፣ ትክክል እንደሆነ አስባለሁ፣ ምክንያቱም እሱ የደረሰበት መድረስ ያልቻልኩ ብኩን ስለሆንኩ በወኔዬ መላሸቅ መናደዱና እኔን መናቁ ያለ ነገር ነዉ፣ እናም ....እራሴን በቻልኩት ሀቅም እሱ ከደረሰበት ቦታ በተሻለ ለመድረስ እጥራለሁ እንጂ አልወቅሰዉም ፣ እንዲያ ነዉ ነገሩ ።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✍️ታገል በንቲ
አደራ
እታባ አብሯአደጌ ፡
የኔ ተንሰፍሳፊ መፅናኛ ታዛዬ ፣
ሞት ጥርሱን አግጥጦ ፡
ሊዉጠኝ ቢመጣ ማምለጫ ቤዛዬ ፣
አሜኬላ ፈርተሽ ፡
ፈራ ተባ ማትይ ቆሳስለሽ ለመድማት፣
ቀና ብዬ ሰዉ ፊት ፡
አምሮብኝ እንድታይ ለረሃቤ ነሽ ሌማት ።
ለደስታዬ ተግተሽ ፡
ያንቺን ሁሉ ለኔ ስትቸሪኝ እያየሁ ፣
ምን እንደ ጎደለው ፡
ሙላቴ ሳላጣሽ ጎደለኝ እላለሁ ።
ሰዉ አልቸገረኝም ፡
የዓለም ፈተናን አልፍበት መበርቻ ፣
ሁሉ ፊቱን ያዙር ፡
እንዳትጨክኚብኝ አደራ አንቺ ብቻ ።
✨✨✨✨✨✨
✍️ታገል በንቲ
👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ወቅት እንዳልጠበቀ ዶፍ እንባ ሳነባ ፣
ምንጩን ማድረቅ ትቶ አዛኝ ቦይ ገነባ ፣
ቁስሌን ማከሚያ መስጠት ሲችል ፋሻ ፣
ስቆ ያፌዝብኛል ሊያሳምመኝ ሲሻ ።
በል እንግዲህ እንባዬ በለዉ ሆድ ሲብስህ ፣
ካመንከዉ ፈጣሪ መልስ እስከሚደርስህ ።
❤❤❤❤
✍️ታገል በንቲ
tiktok.com/@tagelbanti
ቴሌግራም @afkarish
👍 1
ሰዉ ሃገር በድኔን ፡ አታኑሩት አዉጡኝ ፣
ሃብቴን ዉሰዱና ፡ ለሃገሬ ሰዉ ስጡኝ ።
.
ምን አልኩ እስቲ ፡ የሚሞክር አለ ወይ
ህብረ ቃል=
ሰም=
ወርቅ=
✍️ታገል በንቲ
tiktok.com/@tagelbanti
ቴሌግራም @afkarish
Фото недоступноПоказать в Telegram
.......✍️እያንዳንዳችን ፡ አንብበን ከሼልፍ እንዳኖርነዉ መፅሐፍ ፡ ነሸጥ ሲያድርገን ፡ ያሰኘንን ገፅ ከፍተን ፡ በደስታዉ ተሳስቀን ፡ በሃዘኑ ተክዘን ፡ መልሰን የምንዘጋው የትዝታ መዝገብ አለን ።
................
..............
ታገል በንቲ
tiktok.com/@tagelbanti
ቴሌግራም @afkarish
👍 1