cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

wisdom for Ethiopia

🙏🙏በዚህ ቻናል ስለ ፍልስፍና የበለጠ እውቀት እንዲኖራችሁ 📱ድንቃ ድንቅ ታሪኮችን 👉የተለያዩ ፈላስፋዎች የተናገሩትን ጥቅሶች 👉ፕሮፋይል ፒክቸር የሚሆኑ የፈላስፋዎች ፎቶዎች 👉እንዲሁም ስእሎችን ይዘን እንቀርባለን 👉በተጨማሪም ስለ ሁለንታ አለም እንገልፃለን (አፅናፈ ሰማይ) ጥበብ እግዚአብሔርን መፍራት ነው እናመሰግናለን🙏🙏 ጥበብ እግዚሃብሄርን መፍራት ነው።

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
282
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Показать все...
#6300

1234

ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ከእግዚአብሔር ጋር የመታረቃችን፤ ጽድቅንም ያገኘንበት ብቸኛው መንገድ ክርስቶስ እየሱስ ነው። በእርሱ ስራ ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ሰላም አለን፤ ይኽም የእግዚአብሔር ስጣታ ነው እንጂ ከእኛ ስራ ወይም ፅድቅ የተነሳ አይደለም። ሰላም ለኢትዮጵያ 🕊💚💛❤️
Показать все...
ይቅርታ.aac8.66 KB
በአንድ ወቅት አንድ ባለሀብት የመሞቻውን ቀን ከመልዓከ ሞት ይነገረውና በጣም ይደነግጣል፡፡ ከቆይታ በኀላ ግን "ገና እኮ ለመሞት 2 ዓመት ይቀረኛል፤ ለምን እስከዛ ድረስ በደንብ አልዝናናም?" በማለት ከእራሱ ጋር ይማከርና ቀሪ ሁለት ዓመቱን በተሳካ ሁኔታ እና ደስተኛ ሁኖ ለማሳለፍ የተለያዩ እቅዶችን አወጣ፡፡ እናም ሰውየው አለም ላይ አለ የተባለ ባለሀብት ነበረና የተለያዩ ሀገራትን እየዞረ መጎብኘት ጀመረ፡፡ ጣፋጭ የሆኑ ምግቦችን እና መጠጦችን እንደጉድ ይመገባል፤ ይጎነጫል፡፡ ሁለት አመቱን እንደዚህ በተድላ ካሳለፈ በኀላ ሊሞት አንድ ቀን ሲቀረው መልዓከ ሞት ወደ እሱ ይመጣል፡፡ "ነገ ልወስድክ እመጣለው፤ እናም እስካሁን ያላደረካቸውና ምትፈልጋቸው ነገሮች ካሉ ጨራርሰከ ጠብቀኝ" ይለዋል፡፡ ባለሀብቱም ይሄን ሲሰማ በጣም ተረበሸ፡፡ "እኔ አለማችን ካለቻቸው ሀብታሞች ሁሉ ትልቁ ነኝ፤ አለም ላይ በስሜ በሺዎች የሚቆጠሩ ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎች አሉኝ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ አውሮፕላንና መርከቦች አሉኝ፤ የተለያየ ሀገር በጣም ቅንጡ የሆኑ የመኖሪያ ቤቶች አሉኝ፤ በስሜ መቁጠር የሚከብድ ገንዘብ በባንክ አለኝ፤ እና እባክህ ከእነዚህ ሁሉ የፈለከውን ውሰድና ዘላለም የመኖር ዕድልን ስጠኝ" በማለት ጠየቀ፡፡ መልዓከ ሞትም የጠየቀው ነገር ፈፅሞ ተቀባይነት እንደሌለው መለሰለት፡፡ ባለሀብቱ ቀጥሎም "እሺ ያለኝን በሙሉ ውሰድና ተጨማሪ 1 ዓመት ስጠኝ" ብሎ ጠየቀ፡፡ አሁንም ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በመቀጠል 1ቀን ፣ 1 ሰዓት ፣ 1ደቂቃ እንዲጨምርለት ጠየቀው፡፡ መልዓከ ሞት ግን ትሞታለክ በተባለው ቀንና ሰዓት ልወስድክ እመጣለው ብሎት ሄደ፡፡ ✍የሁላችንም መጨረሻ ይሄው ነው፡፡ ዛሬ ላይ ስመጥር ከሆኑ ባለሀብቶች መሀከል አንዱ እንሆን ይሆናል፡፡ ዛሬ ላይ በዓለም ካሉ አዋቂዎች እና ምሁሮች አንዱ እንሆን ይሆናል፡፡ ነገር ግን የትኛውም ሀብታችን ፣ የትኛውም ዕውቀታችን አይደለም ሞትን እንድናመልጥ በህይወታችን ላይ የአንድ ሰከንድ ዕድሜን አይገዛልንም፡፡ ታዲያ ያለን ሀብት ፣ ዕውቀት ፣ ዝና ይሄን ማድረግ ካልቻለ ለምን ለሰዎች ክፉ እንሆናለን? ለምን እራስ ወዳድ እንሆናለን? ዛሬም ፣ ነገም ፣ ከነገ ወዲያም ሁሌም ለሰዎች መልካም እናስብ፤ መልካም እናድርግ፡፡ 🙏መልካም ምሽት🙏
Показать все...
የጀግንነት ጥግ
Показать все...
መሸ ደግሞ አምባ ልውጣ!! (ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን) አምባ ወጥቼ እኩለ- ሌት ፤ ስለት ገብቼ በስሟ ከርሞ ሰይጣን በሷ አስቶኝ፤ ልገላገል ከህመሟ ጠበሏ አፋፍ በጨረቃ፤ ደጋግሜ፤ ማህሌት ቆሜ ሆዴ ቃትቶ ባር ባር ብሎ፤ እርቃኔን ከሷ ታድሜ ደጀ ሰላሟን በአራት እግር፤ ተንበርክኬ ተሳልሜ በስጋዬ እሚነደውን፤ በጸሎት ላቤ አጣጥሜ እፎይ ብዬ አመስግኜ፤ ውዳሴዋን ደጋግሜ . .. ገና ከደጅዋ እልፍ ሳልል፤ ደግሞ ይምጣ የቁም ህልሜ? ሌት በጥምቀቷ የነጣው፤ ነጋ፤ ደፈረሰ ደሜ። . ለሷ እንጂ ለኔ አልያዘልኝ፤ አዬ የስለት አታምጣ! በውጣ ውረድ በጠበል፤ ባሣር ወዜ ቢገረጣ ልክፍቷ እንደሁ አልለቀቀኝ፤ መሸ ደሞ አምባ ልውጣ!
Показать все...
  “ለሕዝብና ለአገር ክብር ሲል ሞትን ንቆ ፊት ለፊት ገጥሞ ከእነ ልጁ በጀግንነት የክብር መስዋእትነት የከፈለው የሸዋው እሸቴ ሞገስ አንዱ” መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡   እሸቴ ሞገስ ከበኩር ልጁ ይታገስ እሸቴ ጋር ሆኖ ለሕዝቡና ለአገሩ የከፈለው መስዋእትነትና የሠራው ጀብዱ ብዙ ያስተምረናል፤ እሸቴ ሞገስ ከልጁ ጋር በርካታ ጠላትን ጥሎ በጀግንነት አልፏል ሲሉም አውስተዋል፡፡   እሸቴ ሞገስ በጀግንነት ሲዋጋ የወደቀው የልጁ አስከሬን ጥግ ሆኖ ሲዋጋ፥ እርሱም በክብር እንደሚሰዋ እርግጠኛ ሆኖ፣ እያለቀሰ ሳይሆን ለወገን የአርበኝነት ስንቅ በሚሆን አልበገርባይነት ነው ብለዋል።   እሸቴ ሞገስ በጀግንነት ሲፋለም መስዋዕት እንደሚሆን እርግጠኛ በመሆን ለመንግስት ቤተሰቦቼን አደራ ማለቱንም አስታውሰዋል፡፡   በርካቶች እንደ እሸቴ ሞገስ የክብር መስዋእትነት መክፈላቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳደሩ፥ በየአካባቢው አስገራሚ አርበኝነት የፈፀሙ በርካታ እሸቴዎች አሉ፤ ወደፊትም ይኖራሉ ብለዋል፡፡   “እኛም የጀግኖቻችን፣ የእሸቴዎችን አደራ በፍፁም አንረሳም” ያሉት ዶክተር ይልቃል፥ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዚህ ዘመቻ እንደ እሸቴ ሞገስ ለህልውናቸው፣ ለሕዝብና ለአገራቸው ክብር መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖችን ቤተሰቦች በመንከባከብና በማገዝ አደራውን እንደሚቀበልም አረጋግጠዋል፡፡   ለጀግናው እሸቴ ሞገስ ቤተሰቦች ስለ መፅናናት አንነግራቸውም፤ ሌሎችም በክብር ሲወድቁ ስለመፅናናት አናነሳም፤ እነ እሸቴ ሞገስ ከልጅ ትኩስ አስከሬን ጥግ ሆኖ በሐዘን ሳይሆን በጀግንነት መፋለምን አስተምረውናል! ሲወርድ ሲወራረረድ ስንዘክረው የኖርነውን የአባቶቻችን አርበኝነት በዘመናችን አሳይተውናል ብለዋል።   ለሕዝባችንና ለአገራችን እስከመጨረሻው መስዋዕትነት እንድንፋለም የሰጡንን አደራ ተቀብለን ለሕልውናችን እስከመጨረሻው መስዋዕትነት እንታገላለንም ነው ያሉት።
Показать все...
በአጭሩ ይህ ነው ጓደኝንት ታዲያ:አንተ እውነተኛ ጓደኛነህ??? :እኔ እውነተኛ ጎደኛ ነኝ?? :እኛ እውነተኛ ጎደኛ ነን??? ??🤔🤔🤔???? ግን እኔ ባልሆን አሱ ባይሆን እንኳን አንተ ለመሆን ሞክር እሺ kira
Показать все...
ይህንን ያውቁ ኖሯል? ጓደኝነት በሁለት የተለያዩ አካላት ውስጥ የምትኖር አንዲት ነፍስ ማለት ነው።እውነተኛ ጓደኛ በልብህ ውስጥ ያለውን መዝሙር የሚያውቅና በረሳሀው ጊዜ መልሶ የሚያዜምልህ ነው።ጓደኛህ በተቸገረ ጊዜ "ምን ልርዳህ?"ብለህ አታናዘው ማድረግ ስለምትችለው አስብና በቀጥታ አድርግ።ጓደኛ ማለት ስለአንተ ደካማ ጎን እያወቀ እንኳ የሚወድህ ነው።ጓደኝነት ጥንቃቄ የሚጠይቅ የህንፃ ላይ መስተዋት ነው።እውነተኛ ጓደኛ ለራስህ እንኳን መንገር የምትፈራውን እውነታ ሊነግርህ የሚችል ነው።ትልቅ ስጦታ እንቁ ወይም አበባ ሳይሆን ለሚወዱት የሚሰጡት ፍቅር ነው።ጓደኛና ጊዜ የተሰበረ ልብን የሚጠግኑ ፍቱህ መድሃኒት ናቸው።ለብቻህ በብርሃን ከመጓዝ ከጓደኛ ጋር በጨለማ መጓዝ ይሻላል።የጓደኝነት ቋንቋ በቃላት ብዛት ሳይሆን በመልእክቱ ይወሰናል።እውነተኛ ጓደኛ ቢጨክን እንኳን ከፊትለፊት እንጂ ከኋላ አይወጋም።እውነተኛ ጓደኛ አለም ሁሉ ስህተት ነህ ባለ ሰአት አብሮህ የሚሆን ነው። ስለ ጓደኝነት ይሄን ሁላ አውቃለሁ ለጓደኛዬ ልሆንለት የምችለው ሊሆንልኝ የሚችለው ጥሩ ጓደኛ መሆን ነው ጓደኛዬን እየናኩት እንዴት ከሱ ክብር እጠብቃለሁ??
Показать все...
p⓷ >ማጠቃለያ ይህን ማጠቃለያ የምነግራቹ ከእኔ ካሣለፍኩት ጋር ነው:' ??እውነት አሁን አንተ የያዝከው እኔ የጠቀስኩት አይነት (ምክንያት የሌው ፍቅር )አለው ወይንም እንደዛ አይነት ነክ ነኝ (እንደዛ አይነት ጓደኛ አለኝ ካልክ እናኔ እንደሌለክ ላረጋግጥልክ ከታች ያሉትን በሙሉ ሚያከናውን ከሆነ ምክንያት የሌለው ፍቅር አለው ማለት ነው -እውነት ላንተ ይሞታል?_______(አዎ/አይደለም) -ሰድበክ ብትገፈትረው ድጋሜ ይቀርብሀል______(አዎ/አይደለም) -ላንተ ውዱን ነገር ይለቅልሀል(ፍላጎቱን ትቶ ለአንተ የሆንልሀል________(አዎ/አይደለም ) እስቲ ሶስቱንም 3/3 አዎ የሚሞላ ካለ ሂድና ሰድበክ ገፍትረው ነገ ስለ አንተ ሲዶልት ታገኘዋለክ ። ???ታድያ ማነው እውነተኛ ጓደኛ??? እኔ ያገኘዋቸው ጓደኞች ሦስቱንም አያሟሉም ግን አንድ ሚያሟላ አገኘው እሱም እራሱን በመስቀል ላይ የሠጠኝ የሱን ውዱን ስጦታ የዘላለም ህይወት የሠጠኝ ስጥለው የማይጥለኝ ስገፋው የማይገፋኝ ስቀርበው በበረከቱ የሚቀርበኝ ልብሴን አይቶ ያልቀረበኝ እድሜዬን አይቶ የማይንቀኝ እውነተኛ ወዳጅ ምክንያት የሌለው አፍቃሪ ኢየሱስ ነው።።።። ወዳጄ:እውነት አውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ህይወት አለው!!!! (ዮሀንስ 6÷47 )ተብሎ ተፅፏል ለዘለአለም ህይወት በኢየሱስ እመንን kira
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.