cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

👳‍♀️ያዐለሙ-_መብራት 😍{ሰይዲ}

አሰላም አለይኩም ያ ጀማዐ ይህ channel አላማው ስለ ዲናችን የምናቀውን ልናሳውቃቹ ወደናል ሐዲሶች ቂሳዎች 🙌 መንዙማዎች😃 ኢስላማዊ ታሪኮች ይገኙበታል 😄 አናሽቃለን 👳👏 አስተያየት ካለ👇 @Buki_reha በሚለው ይስጡን

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
221
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

በጣም የምፈራዉ ነገር ምን እንደሆነ ታዉቃለህ? በጊዜያዊ ስሜት የምወስነዉ ዘላለማዊ ዉሳኔ! ለምሳሌ አንድ ሰዉ ከአባቱ ጋር ተጣልቶ በቃ እራሴን ማጥፋት አለብኝ ምንም አልረባም ብሎ ቢያደርገዉ እራሱን ለዘላለም አጣዉ ማለት ነዉ፡፡ ነገሮች ምንም ያህል ከባድና ፈታኝ ቢሆኑብኝም ጊዜያዊ ዉሳኔ መጨረሻ ለሌለዉ መጥፎ ዉሳኔ እንዳይሰጡኝ እፈራለሁ፡፡ ይህንን ለምን አልኩህ መሰለህ? ብዙ ሰዎች በምኖርበት ህብረተሰብ ዉስጥ እራሳቸዉን እያጡ ስለሆነ ነዉ...ከሚስቱ ጋር አንድ ቀን ክፉኛ ስለተጣላ መፋታት አለብን ብሎ የደመደመ ሰዉ፣ ዉጤቴ ጥሩ ስላልሆነ ለምን እማራለሁ ብሎ ትምህርቱን የሚያቋርጥ ሰዉ፣ ፍቅረኛዬ ጥሎኝ ሄደ ብላ ወንዶችን ሁሉ በአንድ ላይ ለመበቀል ደፋ ቀና የምትል ሴት ኸረ ስንቱ...! እኔም ሆንኩ አንተ ሁኔታዎች እንደሚቀያየሩና ዛሬ አሪፍ ያልናቸዉ ዉሳኔዎች ነገ የእግር እሳት ሊሆኑብን እንደሚችሉ መገንዘቡ ላይ ነዉ፡፡ ምንም ይሁን ምን ሁኔታዎች ሲከፋ ለፈጣሪህ አሳልፎ መስጠትና እራስህን ዘወር ማድረጉ የተሻለ ዉሳኔ ነዉ እላለሁ፡፡ ፀሀፊው ያልታወቀ❓ ☘️☘️🌿🌿🍁🍁🍀🍀 መልካም ምሽት😉😘 JOIN👉 @Sycotube™
Показать все...
   عيدكم مبارك 🔶 Eid Mubarak 🔶 ኢድ ሙባረክ 🔹 تقبل الله منا ومنكم. 🔹 Rabbi hojii gaggaarii nuuf siniirraa haa qeebalu 🔹 ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሀል አእማል። [ወንደሞቼ እና እህቶቼ ፣ አላህ መልካም ስራዎቻቸንን ይቀበለን !!!] "ليس العيد لمن لباس جديد إنما العيد لمن نجا يوم الوعيد"  
Показать все...
#የላቀ ሐዲስ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿اطَّلَعْتُ في الجَنَّةِ فَرَأَيْتُ أكْثَرَ أهْلِها الفُقَراءَ،﴾ “ወደ ጀነት ተመልከትኩ። በውስጧ የሚበዙት የድህነት ባልተቤቶች ናቸው።” 📚 ቡኻሪ (5198) ሙስሊም (2738) ዘግበውታል
Показать все...
#የጎረቤት ሐቅ! ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ለነቢዩ (ﷺ) እንዲህ አልኳቸው፦ ﴿يا رَسولَ اللهِ ! إنَّ فلانةَ تقومُ اللَّيلَ وتَصومُ النَّهارَ وتفعلُ، وتصدَّقُ، وتُؤذي جيرانَها بلِسانِها؟ فقال رسولُ اللهِ ﷺ لا خَيرَ فيها، هيَ من أهلِ النّارِ.﴾ “አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እከሊት ሌሊት ሰላት በመቆም ታሳልፋለች፣ ቀን ትፆማለች እንዲሁም ሰደቃ ታደርጋለች። ነገር ግን ‘በምላሷ ጎረቤቷን በነገር ታስቸግርላች።’ ረሱል (ﷺ) አሉ፦ መልካም የሆነ ነገር የላትም። እሷ የእሳት ነች።” 📚 ቡኻሪ አልአዳቡል ሙፍረድ ላይ ዘግበውታል: 119
Показать все...
👉መቸኮል እና ነገርን አለማጣራት መደምደሚያቸው ጥፋት ነው፤ ሁለቱም በስሜት የሚፈጸሙ ድርጊቶችን ያስከትላሉ ያ ደግሞ ኋላ ሚያስቆጩ ሁኔታ ውስጥ ይከተናል! ውሳኔአችን ከምን የመነጨ እንደሆነ ቆም ብለን ማሰብ ይገባናል!!! 👉ገደብ፡ ይሕ ምን ያህል መሔድ እንዳለብን የሚወስነን ነው፤ ገደብ አስፈላጊ ነገር ነው፤ የምንጠይቀው ፤ የምናወራው ፤ የምናስበው ፤ የምንመኘው ፤ የምንፈጽመው ነገር ሁሉ ገደብ ሊኖረው ይገባል፤ ካልሆነ ኑሮአችን ቅጥ ያጣ ፤ ስብዕናችን የተናቀ ፤ ድርጊታችን የጭካኔ መሆኑ የማይቀር ነው!!! :አላህ ይጠብቀን: @fuadne ,,,,,,,,,,,,,, @fuadne ,,,,,,,,,,,,,,
Показать все...
💜 ወደ ምትወደው ነገር የሚወስድህ መንገድ... መጀመሪያ በምትጠላቸው ነገሮች በኩል ያሳልፍሃል @fuadne
Показать все...
💚 ህይወት የፈለገ ያህል ከባድ ጭንቀተማና አድካሚ ብትሆንም ሁለት ደስ የሚሉ ጣእምን የሚሰጧት ነገሮች አሉ ‥ እንሱም ⇘ አላህን ማውሳት እና ለአላህ ብሎ ከሚወድህ ልብ የሚመጣልህ ዱዓእ ነው ። @fuadne
Показать все...
💚 ከአላህ ፍቅር ያንተ ድርሻ እሱን በምታወሳው ልክ ነውና አላህን በብዙ አውሳው‥ ። @fuadne
Показать все...
▒▒▒ ያኔ ~ አልቅስ ‼️ ▒▒▒ 👉 በነፍስህና በስሜትህ ተበልጠህ ለትናንሽም ሆነ ለትላልቅ ወንጀሎች በቀላሉ እጅ የሰጠህ ቀን። 👉 መልካም ነገርን እያየህ ከመሥራት ስትሰንፍ ፣ መጥፎን ደግሞ መጥፎነቱን እያወቅክ ስትዳፈር። 👉 ለሙዚቃ ፣ ለድራማና ለፊልም ውስጥህ ሲነካ ፡ ለቁርዓን ልብህ ሲደነደን። 👉 ለዱኒያና ለጥቅሞቿ ስትሮጥ እንቅልፍ ስታጣ ለአኺራህ ግድ የለሽ ስትሆን። 👉 ሶላትህ ትርጉም ስታጣብህ ፣ ሩኩዕና ሱጁድ ጎንበስ ቀና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ብቻ ሲሆንብህ። 👉 ከዒባዳህ ጥፍጥና ስታጣ በአምልኮ ተግባርህ እርካታን ከተነፈግክ። 👉 ጊዜህን ባልረባ ነገር ስትጨርስ ፡ ኸይር ሳትጨምር ቀን አልፎ ቀን ከተተካ። 👉 የተውባ በር ሁሌም ክፍት ሆኖ ሳለ ለመግባት ድፍረት ስታጣ። 👉 የዓለማዊው ሕይወት ፍጻሜ መቃረቡን ስታውቅ በበቂ አለመዘጋጀትህን ስትረዳ። @fuadne
Показать все...
💚 ወደ አላህ በተቃረብክ ቁጥር ተስፋ መቁረጥ ካንተ ይርቃል ።  @fuadne
Показать все...