cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ዲናችን

በዚህ ቻናል ላይ አስተማሪ የሆኑ ኢስላማዊ ታሪኮች ኢስላማዊ አጫጭር ልቦለዶች እንዲሁም ግጥሞች ,ወጎች ካነበብኳቸው መፅሀፍቶች አስተማሪ ሀሳቦችን አካፍላችለው ኢንሻአላህ🙂በተለይ ደግሞ ሴቶችን የሚያበረታቱ ነገሮችን ወደናንተ አደርሳለሁ🧕 ለማንኛውም አስተያየት እና ሀሳብ 👇 @IbtiN

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
172
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Показать все...

#ሩሲያዊቷ_ሱመያ ክፍል 5 ባለቤቴም "ባይሆን ማድረግ ያለብኝን ሌላ መፍትሄ ካለ ንገሪኝ"አለቻት ። በመጨረሻም ሀላፊዋ " ይህን ጉዳይሽን ሊፈታ የሚችለው ሞስኮ የሚገኘው ዋና ቢሮ ብቻ ነው " አለችን ። የፓስፖርት ጣቢያውን ትተን ወጣን ። ወደ እኔ በመዞር " ኻሊድ ወደ ሞስኮ እንሂድ "አለችኝ ። ተበሳጨሁ " እነርሱ የሚሉትን ፎቶ ስጪያቸው በቃ " አልኳት ። " አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም ፤ "የቻላችሁትን ያህል አላህን ፍሩ ። " ነው የተባለው ። የግዴታ ስለሆነብሽ ነው የተጠየቅሽውን እያደረግሽ ያለሽው ። ፓስፖርትሽን ሊያዩ የሚችሉት ደግሞ የተወሰኑ አካላት ብቻ ናቸው ። ይህም ግድ ስለሆነ ነው ። ከዚያ ጊዜው እስኪያልቅ ድረስ ቤትሽ ነው የምታስቀምጭው ። ስለዚህ እባክሽን እራስሽን አታጨናንቂ ። ሞስኮ ድረስ ለምን እንሄዳለን?" አልኳት ። "አይሆንም "አለችኝ ። "ተገላልጬማ ፈፅሞ ፎቶ ተነስቼ አልሰጣቸውም ። የአላህ (ሱ.ወ.) ዲን ካወቅኩ በሗላም ይህ ሊሆን አይችልም " በማለት ተከራከረችኝ ። ኻሊድ በመቀጠልም እንዲህ ይላል.............. "ካልሄድን" በሚለው አቋማ በመፅናቷ ወደ ሞስኮ መሄዳችን ግድ ሆነ ። ማረፊያ ክፍል ተከራየን እና በነጋታው ወደ ፓስፖርት ጣቢያው ሄድን ። የተለያዩ ሀላፊዎች ዘንድ ገባን ። በመጨረሻም ዋናው ሀላፊ ዘንድ ቀረብን ። ሲበዛ መጥፎ ሰው ነው 😈። ፓስፖርቱን እያየ ፎቶውን ማገላበጥ ጀመረ ። ከዚያም ወደ ባለቤቴ ቀና በማለት " የዚህ ፓስፖርት ፎቶው የሷ ስለመሆኑ በምን ማወቅ እችላለሁ ?" አለ ። ለማመሳከር ፈልጎ ፊቷን ገልጣ እንድታሳየው ያሰበ ይመስላል ። " ላንተ ፊቴን አልገልጥም ሴት ሰራተኞች ሠራተኞች ካሉ ሊያዩኝ ይችላሉ " አለችው ባለቤቴ ። በዚህን ጊዜ ሰውየው በጣም ተቆጣ ። የድሮውን ፓስፖርት ፣ፎቶዎችና ሌሎችንም ሰነዶች ጨምሮ ወደ ራሱ የማስቀመጫ ቦታ ወረወራቸው ። "ትክክለኛውን የፓስፖርት ፎቶ ይዘሽ ካልመጣሽ በስተቀር ከአሁን በኋላ የበፊቱንም ሆነ አዲስ ፓስፖርት አይኖርሽም " አላት ። ባለቤቴ ከሱ ጋር በማውራት ልታሳምነው ጣረች። በሩሲያንኛ ነበር የሚያወሩት ። የሚያወሩት አይገባኝም😳 ። ባለቤቴ ተናዳለች 😠። ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኛል። ሀላፊው ከያዘው አቋሙ የሚመለስ አይመስልም ። "በፍፁም አይሆንም " አለ። እሷም ተስፋ ሳትቆርጥ ተከራከረች ። ጠብ ያለላት ነገር የለም ። ለጥቂት ጊዜ ዝም ብላ ቆመች ። ወደሷ ጠጋ አልኩኝ ። "አላህ ነፍስን ከማትችለው በላይ አያስገድዳትም ፤ ችግር ላይ መሆናችንን ልብ በይ ። በዚህ መልኩ የምንጉላላው እስከመቼ ነው ?" አልኳት ። " አላህ እሱን ለሚፈራ ሰው መውጫ ያበጅለታል ፤ ባላሰበውም በኩል ሲሳዩን ይለግሰዋል " አለች። እዚያው ሆነን ከኔ ጋር ብዙ ተከራከርን ። የጣቢያው ሀላፊ በሁኔታችን ተቆጣና እንድንወጣለት አስገደደን ። ወጣን ። ደክሞናል ። በአንድ በኩል ስታሳዝነኝ 🥺በሌላ በኩል አናዳኛለች 😠። ተቀምጠን በሰፊው እንድናወራ በማሰብ ወደ ተከራየነው ክፍል አመራን ። እኔ ላሳምናት እጥራለሁ ። እሷም ልታሳምነኝ ትሞክራለች። ዕለቱ መሸ ። ዒሻ ሰገድን ። በዚህ ጉዳይ ላይ በሀሳብ ተወጥሪያለው 🤯። ርቦን ስለነበር ያገኘነውን በላን ። ይቀጥላል........ Join 👇 @din_achen @din_achen @din_achen @din_achen ለሀሳብ እና አስተያየት 👉@IbtiN
Показать все...
Показать все...
★★ Ⓘⓢⓛⓐⓜⓘⓒ ⓚⓝⓞⓦⓛⓔⓓⓖⓔ★★

FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE . . . . . . . Join our channal @seeking_Islamic_knowledge_1 . . Join our group @seeking_islamic_knowledge If u have any comment contact us by @Tinuna

Показать все...
★★ Ⓘⓢⓛⓐⓜⓘⓒ ⓚⓝⓞⓦⓛⓔⓓⓖⓔ★★

FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE . . . . . . . Join our channal @seeking_Islamic_knowledge_1 . . Join our group @seeking_islamic_knowledge If u have any comment contact us by @Tinuna

★★ Ⓘⓢⓛⓐⓜⓘⓒ ⓚⓝⓞⓦⓛⓔⓓⓖⓔ★★ FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE . . . . . . . Join our channal @seeking_Islamic_knowledge_1 . . Join our group @seeking_islamic_knowledge If u have any comment contact us by @Tinuna https://t.me/seeking_islamic_knowledge_1
Показать все...
★★ Ⓘⓢⓛⓐⓜⓘⓒ ⓚⓝⓞⓦⓛⓔⓓⓖⓔ★★

FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE FREE PALESTINE . . . . . . . Join our channal @seeking_Islamic_knowledge_1 . . Join our group @seeking_islamic_knowledge If u have any comment contact us by @Tinuna

#ሩሲያዊቷ ሱመያ ክፍል 4 በዚህን ጊዜ ኻሊድ ተቆጣ ። እሷ ግን እንዲረጋጋ መከረችው ። "አይዞህ አትዘን ፤አትጨናነቅ ። ሶሐቦችን ካገኛቸው ችግር አንፃር ሲታይ ይሄ በጣም ኢምንት (ትንሽ) ነው " አለችው ። እሷም ባሏም ትዕግስትን መረጡ ። በመጨረሻም የተሳፈሩበት አውሮፕላን አረፈ ። ኻሊድ እንዲህ ይላል : ሩሲያ ስንደርስ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት በመሄድ እነርሱ እነርሱ ዘንድ ቀናትን ቆይተን ጉዳያችንን ጨርሰን የምንመለስ ነበር የመሰለኝ ። የሚስቴ ሀሳብ ግን ከዚህ ከፍ ያለ ነበር ። እንዲህ አለችኝ : "ቤተሰቦች ሙስሊም አይደሉም የሌላ እምነት ተከታዮች ናቸው ። ሀይማኖታቸውንም በጣም ያጠብቃሉ ። አሁን እነርሱ ዘንድ መሄድ የለብንም ። ማረፊያ ቤት እንከራይ ።እዚያው ቆይተንም የፓስፖርቱን ጉዳይ እናስጨርስ ። ከጨረስን በኋላ ሄደን ቤተሰቦቼን እንጎበኛለን ።" በሀሳቧ ተስማማሁ ። ማረፊያ ተከራየንና እዚያው ቆየን ። በነጋታው ወደ ፓስፖርት ማደሻ ማዕከል ሄድን ። ወደ ቢሮው ዘለቅን ። አስተናጋጃችን የቀድሞውን ፓስፖርት እና ሌላ ፎቶ ጠየቀን ። በጥቁር እና ነጭ የተንሳችውን ፎቶ አቀበለችው ። የፊቷ ቅርፅ ብቻ ነበር የሚታየው ። አስተናጋጁም : "ይህ ፎቶ ለፓስፖርት አይሆንም ። ባለቀለም ፎቶ ነው የምንፈልገው ። ፀጉር እና ትከሻሽ መታየት አለበት " አላት ። እሷ ግን ከዚህ ፎቶ ውጭ ሌላ ፎቶ እንደማትሰጠው አስረግጣ ነገረችው ። በሱ በኩል የማይሳካ መሆኑን ስታውቅ ሌላ የቦታው ሰራተኛ ዘንድ ሄድን ። ቀጥሎም ሌላ ሀላፊ ዘንድ ሄድን ። ሁሉም ፀጉሯ ተገልጦ የተነሳችው ፎቶ ካልሆነ በስተቀር አንቀበልም አሉ ። ባለቤቴ ግን በእንቢታዋ ፀናች ። እነሱም በዚህ ፎቶ እንደማያስተናግዷት ገለፁላት ። ፎቶውን እንዲያፀድቅላት ብለን ዋናዋ ሀላፊ ዘንድ ሄድን ። ብዙ ጣረች ፤ አስረዳቻት ፤ ተከራከረች ፤ ሞገተቻቸው ። "የሚፈለገው ፊት ነው ። ምንድንነው ልዩነቱ ? ስትፈልጉ ፎቶዎችን አነፃፅሯቸው " አለቻቸው ። ሀላፊዋም አሰራራቸው ይህን የማይፈቅድ መሆኑን አስረዳቻት ። በመሆኑም እንደማትቀበላት ገለፀች ። ባለቤቴም " ከዚህ ፎቶ ውጭ ሌላ በፍፁም አላመጣም " አለቻት። ታዲያ እንዴት ይሁን ፓስፖርቱን የምናሳድሰው??????🤔🤔🤔🤔 ይቀጥላል.................. Join 👉@din_achen ለአስተያየት እና ሀሳብ 👇 @IbtiN
Показать все...
ሩሲያዊቷ ሱመያ ክፍል 3 አይታ የማታውቀውን ነገር በማዕከሉ ውስጥ ተመለከተች ።በማዕከሉም ፊቷን የሸፈነች ሙስሊም ሴት አየች ። ኒቃብ የለበሰች ሴት ሴት ለመጀመሪያ ጊዜ ማየቷ ነው ። እጅግ ገረማት ። ወደ ባለቤቷ ኻሊድ በመዞር ጠየቀችው " ለምንድንነው ይህች ሴት በዚህ መልኩ የለበሰችው ? ፊቷ ላይ የሆነ ነውር ነገር ኖሮ አለመታየት ፈልጋ ነው ወይንስ?...." አለችው ። እሱም " አይደለም ይህች ሴት ሒጃብን አላህ (ሱ.ወ.) ሙስሊም ሴቶች እንዲለብሱት ባዘዘው መልኩ መልበሷ ነው ። የአላህ መልዕክተኛም በዚህ መልኩ ነው እንዲለበስ ያስተማሩት ።" በማለት አስረዳት ። ለጥቂት ጊዜ ዝምታን መረጠች ። ቀጥሎም " አዎን ትክክለኛውና አላህ ከኛ የሚፈልገው ኢስላማዊ አለባበስ በዚህ መልኩ ይመስለኛል " አለችው ። " እንዴት አወቅሽ ?" አላት ። " እዚህ የንግድ ማዕከል ከገባሁበት ጊዜ ጀምሮ የሁሉም አይኖች ወደኔ ሲወረወሩ ልብ ብያለሁ በዐይናቸው ቆርሰው እየጨረሱኝ እስኪመስለኝ ድረስ ። በመሆኑም ፊትን መሸፈን ግዴታ መሆን አለበት ። እንደውም በዚህ ማዕከል የዚህ ዓይነቱን ፊት የሚሸፈንበት ሒጃብን ሳልይዝ መውጣት የለብኝም ። የምገዛበትን አሳየኝ ።" በማለት ጠየቀችው ። እሱም " እንደ እናቴ እና እህቶቼ ሁሉ በዚህ ሒጃብሽ ቀጥይ " አላት ። እሷ ደግሞ " አይሆንም አላህ የሚፈልገውን ሒጃብ ነው የምፈልገው ።"አለችው ። ቀናቶች አለፉ ። ወጣቷም በዲኗ እየጠነከረች ፤ ኢማኗም እየጨመረ መጣ። ከዕለታት አንድ ቀን የመጣችበትን ፓስፓርቷን ተመለከተች ። ጊዜው ሊጠናቀቅ ተቃርቧል ፤ ስለሆነም መታደስ አለበት ። መታደሱ መልካም ቢሆንም ጉዳዩን ከባድ የሚያደርገው ፓስፖርቱ መታደስ ያለበት በትውልድ ከተማዋ መሆኑ ነው ። ስለሆነም ወደ ሀገሯ ሩሲያ መሄድ ግድ ሆነ ። ካልሆነ የመቆያ ቪዛዋ ህገ ወጥ ነው የሚሆነው ። ኻሊድ ከሷ ጋር ለመሄድ ወሰነ ። እሷም ያለ ሙሕሪም መሔድ እንደምትችል አመነች ። ብቻዋን መሄድም አልፈለገችም ። የሩሲያ የአየር መንገድ የሆነውን አውሮፕላን ተሳፈሩ ። ከነ ኒቃቧ ነበር የተሳፈረችው ። ከባሏ ጎን ኩራት እየተሰማት ተቀመጠች ። ኻሊድ እንዲህ አላት "በሂጃብሽ የተነሳ ችግር እንዳያጋጥመን እፈራለሁ "አላት ።እሷም "ሱብሀንአላህ! እነዚህን ኢ_አማንያን እንድታዘዝ እና እንድክድ ትፈልጋለህን ? ወላሂ ፈፅሞ አይሆንም ፤ አላደርገውም ያሉትን ይበሉ " አለችው ። ሰዎች በግርምት ወደርሷ ይመለከታሉ ። አስተናጋጆች ምግብ ማቅረብ ጀመሩ ። ከምግቡ ጋር መጠጥ ይቀርብ ነበር ። የጠጡት ሞቅ እያላቸው ሲሄድ እሷን መናገር እና እሷን በነገር መውጋት ጀመሩ ። ከዚህም ከዚያም ያሾፉባት ጀመር ። አንዱ ይሳለቃል ፤ ሌላው ይስቃል ፤ ሌላው ደግሞ ያላግጣል ። ኻሊድ ይመለከታቸዋል ። ሆኖም ግን በራሳቸው ቋንቋ ያወሩ ስለነበር የሚሉት አይገባውም ። እሷ ግን እየሰማች እና እየሳቀች የሚሉትን ሁሉ ትተረጉምለታልች ። በዚህን ጊዜ ኻሊድ ተቆጣ ....ይቀጥላል.......... Join👇 @din_achen ለአስተያየት እና ሀሳብ👇 @IbtiN
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.