cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

𝑦𝑜𝑢𝑛𝑔 𝑥'𝑠𝑡𝑒𝑟

Youtube📍Arada squad https://youtube.com/c/ARADASQUAD @Hot_beby1

Больше
Эфиопия9 927Амхарский8 680Категория не указана
Рекламные посты
336
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

#የዩንቨርሲቲ_ቀልዶች ያኔ ተማሪ እያለን በተለይ ግቢ ውስጥ በዙ ይቀለዳል አይደል?? ለዛሬ አንዱን ላካፍላችሁና እናንተ ደግሞ የራሳችሁን ትጨምራላችሁ። -------------------------- ፈጣሪ አህያን ፈጠረና እንዲህ አለው…. አህያ ትሆናለህ፡፡ ሸክሞችን በጀርባህ በመሸከም ፀሐይ ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ ያለመታከት ትሰራለህ፡፡ የምትመገበው ደግሞ ሳር ነው፡፡ ምንም አይነት ኢንቴለክት(የማሰብ፣የማመዛዘን ችሎታ) የለህም፡፡ እናም 50 ዓመት ትኖራለህ፡፡ አህያው እንዲህ ሲል መለሰ… አህያ እሆናለሁ ችግር የለውም ነገር ግን 50 ዓመት በጣም ብዙ ነውና ሃያውን ብቻ ስጠኝ፡፡ እግዚያብሔርም የፍላጎቱን ሰጠው፡፡ _ ፈጣሪ ውሻን ፈጠረና እንዲህ አለው…. የሰውን ልጅ ቤት ትጠብቃለህ፡፡ የሰው ልጅም እውነተኛ ጓደኛ ትሆናለህ፡፡ ከጌታህ የሚጣልልህን ፍርፋሪ ትመገባለህ፡፡ እናም 30 ዓመት በሕይዎት ትኖራለህ፡፡ ውሻም ትባላለህ፡፡ ውሻው ሲመልስ… ጌታየ 30 ዓመት እጅግ ብዙ ነው አስራ አምስቱ ዓመት ይበቃኛል አለ፡፡ ፈጣሪም የፍላጎቱን ሰጠው… _ ፈጣሪ ዝንጀሮን ፈጠረና እንዲህ አለው…. ዝንጀሮ ትሆናለህ፡፡ በዛፎች ቅርንጫፍ ወዲያና ወዲህ እየተንጠላጠልክ ትርኢት ትሰራለህ፡፡ በድርጊትህም አስገራሚ ትሆናለህ እናም 20 ዓመት ትኖራለህ፡፡ ዝንጀሮው ሲመልስ… ሃያ ዓመት መኖር በጣም ብዙ ነውና አስሩ ብቻ ይበቃኛል አለ፡፡ ፈጣሪም የሚኞቱን ሰጠው፡፡ __ በመጨረሻም ፈጣሪ ሰውን ፈጠረና እንዲህ አለው…. የሰው ልጅ ትባላለህ፡፡ በምድር ላይ ካሉት ፍጡራን አመዛዛኝ፣ አሳቢና ምክኒተዊ ፍጡር አንተ ብቻ ነህ፡፡ በሌሎች ፍጡራን ላይ ለመንገስም የማሰብ ችሎታህን ትጠቀማለህ፡፡ በሌሎች ፍጡራን ላይ ነግሰህም 20 ዓመትን ትኖራለህ አለው፡፡ የሰው ልጅ የተሰጠውን የማሰብ ችሎታው ተጠቅሞ ሲመልስ… ጌታየ እሽ! የሰው ልጅ እሆናለሁ፡፡ ነገር ግን ሃያ ዓመት መኖር እጅግ ሲበዛ ትንሽ ነው፡፡ ስለሆነም ሠላሳ ዓመት አህያው የተቃወመውን፣ አሥራ አምሥት ዓመት ውሻው አልፈልገውም ያለውን እናም ደግሞ አስሩን ዓመት ዝንጀሮው የማይፈልገውን ስጠኝ ሲል ጥያቄውን አቀረበ (ከራሱ ጋር የሌሎችን ደማምሮ 75ዓመት አደረሰው)፡፡ ፈጣሪም የፍላጎቱን ሰጠው… ___ እናም የሰው ልጅ ሕይዎት ከዛን ጊዜ ጀምሮ 20ውን ዓመት እንደ ሰው ይኖራል (ሳያገባ ትዳር ሳይመሰርት ለአንድ ሆዱ ሲኖር ማለት ነው)፡፡ ከዛ በኋላ አግብቶ ትዳር ሲመሰርትና የቤተሰብ ኃላፊ ሲሆን 30ውን ዓመት ልክ እንደ አህያው የአህያውን ሚና ወስዶ ይኖራል፡፡ የቤተሰብ ኃላፊነቱን ይሸከማል፤ የአባወራነቱን ኃላፊነት ለመወጣትም ቀን ከሌት ያለመታከት ይሰራል፡፡ ቀጥሎም ልጆቹ እያደጉ ሲሄዱ 15ቱን ዓመት ልክ እንደውሻው አይነት ኑሮን ይመራል፡፡ ቤቱን ይጠብቃል ይንከባከባል፣ ከልጆቹ ተርፎ የሚሰጠውንም ይበላል፡፡ አርጅቶ እየሸመገለ በሄደ ጊዜም ጡረታ ይወጣና 10ሩን ዓመት እንደ ዝንጀሮው አኗኗር ዘይቤ ይኖራል፡፡ ልጆቹን አጎራብቶ ከአንደኛው ቤት ወደ ሌላኛው ቤት በመዘዋወር የልጅ ልጆቹን በማጫወት፣በማዝናናት ያለፉ ዘመናትን ታሪክ በማውራት ያሳልፋል፡፡ ሕይዎት ማለት ይች ናት! 😃😃 😊 @amprincedavid 😄
Показать все...
ሁለት ዝንቦች የባለጌ ነገር ሲያደርጉ ፍሊት ልነፋባቸው ስል ወንዱ ዝንብ አሳዘነኝ::ምን አልባት እቺን ቀን ለማግኘት እኮ ብዙ ቀን ጀንጅኗት ስጦታ ሰጥቷትም ይሆናል አልኩና ትቻቸው መሄድ ጀመርኩ!! ግን 1 ሀሳብ ብልጭ አለብኝ . . . ምንአልባት እየደፈራት ቢሆንስ??🤔🙈 🤪 @amprincedavid 😎
Показать все...
እናቴ መርፌ ውስጥ ክር እንዳስገባላት ጠራችኝ። በዚሁ ቅፅበት የአንድ ሰው ምክር ትዝ አለኝ ፦ «እናትህ መርፌ ውስጥ ክር እንድታስገባላት ከጠየቀችህ ተቀብለህ ወዲያውኑ አታስገባው። ይልቁንም ያረጀችና እድሜዋ የገፋ  እንዳይመስላትና  ቀልቧ እንዳይሰበር አውቀህ ታግለህ ታግለህ አስገባው» ብሎ መክሮኝ ነበር ። እኔም ማስገባቱ  ቀላል እንዳልሆነ እየነገርኳት ጥቂት ደቂቃዎችን ታገልኩ ። በድንገት አንድ ጥፊ ፊቴ ላይ አረፈ 👋 «ድሮውንም እውር ያደረገህ ይሄ ሞባይልና ፌስቡክ ነው» đŸ˜˘đŸ˜˘đŸ˜ 😳 @amprincedavid 😅
Показать все...
#ዐቢይ_ጾም ጾም ማለት ሰውነትን ከሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ መከልከል፣ ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነዉ፡፡ ጌታችን መጾም ሳያስፈልገው የጾመው በጾም መሣሪያነት ዲያቢሎስን ድል ታደርጋላችሁ ሲለን ነው፡፡  እርሱ ድል አድርጎታል ካልጾሙ ካልጸለዩ ሰይጣንን ድል ማድረግ እንደማይቻል ጌታ አስተምሮናል፡፡ ጾም ፊትን ወደ እግዚአብሔር ማቅናት እንደሆነ በሰብአ ነነዌ ታውቋል እነዚህ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር የተመለሱት በጾም ነውና፡፡ ወደ እግዚአብሔር በጾም በጸሎት የተመለሱ ድኅነትን እንዳገኙ ሁሉ ያልተመለሱ ደግሞ ጠፍተዋል፡፡ ለምሳሌ ሰብአ ሰዶም ገሞራ እንደ ነነዌ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ባለመመለሳቸዉ እሳት ከሰማይ ወርዶ አቃጥሎ አጥፍቶአቸዋል (ዘፍ ፲፱፡፳፫)፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ከሚጾሙት 7ቱ አጽዋማት አንዱና ትልቁ ዐብይ ጾም ይባላል፡፡ ይህ ጾም ዐብይ ጾም ፣ ጾመ ኢየሱስ ፣ ጾመ ሁዳዴ ፣ አርባ  ጾም በመባል ይታወቃል ፡፡ ዐብይ ጾም መባሉ ትልቅና ታላቅ ጾም መሆኑን ለማሳወቅና አምላካችን ለሰዎች በመጀመሪያ አብነት ለመሆን የጾመው ስለሆነና ቀኖቹም ከሌሎች አጽዋማት በቁጥርም ከፍ ስለሚል ነዉ፡፡ ጾመ ኢየሱስ መባሉ በቅዱስ መጽሐፍ እንደተጠቀሰ ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው በመሆኑ ጾመ ኢየሱስ ተብሏል (ማቴ ፬᎓፩)። ሁዳዴ ጾም መባሉ ይህ ስያሜ የወጣው ሁዳድ ከሚለው ሲሆን ሁዳድ ማለት ሰፊ የእርሻ ቦታ ማለት ሲሆን ዐብይ ጾምም የሥላሴን ልጅነት ያገኙ ክርስቲያኖች በሙሉ ሰፊና ትልቅ ወደሆነው ካገኙት የማያጡት ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚያደርስ ሁሉም ምዕመን የሚጾመው ጾም በመሆኑ አባቶቻችን ጾመ ሁዳዴ ብለዉ ሰይመውታል፡፡  40 / አርባ ጾም ይኸውም ጌታ ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ ሔደ 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾመ፣ ጸለየ ብሎ ቅዱስ መጽሐፍ በማቴዎስ ፬፤፪ እንደ ተጻፈ ጌታ አርባ ቀን የጾመው ጾም ስለሆነ ነው፡፡ ዐብይ ጾም ሦስት ክፍሎችና ስምንት ሳምንታት ያሉት ሲሆን እነሱም ፡-ሦስቱ ክፍሎች የተባሉት እነዚህ ናቸዉ፡፡ ዘወረደ ( ጾመ ሕርቃል )፡-ይህም ጾሙ ከሚገባበት ሰኞ ጀምሮ እስከ እሁድ ድረስ  ያለዉ ቀን ነዉ፡፡ የጌታ ጾም፡-ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣእና ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው 40 ቀን ነው፡፡ ሕማማት ፡- ይህም ጌታችን በአልአዛር ቤት ለማዕድ ከተቀመጠበት የሆሣዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ሥዑር  ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት ነው፡፡ ይህም  7+40+8 = 55 ቀን ማለት ነዉ፡፡  የአብይ ጾም ስምንት ሳምንታት ፩- ዘወረደ ፪- ቅድስት ፫- ምኩራብ ፬- መጻጉዕ ፭- ደብረ ዘይት ፮- ገብርኄር ፯- ኒቆዲሞስ ፰- ሆሣዕና የሰው ልጆች ጠላት የጨለማ ገዢ የሆነው ዲያቢሎስን በጾም እንደምናሸንፈዉ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡ ጾም ሥጋችንን ለነፍሳችን የምናስገዛበት ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት የጽድቅ መንገድ ለሥጋ ጤንነትም ቢሆን አስፈላጊያችን የሆነ አንዱና ዋነኛዉ የጽድቅ እቃ ጦራችን ነው፡፡ሆኖም የጾም  ወቀት ሲመጣ አቀበት የሚወጡ ይመስል የሚፈሩትና የሚያማርሩት ሳይሆን እንኳን መጣልን ተብሎ በጉጉት የሚናፈቅ መሆን አለበት፡፡ በተለይ አሁን በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየደረሰ በሚታየዉ አስቸጋሪ ፈተና እያንዳንዳችን ልባዊ ጾም በመጾም ልዑል እግዚአብሔር የጸሎታችን ምላሽ እንዲሰጠን እንማጸናለን፡፡ ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን፡፡
Показать все...
00:15
Видео недоступноПоказать в Telegram
🙏🏻ሚካኤል አባቴ አንተ ጠብቀኝ 🙏🏻12🙏🏻 🙏🏻ተመስገን 🙏🏻 @amprincedavid 🙏🏻
Показать все...
1.59 MB
00:03
Видео недоступноПоказать в Telegram
1.40 MB
Yemitekash Teffa - Geremew Asefa.m4a5.34 MB
Bey Endashash - Geremew Asefa.m4a4.46 MB
Kerbesh Eyegn - Geremew Asefa.m4a4.67 MB
Chir Ale - Geremew Asefa.m4a6.04 MB