cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

The Bored Therapist

- በአምላክ አይሬ ገብረዮሐንስ -

Больше
Рекламные посты
975
Подписчики
+124 часа
+27 дней
+1030 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

I have this theory (or should I say hypothesis?) ሁላችንም በረሀ ላይ ነን! ትንሽ ስህተት እንሠራለን ከዚያ ያንን ማረም እንዳለብን ይገባናል ግን ቀጥታ ማረም ዋጋ እንዳያስከፍል እንፈራለን። ስለዚህ የአንደበት ወይም የአኳኋን ውሸት ውስጥ እንገባለን። ይህ ውሸት ታድያ በእኛ ሕይወት ላይ ትክክለኛውን መኖር ያስጥለንና ሰንሰለቱ እስኪያልቅ ዙረቱን እስክንዘልቅ ድረስ ማስመሰል ውስጥ እንከርማለን። እየሆንን ያለነው ነገር ሁሉ እኛ አይደለንም እኛ ለሠራነው ቅጽበታዊ ስህተት ምላሽ እንዲሰጥ የቀጠርነው ጋኔን ነው። ያለነውም የኑሮአችን ለምለም መስክ ላይ አይደለንም። ከመስመር ወጥተናል። ብክነት ውስጥ ነን። በረሀ እንበለው? እኛነታችንን እየኖርን ሳይሆን ከኑሮው መስመር ወጥተን እየተሽከረከርን ነው። ዕድል ቀንቶን ቶሎ ከተሳካ ሕይወት ካቆመበት ይቀጥላል። እስከ ቀጣዩ ስህተት ድረስ እንኖራለን። ከዚያ እንደገና። ከዚያ እኛ። ከዚያ ጋኔኑ። አዙሪቱ። ከዚያ ወደ መንገዳችን። ከዚያ ወደ ምድረበዳ። ይቀጥላል። ለምሳሌ አብረን ነን ከጓደኞቻችን ጋር። የሆነ ነገር መግዛት ፈልገዋል። እኛ ብር መያዝ ፈልገናል። አልገዛም ማለት ግን አስነዋሪ መስሎ ተሰማን። ስለዚህ ይህን ነገር አልወድም እንላለን። ይህ ንግግራችን ከዚያ ቀን ወዲህ የሚኖረንን ምግባር ይቀርጸዋል። ምራቃችን እየፈሰሰ እንኳ እንደማይወድ ሆነን ማለፍ ይኖርብናል። አዲስ ማንነት ይጫንብናል። እንትን የማይወደው ልጅ! ወይም በንግግር መሀል ለአንድ ሰው ያለን ንቀት ይገለጻል። እንደሚታወቀው አፍ እግር አይደለም። ወለምታው በቅቤ አይታሽም። ይህን ንግግራችንን እውነቱን ማብራራት አሳፋሪ ሆኖ ይሰማናል። ማመን ያዳግተናል። ስለዚህ ባልሰማ እናልፈዋለን (እኛው ተናግረን)። ከዚያ ያ ሰው የሰማው ከጆሮው እስኪወጣ ድረስ በተግባራችን እና በምላሳችን የቀደመውን የሚሽር ጉዳቱን የሚክስ ቀናነታችንን የሚመሰክር ሁኔታን ለመግለጥ እንፍጨረጨራለን። (የአፍ ወለምታ በምግብ ቅቤ አይታሽም 😁 በማስመሰል አዙሪት ቅቤ ነው የሚታሸው) ይህን ሁሉ ከባድ የሚያደርገው እውነት ቢሆን እንኳ ቀጥታ የሚደረግ ሳይሆን እግረ መንገድ በሚመስል መንገድ ዋና ትኩረታችን ሌላ ጋር በሚመስል ምንም ስህተት እያስተባበልን እንደሆነ በግልጽ በማይናገር ሁኔታ ስለምናደርገው ነው። ብቻ ምንድነው? እኚህ ጥቃቅን ነገሮች ትልቁን ሕይወታችንንም የሚገልጹ ቢሆንስ? በትልቁ የሕይወት ጉዞአችን ያለነው እዚያ አዙሪት ላይ ቢሆንስ? ቅድመ አያቶቻችን ለሠሩት ስህተት እያስተባበልን? ተሳስተው አንዱን ፈረንጅ ሰድበውት ይሆናልኮ ዛሬ መሽቆጥቆጥ ያበዛነው ለነጭ። ብቻ ድፍን ሰባ ዓመታችን ዙር እየጠመጠምን (ዙሪያ ጥምጥም እየሄድን) ቢሆንስ? ወይም ደግሞ እኚህ ጥቃቅኑ ቢደመሩስ ምን ያህል የሕይወታችን ክፍል በማስመሰል ባከነ ማለት ነው? እኛ ሳንኖር? በቀን ሰላሳ ደቂቃ በሰባ ዓመት ስንት ዓመት ነው? የኢትዮጵያ ወጣቶች አንድ ላይ ሲደመርስ ስንት አምራች ኃይል ነው እየጠፋ ያለው? ዋናው ነገር: እውነት መነጋገር የምንችልበት ሕይወት ካለን ምን ያህል ዕድለኞች ነን!
Показать все...
24
Hello friends, hope y'all had a great holiday. A good friend of our channel has now created a new chaotic channel and invites all people especially those interested in.. "Reading, writing, thinking and challenging ideas. And people who appreciate the beauty of poetry and art in general." Follow her at: https://t.me/wildernessofthesoul
Показать все...
Wilderness Of The Soul

A place of solace for the wandering and forgotten @Cr00kedMind

7
Repost from N/a
Фото недоступноПоказать в Telegram
You don't always need food. @becomingminimal
Показать все...
🤣 7😁 2 1
Hey friends, can you suggest good resources to study Ethiopian Feminism?
Показать все...
😁 4 3🤣 3
ተገኝታለች። ደህና ናት። 😊✨
Показать все...
33
Фото недоступноПоказать в Telegram
በዚ ፎቶ ላይ የምትመለከቷት ተማሪ አስቴር ፋንቱ ስትባል በሀዋሳ ዮንቨርሲቲ የመጀመሪያ አመት ተማሪ ስትሆን ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው ማክሰኞ መጋቢት 10 ነው። በማንኛውም አጋጣሚ አህታችን ልትገኝበት የምትችልበትን ቦታ መጠቆም የምትችሉ ሁሉ ከዚህ በታች ባለው ስልክ ቁጥር መደወል ትችላላቹ። Phone no +251964938850 +251921632467
Показать все...
😢 10 4🤯 2
እናቷን ጠላቻት። የአባቷን ሚስት ጠላቻት። ምክንያት ይኖራታል። ማብራሪያ ይኖረዋል ይህ ጥላቻ። እናቷን የጠላቻት እናቷ የጠላቻት ስለመሰላት ነው። በልቧ የምታስበው እንዲህ ነው። እኔ የአባቴ ልጅ ነኝ። እርሱን እወደዋለው። ብዙ ስህተት ቢሠራም ለእኔ ግን ደግ ነው። እሱን ስትጠላው ልቤ ይታመማል። ያ አባትሽ ባለችኝ ቁጥር የነፍሴ ሥጋ ይተረተራል። ስታማው በሰማሁ ልክ አጥንቶቼ ይሰበራሉ። ከእርሱ ጋር የመሆኗን ዕድል ስትረግም መንፈሴ ይታወካል። እኔን ወድሻለው ብትለኝ እንዴት ልመን? እኔኮ ከምትጠላው ባሏ ያስተሳሰርኳት ሰንሰለት ነኝ። በራ እንዳታመልጥ የተያዘችበት ወጥመድ ነኝ። እኔኮ የምትወደውን ሕይወት ያለመኖሯ ማህተም ነኝ። እኔኮ ከተጸየፈችው ምንጭ የፈለቅኩ ድፍርስ ውሃ ነኝ። ዓይኖቼኮ የአባቴ ናቸው። ግማሽ ማንነቴ እኮ እርሱ ነው። ወደሱ የተሰነዘረ የጥላቻ ፍም ሁሉ ይለበልበኛል። ፍላጎቷ ግን እንደምትወደኝ እንዳስብ ነበር። ፍሪውድ ያስቀኛል። ፍሪውድ ያስቀኛል። በእናቴ ቀንቼ አይደለም። የአባቴን አካል ተቀምቼ አይደለም። እንዲህ እንዲህ ትላለች። እናቴ ትጠላኛለች ትላለች። እናቷን ትጠላለች። #family #የሰውቤት #dark
Показать все...
11
ሆደ ሰፊ ነኝ: አንዳንዴ ሆዴን እንደ ኮት ብከፍተው ከውስጤ አንድ ጋሻ መሬት፣ ሁለት ኮረብታዎች፣ አንድ ጅረት፣ ስድስት ሚዳቆኤዎች፣ አራት ኤሊዎች፣ መዓት ንቦች፣ ሰላሳ ላሞች፣ አንድ የበግ ወጥ፣ አንድ ካፌ ላቴ እና መዓት ኩበት ተዘርግፎ ይወጣል። ለምጠላው ትዝታ አለኝ። 🍵 መረቅ፣ አዳም ረታ 📚 #bookquotes #random
Показать все...
🤣 21 8
ዕንባ ጠባቂ ተቋም ነው የሚያስፈልገን ወይስ በደል ጠባቂ? ከተበደልኩማ እሪ ብዬ ነው ማለቅሰው። ማለት ወንድ ስለሆንኩ ከሰው ገለል ብዬ። ✌️🏽
Показать все...
🤣 4
ለሰው ያለኝ አመለካከት፣ ለሕይወት ያለኝ ጉጉት፣ በትላንት ያለኝ ቁጭት፣ ለነገ ሚሰማኝ ተስፋ፣ በአጠቃላይ የአእምሮዬ ጤና ሁሉ ምግብ ከመብላቴ በፊትና በኋላ የተለያየ ነው።
Показать все...
😁 50 3
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.