cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

🇪🇹የሕግ ጉዳይ

Legal matter, Ethiopia Legal Info, #ጠበቃና የሕግ አማካሪ We offer you Reliable services with a very high sense of responsibility. #ከጠበቃ ጋር ተነጋገሩ @TalkToLawyer [email protected]

Больше
Рекламные посты
5 086
Подписчики
Нет данных24 часа
+247 дней
+17230 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የቤት_ኪራይ_ቁጥጥር_አዋጅ_ማሰልጠኛ_ማንዋል13202016.pptx1.56 MB
የኢትዮጵያ ፌደራል የጠበቆች ማኀበር ፕሬዚዳንት፤ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴን አንድነት እና የሥራ ግንኙነት በተመለከተ ከአዋጅ ቁጥር 1249/13 ድንጋጌዎች አንፃር የተዘጋጀ ማብራሪያ ፤
Показать все...
Explanatory note on Presidents ExCom 2015.pdf9.80 KB
Показать все...
ለሕዝብ ጥቅም ክስን ማንሳት?

#በሰለሞን እምሩ ክሱን ማንሳት ለሕዝብ ጥቅም ይበጃል ለማለት ከተቀመጡት ዘጠኝ መሰፈርቶች መካከል አንዱ “ተከሳሹ በዕድሜ መጃጀት ወይም በማይድን በሽታ ወይም በአዕምሮ ልልነት ምክንያት ጉዳዩን መከታተል የማይችል እንደሆነ ነው” ተብሎ በመመሪያው አንቀፅ 5 (3) ላይ ተመልክቷል፡፡ አንድ ተከሳ…

Показать все...
ለሕዝብ ጥቅም ክስን ማንሳት?

#በሰለሞን እምሩ ክሱን ማንሳት ለሕዝብ ጥቅም ይበጃል ለማለት ከተቀመጡት ዘጠኝ መሰፈርቶች መካከል አንዱ “ተከሳሹ በዕድሜ መጃጀት ወይም በማይድን በሽታ ወይም በአዕምሮ ልልነት ምክንያት ጉዳዩን መከታተል የማይችል እንደሆነ ነው” ተብሎ በመመሪያው አንቀፅ 5 (3) ላይ ተመልክቷል፡፡ አንድ ተከሳ…

#Ethiopia ማንኛውንም ሰው #ከሀገር_እንዳይወጣ የማገድ ስልጣንን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለህ/ ተ/ ም/ ቤት  ቀርቧል። የአዋጅ ማሻሻያው ምን ይዟል ? ማሻሻያው ማንኛውንም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ የማገድ ስልጣን ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተርነት ይሰጣል። ነባሩ ህግ ምን ይላል ? " ማንኛውም ሰው #ከኢትዮጵያ_እንዳይወጣ ሊታገድ የሚችለው በህግ መሰረት #በፍርድቤት ሲታዘዝ ብቻ ነው " ይላል። ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበው የአዋጅ ማሻሻያ በነባሩ ህግ ላይ የተቀመጠውን የፍርድ ቤትን " #ብቸኛ_ስልጣን " የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ በተጨማሪነት #ያጋራ ነው። ማሻሻያው የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ፦ ⚫️ ከሚመለከታቸው የደህንነት አገልግሎት እና ህግ አስከባሪ አካላት ከሚያገኘው መረጃ ወይም አገልግሎቱ በራሱ ከሚያገኘው መረጃ በመነሳት ፤ ⚫️ በብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ሊቀለበስ የማይችል ግልጽና ድርስ የሆነ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል ሁኔታ መኖሩን ሲያምን፤ ማንኛውም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ ማገድ ይችላል ሲል ደንግጓል።  የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፤ " ከሀገር እንዳይወጣ ያገደውን ሰው ይዞ የሚያቆይ ከሆነ ፍ/ቤት መቅረቡን ማረጋገጥ አለበት "ም ይላል የአዋጅ ማሻሻያው።  ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣን ላይ ማሻሻያ የተደረገው ፤ በነባሩ ድንጋጌ ምክንያት እየደረሰ ያለውን " ከፍተኛ ጉዳት " ለመቅረፍ እንደሆነ በማሻሻያው ላይ ሰፍሯል። አሁን በስራ ላይ ባለው አዋጅ መሰረት " ከፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ እስኪገኝ ድረስ በብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ወይም ሊያደርሱ የሚችሉ ሰዎች ከሀገር እየወጡ ከተጠያቂነት እያመለጡ በሀገራችን ብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው " ሲል የረቂቅ አዋጁ ገልጿል። በሌላ በኩል ፦ ማሻሻያ አዋጁ " #አስተዳደራዊ_ቅጣት " አንቀጽ ይዟል። " ከጊዜ ወደ ጊዜ በህገ ወጥ መንገድ በሀገራችን ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች እየተበራከቱ፤ በህገ ወጥ ድርጊቶች እየተሳተፉ ከፍተኛ ችግር እየፈጠሩ በመሆኑ በአስተዳደራዊ ቅጣት በመቅጣት ከህገ ወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ አስፈላጊ ነው " ሲል ያስረዳል። በዚህም በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የውጭ ሀገር ዜጎችን " በጥቁር መዝገብ እንዲመዘገቡ እና ከሀገር እንዲወጡ ማድረግ ወደ ህጋዊ ስርዓት እንዲመጡ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ የሆነ ሚና " እንዳለው ተብራርቷል። #የሚኒስትሮች_ምክር_ቤት በሚያወጣው ደንብ አማካኝነት፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መ/ቤት አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጥል በአዋጅ ማሻሻያው ስልጣን ተሰጥቶታል። " ይህን አዋጅ አሊያ በዚህ አዋጅ መሰረት የወጣ ደንብ ወይም መመሪያን የጣሰ ማንኛውም ሰው ፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበታል " ይላል ማሻሻያው። Credit: #EthiopiaInisider  #JournalistTesfalemWoldeyes @tikvahethiopia
Показать все...
👍 3 2
ስለ ኢትዮጵያ የቤተሰብ ህግ የምንዳስስ ይሆናል፡፡ በዚህ ክፍል ላይ ስለ ጋብቻ አይነቶች እና ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች እንመለከታለን፡፡ ቤተሰብ ትልቅ ተቋም በመሆኑ የህግ ጥበቃ የሚደረግለት ተቋም ነው፡፡ የቤተሰባዊ ግንኙነት ከሚመሰረትባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ጋብቻ ነው፡፡ ጋብቻን እና ተያያዥ ጉዳዮች በፌደራል ደረጃ የሚዳኙት ወይም የሚገዙት በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ዓ.ም ነው፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረት በሶስተ አይነት መልኩ ጋብቻ ሊፈፀም እንደሚችል ተቀምጧል፡፡ እነዚህን የጋብቻ አይነቶች ከመመልከታችን በፊት ጋብቻ ለመፈጸመም ሊሟሉ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎችን እናያለን፡፡፡ አንድ ሰው ጋብቻ ለመፈፀም በቅድሚያ ሊያሟሏቸው የሚገቡ አስፈላጊ እና አስገዳጅ ቅድመ ሆኔታዎች አሉ፡፡ የመጀመሪያ በተጋቢዎች መካከል ነጻ ፍቃድ መኖር ነው ፡፡ 2ኛው ተጋቢዎች 18 አመት እድሜ የሞላቸው መሆን ያለበት ሲሆን በልዩ ሁኔታ ግን በፍትህ ሚንስትሩ ፍቃድ ሲሰጥ 16 አመት ለጋብቻ የተፈቀደ ጊዜ ይሆናል፡፡ 3ኛው ደግሞ በተጋቢዎች መካከል የስጋ እና የጋብቻ ዝምድና አለመኖር ነው፡፡ 4ኛው ተጋቢዎቹ በሌላ ጋብቻ ውስጥ አለመሆናቸው ወይም በጋብቻ ላይ ሌላ ጋብቻ ያለመፈጸም ነው፡፡ 5ኛው ተጋቢዎች በፍርድ ያልተከለከሉ መሆን አለባቸው 6ኛው እና የመጨረሻው ቅድመ ሁኔታ ለሴት ልጅ አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ቀሪ ከሆነ በኋላ ወይም ጋብቻው ከፈረሰ በኋላ ለ180 ቀን ወይም ለ 6 ወር ያህል ሌላ ጋብቻ እንዳትፈፅም የተደነገገ ክልከላ ነው፡፡ ቀደም ሲል እንደገለፅኩላችሁ ሶስት የጋብቻ አይነቶች አሉ፡፡ 1ኛ. በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈፀም ጋብቻ ነው፡፡ ይህም ማለት ወሳኝ ኩነት በመሄድ የሚፈፀም ጋብቻ ነው፡፡ 2ኛው. በሃይማኖት ስርአት የሚፈፀም ጋብቻ ሲሆን ይህ ማለት ደሞ በቤተክርስቲያን ስርአት፤ በሼርያ ህግ እና በሌሎችም የሃይማኖት ስርአቶች ሊፈጸም የሚችል የጋብቻ አይነት ነው፡፡ 3ኛው እና የመጨረሻው የጋብቻ አይነት ደግሙ በባህላዊ ሰርአት የሚፈፀም ጋብቻ ሲሆን ይህም በተለያዩ አከባቢዎች በሚገኙ ባህላዊ ስርአቶች የሚፈፀም የጋብቻ አይነት ነው፡፡ በቀጣይ ክፍል ደግሞ ስለጋብቻ ውጤቶች የማቀርብላችሁ ይሆናል፡፡ የነጺ ሎው via Alternative legal enlightenment/ALE* አማራጭ የሕግ እውቀት🔴 #አለሕግ #Alehig @NegereHig https://t.me/NegereHig
Показать все...
ነገረሕግ NegereHig

About laws Ethiopia.......ስለ ኢትዮጵያ ህግጋት.... ስለህጎችና ህግ ጉዳዮች ብቻ.......የህግ ነገሮችን It is All About Laws....Only Law Matters...... It is about law. ስለህጎች....... ጠበቃና የህግ አማካሪ ቢሮ አዲስ አበባ @AboutLaws_bot

👍 3
Показать все...
Legal Manager - Re-Advertising

Bachelor's Degree in Law or in a related field of study with relevant work experience, out of which 2 years in a managerial level Duties & Responsibilities: - Provide updates and legal briefs on all changes to laws and regulations within Ethiopia - Planning, Organizing, coordinating and monitoring the legal service department

👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ውስጥ ያለ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት ፤ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። " የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ " የተሰኘው ረቂቅ አዋጁ የሃይማኖት ተቋማቱ ተቀባይነት ያለው የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚኖርባቸው፣ የኦዲት ሪፖርታቸውን ለሰላም ሚኒስቴር ማቀረብ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡  ረቂቅ አዋጁ ምን ይዟል ? - የሃይማኖት ተቋማት የሚጠቀሙት የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት የገቢ፣ የወጪና አጠቃላይ የንብረት ዝርዝር የያዘ መሆን አለበት። - የገቢ አሰባሰብና የወጪ አስተዳደር በሕጋዊ መንገድ ማከናወን አለባቸው። - የሃይማኖት ተቋም በራሱ #የገቢ_ማስገኛ ሥራዎችን በሚያከናውንበት ጊዜ ለዚሁ ሥራ ሲባል የተለየ የባንክ ሒሳብ መክፈትና የተለየ መዝገብ መያዝ አለበት። - ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ አለበት። ሲያሳውቅም ፦ ° የለጋሹን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስም እና አድራሻ፣ ° የተለገሰው የገንዘብ፣ ስጦታ ዓይነት እና መጠን ፣ ° ስጦታው / ድጋፉ የተሰጠበት ልዩ ዓላማ መካተት አለበት። - ማንኛውም  የሃይማኖት ተቋም  የበጀት ዓመቱ ባለቀ በ3 ወር ውስጥ የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር አለበት። የኦዲተሩን አቋም እና የውሳኔ ሐሳብም መያዝ ይኖርበታል። - የሰላም ሚኒስቴር የደረሰውን የኦዲት ሪፖርት አመቺ በሆነ መንገድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ይኖርበታል። #ሪፖርተርጋዜጣ #tikvahethiopia https://t.me/NegereHig
Показать все...
2
#AddisAbaba #ንግድ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ማህበረሰብ ያለወከባ በተረጋጋ መንፈስ የንግድ ተግባሩን ለማከናወን እንዲያስችል ዕድል ይፈጥርለታል የተባለ አዲስ መመሪያ ስራ ላይ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል። አዲሱ መመሪያ  " በመንደር ንግድ ቁጥጥር አሰራር ስርዓት መመሪያ 159/2016 " እንደሚባል ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። መመሪያው በየትኛው አስተዳደር እርከን የትኛው አይነት እርምጃ እንደሚወሰድ በግልጽ ያስቀመጠ ሲሆን ይህም ሲታይ የነበረውን ግልጽ እና ፍትሃዊ ያልሆነ አሰራር ያስቀራል ተብሏል። በአዲሱ የመንደር ንግድ መመሪያ መሰረት የወረዳ የንግድ ቁጥጥር ባለሙያ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስድ ህጉ የሚፈቅድለት በተመደበበት መንደር ላይ ፦ ➡ ያለ ንግድ ፍቃድ ➡ ባልታደሰ ፍቃድ ➡ በታገደ አልያም በተሰረዘ ንግድ ፈቃድ የሚነግድ የንግድ ድርጅት ላይ #ብቻ_ነው። ይህን ሲያደርግም ለቅርብ ኃላፊ ማሳወቅ አለበት። ከዚህ ወጪ ያሉት ጥፋቶች #በሙሉ እርምጃ ሳይወስድ ለቅርብ ኃላፊው በፅሁፍ በማሳወቅ ለውሳኔ ወደ ንግድ ቢሮ መላክ ይጠበቅበታል ፤ የተወሰነውን ውሳኔ የማስፈፀም ኃላፊነትም አለበት። መመሪያው ፦ https://t.me/tikvahethiopia/87886 #TikvahEthiopiaFamilyAA #tikvahethiopia አማራጭ የሕግ እውቀት 👉Telegram👈 https://t.me/lawsocieties 👉Facebook Page 👈 https://www.facebook.com/lawsocieties/ 👉 LinkedIn 👈 https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/ 👉YouTube 👈 https://youtube.com/@Ale_Hig
Показать все...