cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

health ጤናችን

ስለ ጤና፣የስራ እድል፣ የተለያዩ መረጃዎች እና ማንኛውንም ጤና ነክ መፅሀፎችን የሚያገኙበት ቻናል ነው::አዳዲስ የጤና፣ የህክምናና የመድሃኒት መረጃዎችን የምናቀርብበት ቻናል። ✍️Bring you the latest health news, drug and medical information. ✍️Guidelines ✍️Updates ✍️Clinic @ health ጤናችን ለአስተያየት: @Danihealth ይጠቀሙ ::

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
148
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

መደበኛ ዝውውር.pdf6.44 KB
REGULAR trANSFER 2013.pdf1.08 MB
ስምሪት ስለማገድ.pdf5.98 KB
መደበኛ ዝውውር.pdf6.44 KB
የፀጉር መበጣጠስን ለማስቀረት 5 ቀላል ዘዴዎች የፀጉር መበጣጠስን ለማስቀረት ገንዘብ ከመከስከስ ተፈጥሯዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ለፀጉራችን እንክብካቤ ማድረጉ የሚመረጥ ሲሆን፥ የውበት ባለሙያዎችም ይህንኑ እንድናደርግ ነው የሚመክሩት። በመሆኑም እነዚህን አምስት አማራጮች እንድንተገብራቸው ይናገራሉ። (አሁኑኑ ሼር ያድረጉት።) 1. ተፈጥሯዊ ጭማቂዎች (ጂውሶችን) መጠቀም፣ አመሻሽ ላይ የነጭ፣ ቀይ ሽንኩርት አልያም የዝንጅብል ጭማቂን ወስደን በተመሳሳይ የፀጉራችን ስሩን በደንብ መቀባት፤ ከዚያም በማግስቱ ልንለቃለቀው እንችላለን። 2. አረንጓዴ ሻይ መጠቀም፣ ሁለት የአረንጓዴ ሻይ ከረጢት በአንድ ኩባያ የፈላ ውሃ ላይ በመጠቀም የፀጉራችንን የስረኛው ክፍል መቀባት፣ ለአንድ ሰዓት ያህል ካቆየነው በኋላም እንደምንፈልገው ልንለቃለቀው እንችላለን። በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ የምናገኘው አንቲኦክሲዳንትስ የፀጉር መነቃቀልን ይከላከላል። በተጨማሪም የፀጉር ዕድገትን ያፋጥናል። 3. ዘይት መጠቀም፣ የወይራ ዘይት፣ የኮኮናት ዘይት አልያም ሌላ ማንኛውንም አይነት ዘይት ወስደን እናፈላዋለን፤ ከዚያም ለብ ሲል በጥንቃቄ የፀጉራችንን ስር በደንብ እያዳረስን እንቀባዋለን፤ ለአንድ ሰዓት ያህልም በሻሽ ወይም ፎጣ ጠቅልለን ካቆየን በኋላ በሻምፖ እንለቃለቀዋለን። 4. የጭንቅላት ማሳጅ (መታሸት) የፀጉራችን ስር አካባቢ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በየቀኑ የምናደርገው የማሸት (ማሳጅ) የማድረግ ተግባር የደም ዝውውርን የሚያቀላጥፍ ሲሆን፥ የደም ዝውውር መቀላጠፍም በአንፃሩ የፀጉር ሴሎችን እድገት ያነቃቃል። 5. ጭንቀትን ማስወገድ፣ ለፀጉር መሳሳት እና መነቃቀል አብይ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው ጭንቀት ነው። በመሆኑም ከአላስፈላጊ ጭንቀት ራስን መከላከል እና የተመስጦ (ሜዲቴሽን) ተግባርን በማከናወን የፀጉር መነቃቀልንም ሆነ መሳሳትን መከላከል ይቻላል። ተመስጦ በተጨማሪም የሆርሞን መመጣጠን እንዲኖር በማገዝ የፀጉር እድገት ፍጥነትን እንደሚጨምርም ነው የሚነገረው። ሼር ሼር @healthdani @healthdani @healthdani
Показать все...
የጡት ካንሰር(breast cancer) ትርጉም(definition) > በጡት ላይ የሚከሰት የካንሰር አይነት ሲሆን ወደ ሌላ የሰውነት ክፍል ሊዛመት(disseminate)  ይችላል። > በወንዶችም በሴቶችም የሚከሰት ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ በሴቶች ላይ ያመዝናል። @healthdani መንስኤ(risk factor) > እድሜ መጨመር > ሴት መሆን > በቤተሰብ ውስጥ የጡት ካንሰር ያለበት ካለ(genetics) > የጡት እብጠት እና የዳነ የጡት ካንሰር ታሪክ > ቶሎ የወር አበባ ማየት እና ዘግይቶ ማረጥ(menopause) > ለራዲዬሽን መጋለጥ > ከፍተኛ ውፍረት > ሲጋራ ማጨስ > አልኮል መጠጣት ምልክት(clinical feature) > ጡት ወይም ብብት ላይ የሚወጣ እባጭ መኖር > የጡት ቅርፅና መጠን መጨመር > የጡት ቆዳ መቅላት፣ ወደ ውስጥ መጎድጎድ(dimpling)፣ መላጥ > የጡት ጫፍ(nipple) ላይ የሚወጣ ሽፍታ > የጎደጎደ ወይም የተገለበጠ የጡት ጫፍ > ከጡት የሚወጣ ፈሳሽ በተለይም ደም የቀላቀለ ከሆነ > ጡት ውስጥ ወይም ብብት ላይ ያለ ቋሚ ህመም ቅድመ ካንሰር ምርመራ(screening)---according to ACOG 2017  > እድሜያቸው ከ29- 39 ለሆኑት በየ 1-3 አመቱ፤ 40 አመትና በላይ ለሆኑት ደግሞ በየ አመቱ አካላዊ ምርመራ(clinical breast examination) > ከ 40 አመት ጀምሮ በየ አመቱ የማሞግራፊ ምርመራ ቢያንስ እስከ 50 አመት፥ የሚመከረው እስከ 75 አመት ነው ምርመራ(diagnosis) > አካላዊ ምርመራ > ስካኖች፦ ማሞግራፊ፣ ሶኖግራፊ፣ MRI > የናሙና ምርመራ(biopsy) ህክምና(management) > ቀዶ ጥገና > የጨረር ህክምና > የኬሚካል ህክምና(chemotherapy)  ምን እናድርግ? × አልኮል አብዝቶ አለመጠጣት  × ሲጋራ አለማጨስ × ውፍረትን መቀነስ × የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ × አትክልትና ፍራፍሬ የበዛበት ምግብ መመገብ × ሻወር ሲወስዱ ወይም በማንኛውም ሰአት ጡትን በመነካካት እባጭ መኖሩን፣ የጡት ቆዳ ቀለም መቀየሩን፥ መቁሰሉን...ማየት × ቅድመ ምርመራ ማድረግ © ምናልባት ይህን መረጃ የሚፈልጉት ሌሎች ይኖራሉና እባክዎ share ያድርጓቸው። @healthdani @healthdani @healthdani
Показать все...
#DrLiaTadesse የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦ • የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 7,773 • በበሽታው የተያዙ - 481 • ህይወታቸው ያለፈ - 6 • ከበሽታው ያገገሙ - 867 በአጠቃላይ በሀገራችን 95,301 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,457 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 50,753 ከበሽታው አገግመዋል። 311 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። @healthdani @healthdani @healthdani
Показать все...
አዲስ ዓመት የፈጣሪ ምህረት ማሳያ! ቸሩ መድኃኒዓለም ሆይ አንተ ስላለህ.............. ዛሬን ለማየት በቃን አንተ ስላለህ............. ህይወት ቆየን አንተ ስላለህ.............. ሁሉን አለፍን አንተ ስላለህ............... ከባዱን ተሻገርን አንተ ስላለህ................ አስጨናቂውን አመለጥን አንተ ስላለህ............... በምህረትህ እዚህ ደረስን አንተ ስላለህ............... በዛን በረከትን አንተ ስላለህ............... ታመን ተፈወስን አንተ ስላለህ............... ወድቀን ተነሳን አንተ ስላለህ............... ጠምቶን ጠጣን አንተ ስላለህ............... ርቦን በላን አንተ ስላለህ............... ተኝተን ተነሳን አንተ ስላለህ............... ወተን ገባን አንተ ስላለህ............... አመሰገንህ አንተ ስላለህ................ ዛሬን አየን አንተ ስላለህ ሁሉም ሆነ የጊዜ መስፈሪያ የሌለህ አንተ ለኛ በቸርነትህ ከአመት አመት አሸጋገርከን ... ከቁጥር ሳታጎል በምህረትህ አቆየኧን.....!!! በአመቱ ከንተ በላይ ያስከፋነው ያስቀየምነው ያሳዘነው የለም ... አንተ ግን አንተ ነህ ! ምህረትህ የማያልቅ በረከትህ የማይጎል ፍለጋህ የማይነጥፍ ቸር ነህና እዚህ አደረስከን! ያለፉ ወንድም እህቶቻችን ወገን ዘመዶቻችን ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት አኑርልን! አሜን! አመቱን የንስሃ፣ የመመለስ፣ የበረከት እና የፀጋ ሙላት አድርግልን! ከሁሉ በላይ አንተን በመፍራት እንድንመላለስ ቅዱስ መንፈስህ ያግዘን! አሜን! ስብሃት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ! አሃዱ አምላክ አሜን! 🌼🌼🌼 መልካም አዲስ ዓመት ! 🌼🌼🌼
Показать все...
#COVID19_ETHIOPIA፡ ባለፉት 24 ሰዓታት 1,733 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ የ13 ሰዎች ሕይወት አልፏል! ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 18,766 ላቦራቶሪ ምርመራ 1,733 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ13 ሰዎች ሕይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 586 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 48,140 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 758 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 17,415 ደርሷል።
Показать все...
ነሃሴ 10/2012 ዓ/ም የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1 ፦ #Amhara በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 5,877 የላብራቶሪ ምርመራ 93 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል። በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦ - 18 ከኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን - 14 ከደ/ወሎ ዞን - 13 ከሰ/ሸዋ ዞን - 11 ከባህር ዳር ከተማ - 9 ከአዊ ብ/ሰብ ዞን - 7 ከሰ/ወሎ ዞን ይገኙበታል። #BenishangulGumuz በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 547 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። - 1 ከኩርሙክ ወረዳ - 3 ከካማሽ ወረዳ #Afar በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 415 የላብራቶሪ ምርምራ ተደርጎ 85 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በአፋር ፦ - 415 በቫይረሱ የተያዙ - ያገገሙ 191 #Oromia ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው ምርመራ 3537 ሲሆን 185 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የስምንት (8) ሰዎች ህይወት አልፏል። አጠቃላይ በኦሮሚያ ፦ - 2,953 በቫይረሱ የተያዙ - 35 ሞት - 939 ያገገሙ #Tigray በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,145 ላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 82 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል (ከመቐለ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል) አጠቃላይ በትግራይ ፦ - 1,770 በቫይረሱ የተያዙ - 13 ሞት - 809 ያገገሙ #Somali በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 260 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 9 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል። - 9 ጅግጅጋ @healthdani @healthdani @healthdani
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.