cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Addis Tesfa

ይህ ቻናል የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ትምህርቶች የሚቀርብበት ነው።

Больше
Рекламные посты
345
Подписчики
-124 часа
-27 дней
+630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Repost from N/a
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ጉዳዩ:- የ2016 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናን ይመለከታል፤ 👉በአጠቃላይ ትምህርት ሥርዓተ-ትምህርት ሪፎርም መሠረት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከ2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት መሠረት ወደ ሙሉ ትግበራ መግባቱ ይታወሣል፡፡ በዚህም መሠረት በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች ተለይተው የመማር ማስተማር ሂደቱ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ 👉ከዚሁ ጋር ተያይዞ በ2016 ዓ.ም. በሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችን መወሰን በማስፈለጉ በሁለቱም ዘርፎች ስድስት፡ ስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሆኑ እንደሚከተለው ተወስኗል፡፡ የተፈጥሮ ሣይንስ ✍️እንግሊዝኛ ✍️ሒሳብ ✍️ባዮሎጅ ✍️ፊዚክስ ✍️ኬሚስትሪ ✍️ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት የማህበራዊ ሣይንስ ✍️እንግሊዝኛ ✍️ሒሳብ ✍️ታሪክ ✍️ኢኮኖሚክስ ✍️ጅኦግራፊ ✍️ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት #ከላይ በተጠቀሰው መሠረት የ2016 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትም:- 1. የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም. ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች 👉ከ9ኛ-11ኛ በነባሩ /በአሮጌው ስርአተ ትምህርት እና 👉12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርአተ ትምህርት ያጠቃልላል:: 2. ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ወደፊት ጥናት ተጠንቶ እስከሚለይ ድረስ በነበረው አሠራር መሠረት ውጤት ተደምሮ የሚገለጽ መሆኑን እናሳውቃለን #ትምህርት ሚኒስቴር
Показать все...
👍 3
የሚያነቡ ሰዎች . . . 📚1. ካለማቋረጥ ራሳቸውን ያሻሽላሉ። 📚2.  ጊዜያቸውን በተራ ነገር ከማሳለፍ ይጠበቃሉ። 📚3.  ጸሃፊዎቹ ብዙ ጊዜ ወስደው በልምምድና በጥናት ያገኙትን እውቀት በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ይቀስማሉ። 📚4. አእምሯቸው በንባብ ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ስለሚል ለተራ ወሬና ለወረዱ ነገሮች ጊዜውም ሆነ ፍላጎቱ አይኖራቸውም። 📚5. የውስጥ እርካታና መረጋጋትን ያዳብራሉ።   ➖➖➖➖➖ ➖➖ ➖              ዶ/ር እዮብ ማሞ ➖➖➖➖➖ ➖➖
Показать все...
👏 2
WPS Office: Complete office suite with PDF editor Here's the link to the file: https://eu.docworkspace.com/d/sIG-ns-PbAYvxgK0G Get WPS Office for PC: https://www.wps.com/d/?from=t
Показать все...
WPS Office: Complete office suite with PDF editor Here's the link to the file: https://eu.docworkspace.com/d/sIG-ns-PbAYvxgK0G Get WPS Office for PC: https://www.wps.com/d/?from=t
Показать все...

ከላይ የቀጠለ 👇👇👇👇👇 👉ተማሪዎቹ ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባታቸው በፊት፣ ለኩረጃ ሲዘጋጁ ኔትወርክ ፈጥረው፣ የመጀመሪያው እቅድ ባይሳካ በሚል ሁለት እና ሶስት እቅዶችን ነድፈው መሆኑንም ጠቅሰዋል። 👉ከዚህ በተጨማሪ የነደፉት ስልት በፈተና የመጀመሪያ ቀን ካልሰራ፣ ለቀጣዩ ፈተና ቀን ሌላ ስልት ነድፈው እንደሚመጡም ይናገራሉ። ከዚህ የሞባይል ቴክኖሎጂን ተጠቅመው በሚያደርጉት ኩረጃም ከትምህርት ቤት ውጪ ያሉ ግለሰቦችን እንደሚያካትቱ ጨምረው ያስረዳሉ። 👉አንዳንድ ትምህርት ቤቶች በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ተማሪዎችቻቸውን የመደገፍ ነገር ማስተዋላቸውን የሚናገሩት ወንድይፍራው (ዶ/ር) ፣ በትምህርት ቤቶች መካከል ያለው ውድድር ለዚህ አስተዋጽኦ ማድረጉን ይጠቅሳሉ። 👉ለፈተና ስርቆት እና ኩረጃ መስፋፋት እገዛ የሚያደርገው ቴክኖሎጂ ብቻ ሳይሆን የመምህራን እና የትምህርት ቤቱ አስተዳደሮች ቁርጠኛ አለመሆን ጭምር መሆኑንም አክለው ገልፀዋል። 👉በኩረጃ ሲሳተፉ የተገኙ ተማሪዎች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች ምን ያህል ፈጣን እና አስተማሪ ናቸው? ሲሉ የሚጠይቁት ምሁሩ፣ የተወሰደ እርምጃ ቢኖር እንኳ ለተማሪዎች በፍጥነት አለመንገር ለኩረጃ መስፋፋት አስተዋጽኦ ያደርጋል ሲሉ ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ✅ኩረጃን ማስቀረት ይቻላል? ✅ኩረጃን ማጥፋት ሳይሆን መቀነስ ይቻላል የሚሉት ወንድይፍራው (ዶ/ር) ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ ተማሪዎች ስለታማኝነት እየተማሩ መምጣት እንዳለባቸው ይመክራሉ። 👉ታዳጊዎች ከታች ክፍል ጀምሮ መኮረጅ አስፀያፊ መሆኑን እየነገሩ ማሳደግ በኋላ በከፍተኛ ትምህርት ተቋምም ሆነ በሁለተኛ ደረጃ ላይ በስነምግባር የታነፀ ትውልድ እንዲኖር ይረዳል። 👉ከሥርዓተ ትምህርት አንጻርም ስለኩረጃ፣ ስለታማኝነት በየትምህርት ዓይነቶቹ ላይ ማካተት እንደሚያስፈልግ ያስረዳሉ። 👉መምህራንም ቢሆኑ ኃላፊነት ተሰምቷቸው በትክክል ተማሪዎቻቸውን መመዘን የሚያስችል ፈተና ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ይመክራሉ። 👉ፈተና በሚሰጥበት ክፍል ውስጥም ቢሆን መምህሩ በአግባቡ መፈተን መቻሉ ኩረጃን ለመቀነስ የራሱ አስተዋጽኦ አለው ሲሉ ያስቀምጣሉ። 👉የትምህርት አስተዳደሮችም ቢሆኑ ለተማሪዎች በሚያወጧቸው መመሪያዎችን እና መተዳደሪያ ደንቦችን በአመቱ መጀመሪያ ላይ ለተማሪዎቹ በሚገባ ማስተዋወቅ እንደሚያስፍልጋቸው ይገልጻሉ። 👉የወጡ መመሪያና ደንቦችን ተከትሎም ለሚፈፀሙ ጥፋቶች የተቀመጡ ተገቢ ቅጣቶችን ሳይዘገዩ ተፈጻሚ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ያብራራሉ። 🙄ተማሪው ያጠፋውን ጥፋትን እና ቅጣቱን ለማገናኘት እንዲችል፣ ሲኮርጅ እንደተያዘ ወድያውኑ እርምጃ መውሰድ ለትምህርት ቤቱ ተማሪዎችም ወዲያውኑ ማሳወቅ እንደሚገባ ይናገራሉ። በምንጭነት 👉👉👉BBC Amharic ግሩፓችንን ሸር አድርጉልን🤲🤲 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/activegenerationኩረጃን በጋራ እንከላከል❌❌
Показать все...
ንቁ ትውልድ .2016(የመዝናኛና የትምህርት መንደር)

ጤና ይስጥልኝ እንኳን ደህና መጡ !! 🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ይህ ግሩፕ የመዝናኛ እና የትምህርት ግሩፕ ነው። በዚህ ግሩፕ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እውቀትን የሚያሳድጉ ትምህርቶች ይቀርባሉ። በተጨማሪም ሰዎች ልዩልዩ ተሰጧቸወን የሚያሳድጉበት እና የሚዝናኑበት ግሩፕ ነው። በዚህ ግሩፕ ለህይወት አስፈላጊ ስልጠናዎችም ይሰጣሉ። ✅ለአዕምሮዎ ጤናማ ምግብ ይመግቡ

ኩረጃ ምንድን ነው? (ክፍል አንድ)ወቅታዊ😯 👉ከዚህ ቀደም ቢቢሲ በሰራው አንድ ዘገባ  ተማሪዎች ለኩረጃ ይመቻቸው ዘንድ ከጎበዝ ተማሪዎች ጋር በማመሳሰል ስማቸውን በፍርድ ቤት አስለውጠዋል። 👉ኩረጃ በአንድ የፈተና ክፍል ውስጥ ብቻ የሚካሄድ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ትምህርት ስርዓት ውስጥ የሚዳብር መሆኑን ጨምረው ያስረዳሉ። 👉የራስ ያልሆነን ስራ እንደራስ አድርጎ ማቅረብ፣ ትክክለኛ ምክንያት ባለመስጠት መምህሩን ማሳሳት እና የማይገባውን ውጤት ለማግኘት የሚደረግ ጥረት፣ ያልተገባ ውጤት ለማግኘት መምህርን ማታለል በአጠቃላይ ኩረጃ ነው ይላሉ ወንድይፍራው (ዶ/ር)። 👉ጓደኛ እንዲኮርጅ መርዳት፣ በግል የተሰጠ ምዘናን ወይንም የቤት ሥራ በቡድን መስራት ሁሉ በኩረጃ ስር እንደሚጠቃለሉ ጨምረው ይገልጻሉ። 👉በትምህርት ቤት ሕይወታቸው ቢያንስ አንድ ጊዜ በኩረጃ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች በርካታ መሆናቸውን በተለያዩ አገራት የተሰሩ ጥናቶች ያሳያሉ። 👉ተማሪዎች የሚኮርጁት ለፈተናው ወይንም ደግሞ ምዘናው በቂ የስነልቦና ዝግጅት ሳይኖራቸው ሲቀር መሆኑን ይናገራሉ። 👉ተማሪዎች በተገቢው መጠን ራሳቸውን ካለመዘጋጀት ውጪ፣ ትምህርትን በአግባቡ አለመከታተል፣ ኩረጃ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሌለው ግንዛቤ መያዝ ወደ ኩረጃ የሚገፉ ሌሎች ምክንያቶች ናቸው ይላሉ። 👉ከዚህም በተጨማሪ ወንድይፍራው (ዶ/ር) እንደሚሉት የወላጆች 'ልጆቼ ተምረው፣ ሕይወቴን ይለውጡኛል' የሚለው ገለጻ ልጆች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳርፋል። 👉ይህ ቤተሰብ የሚያደርገው ጫና ተማሪዎችን ለማበረታታት የተደረገ ነገር ቢሆንም ለኩረጃ እንደሚገፋም ያስረዳሉ። 👉በራሱ ጥረት ወላጆቹ ወዳሰቡለት ስኬት መድረስ ያልቻለ ተማሪም የወላጆቹን ጫና ለመሸሽ ጎበዝ የሚባሉ ተማሪዎችን በመደገፍ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ይሞክራል በማለት ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። 👉ኩረጃ ከክፍል ክፍል ሲኬድ እያደገ የሚሄድ ብቻ ሳይሆን፣ በሕይወት ውስጥ ዘላቂ የሆነ ተጽዕኖ እንዳለውም ጨምረው ገልፀዋል። 👉"ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በትምህርት ዓለም የነበረን የኩረጃ ሕይወት ወደ ሥራ ዓለም ስንገባም ያንኑ የመተግበር እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ እና ተያያዥነት እንዳለው ነው፤ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በኩረጃ ታግዞ ወደ ከፍተኛ ተቋም ሲገባ፣ እዚያም በኩረጃ ታግዞ ቢመረቅ በስራው ዓለም መደለያ ለመቀበል አያቅማማም።" 👉ተማሪዎች በጓደኞቻቸው ዘንድ ሰነፍ ሆኖ ላለመታየት፣ በውጤት አንሶ ላለመገኘት፣ ወደ ኩረጃ እንደሚገቡም አክለው ተናግረዋል። ግሩፓችንን ሸር አድርጉልን🤲🤲 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/activegeneration ክፍል ሁለት ይቀጥላል 👇👇👇👇👇👇
Показать все...
ንቁ ትውልድ .2016(የመዝናኛና የትምህርት መንደር)

ጤና ይስጥልኝ እንኳን ደህና መጡ !! 🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ይህ ግሩፕ የመዝናኛ እና የትምህርት ግሩፕ ነው። በዚህ ግሩፕ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እውቀትን የሚያሳድጉ ትምህርቶች ይቀርባሉ። በተጨማሪም ሰዎች ልዩልዩ ተሰጧቸወን የሚያሳድጉበት እና የሚዝናኑበት ግሩፕ ነው። በዚህ ግሩፕ ለህይወት አስፈላጊ ስልጠናዎችም ይሰጣሉ። ✅ለአዕምሮዎ ጤናማ ምግብ ይመግቡ

ውድ ተማሪዎች ፈተና እንዴት ነበር ?Anonymous voting
  • ቀላል
  • መካከለኛ
  • ከባድ
0 votes
8 SOCIAL STUDIES .pdf3.53 KB
CamScanner 01-10-2024 15.18.pdf4.52 KB
CamScanner 01-10-2024 15.26.pdf4.98 KB
English G8 Model Exam.pdf5.32 KB
8 AMHARIC.pdf4.11 KB
8 MATHEMATICS.pdf2.20 KB
👏 1
Maths 8.docx2.42 KB
MATHS G.8.docx0.24 KB
Фото недоступноПоказать в Telegram
ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤ 👉 ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት። 👉አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ። 👉ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ። 👉 በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር:: 👉 ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤ 👉በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ። 👉ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ። 👉በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። 👉መጭው ጊዜ የፈተና ወቅት ነውና ለተፈታኞች #ሸር በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር 🤲🤲🤲🤲 መልካም  ቀን🥰🥰 ✅ግሩፑ ይህ ነው!! 👇👇👇👇👇👇👇 💚💚💚💚💚💚💚 https://t.me/activegeneration
Показать все...
👍 3👏 3
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.