cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ምክረ አበው እና ሌሎችም💒💒💒

+++ኦርቶዶክሳዊ ምክሮች፣ ተግሳጾች ፣ የቅዱሳን አባቶች ወርቃማ አባባሎች (saying of desert holy fathers),ቀደምት የበቁ ቅዱሳን አባቶች ድንቅ ንግግሮች (qoutes of the ancient Harmit fathers).... ይቀርቡበታል +++ የቅዱሳን በረከታችው አይለየን!!!

Больше
Рекламные посты
472
Подписчики
Нет данных24 часа
+17 дней
+630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

00:59
Видео недоступноПоказать в Telegram
46.64 MB
ራስን ዝቅ ስለማድረግ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር #ክፍል_፩ እግዚአብሔርን የምትወዱት አንድም እግዚአብሔር የሚወዳችኁ ልጆቼ! ትሕትናን ገንዘብ ማድረግ ምን ያኽል ጥቅም እንዳለው፥ በአንጻሩ ደግሞ ትዕቢትን ገንዘብ ማድረግ ምን ያኽል ጕዳት እንዳለው ታውቁ ዘንድ እወዳለኁ፡፡ ምንም ያኽል ምግባር ትሩፋት ቢኖረን፣ ብንጾም፣ አሥራት በኵራት ብናወጣ፣ ሌላም ብዙ የብዙ ብዙ ምግባራትን ብናደርግ ትሕትና ግን ከሌለን ከንቱ ነን ብዬ እነግራችኋለኁ፡፡ ምንም ያኽል ኃጥአን ሳለን ነገር ግን የተሰበረ ልቡና ካለን፥ በምግባር በትሩፋት አሸብርቀው ሳለ ትዕቢተኞች ከኾኑት ሰዎች ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጆች ነን ብዬ እነግራችኋለኁ፡፡ ከቀራጩ በላይ ማን ኃጢአተኛ ነበር? /ሉቃ.18፡9-14/፡፡ ነገር ግን ይኽ ኃጢአተኛ ሰው ዓይኑን ወደ ሰማይ ቀና አድርጐ ሊያይ ባለመውደዱ፣ በምትመሰገንበት በቤተ መቅደስኅ መቆም የማይቻለኝ ኀጥእ ነኝ በማለቱ ከማይቀማው፣ ከማይበድለው፣ ከማያመነዝረው፣ በሳምንት ኹለት ጊዜ ከሚጾመው፣ ከገንዘቡ ኹሉ አሥራት ከሚያወጣው ፈሪሳዊው ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አገኘ፡፡ ይኽስ እንዴት ሊኾን ቻለ? ይኽን ያኽል ምግባር ትሩፋትን ገንዘብ አድርጐ የነበረው ፈሪሳዊው የክፋት ኹሉ ስር የኾነውን ትዕቢት በልቡናው አኑሮ ስለነበር ነው ብዬ በእውነት እነግራችኋለኁ፡፡ ብጹዕ ጳውሎስም ይኽን በማስመልከት ሲናገር፡- “ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን፤ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልኾነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል” አለ /ገላ.6፡4/፡፡ ፈሪሳዊው ግን ይኽን አላደረገም፡፡ ይልቁንም ሌላውን ሰው ኹሉ እየኰነነ፥ በሕይወት ካለ ሰው ይልቅም እጅግ ጻድቁ ርሱ ብቻ እንደኾነ እያሰበ ወደ ቤተ መቅደሱ መጣ እንጂ፡፡ ይኽ ፈሪሳዊ ራሱን ያነጻጸረው ከዐሥር፣ ወይም ከአምስት ወይም ከኹለት ወይም ከአንድ ሰው ብቻ አይደለም፤ በዚኽ ዓለም ከሚኖሩ ሰዎች ርሱን የሚተካከለው ማንም እንደሌለ በአደባባይም ጭምር ተናገረ እንጂ፡፡የሚተካከለው እንደሌለ ብቻም አይደለም፤ ዳግመኛም በሰው ኹሉ ላይ ፈረደ እንጂ፡፡ ይኽን በማድረጉም በሽቅድድሙ መም ላይ ወደቀ፡፡ ብዙ ዕቃዎችን የጫነች መርከብ ብዙ አስቸጋሪ የሚባሉ ማዕበላትን ተሻግራ ከወደቡ ጫፍ ልትደርስ ጥቂት ብቻ ሲቀራት ከዐለት ጋር ተላትማ እንደምትሰጥምና ጭናው የነበረው ኹሉ እንዳልነበረ እንደሚኾን ኹሉ ይኽ ፈሪሳዊም ብዙ ከጾመ፣ ሌላም ብዙ በጐ ምግባራትን ከያዘ በኋላ አንደበቱን ባለመግዛቱ ምክንያት የነበረውን ሀብተ ሥጋ ሀብተ ነፍስ ኹሉ አጣ፡፡ ምንም እንኳን ወደ ቤተ መቅደሱ ለጸሎት መምጣቱ በጐ ምግባር ቢኾንም ባደረገው ነገር ስለተመጻደቀበት፣ ራሱን ከፍ ከፍ ስላደረገበት ባዶውን ወደ ቤቱ ሔደ ብዬ በእውነት እነግራችኋለኁ፡፡ ክፍል ሁለትን በ @dr_zebene_lemma ላይ ያገኙታል። ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09
Показать все...
01:21
Видео недоступноПоказать в Telegram
2.53 MB
"መጽሐፈ ምሥጢር" ብሎ የሰየመው ራሱ ነው፡፡ የጻፈው በ1409 ዓ.ም እድሜው 52 በደረሰ ጊዜ ሲሆን በወቅቱም የዚህ መጽሐፍ ቅጅ በነጋድያን እጅ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ሄዶ ነበር፡፡ ✝ ዐፄ ይስሐቅ ለአባ ጊዮርጊስ "ምድረ ሰዎን" የተባለውን የጳጳሳት መቀመጫ የነበረውን ሀገር በርስትነት ሰጥቶት ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ በምድረ ሰዎን ንጉሥ ይስሐቅ ክረምቱን ያሳልፍበት በነበረው ቦታ ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠራ፡፡ በዚያም በማስተማርና በጾም በጸሎት ይተጋ ነበር፡፡ በጋሥጫ እያለ ዐፄ ይስሐቅ አስጠራው፡፡ በዚያ ጊዜ ንጉሡ የመናገሻ ማርያምን ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ ስለነበር እንዲባርክለት ፈልጎ ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ምንም እንኳን በዚያ ጊዜ ታሞ የተኛም ቢሆን ወደ ንጉሡ ተጓዘ፡፡ እዚያ ሲደርስ በጣም ተዳክሞ ነበር፡፡ ሥርዓቱን ለመፈጸምም አቅም አልነበረውም፡፡ ስለዚህም ንጉሥ ይስሐቅ በአልጋ ተሸክመውት እንዲዞሩና ቤተ ክርስቲያኗን እንዲባርካት አድርጓል፡፡ ቡራኬውን ከፈጸመ በኋላ ደቀ መዝሙሮቹን ሰብስቦ "ከሞትኩ አባቴ በጸሎተ ሚካኤል መከራ ወደ ተቀበለባትና እኔም ቤተ ክርስቲያን ወዳነፅኩባት ቦታ ወስዳችሁ ቅበሩኝ" ሲል አዘዛቸው፡፡ ለደቀ መዛሙርቱ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ የመጨረሻ የስንብት ትምህርቱን አስተማራቸው፡፡ እነርሱም በአልጋ ተሸክመውት ወደ ጋሥጫ እያመሩ ሳለ በመንገድ ላይ ሐምሌ 7 ቀን 1417 ዓ.ም በ60 ዓመቱ ዐረፈ፡፡ ከአባታችን ከአባ ጊዮርጊስ እግዚአብሔር አምላክ ዘጋስጫ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቱ ይማረን!። ✝ ✝ ✝ ✝ #ቅድስት_እኅተ_ጴጥሮስ፦ ይቺም ጻድቅ አገሯ ጎንደር ነው። የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ የቅርብ ጓደኛ የነበረች ሲሆን አብረው ከዐላዊያን ጋር በሰማዕትነት ሲጋደሉ ኖረዋል። በደብረ ዳሞ ተራራ ሥር ባለው የሴቶች ገዳም ተቀምጣ ዐላውያን ካቶሊኮችን ስትከራከርና እነርሱም ሲያሠቃዩአት የኖረች ደገኛ ሰማዕት እናት ናት። በደብረ ዳሞ፣ በማኅበረ ሥላሴ ገዳምና በደብረ ሞጊና ገዳም መነኰሳትን እየተራዳችና እያገለገለች ኖራለች። ጻድቋ እናታችን በቀን አንድ ሺህ አቡነ ዘበሰማያት ትጸልይና 1500 ትሰግድ የነበረች ሲሆን መላእክትም ዕለት ዕለት ያነጋግሯት ነበር። በሰማዕትነት ስታርፍም ክብሯን የመሰከሩላት ቅዱሳን መላእክት ናቸው። ከእናታች ከሰማዕቷ ከቅድስት እኅተ ጴጥሮስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቷም ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.