cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

✝ ተዋህዶ ✝ ሀይማኖቴ ✝

ኦሪት ዘፍጥረት/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮን የጠበቁ መዝሙሮች ና የቅዱሳን ገድል ይገኙበታል @orit_the_fetrat ✍️ግሩፑ ላይ መዝሙር ብቻ አይደለም የተለያዩ ነገሮችንም ታገኙበታላችሁ 🙏 ኑ በጋራ ሁነን እንማር 👇 ❷❶ ማርያም ሆይ እኖድሻለን @orit_the_fetrat ለማንኛውም አስተያየትና ሀሳብ 👇👇 @samiyaenatu 3:00 ●━━━━━━─────── 6:00

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
184
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

አዲስ ዓመትን በማሰብ የ ሳሚ መግለጫ 🥰የምወዳቹ ጓደኞቼ እንኳን አደረሳችሁ or ደረሰባቹ 🤪 በነገራችን ላይ የረሳዋቹ የሚመስላቹ ሰዎች አላቹ ግን እኔ በህይወቴ ሰውን እረስቼ አላውቅም 🤔ግን የ አጋጣሚ ጉዳይ ሁኖ ብዙ ቀን ፀጥ ያልኳቹ ሰዎች በጣም ይቅርታ 🥺በምክንያትነት ፀጥ እንዳልኳችሁ እወቁ ምክንያቴን ጠይቁኝ🤨 ከ 1 ሰው ውጪ 😬። ደሞ ከእኔ ጋር ይሄን አዝግ አመት ያለፋቹ ተበላቹ 😲ሌላ አዝግ ዘመን መጣላቹ 🥵ቻሉት ያኔ ገና አዲስ አመት ማገባደጃ ላይ እራሳችሁን አጥፉ ስላቹ 😇አልሰማ ብላቹ እስኪ አሁን መሆን ምን እንደሚውጣቹ 🤯እናያለን ።እኔስ በደና ጊዜ አምልጫለዉ 😳እንዲ ስላቹ ደሞ እራሴን አጠፋሁ እያልኩኝ አደለም 😷i am happy ! ልላቹ ፈልጌ ነው ።ለ አዲሱ አመት አዲስ Challenge ይዤላቹ መጥቻለው ምን እንደሆነ ማወቅ ከፈለጋችሁ በ imbox አዋሩኝ እነግራቸዋለሁ surprise ነው ። 😘🥰እወዳችኋለሁ መልካም አዲስ ዘመን ተመኘሁ by☺️🙏 Sami's statement on New Year's Eve Congratulations to my dear friends By the way, there are people who seem to have forgotten, but I have never forgotten anyone in my life, but unfortunately, people who have been silent for many days are very sorry Know that I am silent because of you. But you and I have eaten this last year You have fought another lazy season You just killed yourself at the end of the new year You said don't listen Let's see what it will be like to be now። I escaped when I was fine happy! I want the rest. I love you and wish you a happy new year by. 😍😍@samiyaenatu 😍😍
Показать все...
✅ስንክሳር 🚩ሐምሌ 25 ✅ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕተ ሮሜ ✏ቅዱሱ ከቀደምት ሰማዕታት አንዱ ሲሆን በ200 ዓ/ም አካባቢ እንደ ተወለደ ይታመናል:: ወላጆቹ ከጣዖት አምልኮ ወደ ክርስትና የመጡት በተአምር ነው:: ስማቸውም #ታቦትና_ኖኅ ይባላሉ:: ቅዱሱ መጀመሪያ " #ፒሉፓዴር" ይባል ነበር:: ትርጉሙ "የአብ ወዳጅ" እንደ ማለት ነው:: ✏ቀጥሎም " #መርቆሬዎስ" ተብሏል:: ይኸውም " #የኢየሱስ_ክርስቶስ_አገል ጋይ" እንደ ማለት ነው:: በጦርነት ኃይለኛ: በመልኩ ደመ ግቡና ተወዳጅ የነበረው ቅዱስ መርቆሬዎስ ስለ ክርስትናው መከራን የተቀበለው በ20 ዓመቱ ነው:: ዘመኑም በዳኬዎስ ቀዳማዊ ነው:: ✏ስለ ሃይማኖቱም ለ5 ዓመታት መከራን ታግሦ በ25 ዓመቱ (ማለትም በ225 ዓ/ም) ሕዳር 25 ቀን አንገቱን ተከልሏል:: በዓለማቀፍ ደረጃም ቅዱስ መርቆሬዎስ ክብሩ ከሊቀ ሰማዕታት ቀጥሎ የሚገኝ ነው:: ✏በተለይ ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን ቅዳሴ ቤቱ ሲሆን ቤቱ በታነጸበት ሁሉ ተአምራትን ያደርጋል:: ስለዚህ ነገር ታሪክ ብቻ ሳይሆን እኛ ኃጥአንም ምስክሮች ነን:: ጋሹ አምባን ጨምሮ ዛሬም ቅዱሱ ድንቆችን ይሠራል:: ✅ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ ✏ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኄኖክ ከአባታችን አዳም 7ኛው ደግ ሰው ሲሆን አባቱ #ያሬድ ይባላል:: በእርግጥ ቅዱሱ ሚስት አግብቶ #ማቱሳላና ሌሎች ልጆችን ወልዷል:: አካሔዱ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ነበርና ሞትን አላየም:: ✏#ነቢዩ_ኄኖክ በ1486 ዓ/ዓ የመጀመሪያውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ( #መጽሐፈ_ኄኖክን) ጽፏል:: የዚሕ መጽሐፍ ባለቤት ደግሞ ሃገራችን ናት:: ቅዱሱ ብዙ ሰማያዊ ምሥጢሮችን ተመልክቷል:: ✏የእርሱ ሞትን አለመቅመስ #በአቤል ሞት የፈሩትን #ውሉደ_አዳም በተስፋ አነቃቅቷቸዋል:: "በአቤል አፍርሆሙ: ወበኄኖክ አንቅሆሙ" እንዳለው ሊቁ:: (ዘፍ. 5:24, ኄኖክ. 4:1) ✅ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት ✏እናታችን ቅድስት ቴክላ በኒቆምድያ ተወልዳ ያደገች: ከአሕዛባዊ እምነት ወደ ክርስትና በሐዋርያው #ቅዱስ_ዻውሎስ አማካኝነት የመጣች እናት ናት:: እርሷ ክርስትናን ከልብ ለሚሹ ሴቶች ሁሉ መሪና ትልቅ ት/ቤት ናት:: ወንጌልን ከሐዋርያው ስትማር ምሥጢሩ እየመሰጣት አንዳንዴ ለ3 ቀናት ምግብ አትቀምስም ነበር:: ✏እጅግ ቆንጆ ወጣትና የሃብታሞች ልጅ ብትሆንም ስለ ክርስቶስ ሁሉን ለመናቅና መስቀሉን ለመሸከም አልተቸገረችም:: ከኒቆምድያ እስከ አንጾኪያ ወንጌልን ሰብካለች:: ወላጆቿን ጨምሮ ብዙ ነፍሳትን አድናለች:: በፈንታውም ብዙ መከራን ተቀብላ በዚህ ቀን ዐርፋለች:: ቤተ ክርስትያን " #ሐዋርያዊት" ብላ ታከብራታለች:: ✅ ቅዱስ አበከረዙን ጻድቅ ወሰማዕት ✏ስም አጠራሩ የከበረ ታላቁ #አባ_አበከረዙን ወደ ክርስትና የተጠራው ከሽፍታነት (ስርቆት) ሕይወት ነው:: ከአጋሮቹ ጋር ገዳም ለመዝረፍ ሒደው አንድ ባሕታዊ ከማታ 12:00 እስከ ጧት 12:00 ሲጸልይ አይተው ተጸጽተው ንስሃ ገብተዋል:: ✏አበከረዙን ግን ዓለምን ንቆ በምናኔ ለ7 ዓመታት ተጋድሏል:: ነገር ግን ሰማዕት ለመሆን ከነበረው ፍቅር የተነሳ ከገዳም ወደ ከሃድያን ነገሥታት ሃገር ሔዶ ስመ ክርስቶስን ሰብኩዋል:: በእርሱ ላይ ከደረሱ ስቃዮች ብዛት የተነሳ ከሥጋው: ከአጥንቱና ከደሙ የተረፈለት የለም:: ✏እንዲያውም አንዴ በዓየር ላይ ዘቅዝቀው ሰቅለው ደሙ በአፍና በአፍንጫው እየጐረፈ ለ10 ቀናት ቆይቷል:: በወቅቱ የመኮንኑ ሴት ልጅ እየመጣች ያለ ርሕሪሔ ታሰቃየው ነበርና እርሷን መልአክ ወርዶ ቀሥፎ ገደላት:: ✏እርሱ በተሰቀለ በ22ኛው ቀን: እርሷ በተቀበረች በደግሞ በ12ኛው ቀን ከተሰቀለበት አውርደውት ከሞት አስነስቷታል:: ታላቁ አበከረዙንን በዚህች ቀን ብዙ አሰቃይተው: ወገቡን ሰብረው: አንገቱንም ሰይፈው ገድለውታል:: ✅ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ ✏ለቤተ ክርስቲያን በንጹሕ ሕይወታቸው ካበሩላት ዐበይት ቅዱሳን አንዱ #ቅዱስ_ዱማድዮስ ነው:: እርሱ ወደ ክርስትና የመጣው ከባዕድ አምልኮ ሲሆን መሪው #መንፈስ_ቅዱስ ነው:: ጣዕመ ሕይወቱን ሲሰሙት ዕዝነ ልቡናን ደስ ያሰኛል:: ✏ገና በወጣትነቱ እንደ #ሐዋርያት ሰብኮ አሕዛብን አሳምኗል:: እንደ #ጻድቃን አካሉ አልቆ አጥንቶቹ እስኪታዩ ተጋድሏል:: እርሱ #ድንግል: #ንጹሕ: #መነኮስ: #ባሕታዊና #ካህን ነው:: ግን ውዳሴ ከንቱን አምርሮ ይጠላል:: በዚህ ምክንያት ካደረበት አይውልም: ከዋለበትም አያድርም:: ✏እርሱ በጸሎቱ የተዘጉ ማሕጸኖችን ከፍቷል:: ዕውራንን አብርቷል:: ለምጻሞችን አንጽቷል:: አንካሶችን አርትቷል:: በፈጣሪው ኃይል ፈሳሽ ወንዝን አቁሟል:: እንደ ገናም እንደ ነበረው መልሶታል:: ✏የቅዱስ ዱማድዮስ መጨረሻው ደግሞ #ሰማዕትነት ነው:: በበዓቱ ውስጥ ሳለ ከደቀ መዝሙሩ ጋር ክፉዎች በድንጋይ ወግረው ገድለውታል:: ድንጋዩም የኮረብታ ያህል ነበር:: ልክ በዓመቱ በዚህች ዕለት ምዕመናን ሥጋውን አፍልሠዋል:: ✥ቸር አምላክ ከነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃንና ሰማዕታት ክብርን ያሳትፈን:: 🚩ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦ 1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ) 2.ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ (ዕርገቱ) 3.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት 4.ቅዱስ አበከረዙን ታላቁ (ጻድቅና ሰማዕት) 5.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ (ጻድቅና ሰማዕት) 6.ቅድስት ኢላርያ ሰማዕት 7.ቅዱሳት ቴክላ ወሙጊ ሰማዕታት 8.ቅዱስ እንዲኒና ሰማዕት 9.አባ ይስሐቅ ሰማዕት 10.አባ ሕጻን ሞዐ ዘደብረ ሊባኖስ 11."25,000" ሰማዕታት (የአትሪብ /ግብፅ/ ሰዎች) 🚩ወርሐዊ በዓላት፦ 1.ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) 2.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ) 3.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
Показать все...
#ገና_ህጻን_ሳለህ የአቡነ ተክለሃይማኖት መዝሙር ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
Показать все...
✅ስንክሳር 🚩ሐምሌ 24 ✅አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ✏ኢትዮጵያዊው ጻድቅ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው ሸዋ (መርሃ ቤቴ) ነው:: ወላጆቻቸው ዘካርያስ እና ሶፍያ እግዚአብሔርን የሚፈሩ : እመ ብርሃንን የሚወዱና ለነዳያን የሚራሩ ነበሩ:: ✏ደጉ ዘካርያስ መስፍን ሲሆን እርሱ በሌለበት የሸዋ ገዢ ሊያገባት በመሞከሩ ቅዱስ ገብርኤል ቀስፎታል:: ሕዝቡ ገዢነቱን ለዘካርያስ ሰጥተውታል:: ከቆይታ በኋላም ድንግል ማርያም የተባረከ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን "ዮሐንስ" አሉት:: በሒደት ግን ዘዮሐንስ (የዮሐንስ) ተብሏል:: ✏ቅዱሱ ዘዮሐንስ እስከ ሰባት ዓመቱ ድረስ በእናቱ እቅፍ ቆይቶ ወደ ትምሕርት ገብቷል:: ጸጋ እግዚአብሔር ጠርቶታልና በአጭር ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቀ:: አደን ይወድ ነበርና ሊያድን ሲወጣ 'ብርሕት ደመና' ድንገት ነጥቃ ከኢትዮጵያ (ሽዋ) ወደ ኢየሩሳሌም (ጐልጐታ) አደረሰችው:: ✏ደስ ብሎት ቅዱሳት መካናትን ተሳልሞ ደመናዋ ወደ ሃገሩ መለሰችው:: ከጥቂት ጊዜ በኋላም ከሰማይ ነቢዩ ኤልያስና መጥምቁ ወርደው ባረኩትና "ክፍልህ ከእኛ ጋር እንዲሆን መንን" አሉት:: ✏ዘዮሐንስ ወላጆቹንና ቤተ ክርስቲያንን እያገለገለ (ዲቁና ነበረውና) ሃያ አምስት ዓመት ሞላው:: ያን ጊዜ ወላጆቹ "እንዳርህ" ቢሉት "የለም! አይሆንም" አላቸው:: አርጅተው ነበርና ስለእነርሱ ዕረፍት ጸለየ:: ፈጣሪም ሰምቶታልና ሁለቱም በክብር ተከታትለው ዐረፉ:: ✏ሕዝቡ በወላጆቹ ፈንታ "እንሹምሕ" ቢሉት "እንቢ" ብሎ ወርቁን : ብሩን : ርስቱን : ቤቱን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገባ:: ጊዜው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ባረፉ በሃምሳ ዓመት አካባቢ ሲሆን አባ ሕዝቅያስ አበ ምኔት ነበሩ:: (ከዚህ በኋላ አንቱ እያልን እንቀጥል) ✏አባ ዘዮሐንስ ለሰባት ዓመታት ገዳሙን ረድተው መነኮሱ:: እንደ ልማዱ ደመና ነጥቆ ወስዷቸው ከኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳሳት ቅስና ተቀብለዋልና በደብረ ሊባኖስ ለሃያ አምስት ዓመታት አገለገሉ:: ቤተ መቅደሱን በመዓልት ሰባት ጊዜ በሌሊት ሰባት ጊዜ ያጥኑ : እልፍ እልፍ ይሰግዱ : ተግተው ይጸልዩ : ይታዘዙም ነበር:: ✏ከዚያም በፈጣሪ ትዕዛዝ በትግራይና በሌሎቹ የሃገራችን ክፍሎች ወንጌልን ሰብከዋል:: እድሜአቸው ሰባ በሆነ ጊዜ ወደ ጌታ መቃብር (ጐልጐታ) ሔደው ተሳልመው በእርሱ (በጌታ) ትዕዛዝ ወደ ደራ (ጣና ዳር) ተመለሱ:: ✏በአካባቢውም ገብርኤልና መስቀል ክብራ የሚባሉ ደጋግ ባለ ትዳሮች ነበሩና በእንግድነት ከቤታቸው አደሩ:: ቤቱ በቅጽበት በበረከት ሞላ:: እነርሱም የጻድቁን አምላክ አመሰገኑ:: ✏ቀጥሎም በመስቀል ክብራ መሪነት ጻድቁ ዘዮሐንስ ወደ ክብራን ገብርኤል ደሴት ገቡ:: (በነገራችን ላይ ደሴቱ ክብራን የተባለ መስቀል ክብራ በምትሰኘው ደግ ሴት ስም ነው:: እርሷና ባሏ ገብርኤል የተቀደሱ ሰዎች ነበሩና::) ✏ጻድቁ አቡነ ዘዮሐንስ ወደ ደሴቶቹ (ክብራንና እንጦንስ ኢየሱስ) እንደ ገቡ ደሴቶቹ በግማሹ የስውራን ቤት : እኩሉ ደግሞ የጣዖት (ዘንዶ) አምላኪዎች መኖሪያ ነበር:: ጻድቁ ክብራን ገብርኤልንና እንጦንስ ኢየሱስን የመሠረቱት በ1315 ዓ/ም አካባቢ በዐፄ ዓምደ ጽዮን ዘመን ነው:: በአካባቢው ዘንዶ ይመለክ ነበርና ያንን በጸሎታቸው አጥፍተው ሕዝቡን አጥምቀዋል:: ✏በዚያም ገዳሙን የወንድና የሴት ብለው ከፈሉ:: የወንዶች ክብራን ሲሆን ሴት አይገባበትም:: አበ ምኔቱም ራሳቸው ጻድቁ ነበሩ:: የሴቶች እንጦንስ ኢየሱስ ከካህናት በቀር ወንድ አይገባበትም:: እመ ምኔቷም እናታችን ቅድስት ክብራ (መስቀል ክብራ) ሆነች:: ✏ጻድቁ አቡነ ዘዮሐንስ በክብራን ለሰላሳ አምስት ዓመታት ተጋድለዋል:: ለጸሎት ከመቆማቸው ብዛት እግራቸው አብጦ : ቆሳስሎ ነበር:: የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወትር ይገለጽላቸው : ያነጋግራቸውም ነበር:: ✏እጅግ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ሠርተው: ለወንጌል እንደሚገባ ኑረው: በተወለዱ በመቶ አምስት ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: ጌታችንም በስማቸው ለተማጸነና ገዳማቸውን ለሳመ የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: ልደታቸው ደግሞ ኅዳር 13 ቀን ይከበራል:: ገዳማቸው (ክብራን ገብርኤልና እንጦንስ ኢየሱስ) ድንቅ ነውና እንድታዩት ተጋብዛቹሃል:: ✅ ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት ✏በምድረ ግብጽ ከታዩ ታላላቅ ከዋክብት አንዱ ቅዱስ ኖብ በሃገረ ንሒሳ ተወልዶ ያደገ ሲሆን ዘመኑም ዘመነ ሰማዕታት (3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነው:: ወላጆቹ በልጅነቱ ብዙ ሃብት ትተውለት ያርፋሉ:: ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ካህኑ ስለ ምናኔና ሰማዕትነት ሲሰብክ ይሰማዋል:: ✏ገና በአሥራ ሁለት ዓመቱ በቤቱ የነበረውን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ መስቀለ ክርስቶስን ሊሸከም ወደ ዐውደ ስምዕ (የምስክርነት አደባባይ -የክርስቲያኖች መገደያ ቦታ) ተጓዘ:: በዚያም በጉባዔ መካከል ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ ምክንያት በሰብዓዊ አካል ሊሸከሙት የማይችሉትን መከራ በልጅ ገላው ተቀብሏል:: ✏በዚያው ልክም ብዙ ተአምራትን ሰርቷል:: በተአምራቱና በጣዕመ ስብከቱም ከመቶ ዘጠና ሺህ በላይ አሕዛብን ወደ ክርስትና መልሶ ሁሉም ተሰይፈዋል:: በእሳት: በስለት: በሰይፍ: በባሕርና በየብስ መከራን ከተቀበለ በኋላ በዚህች ቀን አክሊለ ክብርን ይቀበል ዘንድ አንገቱን ተከልሏል:: ✏ጌታችን የገባለት ቃል ኪዳኑ ግሩም ነውና ዛሬ በግብጽ በድምቀት ይከበራል:: ምንም በእድሜ ልጅ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን አባ (አባታችን) ኖብ ትለዋለች:: ✥ ቸር ጌታ መድኃኔ ዓለም በጻድቁና በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: ✅ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦ 1.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን (ኢትዮጵያዊ) 2.ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት 3.መቶ ዘጠና ሺህ ሰማዕታት (የአባ ኖብ ማኅበር) 4.አባ ተክለ አዶናይ ዘደብረ ሊባኖስ 5.አቡነ ተወልደ መድኅን (ኢትዮጵያዊ) 6.አባ ስምዖን ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት 7.ቅድስት ክብራ (መስቀል ክብራ) ዘእንጦንስ ኢየሱስ ✅ ወርኀዊ በዓላት፦ 1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤጲስቆጶስ) 3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ 4.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ 5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ 6.ሃያ አራቱ ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል) 7.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮጵያዊ)
Показать все...
#ሐምሌ_23 ሐምሌ ሃያ ሦስት በዚች ቀን #ቅድስት_መሪና ሰማዕት ሆነች፣ #ቅዱስ_ለንጊኖስ ሰማዕት ሆነ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅድስት_መሪና ሐምሌ ሃያ ሦስት በዚች ቀን ቅድስት መሪና ሰማዕት ሆነች። የዚችም ቅድስት የአባቷ ስም ዳኬዎስ ነበር እርሱም በአንጾኪያ ሀገር ለጣዖታት ካህናት አለቃ ነበር ያን ጊዜ ንጉሡም ከሀዲው ዳኬዎስ ነበር። አምስት ዓመትም በሆናት ጊዜ እናቷ ሞተች አባቷም ከከተማ ውጭ ለምትኖር ሞግዚት ሰጣት እርሷም ክርስቲያናዊት ነበረች የክርስቶስ የሆነ የሃይማኖት ትምህርትን ሁሉ አስተማረቻት። ዐሥራ አምስት ዓመትም በሆናት ጊዜ አባቷ ሞተ። ከዚህም በኋላ ሰዎች የሰማዕታትን ተጋድሏቸውንና መከራቸውን ሲናገሩ ሰምታ የጌታ ክርስቶስ ፍቅር በልቧ አደረ በሰማዕትነት መሞትንም ፈልጋ ሔደች። በዚያን ጊዜም ከሀዲ መኰንን ወደዚያች አገር ደረሰ እርሷንም አይቶ ወደርሱ አስመጣትና ከወዴት ነሽ አላት ክብር ይግባውና ከጌታ ኢየሱስ ሰዎች ወገን ነኝ ስሜም መሪና ነው አለችው። ደም ግባቷንና ላሕይዋንም አይቶ መታገሥ ተሳነው እሺ ትለው ዘንድ በብዙ ነገር አባበላት። እርሷ ግን ረገመችው የረከሱ አማልክቶቹንም ረገመች። ያን ጊዜም በብረት ዘንጎች ይደበድቧት ዘንድ ደሟ እንደ ውኃ እስኪፈስ ሕዋሳቷን ይቆራርጡ ዘንድ አዘዘ። ያን ጊዜም ወደ ጌታ እግዚአብሔር ጸለየች የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም መጥቶ አዳናት። ሁለተኛም ወደ ወህኒ ቤት ያስገቧት ዘንድ አዘዘ ጌታችንም ወደ ሰማይ አውጥቶ የቅዱሳን ሰማዕታትንና የጻድቃንን ማደሪያዎች አሳይቶ ወደ ቦታዋ መለሳት። በማግሥቱም ሥጋዋን በመጋዝ እንዲሠነጥቁ ጐኖቿንም እንዲሰነጣጥቁና በእሥር ቤት እንዲጥሏት አዘዘ ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ አዳናት። በወህኒ ቤቱ ውስጥም ቁማ ስትጸልይ እጅግ የሚያስፈራ ታላቅ ዘንዶ ወደ ርሷ መጣ በአየችውም ጊዜ ደነገጠች ሰውነቷ ሁሉ ተንቀጠቀጠ መናገርም ተሳናት። ያን ጊዜም እጆቿ በመስቀል ምልክት አምሳል እንደተዘረጉ በልቧም ስትጸልይ ወደርሷ ቀርቦ ዋጣት። ያን ጊዜም ሆዱ ተሠንጥቆ ያለ ጉዳት ወጣች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው። ሁለተኛም በጥቁር ሰው አምሳል ሰይጣንን አየችው እጆቹም በጉልበቶቹ ላይ ተጨብጠው ነበር። ፊቷንም በመስቀል ምልክት አማትባ በራሱ ጠጉር ይዛ ደበደበችው። በእግሮቿም ረገጠችው ያን ጊዜም ክብር ይግባውና የጌታ ክርስቶስ ዕፀ መስቀል ተገለጠላት በላዩም ነጭ ርግብ ተቀምጣ እንዲህ ብላ አነጋገረቻት መሪና ሆይ የመንፈስ ቅዱስን የጸጋ አረቦን ተቀብለሻልና ደስ ይበልሽ። በማግሥቱም መኰንኑ ልብሷን አራቁተው ዘቅዝቀው ሰቅለው እንዲአቃጥሏት ደግሞም ውኃ ከአፈሉበት ጋን ውስጥ እንዲጨምሩዋት አዘዘ። በውስጡም ሁና ስትጸልይ ከሰማይ ርግብ መጣ በአፉም ውስጥ የወርቅ አክሊል ነበር ማሠሪያዋንም ፈትቶ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሦስት ጊዜ አጠመቃት እግዚአብሔርንም እያመሰገነች ከውኃው ውስጥ ወጣች። መኰንኑም እንደ ዳነች በአየ ጊዜ ራሷን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ወደ ሰማዕትነቱ ቦታም በደረሰች ጊዜ ነፍሷን በፍቅር ይቀበል ዘንድ ወደ ጌታችን ጸለየች። ክብር ይግባውና ጌታችንም ተገለጠላት ስሟን ለሚጠራ መታሰቢያዋንም ለሚያደርግ ገድሏንም ለሚጽፍ ወይም ለሚያነበውና ለሚሰማው ኃጢአቱን እንዲአስተሠርይለት ለርሷም ርሱን እንዲሰጣት ቃል ኪዳን ሰጣት። ከዚህም በኋላ ራሷን በሰይፍ ቆረጡ ከእርሷም ብዙ ተአምር ተገለጠ ዕውራን አይተዋልና፣ ሐንካሶች በትክክል ሔደዋልና፣ ደንቆሮዎችም ሰምተዋልና፣ ዲዳዎችም ተናግረዋልና ቁጥር የሌላቸው ብዙ ሰዎችም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ለንጊኖስ_ሰማዕት በዚችም ቀን ከቀጰዶቅያ አገር ለንጊኖስ ሰማዕት ሆነ። ይህም ቅዱስ ከጲላጦስ ጭፍሮች ውስጥ ነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ደኅንነት መከራ እንዲቀበል የፈቀደበት ሰዓት በደረሰ ጊዜ በእርሱ ላይ የፈለጉትን ያደርጉ ዘንድ ለዐመፀኞች ፈቅዶላቸው ነበር። ይህም ለንጊኖስ ጌታን ይሰቅሉት ዘንድ ጲላጦስ ከአዘዛቸው ወታደሮች ውስጥ ነበር። በመስቀል ላይ ከሞተ በኋላ ጌታችንን የቀኝ ጐኑን ወጋው ከጐኑም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ይህንንም አይቶ እጅግ አደነቀ ከዚህም በፊት ፀሐይ እንጨለመ፣ ጨረቃ ደም እንደሆነ፣ ዐለቱም እንደተሠነጠቀ፣ ሙታንም እንደተነሡ አይቶ ነበር። ጌታችንም በተነሣ ጊዜ ስለ ትንሣኤው የሆነውን ሰምቶ ይህን ምሥጢር ይገልጽለት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ሐዋርያው ጴጥሮስንም ላከለት እርሱም ነቢያት ስለ ጌታችን፣ ስለ መከራው፣ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ መሞቱ፣ ስለ መነሣቱ፣ ስለ ዕርገቱም ትንቢት እንደተናገሩ ነገረው። እርሱም ከቅድስት ድንግል በሥጋ ተወልዶ ዓለምን ለማዳን የመጣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እንደሆነ አስረዳው። ያን ጊዜም በቅዱስ ጴጥሮስ ቃል አመነ የምድራዊ ንጉሥ አገልግሎትንም ትቶ ወደ ቀጰዶቅያ ሔደ በውስጧም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደ ሐዋርያት ሰበከ። አይሁድም በጠላትነት ተነሡበት በመሳፍንትም ዘንድ ከሰሱት በላዩም የሐሰት ምስክር አስነሡበት ስለዚህም ራሱን በሰይፍ አስቆረጡት የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ) #share #share #share @yemariyam21 @yemariyam21 @yemariyam21
Показать все...
✅ስንክሳር 🚩ሐምሌ 22 ✅ ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት ✏ሰማዕቱ ተወልዶ ያደገው በአንጾኪያ (ሶርያ) በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን የታላቁ ቅዱስ ፋሲለደስ እና የቅድስት ሶፍያ ልጅ ነው:: ምንም በቤተ መንግስት ውስጥ ቢያድግም ከወላጆቹ ፍቅረ ክርስቶስን : ንጽሕናንና ደግነትን ወርሷል:: ✏በተለይ ነዳያንን ሰብስቦ ዕለት ዕለት ያበላ ነበር:: (መቃርስ ማለት በልሳነ ዮናኒ ብጹዕ : ንዑድ : ክቡር ማለት ነው::) ቅዱሱ ያ የመከራ ዘመን ሲመጣ ሁሉም ቤተሰብ ስለ ክርስቶስ መሞትን በመምረጡ እርሱም ደስ እያለው የመከራው ተካፋይ ሆኗል:: ✏ያን የመሰለ የቤተ መንግስት ክብር ስለ ክርስትና ናቀው:: ተገረፈ:: ተሰቃየ:: በእሳትም ተቃጠለ:: አንድ ጊዜም በአደባባይ የሞተ ሰው በጸሎቱ አስነስቶ "መስክር" አለው:: ከሞት የተነሳውም የክርስቶስን አምላክነት በመመስከሩ በአደባባይ የነበሩ ብዙ አሕዛብ በክርስትና አምነው ተሰይፈዋል:: ✏ቅዱስ መቃርስን ግን ብዙ አሰቃይተው በዚህች ቀን አንገቱን ቆርጠውታል:: ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አጽሙን አፍልሶ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በስሙ ቤተ ክርስቲያን አንጾለታል:: ✅ቅዱስ ለውንትዮስ ሰማዕት ✏ቅዱሱ የተወለደው በተመሳሳይ ዘመን (በቅዱስ መቃርስ) ሲሆን ሃገሩ ጠራብሎስ ትባላለች:: በወቅቱ በወታደርነት ነገሥታቱን ያገለግል ነበር:: ድንግል : ደም ግባት የሞላለት ወጣት ስለ ነበር በሰዎች ፊት ሞገስ ነበረው:: ✏እርሱ ግን ምንም ወታደር ቢሆን ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: በተለይ ደግሞ የዳዊትን መዝሙር እየመላለሰ ይጸልየው : ይወደው ነበር:: ንግግሩ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት የታሸ ነውና ብዙ ጓደኞቹን ከክህደት ወደ ሃይማኖት : ከክፋት ወደ ደግነት መልሷል:: ✏የመከራ ዘመን በደረሰ ጊዜም በገሃድ ስመ ክርስቶስን ይሰብክ ነበር:: ክፉ ሰዎች ከሰውት በመኮንኑ ፊት በቀረበ ጊዜም አልፈራም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው እየደበደቡት : ደሙ እንደ ጐርፍ እየተቀዳ እርሱ ግን ይዘምር ነበር:: ✏በመጨረሻም ስለ ክርስቶስ ፍቅር በዚህች ቀን አንገቱን ተሰይፏል:: ቅዱስ ለውንትዮስ እጅግ ተአምረኛ ሰማዕት ነውና በእምነት እንጥራው:: ✥ እግዚአብሔር ዐጽመ ሰማዕታትን ይጠብቅልን:: ከሰማዕታቱ ጽናትን : ጸጋ በረከትን ይክፈለን:: 🚩ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦ 1.አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት (ኢትዮጵያዊ) 2.ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት (የፋሲለደስ ልጅ) 3.ቅዱስ ለውንትዮስ (ክቡር ሰማዕት) 4.አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት (ቅዳሴ ቤታቸው) 5.ቅዱስ መርካሎስ 🚩ወርኀዊ በዓላት፦ 1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት 2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ 3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ) 4.አባ ጳውሊ የዋህ
Показать все...
✅ ስንክሳር 🚩ሐምሌ 21 ✅ ድንግል እመቤታችን እና ቅዱስ ዑራኤል ✏በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት በዚህች ቀን ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ዑራኤል:- 1.ድንግል ማርያም በአካለ ሥጋ እያለች ወደ ሰማይ አሳርጓታል:: በሠረገላ ብርሃን ጭኖ: በክንፎቹም ተሸክሞ: አስቀድሞ ገነትን ቀጥሎም ሲዖልን አስጐብኝቷታል:: በዚህም ምክንያት እመ ብርሃን ስለ ኃጥአን የምታለቅስ: የምትለምንና የምትማልድ ሆናለች:: ለምናም አልቀረች የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች:: 2.ቅዱሱ መልአክ እመ ብርሃንን በስደቷ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መርቶ አምጥቷታል:: በክንፉ ተሸክሞ: በአራቱም አቅጣጫ አዙሮ አሳይቶ አሥራት እንድትቀበል አድርጓል:: 3.ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ ደሙን በጽዋዕ አድርጐ በኢትዮጵያ ወንዞች ላይ አፍስሷል:: 4.ለብዙ ቅዱሳን (አባ ጊዮርጊስን ጨምሮ) ጽዋዐ ልቡናን አጠጥቷል:: ✅ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ኢትዮጵያዊ ✏ወላጆቻቸው ማርቆስ እና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: ተአምራትን ገና ከእናታቸው ማኅጸን ጀምሮ ይሠሩ የነበሩት ጻድቁ በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው መንነዋል:: በስብከተ ወንጌልም ትግራይና አካባቢውን አድርሰዋል:: በነዚህም ጊዜያት ብዙ አርድእትን አፍርተዋል:: ✏በጋስጫ ገዳም መስርተው የወንድና የሴት ብለውም ለይተዋል:: ሲጸልዩም ሆነ ሲያስተምሩ ተደሞ ይመጣባቸው የነበረ ሲሆን አንድ ቀን እባቡን ዓሣ አድርገው ደቀ መዛሙርትን አስደንቀዋል:: ✏ከጾም: ከጸሎትና ከስግደት ባሻገር ከወቅቱ ንጉሥ ዓምደ ጽዮን መከራ በመቀበላቸው እንደ ሰማዕትም ይቆጠራሉ:: ከብዙ የገድል ዓመታት በኋላም በ1330 ዓ/ም በዚህች ቀን ትግራይ ውስጥ ዐርፈዋል:: በቆይታ ግን ወደ ጋስጫ ዐጽማቸው ፈልሷል:: ✅ቅዱስ ላዕከ ማርያም ኢትዮጵያዊ ✏ቅዱሱ የአፄ ናዖድ የልጅ ልጅ : የቅድስት ሮማነ ወርቅ ልጅ : የልብነ ድንግል የእህት ልጅና የገላውዴዎስ አጐት ነው:: በግራኝ አህመድ ዘመን ተማርኮ ወደ የመን : ከዛም ቱርክ ተወስዷል:: ሃይማኖቴን አልክድም ስላለ ብዙ አሰቃይተው : አባለ ዘሩን ቆርጠው ጃንደረባ አደረጉት:: በድንቅ ተአምር ግን ወደ ሃገሩ ተመለሰ:: እስከ ዕለተ ሞቱም ነዳያንን ሲያበላ ኑሮ ዛሬ ዐርፏል:: ✅ቅዱስ ሱስንዮስ ✏በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የኤፌሶን ሰው ሲሆን ጃንደረባም ነበር:: በ431 ዓ/ም ሁለት መቶውን የጉባዔ ኤፌሶን ሊቃውንት አገልግሎ በዛው ዓመት አርፏል:: ቅዱስ ቄርሎስ ገንዞ ቀብሮታል:: ✅ብጹዕ አወ ክርስቶስ ✏ከተባረከች ሚስቱ ጋር በአንድ ቤት ውስጥ : ግን ደግሞ በድንግልና ኑረዋል:: ቀን ቀን እንግዳ ሲቀበሉ: ነዳያንን ሲያበሉ ውለው ሌሊት ሲገሰግዱና ሲጸልዩ ያድሩ ነበር:: ጌታችን ከሰማይ መስክሮላቸው ዛሬ ዐርፈዋል:: ✅ቅዱስ ዮራኖስ ✏በሉቃስ ወንጌል ላይ (ሉቃ. 23:47) የምናገኘው የመቶ አለቃው ሲሆን በጌታችን ትንሣኤ ቀን የጠፋች ዓይኑ በርታለት በክርስቶስ አምኖ ለሰማዕትነት በቅቷል:: ✥ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟን ፍቅሯን : ከቅዱሳኑ ሁሉ ጸጋ በረከትን እግዚአብሔር ያድለን:: 🚩ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦ 1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ 2.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት 3.አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ጻድቅ (ኢትዮጵያዊ) 4.ቅዱስ ላዕከ ማርያም ሔር (ኢትዮጵያዊ) 5.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ኢትዮጵያዊ) ልደታቸው 6.ብጹዕ አወ ክርስቶስና ሚስቱ (ጻድቃን) 7.ቅዱስ ሱስንዮስ ጻድቅ 8.ቅዱስ ዮራኖስ መኮንን (የመቶ አለቃው) 🚩ወርኀዊ በዓላት፦ 1.አበው ጎርጎርዮሳት 2.አቡነ ምዕመነ ድንግል 3.አቡነ አምደ ሥላሴ 4.አባ አሮን ሶርያዊ 5.አባ መርትያኖስ ጻድቅ
Показать все...
ወእመአኮ ወእመአኮ ከመወሬዛ ሀየል ውስጠ አድባር ቤቴል አዝ......... ሀሌሉያ አበባ ነሽ ድንግል " " " ግዜው ያላለፈ " " " አብቦ ጠውልጎ " " " ደርቆ ያልረገፈ አዛኝ የለኝም ድንግል ሳለው በህይወቴ ጡቶን ሳልጠግበው ድሮ ጥላኝ እናቴ አንቻን የሰጠኝ ጌታ ይመስገንልኝ ከንግዲ ወዲያ ካንቺ ማንም አይለየኝ አዝ....... ሀሌሉያ እኔም እንደ ኤፍሬም " " " እንዳመሰግንሽ " " " አመስግነኝ የሚል " " " አሰሚኝ ከቃልሽ አዛኝ የለኝም ድንግል------- አዝ ሀሌሉያ ማእበሉ ገፍቶ " " " ቢታወክ ህይወቴ " " " ሐመረ ኖህ ድንግል " " " ሆንሺኝ መሰረቴ አዛኝ የለኝም ድንግል----- አዝ ሀሌሉያ ሠባራውን ልቤን " " " ደገፍሽው እንዲቆም " " " ውለታሽ አያልቅም " " " ብጮህ ለዘላለም አዛኝ የለኝም ድንግል- - - - -
Показать все...