cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የልቤን በብዕር ❤❤

የኔን ስም ከስሟ በላይ ያከበረች እንደ እህት አንሶባት እንደ እናት የኖረች የኔ ሁለ ነገር እሷ ብርሃኔ አለም ምጨልመኝ ስትርቅ ከጎኔ የእናቴ ስጦታ ሁለተኛ እናቴ የሃዘኔ ተካፋይ ብርታቴ ፅናቴ ፍቅር ያስተማረችኝ ንፁህ ማንነቴ እህት ምለው ቃል ምያንሳት ምርጧ እህቴ ከራሷ አብልጣ ስለኔ አሳቢ ቁጭ አርጋኝ እንደ ልጅ ገላዬን አጣቢ ደስታዬን ለማንሳት ደስታዋን የጣለች እንደ እህቴ ያለች ሌላ ሴት ማንአለች

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
328
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

አላውቅም 😂 መሳቅ ግን ምንድነው እኔ አላውቅም ስቄ መረዳት አቃተኝ ጠይቄ ጠይቄ አልቅሼም አላውቅም ምንድነው ማልቀስ አንገት አቀርቅሮ ከአይን እንባ ማፍሰስ አፍቅሬም አላውቅም አይገባኝም ጥቅሙ በፍቅር የመክነፍ በፍቅር የመስጠሙ በልቼም አላውቅም ጠጥቼም ለብሼም አመስግኜ አላውቅም ረግሜም ወቅሼም ኖሬም እኮ አላውቅም ምንድነው መኖር😜 ይህን ግጥምስ መች ፃፍኩኝ ጨብጬ ብዕር 😜 ✍✍✍✍✍ በ Birukti @yfonkowa @Tirsite_mikael
Показать все...
የሌት ማሕሌት (በእውቀቱ ስዩም) ትንሽ ቆየት ብሎ ፥ ኮረንቲው ይጠፋል እሱን ተከትሎ፥ደምኖ ያካፋል ከናፍቆትሽ በቀር፥ ሁሉ ነገር ያልፋል :: አሁን መብራት ጠፋ ፥ ተረኛ ነን አይደል ቁና ይዠ ቀረብሁ፥ ጨለማ ሲታደል ፤ እያገላበጠ ብቻነት አመሰኝ፥ “ ዝናቡ እየጣለ ጋራ ጋራውን ጎርፍ ያመጣሽ ‘ንደሁ ልጠብቅ ጎርፉን “ የሚል እንጉርጉሮ፥ በድንገት ታወሰኝ :: ግን ይሄ ትውስታ አራራይ ትዝታ ለቆሰለው ልቤ፥ መዳኒት አልሆነም ያባቶቼ ዘፈን፤ ለኔ አልተዘፈነም፤ ማዶ ዝናብ ዘንቧል፤ ዶፉን ተከናንቧል- -እንጦጦ-ዲልዲላ በገፈጅ ይመስል ፥ቀበናም ቢሞላ ምንም አያመጣም፤ ከ’ድፍ ውሀ ሌላ እሳት ነው ፍጥረትሽ፥ ከውሃ ጋ አትኖሪም አንቺ መብረቅ እንጂ፥ ጎርፍ አትሳፈሪም። (አዳምኤል) @yfonkowa @Tirsite_mikael
Показать все...
ያንድ ምሽት ናፍቆት ዛሬ ታምራለች ጨረቃ ፊትሽን ፊቷ ላይ ፣ እንደ ጭንብል አጥልቃ እንሆ እኔም ቆሚያለሁ የዛፉን መልክ መልኬ አድርጌ በሩቅ ማየት ተፈቅዶልኝ መንካቱን ግን ተነፍጌ [ በእውቀቱ ስዩም ] @yfonkowa @Tirsite_mikael
Показать все...
እኔ ሆይ ተይ በቃሽ እኔ ሆይ ተይ በቃ እራስሽን አትደልይ ገብቶሽ እንዳልገባው እውነቱን አትደልይ ለማይዘልቅ መውደድ ለማይከርም ፍቅር በግዜሽ በእድሜሽ መቀለዱ ይቅር እርቀሽ ተቀመጭ ከወረት አብሮነት ያለፈው በቃ አልፏል ኑሪ አሁን የእውነት እኔ ሆይ እሺ በይ የቆምሽበት ቦታ አይመጥንም ላንቺ እውነቱን ተቀበይ ትችያለሽ በርቺ ሼን #እናት
Показать все...
ያመጣል መንገድ፣ ይወስዳል መንገድ መንገድ ዓይኑ ይፍሰስ አይባልም ደርሶ የወሰደውን ሰው ያመጣል መልሶ #ኢንት
Показать все...
. . አ ን ዳ ን ዴ መኖር ግራ ይገባናል.. ለምን እንደምንኖር. ለማን እንደምንኖር. እንዴት እንደምንኖር ሳይቀር ይጠፋብናል.. ግን ደሞ ገብቶንም ይሁን ሳይገባን መርጠንም ይሁን ተመርጠን መኖር ይቀጥላል.. "በቃቹ!" እስኪለን መኖር ይቀጥላል............ 🦋 #ዮቶራዊት🦋🦋..
Показать все...
........ቃልሽ ቀን ነበረው........ ------- -------- ከጎጆው አጠገብ በረንዳው ላይ ቆሞ ስለሷ እያሰበ ደጋግሞ ደጋግሞ የጻፈውን ግጥም እያነበበችው የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው 😢😢 . . ‘’ቃልሽ ቀን ነበረው… ቃልሽ ቅን ነበረው… ቃልሽ ቀን ገደለው…’’ የሚለውን መግብያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ ቃሏንና ቀኗን አንድ ላይ አስባ መአልትና ሌቱን አንድ ላይ ሰብስባ . . የገደለችውን ቀን ልክ እንዳወቀችው የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው❤️❤️ ‘’ህይወት ውጣ ውረድ የትሙ ብዙ ነው ቀን የገደልሽውም አውቀሽ ሳታውቂ ነው . . . በፀሀይቱና በጨረቃ መሀል በሰዓታት እጣ በቀን ማታ ክፍል ከአንደኛው ትንፋሼ ቀጣዩ ሲቀጥል ስጠብቅሽ ነበር ከእስትንፋሴ እኩል😍😍 እዛው ነሽ አውቃለሁ እዚህ ነሽ መጥተሻል ልቤ ገራገር ነው እስከዚህ ያምንሻል!’’ . . የሚለውን መዝጊያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ ፎቶ ደብዳቤውን 💌💌አንድላይ ሰብስባ ፍቅር የሰጣትን በፍቅር አስባ . . ልበ ገራገሩን… ልቡን እንዳደማች ልክ እንዳወቀችው የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው !! #ብሩክቲ ነኝ 😉 @Yfonkowa @saktawa
Показать все...
.........ሲነጋ❤️❤️❤️ ስለምንወዳቸው ፤ስለምናከብራቸው ፤ቦታ ስለምንሰጣቸው፤ ስለዋሉልን ፤ ስለተረዳናቸው ... ፦ የምንሰጣቸውን ክብር ፤ መውደድ፤ የበዛ ትህትና፤ ገብቶን እንዳልገባን የምንሆነውን፤ የምንለግሰውን ..... ። ሞኛ ሞኝ ሆነን ከመሰላቸው ፤ ለራሳችን ካለን ትንሽ ክብር የመነጨ ሲመስላቸው ፤ ሲያሳንሱን ... ። ግርግር ሳንፈጥር ፤ ሳንጨረጨር ፤ ሳናብራራ ሳይጠይቁን የሰጠናቸውን ሳንጠይቅ መንጠቅ ነው ያለብን !! © Adhanom Mitiku✍
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
በዚህች ቀን ነበር በምጥ የተጨነቅሽው በዚህች ቀን ነበር ማርያም ትማርሽ የተባልሽው በዚህች ቀን ነበር ከማንም በፊት ያየሽኝ በዚህች ቀን ነበር እኔ ለአንቺ አንቺ ለኔ የተሰጠሽኝ በዚህች ቀን ነበር እማ አምጠሽ የወለድሽኝ አመሰግናለሁ እናቴ😘😘 HBD to me😍😍
Показать все...
እቴዋ መነኩሲት ___ እኔ ምንም አልልም አላወራምም.. ዝምም አልልም.. ቀን እጂ (እቴዋ ) ሰው ሰውን አይጥልም! ባወራም ባወራም ማውራትም አልችል፣ ዝም ብዬ በምስር ዝም ብል ዝም ብል፣ ባዶ ትንፍሽ ብቻ በባዶ መዋለል ተልሚድ ሁኖ መዋል፣ ባዶ ጨረቃ ፈርቶ በባዶ መገልገል፣ ባዶ ጥላ ይዞ በጨለማ ማታ በጥላ መጠለል፣ ሲመሳጠር ጊዜ ከሰው ሲወዳጅ፣ ይሆናል ገመድ ይከዳል ከደጅ፣ እቴዋ ገዳሜ ቀበጢት ዋልፈሰስ፣ እቴዋ መነኩሲት ሂያጅ መጪ በፈረስ፣ ምነው ልጓሙ በወዝሽ ዳዊትሽ አደፈስ.. ገብስ አጣ ወይ እግርሽ ፥ከደጅሽ የሚያደርስ፣ ...ኧረ ያንቺስ መሞልከስ... _ ግዕዝ ሙላት ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት @yfonkowa @yfonkowa @yfonkowa @yfonkowa
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.