cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Knowing the bible

The HOLY BIBLE is so amazing so let's talk about it 🙌 If u hv something to share @kirubel77

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
189
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

. የቀጠለ 🙏💛☀️💛🙏 #ክፍል 2⃣ በመግቢያችን በተወሰነ ደረጃ እንዳየነው ተስፋ የሚለውን ቃል የሰው ልጅ በተለያየ መንገድ ይናገረዋል ደግሞም ይኖረዋል። አንዳንዶች፡- ሰው ተስፋ መቁረጥ የሚችለው ራሱ ተስፋ ስላለ ነው ይላሉ። ስለሆነም ብዙ ነገር አጥቶ ሰው መኖር ይችላል፤ ያለ ተስፋ ግን አንድ ሰከንድ መኖር አይችልም ሲባልም እንሰማለን። የተለያዩ የተስፋ አይነቶች እንዳሉ ከአጠቃላይ አኗኗራችንና ከእግዚአብሔር ቃል በመነሳት መናገር ይቻላል። እርሱም አጠቃላይ ተስፋ እና ውስን ተስፋ በማለት ልንመድባቸው እንችላለን። አጠቃላይ ተስፋ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ቸርነቱን የተገለጠበት ምልክትና ምስክር ነው። “ . . . እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።” ማቴ5÷44-45 “ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራ እየሠራ፥ ከሰማይ ዝናብን ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ሲሰጠን፥ ልባችንንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም።” ሐዋ14÷17 ጥቅሶቹ በተለያየ አቀራረብ የተጻፉ ናቸው፤ ከዚህ የእግዚአብሔር ቃል ሁለት ትልልቅ አሳቦችን እናገኛለን፤ የመጀመሪያው ያለ ልዩነት ለጻድቁና ለኃጢአተኛውም የተሰጠ ቸርነትና የተገለጠ የእግዚአብሔር ሥራ ሲሆን ሁለተኛው በዚህ ውስጥ የፍጥረቱ እግዚአብሔርን ተስፋ ማድረግን እናስተውላለን። ለምሳሌ ገበሬው በጠራራ ጸሐይ ሲያርስና ሲያለሰልስ እንደሚዘንብ ተስፋ አድርጎ ነው፤ ዝናብ እያራሰው ምናልባትም ለልጆቹ በቂ ቀለብ ሳይኖረው ያለውን አውጥቶ ከአፈር ሲደባልቀው እንደሚበቅል ተስፋ አድርጎ ነው፤ ሲያርም ሲኮተኩት ብዙ ፍሬ እንደሚሰበስብ ተስፋ ሰንቆ ነው። ተስፋ ባይኖር ከእነዚህ ውስጥ አንዱንም የማድረግ ጉልበት አይኖረውም ነበር። በዚህ አጠቃላይ ተስፋ ውስጥ ሌላኛው መንገድ ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር እርቅ የማድረግና ከሰው ውድቀት ማግስት የተሰጠ ታላቅ ተስፋ ነው። “ . . . በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።” ዘፍ3÷15 ይህ የተነገረው ለጠላትህ ነው፤ ለእርሱ መርዶ ሲሆን ለአንተ ግን ታላቅ ተስፋ ነው። ይህ ተስፋ የድነት ተስፋ፣ የልጅነት ተስፋ፣ ወደ ቀደመው ክብርህ የመመለስ ተስፋ ነው። በመመለስና በመታዘዝ ብቻ የምናገኘው የተስፋ ሙላት ነው። ሁለተኛው ውስን ተስፋ የምንለው ነው። በተለይ ይህኛው አሳብ በጥንቃቄ ልናየው የሚገባ መሆኑን ላሳስብ እወዳለሁ። ጌታ አለኝ፣ ተናገረኝ፣ ገለጠልኝ ያንንና ይህንን ተስፋ ሰጠኝ ወዘተ ማለትና በእግዚአብሔር ቃል ተረጋግቶ ከመፈተሸ ይልቅ በስሜት መክነፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ በቅዱሳን መካከል እየጨመረ መጥቷል። እርሱን ማስተካከልና ሚዛን ማስጠበቅ ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል። አንዳንድ ጊዜ በሆኑ ሰዎች እጅ አንድ ነገር ስለተበላሸ ብቻ ያ ጉዳይ ስህተት ነው ብሎ መፈረጅ ራሱ ስህተት ነው። ለምሳሌ በጸጋ ስጦታ አጠቃቀም የሆኑ ሰዎች ስላበላሹ የጸጋ ስጦታ የሚባል የለም ማለት ስህተት ነው። ስለ ጸጋ ስጦታ ትክክለኛውን ትምህርት ማስተማርና ትክክለኛው አገልግሎት እንዲኖር ማድረግ ተገቢ ነው። ውስን ተስፋን እግዚአብሔር ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፣ ለቡድን፣ ለግለሰብ፣ ለማህበረሰብ ወዘተ በጊዜ ውስጥ የሚፈጸም ተስፋ ሊሰጥ ይችላል። ይህ ተስፋ ድፍን አይደለም፤ በጊዜ፣ በስፍራ፣ በሁኔታ የተቀነበበ ሲፈጸምና ሳይፈጸምም የሚታይ ተስፋ ነው። ለአንድ ግለሰብ የተነገረ ተስፋ ቢሆን ቢያንስ የመጨረሻ ጣሪያው ሰውየው ሳይሞት የሚፈጸም ነው። አንዳንዱ ደግሞ ከእድሜ ጋር የተያያዘ ሊሆን ግድ ነው። ለምሳሌ ያህል ታገለግላለህ፣ ታገባለህ የመሳሰሉት ቢሆን ተስፋው፤ (አብርሃም በመቶ አመቱ ወልዷል ሙሴም በሰማንያ አመቱ ለአገልግሎት ተጠርቷል) ካላልን በስተቀር እነዚህ ጉልበታም ሳለን የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው። ስለዚህ ስለ ተገባልን ተስፋ ከተቻኮለ ስሜት ወጥተን በብስለትና በእግዚአብሔር ቃል ሚዛን በማጥለል እናስብ ዘንድ ማበረታታት እፈልጋለሁ። ይቀጥላል . . .
Показать все...
"የተስፋን በር ጠብቅ"☺️😇 "እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።" መዝ27÷14 "በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።" ሮሜ5÷5 "የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።" ሐዋ2÷39 #ክፍል 1⃣ አጠቃላይ መንደርደሪያ፡- “ተስፋ” የሚለው ቃል በአማኙም ሆነ በአላማኙ የሚታወቅና ሰዉም እንደየ ምልከታው ፍቺ የሚሰጠው ቃል ነው። በመጽሐፍ ቅዱሳችንም ልክ ከላይ እንዳስቀመጥነው ጥቅስ በተለያዩ አውዶች ከሁለት መቶ ስልሳ ሦስት ጊዜ በላይ ተስፋ የሚለው ቃል እንደተጠቀሰ ማረጋገጥ እንችላለን። ስፐርጂን የተባለው ሰው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የተስፋ ቃሎች ከተናገረው ሰዎች እንዲህ ይጠቅሱታል፡- “የመጽሐፍ ቅዱስ የተስፋ ቃሎች በእምነት ፈርመን ለክፍያ ወደ እግዚአብሔር እንደምናመጣቸው ከሰማይ ባንክ የተገኙ ቼኮች ናቸው።” ብሏል ሌላው ርዕሳችንን ስንመለከት የምንነጋገርው ስለ ተስፋ ቢሆንም “መጠበቅ” የሚለውን ቃልም በቀላሉ የማናልፈው መሆኑን ልብ ይሏል፤ ምክንያቱም ስለ ተስፋ የምናወራበት ዋናው ተሸካሚ እርሱ ስለሆነ ነው። “ተስፋ” በሁለት ቃላት ተሰቅዛ የተያዘች ትመስላለች፤ “በመቁረጥ” እና “አለመቁረጥ” የመጠበቅ ዋጋ የሚገባን ይህን ጊዜ ነው። እናም ተስፋ መቁረጥ ስላለ ተስፋ ላለመቁረጥ በሯን ጠብቅ ማለት ወደድን። ታላላቅ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ወይም ተቋማት በሮቻቸው በጥንቃቄ በታመኑ ጠባቂዎች ይጠበቃሉ። እንዲሁም ታላላቅ ታዋቂ ሰዎችና የመንግስት ባለስልጣናትም በተለይም በአፍሪካችን በተመሳሳይ ሁኔታ እነርሱ ራሳቸውና የእነርሱ የሆነውን ሁሉ ያስጠብቃሉ። ለምን ማስጠበቅ አስፈለጋቸው ቢባል ቢያንስ ሁለት አሳማኝ ምክንያት ይኖራቸዋል። የመጀመሪያው ከበሩ በስቲያ ንብረት/ የተከማቸ ሃብት ስላለና በሌባ እንዳይዘረፍ ሲሆን ሁለተኛውና ዋናው ነፍሳቸውን ጭምር የሚፈልግ ሊኖር ስለሚችል በጥብቅ ይጠበቃሉ ያስጠብቃሉም። በእነዚህና በሌሎች በተለያዩ ምክንያቶች የሚያጠቃቸው ሰው ሊኖር ይችላል በሚል አስቀድመው ጥንቃቄ ያደርጋሉ። በዓለማችን ላይ የገንዘብ ብቻ ሳይሆን የሰው ነፍስ ሌባም ስላለ በተቻላቸው መጠን ራሳቸውንና ያለቸውን ለመጠበቅ ሰዎች ይተጋሉ። በተለይም ባለ ስልጣናትና የታወቁ ሰዎች በአንድም በሌላ ብዙ ጠላት ሊኖርባቸው ስለሚችል ማን ምን እንደሚያደርግ ስለማይታወቅ ያለው አማራጭ ጠንካራ ጥበቃ ማቆም ይሆናል። የሰው ልጅ ሁለት አይነት ሃብት አለው አንደኛው የሚታይ የሚዳሰስ የሚጨበጥ የሚቆጠር . . . “የዚህ ዓለም ገንዘብ” ብሎ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ሲሆን፤ ሁለተኛው የማይታየው ውስጣዊ ሃብት ነው። እምነት ተስፋ ትዕግስት ቸርነት በጎነት ቅንነት . . . የሚባሉ ሃብቶች የሰው ውስጣዊ ሃብቶች ናቸው። ሁለቱም በሌባ ሊሰረቁ ይችላሉ፤ የሚታየውን የሚታይ ሌባ ይዘርፈዋል የማይታየውንም የማናየው ሌባ ሊዘርፈው ይችላል። የሚታየው ንብረታችን እንዳይዘረፍ በራችንን እንደምንዘጋ ሁሉ የማይታየውም ሃብታችን እንዳይዘረፍ የውስጥ በራችንን መዝጋት ይኖርብናል ማለት ነው። "ተስፋ" በር አለው፤ ካልጠበቅነው ይሰረቃል፤ ከጠበቅነው ይጠበቃል። ስለተስፋ ሲነሳ ብዙ ነገሮች ሊታሰቡን ይችላሉ። ከሁሉ አስቀድሞ መታሰብ ያለበት ግን ከተስፋው በር በስተውስጥ እግዚአብሔር የጠበቀልን ሃብት እንዳለ ነው። ይቀጥላል . .
Показать все...
👇የእለት እንጀራ 👏ማንበብ _ማሰላሰል _ከራሰ ህይወት ጋር ማዛመድ። ✝ወደ እግዚአብሔር መጮህና ዉጤቱ 💟 ኤርምያስ 33 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ኤርምያስ ገና በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል ሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል መጣለት፦ ² ስሙ እግዚአብሔር የሆነ፥ ያደረገው እግዚአብሔር፥ ያጸናውም ዘንድ የሠራው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ³ ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ። ⁴ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለአፈር ድልድልና ለምሽግ ስለ ፈረሱ ስለዚህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች እንዲህ ይላልና፦ ⁵ ከለዳውያን ለመዋጋት መጥተዋል፤ ነገር ግን በቍጣዬና በመዓቴ በገደልኋቸው ሰዎች ሬሳዎች ሊሞሉአቸው ነው፥ ስለ ክፋታቸው ሁሉ ፊቴን ከዚህች ከተማ ሰውሬአለሁና። ⁶ እነሆ፥ ፈውስንና መድኃኒትን አመጣላታለሁ፥ እፈውሳቸውማለሁ፤ የሰላምንና የእውነትን ብዛት እገልጥላቸዋለሁ። ⁷ የይሁዳን ምርኮና የእስራኤልንም ምርኮ እመልሳለሁ፥ ቀድሞም እንደ ነበሩ አድርጌ እሠራቸዋለሁ። ⁸ እኔንም ከበደሉበት ኃጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ እኔንም የበደሉኝን ያመፀብኝንም ኃጢአታቸውን ሁሉ ይቅር እላለሁ። ⁹ ይህችም ከተማ እኔ የምሠራላቸውን በጎነት ሁሉ በሚሰሙ እኔም ስላመጣሁላቸው በጎነትና ሰላም ሁሉ በሚፈሩና በሚደነግጡ አሕዛብ ሁሉ ፊት ለደስታ ስም ለምስጋናም ለክብርም ትሆናለች። ¹⁰ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተ፦ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት በምትሉአት በዚህች ስፍራ፥ የሚቀመጥባቸው በሌላ፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባድማ በሆኑ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ፥ ¹¹ የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚሉ ድምፅ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡት ድምፅ እንደ ገና ይሰማል። የምድርን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር። ¹² የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ባድማ ሆኖ፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባለው በዚህ ስፍራ በከተሞችም ሁሉ መንጎቻቸውን የሚያሳርፉት የእረኞች መኖሪያ ይሆናል። ¹³ በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች በቈላውም ባሉ ከተሞች በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም አገር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች መንጎቹ በተቈጣጣሪው እጅ እንደ ገና ያልፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። ¹⁴ እነሆ፥ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን መልካም ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር። ¹⁵ በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቍጥቋጥ አበቅልለታለሁ፤ እርሱም ፍርድንና ጽድቅን በምድር ያደርጋል። ¹⁶ በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም ተዘልላ ትቀመጣለች፤ የምትጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው። ¹⁷ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከዳዊት ዘንድ አይታጣም፤ ¹⁸ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት የሚያቀርብ የእህሉንም ቍርባን የሚያቃጥል ሁልጊዜም የሚሠዋ ሰው ከሌዋውያን ካህናት ዘንድ በእኔ ፊት አይታጣም። ¹⁹ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ ²⁰ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቀንና ሌሊት በወራቱ እንዳይሆን የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፥ ²¹ በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ልጅ እንዳይሆንለት ከባሪዬ ከዳዊት ጋር፥ ከአገልጋዮቼም ከሌዋውያን ካህናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈርሳል። ²² የሰማይን ሠራዊት መቍጠር የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፥ እንዲሁ የባሪያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ። ²³ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ ²⁴ ይህ ሕዝብ፦ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሁለቱን ወገን ጥሎአቸዋል ያለውን ነገር አትመለከትምን? እንዲሁ በፊታቸው ከእንግዲህ ወዲህ ሕዝብ እንዳይሆን ሕዝቤን አቃልለዋል። ²⁵ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን የሰማይንና የምድርንም ሥርዓት ያላጸናሁ እንደሆነ፥ ²⁶ እኔም ደግሞ በአብርሃምና በይስሐቅ በያዕቆብም ዘር ላይ ገዦች ይሆኑ ዘንድ ከዘሩ እንዳልወስድ፥ የያዕቆብንና የባሪያዬን የዳዊትን ዘር እጥላለሁ፤ ምርኮአቸውን እመልሳለሁና፥ እምራቸውማለሁና።
Показать все...
☀️🌻☀️🌻☀️🌻☀️🌻☀️🌻☀️🌻☀️🌻 ከቆመው ጋር አትቁም🤔 ❝ፍቅርን ተከታተሉ፤ መንፈሳዊ ስጦታዎችን፣ በተለይም ትንቢት የመናገርን ስጦታ በብርቱ ፈልጉ።❞ 1ኛ ቆሮንቶስ 14: 1 የተአምራት፡ የትንቢትና በልሳን የመናገር ሥጦታዎች በሐዋርያት ዘመን በነበረች ቤተክርስቲያን ጊዜ ብቻ የሰራና ከዚያ በኃላ ግን #ቆሟል ብሎ ቆሞ የሚሟገት ሰው እንቅፋት ሆኖብህ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ከመፈለግ ከማቆም ውጪ የሚረባህ ነገር ስለሌው አልፈኸው ተራመድ፡፡ የዚህ አስተምህሮ ሰለባ የሆኑ ሰዎች መቆምና ቆሟል ብሎ መሟገት ሕይወታቸው ስለሆነ አንተም ከእነሱ ጋር ቆመህ እንድትነታረክ ይጋብዙሃል፡፡ ትልቁ ግብዣቸው ክርክር ነውና፡፡ ፀሎት አላርጂካቸው ነው!! ትናንት በልሳን ስፀልይ በመንፈስ ቅዱስ እሳት ሲቀጣጠል፣ በብዙ ትንቢታዊ መልዕክት ሲፅናና የነበረ ሰው ዛሬ አንድ መንገደኛ መጽሐፍ አንብቦ ተሳስቻለሁ ብሎ እንቁ የሆነውን ስጦታውን ከጣለ የአስተሳሰብ ችግር ያለበት ቀድሞውኑ ያልተተከለ ሰው ይመስለኛል፡፡ ደግሞ በየዘመናቱ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ተዓምራዊ ሥራ፣ የትንቢት አገልግሎት ሽምጥጥ አርጎ መካድ እውርነትስ አይደለም? ጓዴ! የንትርክ ግብዣቸውን ወዲህ ጥለህ የእግዚአብሔርን ክብር የተአምራት፣ የትቢንትና በልሳን የመናገርን ስጦታ በብርቱ ፈልግ! ☀️🌻☀️🌻☀️🌻☀️🌻☀️🌻☀️🌻☀️🌻
Показать все...
❣️ተቆጠረልን❣️ 🔸ይሄ ቃል በጣም ከባድ ነው፡፡ አብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሁኖ ተቆጠረለት ሲል፣ ጽድቅ የእግዚአብሔር ባህሪይ ነበር፣ ነገር ግን ለአብርሃም በእምነቱ ምክንያት ለእርሱ ተቆጠረለት፡፡ 🔷ስለዚህ “ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት። ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት” የሚለው ቃል የተጻፈው ለእርሱ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ጽድቅ አድርጎ ለሚቈጥርልን፣ ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው በእርሱ ለምናምን ለእኛም ጭምር ነው። [ ሮሜ 4፥22-25 ] 🔶እርሱ ስለ ኀጢአታችን እንዲሞት ዐልፎ ተሰጠ፤ እኛን ጻድቅ አድርጎ ለማቅረብም ከሞት ተነሣ። ምን ማለት መሰላችሁ፣ ኃጢአት የማያውቀው እርሱ[ኢየሱስ] ኃጢአት ሆነ፤ ኢየሱስ ኃጢአት ሰርቶ አይደለም ኃጢአት የሆነው፡፡ 🔷ነገር ግን የእናንተን ኃጢአት ተቀብሎ በእናንተ ቦታ ሁኖ በመስቀል ሞት ተቀጣላችሁ፡፡ ልክ እርሱ የእናንተን ጽዋ ሲጠጣ፤ ለእናንተ ደግሞ የክርስቶስን ጽድቅ ተቀበላችሁ፡፡ ኢየሱስ ኃጢአት ሰርቶ ኃጢአት እንዳልሆነ ሁሉ፤ እናንተም የጽድቅ ሥራ ሰርታችሁ አይደለም የጸደቃችሁት፡፡ 🔶የእናንተ ኃጢአት ኢየሱስ ሲወስደው፤ እናንተም በእምነት የእርሱን ጽድቅ ትወስዳላችሁ፡፡ በመስቀል ላይ የሆነው ይሄ ነው፡፡ ተለዋወጣችሁ፡፡ አንድ ሰው በክርስቶስ ኢየሱስ ሲያምን ወድያው እምነቱ ጽድቅ ሁኖ ይቆጠርለታል፡፡
Показать все...
Reminder :- No matter what happens today No matter how much life is knocking you down No matter nobody understands you The Sun will rise up and GOD will wake u up cause it’s ur Day U deserve it Don’t just exist..... LIVE💛☀️ NEAL🤲🏽 and PRAY 🙏 May The LORD make ur day as bright as the Sun 🌞
Показать все...
⁃ 🙏እንዴት እንኑር🙏 የሰው ልጅ የአካሉ መስኮት ዓይን ናት። አይን የራሷ ብርሃን የላትም። ከሚታየው የዓለም ብርሃን ጋር ስትስማማ ማየት ትችላለች። አጥርቶ ለማየት ሁለት ዓይንን መጠቀም ተገቢ ቢሆንም ሁሉንም ነገር በሁለት ዓይን ማየትም ተገቢ አይደለም። የምንኖረው በአንድ ዓይናችን እየሳቅን በአንደኛው እያለቀስን ነው። ህይወትን አመዛዝነን መኖር አለብን። አንድ ዓይናችንን ሸፍነን በዓንደኛው ብቻ ለማየት ስንሞክር የምናየው ነገር ያንስብናል ይርቅብናል። በሁለቱም ስንመለከተው ይጎላብናል። ችግራችንን በሙሉ ዓይን ስናየው ልባችንን ያርዳል እምነታችንን ይሸረሽራል ስለዚህ በአንድ አይናችን ልንመለከተው ይገባል። እንደ ክርስቲያን በነገር ሁሉ እይታችን መሆን ያለበት አንድ አይናችን ቀራንዮ ላይ መተከል አለባት። በዚያ መከራውን ችንካሩን ስቃዩን ስንመለከት በመከራችን እንዳንታበይ ያደርገናል። የምንጓዘው ጉዞ ክርስቶስ መርቆ በከፈተው ጎዳና ላይ መሆኑን እንገነዘባለን። አንደኛው አይናችንን በአብ ቀኝ በክብር የነገሰው ኢየሱስ ላይ ማረፍ አለባት። በዚህ ጊዜ የሚደርስብን መከራና ስቃይ የተለያዩ ውጣውረዶች ተስፋ እንዳያስቆርጡን ያደርገናል። "ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ" ( ዕብ 31 )
Показать все...
❣️የእግዚአብሔር ህይወት❣️ 🔐የእግዚአብሔር ልጆች ማረፊያ የሆነው በጣም ፀጥ ያለ ቦታ ወይም የለመለመ ሥፍራ ሳይሆን እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ 🔐ስለዚህ ህልውናው እና መገኘቱ ውስጥ ህይወታችንን እና ኑሮአችንን በዚያ እንስራ፡፡ እኔ ምለው ፥በውስጣችሁ ያለው የእግዚአብሔር የራሱ ህይወት እንደሆነ ታውቃላችሁ?እርሱም በሰማይ ያለውን ሕይወት ለእኛ በምድር ላለነው ያካፈለን ሕይወት ነው፡፡ 🔐ይህ እጅግ የከበረ የእግዚአብሔር ስጦታ በልጁ_በኢየሱስ የሆነልን የዘላለም ህይወት ነው ፤ የጽድቅንና የቅድስናን ሕይወት ለመኖር ብቃት ያገኘነውም ከዚህ የተነሳ እንጂ የእኛ ጥረት ተደምሮበት አይደለም፡፡
Показать все...
#💟ምርጫ አለህ የሰው ልጅን ልዩ ካደረገው ዋነኛው ነገር መካከል አመዛዝኖ እንዲወስን ፍቃድ ይዞ መፈጠሩ ነው። የሰው ልጅ በሌሎች ፍቃድ መሰረት የሚመራ ሮቦት አይደለም። ሁለት ዓይነት አኗኗር አለ። አንደኛው በዚህች ዓለም ከሰማይ በታች አዲስ ነገር የለም ብሎ መኖር !!! ሁለተኛው ደግሞ ለሁሉም ነገር አዲስ ሆኖ መኖር። ምርጫው የናንተ ነው። ይህች አለም ሁልጊዜ መልካም ነገሮችን በመሸፈን እንዲሁም በማዘግየት ተስፋ እንድንቆርጥ ፥ በትጋት ትሰራለች። ለክፋት ግን ሁሌም በርዋ ፣ መንገድዋ ክፍት ነው። ማለትም "እውነት ካልሲ ለብሳ ጫማ እስክታጠልቅ ድረስ ውሸት ዓለምን ዞራ ትመጣለች። እኛ ግን መልካም ነገር ቢዘገይም ምርጫችን ሁልጊዜ ከእውነት ጎን መሆን አለበት። መሪያችንም ሲፀልይ ያለው ፦ ከአለም አውጣቸው ሳይሆን በአለም ሳሉ ጠብቃቸው ነው ያለው። በአለም ላይ ሁለት መንግስታት ብቻ ናቸው ምድር ላይ ያሉት፦ 1ኛው. የእ/ር መንግስት ሲሆን 2ኛው. የጨለማው መንግስት ነው። በምድር ላይ ያለው የትኛውም ኑሮዋችን ከእ/ር መንግስት አኳይ መቀረፅ ይኖርበታል!በአንድ ዛፍ የሚዘሉ ጉሬዛ እና ጦጣ አብረው ቢውሉም ተቃቅፈው አይተኙምና።
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.