ru
Feedback
EECSF

EECSF

Открыть в Telegram

ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::

Больше
508
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
Архив постов
ሰላም ቤተሰብ👋 ዛሬ ከእኔ(ሱራፌል ፈቀደ) ጋር ስለ ሸክም አብረን እንማማራለን😊 ሸክም / Burden ❇️ ማንኛውም ካባድ ይሁን ቀላል የምንሸከመው ቁስ አካል ወይም ጥብቅ የስራ ተግባር /severe task/ ሸክም ልንለው እንችላለን። በሀሳብ ደረጃም ስሜትን ከመፍጠር አንፃር ሸክም ብለን ልንገልፃቸው የምንችልበት ሁኔታዎች አሉ። ከዚህ በመነሳት ከባድ ቢሆን ቀላል ቁሳዊ ቢሆን ሀሳባዊ ፤ ሸክም ሸክም ነው።🤷‍♂ 👉 ሸክማችንን በሚገባ ማወቅ በጣም ብልህነት ነው ብዬ አስባለሁ። አብዛኛውን ጊዜ እግዚአብሔር ልንሸከመው ያልሰጠንን ሸክም በራሳችን ስንሸከም እንገኛለን። 😔Huuuh ❓❓እኛ ደካሞች ተብለን የተጠራን ምን አይነት ሸክም ልንሸከም ይገባናል? የተሰጠን ሸክምስ ምን አይነት ነው? ------------------------------------- ማቴዎስ 11 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁸ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ²⁹ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ³⁰ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና። -------------------------------------- 📌 ጌታ ኢየሱስ ይህንን የተናገረው ለሆኑ ለተወሰኑ group of people አይደለም። ነገር ግን ሰው ለተባለው ፍጥረት ሁሉ ነው። ስራን በራሱ አቅም በመስራት የዛለ ሰዉን፣ የደከመ ሰውን...ወዘተ፤ በየትኛውም ምክንያት ይሁን ሰው ያለው አቅም ተስፋ አስቆራጭ በሆነ መልኩ ከንቱ መሆኑ ስለተረጋገጠ ለሁሉም ሰው ነው። 🔐 ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ ሰው እንዴት ሊያርፍ እንደሚችል ለማሳየት "...ወደ እኔ ኑ..." እያለ ሲጣራ ወይም ሲጋብዝ እንመለከታለን። እስቲ ቃሎቹን ለይተን እንያቸው ፡ ✅ አሳርፋችኃለሁ በስራ ሳይሆን ወደ ኢየሱስ በመምጣት ብቻ እረፍትን ማግኘት ✅ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ በእርሱ ስራ ላይ ተካፋይ partners ሆነን አብረን መስራት ✅ ከእኔ ተማሩ ወደ እርሱ ከመጣን የምናደርገውን ነገር ከእርሱ እያየን ነው የምናደረገው ✅ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል - ቀንበሩን ከእኛ ጋር share ስለሚያረግ እና በልካችን ስለሆነ easy ነው - ሸክሙ በ partnership ስለሚሰራ እና በእርሱ አቅም ስለሚሰራ አያደክምም 💡ስለዚህ ወደ አርሱ ከመጣንና ከእርሱ ጋር እስከሆንን ድረስ ከሸክማችን የተነሳ አድካሚና አሰልቺ ሕይወት አይሆንብንም ማለት ነው🤔? አዎ በትክክል!!! 📌 ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ያልተሰጠንን ስንሸከም እንገኛለን፤ ለዚያውም ከባዶቹን። ለምሳሌ ያህል ልንሸከማቸው የማይገቡ ግን የተሸከምናቸው ፡ ❌ ጭንቀት(worry)፣ ውድቀት(failure)፣ ኃጢአት(sin)፣ ጥፋተኝነት(guilt).....ወዘተ ኃጢአት የሚለው ሰፊ ቃል ነው። በውስጡ ይቅር አለመባባል፣ቂም በቀል፣ ትዕቢት....ይኖርበታል። ስለዚህ ከላይ በጠቀስናቸው ከባድ ሸክሞች ምክኒያት ሕይወታችን አሰልቺ እና አድካሚ ይሆናል?🤔🤔 አዎ ይሆናል!!

👇 አሁን: የቃለ እግዚአብሔር ጊዜ 👆 ከወንድም : ሱራፌል ፈቀደ ጋር 👑 Tuesday Service 👑 —EECSF—

“ you can’t be anything you want to be,but you can be everything God wants you to be.” @Finding_purpose
“ you can’t be anything you want to be,but you can be everything God wants you to be.” @Finding_purpose

🙏ለዝማሬው ጌታ ይመስገን🙏

በዘመኔ አያለሁ | አስቴር አበበ 🎶New Song 🎶 📢 @EiABC_fellowship

photo content

አሁን.... 🎙#የሳምንቱ መልካም ዝማሬ # ከ Adadis songs ጋር 👇👇👇👇

አዎንታዊ አመለካከት የሰዉነታችን በሽታ የመከላከል ተፈጥሮአዊ ክትባት ነው። --ዶ/ር ምህረት ደበበ Credit : @bdu_fellowship
አዎንታዊ አመለካከት የሰዉነታችን በሽታ የመከላከል ተፈጥሮአዊ ክትባት ነው። --ዶ/ር ምህረት ደበበ Credit : @bdu_fellowship

እስኪ ይህችን መልካም ሀሳብ ተጋበዙ 🍗

ሰላም🤗🤗 የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጀምራለን፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር አምላክ በምህረቱ ጠብቆን ለዛሬ ደርሰናልና ክብር ሁሉ ለ
ሰላም🤗🤗 የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጀምራለን፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር አምላክ በምህረቱ ጠብቆን ለዛሬ ደርሰናልና ክብር ሁሉ ለእርሱ ይሁን፡፡ ዛሬም የምንተናነፅበትን መልካም ፍሬ አብረን እንካፈላለን አብራችሁን ቆዩ።😊

photo content

የራሳችንን ፍላጎት ትተን እርሱ እንደሚለን እንድንሆንለት እግዚአብሔር ይርዳን " ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።" (የማቴዎስ ወንጌል 6:33) የዛሬው ኘሮግራም በዚህ አልቋል እግዚአብሔር ይባርካችሁ

ወደ እኛ ስናመጣው እንደምሳሌ ሆኖ የወታደር አይነት ህይወት እንድንኖር ተጠርተናል 👉 ወታደር በባህሪው ✨አዛዡ ያለውን ይፈጽማል ✨ የእኔ ፈቃድ፣ፍላጎት አይልም ✨ አዛዡን ለማስደሰት ይሰራል ✨አላማ አለው ✨ሁሌ ዝግጁ ነው ✨ስራው ምቹ የሚባል አይደለም ስለዚህ እኛ ዛሬ ክርስቶስን ስንከተል 👉 የእርሱን ፈቃድ ለማድረግ 👉ለመታዘዝ፣ ለማገልገል 👉በፈለገው ስፍራ ለመሰማራት 👉 ለእርሱ ለመገኘት ተጠርተናል እንጂ ምቾታችንን ለመጠበቅ፣ ሁሌ አድርግልን ለማለት አልተጠራንም እርሱን ስንከተል ፈተና ሲያጋጥም እግዚአብሔር አብሮን እንዳለ ፣ እንደሚረዳን እንወቅ። እግዚአብሔር ይባርካችሁ

በጎ ወታደር 👋👋ሰላም እህቶቼ እና ወንድሞቼ ዛሬ በጎ ወታደር በሚል ሀሳብ ከእኔ ጋር የእግዚአብሔርን ቃል እንከፋፈላለን " እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል። የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም።" (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:3-4) በዚህ ምድር ክርስቲያን ሆነን ስንመላለስ ፈተና ያለበት፣ አንዳንድ የሚያስቸግሩ፣ የሚከብዱ ቀናት ይኖራሉ ። ሁሌም የተመቻቸ፣ የተደላደለ ኑሮ አንጠብቅ። 👉 እግዚአብሔርን ስንከተል እኛ የፈለግነውን ነገር ሁሉ ሁሌ እንዲያሟላልን ፈልገን አይሁን። ✨ነገር ግን የእርሱን ፈቃድ ለመፈጸም እንደ በጎ ወታደር ፤ እርሱን ለመታዘዝ፣ ለማስደሰት እና ለማገልገል እራሳችንን ዝግጁ አድርገን እናቅርብ ። እስቲ ጥቂት የአብርሃምን ህይወት እንመልከት አግዚአብሔር አብርሃምን ሲጠራ 📌 መጀመሪያ ያለው " እግዚአብሔርም አብራምን አለው። ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።" (ኦሪት ዘፍጥረት 12:1) ታዲያ ይሄ የአብርሃምን የምቾት ህይወት አይነግፍም? ማለቴ ከለመደው፣ ከሚያውቀው ቤተሰብ፣ ስፍራ፣ ተረጋግቶ ከኖረበት ፤በዛ እድሜው ውጣ መባል ወደማያውቀው መላክ አይከብድም? 📌 ሌላው በጉዞው ውስጥ ሚስቱ ተወስዳ ታውቃለች 📌 አብርሀም እግዚአብሔር የገባለትን ቃል ኪዳን ሲጠራጠር እናገኘዋለን 📌ልጅህን ሰዋልኝ ሲባል እናገኘዋለን በዚህ በላይ ባነሳናቸው እንድናይ የፈለኩት ነገር 👉 እግዚአብሔር አብርሀምን ሲጠራ ከተደላደለበት ውጣ ሲለው አብርሀም እሺ ብሎ ነው የታዘዘው ✨ምቾቱን ለማስጠበቅ አልታገለም 👉 የአብርሃም ህይወት ፈተና ነበረው። እግዚአብሔር በመታመን ግን ሲኖር እናየዋለን በዚህ ሁሉ ቢያልፍም በመንገዱ ግን እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ሲገባለት፣ ሲፈጽም፣ ሲመራው፣ ድል ሲሰጠው ፣ ሲባርከው እናያለን።

አሁን ደግሞ የእግዚያብሄርን ቃል የምንከፋፈልበት ጊዜ ነው ከእህታችን ሩት ጋር

New_protestant_mezmur_2017_Yishak_Sedik_TEMESGEN_YouTube_Amen_Media.mp35.99 MB

አሜን አሁን ደግሞ እግዚአብሔርን በዝማሬ እናመልከዋለን

እግዚአብሔር አባታችን ሆይ በጌታ በኢየሱስ ስም እናመሰግንሀለን።ስለምህረትህ ስለቸርነትህ ስለመልካምነትህ ደግመን እናመሠግንሀለን።ገና ደካሞች እና ሀጢያተኞች ሳለን ሥለወደድክን የምትወደውን ልጅህን ነፍሥ ሥለኛ አሣልፈህ ሥለሠጠኽን እናመሠግናለን።በፀጋህ በእምነት በኩል ስለሆነልን መዳን ተመስገን።ደካሞች እንደሆንን ያላንተ ምንም ማድረግ እንደማንችል አውቀን ወደአንተ መጥተናል አባት ሆይ እርዳን።ደግሞም ጌታ ሆይ ምህረትን እንድንቀበል በሚያሥፈልገንም ጊዜ የሚረዳን ፀጋ እንድናገኝ ወደ ፀጋህ ዙፋን በእምነት እንድንቅርብ በቃልህ ተናግረኸናል ስለዚህም ጌታ ሆይ ምህረትን እንድታበዛልን ሀጢያታችንን እና በደላችንን በክርሥቶሥ ደም እጠበው።አባት ሆይ ንፁህ ልብን እንድትፈጥርልን ያለዛ አንተን ማየት አንችልምና ልባችንን አጥራው።በፈቃዳችን ለፈቃድህ እንገዛልን ያንተ ሀሣብ ብቻ በህይወታችን ይፈፀም።ሥለሠማኽን እናመሠግንሀለን።እንወድሀለን።በልጅህ በኢየሱስ ስም።አሜን።

ኘሮግራማችንን በጸሎት እንጀምራለን ከእህታችን ዲቦራ ጋር አብረን እንጸልይ

ሰላም የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ስም እንጀምራለን። እንግዲህ ጌታ በምህረቱ ደግፎናልና ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፤ አሜን። ዛሬ ደግሞ አጠር አድ
ሰላም የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ስም እንጀምራለን። እንግዲህ ጌታ በምህረቱ ደግፎናልና ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፤ አሜን። ዛሬ ደግሞ አጠር አድርገን የምንተናነጽባቸውን ፍሬ ነገሮች እንከፋፈላለን፤ አብራችሁን ቆዩ።