cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ብልጽግና ፓርቲ - PROSPERIY

We provide Latest news and information about prosperity party and Ethiopian politics;We will ensure unity,peace and prosperity of the motherland Ethiopia!!! ስለ ብልጽግና ፓርቲ እና ኢትዮጵያ ወቅታዊ መረጃዎችን እናቀርባለን፤ የኢትዮጵያን አንድነት፣ ብልጽግናና ሰላም እናረጋግጣለን!!!!

Больше
Рекламные посты
2 041
Подписчики
+124 часа
+87 дней
+1530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ከማርዮት ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አንቶኒ ካፑአኖ ጋር በቱሪዝም ዘርፍ ኢትዮጵያ ያላትን ፍላጎት እና የሀገራችንን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ለመጠቀም በትብብር ለመሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ውይይት አድርገናል። Productive discussions with Marriott International President and CEO Anthony Capuano focused on Ethiopia’s aspirations in the tourism sector and ways and means of collaborating to maximize our nation's potential.
Показать все...
በአረንጓዴ ዓሻራ ጥረቶቻችን አማካኝነት ልናሳካው ለምንፈልገው ለውጥ የአመለካከት እና የአዕምሮ ውቅር ሽግግር ያስፈልገናል። እንደ ሀገር ልናሳካ ካለምነው 50 ቢሊዮን ችግኞች በያዝነው አመት 40 ቢሊዮን ችግኞች ላይ ለመድረስ እየጣርን በመሆኑ በዘንድሮው የተከላ ዙር 7.5 ቢሊዮን ችግኞችን በጋራ መትከል ይኖርብናል። ለነገው ትውልድ ቅርስ ለመተው የሚሻ ሁሉ ዛሬ ላይ ማዋጣት የግድ ይለዋል። A paradigm and mindset shift is needed for the change we want to see in our Green Legacy endeavors. Our goal for this year is to reach 40 billion seedlings from our overall target of 50 billion, which means we need to collectively plant 7.5 billion seedlings this planting cycle. For anyone who wants to leave a legacy for future generations, we must invest in the future today.
Показать все...
👍 13 1
04:19
Видео недоступноПоказать в Telegram
በኢትዮጵያ በተለያዩ ሥነ ምኅዳሮች ከ6ሺ በላይ ዕጽዋት ይገኛሉ። ከእነዚህ መካከል 12% ገደማው በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ሲሆን የተቀሩት እኛም ጋር፤ ከኛም ሀገር ውጪ የሚገኙ ናቸው። Ethiopia hosts over 6,000 plant species across various ecosystems. Approximately 12% of these species are exclusive to Ethiopia, while the remainder are found both within and outside our borders.
Показать все...
89.68 MB
👍 12
13:14
Видео недоступноПоказать в Telegram
ሙዚቃ የማይታይ ነገር ማሳየት ነው ያልገባን ነገር እንዲገባን ማድረግ ነው። Muuziqaan waan hin argamne agarsiisuudha; waan nuuf hin galle akka nuuf galu gochuudha.
Показать все...
172.41 MB
👍 11
ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ በኢስታና ላደረጉልኝ አቀባበል አመሰግናለሁ። በቅርቡ ለጀመሩት የጠቅላይ ሚኒስትርነት ኃላፊነትም እንኳን ደስ አለዎ ለማለት እፈልጋለሁ። ሁለቱ ሀገሮቻችን እርስ በርስ የሚማማሩት ብዙ ጉዳይ አለ። የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታችንን ከፍ ለማድረግ፣ በአቅም ግንባታ፣ በሲቪል ሰርቪስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በላቀ የማኑፋክቸሪንግ ስራ እና ቱሪዝም ልማት ትብብራችንን ለማጠናከር ተስማምተናል። የወዳጅነት ትብብራችንን ይበልጥ ለማስፋት የምንሰራም ይሆናል። Thank you to Prime Minister Lawrence Wong for the warm reception today at the Istana. I also take this opportunity to congratulate him for recently assuming office. Our two nations have a lot to learn from each other and we have agreed with President Wong to enhance our people to people ties; capacity development; civil service cooperation; technology; advanced manufacturing and tourism development. I look forward to building on this partnership.
Показать все...
👍 10 3👏 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ማንበብ ባህል መጻሕፍትም ቤተኛ እንዲሆኑ እንደ ሀገር መሥራት አለብን። የሰከነ፣ የሚያሰላስልና በሐሳብ ልዕልና የሚያምን ማኅበረሰብ ለመገንባት ንባብ ወሳኝ ነው። የንባብን ባህል ለመገንባት ወሳኝ የሆኑትን አብያተ መጻሕፍት፣ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እየገነባን ነው። በጀመርነው የዲጂታል ኢትዮጵያ መርሐ ግብር በኩል መጻሕፍትን በቀላል መንገድ ለማዳረስ እንሠራለን። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በኩል በ2016 ለ አንድ መቶ ቀናት ንባብን ሲያበረታታ ቆይቷል። ሌሎች ሚዲያዎችም በተመሳሳይ መንገድ ንባብን እንዲያበረታቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ። መጪው ክረምት ነው። ብዙ ወጣቶች ዕረፍት ላይ ይሆናሉ። ጊዜያቸውን በንባብና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲያሳልፉ በብርቱ ልንሠራ ይገባል።
Показать все...
👍 11 6
Фото недоступноПоказать в Telegram
የዛሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ለ #ጽዱኢትዮጵያ ስራችን ሃምሳ ሚሊዮን ብር ኢትዮጵያውያን ሁሉ ልናዋጣ አቅደን ነበር። ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር ከ154 ሚሊዮን ብር በላይ ማዋጣት ችለናል። ኢትዮጵያን ሲያኮሩ የኖሩ አትሌቶች፣ ስፖርተኞች እና ደጋፊዎች፣ የዘወትር አገልጋይ የታክሲ አሽከርካሪዎች፣ ለኅሊናም ለአካባቢም ንፅህና የሚቀኙ ከያንያን፣ ምሁራን፣ ባለሃብቶች በቴሌቶኑ ስፍራ በመገኘት ላደረጉት አስተዋጽዎ እነሆ ምስጋና። በመላው አለም ሆነው በዛሬዋ ጀምበር በዲጂታል ቴሌቶኑ የተሳተፉ ከአርባ ሺህ በላይ ዜጎች ለፅዱ ኢትዮጵያ ያላቸው ምኞት መግለጫ የሆነው አስተዋፅዖ በተግባር በየአካባቢው በሚገነቡ የሕዝብ መፀዳጃዎች ይታወሳል። ይህ ትውልድ ጀምበር ወጥታ በገባች ቁጥር ለመጪው ትውልድ መስፈንጠሪያ የሚሆን ብሩህ እና ፅኑ መሰረት ደልድሎ ያወርሳል። ምኞት ተግባራችን ሁሉ የተሻለች ኢትዮጵያን በኅብረት ገንብቶ ማቆየት ነው።
Показать все...
👍 9 4😁 1
👏 4👍 2
Перейти в архив постов
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.