cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች

በዚህ ቻናል ላይ አበው ያስረከቡንን መጻሕፍትን እንዲሁም መንፈሳዊያት ጽሁፎችን ለምዕመናን ተደራሽ ማድረግ ነው። https://linktw.in/mejQ6H ሰብስክራይብ ያድርጉ

Больше
Рекламные посты
4 130
Подписчики
+724 часа
+317 дней
+16430 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

"Not only men, but women, the weaker sex, in going by the narrow path of Christ have received for themselves the Kingdom of Heaven. For there is neither male nor female, but everyone receives his own reward according to his own labor. The Eternal Joy of Christians" - St. Ephraim the Syrian
Показать все...
ሰንበት ትምህርትቤቴ ያወጣው አዲስ ዝማሬ ነው ከቻላችሁ ገብታችሁ አበረታቷቸው። እንኳን ለአቡነ ዜና ማርቆስ ወርሐዊ በዓል አደረሳችሁ። https://youtu.be/3hZckz7wxyM?si=zvmlTXWUkqeWOLS0
Показать все...
🔴 አዲስ ዝማሬ “ የበዛ ነው ጸጋህ “ አንቀፀ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት @-mahtot

🔴"ልቦናዬ ያውጣ" የሚለው ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዘመረው ከ 20 Million + እይታ ያገኘውን ዝማሬ በዚህ ሊንክ ያገኙታል :: 👇 👇 👇

https://www.youtube.com/watch?v=H0jd74NmdwY

🔴 በማኅቶት ቲዩብ የተለቀቁ ተወዳጅ መዝሙሮችን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፡፡ 👇 👇 👇

https://bit.ly/3C2YHGp

🔴 አዲስ ዝማሬ “ የበዛ ነው ጸጋህ “ አንቀፀ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ​⁠@-mahtot

በኮሪደር ልማት ምክንያት በፈረሱ ቤቶች ምትክ በቤተክርስቲያኒቱ የሚገነባ ሕንጻ የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ። መሠረት ድንጋዩን ያስቀመጡት የኢኦቴቤ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዕ አቡነ ማትያስ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር ከንቲባ አዳነች አበቤ ናቸው። በዕለቱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል። በመርሐ ግብሩ በቅዱስ ፓትርያርኩ በኩል ለከንቲባዋና ለአስተዳደሩ ሌሎች ኃላፊዎች ስጦታ ተበርክቷል። ከንቲባ አዳነችም “ቤተ ክህነት የከተማውን ልማት ሥራ በላቀ ሁኔታ በመደገፍ እና ለኮሪደር ልማት ስራዎች መጀመር፤ በማፍረስ ሂደትም ሆነ መልሶ በመገንባት ሂደት እንዲሁም ሕንጻዎችን በማደስ ላደረገችው ተሳትፎ እና ተግባራዊ የሆነ ምላሽ ከልቤ ለማመስገን እወዳለሁ” ። ሲሉ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።
Показать все...
Показать все...
🔴አጥፍቻለኹኝ ይቅርታ አድርጉልኝ መመለስ እፈልጋለሁኝ❗

#ጸጋዬ_ክፍሉ #tsegayekiflu #joinmembership ሁለተኛ ቻናሌ ለመቀላቀል

https://www.youtube.com/@TsegayeTutorial

https://t.me/tsegayekiflu

www.tiktok.com/@tsegaye_kiflu

https://t.me/tseomm

It is a platform for providing orthodox audio-visual teachings, hymns, bibliography, current church information, religious verses and sayings, as well as educational live broadcasts. When searching for any Orthodox Tewahedo, you can use your first destination TSEGAYE KIFLU / ጸጋዬ ክፍሉ Welcome to the online context of our church's doctrine, tradition, and history. In This Channel You will get an ORTHODOX REACTION VIDEOS AND Entertaining Content for the Habeshan Community. FAIR-USE COPYRIGHT DISCLAIMER Copyright Disclaimer Under Section 107 of the Copyright Act 1976, allowance is made for "fair use" for purposes such as criticism, commenting, news reporting, teaching, scholarship, and research. Fair use is a use permitted by copyright statute that might otherwise be infringing. Non-profit, educational or personal use tips the balance in favor of fair use. 1) This video has no negative impact on the original works (It would actually be positive for them) 2) This video is also for informational purposes. 3) It is not transformative in nature. 4) I only used bits and pieces of videos to get the point across where necessary. Tsegaye kiflu does not own the rights to these video clips. They have, in accordance with fair use, been repurposed with the intent of educating and inspiring others.

የተባለው እንዳለ ሆኖ... ልቅሶ ያክማል -- ልቅሶ ቀቢፀ ተስፋ አይደለም። በአግባቡ ከሆነ ቴራፒ ነው። ፊት አትንጩ፣ ትንሣኤ ሙታን እንደሌለ አድርጋችሁ ምርር አትበሉ እንላለን። ሲያስፈልግ እንገዝታለን። ነፍስ ሲወጣ፣ አስከሬኑ ከቤት ሲወጣ፣ አፈር ሲቀምስ ማልቀስን ሥርዓታችን ይፈቅዳል። የፍትሐት ጸሎት ብዙ ሰው ለሟች ብቻ የሚደረግ ይመስለዋል። አይደለም! ለኀዘንተኛም ነው። "መናኅየ ወመናዝዘ ለሰብኦሙ ፈኑ- ለኀዘንተኞች መጽናናትን መረጋጋትን ስጥ" በጣም የሚደጋገም የጸሎት ክፍል ነው። ቀን ቆጥሮ ስለሟች መመጽወት መዘከር ለቋሚ የሚሰጠውን መጽናናት በቤተክርስቲያን ካብ ዙሪያ ላደግነው ሕያውነት ያለው ማስረጃ ነው። ሃይማኖቱ ይቆይ... -- በባሕል ብዙ ይደረጋል። አፈር መበተን ፣ እርም ማውጣት ፣ ከቀብር መልስ እጅ መታጠብ ፣ ንፍሮ መቅመስ፣ ኀዘንተኛን አቅፎ እግዚአብሔር ያጽናህ ማለት ፣ ድንኳን ውስጥ ተራ ተመዳድቦ ኀዘንተኛውን ማጽናናት፣... ብዙ ነው። ማኅበረሰቡ በዘመናት የገነባው ቴራፒ ነው። ድባቴ፣ ቀውስ፣ የአእምሮ ሕመም ፣ ወዘተ በመዝገበ ቃላችን እንዳይዘወተሩ የሚያደርገው ይህ ቴራፒ ነው። ሀገሩ የልቅሶ ቀጠሮ ይዞ በቁም ነገር በጋራ እርም አወጣን ብሎ ይታከማል። ይወጣለታል! ኀዘንን መሸካከምን አታቅልለው። ከቀብር መልስ "አይገባም፣ ይበቃል፣ የእግዚአብሔርን ዐይን መውጋት ነው" እያለ ያክማል። ልቅሶ ቴራፒ ነው። ያክማል። ብቻ፥ በአግባቡ በልኩ ይሁን። በአማን ነጸረ እንደጻፈው
Показать все...
3
ሁለቱ የዘመኑ ክርስትና ፈተናዎች: Deductive Reasoning /ተጠየቃዊ አመክንዮ/ እና ግላዊ የመላ መት ትርጉም /Speculative Theology/ (አሁንም ከብርሃኑ አድማስ) -- በዘመናችን ላሉ በርካታ ሃይማኖታዊ የአስተምህሮ ችግሮች ክፍተቶች የሚታዩት ሌሎች ጠንክረው ሳይሆን እኛ ከሚገባው በታች ሆነን ስለምንገኝ ነው። የዚህ ችግር ዋናው ምክንያት ደግሞ የምንጽፍበትንም ሆነ የምንናገርበትን ጉዳይ በአግባቡ ስለማናውቅ ነው ብዬ አስባለሁ።... የኦርቶዶክሳዊ የአስተምህሮ መንገዶች ሊተገብሩ ከማይችሉት አሁንም ዋና ዋና የምላቸውን ማስታወስ ይኖርብኛል።... #1 የመጀመሪያው ከዘመናዊ ፍልስፍና እና ሥነ ጽሑፍ እድገት ጋር በሌላው ዓለም የገነነው ተጠየቃዊ አመክንዮ ልበለው መሰል እንግሊዝኛ Deductive reasoning የሚለው የማይሠራ መሆኑን ማስታወስ እፈልጋለሁ። ለምን? ብዙ ሰዎች ያወቁ የነቁ እየመሰላቸው በዚህ መንገድ ብዙ ስሕተቶችን ያመጣሉና። ይህንን ከዚህ ሞያ ጋር ቅርበት ለሌላቸው ሰዎች በቀላሉ ላስረዳ መሰል። ዲዳክቲቭ ሪዝኒንግ የሚባለው ከሁለት መነሻ ሀሳቦች ተነሥቶ የምንደርስበት ማጠቃለያ ነው። ለምሳሌ አበበ ሰው ነው። ሰው ሁሉ ደግሞ ሟች ነው። ስለዚህ አበበ ሟች ነው የሚል ማጠቃለያ ላይ መድረስ ዐይነት ነው ዲዳክቲብ ሪስኒንግ የሚባለው መንገድ።... የዚህ ዓይነት መንገድ ፈጠራቸው ብዬ ክማስበው አንዱን ማንሣትም እችላለሁ። እመቤታችን መንፈሴ በአምላኬ በመድኃኒቴ ደስ ይላታል ብላለች ። ከዚህ ንግግር ጌታ እንዳዳናት መመስከሯን መረዳት ይቻላል። ስለዚህ ከአዳናት ኃጢአት ነበረባት ማለት ነው የሚሉ ሰዎች ገጥመውኝ ያውቃሉ። እንዲህ የሚሉ ሰዎች ዲዳክቲቭ ሪስኒንግ ምን እንደሆነ ባያውቁ ከዚህ ዓለም ከተማሩት ትምህርት ተነሥተው አስተሳሰባቸው በተሠራበት የፍልስፍና መንገድ መናገራቸውንና ይህንን እንደማይጠየቅ ተፈጥሮአዊ ዕውቀት አድርገው በመውሰዳቸው የሚሳሳቱት ስሕተት ነው። ዲዳክቲቭ ሪስኒንግ ለሃይማኖት ለምንድን ነው የማይሠራው የሚልጥ ጥያቄ ካለ መልሱ በአጭሩ በሃይማኖት የሚሠራማ ከሆነ ሃይማኖት ተራ የሰዎች ግኝት ፍልስፍና ብቻ ነው ማለት ነው። ዲዳክቲቭ ሪስኒንግን ተጠቅመው ሃይማኖታቸውን ማስተማር የጀመሩ አካላት የደረሱበትን የክፍፍል ብዛት ዓይነት እና ምስቅልቅልም በዓይናችን በግልጽ የምናየው ነው። ስለዚህ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ጸሐፊ ይህች ጉዳይ በተለይ በመሠረታዊ የሃይማኖት ዶክትሪኖች ላይ ከተገለጠው ወጥቶ ወደዚህ መንገድ ከሔደ በግልጽ የክህደት ጎዳናን እየጀመራት ነው ማለት ይቻላል። #2 ሁለተኛው እና ልክ እንደዚሁ አስፈላጊው ነገር መላምታዊ ወይም ግምታዊ ወይም ደግሞ የግለሰቡ መረዳት የተጫነውን አተረጓጎም (Speculative Theology) ውስጥ እንዳይገባ አሁን መጠንቀቅ ነው። ይህኛው በብዙዎች የተሻለ ይታወቃል ብዬ አስባለሁ። ሆኖም በብዙ ስብከቶቻቸን እና በብዙ መጻሕፍትም ላይ እነዚህን ችግሮች አስተውላለሁ። በነገራችን ላይ የእኛ ሊቃውንት በእነዚህ ጉዳዮች ላይ በጣም ጠንቃቆች እንደሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ለምሳሌ አዲስ ነገር ካሰማህ ከየት አገኘኸው ከማን ሰማኸው የሚል ጥያቄ ይጠይቃሉ። ይህም በግምት በልብወለድ እና በአእምሮ ሥሪት ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ በገለጸው እውነት ብቻ እንድንጓዝ ጠብቆ ኖሯል። እነዚህን ሁለቱን መጠንቀቅ ለማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ መሠረታዊ ነው ብዬ አምናለሁ። -- ምንጭ :- #Janderebaw ገጽ
Показать все...
👍 5
Фото недоступноПоказать в Telegram
“If anyone does not believe that Holy Mary is the Mother of God, such a one is a stranger to the Godhead.” St. Gregory of Nazianzus
Показать все...
የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መግለጫ ++++++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚሁ መሠረት፡- 1. በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤ 2. በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል፤ 3. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሱ የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታ በመስጠትና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ መልሶ ማልማት እንድትገባ ድጋፍ በማድረግ፤ በተለይም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፈረሰው የጽርሐ ምኒልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃ ምትክ በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጭ ተጨማሪ ምድር ቤትና የቦታ ስፋት ያለው B+G+4 ሕንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባትና የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ኃላፊ አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ማድርጋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከምስጋና ጋር የተቀበለው ሲሆን በተሰጠን ምትክ ቦታ ላይም የከተማው ፕላን በሚፈቅደው መሠረት የመልሶ ማልማት ሥራው እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 4. የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጂ ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከ አሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡ 5.የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስመልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችን ምልዐተ ጉበኤው ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ አሳልፏል። 6. የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡ 7. በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑ ቢታወቅም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገለጸ ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉባኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል። 8. ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቡና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ 9. በደቡብ የሀገራችን ክፍል የቤተ ክርስቲያኒቱን አብነት ትምህርት ከማስፋፋትና ከፍ ያለ መዐርግ ከመስጠት አንፃር የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት ማስመስከሪያ ትምህርት ቤት እንዲሆን በቀረበው ጥናት መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ለምሥክር ጉባኤ ቤቱ ዕውቅና በመስጠት ወደ ትግበራ እንዲገባ ወስኗል፡፡ 10. ከሀገራችን ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀ ጳጳስ ሲጠየቅ በሙያ ብቃታቸው፣ በምግባራቸውና በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 11. የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሠረት ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 12. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ፤ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
Показать все...
1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቅዱስ ሲኖዶስ በኦሴኤን ቴሌቭዥን ጉዳይ ውሣኔ አሳለፈ። ++++++++++++++++++++++++++++++ በግንቦቱ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የኦሲኤን ቴሌቪዥን ዝርዝር ጉዳዩ ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ድረስ ሚዲያውን በጊዜያዊነት የሚመራ ኃላፊ በቋሚ ሲኖዶስ ተጠንቶ እንዲመደብ ተወሰነ። ከጉዳዩ አሳሳቢነት አንጻር ተገቢው ጥናት ሳይደረግ መወስን ስለማይችል 5 አባላት ያሉት ኮሚቴ በመመደብ ኮሚቴዎቹም ዝርዝር ጉዳዩን አጥንተው እና የሚዲያው መሥራች በምልዓተ ጉባኤው ፊት በአካል ቀርበው ንብረትነቱ የቤተ ክርስቲያኒቱ እንዲሆን በገቡት ቃል መሠረት ስመ ሀብቱ ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዴት መዞር እንደሚችል አጠቃላይ የሚዲያውን አስተዳደር ምን መሆን እንዳለበት ከሁለት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አጣርተው እንዲያቀርቡ ጉባኤው ወስኗል። ቅዱስ ሲኖዶስ ኦሴኤን ቴሌቭዥን ለአስተዳደርና ለቁጥጥር ያመች ዘንድ አሁን ካለበት ቦታ ወጥቶ ወደ ዋናው መ/ቤት ግቢ መጥቶ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በሚያዘጋጅለት ቦታ ሥራውን እንዲቀጥል ይደረግ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በተጨማሪ ቅዱስ ሲኖዶስ በተወያየበት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ አጀንዳ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ወስኗል ዘጋቢ:- መምህር ማርቆስ ተበቃ
Показать все...
👍 4