cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የሀይማኖት ንፅፅር ☪️vs✝️

📖የሀይማኖት ንፅፅር☪️ ይህ ግሩፕ 👉 እዉነትን የምናቅበት ወደተፈጠርንበት እምነት የምንመለስበት በቂ እዉቀት የምናገኝበ ነዉ:: @islam_ustaz_abuhayder 🤥ሼር ያድርጉን::

Больше
Рекламные посты
3 244
Подписчики
+524 часа
+267 дней
+6630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
ለምን ዲኑል ኢሥላምን ለሌላ ሰው አስተማርክ ተብሎ ለታሰረው ለወንድም ቢላል "ፍትሕ ለቢላል! እኔም ቢላል ነኝ።" በሚል መርሕ ቃል ሁላችንም ለቢላል እንጩው!
Показать все...
እነዚያ ጣዖታውያን በአሏህ ሌላ የሚያጋሩትን ጣዖታት፦ “አማላጆቻችን ናቸው” ይበሉ እንጂ ለእነርሱ ወደ አሏህ የሚያማልድ አማላጅ የላቸው፦ 6፥51 እነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳት እና አማላጅም የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ በቁርኣን አስጠንቅቅ፡፡ وَأَنذِرْ بِهِ الَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحْشَرُوا إِلَىٰ رَبِّهِمْ ۙ لَيْسَ لَهُم مِّن دُونِهِ وَلِيٌّ وَلَا شَفِيعٌ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ 40፥18 ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع "ወሊይ" وَلِيٍّ ማለት "ረዳት" "ወዳጅ" ማለት ሲሆን አሏህ ወሊይ ነው፥ ከእሳት ቅጣት የሚያድን ከአሏህ ሌላ ረዳት የለም። በተጨማሪ በአሏህ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፦ 32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون “ማ ለኩም ሚን ዱኒሂ ሚን ወሊይ” مَا لَكُمْ مِنْ دُونِهِ مِنْ وَلِيٍّ ማለትም “ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት ሲሆን ከአሏህ ውጪ በጀነት ለመጥቀምና በጀሃነም ለመቅጣት የሚችል ማንም እረዳት የላቸውም፥ “ሚን ዱኒሂ” مِنْ دُونِهِ ማለትም “ከእርሱ ሌላ” የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም ከሰዋስው አንጻር አሏህ ብቻ በመጥቀምና በመጉዳት ረዳት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። አንቀጹ ላይ፦ “ወላ ሸፊዒን” وَلَا شَفِيعٍ ማለት “እና አማላጅም የላችሁም” ማለት ሲሆን ከመጀመሪያው ሐረግ ለመለየት “ወ” وَ የሚል መስተጻምር ይጠቀማል፥ ያ ማለት “በተጨማሪም አማላጅም የላችሁም” ማለት ነው። “ማ” مَا የሚለው "ሐርፉን ነፍይ" حَرْف النَفْي በመጀመሪያው ሐረግ ላይ ገብቶ በተጨማሪ በሁለተኛው ሐረግ ላይ “ላ” لَا የሚለው ሐርፉን ነፍይ መደገሙ ጣዖታውያን ጣዖቶቻቸውን "ወደ አሏህ በማማለድ ያቀርቡናል" ብለው የሚናገሩላቸውን ጣኦታት አማላጆች አለመሆናቸውን ለማሳየት ነው። በዚህ ምክንያት “አማላጅ የላችሁም” በማለት ዘግቶታል፦ 30፥13 ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም። وَلَمْ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَائِهِمْ شُفَعَاءُ ስለዚህ “አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር እናንተ ከምታጋሯቸው የሚያማልድ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው እንጂ በአሏህ ፈቃድ የሚያማልዱ አማላጆች የሉም ማለትን አሊያም አሏህ አማላጅ ነው ማለትን አያሲዝም። ከአሏህ ሌላ ከቅጣት ሊያድናቸው የሚችል ረዳት የላቸውም፥ እንዲሁ ቅጣት እንዳይቀጡ ወደ አሏህ የሚያማልዱ አማላጅ የላቸውም ማለት ነው። ሙፈሢሮችም የፈሠሩት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦ 36፥23 ”ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልረህማን በጉዳት ቢሻኝ ምልጃቸው ከእኔ ለመመለስ ምንም አትጠቅመኝም፥ አያድኑኝምም፡፡ أَأَتَّخِذُ مِن دُونِهِ آلِهَةً إِن يُرِدْنِ الرَّحْمَـٰنُ بِضُرٍّ لَّا تُغْنِ عَنِّي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا وَلَا يُنقِذُونِ ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 32፥4 "ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት “እርሱ ብቻ ሉአላዊ የሁሉንም ጉዳዮች ተቆጣጣሪ፣ የሁሉም ነገር ፈጣሪ፣ ሁሉን ነገር አድራጊ ነው፤ ከእርሱ ሌላ ፈጣሪ የለም” ማለት ነው። “እናም አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው። ( ما لكم من دونه من ولي ولا شفيع ) أي : بل هو المالك لأزمة الأمور ، الخالق لكل شيء ، المدبر لكل شيء ، القادر على كل شيء ، فلا ولي لخلقه سواه ، ولا شفيع إلا من بعد إذنه . "መላእክት፣ ነቢያት እና ሰማዕታት ለሙእሚን ያማልዳሉ" ማለት እና "እኛ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ" ይለያያል፥ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ምልጃ ሳይሆን ሺርክ ነው። የሁሉንም ፍጥረት ልመና፣ ጥያቄ እና ጸሎት ጊዜና ቦታ ሳይወስነው ሁሉን የሚሰማ፣ ሁሉን የሚያይ እና ሁሉን የሚያውቅ የዐለማቱ ጌታ አሏህ ብቻ እና ብቻ ነው።  "አሏህ አማላጅ ከሆነ ተማላጁ ማን ነው? የሚለው የሚሽነሪዎች ቅጥፈት ውኃ በላው፥ አሏህ ተማላጅ እንጂ አማላጅ አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Показать все...
ሸፊዕ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون “ሸፊዕ” شَفِيع ማለት “አማላጅ” ማለት ሲሆን በአሏህ ፈቃድ ለሙእሚን የሚያማልዱት መላእክት፣ ነቢያት እና ሰማዕታት ናቸው። ለምሳሌ መላእክት፦ 53፥26 በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻው እና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ 21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ “ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም” የሚለው ኃይለ ቃል መላእክት ለአማንያን እንደሚያማልዱ ያሳያል፥ ሌላው አማላጆች አሏህ ቃል ኪዳን የገባላቸው ነቢያት ናቸው፦ 19፥87 አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا 2፥255 ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?። مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ 33፥7 ከነቢያትም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም እና ከመርየም ልጅ ከዒሳም ጋር በያዝን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا ከላይ በግልፅና በማያሻማ መልኩ አሏህ የፈቀደለት አማላጅ እና የሚማለድለት ተመላጅ ሰው እንዳለ ተቀምጧል፦ 10፥3 ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አሏህ ጌታችሁ ነውና አምልኩት! አትገሰጹምን?። مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِن بَعْدِ إِذْنِهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! ነገር ግን ጣዖታውያን ቁሬሾች ከአሏህ ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፥ “እነዚህም አሏህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ። እነዚህም በትንሳኤ ቀን፦ “እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው" የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም” ይባላሉ፦ 10፥18 ከአሏህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አሏህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ 6፥94 እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፤ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ "ያማልደናል" የምትሉት ጠፋ ይባላሉ፡፡ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمْ شُفَعَاءَكُمُ الَّذِينَ زَعَمْتُمْ أَنَّهُمْ فِيكُمْ شُرَكَاءُ ۚ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيْنَكُمْ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمْ تَزْعُمُونَ
Показать все...
ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል ማን ናቸው?
Показать все...
4.23 KB
ኤጲስ ቆጶሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 2፥120 አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ከአንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል"Bishop Mar Mari Emmanuel" በሲድኒ አውስትራሊያ በሚገኘው የአሦራውያን ቤተ ክርስቲያን"Assyrian Church" ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ በአሁን ሰዓት "ክርስቶስ መልካም እረኛ ቤተ ክርስቲያን"Christ The Good Shepherd Church" ውስጥ ያገለግሉ ነበር። የአሦራውያን ቤተክርስቲያን የምሥራቅ ሶርያዊ ሥነ መለኮት አቀንቃኝ ሲሆን መሠረቱ የንስጥሮስ ትምህርት ነው፥ የንስጥሮስ ትምህርት "አንዱ ኢየሱስ ሁለት ማንነት"Hypostasis" አለው፥ በፍጹም አምላካዊ ማንነት የአብ ልጅ በፍጹም ሰዋዊ ማንነት የማርያም ልጅ ነው። ማርያም የወለደችው ሰው እንጂ አምላክ አይደለም" የሚል ትምህርት ነው። ይህ ትምህርት በ 431 በተካሄደው ዓለም ዓቀፍ የኤፌሶን ጉባኤ የተወገዘ ሲሆን ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል የንስጥሮስ እሳቤ አራማጅ ናቸው። በዓለም ላይ ያሉ ብዙ ኦርቶዶክሶች እኚህን አባት እንደ ኦርቶዶክስ አባት አርገው የሚመለከቱት ትምህርታቸው ከራሳቸው ትምህርት ጋር አነጻጽረው በቅጡ መረዳት የማይችሉ ስለሆኑ ናቸው፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን የንስጥሮስ ትምህርት በካቶሊክ፣ በምሥራቅ ኦርቶዶክስ፣ በጽብሐዊ ኦርቶዶክስ እና በፕሮቴስታንት የተወገዘ ምንፍቅ ና ነው። ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል በተለያየ ርእሰ ጉዳይ በእንግሊዝኛ መርሐ ግብር የተለያ እሳቦትን በመተናኮል እና በመጎንተል በዓለም ላይ ይታወቃሉ። እስራኤልን፣ ምዕራባውያንን፣ አሜሪካንን፣ ግብረ ሰዶማ ውያንን ሳይቀር ይተቻሉ፥ አልፎ አልፎ ካቶሊክን፣ ፕሮቴስታንትን ሲላቸውም ዲኑል ኢሥላምን ሲወርፉ ይሰማል። ትላንት አንድ ሰው በሚያስተምሩበት ቤተክርስቲያን አደጋ አድርሶባቸው ህክምና ላይ እዳሉ እየተሰማ ነው። አደጋ ያደረሰባቸው ማንነት እስካሁን እንዳልተጣራ እየታወቀ ሆኖ ሳለ ክርፋታቸውን እና ልጋጋቸውን በተገኘው አጋጣሚ የሚያዝረከርኩ ክርስቲያኖች ለሙሥሊም ያላቸው ጥላቻ ምን ያክል የከፋ እና የከረፋ መሆኑን የምታውቁት ሰውዬውን "ሙሥሊም ነው" በማለት ዲናችንን መዝለፍ እና ማብጠልጠል ተያይዘውታል። ሰውዬው ሙሥሊም ቢሆንስ? ሰውዬውን "ትክክል አይደለም" ብሎ እራሱን ማውገዝ እንጂ ዲናችንን ለምን አሳቻ ሰዓት ላይ ጠብቃችሁ ትጎነትላላችሁ? ስንት እና ስንት ሙሥሊሞች በክርስቲያኖች ተገለው እንደ ኖርማል እየታየ አንድ ክርስቲያን ስለተገደለ ክርስትናን የእውነት ሚዛን አርጎ መውሰድ ቂልነት ነው። በእርግጥም ኤጲስ ቆጶሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል ለዲኑል ኢሥላም ያላቸው ጥላቻ አይጣል ነው፥ በአገኙት አጋጣሚ ዲናችንን በማበሻቀጥ እና በማብጠልጠል የዘመኑን የውረፋ ዋንጫ ወስደዋል። ከዚህ ሁሉ የገረመኝ ተከታዮቻቸው "ዓይን ስለ ዓይን ጥርስ ስለ ጥርስ" የሚለውን ሕግ ይዘው "የእጁን እንስጠው" ብለው ግብግብ ሲይዙ ነበር። "ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት" የሚለው የሚሠራው ስብከት ላይ ብቻ ነው፦ ማቴዎስ 5፥38 ‘ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ፡’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት። አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምንከተል ድረስ እንዳይወዱን አሏህ በቁርኣኑ ነግሮናል፦ 2፥120 አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ከአንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ አሏህ ለእነርሱ ልብ ይስጣቸው! ለእኛም ትእግስቱን ይስጠን! አሚን። አንብበው ሼር በማድረግ አስነብቡ! ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
01:18
Видео недоступноПоказать в Telegram
ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል "ኢየሱስ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው፥ ከኢየሱስ ውጪ አምላክ የለም" በማለት አብ እና መንፈስ ቅዱስን በማሽቀንጠር የሰባልዮስ ትምህርት እያራመዱ ነው። "ኢየሱስ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው፥ ከኢየሱስ ውጪ አምላክ የለም" የሚል ባይብል ላይ ሽታው የለም። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Показать все...
7.61 MB
01:09
Видео недоступноПоказать в Telegram
4.32 MB
ሸፊዕ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون “ሸፊዕ” شَفِيع ማለት “አማላጅ” ማለት ሲሆን በአላህ ፈቃድ የሚያማልዱት መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ናቸው፤ ለምሳሌ መላእክት፦ 53፥26 በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻው እና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ 21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ “ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም” የሚለው ኃይለ ቃል መላእክት ለአማንያን እንደሚያማልዱ ያሳያል፥ ሌላው አማላጆች አሏህ ቃል ኪዳን የገባላቸው ነብያት ናቸው፦ 19፥87 አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا 2፥255 ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?። مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ 33፥7 ከነቢያትም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም እና ከመርየም ልጅ ከዒሳም ጋር በያዝን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا ከላይ በግልፅና በማያሻማ መልኩ አሏህ የፈቀደለት አማላጅ እና የሚማለድለት ተመላጅ ሰው እንዳለ ተቀምጧል፦ 10፥3 ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አሏህ ጌታችሁ ነውና አምልኩት! አትገሰጹምን?። مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِن بَعْدِ إِذْنِهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! ነገር ግን ጣዖታውያን ቁሬሾች ከአሏህ ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፥ “እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ። እነዚህም በትንሳኤ ቀን፦ “እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው" የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም” ይባላሉ፦ 10፥18 ከአሏህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አሏህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ 6፥94 እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፤ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ "ያማልደናል" የምትሉት ጠፋ ይባላሉ፡፡ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمْ شُفَعَاءَكُمُ الَّذِينَ زَعَمْتُمْ أَنَّهُمْ فِيكُمْ شُرَكَاءُ ۚ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيْنَكُمْ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمْ تَزْعُمُونَ እነዚያ ጣዖታውያን በአሏህ ሌላ የሚያጋሩትን ጣዖታት፦ “አማላጆቻችን ናቸው” ይበሉ እንጂ ለእነርሱ ወደ አሏህ የሚያማልድ አማላጅ የላቸው፦ 6፥51 እነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳት እና አማላጅም የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ በቁርኣን አስጠንቅቅ፡፡ وَأَنذِرْ بِهِ الَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحْشَرُوا إِلَىٰ رَبِّهِمْ ۙ لَيْسَ لَهُم مِّن دُونِهِ وَلِيٌّ وَلَا شَفِيعٌ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ 40፥18 ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع "ወሊይ" وَلِيٍّ ማለት "ረዳት" "ወዳጅ" ማለት ሲሆን አሏህ ወሊይ ነው፥ ከእሳት ቅጣት የሚያድን ከአሏህ ሌላ ረዳት የለም። በተጨማሪ አሏህ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፦ 32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون “ማ ለኩም ሚን ዱኒሂ ሚን ወሊይ” مَا لَكُمْ مِنْ دُونِهِ مِنْ وَلِيٍّ ማለትም “ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት ሲሆን ከአሏህ ውጪ በጀነት ለመጥቀምና በጀሃነም ለመቅጣት የሚችል ማንም እረዳት የላቸውም፥ “ሚን ዱኒሂ” مِنْ دُونِهِ ማለትም “ከእርሱ ሌላ” የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም ከሰዋስው አንጻር አሏህ ብቻ በመጥቀምና በመጉዳት ረዳት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። አንቀጹ ላይ፦ “ወላ ሸፊዒን” وَلَا شَفِيعٍ ማለት “እና አማላጅም የላችሁም” ማለት ሲሆን ከመጀመሪያው ሐረግ ለመለየት “ወ” وَ የሚል መስተጻምር ይጠቀማል፥ ያ ማለት “በተጨማሪም አማላጅም የላችሁም” ማለት ነው፤ “ላ” لَا የሚለው “ሐርፉ ነፍይ” በመጀመሪያው ሐረግ ላይ “ማ” مَا የሚለው ሐርፉ ነፍይ ሆኖ ገብቶ በተጨማሪ በሁለተኛው ሐረግ ላይ “ላ” لَا የሚለው ሐርፉ ነፍይ መደገሙ ጣዖታውያን ጣዖቶቻቸውን "ወደ አሏህ በማማለድ ያቀርቡናል" ብለው የሚናገሩላቸውን ጣኦታት አማላጆች አለመሆናቸውን ለማሳየት “አማላጅ የላችሁም” በማለት ዘግቶታል፦ 30፥13 ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም። وَلَمْ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَائِهِمْ شُفَعَاءُ ስለዚህ “አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር እናንተ ከምታጋሯቸው የሚያማልድ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው እንጂ በአሏህ ፈቃድ የሚያማልዱ አማላጆች የሉም ማለትን አሊያም አሏህ አማላጅ ነው ማለትን አያሲዝም። ከአሏህ ሌላ ከቅጣት ሊያድናቸው የሚችል ረዳት የላቸውም፥ እንዲሁ ቅጣት እንዳይቀጡ ወደ አሏህ የሚያማልዱ አማላጅ የላቸውም ማለት ነው። ሙፈሢሮችም የፈሠሩት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦
Показать все...
አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦ 49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106 አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ ‏"‏ እዚህ ቁርኣን እና እዚህ ሐዲስ ላይ ሐሜት ልክ የሰውን ሥጋ እንደ መብላት ሐራም ከሆነ የሰውን ሥጋ ለምግብነት መጠቀም ሐራም ነው። ሰው ከሞተ በኃላ ሥጋው ሬሳ ነውና መቅበር እንጂ የሞተ ሰው ሥጋ መብላት በቁሙ ያለው ሰው ሥጋ እንደ መብላት ይቆጠራል፦ ሡነን እብኑ ማጃህ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 184 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሞተ ሰው አጥንት መስበር በሕይወት እያለ እንደ መሰባበር ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ كَسْرُ عَظْمِ الْمَيِّتِ كَكَسْرِهِ حَيًّا ‏"‏ ‏ ኢማም ሙሐመድ ኢብኑ ኢድሪሥ አሽ ሻፊዒይ "የሞተ ሰው ሥጋ ሕይወትን ለማትረፍ በረሃብ ጊዜ ይፈቀዳል" ብለዋል፥ ለዚህ አባባል ምንም ዓይነት የቁርኣን ሆነ የሐዲስ ደሊል እንከሌለ ድረስ ንግግራቸው ውድቅ ይሆናል። እርሳቸው በ 204 ዓመተ ሒጅራህ በትህትና "የእኔን ንግግር የሚቃወም ሶሒሕ ሐዲስ ሲኖር በሐዲሱን ተግብሩ! ቃሌን ተዉት" ብለዋል፦ "የእኔን ንግግር የሚቃወም ሶሒሕ ሐዲስ ሲኖር በሐዲሱን ተግብሩ! ቃሌን ተዉት"። إذا صح الحديث خلاف قولي فاعملوا بالحديث واتركوا قولي ጃሚዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37 ሐዲስ 106 አቢ ሠዒድ አል ኹድሪይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ይሁን መልካሙን የበላ፣ በሡናህ የተገበረ እና ሰዎች ከሚያስከትለው መዘዝ የታደገ ወደ ጀናህ ይገባል"። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ مَنْ أَكَلَ طَيِّبًا وَعَمِلَ فِي سُنَّةٍ وَأَمِنَ النَّاسُ بَوَائِقَهُ دَخَلَ الْجَنَّةَ ‏"‏ ‏.‏ "ሐላል" حَلاَل ማለት "የተፈቀደ" ማለት ሲሆን በተቃራኒው "ሐራም" حَرَام "የተከለከለ" ማለት ነው። አንድ ጉዳይ ሐላል ወይም ሐራም ማለት የሚቻለው የዓለማቱ ጌታ አሏህ በቁርኣን የነገረን እና ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” በሐዲሳቸው የነገሩን ብቻ እና ብቻ ነው፥ ሐላል የሆነ ጉዳይ ሆነ ሐራም የሆነ ጉዳይ በሸሪዓችን በግልጽ የተቀመጡት ብቻ ናቸው፦ 7፥157 "መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፥ መጥፎ ነገሮችንም በእነርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል"፡፡ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 23, ሐዲስ 4 አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ሐላል ግልጽ ነው፥ ሐራምም ግልጽ ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ግን አጠራጣሪ ነገር ነው”። قَالَ سَمِعْتُ النُّعْمَانَ بْنَ بَشِيرٍ، – وَلاَ أَسْمَعُ أَحَدًا بَعْدَهُ يَقُولُ – سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏”‏ إِنَّ الْحَلاَلَ بَيِّنٌ وَإِنَّ الْحَرَامَ بَيِّنٌ وَبَيْنَهُمَا أُمُورٌ مُشْتَبِهَاتٌ ‏”‏ አንድ ጉዳይ በግልጽ መፈቀዱ እና መከልከሉ ካልተገለጸ "ተፈቅዷል" "ተከልክሏል" ማለት የለብንም፥ ያልተፈቀደ እና ያልተከለከለ ነገር ጉዳይ አጠራጣሪ ነው፥ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ፦ "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል" ብለውናል፦ ጃምዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 2708 አቢል ሐውራእ አሥ-ሠዕዲይ እንደተረከው፦ "እኔ ለሐሠን ኢብኑ ዐሊይ፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ምን ሐፈዝክ? ብዬ አልኩኝ፥ እርሱም፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሐፈዝኩኝ፦ "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል"። عَنْ أَبِي الْحَوْرَاءِ السَّعْدِيِّ، قَالَ قُلْتُ لِلْحَسَنِ بْنِ عَلِيٍّ مَا حَفِظْتَ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ حَفِظْتُ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ دَعْ مَا يَرِيبُكَ إِلَى مَا لاَ يَرِيبُكَ فَإِنَّ الصِّدْقَ طُمَأْنِينَةٌ وَإِنَّ الْكَذِبَ رِيبَةٌ ‏"‏ "መሽቡህ" مَشْبُوه የሆኑ ነገሮችን መተው ተመራጩ ሒክማህ ነው። አምላካችን አሏህ በግልጠተ መለኮት "ሐላል" ያለው "ሐላል" ማለት "ሐራም" ያለው "ሐራም" ማለት ትልቅ ታዛዥነት ነው፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 29, ሐዲስ 117 ሠልማን አል ፋርሢይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” ስለ ቅቤ፣ ስለ ዓይብ እና ስለ አህዮች ተጠየቁ፥ እርሳቸው እንዲህ አሉ፦ "ሐላል አሏህ በመጽሐፉ የፈቀደው ነው፥ ሐራም አሏህ በመጽሐፉ የከለከለው ነው። عَنْ سَلْمَانَ الْفَارِسِيِّ، قَالَ سُئِلَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ عَنِ السَّمْنِ وَالْجُبْنِ وَالْفِرَاءِ قَالَ ‏ "‏ الْحَلاَلُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ فِي كِتَابِهِ وَالْحَرَامُ مَا حَرَّمَ اللَّهُ فِي كِتَابِهِ "‏ ‏.‏ አምላካችን አሏህ ሡናን ከሚተገብሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.