cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ƝƲƦƲ ቴክ

ይህ ቻናል ፈጠራዎችን ፣ መረጃዎችን በአማርኛ& English፣የቴክኖሎጂ እውነታዎችን ፣ የወደፊቱን ቴክኖሎጂ እና የአይቲ ምክሮችን በማካተት የቴክኖሎጂ ዓለምን ያቀርባል፡፡ በተጨማሪም፦ ዌብሳይት በተመጣጣኝዋጋ እንሰራለን 🔷 ማህበራዊ ሚዲያን ለእውቀት ብቻ እንጠቀምበት ! 🔺 ጥያቄ እና አስተያየት ካለ በዚህ ቦት ያሳውቁን! https://t.me/nurudish_bot

Больше
Рекламные посты
4 295
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል ፊጥር በዐል በጤና አደረሳችሁ ፤ አደረሰን! ኢድ ሙባረክ!
Показать все...
Nuru Tech Wish a happy Easter holiday! 🙏
Показать все...
ስለ ቴክኖሎጂ ማወቅ መማር ይፈልጋሉ እነሆ ጋው ቴክኖሎጂ አቤት ምን እንታዘዝ ይሎታል በኮምፒውተር በ ኔትወርኪንግ በግራፊክስ ዲዛይን እና በመሳሰሉት ነገሮችላይ ጥያቄ ካሎት ጋው ቴክኖዎሎጂን መጎብኘት ብቻ ነው https://t.me/Dwped
Показать все...
GAW Technology’s

If you have any questions about technology, you can ask Contact 0922870570

ውድ የኑሩ ሳይቴክ ቤተሰቦች ተመልሰናል በ DOC File እና በ DOCX File መካከል ያለው ልዩነት ********** በኮምፒውተር የተለያዩ የጽሁፍ ስራዎችን ለመስራት ስናስብ በብዛት የምንጠቀምባቸው መጻፊያዎች DOC እና DOCX የሚባሉት ናቸው፡፡ ሁለቱም የማይክሮሶፍ ወርድ ዶክመንት ክፍሎች ሲሆኑ የተለያዩ ምስሎችን፣ የተለያዩ ቴብሎችን እና ቻርቶችን ለመጻፍ ያገለግላሉ፡፡ ለመሆኑ በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ማይክሮሶፍት ዎርድ DOC የሚባለውን የመጻፊያ ስርዓት ዋና መገልገያ (default) አድጎት ቆይቷል፡፡ እስከ 2006 ድረስ DOC በምዝገባና በፈቃድ ጥቅም ላይ የሚውል ነበር፡፡ ከዚያ በኋላም የተለያዩ መሻሻሎች ተደርገውበታል፡፡ አሁን ላይ እንደ LibreOffice Writer፣ OpenOffice Writer፣ KingSoft Writer የመሰሉ በነጻ የቀረቡና በክፍያ አገልግሎት የሚሰጡ መጠቀሚያዎችን አካትቶ ቀርቧል፡፡ እነዚህ ፐሮግራሞች የ DOC ፋይሎችን ለመክፈትና ለማስተካከል ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ በሌላ በኩል DOCX የተባለው የመጻፊያ ፕሮግራም የ DOC ተከታይ ሆኖ በማይክሮሶፍት ወርድ የቀረበ ነው፡፡ በ2007 ተሻሽሎ በቀረበው የወርድ ወይም የመጻፊያ ፕሮግራም ቀዳሚ መጠቀሚያ ሆኖ የቀረበው DOCX ነው፡፡ ይህም የሆነው ማይክሮሶፍት ወርድ እንደ ኦፕን ኦፊስና ODF ካሉ ነጻና ክፍት መጠቀሚያዎቸ በገጠመው ፉክክር ምክንያት ነው፡፡ በ DOCX ውስጥ ያለው የኮድ መስሪያ በ XML የተሰራ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ያለችው X ይህንን የምታመለክት ናት፡፡ ይህ ኮዲንግ ሲስተም አዳዲስ መገለጫዎችን ጥቅም ላይ ያዋለ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንደ PPTX እና XLSX ያሉ ፎርማቶች ላይ ለውጥ አድርጓል፡፡ አሁን ላይ በሁለቱ መካከል ይህ ነው የሚባል ትልቅ ልዩነት ባይኖርም በጣም ትናንሽ ፋይሎችን ለመፍጠር DOCX የተሻለ አማራጭ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የቴሌግራም ቻናል 👉 https://t.me/nurutech
Показать все...
ይህንን የዩቱብ ቻናል ተቀላቀሉ ይጠቅማችኋል https://www.youtube.com/channel/UCYI90Vo6zsDqhqQR85dFyBg
Показать все...
🎯Telegram Update ከሆነ ቦኋላ ያመጣቸው አዳዲስ ገራሚ ፊውቸሮች🔥 ፩ Protected Content in Groups and Channels🛡 ብዙዎችን ያስደሰተ በተለይ የTelegram ቻነል ና ግሩፕ ላላቸው ሰወች እንደምናውቀው Copypast እና Forward ለብዙ የቻነል Owneሮች ራስምታት ና ሲያስመርር የቆየ ነገር ነው አንዱ ላብን ጠብ አድርጎ ግዜውን ሰውቶ ቻነሉ ላይ የፃፈውን ማንኛውም Program ሌላኛው ዘና ፈታ ብሎ ወደ ራሱ ቻነል Copy past በማድረግ እራሱ እንዳዘጋጀው አስመስሎ ይለቃል ይሄ በራሱ የሚሰራውን ሰዉ Moral ይገላል አንዳንዶቹ ደግሞ Credit እያሉ Copy ና Forward ያደርጋሉ ከዚህ ቦኋላ ከማንኛውም ቻነል Copypast ና Forward ማድረግ አይቻልም. ቁርጥሽ እወቂ አዳሜ እስካሁን ያዛጋቹን ይበቃል😏 ፪ Auto Deleted Message ይሄ ፊውቸር ደግሞ ለ አንድ ሰው መልክት ልከን ከ 24 ሰአት ከ 1ድ ሳምነንት ና ከ 1ድ ወር ግዜ ቦኋላ ከላክልነት ሰውዬ ጋር Automatically Deleted እንዲሆን የሚያስችል ነው. ፫ New emoji ለምሳሌ የአንድ ሰዉ Bio ላይ ይሄን emoji 💔 ብንመለከት በቀላሉ ስለ ሰውየው feeling Guess እናደርጋለን እንደሚታወቀው emojiወች የሰወችን Emotion ወይም ስሜት ከቃላት በማይተናነስ መልኩ ይገልፃሉ Telegramምም ይህን በመገንዘብ ሰወች በይበልጥ የተሰማቸውን ስሜት እንዲገልፁ አዳዲስ emoji አምጥቷል በጥቂቱ 😮‍💨😵🤝❤️‍🩹❤️‍🔥 ፬ Delete My Message ይህኛው ፊውቸር ደግሞ ከ አንድ ሰዉ ጋር ካወራነው የChat History ላይ የኛን Message ብቻ ከላክልነት ሰውዬ ጋር ነጥሎ ያጠፋል🔥 የClear History እህት በሉዋት😆 ፭ Change Color / Theme ይሄ ደግሞ የChat Background Color ና Themeን ለመቀየር ና ለማስዋብ የሚያስችለን Setting ሲሆን በፊትም ነበር ሲሆን አሁን ግን ተሻሽሎ በአዳዲስና ማራኪ Themeሞችና Background colors መቷል ሞክሩት ፭ Attach ከስሙ እንደምንረዳው Attach ማያያዝ ሲሆን ማንኛውንም ፃሁፍ ከPhoto ጋር አንድ ላይ ለማያያዝ ያስችላል ትንሽ ቀለል ብሎ መጣ እንጂ ድሮም ያለ ፊውቸር ነው እንደ ከአለም ጋለሪ የድንቃድንቅ የግጥም Channel ላላቹ Owneሮች ምርጥዬ ናት 👌 ፮ Automatic Terminate ይሄ ፊውቸር ደግሞ ከኛ ስልክ ውጪ በሌላ ሰዉ ወይም በጓደኛችን ስልክ የTelegram አካውንታችንን Login ካደረግንና ከተጠቀምን ቦኋላ Automatically ከጓደኛችን ስልክ አካውንታችንን በራሱ Logout ያደርጋል እኛ Logout ማድረግ አይጠበቅብንም.🤗 ይሄ ሚሆነው ግን በገባንበት ሰው አካውንታችንን Automatic Terminate ከሞላን ነዉ ፯ Jump to Next Channel እንደምናውቀው አብዛኞቻችን Telegram ላይ የተለያዩ ቻነሎች ውስጥ join ብለናል ይሄ ፊውቸር ምንድነው የሚያደርገው አንድ ቻነል ላይ ተገብታቹ የሆነ ነገር እየተመለከታችሁ ወይም እያነበባቹ ወደ ሌላኛው ቻነል ለመሄድ ከዛ ቻነል መውጣት አይጠበቅብንም የስልካችንን Screen ወደ ላይ Scroll ስናደርገው ወደ ሌላኛው ቻነል ይወስደናል or ያልፋል🚀 ፰ Live Stream live stream is a one-way video broadcast System. Live Stream ማለት ባጭሩ ቀጥታ ስርጭት ማለት ነው ለምሳሌ ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ሲያዘጋጅ እኛ ቤታችን ሆነን በቀጥታ በTvያችን ቴዲን እንመለከታለን እሱ ግን እኛን አያየንም ቴዲ መመልከት የሚችለው ኮንሰርቱን ላይ የታደሙትን ነው ስለዚህ Live Stream የተባለው Technology አንድን ሰው የትም ቦታ ሆነን በTv በTablets በስልክ ቀጥታ መከታተል ያስችላል ኮንሰርቱን ታደምን ማለት ነዉ Telegram ይህን ፊውቸር ነው ያመጣው 🙈 ፱ Flexible Forwarding ይሄ ፊውቸር ጥቅሙ ለምሳሌ አንድ ሰዉ message ቢልክልን ያን መልክት ለሌላ ሰዉ ሶስተኛ ወገን ስልንክ መጀመሪያ የላከውን ሰው Name Hide ያደርጋል ይሄ ደግሞ መጀመሪያ ላይ ለላከው ሰውዬ privacy ደህንነት የተጠበቀ ያደርገዋል.🤟 ፲ Unpin All Message ቻነላቸን ላይ Pin ያደረገውን Post በሙሉ በአንዴ Unpin ለማድረግ የሚያስችል ፊውቸር ነው እያንዳንዱን Post Unpin ከማድረግ ይታደገናል😎 Telegraph ሌሎችም ብቹ ገራሚ ፊውቸር አምጥቷል Telegram በዚህ ከቀጠለ Social mediaውን መቆጣጠሩ አይቀርም Facebook IG Twitter WTs'App የመሳሰሉት ላይ የሌለ ፊውቸር ነው እያሳየን ያለው Developeሮቹ ማሻሻያውን እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል👍
Показать все...
ሁሉንም የስራ ማስታወቂያዎች በአንድ ቦታ ለማግኝት HaHuJobsን ይቀላለቁ ! @HaHuJobs @HaHuJobs የ0 ዓመት የስራ ልምድን የሚጠይቁ ስራዎችን ብቻ ለማግኝት ከፈለጉ HaHuJobs Fresh Graduates ን ይቀላቀሉ ! @hahujobsforfreshgraduates @hahujobsforfreshgraduates በመረጡት የስራ ዘርፍ ብቻ የስራ ዕድሎችን መከታተል ከፈለጉ ደግሞ HaHuJobs Bot ን ሰብስክራይብ አድርገው ተጠቃሚ ይሁኑ ! @hahujobs_bot @hahujobs_bot ምንግዜም ለሃገር ልጅ በሃገር ልጅ!! @hahujobs @hahujobs_bot Promo Details Contestant Name: #Sal@Deen Contestant ID: #402939984
Показать все...
Join
ውድ የኑሩ ሳይቴክ ተከታታዮች ይህን የዩቱብ ቻናል Subscribe በማድረግ ብዙ ነገሮችን ይወቁ 👇👇 Subscribe 👇👇👇 https://youtu.be/sqvWGuEH08k
Показать все...
#የፌስቡክ_ፕሮፋይላችንን_እንዴት_መቆለፍ_እንችላለን? የፌስቡክ ፐሮፋይላችሁን እንድትቆልፉ እመክራለሁ፡፡ ፌስቡክ ላይ ፖስት የምታደርጉት ፎቶ፤ቪዲዮ፤ ወይም መልዕክት ከፌስቡክ ጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ሰው እንዳያየው ለማድረግ ፐሮፋይላችንን መቆለፍ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፕሮፋይላችንንም ከጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ሰው እንዳያይ ፕሮፋይላችንን መቆለፍ አለበት፡፡ ለአንድሮይድ ስልኮች ላይ ብቻ ነው ይሄ አገልግሎት ያለው፡፡iOS ስልኮች ላይ አይገኝም፡፡ እንዴት ነው የፌስቡክ ፕሮፋይላችንን ሎክ /መቆለፍ የምንችለው? 1ኛ፦ፌስቡክ አፕሊኬሽን እንከፍትና ወደ ፕሮፋይላችንን እንገባለን 2ኛ፦ በቀኝ በኩል በመደዳ የሚታዩትን ሶስት ነጥቦችን ክሊክ ማድረግ፤ 3ኛ፦ “Lock Profile” የሚል አማራጭ ሲመጣ እሱን ክሊክ ማድረግ፤ 4ኛ፦ ቀጥሎ “Lock Your Profile“ የሚል ምርጫ ከስር ይመጣል፡እሱን ክሊክ ማድረግ፤ 5ኛ፦ በመጨረሻ‘You Locked Your Profile' የሚል ይመጣል፤እዛው ላይ OK ብለን እንጨርሳለን፡፡ አሁን ፌስቡክ ፕሮፋይላችን ተቆልፋል፡፡ ፕሮፋይላችንን ጨምሮ ፖስት የምናደርጋቸው ፎቶዎች፤ቪዲዮዎች እና መልዕክቶች ከፌስቡክ ጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ማንም ሰው ማየት አይችልም፡፡
Показать все...
አንድ አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ #ጎጂ ወይም #ጠቃሚ መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? ከGoogle Play Store ላይ የምናወርዳቸው አፕሊኬሽኖች ጠቃሚ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው እና ጎጂ እንዳልሆኑ የተመሰከረላቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን አንድ አንድ ግዜ ጠቃሚ መስለው ጎጂ አፕሊኬሽኖችን Play Store ላይ ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡ ታድያ Play Store ላይ አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ስናደርግ አፕሊኬሽኑ ጠቃሚ ወይም ጎጂ መሆኑን እንዴት መለየት እንችላለን? 1. አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ እንደተደረገ መመልከት ዳውንሎድ ማድረግ የፈለግንው አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ (Download Count) እንደተደረገ በደንብ መመልከት ለምሳሌ ዳውንሎድ የምታደርጉት አፕሊኬሽን አንድ ሚሊዮን ግዜ ወይም ከዚያ በላይ ዳውንሎድ እንደተደረገ ካያችሁ ወድያው አፕሊኬሽኑ የተለቀቀበት ቀን በደንብ መመልከት፡፡ ምክንያቱም አብዛኛው አፕሊኬሽን ከተለቀቀበት ግዜ ጀምሮ አንድ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የቆየ ሲሆን ነወ ከሚሊዮን በላይ ዳውንሎድ ሊኖረው የሚችለው፡፡ ስለዚህ እናንተ ማውረድ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ከተለቀቀ አንድ ዓመት ካልሞላው እና ዳውንሎድ የተደረገው ከሚሊዮን በላይ ከሆነ አፕሊኬሽኑን ከማውረድ ብትቆጠቡ ይሻላል፡፡ 2. ስለ አፕሊኬሽኑ የተሰጡ የተወሰኑ አስተያየቶችን ማንበብ ዳውንሎድ ማድረግ የምትፈልጉት አፕሊኬሽን ከማውረዳችሁ በፊት ከዚህ በፊት አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ያደረጉ ሰዎች ስለ አፕሊኬሽኑ አስተያየት (Reviews)ያስቀምጣሉ፡፡ እነዚህን አስተያቶች በጥንቃቄ ማንበብ፡፡ ስለ አፕሊኬሽኑ በጣም የሚያማርሩ አስተያየቶች ካነበባችሁ አፕሊኬሽኑ ከማውረድ እንደጥቆጠቡ እመክራለሁ፡፡ 3. የአፕሊኬሽኑ ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ አፕሊኬሽኑ ከላይ የተጠቀሱትን ፍተሸዎች ካለፈ ዳውንሎድ ታደርጉታላችሁ፡፡ ከዚያ ኢንስቶል ስታደርጉት የአፕሊኬሽኑን ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡ ሁላችንም ማለት ይቻላል አፕሊኬሽን ኢንስቶል ስናደርግ ስምምነቱን ሳናነብ "Accept" እንላለን፡፡ ልክ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የሳይበር ወንጀለኞች ይህንን ባህሪያችን ስለሚያውቁ እኛን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን ስምምነቱ ላይ በማስገባት ጥቃት ሊፈፁሙብን ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ስምምነቱን ስታነቡ ለምሳሌ data mining, data sharing, pop-ups ወዘተ የሚሉ ቃላት ከተመለከታችሁ የአፕሊኬሽኑን ኢንስቶሊንግ ሂደት እንድታቋርጡ እመክራለሁ፡፡፡ ስለዚህ ዳውንሎድ ማድረግ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ቢያንስ እነዚህን 3 ፍተሸዎችን ካለፈ ጎጂ አይደለም ማለት ነው፡፡
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.