cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!

Рекламные посты
1 050
Подписчики
+124 часа
+17 дней
+3530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

وَٱلسَّٰبِقُونَ ٱلْأَوَّلُونَ مِنَ ٱلْمُهَٰجِرِينَ وَٱلْأَنصَارِ وَٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُم بِإِحْسَٰنٍۢ رَّضِىَ ٱللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا۟ عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّٰتٍۢ تَجْرِى تَحْتَهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًۭا ۚ ذَٰلِكَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡(التوبة 100)
Показать все...
የሰለፍይነት ጥሪ (ደዕወቱ አሰለፊያ)ማለት በቁርኣንና በሀድስ ወደመስራትና ቁርኣንና ሀድስን በደጋግ ቀደምቶች (በሶሀቦች ፣በታቢዖችና እነሱን በመልካም በተከተሏቸው )ምርጥ ትውልዶች አረዳድ ወደመረዳትና ተግባራዊ ወዴማድረግ የምትደረግ ጥሪ ናት። በማንኛውም የህይዎት አቅጣጫ በአምልኮ፣በሙዓመላ ና በማህበራዊ አኗኗር የነዚህን ምርጥ ትውልዶች ፈለግ መከተል ነው እውነተኛ ሰለፍይነት። አላህ ሱብሃነ ወተዓላ በቁርኑ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሀድሳቸው እንድንከተል ያዘዙን ይችን ጥሪ ነው። አላሁ ተዓላ እንድህ ብሏል፦ ٱتَّبِعُوا۟ مَآ أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ وَلَا تَتَّبِعُوا۟ مِن دُونِهِۦٓ أَوْلِيَآءَ ۗ قَلِيلًۭا مَّا تَذَكَّرُونَ ከጌታችሁ ወደእናንተ የተወረደውን ተከተሉ፡፡ ከአላህም ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ፡፡ ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ፡፡ በሌላ አንቀፅም እንድህ ብሏል፦ وَمَن يُشَاقِقِ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ ٱلْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ ٱلْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِۦ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِۦ جَهَنَّمَ ۖ وَسَآءَتْ مَصِيرًا ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች! እንድሁም ሱረቱል በቀራ አንቀስ  137 እንድህ ብሏል፦ فَإِنْ ءَامَنُوا۟ بِمِثْلِ مَآ ءَامَنتُم بِهِۦ فَقَدِ ٱهْتَدَوا۟ ۖ وَّإِن تَوَلَّوْا۟ فَإِنَّمَا هُمْ فِى شِقَاقٍۢ ۖ فَسَيَكْفِيكَهُمُ ٱللَّهُ ۚ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ በርሱ ባመናችሁበት ብጤ ቢያምኑ በእርግጥ ተመሩ፡፡ ቢዞሩም እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱንም አላህ ይበቃሃል፤ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው (البقرة 137) አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ሙሃጅሮችንና አንሷሮችን እንድሁም እነሱን በመልካም የተከተሏቸውን ሲያወድስ እንድህ ይላል፦ وَٱلسَّٰبِقُونَ ٱلْأَوَّلُونَ مِنَ ٱلْمُهَٰجِرِينَ وَٱلْأَنصَارِ وَٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُم بِإِحْسَٰنٍۢ رَّضِىَ ٱللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا۟ عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّٰتٍۢ تَجْرِى تَحْتَهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًۭا ۚ ذَٰلِكَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡(التوبة 100)   ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሂህ በሆነ ሀድስ እንደመጣው እንድህ ብለዋል ፦ عليكم بسنتي وسنت الخلفاء الراشدين المهديين من بعدي...الحديث. "የኔንና ከእኔ በኋላ ያሉ ቅንና የተመሩ የሆኑ ምትኮዎችን ሱና በመያዝ ይኑርባችሁ... ! እንደዚሁም ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ይቺ ኡማ ወዴ ሰባ ሶስት እንደምትከፋፈል ከገለፁ በኋላ ከእነዚያ ውስጥ ሰባ ሁለቱ የእሳት ሲሆን ከእሳት የምትድነው አንዷ ቡድን እሳቸውና(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)ባልደረቦቻቸው በነበሩበት ነገር ላይ ያለች ቡድን እንደሆነች ተናግረዋል። ስለዚህ ትክክለኛ ሰለፍይ መሆን የፈለገ ሰው የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለምና የእነዚያን ምርጥ ትውልዶች አካሃድ በመማር እግር በእግር መከታተል አለበት!!አለዚያ ሰለፍይነት ነኝ ብሎ በመሞገት አትገኝም:: https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
Показать все...
በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!

إحرص على ما ينفعك @Abu_babelheyr_bin_Sadik

https://t.me/+Se4xqUVr3TtG4W9L

የፈለግከውን ነገር ስራ ስራው ጥሩ ከሆነ መጀመሪያ የምትጠቀመው አንተ ነህ ስራው መጥፎ ከሆነም መጀመሪያ የምትከስረው እራስህ ነህ ። ( مَنْ عَمِلَ صَالِحًا فَلِنَفْسِهِ ۖ وَمَنْ أَسَاءَ فَعَلَيْهَا ۗ وَمَا رَبُّكَ بِظَلَّامٍ لِلْعَبِيدِ መልካም የሠራ ሰው ለነፍሱ ነው ፡፡ ያጠፋም ሰው በእርሷ ላይ ነው ፡፡ ጌታህም ለባሮቹ በዳይ አይደለም ፡፡" [ፉሲለት 46]         https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
Показать все...
የግል አቋማችን ለማፅናት ብለን የማይነቃነቁትን መነቅነቃችን ከነስራችን የመነቀል እጣ ፋንታችን ያቀረብን ይመስላል ኑር
Показать все...
👍 3👎 1
➴⁾⁾⁾⁾ልጅነት⁽⁽⁽⁽ የለሰለሰ መሬት   ➴⁾⁾⁾⁾ወጣትነት⁽⁽⁽⁽ የአዝመራ ዘመን ➴⁾⁾⁾⁾ሽምግልና⁽⁽⁽⁽ ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን እናስተውል! ➴በሽምግልናችን የምናጭደው   የወጣትነታችንን አዝመራ ነውና   ዛሬ ለምንዘራው እንጠንቀቅ። @Abu_babelheyr_bin_Sadik
Показать все...
👍 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
◎ ከሰለፎች አንደበት ◎ قال سعيد بن المسيب ◉ إن الرجل ليصلي بالليل ، فيجعل الله في وجه نورا يحبه عليه كل مسلم ◎فيراه من لم يره قط فيقول : إن لأحبُ هذا الرجل ◉ሰዒድ ኢብኑል ሙሰየብ አሏህ ይዘንለት እንድህ ይላል ◉አንድ ሰው ለሊት ይሰግዳል አሏህ በፊቱ ላይ ብርሃን ያደርግለታል ያንንም ብርሃን ሙስሊም ሁሉ ይወደዋል። አንድም ቀን አይቶት የማያውቅ ሰው ያየውና (ወሏሂ እኔ ይህን ሰው እወደዋለሁ ይላል። (ሩህባኑ ለይል (2/454) https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
Показать все...
👍 2
መቼ ይሆን ከስድብ ከዘለፋ ከማሽሟጠጥ የፀዳ ረድ ምንሰማው❓    የረድ ጥቅሙ ሰዎችን ካሉበት ስህተት ለማውጣት ነው ወይስ በስህተታቸው ላይ ለማዘውተር❓ ከስህተታቸው ለማውጣት ከሆነ እንዴት ሆኖ ነው አንድ ሰውን እየዘለፍከው እየሰደብከው ተውበት አድርግ ምትለው?  እኔ በራሴ በእዝነት የተሞላ ሰዎችን ካሉበት ችግር ለማውጣት የተደረገ ረድ መስማት ናፈቀኝ ❗️ ግንፍልተኛ ፣ለምን ተነካው❗️ቂም በቀል❗️ጥቅም❗️ወገንተኝት፣ ሌሎችም ነገራቶች የሚንፀባረቁበት ረድ ብቻ ለምን ይሆናል❓እዝነት ፣ርህራሄ ፣ ማስተማር፣ መቀየር፣ መስዋት መክፈል ወዘተ የመሳሰሉት ነገራቶች ቢኖሩ ፈጠነም ዘገየም ለውጥ ይመጣል።     👉አንድ ወንጀል ላይ ያለን አካል ወንጀሉን ለማስተው እየሞለጭከው እየዘለፍከው እያንጓጠጥክበት  ልትመክረው ነው?  ይሄ መቼም አያዳምጥህም ❗️እንኳን ረድ የተደረገበት ይቅርና ከሩቅ ሆኖ የሚሰማ አካል እንኳን ይታዘብሃል።     👉እንዴት ሆኖ ነው  ኪኪኪኪኪኪ ይባልና ተውበት አድርግ ሚስጥር ይዘረገፍና ተውበት አድርግ ጉድህን አወጣዋለውና ተውበት አድርግ የሆነ የመንደር ፀብ እኮ ነው ሚመስለው ❗️ 📌 ሌላው ደግሞ  ጦር ሜዳ ያለ ይመስለዋል መሰለኝ ዲሽቃ ፣ድሮን፣ መትረየስ፣ ጂኒ ጃንካ ምናምን ይላል እንዴ❓ መጀመሪያ ትጥቅ ፍቱ እንጂ የምን ማስፈራራት የምን ቀረርቶ ነው ጦር ሜዳ ጫካ መሽገህ ነው እንዴ ያለከው❓❗️      እሱን እናውቀዋለን ምን ያውቃል ባዶ ነው ቀፎ ነው  እያለ የሚያሽሟጥጥ የሰዎችን ማንነት የሰዎችን የአፈጣጠር ሁኔታ እያወሩ ረድ ተደራረግን ማለት በጣም የሚገርም ጉዳይ ነው።       እንደው መረጃ አምጥቼ ነው ረድ ያደረኩት ብትለም እንኳን ያመጣከው መረጃ ስሜትህን ማብረጃ እንጂ ሌላ አይደለም❗️    🤌እናስብ እናስተውል ጭቅጭቅ ሰለቸን እንደው ለምን ለተራው ማህበረሰብ አይታሰብም አንተ እንደፈለክ የምታወራው መስአላ ብዙ ሰዎችን ሊያጨናንቅ እንደሚችል አለማወቅ ራሱ የዳዕዋ ጥበቡን አካሄዱን ያልተረዳ ሰው መንገድ ነው። ለሰዎች እናስብ አይምሮን ሚመጥን ነገር ብናሰራጭ የተሻለ ነው።    እኛ ሁል ጊዜ ጠላቶቻችን ያስቀመጡልንን የቤት ስራ በመስራት እርስ በርስ በመቦጫጨቅ  እንወጠራለን❗️ እነሱ ከስር ስር ስንትና ስንት የአክፍሮት ስራዎቻቸውን ይሰራሉ❗️ ለምን አናስብም የተወሰነ ነገር ይሰራና አሁንማ ዳዕዋዋ ሰፍታለች ይባላል አረ ገና ብዙ እጅግ በጣም ብዙ ያልተሰሩ ጉዳዮች አሉ፦ ስንትና ስንት ሰው በጭለማ ውስጥ የሚኖር አለ ሊመለስ ወደ ዲን ሊገባ ያሰበውን ሰው በጭቅጭቃችን ስንቱን መለስነው ስንቱን ገፋነው ❓አረ ወገን ቆም ብለን እናስብ እንጂ❗️እኛ እኮ አላፊዎች ነን ለተተኪ ትውልድ ጭቅጭቅና ንትርክ ለምን እናወርሳለን ❓እኛ በዚህ ደረጃ መደማመጥ ካቃተን ቀጣዩ ትውልድ ከኛ የባሰ ነገራቶችን አስፍቶና ችሎ የማለፍ አቅም አይኖረውም  ስትሳደብ ስድብክን ይይዛል ስትጨክን ጭካኔክን ይማራል።  ስትከባበር መከባበርን ይማራል ስትዘረጥጥ ዘርጣጭ ይሆናል።          ታዲያ ምን አተረፍን ወንድሞች 👉https://t.me/AbuEkrima https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
Показать все...
አቡ ዒክሪማ أبو عكرمة

ይህ ቻናል የተለያዩ አስተማሪ የሆኑ ትምህርቶችን፣ ሙሃደራዎችን፣ የቀደምት አኢማዎችን ንግግሮች እንዲሁም የተለያዩ በጊዜያችን ያሉትን የሱና ዑለማዎች ፈትዋና ንግግር የምናቀርብበት ቻናል ነው።

👍 2
መነጋ ስትሆን ያንተ ወገን ፖለቲካ ሐላል የሌላው ደግሞ ሐራም፣ያንተ የሌላን ሰው ስም ማጥፋት ትክክል፤የሌላው ግን ስህተት፤ያንተ ዘረኝነት ሽቶ የነርሱ ደግሞ ጥንብ፣ያንተ ሸይኽ ቅዱስ የሌላው ዕርኩስ፣ያንተ ኡስታዝ ጀግና የሌላው ፈሪ፣ያንተ ዓሊም ምሁር የሌላው ጃሂል ይመስልሃል። መንጋ ስትሆን  በአንድ ሰው ላይ በሚነሳ ጥያቄ ገና ጥያቄው ሳይገባህ ቱግ ትላለህ ጥያቄውን ራሱ እንደ ትልቅ ድፍረት ትቆጥራለህ። ወዳጄ የፈለከውን መሆን ትችላለህ፤መንጋ ግን አትሁን እባክህ።ምክኒያቱም መንጋነት የራስን ማገናዘቢያ አዕምሮ ቁጭ አድርጎ የሌላውን በራስ ላይ መትከል ነው።ሌላውን በጭፍን መከተል ነው። መንጋነት ጥፋት ነው  ዕውቀትና ብስለት ማጣት ነው።ለኢስላምም ሆነ ለሙስሊሙም አይበጅም፤ጥርጣሬን ያሰፍናል፣ውሸትንና ሀራምን ያፀናል።ማህበረሰብን ይከፋፍላል፣አንድነትን ይሸረሽራል። ለግለሰብና ለቡድን ሳይሆን ለዲናችን እያሰብን፣ስለዲናችን እየጠየቅን ፣እየተማርን፣እየተመራመርን፣በራሳችን ላይም ቢሆን እውነትን እየተናገርን ፍትህን እያሰፈንን እንኑር።የሰው ሀሳብ ብቻ ተሸካሚ አንሁን። ወዳጆቼ!ከመንጋነት እንላቀቅ።በዕውቀት ራሳችንን እንቻል። ሰው አምላክ እንዳልሆነ እንወቅ።የአደም ልጅ ይሳሳታል፣ወደ ስሜቱ ያዘነብላል አውቆም ሆነ ሳያውቅ ያጠፋል.... https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
Показать все...
በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!

إحرص على ما ينفعك @Abu_babelheyr_bin_Sadik

https://t.me/+Se4xqUVr3TtG4W9L

👍 2
☞ሐጅ አድርጎ የመጣን ሰው "ሐጂ" ማለት እንዴት ይታያል? በበርካታ የሙስሊም ሀገሮች ላይ ሐጅ ያደረጉ ሰዎች ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱ ወዲያውኑ "ሐጂ" የሚል ስም ይሰጣቸዋል። ይህም ስም እስከ መጨረሻው አብሮት ይዘልቃል ይህ ተግባር እንዴት ይታያል? ☞ኢብኑ ዑሠይሚን "ይህ ስህተት ነው። የሪያእ (ይስሙልኝ፤ ይወቁልኝ) አይነት ጠንቅ በውስጡ ያያዘ ነው። ይህን ስም እንደ ማዕረግ አድርጎ መጠራት የለበትም። ሰዎችም በዚህ ስም መጥራት የለባቸውም። በረሱል ዘመን ሐጅ ላደረገ ሰው "ሐጂ" ብለው ስም አላወጡለትም።" 📚 مجموع الفتاوى والرسائل(٢٤٠/٢٤) https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
Показать все...
በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!

إحرص على ما ينفعك @Abu_babelheyr_bin_Sadik

https://t.me/+Se4xqUVr3TtG4W9L

👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
🔥ምን ሊጠቅም‼️ መልካም ስራ ሰርተህ ካልሆነህ ላኼራ ካፈር በታች ገብተህ ስላንተ ቢወራ ስምህ ተደጋግሞ በአለም ላይ ቢጠራ ቢዘከር ቢወደስ ሀውልት ቢሰራ ቢነገር ታሪክህ ዝንት አለም ቢወራ ጨለማው ተገፎ ቀብርህ ካላበራ ምን ሊጠቅም ወሬ ዝናስ ምን ሊሰራ።
Показать все...
👍 6
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.