ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Открыть в Telegram
1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
በቂርቆስ ባለፉት 9 ወራት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች አመርቂ ውጤት የተመዘገበባቸው መሆኑ ተገለፀ። አጠቃላይ ስራዎቹን ከከተማ አስተዳደሩ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የተውጣጡ ልዑካን ቡድኖች በዛሬው እለት ጎብኝተውታል። ምልከታው የተካሄደው በአቶ ተፈራ ሞላ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ በሚመራ ቡድን ሲሆን ቡድኑም በምልከታው በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ በወረዳ 04 እና 09 የተገነቡ የቅብብሎሽ ጣቢያ ግንባታዎችን፤በወረዳ 11 መንገድ አካፋይ የተነሳ ቅብብሎሽ ጣቢያና ወረዳ 03 ፤በፅዳት ሞዴል ብሎኮችና ሞዴል ወረዳ 02፤የሽርክና ማህበራት የስራ እንቅስቃሴ፤የመልሶ መጠቀምና ዑደት ማድረግ፤ተቋማትን ፅዱና ምቹ ከማድረግ አኳያ፤የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ፤የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታና አገልግሎት ፤የዋና ዋናና ሁለተኛ መንገዶች የፅዳት ስራዎችንና የሲቪል ምዝገባ አገልግሎት አሰጣጥ ምልከታ አካሂደዋል። በመጨረሻም በጥንካሬ የታዩትን እንዲቀጥሉ እንዲሁም በክፍተት የታዩትን ማረም እንደሚገባ በድጋፍና ክትትሉ የተመላከተ ሲሆን የተሰጡ ግብረመልሶችንና አዳዲስ ፈጠራዎችን በማከል ቂርቆስን በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ሞዴል ለማድረግ በቀሪ 3 ወራት እንደሚሰሩ አቶ አብዱልሃዲ ረሺድ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ኃላፊ ገልፀዋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት በተሰሩ ስራዎች ላይ ምልከታ ተካሄደ:: በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አሰኪያጅ ፅ/ ቤት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ባለፉት 9 ወራት የተከና
+1
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት በተሰሩ ስራዎች ላይ ምልከታ ተካሄደ:: በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አሰኪያጅ ፅ/ ቤት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ባለፉት 9 ወራት የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም አስመልክቶ የመስክ ምልከታ አካሄዷል። በምልከታው በክፍለ ከተማው በፅዳት ሞዴል ብሎኮች፤የጽዳት ማህበራት፤በመልሶ መጠቀም፤ተቋማት ፁዱና ምቹ ከማድረግ አኳያ፤የደረቅ ቆሻሻ የቅብብሎሽ ጣቢያዎች፤የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት፤ዋና ዋና የአስፓልት መንገዶች የፅዳት ስራዎችን ምልከታ ተካሄዷል፡፡ በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ የመስክ ምልከታውና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚሰጠው ግብረመልስ በክ/ከተማው ባለፉት 9 ወራት የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን ለማጎልበትና ክፍተቶችን ደግሞ ፈጥኖ ለማረም ከፍተኛ እገዛ አለው ብለዋል፡፡ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+9

በቦሌ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤቶች ያለፉት 9 ወራት የስራ አፈፃፀምን አስመልክቶ የመስክ ላይ የስራ ምልከታ ተካሄደ። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሁለቱ ክፍለ ከተሞች ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤቶች እየተከናወኑ ካሉ በተለይ የፅዳት እና የመብራት አገልግሎት ላይ በተግባር ያለዉን የስራ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረ የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል። በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በዚሁ ወቅት በክፍለ ከተሞቹ በተለያዩ ወረዳዎች ከጽ/ ቤቱ ሌሎች አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በጋራ በጽዳት ሞዴል የሆኑ ወረዳዎችና ብሎኮች፣የቅብብሎሽ ጣቢያዎች፣ የተሰሩ የኮምፓስት ስራዎች ፣ በኤሌክትሪክ አገልግሎት ረገድ ደግሞ የመንገድ ዳር መብራቶች በምን ያህል ደረጃ አገልግሎት እየሰጡ እንዳሉና እና አገልግሎት የማይሰጡትንም ለመለዬት የሚያግዝ የመስክ ምልከታ ለማድረግ ተችሏል። ከምልከታው በሁዋላ አቶ ተፈራ ሞላ እንደተናገሩት የመስክ ሞልከታው በ9 ወራት የስራ አፈፃፀም የቀረቡ ስራዎች በመስክ ምልከታው በክ/ከተሞች ስለ መከናወናቸው ተጨባጭ ማረጋገጫዎች ሆነው መገኘታቸውን አድንቀው የታዩ መጠነኛ ክፍተቶችን ደግሞ በቀጣይ 3 ወራት በሙሉ አቅምና ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ በርብርብ መፈፀም እንደሚገባ አስገንዝበዋል:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ኤሌክትሪክን ስንጠቀም ሁል ጊዜም ቅድሚያውን ለጥንቃቄ እንስጥ! ============== በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማህበራዊም ሆነ ለኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴያችን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ኤሌ
ኤሌክትሪክን ስንጠቀም ሁል ጊዜም ቅድሚያውን ለጥንቃቄ እንስጥ! ============== በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማህበራዊም ሆነ ለኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴያችን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ኤሌክትሪክ እጅግ አስፈላጊ የመሆኑን ያህል ተገቢውን ጥንቃቄ ተግባራዊ ካላደረግን በአካልና በንብረት ጉዳት ላይ ጉዳት ያደርሳል፤ ከዛም ባለፈ ውድ የሆነውን የሰው ህይወትን ሊያሳጣም ይችላል፡፡ በመሆኑም ሁል ጊዜ ቅድሚያውን ለጥንቃቄ ልንሰጥ ይገባል፡፡ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+7

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ባለፉት 9 ወራት በጽዳትና በኤሌክትሪክ አገልግሎት ረገድ የተከናወኑ ስራዎች ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ። በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ባለፉት 9 ወራት በለሚኩራ ክ/ ከተማ በተለይም በጽዳትና በኤሌክትሪክ አገልግሎት ረገድ የተከናወኑ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ለማረጋገጥ የሚያስችል የመስክ ምልከታ በዛሬው እለት ተደርጓል። በመስክ ምልከታውም ወቅት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በፅዳት ሞዴል ብሎኮች፤ሞዴል ወረዳዎች፣የጽዳት ማህበራት፤በመልሶ መጠቀም፣ኮምፖስት ቦታዎች ፤የቅብብሎሽ ጣቢያዎች፤ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት አገልግሎት አሰጣጥ ማለትም በዋና ዋና የመንገድ ዳር መብራቶች ዙሪያ ላይ ነው የመስክ ምልከታዉ የተካሄደው፡፡ የመስክ ምልከታዉ በክፍለ ከተማዉ ያሉትን ጥንካሬዎችን በይበልጥ ለማስቀጠል እና አንዳንድ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም እንዲሁም በቀጣይ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚረዳ በምልከታዉ ወቅት ተገልጿል፡፡ በተጨማሪ በጉብኝቱ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ሃይማኖት ዘለቀ እንደገለፁት ምልከታ የተደረገባቸዉ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጡን ምቹ ለማድረግ የተሰሩትን መልካም ስራዎችን በማስቀጠል እንዲሁም አንዳንድ የተስተዋሉ ክፍተቶችን በቀሪ የበጀት አመቱ ሶስት ወራት ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከርና በጋራ በመስራት ማረም እንደሚገባ በመስክ ምልከታዉ ወቅት አሳስበዋል፡፡ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+6

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከማዕከል አስከ ወረዳ ከሚገኙ አመራሮች ጋር የ9ወር የሪፎርም ሪፖርት እና እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ:፡ የኤጀንሲው እቅድ እና በጀት ዳይሬክቶሬት አቶ ጥጋቡ ሹመይ ኤጀንሲው በሪፎርም ስራዎች የሰራቸውን እንዲሁም በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር በመዘርጋት ለህብረተሰቡ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረጉን በሪፖርቱ አካተው አቅርበዋል፡፡ በተመሳሳይም የኤጀንሲው እቅድ እና በጀት ባለሙያ የሆኑት አቶ ደምሰው ቢሻው የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የመጣው ውጤት የሁሉም ተሳትፎ የታከለበት እንዲሁም በቀጣይም ስራዎችን በመስራት ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማምጣት እንተጋለን በማለት ሀሳባቸውን ገልፀዋል፡፡ የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ኤጀንሲው ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር የሪፎርም ስራዎችን በመተግበር እንዲሁም ከእጅ ንኪኪ ነጻ በሆነ ቴክኖሎጂ አገልግሎቱን ለማሻሻል ኤጀንሲው እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በመስጠት ግምገማው ተጠናቋል፡፡ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ሬ ባካሄድነው የምክር ቤታችን ጉባኤ ላይ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ ለማድረግ በገባነው ቃል መሠረት የጀመርናቸውን የኮሪደር ልማት ስራዎችና የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ማኅበራዊ ትስስራቸው ሳይፋለስ የ
+5
ሬ ባካሄድነው የምክር ቤታችን ጉባኤ ላይ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ ለማድረግ በገባነው ቃል መሠረት የጀመርናቸውን የኮሪደር ልማት ስራዎችና የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ማኅበራዊ ትስስራቸው ሳይፋለስ የተሻለ አካባቢና መኖሪያ ቤት፣ ካሳ፣ ምትክ መሬትና መስሪያ ቦታዎችን በመስጠት ያስተናገድንበትን ስራ እንዲሁም የኮሪደር ልማቱ እየተፋጠነ ያለበትን አግባብ የተመለከተ ሪፖርት አቅርበናል። በተጨማሪም ምክር ቤታችን የ21.7 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ያጸደቀ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 96 በመቶው ለካፒታል በጀት የሚውል ይሆናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት የከተማዋን የልማት ኮሪደርን አስመልክቶ ከተናገሩት:- - ለንግድ ቤቶች እና ለግል ባለይዞታዎች ምትክ መሬትና የካሣ ክፍያዎችን መፈጸም፣ የልማት
+2
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት የከተማዋን የልማት ኮሪደርን አስመልክቶ ከተናገሩት:- - ለንግድ ቤቶች እና ለግል ባለይዞታዎች ምትክ መሬትና የካሣ ክፍያዎችን መፈጸም፣ የልማት ተነሺዎች ወደ ተዘጋጀላቸው የመኖሪያና የመስሪያ ቦታ የሚያጓጉዝ ትራንስፖርት ማዘጋጀት ፣ በገቡበት አካባቢ ልዩ አቀባበል እየተደረገላቸው ፣ በአብዛኛው ማህበራዊ ትስስራቸው ተጠብቆ የማዘዋወር ሥራዎች በከፍተኛ ጥንቃቄና የኃላፊነት ስሜት ተከናውኗል - ግልፅና ዝርዝር የማስፈጸሚያ እቅድ በማዘጋጀት የዲዛይን ዝግጅት፣ በጀትና ለልማት ተነሺዎች መኖሪያ ቤት ግንባታ፣ መስሪያ ቦታና ምትክ መሬት የማዘጋጀት ስራ ተሰርቷል፡፡ - ከመኖሪያ እና መስሪያ ቦታቸዉ የሚነሱ የልማት ተነሺዎችን መረጃ ማደራጀት፣ ተነሺዎችን ማወያየት፣ በምርጫቸዉ መሰረት በተቀላጠፈ አግባብ የሚስተናገዱበት ስርዓትና የሚያጋጥሙ ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያስችል አሰራርና አደረጃጀት ተዘርግቶ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡ - የልማት ተነሺዎች የገቡባቸዉ የመኖሪያ ቤቶች የመንገድ፣ የመብራት፣ የውሃና ፍሳሽ መሠረተ ልማቶች የተሟላላቸው ስለመሆኑና የቅርብ ክትትል በማድረግ ተነሺዎች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንዲሰጣቸው ተደርጓል፡፡ - የከተማው ከፍተኛ አመራር የመኖሪያ ቦታዎችን ሁኔታ እና የልማት ተነሺዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመጎብኘትና አገልግሎት ስለመሟላቱና ጉድለቶችም ካሉ ለማረም የሚያስችል ጉብኝት በሁሉም ሳይቶች ላይ በተደጋጋሚ አድርጏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ሶስተኛ ዓመት የስራ ዘመን ሶስተኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል። ምክር ቤቱ በዛሬው መደበኛ ጉባዔው የሶስተኛ ዓመት የስራ ዘመን ሶስተኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤውን ማፅደቅ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማት የአንድ ወር ከ15 ቀን አፈፃፀም ሪፖርትን ተወያይቶ ማፅደቅ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጨማሪ የበጀት አዋጅ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ ፣ የምክር ቤቱ የተሻሻለ የአባላት ስነ -ምግባር እና ደንብ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ ፤ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ::

በጽዳት ላይ የሚታይ ህገወጥነትን መከላከል ሁላችንም ይመለከተናል! ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ይህን አዲስ ተግባር ስንጀምር ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለሁሉም ምቹ የሆኑ ከተሞችን በመፍጠር ጥረት ላይ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቀርባለሁ። #ጽዱኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ አሊ "Daandii Qulqulluu - Jireenya Fayyaa" Sochii haaraa kana wayita jalqabnu Itoophiyaanonni hundi tattaaffii magaalota hundumaaf mijaawaa ta'an uumuuf godhamu keessatti gaheesaanii akka gumaachan waamichakoon dhiyeessa. #ItoophiyaaQulqulluu “Clean Streets – Healthy Lives” As we embark on this new initiative, I call upon all Ethiopians to contribute their share in creating cities that are conducive for everyone. Prime Minister Dr.Abiy Ahmed Ali #CleanEthiopia

photo content
+1

photo content
+9

በየካ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ያለፉት 9 ወራት የስራ አፈፃፀምን አስመልክቶ የመስክ ላይ የስራ ምልከታ ተካሄደ። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በክፍለ ከተማዉ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት እየተከናወኑ ካሉ በተለይ የፅዳት እና የመብራት አገልግሎት ላይ በተግባር ያለዉ የስራ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረ የመስክ ጉብኝት አድርጓል። በምልከታዉ ወቅትም በክፍለ ከተማዉ በጽዳት ሞዴል የሆኑ ወረዳዎች፣የቅብብሎሽ ጣቢያ፣የቆሻሻ ማቆያ፣ሞዴሎች በሆኑ ብሎኮች የተሰሩ የኮምፓስት ስራዎች ፣ በኤሌክትሪክ አገልግሎት ረገድ ደግሞ የመንገድ ዳር መብራቶች በምን ያህል ደረጃ አገልግሎት እየሰጡ እንዳሉና እና አገልግሎት የማይሰጡትንም ለመለዬት የሚያግዝ የመስክ ምልከታ ለማድረግ ተችሏል። በተጨማሪም በክፍለ ከተማው ፅዱ እና ሞዴል የሆኑ ወረዳዎችን መመልከት የተቻለ ሲሆን በሌሎችም ወረዳዎች መሰል ስራዎችን ለመስራት የሚስተዋሉ አንዳንድ ክፍተቶችን በቀጣይ ለመቅረፍ ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት በመሆን በጋራ መስራት እንደሚገባ በመስክ ምልከታዉ የጋራ ተደርጓል። በምልከታዉም ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አመራሮች፣ባለሙያዎች፣የክፍለ ከተማ ባለሙያዎች፣የወረዳ የፅዳት አስተዳደር ባለሙያዎች፣ ስራ አስኪያጆች እየተሳተፉ ናቸው:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+1

photo content
+9

በኮልፌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት በተሰሩ ስራዎች ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አሰኪያጅ ጽ/ ቤት አማካኝነት የድጋፍና ክትትል ቡድን በማዋቀር በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ባለፉት 9 ወራት የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም አስመልክቶ የመስክ ምልከታ አካሄዷል። በምልከታው በክፍለ ከተማ አስተዳደር በፅዳት ሞዴል ብሎኮች፤የጽዳት ማህበራት፤በመልሶ መጠቀም፤ተቋማት ፁዱና ምቹ ከማድረግ አኳያ፤የደረቅ ቆሻሻ የቅብብሎሽ ጣቢያዎች፤የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት፤ዋና ዋና የአስባልት መንገዶች የፅዳት ስራዎችን ምልከታ ይካሄዳል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ቢሮ ፅሀፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወሰን መርጋ ድጋፉና ክትትሉ ያሉ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እንደዚሁም ድክመቶች የእቅድ አካል በማድረግ ፈጥኖ ለማረም እንደሆነ ገልፀው በክፍለ ከተማው በ9 ወራት በተሰሩ ስራዎችን በመስክ ምልከታ የማረጋገጥ ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል፡፡ ቡድኑ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ በክፍለ ከተማው አስተዳደር፤በወረዳ 06 አስተዳደር፤በክፍለ ከተማው ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ በመገኘት በተቋማትን ፅዱና ምቹ ከማድረግ ጋር ተያይዞ የተሰሩ ስራዎችን ምልከታ በማካሄድ በጥንከሬ የታዩትን እንዲቀጥሉ እንዲሁም በድክመት የታዩትን ማረም እንዲገባ በድጋፍና ክትትሉ አመላክቷል፡፡